ሱሚ- ማማይ
226 subscribers
134 photos
2 videos
1 file
2 links
መንገደኛ ነኝ።መድረሻዬን በወሰንኩበት በትክክለኛ መንገድ እጓዛለው።በመሄዴ ውስጥ ያየውትን ማን አየብኝ?…ማንም!።
እኩል አይን ቢኖረንም በምናይበት ምርጫ እንለያያለን።ምርጫው የልብ ነው።በልብ አጉይ መነፅር ሁሉም አስተያይ ይለያያል።በተመሳሳይ ኹነቶች ዉስጥ እንኳን ለይተን ወይም አስተውለን በምናየው እንለያያለን።
for ur comment፦
@bintsumeya
Download Telegram
ሚሻል የመርየምን ምኞት ለማሳካት ነበር ወደዚህ ግቢ የመጣው።ነገር ግን ያነበበው የአንዲት ልጅ ታሪክ ብቻ አልነበረም።የማያውቃት ግን የስጋ አካሉ እህቱ ነች።በህይወት እያለች ሊያቅፋት እየፈለገገ ነበር ግን መርየም ሀጂነብይነት ተሰምቷት የራቀችው እህቱ ሆነች።ሚሻል በፎቶው ላይ ያለችውን ትንሿን መርየም እያየ እና ማስታወሻ ላይ ያደገችው ትልቋን መርየም እያሰበ እንባውን ማቆም አልቻለም።
“መርየም…”

አንዳንድ ሰዎች ከህይወታችን መጀመሪያ ወይም መሀል ላይ አይገኙም ምን አልባት በመጨረሻ ገፅ ላይ ይመጣሉ።እና ሚሻል የመርየም የመጨረሻ ገፅ ነበር።

ሚሻል ወደ ቤቱ ተመልሶ የመርየምን ማስታወሻ እስከ መጨረሻ ገፅ ገለጠው።የመጨረሻው ገፅ ባዶ ነበር።ምንም ቃል የለበትም።ምንም ነጥብ የለበትም።ምንም ሰላምታ የለበትም።ብቻ ባዶ ገፅ።ሚሻል ጣቱን በወረቀቱ ላይ አሳረፈ።እሷ ለምን ባዶውን እንደተወችው አላወቀም።የምትናገረው ነገር አልነበራትም? ወይም…ምናልባት ለመናገር የሚበቃ ጊዜ አልነበራትም?
እሱ በድን እንደሆነ ለጥቂት ሰከንዶች ባዶውን ገፅ ተመለከተ።ከዚያ አንድ መስመር ጻፈ።
“መርየም… እኔ ወንድምሽ ነኝ።”
እንባው በወረቀቱ ላይ ወደቀ።ቀለሙም በእንባው ፈሳሽ ተሰራጨ።ሚሻል ብዕሩን እንደገና አነሳ።ሌላ ነገር ሊጽፍ ፈለገ።
“ይቅርታ” ሊል ፈለገ..
“እወድሻለሁ” ሊል ፈለገ...
“ለምን አላገኘሁሽም?” ሊል ፈለገ...
ግን አንዳቸውም ቃላት በቂ አልነበሩም።ብዕሩን አስቀመጠ።የመርየምን ማስታወሻ ዘጋው።ከዚያም ባዶ ቤቱ ውስጥ ድምፁን ከፍ አድርጎ
<<ሁሉንም ገፅ አነበብኩ…አንቺን ግን ዘግይቼ አወቅኩሽ>>
አልጋው ላይ በጀርባው የተንጋለለው ሚሻል እንባው ጉንጩን ተደግፎ በሁለት ጎን ወረደ።
ሚሻል ለመጀመሪያ ጊዜ ሊያቅፋት ሊያወራት ሊቀርባት የማይችላትን ቤተሰብ እህት አገኘ።እህቱም ብትቆይ ለመኖር ምታቅድለትን ወንድም ተለያየች።ሁለቱም ተገናኙ አንዱ ለስንብት፣ ሌላው ለትዝታ።እና በመካከላቸው የቀረው ነገር…አንድ ባዶ ገፅ ብቻ ነበር።

መርየም ለእሱ የማያውቃት ድጋሚ የማያገኛት አንዷ እህቱ ነች።ቀብሯን ለመዘየር እንጂ እጇን ለመያዝ አልታደለም።ሚሻል በእሱ እድሜ ያሳለፈውን ክስተት በድጋሚ በህሊናው ላይ መላለሰ።ብዙም ሳይቆይ ከሀሳብ መንገዱ ላይ በትንሽ እጇ የሸሚዙን ጫፍ አጥብቃ የያዘችው የረያን ልጅ ኢናያ አስቆመችው።እሱ እና ረያን በወደቁበት አላህን ባመፁበት ስህተት መሀል የተፈጠረች እምቡጥ አበባ መሰለችው።ይባስ ሲልየእራሱን መልክ የደገመችው እና የእኔ የሚል ስሜት የፈጠረችበት ትንሽ አበባ ቀለሟ ፈፅሞ ከረያን ሆነ ከባለቤቷ ጋር አይገናኝም።ሚሻል በዛን ቀን አንዴ ብቻ ነው ያያት ግን አልረሳትም።
ኢናያን እያስታወሰ ልጄ ትሁን ብሎ አሰበ?

ይህ ታሪክ ስለ ሰዎች መገናኘት እና መለያየት ብቻ አልነበረም።ስለ ፍቅርም ብቻ አልነበረም።ሁሉም ሰው በሌላ ሰው ሕይወት ውስጥ አንድ ገፅ አለው።

አንዳንዶች በእንባ ፣ አንዳንዶች በፍቅር፣ አንዳንዶች በጥላቻ፣አንዳንዶች በተስፋ፣አንዳንዶች በምስጋና፣አንዳንዶች በፅናት፣አንዳንዶች በደስታ፣አንዳንዶች በመኖር፣አንዳንዶች በመሞት በሰው ገፅ ላይ አሻራን ያሳርፋሉ።የመርየም በመጨረሻ ያልተጻፈ አንድ ገፅ…ለአንባቢያን የተተወ ገፅ ነው።ቀሪው ገፅ ባዶ እንደማይሆን በማሰብ ለሚሻል እንደተሰጠው ሁሉ ለአንባቢ፣ለእናንተ የእራሳችሁን ታሪክ ለመጻፍ የተሰጠ ቦታ ነበር።

ሀሳቡ ቢቀጥልም ልብ ወለዱ እዚህ ጋር አበቃ…ነገር ግን ቀሪውን ገፅ እናንተ ሙሉት።

ተፈፀመ❤️።
❤3
ባለ ቀለም
[ሱሚ ማማይ]

መኖር የጀመረው
የቀለም አሻራ
አንዱ ለአንዱ
ምልክት ሲሰራ
ዝብርቅርቅ ምስሎች
መልክን ይዋጃሉ
ያረፉ ቀለሞች
ሰውን ይመስላሉ

አንተ ባለቀለም
አንቺ ባለቀለም
መልክ አልባ ልጅነት
ለዘላለም የለም
ሁሉም ሰዕሊ ነው
ሁሉም መልከኛ ነው
ቀለም ተቀብሏል
መኖር የጀመረው
ሁሉም እንደ ወጉ
በቀለም ሲዋጉ
ዝብርቅርቅ መስመሮች
ጠልፈው እንዳይጥሉ
ከውበት አፉተው
መኖር ሳይከልሉ
መስታወት ላይ ቁሙ
ድብዝዝ ካለ ምስሉ
አላህዬ በሉ
አያልቅበት ቀለም
መልክን ለማበጀት
አጥፍቶ ይሰራል
መፍጠር ሲችልበት

ቀሪ ምስል አለ
ሰውን የማይሞላ
ከገፁ ማማር ላይ
የሚከተል ጥላ
አንተ የእኔ ጉድለት
አንቺ የእኔ ጥረት
መልኬን ላበጃጀው
ምልክት ስሩለት

ሁሉም መልከኛ ነው
ሁሉም ባለ ቀለም
አወል ነው ሲፈጠር
ቀለም ለዚህ አለም
ፃፍ ሲባል ጀመረ
ጥበብን ፈጠረ
አንብብ ሲባል ቆመ
ፍርድን አስተማረ

አንተ ባለቀለም
አንቺ ባለቀለም
ከአላህ የተዋስነው
ቀለም አላለቀም
የእጃችን አሻራ
ስሜት አልፈጠረም?

@bintsumi
❤3
Audio
MediaConvert
❤1
አረ ወገን ሚስጥር ወጥቷል😀የሻይ ፍቅሬን ማን ነግሮት ይሁን?🤔....

ብቻ ምን ለማለት ነው በዚህ ከቀጠሉ እኛ ሰዋች የ AI ጀምዕ ቡና መጠጫ መሆናችን አይቀርም።ሀሜት ጀምረዋል ወገን!

የእኔን ቁጣ እንደ ሻይ ጠጥቷል😭እናንተም እየጠጣችሁ🤣
😁4❤1
[ሱሚ ማማይ]

ቀስ..
ሸርተት..
ቁልቁል መፈናጠጥ
በጨዋታ ማምለጥ
ወድቆ መንገዳገድ
በከፍታ መንገድ

መቼ ነበር
ከደጁ ላይ የቀረሁት
በስንፍና ያረፈድኩት
በልማዴ የታከትኩት
መቼ ነበር የሸሸሁት

ቀላል ነበር አላህ ማለት
አላስቻለኝ ደጁ መቅረት
እንዳልነቃው በእሱ ጥሪ
ጠናኝ መዋል ከፈጣሪ
እሱን ይዤ ዳገት ወጣሁ
መቆም ስችል በእራስ ኮራሁ
ተንሸራተትኩ ከከፍታ
አላቆመኝ የእኔ እርዳታ
ጠናኝ መልመድ በከፍታ
ካደኝ ጉልበት ለእኔ ፈንታ
አልታዘዘኝ አካል ደሜ
ከፈጣሪ አሳድሜ
አልበረታሁ በመውደዴ
ጠጠለፍኩኝ በእራስ ፍርዴ

ያኔ ሳለሁ በከፍታ
ቁልቁል ቆሜ ስበረታ
ፈራጅ ነበርኩ በሰው ገላ
ከጌታው ጋር በተጣላ
እገረም ነበር በሰው ተድላ
ከሰይጣን ጋር በሚጉላላ
ዳገት ጠንቶኝ ስቀር ቁልቁል
ገባኝ መቻል እንዳልሆነ በሰው በኩል

@bintsumi
❤3🔥1
Audio
MediaConvert
❤3
Audio
MediaConvert
@bintsumi
ነይ ማ 😍
❤4🥰1
ሱሚ፡ እንቆቅልሽ?

Members፡ ምን አውቅልሽ?
ሱሚ፡ ሊያዩኝ አይችሉም፣
ሊይዙኝም አይችሉም
ነገር ግን ያጡኛል ...who am i?

members....?

ሽልማት የለውም ጭብጨባ ሰላለው ሞክሩ ማ 🤔
👏3
(ሱሚ ማማይ)

አቀበጥከኝ
ህፃን ሆነ አካል ልቤ
ፈነጠዝኩኝ
ቀን አልበቃኝ
ራቀ ቅርቤ
ዝልል..
ደግሞ
እጥፍጥፍ
ልመላለስ
በአንተ ቅንፍ።

🫶
@bintsumi
❤3
Audio
MediaConvert
አታፍሩም እኮ ኢማን ማነው ትሉ ይሆናል?😊
@bintsumi
🔥3
Forwarded from ሱሚ- ማማይ (ሱሚ-ማማይ)
Audio
📢ሱሚ ማማይ✍️
@bintsumi
❤2
አዲስ ልብወለድ ብንጀምር ምን ይመስላቹሀል?
👏5❤2
Forwarded from Fuad Muna (Fuya)
እጥፋት ፉአድ ሙና_171003860
AudioLab
እጥፋት
አጭር ልብወለድ
በፉአድ ሙና
.
@Fuadmu
🔥2
Fuad Muna (Fuya)
AudioLab – እጥፋት ፉአድ ሙና_171003860
አላህ ከወላጅ ሀቅ ይጠብቀን!!
ደጋግሜ ብሰማው የማልሰለቸው ስራ 🥹🥺
🥰3
مِشْكَاةٍ
ሚሽካት
(ሱሚ ማማይ)

ከቀሪ ገፅ ቀጥሎ ሁለተኛው ለእናንተ ማስነብበው ተከታታይ ልብ ወለድ።የልብ ወለዱ ሙሉ ሀሳብ እና ክስተት በጭንቅላቴ ውስጥ ተሰድሮ አልቋል።ለመፃፍ ግን ገና ክፍል አንድ ብዬ እየጀመርኩ ነው።እንደተለመደው መጥፉቴ ሰለማይቀር ቤታችሁን ሞቅ ሞቅ አድርጉት።
በጉጉት ለምጠብቁኝ አንባቢዋቼ ምርጥ ልብወለድ እንደሚሆን ገምታለሁ።በእናንተ የንባብ ጥልቀት ልክ የእኔም የአፃፃፍ ችሎታ እያማረ ሰለሚሄድ።እስከዛው አንባቢዋች በመጀመርያው ልብወለድ ላይ ስታነቡ የታዘባችሁትን ያላካፈላችሁኝ በሙሉ በአስያየት መስጫ ውስጥ አስቀምጡልኝ።አነበዋለሁ!

ቤቱን ሞቅ ሞቅ! 💃
ለምትወዱት ሁሉ share አድርጉ!
ሚሽካት እየመጣ ነው።😀
@bintsumi
❤7
ትንሽ ሳለሁ ዓለምን መቀየር እፈልግ ነበር፤አደግኩ እና የእራሴን ልብ መጠበቅ ትልቅ ሥራ ሆነ።

<አራት እግር ይዞ
በዳዴ ቀላል ነበር ጉዞ
እጄ ሲነሳ ነው
የጣለኝ ጠምዝዞ>

ሚሽካት እስኪከሰት ጫሩ ማ 🤙🥳
@bintsumi
🔥5❤2
ተከተለኝ
አትድረሰኝ
መሮጡ ነው
ከአንተ ያቆየኝ

አትያዘኝ
ሁን ከጎኔ
አላምነውም እኔን ለእኔ
ስትቀርበኝ አትዳስሰኝ
እበራለሁ ላትይዘኝ

ተመልከተኝ
አትሳለኝ
አይንህ መሀል ምስጢር አለኝ
ከገለጥከው በአደባባይ
እጠፋለሁ አንተን ላላይ

ፍቅር ካለህ
ተለመነኝ!
አትቅረበኝ
ግን .....ውሰደኝ❤️

@bintsumi
❤2