Forwarded from የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ /Addis Ababa Diocese Media
#ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለምትገኙ ለሁሉም ገዳማትና አድባራት የተላለፈ መልእክት!!
+++++++++++++++++++++++++++++++++++
(ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ)
በሕገወጥ መንገድ 26 ኤጲስ ቆጶሳነትን በመሾሙ እና መፈንቅለ ሲኖዶስ በማድረጉ የተነሣ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ቃለ ውግዘት የተላለፈበት ሕገወጥ ቡድን መንበረ ጵጵስናዎችንና ቢሮዎችን በኃይል በመውረር እና በመስበር ከፍተኛ ጥፋት እያደረገ መሆኑ ሰሞነኛው የአደባባይ ሐቅ ነው።
ይህንን ሕገወጥ ቡድን እንዲያስቆም ለመንግሥት ተደጋጋሚ ጥሪ ቤተክርስቲያናችን ብታደርግም ሕግ ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጥ ቡድኖች መዋቅራዊ ድጋፍ በመስጠት የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችንና ሠራተኞችን እንዲሁም ካህናትና ምእመናንን ከማሰርና ከማንገላታት አልፎ ንጹሐንን በመግደል ላይ ይገኛል፡፡
ቋሚ ሲኖዶስ ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾም እና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተክርስቲያን እንዲሁም ዓውደ ምሕረት በመገኘት ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው አምላካችን እንጩህ ሲል ጥሪውን አቅርቧል።
በዚሁ መሠረት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ሥር በሚገኙ የሁሉም ገዳማት እና አድባራት የሥራ ኃላፊዎች ለውሳኔው ተግባራዊነት በመትጋት በየትኛውም አጋጣሚ በዕለተ ሰንበት ለሚሰበሰቡ ምዕመናን የሲኖዶሱን ውሳኔ ከማስተጋባትና ከማስተላለፍ ጀምሮ ጸሎትና ምሕላ፣ እንዲሁም የማጽናኛ ትምህርተ ወንጌል በሰፊው እንዲከናወን የታዘዘ መሆኑን እናስታውቃለን።
#የአዲስ_አበባ_ሀገረ_ስብከት_ጽ/ቤት
ለተጨማሪ መረጃ የሀገረ ስብከቱ ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ:-
1. ድረ-ገጽ:- www.addisababa.eotc.org.et
2. ፌስ ቡክ ገጽ:- አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት/Addis Ababa Diocese
3. ቴሌግራም ቻናል: t.me/AddisAbabaDiocese
4.ትዊተር :-www.Twitter.com/AddisDiocese
5.መረጃዎችን በክፍሉ መረጃ መቀበያ ሞባይል ቁጥር #09 -09 -84-94-80 በቴሌግራም ይላኩልን፣

Telegram
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ /Addis Ababa Diocese Media
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
Forwarded from የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ከአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተላለፈ መልዕክት !!!
ከወቅታዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በአንዳንድ አጥቢያዎች ችግሮች እየታዩ ያለ ቢሆንም ችግር በሌለባቸው እና ምንም መረጃ በሌለበት ሁኔታ የቤተክርስቲያን ደወል እየተደወለ እንደሆነ ለመረዳት ችለናል። በመሆኑም ትክክለኛ መረጃ በሌለበት ሁኔታ እና ከደብሩ አስተዳደር እንዲሁም ከሰንበት ት/ቤት እውቅና ውጪ ደወሎችን በመደወል ግርታ እንዳይፈጠር ጥንቃቄ እንዲደረግ ለማሳሰብ እንወዳለን።
ማሳሰቢያ ፦ ችግር በተፈጠረባቸው አጥቢያዎች ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት እየተከታተልን የምንገኝ መሆናችንን ለማሳወቅ እንወዳለን።
#የአዲስ_አበባ_ሰንበት_ትምህርት_ቤቶች_አንድነት
ከወቅታዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በአንዳንድ አጥቢያዎች ችግሮች እየታዩ ያለ ቢሆንም ችግር በሌለባቸው እና ምንም መረጃ በሌለበት ሁኔታ የቤተክርስቲያን ደወል እየተደወለ እንደሆነ ለመረዳት ችለናል። በመሆኑም ትክክለኛ መረጃ በሌለበት ሁኔታ እና ከደብሩ አስተዳደር እንዲሁም ከሰንበት ት/ቤት እውቅና ውጪ ደወሎችን በመደወል ግርታ እንዳይፈጠር ጥንቃቄ እንዲደረግ ለማሳሰብ እንወዳለን።
ማሳሰቢያ ፦ ችግር በተፈጠረባቸው አጥቢያዎች ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት እየተከታተልን የምንገኝ መሆናችንን ለማሳወቅ እንወዳለን።
#የአዲስ_አበባ_ሰንበት_ትምህርት_ቤቶች_አንድነት
Forwarded from የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ /Addis Ababa Diocese Media
የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የብፁዓን አባቶች የሀገረ ስብከት ዝውውር መደባ ላይ ውሳኔ አሳለፈ።
ግንቦት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
ርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የብፁዓን አባቶች የሀገረ ስብከት ዝውውር መደባ ላይ ውሳኔ አሳለፈ።
የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ለኢኦተቤ ቴቪ (#EOTCTV) በላከው መረጃ ጉባኤው ከግቦት 21 ቀን 2016 ዓም ጀምሮ ባካሄደው ስብሰባ በበርካታ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን፡- በ4ኛ ቀን ውሎው የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትንና የጳጳሳትን ዝውውር ላይ ውሣኔ ማሳለፉን ገልጽዋል፡፡
በዚህም መሠረት፡-
1. ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ከምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ወደ ኤድመንተንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
2. ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ ከኢትዮ ሶማሌ ሀገረ ስብከት ወደ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
3. ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ ዳውሮ ኮንታ ሀገረ ስብከትን እንደያዙ የከንባታ አላባ ጠምባሮ ሀገረ ስብከትን ፣
4. ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ ከምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ወደ የኢትዮ ሶማሌ ጅግጅጋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ፣
5. ብፁዕ አቡነ ዳንኤል፣ ከምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ወደ የአፋር ሀገረ ስብከት ጳጳስ፣
6. ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ፣ ከሆሮ ጉድሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ወደ የምሥራቅ ጉራጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ፣
7. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል፣ ሌሎች አህጉረ ስብከታቸውን እንደያዙ የምሥራቅ ወለጋ ፣ የምዕራብ ወለጋ እና የሆሮ ጉድሩ ወለጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ሆነው እንዲያገለግሉ መመደባቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ለኢኦተቤ ቴቪ በላከው መረጃ ገልጽዋል።
©EOTC TV
#ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በአማን ተንሥአ እሙታን
#የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ