ብራና ሚድያ - Birana Media
618 subscribers
1.68K photos
40 videos
4 files
577 links
+ የወጣቶች መንፈሳዊ ሕይወት
+ ገዳማትና ታሪካዊ ስፍራዎች
+ የቅዱሳን አበው መንፈሳዊ ተጋድሎና ታሪክ
+ እንዲሁም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የውይይት መድረክ በማዘጋጀት ወደ እናንተ ውድ ተከታታዮች መንፈሳዊ ይዘቱን ጠብቆ በየእለቱ ይቀርባል።
ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ይቀላቀሉን።
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia
ጥያቄ ካሎት በዚህ ይጻፉልን @birana259
Download Telegram
ባለፈው ዓመት በሕገወጥ መንገድ "ጵጵስና  ተሹመናል በማለት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላት በዛሬው ዕለት በዚሁ ሕገወጥ መንገድ በመቀጠል "መንበረ ጴጥሮስ" የተባለ ሕገወጥ ቤተ ክህነት መሥርተናል አሉ !

ጥር 14 ቀን 2016 ዓ.ም (ብ.ሚ./አዲስ አበባ)


በኦሮሚያ ክልል ፖለቲካዊ ካባ የደረበ አጀንዳ ይዘው የኢትዮጵቻ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል እየተንበሳበሱ የሚገኙት በቀድሞ ስማቸው "አባ" ገ/ማርያም ነጋሳ እና ግብረ አበሮቻቸው ሕገወጥ ተግባራቸውን በመቀጠል "መንበረ ጴጥሮስ" የተባለ ቀኖናዊ መሠረት የሌለው እና ሕገወጥ የሆነ ቤተ ክህነት መሥርተናል ሲሉ ስትራቴጂክ አጋሮቻቸው በሆኑ የሚዲያ ተቋማት አማካይነት በሰጧቸው መግለጫዎች አስታውቀዋል።

 
በቋንቋችን ለመማር እና በነጻነት ለማምለክ ለዘመናት ተከልክለናል በሚል ሀሰተኛ ሽፋን ይህን እንቅስቃሴ እያደረጉ የሚገኙት ነውጠኛ መነኮሳት በመንግስት አደራዳሪነት ችግሩ ተፈትቷል ከተባለ በኋላ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ስምምነቱን የጣሰ እና በሚዲያዎች እና ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት በሚጥሩ ኃይሎች ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ማሳያ ነው።

ልክ የዛሬ ዓመት ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም ሕገኸጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት በመፈፀም የኦሮሚያና የብሔር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ በሚል "አብዮታዊ ዴሞክራሲን" እናት ፍልስፍና አድርጎ ተመሠረተ የተባለው የመነኮሳት ስብስብ በአሁኑ ወቅትም ከ5 በማይበልጡ የቀድሞ መነኮሳት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማፍረስ የውክልና እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።

"ለትግራይና ለአማራ ሲኖዶስ እንዲቋቋም ተፈቅዷል" በማለት ሀሰተኛ እና በቤተ ክርስቲያኒቱ ያልተደረገን ነገር ማስተላለፋቸው ሳያንስ "ለ5 ኪሎ ሲኖዶስ" እንዳትገዙ በማለት ጭምር ሕዝብን በሕዝብ ለማነሳሳት ከፍተኛ ቅስቀሳ እና የጦርነት አዋጅ እያወጁ ይገኛሉ።

#Ethiopia 
#Birana_Media
#BM_Addia_Ababa

ብራና ሚዲያ
የኦርቶዶክሳዊያን ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/birana3

በፌስቡክ ገጻችን ትምህርቶች እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
https://www.facebook.com/birana22

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@birana16

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/birana96
የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን የሕንጻ እድሳት ሥራ ተጠናቆ በብፁዕ ወቅዱስ  ፓትርያርኩ ቡራኬ ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ።

(አዲስ አበባ / ብ.ሚ. / የካቲት ፱ /፳፻፲፮ ዓ/ም)

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጥንታዊው የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን የሕንጻ ዕድሳት ሥራ ተጠናቆ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ተባርኮ ታቦተ ሕጉ ከመቃኞ ቤተመቅደስ ወደ ጥንታዊ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በዛሬ ዕለት  ገብቷል።

በክብረ በዓሉ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የባሕርዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት  ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣  እንዲሁም በርካታ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ሐላፊዎች ፣ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣  የሀገረ ስብከቱ እና የክፍላተ ከተማው የክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ምእመናንና እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ለረጅም ዓመታት ዕድሳት ሳይደረግለት በመቆየቱ ለጉዳት የተዳረገው ጥንታዊውና ታሪካዊው የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም ታቦታቱ ወደ አዲሱ መቃኞ ቤተክርስቲያን ገብቶ ጥንታዊ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን እድሳት ሲደረግለት መቆየቱ ይታወቃል።

የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ፲፰፻፸፭(1875) ዓ/ም በወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት በነበሩት  በአፄ ምኒልክ ዳግማዊ  አማካኝነት እንደተሠራ ታሪክ ያስረዳል።


#Ethiopia 
#Birana_Media
#BM_Addia_Ababa

ብራና ሚዲያ
የኦርቶዶክሳዊያን ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/birana3

በፌስቡክ ገጻችን ትምህርቶች እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
https://www.facebook.com/birana22

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@birana16

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/birana96
ሰበር መረጃ

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም እራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ አራት አባቶችን መግደሉን ገዳሙ አስታውቋል፡፡
ሰኞ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ታጣቂዎቹ ሦስት አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ከወሰዱ በኋላ የታገቱትን ለማስለቀቅ ገዳሙ ጥረት በሚያርግበት ወቅት የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተጨማሪ አባቶችን በመያዝ
1.  የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2.  የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3.  የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4.  በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም ወልደሰንበት
የተባሉት የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች እንደተገደሉና አብረው ከነበሩት አንድ አባት ብቻ ማምለጥ መቻላቸውን እንደተረዱ የገዳሙ ኃላፊዎች ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) ገልጸዋል፡፡
የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች ቡድኑ ከዚህ ቀደም ገዳሙን በመዝረፍ ለከፋ ችግር አጋልጦት መቆየቱን አስታውሰው ገዳሜ ጸጥታውን የሚያስከብረበት  መሣሪያች በቡድኑ በመወረሳቸው ለከፋ የጸጥታ ችግር መጋለጡን ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ገዳማውያ በስጋት ላይ መሆናቸውንና የመንግሥት የጸጥታ አካላትን እገዛ እንደሚሹ አስታውቀው መረጃውንም በየደረጃው ለሚገኙ የሀገረ ስብከቱና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ማሳወቃቸውን ገልጸዋል፡፡
©️EOTC TV

#Ethiopia 
#Birana_Media
#BM_Addia_Ababa

ብራና ሚዲያ
የኦርቶዶክሳዊያን ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/birana3

በፌስቡክ ገጻችን ትምህርቶች እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
https://www.facebook.com/birana22

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@birana16

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/birana96
በታላቁ ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የተፈፀመውን ጥቃት አስመልክቶ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በተገኙበት ከመንግሥት አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

 የካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ( ብ.ሚ./ አዲስ አበባ )       

በጥንታዊውና ታሪካዊ ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የተፈፀመውን የመነኮሳት ግድያ   አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በምሥራቅ ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባቡ ዋቆ መሪነት ተካሂዷል።

በውይይቱ  የምሥራቅ ሸዋ ዞን የጸጥታ ክፍል ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ በሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮነን የተመራ ልዑክ፣የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አበምኔትና የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የሀገረ ስብከቱ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በግፍ የሰማዕትነትን ጽዋ የተቀበሉ አባቶች መርዶ በትናንትናው ዕለት የተሰማ ሲሆን በመላው ዓለም የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ሀዘናቸውን በመሪር እንባ እየገለጹ ይገኛሉ።

የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከትም ከገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በትኩረት ጉዳዩን ሲከታተል የቆየ ሲሆን በዛሬ ዕለትም በቢሾፍቱ ከተማ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል ግቢ ዐራት ሰዓታትን የፈጀ ሰፊ ውይይት ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በውይይቱ የተቀመጡ የመፍትሔ ሃሳቦች፡-

1ኛ፡- በመንግሥት የፀጥታ አካላት አማካኝነት  የሰማዕታቱን አስክሬን ከወደቁበት አንስቶ በክብር ወደ ገዳሙ በማምጣት ሥርዓተ ቀብር እንዲፈፀምላቸው

2ኛ-  በቋሚነት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊትና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ጸጥታ መዋቅር ገዳሙንና ገዳማውያንን በዘላቂነት መጠበቅ እንዲቻል

3ኛ፡- በመንግሥትና በሀገረ ስብከቱ እንዲሁም በቤተክርስቲያን አባቶች ልባቸው የተሠበረና የተጎዱ የገዳሙ አባቶችና እናቶችን በጋራ ማጽናናት እንዲችል፡፡

የውይይቱ  የውሳኔ ሃሳቦች ሲሆኑ ይኼው ግብረ ኃይል ከሀዘኑ በኋላ ዳግም ተገናኝቶ በተሠሩ ሥራዎችና ወደ ፊት አስተማማኝ ሰላም በሚሠፍንበት ጉዳይ ላይ ለመመካከር ቀጠሮ ተይዞ በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዕለቱ ውይይት በጸሎት ተዘግቷል፡፡

     ዘገባው የሀገረ ስብከቱ ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ነው

#Ethiopia 
#Birana_Media
#BM_Addia_Ababa

ብራና ሚዲያ
የኦርቶዶክሳዊያን ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/birana3

በፌስቡክ ገጻችን ትምህርቶች እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
https://www.facebook.com/birana22

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@birana16

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/birana96
ኪዳነ ምሕረት

በድንቅ ጥበቡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ያደነው እጅጉን መሐሪ ስለሆነ ነው፡፡ የቀደሙት የብሉይ ኪዳን ኪዳናት ሕዝቡን ከሲኦል መታደግ አልቻሉም ነበር፡፡ ፍጹም የሆነው ኪዳን የተደረገው በሰባተኛው ኪዳን ይህም ለሰው ዘር ምሕረትን ባስገኝች በንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ነው፡፡  
 
የምሕረት ቃል ኪዳን የተሰጠችውን እናታችንንም ‹‹ኪዳነ ምሕረት›› እያልን የምንማጸናት ለዚህ ነው፡፡ ለአዳም የተገባለት የምሕረት ቃል በእርሷ ተፈጽሟልና፡፡ እመቤታችን አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ወልዳዋለችና፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራን ተቀብሎ እንዲሁም በመስቀል ተሰቅሎ ዓለምን ያዳነው ከእርሷ በነሣው ሥጋና ነፍስ ነውና፡፡  
 
በነገረ ማርያም ተጽፎ እንደምናገኘው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት በኋላ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ልጇ መቃብር ቦታ ጎልጎታ እየሄደች ትጸልይ ስለ ነበር  በየካቲት ፲፮ ቀን በጸለየችው ጸሎት ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ ጸሎቷም እንዲህ የሚል ነበር፤ ‹‹ልጄ ወዳጄ ሆይ፥ ከሥጋዬ ሥጋ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በቻለችህ ማኅፀኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መጥተህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡››
 
ጌታችንም ምን ሊያደርግላት እንደምትሻ ሲጠይቃት በስሟ ለሚማጸኑ፣ መታሰቢያዋን ለሚያደርጉ፣ ለችግረኛ ለሚራሩ፣ በስሟ ቤተ ክርስቲያን ለሚያንጹ፣ ዕጣን፣ ዘይትና መብአ ለቤተ ክርስቲያን ለሚሰጡ ምሕረትን እንዲያደርግላቸው ጨምራ ጠየቀችው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በየካቲት ፲፮ ዕለት የገባላትን ቃል ኪዳን እንዲህ በማለት በመሐላ አጽንቶታል፡፡  ‹‹መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበአቡየ ወበመንፈስ ቅዱስ ሕያው፤ በራሴ፣ በአባቴ እና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ፡፡›› 

የምሕረት ቃል ኪዳን የተሰጠበት ይህ ዕለት ታላቅ ነውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቅት ታከብረዋለች፡፡ ቀድሞ ለነበሩ ኪዳናት ማለትም ኪዳነ አዳም፣ ኪዳነ ኖህ፣ ኪዳነ መልከ ጸዴቅ፣ ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ሙሴና ኪዳነ ዳዊት መደምደሚያ ነውና፡፡ ዘለዓለማዊ ስለ ሆነው የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳን እየታሰበም በመዝሙር፣ በማኅሌትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡
 
በክርስቶስ ክርስቲያን ለምንባል ለእኛ የሐዲስ ኪዳን የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ይህ አዲስ ውል የተደረገልን ለነፍሳችን ድኅነት በመሆኑ በስሟ እየተማጸንን እንዲሁም መታሰቢያዋን እያደረግን ለተራቡት ማብላት፣ ለተጠሙት ማጠጣትና ችግረኛ መርዳት ይገባናል፡፡  

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎት፣ አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን! 


#Ethiopia 
#Birana_Media
#BM_Addia_Ababa

ብራና ሚዲያ
የኦርቶዶክሳዊያን ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/birana3

በፌስቡክ ገጻችን ትምህርቶች እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
https://www.facebook.com/birana22

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@birana16

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/birana96
"ግብረ ሰዶማውያን ንስሐ እስኪገቡ ድረስ ማስጠንቀቂያ ሊሰጣቸውና ከሕብረት ሊከለከሉ ይገባል" የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ

የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም (ብ.ሚ./አዲስ አበባ)

የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በትናንትናው እለት በዋዲ አል ናትሩ በሚገኘው አባ ቢሾይ ገዳም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን በአጀንዳነት ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል የግብረሰዶማውያን ጉዳይን የተመለከተው አጀንዳ ይገኝበታል።

ቅዱስ ሲኖዶሱ ግብረሰዶማዊነትን አጥብቆ እንደሚቃወም እና ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ከሰው ተፈጥሯዊ ባሕርይ ውጭ የሆነ ፣ ከሕገ እግዚአብሔር የራቀ መሆኑን በመግለጫው አመላክቷል።

በግብረ ሰዶም ተግባር የወደቀ ማንኛውም ሰው እውነተኛ ንስሐ ፣ መንፈሳዊ እና ሥነ ልቦናዊ ክትትል ያስፈልጋቸዋል ያለው ቅዱስ ሲኖዶሱ መንፈሳዊና ሥነ ልቦናዊ ድጋፍን አለመቀበል እና በግብረ ሰዶማዊነት ለመቀጠል እና የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለመጣስ የሚሞክር በዝሙት ከሚኖር ሰው ይልቅ ሁኔታው ​​ይከፋል ያለ ሲሆን ስለዚህ በዚህ ሕይወት የሚኖሩ ሰዎች ንስሐ እስከሚገቡ ድረስ ማስጠንቀቂያ ሊሰጣቸውና ከሕብረት ሊከለከሉ ይገባል በማለት ገልጿል።

ቤተክርስቲያን ተመሳሳይ ጾታ ባላቸው ሁለት ሰዎች መካከል ያለውን የጾታ ግንኙነት ታወግዛለች ፣ ታስጠነቅቃለች ፣ ትከለክላለች  ያለው ቅዱስ ሲኖዶሱ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በግብረሰዶም ዝንባሌ የሚሰቃዩ ልጆቿን ከዚህ ሕይወት እንዲወጡ በመርዳት ረገድ ያላትን የኖላዊነት ሚና ፣ እንዲሁም እነሱን ባሉበት ሁኔታ አለመቀበሏን ወይም እንዲወጡ ድጋፍና እገዛን በማድረጓ ሥነ ልቦናዊና መንፈሳዊ ፈውስ ለመስጠት የምታደርገውን ጥረት በመደገፍ እምነትዋን በጽናት ታረጋግጣለች ብሏል።


#Ethiopia 
#Birana_Media
#BM_Addia_Ababa

ብራና ሚዲያ
የኦርቶዶክሳዊያን ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/birana3

በፌስቡክ ገጻችን ትምህርቶች እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
https://www.facebook.com/birana22

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@birana16

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/birana96
"#የትናንት ሊቃውንት አባቶቻችን ጦም እያደሩ  የጠበቋትን ቤተ ክርስቲያን እኛ እየበላን አሳልፈን መስጠት አይገባም"  ብፁዕ አቡነ አብርሃም

ከ200 በላይ የአብነት መምህራን የተሳተፉበት የምክክር ጉባኤ በመንበረ ፓትርያርክ ጽርሐ ተዋሕዶ እየተካሔደ ይገኛል።

አዲስ አበባ (ግንቦት ፲፭/፳፻፲፮ ዓ/ም / ብራና ሚድያ )

በመንበረ ፓትርያርክ ትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ ከሊቃውንት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው  ሀገር አቀፍ የምክክርና የውይይት ጉባኤ ማካሔዱን ጀምሯል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ የበላይ ሊቀ ጳጳስ፣የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ሐላፊዎች  ከየ አህጉረ ስብከቱ የመጡ ከ200 በላይ ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያንና የጉባኤ መምህራን  ተገኝተዋል።

ጉባኤው በጸሎተ ወንጌል የተጀመረ ሲሆን በማስከተልም የደብረ ምሕረት ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል ሊቃውንት
"ያሬድ ካህኑ ለእግዚአብሔር
ትርድአነ ነዐ በህየ መካኑ ያሬድ ነዐ ትርድአነ" የሚለውን ወረብ አቅርበዋል።

የመምሪያው ሐላፊ  መልአከ መዊዕ ሳሙኤል እሸቱ ሊቃውንቱ ከየጉባኤ ቤቱ የመጡትን ሊቃውንት አስተዋውቀዋል።
በዚህም የድጓ፣ የዝማሬ መዋስዕት ፣ የቅኔ ፣የአቋቋም ፣ የሐዲሳትና የብሉያት  መጻሕፍት ትርጓሜ መምህራን መሆናቸው ተገልጿል።

መልአከ መዊዕ ሳሙኤል እሸቱ ለጉባኤ መሳካት የበኩሉን ድርሻ የተወጡትን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የትምህርትና ስልጠና ዋና ክፍልንና ሌሎችን አመስግነዋል።

አክለውም ጉባኤ  ሁልጊዜ በየዓመቱ ከግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ከመጀመሩ በፊት ጉባኤ እንዲዘጋጅና እውቅና እንዲሰጠው ጥያቄ አቅርበዋል።

የእንኳን ደህና መጣችሁ አባታዊ መልእክት ያስተላለፉት ብፁዕ አቡነ አብርሃም  ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አልፈው ወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ ተቋቁመው   የተገኙትን ሊቃውንት እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉ ሲሆን የምክክር ጉባኤውን  ያሰናደውን የትምህርት ማሰልጠኛ መምሪያ  አመስግነዋል።

ብፁዕነታቸው  አክለውም ለዘመናት የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶች ቤተ ክርስቲያናችንን በበላይነት በሚመሩበት ጊዜ  "አማኙን ከሀገሩ" "እምነቱን ከታሪኩ" ጠብቀው ያቆዩ ሊቃውንት መሆናቸውን በማስታወስ አሁንም የበኩላችሁን የሊቅነት ድርሻችሁን በመወጣት ቤተ ክርስቲያናችንን ልታስከብሩ ይገባል ብለዋል።

በዚህ ዘመን በሕይወት የሚያገለግሉትን ሊቃውንት በኑሯቸውም ልናስባቸውና የት አሉ ልንል ይገባልም ብለዋል።

"የትናንት ሊቃውንት አባቶቻችን ጦም እያደሩ  የጠበቋትን ቤተ ክርስቲያን እኛ እየበላን አሳልፈን መስጠት አይገባም" ሲሉ ገልጸዋል።

ስለሆነም ሊቅነትን ከቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ውጤት ጋር በማጣመር ዘመኑን የዋጀና ትውልዱን የሚያተርፍ  አገልግሎት እንድታገለግሉ ወደፊት መምጣት ይገባችኋል ብለዋል።
 
ጉባኤው ለሁለት ቀናት የሚቆይ እንደሆነ ከወጣው መርሐ ግብር ለማወቅ ተችሏል።
#Ethiopia 
#Birana_Media
#BM_Addia_Ababa

ብራና ሚዲያ
የኦርቶዶክሳዊያን ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/birana3

በፌስቡክ ገጻችን ትምህርቶች እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
https://www.facebook.com/birana22

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@birana16

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/birana96
ማኅሌተ ጽጌ
በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ፣ በሀገራችን በኢትዮጵያ የወቅቶች ሥርዓተ ዑደት መሠረት ከመስከረም ፳፮ ቀን ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ ፳፭ ቀን ድረስ ያለው ፺ ቀናትን የሚያጠቃልለው ጊዜ ‹ዘመነ መጸው› ይባላል፡፡

‹መጸው› ማለት ‹ወርኀ ነፋስ› (የነፋስ ወቅት) ማለት ሲኾን ይኸውም ‹መጸወ ባጀ፤ መጽለወ ጠወለገ› ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ዘመነ መጸው ከዘመነ ክረምት ቀጥሎ የሚብት (የሚገባ) የልምላሜ፣ አበባ፣ የፍሬ ወቅት ነው፡፡

በውስጡም ዐምስት ንዑሳን ክፍሎችን የሚያካትት ሲኾን እነዚህም፡- ዘመነ ጽጌ፣ ዘመነ አስተምህሮ፣ ዘመነ ስብከት፣ ዘመነ ብርሃን እና ዘመነ ኖላዊ ናቸው (ያሬድና ዜማው፣ ገጽ ፵፰-፵፱)፡፡ከዐምስቱ የዘመነ መጸው ክፍሎች መካከልም የመጀመሪያው ክፍል ‹ዘመነ ጽጌ› ተብሎ ይጠራል፡፡

ይህ ወቅት ዕፀዋት በአበባ የሚያጌጡበት፣ ምድር በአበቦች ኅብረ ቀለማት የምታሸበርቅበት፣ ወንዞች ንጹሕ የሚኾኑበት፣ ጥሩ አየር የሚነፍስበት፣ አዕዋፍ በዝማሬ የሚደሰቱበት፣ እኛም የሰው ልጆች ‹‹አሠርጎካ ለምድር በሥነ ጽጌያት፤ አቤቱ ምድርን በአበቦች ውበት አስጌጥሃት›› እያልን የዘመናት አስገኚ እና ባለቤት የኾነውን ልዑል እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት፤ ከዚህም ባሻገር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደ ልጇ ጋር ከገሊላ ወደ ግብጽ ምድር መሰደዷን የምናስብበት ወቅት ነው፡፡

ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተ ልሔም በተወለደ ጊዜ የዘመኑ ንጉሥ ሄሮድስ ሥልጣኔን ይቀማኛል በሚል ቅናት ተነሣሥቶ ጌታችንን ለማስገደል አሰበ፡፡ ጌታችንም በተአምራት መዳን ሲቻለው የትዕግሥት፣ የትሕትና አምላክ ነውና በለበሰው ሥጋ በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ጀርባ ታዝሎ በመልአኩ ተራዳኢነት፣ በአረጋዊው ዮሴፍ ጠባቂነትና በሰሎሜ ድጋፍ ከገሊላ ወደ ግብጽ ተሰዶ ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ ቆይቷል፡፡

ዘመነ ጽጌ ሰው ዘመኑ እንደ አበባ በቶሎ የሚረግፍ መሆኑን በማሰብ ይህ ዘመን ሳያልፍ መልካም ሥራ ለመሥራት ትንሣኤ ኅሊና የሚነሣበትበትም ጊዜ ነው፡፡

በአባ ጽጌ ድንግል የተደረሰው  “ማኅሌተ ጽጌ” በማንኛውም ጊዜ የሚጸለይ ቢሆንም በተለየ ሁኔታ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውለው ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ቀን ድረስ ባለው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የስደት ዘመን ነው፡፡

በዚህ ወቅት በየሳምንቱ እሑድ ሌሊት በሙሉ የእመቤታችንን ከልጇ ጋር ወደ ግብፅ መሰደድና መንከራተት እያሰቡ የሚደረስ ምስጋናና ጸሎት ነው፡፡

አባ ጽጌ  እመቤታችንንና ልጇን በጎ በጎ መዐዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግነውን ማኅሌተ ጽጌ የተባለውን ድርሰት፤ በአባቷ በዳዊት መዝሙር መጠን መቶ ኀምሳ አድርጎ ደርሷል፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ጋር በተሰደደች ጊዜ የደረሰባትን መከራ በማስታወስም ብዙ ካህናትና ምእመናን ዘመነ ጽጌን በፈቃዳቸው ይጾማሉ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ምንጭ፡- ሐመር መጽሔት፣ መስከረም 2005 ዓ.ም.
           

#Ethiopia 
#Birana_Media
#BM_Addia_Ababa

ብራና ሚዲያ
የኦርቶዶክሳዊያን ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/birana3

በፌስቡክ ገጻችን ትምህርቶች እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
https://www.facebook.com/birana22

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@birana16

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/birana96
የ፵፫ ኛው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዓለም አቀፍ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ  በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

ጥቅምት ፬/፳፻፲፯ ዓ/ም  ( ብራና ሚድያ )

የ፵፫ ኛው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዓለም አቀፍ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ  በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

ጉባኤ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ  ተክለ ሃይማኖት ርእሰ መንበርነት እየተመራ ይገኛል።

ቅዱስነታቸው የመክፈቻ መልእክት አስተላልፈዋል።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም  የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክሆነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  የዋና መሥሪያ ቤቱን አጠቃላይ  ሪፖርት አሰምተዋል።

በሪፖርቱ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ  ፓትርያርክ  በዓመቱ ያከናወኗቸውን ሐዋርያዊ አገሎግሎቶች፣ የየመምሪያውና የድርጅቶች፣ የመንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች ዓመታዊ ሥራ ክንውኖችን አቅርበዋል።

በጉባኤዎ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣  የየመምሪያና የድርጅት ሐላፊዎች፣ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፣ የሀገረ ስብከቱ የዋና ዋና ክፍል ሐላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጆች፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ምክትል ሊቃነ መናብርትና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች  ተገኝተዋል።

ጉባኤው እስከ ጥቅምት ፲/፳፻፲፯ ዓ/ም እንደሚቆይ ከወጣው መርሐ ግብር ለማወቅ ተችሏል።

የመጀመሪያው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዓለም አቀፍ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ  በ1975 ዓ/ም እንደተካሔደ መረጃዎች ያመለክታሉ።

#Ethiopia 
#Birana_Media
#BM_Addia_Ababa

ብራና ሚዲያ
የኦርቶዶክሳዊያን ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/birana3

በፌስቡክ ገጻችን ትምህርቶች እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
https://www.facebook.com/birana22

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@birana16

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/birana96
በ2016 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት 271 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው ተገለጸ !

ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም(ብ.ሚ./አዲስ አበባ)

በየዓመቱ በሚካሄደው በ፵፫ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ዓመታዊ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በሀገረ ስብከቱ በሚገኙ ከተሞችና ወረዳዎች የሚገኙ መንፈሳዊ የአብነት ትምህርት ቤቶች የመምህራንና የተማሪዎች መሠረታዊ ፍላጎት ማሟላት መቻሉ ተገልጿል፡፡

በአሰላ ማኅደረ ስብሐት በዓታ ለማርያም ቅ/ፋኑኤል ወቅ/ዮሐንስ  ወ/ነጎድጓድ ገዳም በማኅበረ ቅዱሳን ከተገነባው ሕንጻ በተጨማሪ በመንፈሳዊ ትምህርት ቤቱ የመማርያ ክፍሎች አንዲሁም የመምህራንና የደቀ መዛሙርት ማረፊያ ቤቶች መሥራት ተችሏል ተብሏል፡፡

በሀገረ ስብከቱ በሽርካ ወረዳ ከ10 ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ 91 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ ምእመናን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ሲል ሀገረ ስብከቱ በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም በደጁ ወረዳ ቡርቃ ጉራቻ ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚኖሩ 150 ምእመናን በጉሬ ደቢኖ ቅ/እግዚአብሔር አብና አርጆ ቅ/ጊዮርጊስ ከ30 በላይ ምእመናን መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን 499 አባወራና እማወራ ለስደት መዳረጋቸው ተነግሯል፡፡

#Ethiopia 
#Birana_Media
#BM_Addia_Ababa

ብራና ሚዲያ
የኦርቶዶክሳዊያን ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/BiranaMedia

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/birana3

በፌስቡክ ገጻችን ትምህርቶች እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
https://www.facebook.com/birana22

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/@birana16

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/birana96