ጤና ይስጥልን ውድ ወላጆች! በትላንትናው እለት የ በጎ አድራጎት ክበብ ተወካይ ተማሪዎች :መምህራን:የወላጅ ኮሚቴ:እንዲሁም የብሎሠም ት/ቤት አስተዳደር ሠራተኞች አንድ ላይ በመሆን መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማእከልን ጎብኝተዋል። በእለቱ ከወላጆች:ከተማሪዎች እንዲሁም ከመምህራን የተሠበሠቡ አልባሳት እንዲሁም ደረቅ ምግቦችን ለድርጅቱ ገቢ አድርገናል። በቱሉዲምቱ የሚገኙ የወላጅ ኮሚቴ አባላት በመሠባሠብ የ ንጽህና መጠበቂያ ግብአቶችን እንዲሁም የገንዘብ ልገሳ ያደረጉ ሲሆን ት/ቤታችንም በመርጃው ማእከል ለሚገኙ ወገኖቻችን የምሳ ግብዣ ኘሮግራም አድርጓል። በዚህ የማይረሳ የበረከት ስራ ለተሳተፋችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ብሎሠም ት/ቤት
ብሎሠም ት/ቤት
😁2👏1
Forwarded from Weyn Tesfaye
❤2