ብራና ሚድያ - Birana Media
618 subscribers
1.68K photos
40 videos
4 files
577 links
+ የወጣቶች መንፈሳዊ ሕይወት
+ ገዳማትና ታሪካዊ ስፍራዎች
+ የቅዱሳን አበው መንፈሳዊ ተጋድሎና ታሪክ
+ እንዲሁም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የውይይት መድረክ በማዘጋጀት ወደ እናንተ ውድ ተከታታዮች መንፈሳዊ ይዘቱን ጠብቆ በየእለቱ ይቀርባል።
ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ይቀላቀሉን።
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia
ጥያቄ ካሎት በዚህ ይጻፉልን @birana259
Download Telegram
"ለማኅበራዊ ሚዲያ ማድመቂያ በማኅሌቱ የሚታየው የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጥሰት ሊቆም ይገባል " ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ

ጥቅምት 24 ቀን 2016 ዓ.ም (ብ.ሚ./አዲስ አበባ)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምትታወቅባቸው እና ከምትገለገልባቸው የማይዳሰሱ ሀብቶቿ መካከል አንዱ እና ዋነኛው ሥርዓተ ማኅሌት ነው ሲሉ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው በገለጻቸው ቤተክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮዋን በማኅሌት ታቀርባለች ፤ ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይዘቱን በለቀቀ መልኩ አቀራረቡ ተለይቶ ማኅሌት በማይመስል መልኩ ባልተገባ ሁኔታ ሥርዓቱን ባልጠበቀ አቀራረብ ሲቀርብ እየተመለከትን ነው ብለዋል።

በዚህ ሁኔታ በአሁን ወቅት በተለያዩ የሶሻል ሚዲያዎች የቤተ ክርስቲያኗን ስልት እና ሥርዓት በትክክል በሚገልጽ መልኩ ሲገለገሉ አይታይም ይህን ነገር እግዚአብሔር አይቀበለውምና ሊቀር ይገባል ብለዋል ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ።

አሁን ያለው ሥርዓት ከእግዚአብሔር ጋር አያገናኘንም ቤተክርስቲያንንም አይገልጻትም የጥንት አባቶቻችን ሥርዓት በልክ ተሰርቶ ተቀምጦ ያለው ከሚፈልገው መንገድ ወጥቷልና የሚመለከታቸው አካላት ሊቃውንትን ጨምሮ ይህን እንቅስቃሴ በጊዜ ሊያስቆሙ ይገባል ነው ያሉት።
©eotc tv

#Ethiopia 
#Birana_Media
#BM_Addia_Ababa

ብራና ሚዲያ
የኦርቶዶክሳዊያን ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/birana3

በፌስቡክ ገጻችን ትምህርቶች እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
https://www.facebook.com/birana22

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@birana16

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/birana96
ከስልጤ ዞን ቅበት ከተማ ተሰደው በቡታጅራ የነበሩት ኦርቶዶክሳውያን እና አብሮ የተሰደደው የቅድስት ድንግል ማርያም ጽላት ወደ አካባቢያቸው ተመለሱ።

ጥቅምት 26 ቀን 2016 ዓ.ም (ብ.ሚ./ አዲስ አበባ)

ከስልጤ ዞን ቅበት ወረዳ በደረሰባቸው ጥቃት ምክንያት የተሰደዱት ኦርቶዶክሳውያን እና አብሮ የተሰደደው የቅድስት ድንግል ማርያም ጽላት ወደ አካባቢያቸው መመለሳቸውን የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት መልአከ ሕይወት ቀሲስ ንጉሤ ባወቀ ለተሚማ ገልጸዋል።

መልአከ ሕይወት ቀሲስ ንጉሤ ባወቀ የሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ከተ.ሚ.ማ ጋር ባደረጉት የስልክ ቆይታ እንደገለጹት  ከአዲስ አበባ 130 ኪ.ሜ ከስልጤ ዞን 12 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ቡታጅራ ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው ለ2 ወራት የቆዩት ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ወደ አካባቢያቸው ገብተዋል ብለዋል።

ከስልጤ ዞን ቅበት ወረዳ በደረሰባቸው ጥቃት ምክንያት የተሰደዱት ከ1500 በላይ ኦርቶዶክሳውያን መካከል አብዛኞቹ ህጻናት ፣ ሲሆኑ አዛውንት ፣ ወጣቶች ፣ ጎልማሶች እና አራስ እናቶች እንደሚገኙበት ተ.ሚ.
ማ በቦታው ተገኝቶ መዘገቡ አይዘነጋም።

ሥራ አስኪያጁ በገለጻቸው ወደ ቀያቸው የተመለሱት ኦርቶዶክሳውያን በዞኑ የሚገኙ ጽንፈኞች መኖርያ ቤቶቻቸውን አቃጥለውባቸው እና ዘርፈውባቸው ስለነበር መታደስ እና መስተካከል የሚችሉ ቤቶችን ዞኑ እንደሚያስተካክል እና ካሳ እንደሚሰጣቸው ፤ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን ቤቶች በድጋሚ እስኪሰሩ ድረስ ዞኑ ቤት ተከራይቶላቸው እንደሚቆይ አክለዋል።

በስልጤ ዞን ቅበት ወረዳ በሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ያለው ስጋት አሁንም እንደሚኖር ገልጸው ከዚህ በኋላ ከፌደራል ጀምሮ ጥብቅ ክትትል እንደሚደረግ እና ምንም አይነት ጥቃት እንደማይደርስባቸው የዞኑ የመንግሥት አካላት ፣ የከተማው አስተዳደር እና የሀገር ሽማግሌዎቹ ዋስትና እንደሚወስዱ ቃል ገብተዋል ነው ያሉት ሥራ አስኪያጁ።

በመጨረሻም መልአከ ሕይወት ቀሲስ ንጉሤ ባወቀ የሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የተፈናቀሉት ኦርቶዶክሳውያንን ለመርዳት ለተደረገው ርብርብ በመላው ዓለም የሚገኙ ምዕመናንን ፣ የመንግስት አካላትን ፣ በቦታው ድረስ በመገኘት እርዳታ ላደረጉ ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ለሚዲያ አካላት ፣ ቡታጅራ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያንን እና የቡታጅራ ነዋሪዎችን አመስግነዋል።

©️ተ.ሚ.ማ.

#Ethiopia 
#Birana_Media
#BM_Addia_Ababa

ብራና ሚዲያ
የኦርቶዶክሳዊያን ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/birana3

በፌስቡክ ገጻችን ትምህርቶች እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
https://www.facebook.com/birana22

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@birana16

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/birana96
በብዙ ልፋት የተሰሩ ብዙ ታሪክን ሰንደው የያዙ ገዳማት በጦርነቱ ምክንያት እየወደሙ እንደሚገኙ ተገለጸ።

ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም (ብ.ሚ/አዲስ አበባ)

በብዙ ልፋት የተሰሩ ብዙ ታሪክን ሰንደው የያዙ ገዳማት በጦርነቱ ምክንያት እየወደሙ እንደሚገኙ መጋቤ ካህናት አባ ሀብተጊዮርጊስ አስራት ለተ.ሚ.ማ ገለጹ።

ገዳማት እና ገዳማውያን  በሀገሪቱ አሁናዊ የሰላም ሁኔታ ምክንያት አገልግሎት መስጠት እንዳልቻሉ መጋቤ ካህናት አባ ሀብተጊዮርጊስ አስራት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ዋና ኃላፊ ከተ.ሚ.ማ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ያለው ተዋረድ የተገኙት እና መፍለቂያቸው ገዳም ነው ያሉት ኃላፊው የገዳማት አገልግሎት የሚቋረጥ እና የሚዘጉ ከሆነ የቤተ ክርስቲያን ህልውና አደጋ ውስጥ የሚገባ ነውም ብለዋል።

መጋቤ ካህናት አባ ሀብተጊዮርጊስ አስራት አክለውም በትግራይ አካባቢ ያሉ ገዳማት ከዚህ ቀደም በነበረው ጦርነት ጉዳት ደርሶባቸው እና "መንበረ ሰላማ" በማለት ራሳቸውን በነጠሉ አካላት ምክንያት አገልግሎት እየሰጡ አይደለም ነው ያሉት።

በጦርነቱ ምክንያት በገዳም ውስጥ ያሉ ገዳማውያን የልማት ሥራን ሠርተው ራሳቸውን ማስተዳደር ፣ መብል ማግኘት አለመቻላቸውን እንዲሁም በሸዋ ፣ በወሎ ፣ በጎጃም እና በጎንደር ብዙ ደቀመዛሙርት እና ጸበልተኞች በገዳም ውስጥ ሆነው መሞታቸውን ፤ ገዳማት እንዳልነበሩ ሆነው እየወደሙም መሆኑን ገልጸዋል ኃላፊው።

በመጨረሻም የተቸገሩ ገዳማትን ለመርዳት እና ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ለመመለስ ሰላም በእጅጉ ያስፈልገናል ያሉት ኃላፊው በችግር ላይ የሚገኙ ገዳማትን እና ገዳማውያንን መርዳት የሁላችንም ኃላፊነት ነውና ገዳማት ራሳቸውን እንዲችሉ ሁሉም የበኩሉን ለመወጣት እና ለማገዝ መረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል።


#Ethiopia 
#Birana_Media
#BM_Addia_Ababa

ብራና ሚዲያ
የኦርቶዶክሳዊያን ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/birana3

በፌስቡክ ገጻችን ትምህርቶች እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
https://www.facebook.com/birana22

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@birana16

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/birana96
በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ደኅንነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ።

ጥቅምት 29 ቀን 2016 ዓ.ም (ብ.ሚ/አዲስ አበባ)

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በአማራ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው ጦርነት ምክንያት የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ደኅንነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን  የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የላሊበላ አካባቢ ነዋሪዎች እንደገለጹት በአብያተ ክርስቲያናቱ ዙሪያ ያለው ተኩስ የጥንታውያኑን አብያተ ክርስቲያናት ደኅንነት አደጋ ላይ እንደሆነ ነው የተናገሩት።

ለደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት መጠለያነት የተሠሩ የብረት ሽፋኖች በተባራሪ ጥይቶች መመታታቸውን ፤ ሁሉንም ዓይነት የጦር መሳሪያዎች እየተጠቀሙ መሆኑን እና "የተኩሱ ንዝረት ይሰማኛል” በማለት ውጊያው በከተማዋ ውስጥ የፈጠረውን ስጋት እና የደቀነውን አደጋ የሮይተርስ የዜና ወኪል ያናገረው አገልጋይ ገልጸዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነትን ብንጠይቅም ከሀገረ ስብከቱ መረጃው እንዳልደረሰው የተገለጸልን ሲሆን ወደ ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ያደረግነው የስልክ ሙከራም አልተሳካም።

#Ethiopia 
#Birana_Media
#BM_Addia_Ababa

ብራና ሚዲያ
የኦርቶዶክሳዊያን ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/birana3

በፌስቡክ ገጻችን ትምህርቶች እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
https://www.facebook.com/birana22

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@birana16

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/birana96
የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያንን እድሳት ለማስጀመር ታቦተ ሕጉ ወደ ተዘጋጀለት ማረፊያ መቃኞ ቤተ ክርስቲያን በክብር ገባ !

ኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም (ብ.ሚ /አዲስ አበባ)

የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያንን እድሳት ለማስጀመር ታቦተ ሕጉ  ወደ ተዘጋጀለት ማረፊያ መቃኞ ቤተ ክርስቲያን በዛሬው ዕለት ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በደማቅ ስነ ሥርዓት በክብር ገብቷል ።

ታሪካዊው የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን በጊዜ ብዛት ከመሠረቱ ጀምሮ እስከ ጣሪያው ድረስ ከፍተኛ ጉዳት የደረስበት ሲሆን ፤ አስቸኳይ እድሳት እንደሚያስፈልግ በመወሰኑ እድሳቱን የማስጀመር ሥራ የተከናወነ ሲሆን ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ምእመናን ሁሉም በጸሎት እና በሀሳብ እንዲተባበሩ፣ በእድሳት ሂደት ሁሉ መለኮታዊ መመሪያን እና ጥንካሬን እንዲፈልጉ ጥሪ በማቅረብ የተከበረውን የእግዚአብሔር መልአክ የቅዱስ ዑራኤልን ቤት ለመመለስ የጋራ ርብርብ አስፈላጊ መሆኑን በማሳየት ማህበረሰቡ በሚያደርገው የማይናወጥ ድጋፍ ላይ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ሕንፃ ቤተክርስቲያኑ ለዚህን ያህል ዓመታት አገልግሎት መስጠቱ የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያንን የሰሩት አባቶቻችን እና ምእመናን  የነበራቸውን ጽናት ፣ እምነት የሚያሳይ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው እድሳቱ ተጠናቅቆ ወደ ቀደመው የአምልኮ ሥርዓት በቅርብ እንደሚመለስ እምነታቸው ገልጸዋል።


#Ethiopia 
#Birana_Media
#BM_Addia_Ababa

ብራና ሚዲያ
የኦርቶዶክሳዊያን ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/birana3

በፌስቡክ ገጻችን ትምህርቶች እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
https://www.facebook.com/birana22

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@birana16

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/birana96
ቀደም ሲል ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በመላው ዓለም ለሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን የታወጀውን አዋጅ አስተላልፈዋል፡፡ በዚሁ መሠረት ያለፈውን በይቅርታና በምህረት ዘግተን በእውነተኛ ንሥሓ ልቅሶና በምህላ፣ በጾምና በጸሎት ወደ ፈጣሪ እንድንቀርብ፣ በመካከላችንም ፍቅርና አንድነት እንዲመጣ ይኽንን ጾመ ነቢያት ወይም የገና ጾም በልዩ ሁኔታ እንድንጾም መንፈሳዊ አዋጅ ተላልፏል፡፡ 

ይኽ ጥንታዊ የአዋጅ ጾም ሁለት አበይት ታሪኮችን የያዘ ነው፡፡ የመጀመሪያው ክፍል ቅዱስ አብርሃም ሶርያዊ የተባለ ጻድቅ አባት በጸሎት፣ በጾምና በምኅላ ተራራን ከመሬት ከፍ በማድረጉ ኃይለ ጸሎቱና ክብረ አምለኩ የሚዘከርበት ነው፡፡ በሁለተኛው ክፍል ነቢያት የጌታችንን ሰው መሆን እያፈለጉ፣ ድህነትንና ሰላምን በመሻት መጾማቸው ይዘከራል፡፡ (፩ኛ ጴጥ ፩፡፲) እኛም ይኽንን አብነት አድርገን ታላቋ ቤተ ክርስቲያን፣ ኃላፊነቷን እንድትወጣ ስለችግራችን፣ ስለሀገር ሰላምና ስለ ሕዝቡ ደኅንነት በአንድነት ሆነን ወደፈጣሪያች እንድንጮኽ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጥቅምት ወር ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም ወስኖ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ሀገራችን እንድትፈወስ፣ የወገን በወገን ደም መፋሰስ እንዲቀር፣ ያለፈውን በይቅርታና በንሥሓ ዘግቶ ለወደፊቱ ብሩህ ዘመንን እንዲመጣ በንሥሓና በፍጹም ለቅሶ፣ በቁመትና በሰጊድ፣ በሰፊሕና በአንቅአድዎ፣ ወደፈጣሪ እንድንቀርብ የምልኣተ ጉባኤውን ውሳኔ መሠረት በማድረግ ቋሚ ሲኖዶስ በኅዳር ወር ፳፻፲ወ፮ዓ/ም የሚከተለውን ዝርዝር አፈጻጸም አውጥቷል፡፡

፩ኛ. የጾሙ የመጀመሪያ ሳምንት ከቅዳሜ ኅዳር ፲፭ እስከ ኅዳር ፳፩ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም በሁሉም የሀገራችን ክፍልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ባለችበት በመላው ዓለም የንሥሓ፣ የጾም፣ የጸሎትና የምኅላ ሳምንት እንዲሆን፤
 
፪ኛ. በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ በአጥቢያ አለቆችና በገዳም አበምኔቶች መሪነት ሁሉም ዲያቆናት፣ ቀሳውስት፣ መነኰሳት፣ ሰባክያንና ሊቃውንት በሙሉ በየመዐርጋቸው ልብሰ ተክህኖና ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ዩኒፎርማቸው ለብሰው፣ ሁሉም ምእመናን ጋር በአንድነት በዐውደ ምህረት ጸሎተ ምኅላውን እንዲያደርሱ፤ 

፫ኛ. በላው ሕዝበ ክርስቲያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ሕፃናት፣ ወጣቶች፣ እናቶች አባቶች አረጋውያን ሁሉ የቻለ በቤተ ክርስቲያን፣ ያልቻለ በያለበት ሆኖ የተጣላ ታርቆ፣ በፍቅርና በአንድነት፣ በእውነተኛ ንሥሓና ጸጸት በምኅላው እንዲሳተፍ፤ በማእከል የሚደረገው ጸሎተ ምኅላ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ገዳም ሆኖ በመገናኛ ብዙኀን የቀጥታ ሥርጭት ለመላው ዓለም እንዲተላለፍ፤

፬ኛ. በመጀመሪያው የሱባኤ ቀን ኅዳር ፲፭ ቀንና፣ በሰባተኛው ቀን ኅዳር ፳፩ ቀን በጸሎተ ምኅላው በሚደረግበት ጊዜ ታቦቱ ከመንበሩ ተነሥቶ በዐውደ ምኅረት በቀሳውስት እንዲከብር ሆኖ፤ በሁሉም የምኅላው ቀናት ሥዕለ ማርያም፣ ወንጌልና መስቀል ወጥቶ በአራቱ መዐዝን ሥርዓተ ጸሎተ ምኅላው ከጸሎተ ወንጌል ጋር በየቀኑ በነግህና በሠርክ የሥራ ሰዓትን በማይነካ ሁኔታ እንዲፈጸም፤

፭ኛ. በየዕለቱ የሚነበቡት የወንጌል ክፍሎችን ስለ ሰላም፣ ስለንሥሓና ጸጸት፣ ስለ ፍቅርና አንድነት፣ ስለ በጎነትና መደማመጥ፣ ስለመሰማማትና ጥላቻን ስለማራቅ እንዲሆን፤

፮ኛ. በሰፊህና በአንቀዓድዎ፣ በሰጊድና በአስተብርኮ፣ ምኅላው ከደረሰና፣ ጸሎተ ወንጌል ደርሶ ዕለቱ ወንጌል ከተነበበ በኋላ በአንድነት የንሥሓ መዝሙር በመዘመር፣ ሕዝበ ክርስቲያን ስለሀገራቸውና ስለሰው ልጆ ደኅንነት እያሰቡ ወደቤታቸው እንዲሄዱ፤

፯ኛ. ከመጀመሪው ሳምንት በኋላ እስከ በዓለ ልደት ድረስ የሰርክ ምህላ ሳይቋረጥ መደበኛው ሥርዓተ ጾምና ጸሎት እንዲቀጥል፣ የቤተ ክርስቲያንን ታላቅነት፣ የአበውን ተቀባይነት በሚገለጽ፣ በቀጣይም ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን በመንፈሳዊ ጽናት የሰላም ልዑካን ሆነው እንዲቀጥሉ በሚያደርግ ሁኔታ እንዲፈጸም፤ 
 
፰ኛ. አስቀድሞ የደረሰውንና፣ እየደረሰብን ያለው ችግር የጦርነትና የግጭት ብቻ ሳይሆን የረሀብ፣ የድርቅ፣ የኑሮ ውድነት፣ የመፈናቀልና የስደት ጭምር ስለሆነ ከጸሎትና ምኅላችን ጎን ለጎን መረዳዳትና መተዛዘን፣ ርኅራሄና መደጋገፍ አብሮ እንዲፈጸም፤   

፱ኛ. ይኽንኑ መልእክት መላው ዓለም እንዲውቀው፣ በተለይም የኦሬንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በጸሎት እንዲያስቡን፣ የጸሎታችንና የምኅላችን መነሻ ምክንያቱ የሀገራችን ወቅታዊ ችግር ቢሆንም የምንጸልየው ለመላው ዓለም መሆኑ ተገልጾ በደብዳቤ እንዲላክ እንዲደረግ፣ በማለት ቅዱስ ሲኖዶስ ጥብቅ መመሪያ አስተላልፏል፡፡ 

እግዚአብሔር አምላካችን በእንባና በንሥሓ የምናቀርበውን ጸሎተ ምኅላችንን በምህረቱ ተቀብሎ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን፣ ሕዝባችንን ይጠብቅልን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 
ቅዱስ ሲኖዶስ

#Ethiopia 
#Birana_Media
#BM_Addia_Ababa

ብራና ሚዲያ
የኦርቶዶክሳዊያን ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/birana3

በፌስቡክ ገጻችን ትምህርቶች እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
https://www.facebook.com/birana22

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@birana16

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/birana96
የማኀበረ ቅዱሳን ዋና ማእከል ምዕራፍ ሁለት የሕንጻ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተከናወነ

ኅዳር 16 ቀን 2016 ዓ.ም (ብ.ሚ/አዲስ አበባ)

ማኅበረ ቅዱሳን ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን በኹለንተናዊ አቅሟ እንድትጠናከር ለማድረግ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። አገልግሎቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ የመጣው ማኅበሩ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ ማስፈጸም የሚችሉ ማእከላት በማቋቋም ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ላይ ይገኛል።

ማኅበሩ ዘመኑ የሚጠይቀውን የአገልግሎት መንገድ በመከተል በዘመናዊ አሠራር ቤተ ክርስቲያንን ማገዝ የሚችሉ በርካታ አሠራሮችን ወደ ተግባር እያስገባ ሲሆን ለዚህ ተግባር የሚያግዙ የሰው ኃይል እና የግብዓት ማሟላት ላይ በትኩረት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።ለዚህ ማሳያ የሚሆነው ደግሞ አሁን ግባታውን ለመጀመር በዝግጅት ላይ የሚገኘው የምዕራፍ ሁለት የማኅበሩ ሕንጻ ማስፋፊያ ነው።

ማኅበሩ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ የተነገረለት አዲሱ የማኅበሩ ሕንጻ የመሬት ወለልን ጨምሮ 14 ወለሎች እንደሚኖረው የተነገረለት ሲሆን ኅዳር 15 ቀን 2016 ዓ.ም ግንባታውን ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተከናውኗል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ጸሎተ ወንጌልን ጨምሮ ሌሎች ዝግጅቶችም የቀረቡ ሲሆን በቦታው ለተገኙ ታዳሚዎች የሕንጻውን ግንባታ እና ያካተታቸውን አገልግሎቶች በተመለከተ ማብራሪያ ተሰጥቷል።በተጨማሪም የማኅበሩ ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እንደተናገሩት ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያን የጣለችበትን ኃላፊነት ለመወጣት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው ያሉ ሲሆን ይህንን ሕንጻም አባላቱ እና በጎ አድራጊ አጋር አካላት በመተባበር ወደ ፍጻሜ እንዲያደርሱት የአደራ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በቀጣይ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ  ግንባታው እንደሚጀመር የተነገረለት አዲሱ የማኅበሩ ሕንጻ የአርክቴክቸራል እና ስትራክቸራል ዲዛይን ሥራዎቹ እና ወደ ግንባታ ለመግባት የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶች በሙሉ መጠናቀቃቸው ተገልጿል።


#Ethiopia 
#Birana_Media
#BM_Addia_Ababa

ብራና ሚዲያ
የኦርቶዶክሳዊያን ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/birana3

በፌስቡክ ገጻችን ትምህርቶች እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
https://www.facebook.com/birana22

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@birana16

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/birana96
በደብረ ታቦር ከተማ የደብረ በረከት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን በከባድ መሳሪያ መመታቱ ተገለጸ!

ኅዳር 17 ቀን 2016 ዓ.ም (ብ.ሚ/አዲስ አበባ)

በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ጦርነት በደብረ ታቦር ከተማ በሚገኘው ደብረ በረከት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን በከባድ መሳሪያ መመታቱ ተገልጿል።

ጥቃቱ የደረሰው  ኅዳር 15 ቀን 2016 ዓ.ም  ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ገደማ  የሥርዓት ቅዳሴ አገልግሎት በመጠናቀቅ  ላይ ሳለ ሲሆን በጥቃቱ አንድ ዲያቆንና አንድ ምእመን  መሞታቸው ፣ ስምንት አገልጋዮችና ምእመናን ተጎድተው በሕክምና ላይ እንደሚገኙ ፣ ቤተክርስቲያኑም  ከባድ  ጉዳት  እንደደረሰበት ተጠቁሟል።

© ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት

#Ethiopia 
#Birana_Media
#BM_Addia_Ababa

ብራና ሚዲያ
የኦርቶዶክሳዊያን ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/birana3

በፌስቡክ ገጻችን ትምህርቶች እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
https://www.facebook.com/birana22

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@birana16

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/birana96