ብስራት ስፖርት 🇪🇹
171K subscribers
30.5K photos
1.73K videos
8 files
1.17K links
ብስራት ስፖርት በኢትዮጵያ
ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ!
══════════════
➮የሃገር ቤት ትኩስ ትኩስ መረጃዎች
➮የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ሙሉ መረጃ
➮ቁጥራዊ መረጃዎች እና ዳሰሳዎች
➮ጨዋታዎችን በቀጥታ ከየስታዲየሙ
➮የተለያዩ ስፖርታዊ ታሪኮች

Crated By @Amanuu11
Download Telegram
ብስራት ስፖርት 🇪🇹
Photo
#እግር_ኳስ_በዛሬው_ቀንና_አጫጭር_እውነታዎች
ሜሲ የመጀመሪያ የባርሴሎና ጫወታውን ያደረገበት
ኔይማር 400ጎል ለማስቆጠር 13 ጎል ብቻ ይቀረዋል
ጄራርድና የሻምፒየንስ ሊግ ጎል የተዋወቁበት ዕለት
ዴጊያ ተጎድቷል ፣ ሮሜሮ አስገራሚ ሪከርድ አለው
የግብ ዕድል በመፍጠር ኦዚል ወይስ ፖየት?
አርኖልድ ከጊነስ ወርልድ ሪከርድ ማረጋገጫ ወሰደ
ቀዮቹ ኦልትራፎርድ ላይ ባለፉት 14 ጫወታ 9 ተሸንፈዋል
አሎንሶ በሊቨርፑል የመጀመሪያ ጎሉን ያስቆጠረበት
ካናዳ ከ34 አመት በኋላ አሜሪካን ማሸነፏን ያውቃሉ?
ጋናዎች ብራዚልን አሸንፈው አፍሪካን ያኮሩበት ቀንም እንዘክራለን
LIKE እና SHARE ለማድድረግ አትሰስቱ ዳይ
───────────────────────────
🔵 አምና በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አስደናቂ ሲዝን በማሳለፍና የሲዝኑ ምርጥ 11 ውስጥ የተመረጠው የሊቨርፑሉ ተከላካይ አሌክሳንደር አርኖልድ በእንግሊዝ ምድር በአንድ ሲዝን ተከላካይ ሆኖ 11 ጎል የሆኑ ኳሶችን በማቀበል አዲስ ሪከርድ ማስመዝገቡ ይታዋቃል። ዛሬ ለዚህ ሪከርዱ ከጊነስ ወርልድ ሪከርድ የማረጋገጫ ሰርተፍኬቱን በይፋ ተቀብሏል።
───────────────────────────
🔴 በ2009 ልክ በዛሬው ቀን ጋና በአለም ዋንጫ ከ20 አመት በታች የፍፃሜ ጫወታ ላይ ብራዚልን በፍፁም ቅጣት ምት 4ለ3 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነች። በዛ ቀንም በውድድሩ ታሪክ ይህን ዋንጫ ወደ አፍሪካ ይዞ የተመለሰ ብቸኛ ቡድን በመባል ታላቅ ሙገሳን አፍሪካ ላይ ተሰማ።
───────────────────────────
🔵 በ2004 ልክ በዛሬው ቀን የ17 አመቱ ታዳጊ በባርሴሎና የመጀመሪያ የላሊጋ ጫወታውን አደረገ። ዛሬ ላይ ከ15 አመት በኋላ
✔️በ420 ጎሎች የምንግዜም የላሊጋ ጎል አስቆጣሪ
✔️በ163 assist የምንግዜም የላሊጋ ባለሪከርድ
✔️10 የላሊጋ ዋንጫወችን ያሸነፈና የምንግዜም የላሊጋ ምርጡ ተጫዋች በሚል ስሙ ከየትኛው ተጫዋች በላይ ከፍ ብሎ ተሰቅሏል።
#ሊዮኔል_ሜሲ
───────────────────────────
🔴 በሊቨርፑል ማልያ እጅግ የሚወደድ ተጫዋች ነበር ፣ ግን ሳይፈልጉት ተገደው ለሪያል ማድሪድ ሸጡት ፣ በቀዩ ማልያ 210 ጫወታዎችን አድርጎ 19 ጎሎችን በስሙ አስቆጥሯል ፣ ከመርሲሳይዱ ክለብ ጋር ሻምፒየንስ ሊግ እና ኤፍኤ ካፕ ዋንጫዎችንም አጣጥሟል። በ2004 ልክ በዛሬው ቀን ነበር ለሊቨርፑል ተቀይሮ ገብቶ የመጀመሪያ ጎሉን ያስቆጠረው
#ዣቪ_አሎንሶ
───────────────────────────
🔵 ብራዚላዊው የፒኤስጂ ኮከብ ኔይማር በተጫዋችነት ዘመኑ 400ኛ ጎሉን ለማስቆጠር 13 ጎል ብቻ ይቀረዋል። ለመሆኑ ከሜሲና ሮናልዶ ጋር ሲነፃፀር በአነስተኛ ጫወታ 400 ጎል ላይ የደረሰው ማን ይመስላችኋል?
በ525 ጫወታው 400ኛ ጎል.... ሊዮኔል ሜሲ
በ623ጫወታው 400ኛ ጎል..... ክርስቲያኖ ሮናልዶ
በ573ጫወታው 387ኛ ጎል..... ኔይማር
───────────────────────────
🔴 የሊቨርፑል የምንግዜም ምርጥ ተጫዋች በሚል ደጋፊዎች በ2017 መርጠውታል። የቡድን መሪነት ፣ ከረጅም ርቀት በሚያስቆጥራቸው ጎሎችና ታጋይነት መለያዎቹ ናቸው። በሻምፒየንስ ሊጉ ለመጀመሪያ ግዜ ጎል ያስቆጠረው በ2001 ልክ በዛሬው ቀን ነበር። ከዛ በኋላ በመድረኩ 21 ጎሎችን በማስቆጠር በሊቨርፑል ማልያ ባለሪከርድ ነው።
#ስቴቨን_ጄራርድ
───────────────────────────
🔵 በጉዳት እየታመሰ የሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድ ጭራሽ ወሳኙን ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴጊያን በትላንትናው የስፔን ጫወታ በጉዳት ከሜዳ አጥቷል። ዴጊያ በእሑዱ የላንክሻየር ደርቢ ላይደርስ ይችላል በምትኩ የሚገባው ሰርጂ ሮሜሮ ሲሆን በፕሪምየር ሊጉ ለማንችስተር ዩናይትድ ባደረገው 7 ጫወታው በ6ቱ መረቡን ከግብ በመታደግ ምርጥ ሪከርድ አለው። የተቆጠረበት ጎልም 2 ብቻ ሲሆን የተሞከሩበትን ኳሶችን የማዳን ስኬቱም 92% ነው።
───────────────────────────
🔴 ሊቨርፑሎች ወደ ኦልትራፎርድ ተጉዘው ባደረጉት ያለፉት 14 ጫወታቸው ያሸነፉት 2 ግዜ ሲሆን በሁለቱም 3+ ጎል ማስቆጠር ችለው ነበር። (በተቀረው ጫወታ ግን 9 ተሸንፈው 3 አቻ ተለያይተዋል)
2009 ላይ ማንችስተር ዩናይትድ 1-4 ሊቨርፑል
2014 ላይ ማንችስተር ዩናይትድ 0-3 ሊቨርፑል
───────────────────────────
🔵 ከኦገስት 2006 በኋላ በአውሮፓ 5ቱ ታላላቅሊጎች ውስጥ ከ1000 በላይ የግብ ዕድል በመፍጠር 2 ተጫዋቾች ብቻ ስማቸው ይጠራል (ሜሱት ኦዚል እና ዲሚትሪ ፖየት) ግን ከሁለቱ ማን የተሻለ ነው?
373 ጫወታ ፣ 130 assist ፣ 1070 የግብ ዕድል (ኦዚል)
432 ጫወታ ፣ 105 assist ፣ 1084 የግብ ዕድል (ፖየት)
───────────────────────────
🔴 በመጨረሻም በሰሜን አሜሪካ ዞን ኔሽንስ ሊግ ጫወታቸውን ትላንት ምሽት ያደረጉት ካናዳ እና አሜሪካ ያልተጠበቀ ውጤት ተመዝግቧል። ይኸውም ከ34 አመት በኋላ ካናዳ አሜሪካን ማሸነፍ ችላለች። ጫወታው በካናዳ 2ለ0 አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን አሜሪካ ለመጨረሻ ግዜ በካናዳ የተሸነፈችው በ1985 ነበር።

───────────────────────────
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ2026 የአለም ዋንጫ ላይ እንደሚሳተፍ አረጋግጧል !

የፖርቹጋላዊው ኮከብ ለአንድ የመጨረሻ ዳንስ ዝግጁ ነው 😤🇵🇹

#ክርስቲያኖ_ሮናልዶ #ሮናልዶ #Cristiano #CR7 #የአለም_ዋንጫ #ፊፋ_የአለም_ዋንጫ #ፊፋ #የአለም_ዋንጫ2026 #GOAT #ፖርቱጋል #እግር_ኳስ #Fyp

#SHARE @Bisrat_sport_offical