ሱሚ- ማማይ
226 subscribers
134 photos
2 videos
1 file
2 links
መንገደኛ ነኝ።መድረሻዬን በወሰንኩበት በትክክለኛ መንገድ እጓዛለው።በመሄዴ ውስጥ ያየውትን ማን አየብኝ?…ማንም!።
እኩል አይን ቢኖረንም በምናይበት ምርጫ እንለያያለን።ምርጫው የልብ ነው።በልብ አጉይ መነፅር ሁሉም አስተያይ ይለያያል።በተመሳሳይ ኹነቶች ዉስጥ እንኳን ለይተን ወይም አስተውለን በምናየው እንለያያለን።
for ur comment፦
@bintsumeya
Download Telegram
ቀሪ ገፅ
[ሱሚ ማማይ]
ክፍል አስራ ስምንት
****

የዲህያ የንግግር ውበት በፍቅር አጠመደኝ።ለእሱ በነበረኝ ፍቅር ምንም ስሌት አልነበረኝም።ለምን? ስባል ቀድሞ የሚመጣልኝ ምመልሰው ምክንያትም የለኝም።እኔ ማውቀው ከቀን ወደ ቀን እሱን መናፈቄን ብቻ ነው።
ዛሬም ሞተሩን እየነዳ ከሱቁ ፊት ቆመ።ዲህያ እህቱ የሌለችበትን ሰዕት ጠብቆ ነበር የሚመጣው።

<ሰላም አለይኩም>አለኝ ደከም ባለ አነጋገር።
<ወአለይከ ሰላም>አልኩት።የእሱ ድካም እኔም ጋር እየተጋባ።
<አልሀምዱሊላህ ሁሉም ነገር ከአንቺ አይን በሃላ ይቀለኛል>አለ።ለእንባ ትግል በገባ ቀይ አይኑ።
<ምነው? ደህና አይደለህም>አልኩት።በፍርሀት እና በስስት ብዝዝ ባለ አይኔ።
<የማስበውን ማሳካት አልቻልኩም ሀሳቤ እና እኔ ሰማይ እና ምድር ነን ቅርብ መሳይ ሩቆች በአላህ ላይ ተስፋ አለኝ ያጎደልኩት ቢበዛ ውስጤ ደከመ ልቤ ታመመ>አለኝ።በተደጋጋሚ ስጠይቀው ለመስራት የጀመረውን የእራሱን ቤት መቀጠል እንደከበደው እና ከሰው ጋር መግባባት እንዳዳገተው ቀጥሎ ነገረኝ።በመሀል እህቱ ስትመጣ ወሬያችን ተቋረጠ።

<አኩ ከመጣህ ቆየህ?>አለች።ሲሀም ዲህያን አኩ ብላ ነው ምትጠራው።
<ብዙም አይደለም...የት አርፍደሽ ነው>አላት።
<አይመስለኝም...እኔን ፈልገህ አልመጣህም ችግር አለ>አለች።ከኒቋቧ ውጭ ብቸኛ የሚታየውን አይኗን ወደ እኔ እያዞረች።
<የለም አብሽሪ የቤቱ ጉዳይ አስጨንቆኝ ነው>አለ።ዲህያ ንግግሩን ቀለል እያደረገ።
<ታዲያ ልብስ ቤት ውስጥ ግንበኛ እየፈለክ ነው>አለች በአሽሙር።በአነጋገሯ ፈገግ ያለው ዲህያ<የእህቴ ቤት ሙሉ ነው አይታጣበትም ሲባል ሰምቻለሁ>አላት።
<ተው እሱን..እኔን ሲሀም አትሸውደኝም ብቻ እናወራለን>አለችው።ከድሮም ጀምሮ ምፈራት እኔ ይህን ከሰማው በሃላ ይበልጥ ባሰብኝ።ልክ ሳያት ውሀ ውስጥ እንደ ገባ ብስኩት እፈራርሳለሁ።ከዚህ ንግግር በሃላ ሰለ እኔ እንደሚያወሩ በማሰብ ዳግም ዲህያን አግንቼው ድብቅ ስሜቱን በመፈተሽ እስክረዳ ትዕግስት አጥቼ ጠበቅኩ።ከሁለት ቀን በሃላ ወደ ሱቅ መጣ።እህቱ ሲሀም አብራኝ ሰለነበረች እሱን ሳየው ድንብርብሬ ወጣ።የአላህን ሰላምታ ለሁለታችንም በማቅረብ ኒቃቧን ፈታ ወደ ውስጥ ከተቀመጠችው እህቱ ጎን ሄዶ ተቀመጠ።
<ኡክተል ጋሊ ምሳ በአንቺ ግብዣ ነው አልተቋጠረም ዛሬ>አለ ባዶ እጁን እያሳያት።
ሲሀም<ኡሚ ነግራኛለች በጣም ሰለራበኝ አሁኑኑ ቆንጆ ሽሮ እናዛለን>አለች።እኔን ከቦርሳዋ ብር አውጥታ ወደ ምግብ ቤት እየላከችኝ።እኔ ከድርጅቱ ምግብ ቋጥሬ ሰለምመጣ ብዙን ግዜ ቀደም ብዬ ነው ምበላው።በልተው ሲጨርሱ ንግግራቸውን ቀጠሉ።<ሷሊሃን አገኘሀት እንዴት እንዳማረባት በፊት እንደምታውቃት አይደለችም>አለች እህቱ።መስማት ሰለምፈልግ ንግግራቸው ከመጋረጃ ጀርባ ይሰማኛል።
<እረፍት መጥታ ነው? ግቢ ከሄደች አላገኘሃትም>አላት።
<ከድሮም ማሻ አላህ ቆንጆ ነች ግን ይበልጥ ግቢ ከገባች በሃላ አማረባት>አለች።ሲሀም በመገረም ታወራለች።እኔ ግን ከዲህያ ጋር ሰለ ሴት እያወሩ ሰለሆነ ወሬው ምቾት አልሰጠኝም።ወንበሩ ጠቦኝ በተቀመጥኩበት ተንቆራጠጥኩ።ዲህያ እየቀጠለ<ውበት ቋንቋ ነው የተለያየ ፍቺ አለው እኔ መልክ የሚታየኝ የምወዳት ሴት ስትሆን ብቻ ነው ከእርሷ ውጪ ያለ ውበት ሁሉሉ የአይን ጥላ ነው
ፍቅር የውበት ቅመም ነው ልብ ባልወደደው ፊት ላይ ውበት አይቆጥርም>አላት።ሲሀም የሀሳቡ ደጋፊ መሆኗን አንገቷን ነቅንቃ ገለፀች።እኔ ግን ልቤ ከደረቴ ውስጥ ለመውጣት በኃይል ይመታ ጀመር። እነዚያ ቃላት ለእኔ የተባሉ መስለው ቢሰሙኝም በሆነ ምክንያት ግን ልቤ ውስጥ እየተደጋገሙ ነበር።ዓይኔን ከእሱ ላይ ለማንሳት እሞክር ነበር፤ ነገር ግን ሳላስበው በድብቅ እየተመለከትኩት ነው።ዲህያ የሚናገረውን ሲጨርስ ለአፍታ ዝምታ ሰፈነ። በሱቁ ውስጥ የሚሰማው የሰዓቱ ቲክታክ የሚለው ድምፅ እና ከመንገድ ላይ የሚሰማው የመኪና ረብሻ ብቻ ነበር።ረጅም ሰዕት ምግብ በልተው በዝምታ አረፍ ካሉ በሃላ እህቱ ቀድማ ወጣች።ዲህያ እህቱ እንደወጣች ዓይኖቹ ወደ እኔ ተመለሱ። ለጥቂት ሰከንዶች ብቻ ተያየን፤ ነገር ግን ያቺ ቅጽበት ለእኔ እንደ ሰዓታት ረዘመች።
<መርየም...ልሂድ ወደ በኋላ እመጣለሁ>አለኝ።ወደ በሩ እየተራመደ እያለ ተመልሶ ቆመ። ወደ ኋላ ሳይዞር በተረጋጋ ድምፅ
<አንዳንድ ስሜቶች… ለመናገር ቀላል አይደሉም ነገር ግን ለዘልዕለም መደበቅ አይችሉም>አለ።ያን ብሎ ወጣ
በዚያው ምሽት ሲሀም ደወለችልኝ።ድምፆ እንደተለመደው አልነበረም።
<መርየም… ዲህያ ስለ አንቺ የነገረኝ አንድ ነገር አለ…>ልቤ የቆመ መሰለኝ።
<ምንድን ነው?>አልኳት በተንቀጠቀጠ ድምፅ።

ይቀጥላል
@bintsumi
❤3
ቀሪ ገፅ
[ሱሚ ማማይ]
ክፍል አስራ ዘጠኝ
****

ዲህያ እኔን የሚያውቀኝ በዛች የእህቱ የልብስ መሸጫ ቤት ውስጥ ብቻ አልነበረም።ሰለ እኔ በተለያየ መንገድ የሚያውቀው ነገር ነበረው።እህቱ ጋር እንድሰራ ያመቻቸልኝ እራሱ ነበር።

ያን ምሽት ስልኬ ጠራ። ቁጥሩን ሳየው ሲሀም ነበረች። ልቤ በድንገት ፈጠነ፤ ከዲህያ ጋር የተያያዘ ነገር እንደምትነግረኝ ተሰማኝ።
<አሰላሙ ዐለይኪ መርየም>
<ወዐለይኪ ሰላም፣ ሲሀም>ለጥቂት ሰከንዶች ዝም አለች።
<አንድ ነገር ልጠይቅሽ?>
<እሺ>
<መርየም፣ እኔ በቀጥታ እና በግልፅ መንገድ መናገር እወዳለሁ ወንድሜ አንዴ ሰውን ከወደደ… እስከመጨረሻ ይወዳል>ልቤ በሀይለኛው መምታት ጀመረ።
<.....ወንድሜ አንቺን እንደሚወድሽ አስተውያለሁ>ይህን ቃል ስትናገር እጄ ላይ የነበረው የስልክ ክብደት ተሰማኝ።
<ነገር ግን…>ድምፆዋ መልሶ ቀዝቀዝ አለ።<...እኔ ይህን ነገር አልወደድኩትም>ይህን ስትል የደም ዙውውሬ እንደቆመ ተሰማኝ።ንግግሯን ቀጠለች<....ምክንያቱም ወንድሜን አውቀዋለሁ ብዙ ኃላፊነቶች እና ህልሞች አሉት አንቺ ደግሞ እሱን መረዳት የምትችይ አይመስለኝም እንደሰማውት በቤተሰብ መሀል አላደግሽም ይህን ስል ለማሳነስ አይደለም፤ ግን ትዳር የሁለት ሰዎች ብቻ አይደለም>ዓይኖቼ በእንባ ተሞሉ።<ስለዚህ… እሱም አይስማ ከወንድሜ ራቂ እሱን ከወደድሽው እንኳን… ልብሽን የማይሆን ተስፋ አትስጪ>ሲሀም ይህን ስትል ከንፈሬ ተንቀጠቀጠ።
<እንዳልሽው እኔ ወላጅ የለኝም፤ ግን በዚህ ሰበብ ክብሬን አልጥልም ብትረጂ ድህነት እና ወላጅ ማጣት የሰውን ዋጋ አይቀንስም>ስል በተሰበረ ድምፅ አወራሃት።
<ይቅርታ መርየም… ልጎዳሽ አልፈለግኩም ወንድሜን በጣም እወደዋለሁ..ለዛ ነው>አለች።
ስልኩም ከተዘጋ በኋላ ለረጅም ሰዓት ከቦታዬ ሳልነሳ ተቀምጬ ቀረሁ።
ከዚያ ቀን በኋላ ዲህያ ለጥቂት ቀናት አልመጣም። ሱቁ ፊት የሞተር ድምፅ በሰማሁ ቁጥር ልቤ እንደ ልጅ ይዘል ነበር፤ ነገር ግን እሱ አልነበረም።አምስተኛው ቀን ምሽት ላይ ግን መጣ። ፊቱ እንደተለመደው ፈገግታ አልነበረበትም።ሰላምታ አቅርቦልኝ።እህቱ ሰለነበረች ነገ የሚነግረኝ ነገር እንዳለ ነግሮኝ ወጣ።ዲህያ ከሱቁ ከወጣ በኋላ እኔ እዚያው ቦታ ተቀምጬ ቀረሁ።ሰዓቱ እየተንቀሳቀሰ ነው።እኔ ግን በነገረኝ ቃላት ውስጥ ተጣብቄ ቀረው።
<ነገ ስመጣ… አንድ ነገር እነግርሻለሁ>ምን ሊነግረኝ ነው?የልቤ ጥያቄ ነበር።
ሲሀም ዲህያ እንደወጣ ወደ እኔ ለደቂቃ ተመለከተች።
<መርየም…ዲህያ ምን ነበር ያወራሽ?>ጥያቄ ቢሆንም ውስጡ ግን ጥርጣሬ ነበረው።
<ምንም ሰላም ነው ያለኝ>አልኳት።
ሲሀም አንገቷን ዝቅ አድርጋ ለጥቂት ሰከንዶች ዝም አለች።ከዚያም <መርየም፣ አንድ ነገር እንድትረጂ እፈልጋለሁ አኩ ቀላል ሰው አይደለም ሰውን ሲወድ ልቡን ሙሉ ይሰጣል እኔ ደግሞ ወንድሜ እንዲጎዳ አልፈልግም>የቃሏ ክብደት ተሰማኝ።
<እኔም እንዲጎዳ አልፈልግም>አልኳት በድፍረት።
<እንግዲያ ራቂው>አለች።ዓይኔን ከእሷ ላይ ማንሳት አልቻልኩም።ምክኒያቷን እያወክቁት<ለምን?>አልኳት።
ሲሀም በቀጥታ ተመለከተችኝ።<ምክንያቱም እኔ አንቺን እንደ ወንድሜ ሚስት አላይሽም>ያ ቃል በልቤ ላይ እንደ ድንጋይ ተወረወረ።ለአፍታ ዝም አልኩ።
<አውቃለሁ የምለው ነገር ሊያሳምምሽ እንደሚችል ነገር ግን ትዳር መመጣጠን ይፈልጋል የእሱ እድገት ከአንቺ አስተዳደግ ጋር ፈፅሞ አይገናኝም>አለች ሲሀም።ይህን ስትል ድምፄ ሳላስበው ተንቀጠቀጠ።
<አዎ… ወላጅ የለኝም ይህ ማለት ግን ፍቅርን አላውቅም ማለት አይደለም እኔ ለብዙ ሰው ሰው ሆኜ ነው የኖርኩት የአንቺን መመዘኛ ባልረዳም ለዲህያ ግን አላንስም...እኔን ተይኝ! ቀድሞ ይሄንን ጥያቄ ያነሳውን ወንድምሽን ጠይቂው ተይኝ በቃ! >በንዴት ሰውነቴ ተንቀጠቀጠ።
<እኔ እንደዚያ ማለቴ አይደለም ግን የሚሰማኝን አልደበቅኩሽም>አለች።በንግግሯ ምንም ሳታፍር።
እንባዬ ሊወርድ ሲል በፍጥነት በእጄ መለስኩት።እኔ የምፈልገው ማንም እንዲያዝንልኝ አልነበረም።ብቻ እንደሌሎች ሰዎች መፈቀር ነበር የፈለግኩት።ሲሀም ቀጠለች።<ዲህያ አንቺን እንደሚወድሽ አውቃለሁ ግን ፍቅር ብቻውን ትዳር አይገነባም>ያህን አባባሏን በውስጤ ደገምኩት።ፍቅር ብቻውን ትዳር አይገነባም።ምናልባት እውነት ነበር...ነገር ግን ዲህያን ከልቤ እንዴት አወጣዋለሁ?

በዚያ ቀን ሌሊት ላይ አልተኛሁም።የሲሀም ቃል እና የዲህያ ፊት በአእምሮዬ እየተፈራረቁ ነበር።
ስልኬን አነሳሁ።የዲህያን ቁጥር ከፈትኩ።መልዕክት መጻፍ ጀመርኩ።
<ዲህያ…> መፃፌን አቆምኩ።ሰረዝኩት።እንደገና ጻፍኩ።<እኔ እና አንተ..እጄ ተንቀጠቀጠ።ሀሳቤ ተበታተነ።መልዕክቱም ቀረ።ስልኩን ዘጋሁ።እንባዬ ወረደ።
<አላህ ሆይ… የእኔ ከሆነ የአዩብን ትዕግስት ስጠኝ የእኔ ካልሆነም የሀጀራን ፅናት አልብሰኝ>አልኩኝ በዱዖ።
በማግስቱ ከሰዓት ላይ ዲህያ ወደ ሱቅ መጣ።ዓይኖቼ እሱን ሲያዩ ልቤ ያለፈውን ሁሉንም ረሳ።
<ሰላም አለይኩም><ወዐለይከ ሰላም…>
ድምፄ ዝቅ አለ።ዲህያ ተመለከተኝ።
<ደህና ነሽ?>
<አዎ>
<እውነት?>ዝም አልኩ።እሱ ግን ፈገግ አለ።<ነገ ስመጣ አንድ ነገር እነግርሻለሁ ብዬሽ ነበር>ሰውነቴ ተንቀጠቀጠ።<ግን ዛሬ
ም አልነግርሽም>አለኝ በፈገግታ።
<ለምን?>አልኩት።
ወደ በሩ እየተመለከተ<ምክንያቱም ዛሬ በቅድሚያ አንድ ነገር ማወቅ እፈልጋለሁ>
<ምንድነው?>ወደ እኔ ተመለከተ።
<እኔ ባልመጣ… ትፈልጊኛለሽ?>ልቤ ፍርሀት ተላበሰ።ጥያቄውን ቀላል አድርጎ ቢጠይቀኝም፣መልሱ ግን ለእኔ ቀላል አልነበረም።
<አላውቅም…>
<እውነት አታውቂም?>
<አንድ ቀን ብትቀር…እጠብቅሃለሁ ሁለት ቀን ብትቀር…እጠይቅሀለው>ትንሽ ዝም አልኩና
<ግን ለረጅም ጊዜ ባትመጣ… አልረሳህም ምክኒያቱም እራሴን መዋሸት አልችልም አሁን… መምጣትህን መጠበቅ ልማዴ ሆኗል አንተ ካልመጣህ ጎዶሎነት ይሰማኛል>ዓይኖቼን ዝቅ አደረግኩ።
<መሩ አንቺን ገና አስረኛ ክፍል ስትማሪ ጀምሮ ነው የማውቅሽ ለጥንካሬሽ ጥርጥር የለኝም ትንሿን አንቺን ላለመረበሽ ስል እስክቀርብሽ አንቺም ይበልጥ እስክታድጊ ድረስ በትዕግስት ጠብቂያለሁ አሁን ላይ ግን ከምን ግዜም በላይ ትዕግስት አጥቻለሁ>አለኝ ለስለስ ባለ አነጋገር።ንግግሩ የፈጠረበት ስሜት ጥንቃቄን ሰለሚፈልግ ከመቀጠል ይልቅ ዝምታን መረጥኩ።

እንደ ነገው የመጣው ዲህያ<መሩ እኔ አንቺን ባገኘው እና በራቅኩኝ ቁጥር ፍቅርሽ እየጨመረ ትዕግስት አጣሁ የቤቱም ጉዳይ እንደምታውቂው ግዜ ወሰደብኝ ሳላይሽ መዋል ባልችል ሀራም ላይ መውደቅን ፈራሁ ሰለዚህ ቀለል ባለ ኒካህም ቢሆን አብረን እንሁን?>አለኝ።ይህን ሰላልጠበቅኩ ደነገጥኩ።የምለው እየተጠላለፈብኝ<ዲህያ እንደምትወደኝ አልተጠራጠርኩም እኔም ብሆን እንዳንተው ነኝ ግን...ድምፄ ተቋረጠ።<ፍቅራችን ተቻኮለ በዚህ ፍጥነት የሚወሰን ውሳኔ የህይወት ቀሪ እድሜ ነው ሰለዚህ ተራርቀን እንሞክረው>ይህን ስናገር የሲሀም ቃል በልቤ ውስጥ እንደ ጥላ ተከትሎኝ ነበር።“መርየም አንቺን እንደ ወንድሜ ሚስት አላይሽም"
ሰውን ከሕይወትህ ማራቅ ቀላል ሊሆን ይችላል።ከልብ እና ከሀሳብ ግን እንዴት? ዲህያ የሀሳቤን ንጉስ በምን ሰበብ ከዙፉኑ ላውርድ?
ዝም ብዬ ፊቱን ተመለከትኩት።በዓይኖቹ ውስጥ ያልተመለሰ ጥያቄ አለ።
<ዲህያ… እኔ አንተን መራቅ አልፈልግም እውነት ነው ግን አንተን ስለምወድህ እፈራለው>ይህን ስል የፊቱ ቀለም ተለወጠ።
<ስለምትወጂኝ ትፈሪያለሽ?>አለኝ ንዴት በቀላቀለ አነጋገር።
<አዎ አንዳንዴ ፍቅር ሰውን እስከ ሚያጠፋው ድረስ ያሰክራል እኔም ባለን ፍቅር እንዳንሳሳት እፈራለሁ..>ንግግሬን አቋረጠ።
<እኔ ኒካህ እንሰር ነው ያልኩት ቀን በቆጠረ ቁጥር እምነቴን እያጣሁ አንቺን ማግኘት ህልም እየሆነብኝ ነው...>እኔም ንግግሩን አቋረጥኩት።
<ኒካህን እየከለከልኩህ አይደለም በፍጥነት እንዳንወስን እና የዛሬ ስሜት ብቻ ሳይሆን የነገ እርግጠኝነት እንዲኖረን ሰለምፈልግ ነው>አልኩት።
<መሩ እኔ እኮ ለዛሬ አይደለም የፈለግኩሽ አሁን እሺ ካልሽኝ ሸርያዕ ፍርድ ቤት ሄደን ኒካህ እንሰር ሀላሌ ሁኚ ነው ያልኩት እስካሁን ያመንሽበት ፍቅር ላይ መጠራጠር እንዴት ጀመርሽ?...መሩ አላህን ፍሪ ፈተናዋቼ ብዙ ናቸው አንቺ እንኳን አቅልይልኝ>አለኝ በተማፅኖ ድምፅ።
እህቱ ሲሀም “መርየም፣ አንቺን እንደ ወንድሜ ሚስት አላይሽም’ ያለችኝ ቃል ከአእምሮዬ አልወጣ አለኝ።
<ዲህያ እኔ ወደ አንተ ስመጣ የእራሴን ልብ ብቻ ይዤ አልመጣም የቤተሰብህን ፍላጎት የአንተን ሰለም የነገህን ተስፋ እፈልጋለሁ>
<እኔ ግን አንቺን በፍርሃት ምክኒያት ማጣት አልፈልግም>ዓይኖቼ በእንባ ተሞሉ።<እኔም አንተን በፍቅር ምክንያት የነገህን ሰላም ማሳጣት አልፈልግም>
<መሩ ውሳኔሽን አከብራለሁ ግን ብዙ ግዜ አትወሰጂ..>ብሎኝ ዲህያ እንደተረበሸ ወጣ።

ሁለታችንም ፍቅርን አልካድንም። ነገር ግን ፍቅራችንን ለመጠበቅ ስንል ርቀትን መረጥን።አሁን ላይ ከትዳር እኩል ፍቺም ብዙ ነው።ሰዎች ትዳርን ሲጀምሩ የደስታውን ክፍል ብቻ ያስባሉ።የችግሩን፣ የመታገሱን እና አብሮ የመቆሙን ትርጉም ይረሳሉ።በትንሽ ንግግር ምክኒያት ልብን ይሰበራሉ ፣ በትንሽ ክርክር በር ይዘጋሉ፣ በመጨረሻም “ፍቺ” መፍትሔ ይሆናል።ትዳር ሁለት ፍጹም ያልሆኑ ሰዎች እርስ በእርስ ለመማር፣ ለመታገስ፣ ለመለወጥና አብረው ለመጠንከር የሚሞክሩበት ሕይወት ነው።ትዳር ለመጀመር ፍቅር ብቻ ሳይሆን፣ ትዕግስት፣ መረዳዳት፣ ይቅርታ እና አላህን መፍራት ያፈልጋል።ሰዎች ለመጋባት ብዙ ሕልም እና ቁሳቁስ ይሰንቃሉ ግን ትዳርን ለመጠበቅ የሚያስፈልገውን ትዕግስት፣ መረዳዳትና መስዋዕትነት አይዘጋጁበትም።በትንሽ አለመግባባት ትልቅ ያሳለፉትን ድንቅ ግዝያት ይጥላሉ።ችግሩ ፍቅር መጥፋቱ አልነበረም፤ ፍቅርን መሸከም የሚችል ልብ መጥፋቱ ነው።ምክንያቱም መውደድ ቀላል ነው፤ነገር ግን ሰውን በስህተቱ ጊዜ መረዳት፣በችግሩ ጊዜ አለመሸሽ፣እና በተጣላህ ጊዜ እንኳን በጥበብ መነጋገር ያ ነው እውነተኛ ፍቅር።

ትዳር መወዳ እንዳለበት ሁሉ ፈተና ነው።ሁለቱም አላህን ፈርተው፣ እርስ በእርሳቸው በርኅራኄ ከተያያዙ፣የተሰበረውን ነገር እንደገና መጠገን ይችላሉ።ምክንያቱም ጥሩ ትዳር ማለት ፈጽሞ የማይጣሉ ሁለት ሰዎች አይደለም፤ከተጣሉ በኋላ እንዴት ወደ እርቅ እንደሚመለሱ የሚያውቁበት ሁለት ሰዎች ናቸው።

ዲህያን ለመራቅ ሞከርኩ ግን አልቻልኩም።ሰውን ከፊት ማራቅ ይቻል ይሆናል፤ከአይንም ማጥፋት እንደዛው ግን አንድን ሰው ከልብህ ለማስወጣት
ምን ያህል ርቀት ያስፈልጋል? እኔ አላውቅም ነበር።የማውቀው አንድ ነገር ቢኖር ዲህያን ከፊቴ እንጂ ከልቤ ማራቅ አልቻልኩም።

በሌላ ቀን ሲመጣ እንዳላየሁት በመሆን ሱቅ ውስጥ ያሉትን እቃዎች እያስተካከልኩ ቆየሁ።
<ሰላም አለይኪ><ወዐለይከ ሰላም>
እሱ ለጥቂት ሰከንዶች ዝም አለ።
<ደህና ነሽ?> አለ።<አዎ።>በአጭሩ
<እርግጠኛ ነሽ?><አዎ>በድጋሚ።
ሁለተኛ ጊዜ አልጠየቀኝም።ብቻ ተመለከተኝ።እይታው ግን ከየትኛውም ጥያቄ የበለጠ ተመራማሪ ነበር።
<የምታወሪኝ ቃል ሌላ አይንሽ የሚለኝ ሌላ>ልቤ በፍጥነት መታ።ዓይኔን ዝቅ አደረግኩ።
<ምንም የለም ዲህያ>አልኩት።
<እኔን ለመራቅ እየሞከርሽ ነው?>አለኝ። ዳግም ዝም አልኩ።ዝምታዬም መልስ ሆነ።
<እሺ ብቻ አንቺ እስክትወስኚ ድረስ አልጠይቅሽም>ወደ በሩ ሄደ።
ከመውጣቱ በፊት ቆሞ<ግን አንድ ነገር እወቂ...ወደ እኔ ተመለከተ<...ከእኔ መራቅ ከፈለግሽ አልከለክልሽም ግን ምክንያቱን ሳላውቅ ልቤን ማሳመን አልችልም>ትንሽ እንኳን ሳይቆይ ጥሎ ወጣ።
ዲህያ ከሱቁ ከወጣ በኋላ ወንበሩ ላይ ተቀምጬ ቀረሁ።እንባዬ በዝምታ ወረደ።እሱን እየጎዳሁት ነው?እራሴን ጠየቅኩ።ነገር ግን የሲሀም ንግግር አልተረሳኝም።እኔ ወላጅ የሌለኝ ልጅ ነኝ።እሱ ደግሞ ቤተሰብ አለው።
ምናልባት የእኔ ወደ እሱ ሕይወት መግባት ለእሱ ደስታ ሳይሆን ጭንቀት ይሆን?። ፍቅር አንድ ሰውን ማግኘት ብቻም ሳይሆን እሱን ከእራስ ጥፋት መጠበቅም ነው።
ሁለት ቀናት ዲህያን አላየሁትም።ዝምም እንዳለ ቀጠለ።እንዲመጣ እጠብቀው ነበር።ግን ከዛን ቀን ወዲህ አልመጣም ነበር።

ይቀጥላል
@buntsumi
🔥4
ቀሪ ገፅ
[ሱሚ ማማይ]
ክፍል ሀያ
****

ሰውን መውደድ ማለት ማሳደድ አይደለም። አንዳንዴ የእሱን ሰላም ብቻ መመኘት ይሆናል።
<ከእኔ መራቅ ከፈለግሽ እኔ አልከለክልሽም ግን ምክኒያቱን ሳላውቅ ልቤን ማሳመን አልችልም>ያለኝ ቃል በልቤ ውስጥ ደጋግሞ ይሰማኝ ጀመር።ምን ሆኖ ነው? የልቤ አንድ ክፍል <ይመጣል ጠብቂው>ይለኛል።ሌላኛው ግማሽ ልቤ ግን በተደጋጋሚ ሰለ እሱ እንዳላስብ ይፈልጋል።እሱን ከማግኘቴ በፊት የነበረኝን መረጋጋት የት እንደጠፋ አላውቅም።ዲህያ ሕይወቴ ውስጥ ገና አልገባም ብዬ ሳስብ፣ልቤ ግን ለእሱ ያለጥርጥር ትልቅ ቦታ ሰጥቶታል።ሌሊቱን ሙሉ አልተኛሁም።ከአልጋዬ ላይ ተነስቼ ውሃ ጠጣሁ። ከዚያም ወደ መስኮቱ ቀረብኩ።ከተማው በለሊት ጸጥ ብሏል።እኔ ግን ከውስጤ ጋር ጦርነት ላይ ነበርኩ።
“አላህ ሆይ…”እጆቼን አነሳሁ።
<እሱ ለእኔ ከሆነ መንገዱን አመቻችልኝ ካልሆነ ደግሞ ልቤን ከእሱ ጠብቅልኝ>ዱዕዬ ይህ ብቻ ነበር።ምክንያቱም ዲህያ እራሱን ለሌላ ሰው በፍጥነት የሚሰጥ ባለ ስስ ልብ ነው። እኔ ደግሞ በዚህ ምክኒያት እንዳይጎዳ እፈራለሁ።ቀኑ እየገፋ ሄደ።ዲህያ ግን ወደ ሱቁ አልመጣም።እያንዳንዱን የሞተር ድምፅ ስሰማ ልቤ በጉጉት ይዘላል።ድምፁ የእሱ እንዳልነበር እንዳወቅኩኝ አካሌ ላይ ከባድ ነገር እንዳረፈ ያክል ይሰብረኛል።አመሻሽ አከባቢ ግን ዲህያ ወደ ሱቅ መጣ።
<ሰላም አለይኩም>
<ወዐለይከ ሰላም>
ናፍቆቱ አይኑን በማየት ብቻ አልበርድ አለልኝ።ዘልዬ ማቀፍ ተመኘው።ግን እግሮቼ አልተንቀሳቀሱም።ልቤ ግን ያለሀፍረት በሀሳብ ወደ እሱ ሮጦ ተጠመጠመ።ውስጤ ላይ ያለው ናፍቆት አይኑን ሳይ አቁነጠነጠኝ።በሀፍረት አይኔን ከእሱ ላይ አንስቼ ቆምኩኝ።
እሱ እንደተለመደው ፈገግ አለ።እኔ ይህን ፈገግታ ለአምስት ቀናት እንደናፈቅኩት አውቃለሁ።ግን ደፍሬ ቀና ብዬ እንዴት ልየው!።ብርታት አሳጣኛል።
<እንዴት ነሽ?>
<ደህና ነኝ።>ውሸት ነበር።እሱ በቀረበት ደህና አልነበርኩም።
<እንዴት አለፈ አምስቱ ቀናት?>
<በጣም ፈጥኖ>እንደገና ውሸት ነበር።እነዚያ አምስት ቀናት ለእኔ እንደ አምስት ወራት ነበሩ።
<እኔ ግን ናፍቀሽኛል>ይህን ቃል መስማት ፅናቴን አንቀጠቀጠው።
<እኔም እንደዚሁ>አልኩት።በናፍቆት የደማው አይኔን ከእሱ ለመሸሸግ እየሞከርኩ።
<እንደዚሁ ምን?>
<ናፍቀሀኛል>ተሽኮረመምኩ።በእጄ የአፌን መወላገድ ሸፈንኩት።
እሱም በሁኔታዬ ፈገግ አለ።እኔ ግን ዓይኖቼን ወደ ሌላ ቦታ አሸሸው።ምክንያቱም አይኑ መሀል አቅም ያንሰኛል።ናፍቆት ለካ ያሳሳል።
<መራራቁን የመረጥሽው አንቺው ሰለሆንሽ እንጂ እኔ ችየው አይደለም ግን አንዳንድ ርቀት ከመጠፋፋት ይልቅ ናፍቆት ያስተምራል>
እሱ ፈገግ አለ። እኔ ግን የመቀጠል እና ብዙ የመናገር አቅም አጣው።በእጁ በዶሲ የታሸገ ነገር ይዞል።
<ይሄ ምንድነው?>አልኩት።
<የቤት ፍቃድ ነው>
<ቤት?>በጥርጣሬ አየውሁት።
<የእኛ ቤት>አለ በፈገግታ።
<እየጨረስክ ነው?>
<በጣም እንደተቸገርኩ ነግሬሽ ነበር አሁን ግን ለመጨረስ ተስፋ አለኝ>
ከዚያም ትንሽ ዝም ብሎ እየቀጠለ<አንዳንድ ቤቶች በብሎኬት ብቻ አይገነቡም>አለኝ።
<ታዲያ በምን ይገነባሉ>አልኩት።መልሱን ለመስማት በመፈለግ ።
እሱም መልሶ <በኒያ>አለኝ።ንግግሩ ውስጤን ነካው።እሱ ግን ሌላ ነገር ሳይል ተሰናብቶኝ ወጣ።ያን ቀን ለሊት የዲህያን ቃል ሳስብ አንድ ነገር ተረዳሁ።ግልፅ ሆኖ ባይገባኝም እሱ ስለ ቤት ብቻ እያወራ አልነበረም።

በቀጣዮቹ ቀናት ዲህያ በየጊዜው ይመጣ ጀመር።አንዳንድ ጊዜ ለአምስት ደቂቃ።አንዳንድ ጊዜ ለአስር።አንዳንድ ቀን ደግሞ ሳይናገር ብቻ ሰላም ብሎኝ ይሄዳል።እኔ ግን በየቀኑ የበለጠ እየተለማመድኩት ነበር።የእሱን ድምፅ።የእሱን ፈገግታ።የሚመጣበትን ጊዜ።እንዲያውም የሞተሩን ድምፅ ከሩቅ ስሰማ የዲህያ መሆኑን መለየት ጀምርያለሁ።ይህን ስረዳ ግን ፈራሁ።
ሰውን መልመድ ምን ያህል አደገኛ ነው?ምክንያቱም…ከእሱ ጋር የማይጠፉ ቀሪ የሆኑ የማይረሱ ትዝታዋች አሉ።

አንድ ቀን ዲህያ ሱቁ በር ላይ ቆሞ ነበር።
<መርየም አንቺን እንደምወድሽ ለመናገር አልፈራም የምፈራው አላህ እኔን ለአንቺ ካልጻፈኝ እንዴት ከልቤ ጋር መስማማት እንደምችል ነው>አለኝ።የውስጡ ስሜት አይኑ ላይ እየተነበበ።
እኔም በተራዬ <እኔም አንተን ማግኘት ብቻ አይደለም የምፈልገው… ከአንተ ጋር ስሆን የምሆነውን እኔነቴን ይበልጥ እወደዋለው>አልኩት ውስጤ ያለው ፍቅር ልቤን እያቃጠለው።ሁለታችንም ለደቂቃ ተያየን።በአይናችን ብዙ አወራን።ከቃላችን በላይ አይናችን ድፍረት ነበረው።አይናችን ለመናገር የደበቀው ስሜት፣ለማንበብ የቆጠበው ቋንቋ አልነበረውም።ያን ጊዜ ሀፍረት የገባውን አይኔን ለመሸሸግ ስሞክር ይዞት የነበረውን ትንሽ ወረቀት እኔ ጋር ማስቀመጡን አየሁ ።
<ይሄን ረስተህ ነው?>
<አይ ለአንቺ ነው>
<ምንድነው?>
<ክፈቺው>
ከፈትኩት። ውስጡ ትንሽ የብሎኬት ቁራጭ ነበር።አስቂኝ መስሎኝ ፈገግ አልኩ።
<ይሄን ለምን ሰጠኸኝ?>
<አንድ ቀን ቤቱ ሲጠናቀቅ… የመጀመሪያው ብሎኬት የት እንደነበረ እንድታውቂ>
<እና እኔ ምን አደርገዋለሁ?>
እሱም ፈገግ ብሎ<ጠብቂው>አለኝ።የሰጠኝ የቃል አደራ ከብሎኬቱ በላይ ከባድ ነበር።<ጠብቂው>
<ዲህዩ…ቤቱ ካልተጠናቀቀስ?>
ለጥቂት ጊዜ ዝም አለ።
<በአላህ ውሳኔ ጣልቃ አይገባም>
ከዚያም እሱ ለመሄድ ተዘጋጀ። እኔም በድንገት<ዲህዩ…>ወደ እኔ ዞሮ ተመለከተኝ።<ነገ ስትመጣ…ምሳ አብረን አንበላም?>አልኩት።ፈገግ አለ።
<እሺ እኔም ነገ አንድ ነገር እነግርሻለሁ>
<ምንድነው?>
<ነገ ትሰሚዋለሽ>
<አሁን ንገረኝ>
<አንዳንድ ነገር ለነገ ማቆየት ያምራል>ከዛም ጥሎ ሄደ።እኔ ግን በቦታዬ ቆሜ ቀረሁ።በእጄ ያለውን ትንሽ ብሎኬት እያየሁ፣ እንደ ልጅ በጥንቃቄ ወደ ልብሴ ኪስ አስገባሁት።
ያን ቀን ተረዳሁ።ፍቅር ሁልጊዜ አበባ አይደለም።አንዳንዴ ትንሽ ብሎኬት፣አንዳንዴ ጉርሻ፣አንዳንዴ ደግሞ “ነገ እመጣለሁ” የሚል ቃል ነው።
እኔ ግን …ያ “ነገ” ምን ያህል ሩቅ እንደሆነ እና ከምጠብቀው በላይ ምን እንደሚያመጣብኝ አላውቅም ነበር።ከሁሉ በላይ አንድ ቀን ያንን ትንሽ ብሎኬት እያየሁ፣ዲህያን እንደማስታውስ አላውቅም ነበር።
“አንዳንድ ነገር ለነገ ማቆየት ያምራል…”
ሆኖም አንዳንድ “ነገዎች” ፈጽሞ ላይመጡ ይችላሉ። ዲህያ ከሱቁ ሲወጣ የሄደበትን አቅጣጫ ተመለከትኩ። እሱ ሲርቅ የሞተሩ ድምፅ ቀስ በቀስ ጠፋ።ያን ጊዜ ግን አልፈራሁም ነበር።ምክንያቱም ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅር ማለት አንድን ሰው በአጠገብህ ማየት ብቻ እንዳልሆነ ተረድቻለሁ።
ፍቅር ማለት…እሱ ከአንተ ጋር ቢቆይ መደሰት፣ቢርቅ መልካም ነገር ሁሉ መመኘት፣አላህ ከፈቀደ ደግሞ እንደማያሳጣኝ ማመን ነው።

ወደ አመሻሽ አከባቢ የልቤ መረጋጋት እንደገና ተሰርቀ።ያን ሌሊት እንደገና እጆቼን ወደ ሰማይ አነሳሁ።“አላህ ሆይ… ዲህያን ለእኔ ከፃፍከው ፍቅራችንን ወደ ሀላል አድርሰው ካልፃፍከው ደግሞ… እሱን ሳላጣ ከልቤ እንድለቀው አስተምረኝ።”ይህን ዱዕ ደጋገምኩት።ፈራሁ! ይህ ምሽት ለእኔ እንደሌሎቹ ምሽቶች አልነበረም።ቤቱ ጸጥ ብሏል።ከመስኮቱ ወደውስጥ የሌሊት ንፋስ ቀስ ብሎ ይነፍስ ነበር።ከዚህ በፊት ያላስተዋልኩት ነገር ዛሬ ቁልጭ ብሎ መንፈሴን መቆጣጠር ጀመረ።ተደራራቢ አልጋ ላይ ሆኜ የዲህያን የቆየ መልዕክት ደግሜ ማንበብ ጀመርኩ።
“አንድ ቀን አላህ ፈቅዶ የጋራ አላማ የጋራ ህይወት ይኖረናል..”
እሱን ሳስብ ሰላም እና ረብሻ አንድ ላይ ይሰማኛል።ከእሱ ጋር ስለሚኖረኝ ህይወት፣ ስለሚኖሩን ልጆች፣ ስለምናወራው ትንንሽ ነገሮች እያሰብኩ ደስ አለኝ።
ልቤ አከባቢ ክብደት ተሰማኝ በአንድ እጄ ደረቴን አጥብቄ ያዝኩት።ለመጀመሪያ ጊዜ ከእሱ ጋር ስለነበረኝ ንግግር፣ እሱ ሲስቅ ሰለሚታየኝ የሚያምር ፊት፣የሚናገራቸውን ትንንሽ ቃላት እያሰብኩ ነበር።
ዲህያ እና መርየም ያሳለፉት ብዙ ነገር አልነበራቸውም።ነገር ግን ብዙ “አንድ ቀን” ነበራቸው።
አንድ ቀን ኒካህ።አንድ ቀን የራሳቸው ቤት።አንድ ቀን አብረው ሶላት።አንድ ቀን “ባለቤቴ” ተባብለው የሚጠራሩበት።አንድ ቀን አንድ መኝታ ሚጋሩበት።አንድ ቀን.....

እነዚህ ሁሉ ግን የሚመጡ ቀናት ነበሩ? አያውቁትም።

የህልም ፈረስ እየጋለበ ምሽቱ ተገባዶ መርየም ወደ ስራዋ ገባች።ሱቁን ሳይሆን<ነገ ስመጣ> ያላትን ካሊድ እየጠበቀች ነበር።ጣፉጭ ምግብ በምሳቃዋ እንደያዘች ምሳዋን ሳትበላ እሱን ስጠብቅ የሚመጣበት ሰዕት አለፈ።ስልኳን በየደቂቃው ትመለከተች።
“ምናልባት እየመጣ ይሆናል…”
“ምናልባት ስራ በዝቶበታል…”
“ምናልባት ትንሽ ቆይቶ ይመጣል…”
ልቧ ምክንያት እየፈጠረ ነው።በዚህ መሀል ስልኳ ጠራ።ሲሀም ነበረች።ግር ባለ ስሜት አነሳችው።
“ሄሎ?”
<ዲ.ዲ...ያያ...አ..አአኩ

የተሰበረ እና የሚቆራረጥ ድምፅ።

ይቀጥላል...
@bintsumi
❤2
ቀሪ ገፅ
[ሱሚ ማማይ]
ክፍል ሀያ አንድ
****

ከስልኩ ውስጥ የሚሰማት ድምፅ የተበታተነ እና የተቆራረጠ ነበር።በመሀል ግን መርየም ልቧን ቀጥ ያደረገ መልዕክት ሰማች።<ዲህያ.?? ዲህ... ያያያ የሞተር አደጋ ....ሞተብኝ ሞተብኝ>የሚል በሳግ የታጀበ ድምፅ።መርየም የያዘችው ስልክ ከእጇ ሊያመልጣት ተንቀጠቀጠ።
«ምን?… ምን አልሽ?»አለች።
«ሲሃም! ምን አልሽ?!»ከስልኩ ውስጥ የሚሰማው ለቅሶ ብቻ ነበር።መርየም በዝምታ ቆመች።እሱን ወደእሷ የሚያደርሰው ሞተር ዛሬ ወደእሷ አልተጓዘም።ዲህያን ወደፈጠረው ወደማይቀረው ወደ አላህ ዘንድ ላይመልሰው አደረሰው።
ዲህዩ…«አይ…»ቀስ ብላ ተናገረች።
«ነገ እመጣለሁ ብሎኝ ሊሄድ አይችልም
ምሳ እየጠበቅኩት?..አይ ሲሀም ዋሸችኝ..?እንዴት በዲህያ ትቀልዳለች>ላለማመን ታገለች።

የመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ፣የእሱ ስሜት አልባ ፊት፣የእሷ በሀፍረት መሸማቀቅ…«አንድ ቀን እኔ እና አንቺ እንጋባለን»ሁሉም በልቧ ውስጥ እንደ ስዕል ተደጋገመ።መርየም እጇን በደረቷ ላይ አደረገች።እንባዋ ወረደ።
“ዲህያ ሞቷል…”
ዓለም ቆመች።አንድ ደቂቃ።ሁለት ሰከንድ።ሦስት…
“አይ… አይ… አይ…”ስልኩ ከእጇ ወደቀ።
“ዲህያ…”
ስሙን ስትጠራው የሚመልስላት ድምፅ እንደማይኖር ማመን አልቻለችም።የልቧ ምት ተበታተነ። በዚያ ቅጽበት የሞተው ዲህያ ብቻ አልነበረም፤ እሷ ከእሱ ጋር ያሰበችው ነገር ሁሉ አብሮት ተሸኘ።
አንድ ቀን እንዲመጣ የጠበቀችው ፍቅር፣አንድ ቀን እንዲሰማት የጠበቀችው የእሱ ደስታ፣አንድ ቀን እንዲያያት የጠበቀችው ቆንጆ መልኩ።
ሁሉም ነገር በአንድ ዜና ውስጥ ቀረ።

“አላህ ሆይ…”እጆቿን ወደ ፊቷ አነሳች።“አላህ ሆይ… እባክህ… ህልም ይሁን…”እንባዋ ጉንጫን ተንተርሶ ፈሰሰ።ነገር ግን ህልም ሳይሆን መራር እውነታ ነበር።
“ገና ብዙ እቅድ ነበረን…”
የምንወደው ሰው የቱንም ያህል እድሜ ምድር ላይ ቢቆይ በቂ አይደለም።መርየም የዲህያ ስልክ ላይ ደወለች።
አንድ ጊዜ።
ሁለት ጊዜ።
ሦስት ጊዜ…
“ጥሪ አይቀበልም…”እሱ የአምላኩን ጥሪ ተቀብሏል።ስልኩን ደረቷ ላይ ለጠፈች።

“መቼ ተሰናበትኩህ…”እንባዋ እየወረደ ነበር።

“እንዴት ሄድክ? ምን ተሰምቶህ ይሁን? አመመክ?”
አንዳንድ ሰዎች ከሕይወታችን ሲሄዱ የከፈቱትን በር አይዘጉም።ልብን እርቃን ያደርጋሉ።ትዝታቸው ላይ ወደሃላ ያስቀራሉ።አንድ እርምጃ ያለትዝታ ወደፊት መጓዝ ይነፍጋሉ።
<ዲህያ የእኔ ውድ የእኔ ስስ ልብ.. ሞተህ እንኳን አትርቀኝም ግን ከአንተ ጋር የሚኖረኝን ነገር ሁሉ ይዘህ ሄድክብኝ።አላህ ሆይ… እኔ እንዴት ልኑር እሱን ሳላይ? እንዴት ልስቅ እሱን ሳልሰማ? እንዴት ልጠብቅ እሱ እንደማይመጣ እያወቅኩ?
«አላህ…»ድምፇ ተሰበረ።«እኔ ምን አደርጋለሁ?»እንባዋ በጉንጮቿ ላይ ወረዱ።«እውነት ከሆነ እሱን እንዴት ችዬ እረሳዋለሁ?»ለጥቂት ሰከንዶች ዝም አለች።
«አላህ እሱን የሰጠሀኝ አንተ ነህ… ከእኔ የምትወስደውም አንተ ነህ።»

አንዳንድ ፍቅሮች በጥላቻ አይፈርሱም።በክህደትም አይጠናቀቁም።አንዳንዶቹ በ«እወድሻለሁ» እና «እወድሃለሁ» መሀል ብቻ ይቆማሉ።ሞት አንዱን ይወስዳል።ሌላውን ደግሞ በትዝታ ውስጥ እንዲኖር ይፈርድበታል።
«ምን ልትነግረኝ ነበር?»እንባዋ እንደገና መጣ።«ለምን ነገን ጠበቅክ… ፍቅርህ በድንገት እንደሚቋረጥ ብታውቅ ኖሮ… የምንችለውን ሁሉ እንኖር ነበር እኔ ግን ዛሬም እዚህ ነኝ አንተ ግን…»ቃሏ ተቋረጠ።ሞቱን ለማመን ሬሳውን ቤት ድረስ ሄዳ አየች።
ልቦ እንደተረበሸ አቅሟን ሰብስባ ቀረብ ብላ ፊቱን ተመለከተች።ፊቱ በደረሰበት አደጋ ተቦጫጭሮ በተለያየ ቦታ መስመር የሰራው ቁስል መልኩን አጥፍቶታል።
ግን እሱ ነበር።የምታውቀው ፊት።የምትናፍቀው ፈገግታ።
ግን አሁን… ለመጨረሻ ግዜ በድን ሆኗል።እንደማይቻል እያወቀች እጇን በቀስታ ወደ እጁ ዘረጋች።ቀዝቃዛ ነበር።የእሱ ቅዝቃዜ ነፍሷን አንቀጠቀጠው።መርየም መቆም አቅቷት እራሷን ሳተች።
ቀብረው የተመለሱትን ሰዋች የውዱ ነብይ ልጅ እንደ ሆነችው ፋጢማ<እንዴት ቻላቹበት የአላህን መልእክተኛ ﷺ ላይ አፈር መመለስ እንዴት አስቻላችሁ?>እንዳለችው እሷም መጠየቅ አሰኛት።ሀዘኗን በትዕግስት እንደዋጠች ለመጨረሻ ግዜ እሱን የሚያስታውሳትን ሁሉ ጥላ ራቀች።

ከዲህያ ሞት በኋላ መርየም ቀስ በቀስ ተለወጠች።በየቀኑ የሱን ስም በማስታወሻዋ ላይ ትጽፍ ነበር።አንድ ቀን ግን አንዱ ገፅ ላይ እንዲህ ጻፈች
“ዲህያ ከሄደ በኋላ ሞትን አልፈራም።የምፈራው እሱን ሳልረሳ መኖር ነው።”ወራት አለፉ።የእራሷን ስሜት ማዳመጥ የዘነጋችው መርየም ህመሟ በሰውነቷ ውስጥ በጸጥታ እየጨመረ ነበር።በዲህያ ሰበብ የተጀመረ ማስታወሻዋ በዲህያ ስም ሸበረቀ።
ውድ ዲህያ…
ዛሬ ስምህን ስጽፍ እጄ ይንቀጠቀጣል።ምክንያቱም ከአሁን በኋላ ስምህን መጥራት እንጂ መልስህን መስማት አልችልም።
ሰዎች ሞት ሰውን ከህይወት ላይ እንደሚያስወግድ ይናገራሉ።እኔ ግን አልስማማም።አንተ ከህይወቴ አልወጣህም።ዛሬም ድረስ እየተነፈስክ ነው።ዛሬም ስልኬን ስከፍት ስምህን እፈልጋለሁ።
“ዲህያ ይደውላል…” ብዬ እጠብቃለሁ።አንተን የወደድኩት ስለነበርክ ብቻ አይደለም።ከአንተ ጋር ያለሁትን እኔን ስለምወደው ነው።ሙሉ አንተነትህን ወድጅያለሁ።ጉድለቶችህንም፣ ዝምታህንም፣ ትንሽ ቁጣህንም።አንተ የእኔ ምርጫ ነበርክ፣ ዲህያ።እና ምንም እንኳን እጣ ፈንታችን አንድ ላይ ባይቆይም፣የነበረንን ፍቅር በልቤ እንደ ሚስጢር እጠብቀዋለው።አንድ ቀን አንተን እንደምረሳ ሰዎች ሊነግሩኝ ይችላሉ።እኔ ግን አልፈልግም።ምክንያቱም አንተን መርሳት ማለት
ከህይወቴ አንድ ውብ ገፅ መቅደድ ማለት ነው።ስለዚህ አልረሳህም።
እኔ እስካለሁ ድረስ በዚህ ማስታወሻ ውስጥ ትኖራለህ።እና አንድ ቀን…አላህ ከፈቀደ…እንደገና እንገናኛለን።ማስታወሻዋ ላይ በምህፃረ ቃል ታጥረው በተናጥል የተፃፉ የፍቅር ቃላቶች ብዙ ናቸው።
"ዛሬ አንተን ሳስብ አልተኛሁም።
አንተን ማሰብ ለእኔ ትዝታ አይደለም፤ ልማዴ ሆኗል።”
“አንድ ጊዜ ደውለህ ‘ደህና ነሽ?’ እንድትለኝ ብቻ እፈልጋለሁ።እኔም ‘አዎ’ ብዬ እዋሽሀለሁ።ምክንያቱም አንተ ከሌለህ ደህና አይደለሁም።”
“በህይወቴ ውስጥ እንደመጣህ ሳስብ አላህን አመሰግናለሁ።ለምን እንደወሰደህ ግን አላውቅም።ምናልባት እኔ የማላውቀው ምክንያት አለው።ስለዚህ እያለቀስኩም ቢሆን ‘አላህ ሆይ፣ አመሰግንሃለሁ እላለሁ።’”
“አንተን መውደድ በህይወቴ ውስጥ የተሰጠኝ በጣም ውብ ስጦታ ነበር።
አንተን ማጣት ደግሞ በጣም ከባዱ ፈተናዬ ሆነ።”
ዲህያ…ከአንተ ጋር የነበሩትን ትንንሽ ነገሮች እንኳን ናፍቃለሁ።
“ደህና ነሽ?” የምትለኝን።“ተጠንቀቂ” የምትለኝን።ስሜን የምትጠራውን።እኔ ስበሳጭ የምታስቀኝን።ሳልናገር የምትረዳኝን።እነዚህ ለሌላ ሰው ትንሽ ነገሮች ናቸው።ለእኔ ግን…እነዚህ አንተ ነህ።
“እሱ ከእኔ ጋር ሲሆን ዓለም ትንሽ ትመስለኝ ነበር፤ እሱ ሲርቅ ግን ዓለም በጣም ትልቅ ሆና እኔን ብቻዬን ትታኛለች።”
ምናልባት የእኛ ፍቅር የዚህ ዓለም ታሪክ ብቻ አይደለም።ምናልባት ይህ ዓለም የመጀመሪያው ገፅ ብቻ ነው።እና እኔ የምመኘው ቀጣዩ ገፅ አንተ ያለህበት እንዲሆን ነው።አሁን
አንተን ስናፍቅ ሰማይን እመለከታለሁ።“እዚያ ነው?” ብዬ አልጠይቅም።አላህ ብቻ ያውቃል።
“አላህ ሆይ፣ እሱን በምሕረትህ ክበበው።እሱን ከምትወዳቸው ባሮችህ አድርገው።የመጨረሻ ቦታውን ውብ አድርግለት።እኔም ከዚህ ጠፊ አለም በኋላ ዳግም ከእሱ ጋር እንደምታገናኘኝ ተስፋ አደርጋለሁ።”
“አንድ ጊዜ እንዲህ ብዬ አስብ ነበር‘ዲህያ ከእኔ ጋር ቢሆን ምን ያህል ደስ ይለኝ ነበር?’አሁን ግን ጥያቄዬ ተቀይሯል‘ዲህያ አላህ ዘንድ ደስተኛ ይሆን?’ምክንያቱም እውነተኛ ፍቅር የምትወደውን ሰው ለራስህ ብቻ አትመኝም።ለእሱ የሚደረግለትን ምርጥ ነገር ትመኛለህ።
“አንድ ቀን ጀነት ውስጥ እንደገና ካየውህ…ምናልባት መጀመሪያ ምንም አልልም።ረጅም ጊዜ እመለከትሃለሁ።ምክንያቱም በዚህ ዓለም ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ስትሄድ በደንብ ሳላይህ ቀርቻለሁ።
ዲህያ…ምናልባት በጀነት ውስጥ ውብ የሆኑ ሁረል ዕይን ይኖራሉ።እኔ ግን በዚህ ዓለም ላይ ስለአንተ ስቀና እንደነበረው እዚያም ልቤ ትንሽ ቅናት ሊሰማው ይችላል።
“እውነት ግን ልንገርህ?
አንተን በጀነት ማሰብ ከእኔ የማይለይ ትዝታ ሆኗል።ስለአንተ ስጨነቅ ወደ ዱዓ እሮጣለሁ።ስናፍቅህ ወደ ሰማይ እመለከታለሁ።ስፈልግህ ሰደቃን አበዛለሁ።እና አንተ ጀነት እንደምትሆን ሳስብ፣ አንድ የማልፈልገው ጥያቄ ይመጣል፦
“ዲህያ… እዚያ ሌሎች ሴቶች አይኖሩም?”
በሀያእ ለተሰበሩ አይኖችህ አላህዬ ገላቸው እንደመስታወት የነጡትን የልብሳቸው መዕዛ ምድር ላይ ቢወድቅ ሽታው ከምድር ጫፍ እስከ ጫፍ የሚያዳርስ ሁረል አይኖችን እንዳይሰጥህ ቀናለሁ።
የጀነት ፀጋዋ እኔን እንዳያስረሳህ ፈራለሁ።እኔም ከሞት በሃላ አንተን እንጂ ሌላ የምጠይቀው የለኝም።
ቀብር ውስጥ ከአንተ ቀጥሎ ወደ ሞት ለሚመጣ ሁሉ ጥያቄ እንደምታቀርብ በወይህ የሚታገዙት ረሱል (ሰዐወ) ቀድመው ተናግረዋል።ምን አልባት ሰለ እኔ ከተጠየቅክ ወደ አንተ እስክመጣ ድረስ ጀነትህን እየገነባው ነው።

ዛሬ ህመሜ ከምችለው በላይ ሆኖብኛል።ለረጅም ጊዜ ከአላህ ጋር ብቻዬን መቆም እንደምችል አምኜ ኖርያለሁ።ነገር ግን ዛሬ… አልቻልኩም።
ሰው ሲታመም መድሀኒት ብቻ አይፈልግም።“አትፍሪ፣ እኔ አለሁ” የሚለውን ድምፅ ይፈልጋል።ዛሬ ያንን ድምፅ ፈለግኩኝ።
የእናትን እጅ ፣የአባቴን ደረት፣የወንድም ከለላ ፈለግኩ።የእህት ጨዋታ ፈለግኩኝ።“እኔ አለሁልሽ” የሚለኝን ሰው ፈለግኩኝ።እኔ ቤተሰብ አልናፈቀኝም ብዬ እራሴን ለዓመታት አታልዬ ነበር።
አላህ ሆይ…
ምንም እንኳን በሰው መሀል ዱንያ ውስጥ ብቻዬን ብሆን፣በአንተ ፊት ግን ብቻዬን እንዳልቀር አደራ።

ማስታወሻዋ በመሰል የሰማይ ቤት ናፍቆት ደብዳቤ ተሞልቷል።ሚሻል ያለ እረፍት ማስታወሻዋን እያነበበ ቀጠለ።

ከቀን ወደ ቀን እየደከምኩ ነው።አንዳንድ ቀን ከአልጋዬ መነሳት እንኳን ይከብደኛል።አንድ ቀን ህመሜ በጣም በረታ።እስትንፋሴ ከበደኝ።እጆዋቼ ተንቀጠቀጡ።እንባዬ በጸጥታ ወረደ።በዚያ ቅጽበት ሞትን አስቤ ነበር።ነገር ግን የሞት ሐሳብ ብቻ አላስፈራኝም።ያስፈራኝ

‘ዲህያን እንደገና አገኘዋለሁ?’

ይቀጥላል..
@bintsumi
❤6😭1
ቀሪ ገፅ
[ሱሚ ማማይ]
ክፍል ሀያ ሁለት
*******

ዲህያ ከሞተበት ቀን ጀምሮ መርየም የምትኖረው ህይወት ቀስ በቀስ ወደ ትዝታ ተቀየረ።ለፈጅር ስትነሳ የመጀመሪያ ሐሳቧ ዲህያ ነበር፤ ሌሊት ዓይኖቿን ስትዘጋም የመጨረሻው ሐሳቧ እሱ ነበር።ህመሟ ይበልጥ በለሊት ይብሳል።ስራዋን ያቋረጠችው መርየም ቀን ላይ ከሰዎች ጋር በፈገግታ ማሳለፍ ትችላለች፤ ሌሊት ግን እራሷን ማታለል አትችልም። በአልጋዋ ላይ ተኝታ ጨለማውን ትመለከታለች።እንቅልፍ ከወሰደኝ ብላ ዓይኖቿን ትዘጋለች፤ ነገር ግን የዲህያ መልክ በሐሳቧ እየመጣ ያጫውታታል።ንግግሩ፣ፈገግታው፣እሷን የሚያይበት መንገድ… እያንዳንዱ ትዝታ እንደ አዲስ በህልም አለም ይደገማል።
አንድ ለሊት መርየም እንደሌላው ግዜ ለይል ሰግዳ መስገጃዋ ላይ እንቅልፍ ወሰዳት።በህልሟ አንድ ወጣትን ከጀርባው ስትከተል ታያለች።ይህ ወጣት አሸዋማ መሬት ላይ በፍጥነት ይራመዳል።መርየም ወደ እሱ ለመድረስ ትሮጣለች።የምትከተለውን ሰው ደርሳበት ሰላላወቀች<ማነህ?>ብላ በድካም ስሜት በማለክለክ ተጣራች።<ሀዘን አታብዢ እኔ በሰራሁት የዱንያ ቤት አብረን አልኖርንም በቅርቡ በገነባሽው የጀነት ቤት አብረን እንኖራለን>አለት።ጀርባውን ከሰጠበት ፊቱን አዞረ።አቧራ የቀላቀለ ንፉስ ፊቱን ሸፈነው።ፊቱን ሳታየው መርየምም ከህልሟ ድንገት ባነነች።
አንድ ሌሊት ህመሟ በጣም በረታ።እጇን ወደ ደረቷ አስጠግታ ቀስ ብላ ተቀመጠች። እስትንፋሷ ተረበሸ።ዓይኖቿ እንባ ሞሉ። ማንም እንዳይሰማት ከንፈሯን ነከሰች።
“ዲህያ…”ብላ አቃሰተች።ያ ስም ከአፏ ሲወጣ እንባዋን ተቆጣጠረችው።<በጣም ናፍቀኸኛል…>በዚህ ሌሊት ሀዘን እና ህመሟ ሰውነቷን እንዳደከመ ተረዳች።
ወደ ሀኪም ቤት ሄዳ ተመረመረች።ሳይታወቅ የቆየ መዳን የማይችሉ የብዙ ህመም ባለቤት ሆነች።ህመሟን በመድሀኒት ናፍቆቷን በትዝታ እያስታገሰች ወደ አምስት ወር አሳለፈች።
መርየም ሰዎች ፊት የበለጠ ጠንካራ ሴት ሆነች። ስትሰቃይ አትናገርም።ስትደክም አትታይም።ፈገግታዋ ብቻ ደመቀ።ህመሟን የመድህኒት ሰዕት ሲደርስ እንጂ አታዳምጠውም።ጥንካሬዋ ለህመም አልተበገረም።አመስጋኝ ናት።ለማማረር ግዜ የላትም።ያለ እድሜዋ ትልልቅ ሰው ትመክራለች።
የዲህያ እሀት ሲሀም በመሀል ከለቅሶ በሃላ መርየምን ለመጠየቅ መጣች።መርየም ያለችበትን ሁኔታ አይታ አዘነች።ዲህያ እየሰራው የነበረው ቤት ለመድረሳነት እንደተሰጠ ነገረቻት።መርየም በዲህያ ስም የሚደረግ መልካም ተግባር በሙሉ ያስደስታታል።
<መርየም በቃላቴ ድንበር አልፋያለሁ እኔ ለሁለታችሁም ስል ያሰብኩት ነገር ነው እኔ የምወደውን ሰው አግብቼ መኖር ተስኖኝ የፈታው ሰው ነኝ እሱም በጣም ይወደኝ ነበር የባህሪ አለመጣጣም የሚያመጣውን ችግር አውቀዋለሁ በዚህ ምክኒያት አንቺን እና እሱን ሳያችሁ በእኔ አመለካከት ልክ አልመጣልኝም ነበር ይህ አንቺን ዝቅ ከማድረግ ሳይሆን ለሁለታችሁም በማሰብ ነበር በትላንት ህይወቴ ሰበብ የእናንተ ፍቅር በጠበጥኩ ልክነቴን እና ስህተቴን አላውቅም ብቻ ዲህያ ግን እንዳንቺ የሚወደው ሰው አልነበረም ነፍሱ ወዲያው አልወጣም ሆስፒታል ተወስዶ እኛም አግኝተነው ነበር ሞት እንደቀረበው ታውቆት ቤተሰቡን አውፍታ ጠይቆ ሰለአንቺ ነበር የሚያወራው "መርየም አላህ ሰላልፈቀደ ቃልሽን አጠፍኩ"ይል ነበር በተደጋጋሚ እያለቀሰ መርየምን አደራ ብሎናል የእኔን እጅ ይዞ ቀልቧን ሰብረሻል አውፍታ ጠይቂያት እሷ ንፁህ ናት ሰለ እሷ እኔ ማውቀውን ብታውቂ በተናገርሽው ቃል በተፀፀጥሽ ነበር እኔም ለአንቺ ባለኝ መውደድ ልብሽን ላለመስበር እስክትረጂኝ ጠብቂያለሁ አላህ አልፈቀደም እንጂ ዛሬ ለእሷ ኒካህ ማስርበት ቀን ነበር ውስጤ ላይ ያለው ደስታ መንገድ አስረሳኝ በአደጋው ምክኒያት እራሴን እንደሳትኩ መርየም የሚያምር ነጭ ቀሚስ ለብሳ በብርሀን ውስጥ ሆና የእኛ ሰርግ ጀነት ነው አለችኝ ከሰመመን ስነቃ እራሴን እዚህ አገኘሁት ሲሁ እንደምትወጂኝ አውቃለሁ መርየም ቀብር ውስጥ ምጠብቃት የጀነት ሙሽራዬ ናት ተንከባከቢያት>ይህን እንዳለኝ ገርገራ መጣበት ሀኪሞች ለማስወጣት ሲሞክሩ እጁን አጥብቄ ይዤ ታገልኳቸው እንባዬ እያነቀኝ ሸሀዳን አጠገቡ ሆኜ ድምፄን ከፍ አድርጌ ደጋገምኩለት ወላሂ አኩ በተደጋጋሚ ሸሀዳ እያለ ነበር የሞተው ሀኪሞቹ ማሽኑን ነቅለው ሲወጡ ቀዝቃዛ የሆነውን ባለ ኑር ግንባሩን ሳምኩት በደም የረጠበው አንገቱ ስር ያለው መዕዛ ይለይ ነበር...በዚህ ንግግሯ ሁለቱም አለቀሱ።ዲህያ ለኒካህ ያጠራቀመውን ብር ሲሀም ለመርየም ሰጠቻት።መርየም እምቢ ብትልም ሲሀም የአንቺ ሀቅ ነው ብላ ጠነከረችባት።ሁለቱም ሰለውዳቸው ዲህያ እያወሩ አንዴ ሲስቁ አንዴ ሲያለቅሱ ዋሉ።መርየም ፊቷ ተጎሳቁሏል ሲሀምም ብትሆን ሰውነቷ ከስቷል።መርየም ለሲሀም ሰለ ህመሟ አልተናገረችም።መርየም ከባህሪዋ አላህ እንጂ ሰው እንዲያዝንላት አጠብቅም።እንባዋ ከመስገጃ ውጪ ለደስታ ካልሆነ በቀር ሰወ ፊት አይፈስም።ሲሀም ሰለዲህያ ያላትን ስሜት ሰለተጋራቻት ትንሺም ቢሆን ቀለል አለላት።ከሲሀም ጋር በአውፍታ ተቃቅፈው ተለያዩ።

መርየም ሰዎች ሲጠይቋት “ደህና ነኝ” ትላለች።እውነቱ ግን በየቀኑ ፊቷ እየቀነሰ።ዓይኖቿ ወደውስጥ እየጠለቁ።እጆቿ እየደከሙ።ድምፇ እየቀለለ።ወዟም ቀስ በቀስ እየጠፋ ነበር።አንድ ቀን ከመስታወት ፊት ቆማ እራሷን ስትመለከት የድሮ መልኳ የለም።“ይህች መርየም ናት?”ብላ እራሷን ጠየቀች።መርየም የት ሄደች?የፊቷ መልክ እንደ መሬት ስበት የሚጣራ፣ ጉንጯ እንደ ስስ ፊኛ የተነፋ፣ስለነገ ብዙ ህልም የነበራት መርየም የት ሄደች?
ከዚያም ቀስ ብላ ደብተሯን ከመሳቢያው አወጣች። በገፁ ላይ ምንም ሳትጽፍ ለደቂቃ ተቀመጠች። በመጨረሻ ብዕሯን አነሳችና በዝግታ መጻፍ ጀመረች።

“ዲህያ…እኔ አሁንም እዚህ ነኝ።ግን አንተ ከሄድክ በኋላ እኔ የቀድሞዋ መርየም አይደለሁም።ሰውነቴ ከስቷል።አይኔ ጠቁሯል።ፀጉሬም ተልጯል ።በዚህ ሁኔታ አንተ አጠገቤ አለመኖርህ ደስ ብሎኛል።እንዲህ ውበቴ በወጣትነት ሲረግፍ ምኑን ችለህ ትቋቋመው ነበር።አላህ ሁሉን አዋቂ ነው።ከአላህ ቀጥሎ ለአንተ እንጂ ህመሜን ለማካፈል የምፈልገው ሰው የለም። ሰዋች አተን አጣን ይላሉ።ከአንተ ጋር የሄደችውን መርየም ግን አያውቁም።”እጇን ደከማት።ብዕሯን አስቀመጠች።ህመሟ በረታ።አንዳንድ ጊዜ ከወንበር ለመነሳት እጇን በጠረጴዛው ላይ ታሳርፋለች።አንዳንድ ጊዜ እስከ ክፍሏ ድረስ ለመድረስ መንገዱ በጣም ረጅም ይመስላታል።አንዳንድ ጊዜ በደረጃ ላይ ቆማ እስትንፋሷን ለመሰብሰብ ትጠብቃለች።የህመሟ ክብደት ወደ ዲህያ መቃረቧን ሲጠቁማት እያመማትም ደስ ይላታል።
መርየም ከሞተች ዲህያ የሚኖርበትን ጀነት ተመኘች።ወደ ጌታዋ ከበፊቱ በላይ ተቃረበች።ሰላቷ ላይ በረታች።

ያለማቋረጥ የመርየምን ማስታወሻ የሚያነበው ሚሻል መርየም በእንቅልፍ ተደብቃ ከመሞቷ ከሰዕታት በፊት ወደ ፃፈችው የመጨረሻ ገፅ አከባቢ ደረሰ።
ዛሬ ሰውነቴ እንደሌሎቹ ቀናት አይሰማኝም።በጣም ደክሞኛል።እጄን ለማንሳት እንኳን ኃይል እየተቸገረኝ ነው።ዓይኖቼ ሲዘጉ ለመክፈት እንደገና ኃይል መፈለግ አለብኝ።እና በልቤ ውስጥ አንድ ስሜት አለ…ምናልባት ይህ የመጨረሻዬ ሌሊት ሊሆን ይችላል።ይህን ስጽፍ እጄ እየተንቀጠቀጠች ነው።ሞትን እፈራለሁ።አዎ… እፈራለሁ።ምክንያቱም በህይወቴ ብዙ ያልተጠናቀቁ ገፆች አሉኝ።ብዙ ያልተነገሩ ቃላት አሉኝ።ብዙ ያልተሳሳምኳቸው ግንባሮች።ብዙ ያልተሰናበትኳቸው ሰዎች።በእዝነቱ በመማሩ ካልተጠጋው ያጎደልኩት ስራዬ ብዙ ነው።አላህ ካላዘነልኝ ጀነትን ለመጠየቅ የሚያስችል ስራ የለኝም።ስለ ሞት ሳስብ ከሞት በላይ የሚያስፈራኝ ነገር አለ።እሱም አንተን እንደገና ሳላገኝ መቅረት ነው።ዲህያ…እኔ በምድር ላይ አንተን ለማጣት ተገደድኩ።ምናልባት አላህ በሌላ ቦታ እንደገና እንድንገናኝ ያደርገን ይሆናል።ይህ ለእኔ ትልቁ ምኞት ነው።እዚያ ህመም የሌለበት ቦታ።እንባ የሌለበት ቦታ፣መለያየት የሌለበት ቦታ፣ድካም እና ማርጀት የሌለበት ቦታ፣አይን አይቶት ልብ ገምቶት በማይችለው ፀጋ ውስጥ ለዘልዕለም ከዲህያ ጋር መሰንበት እመኛለሁ።አሁን ግን ዓይኖቼ እየከበዱኝ ነው።የምጽፈው ፊደል እየተወላገደ ነው።ልቤም በጣም ደክሟል።ብዕሩን ለመያዝ እጄ እየተቸገረች ነው። ፊደሎቼም እንደቀድሞው ቀጥ አላሉም። ምናልባት ዛሬ የጻፍኩት የመጨረሻዬ ገፅ ሊሆን ይችላል?ግን እንደ መጨረሻ ማሰብ አልፈልግም።ህይወቴን ስመለከት ብዙ ነገር አስባለሁ። የሳቅኩባቸው ቀናት፣ ያለቀስኩባቸው ሌሊቶች፣የጠበቅኳቸው እና ያጣኋቸው ሰዎች።ሰለሁሉም አልሀምዱሊላህ።
ዲህያ በህይወቴ ውስጥ ለምን እንደመጣ አላውቅም። ለምን እንደተወኝም አላውቅም። ግን እሱን ከወደድኩበት ቀን ጀምሮ የደስታ ምክኒያት አግንቺያለሁ።ዲህያ…አንተን መውደድ ለእኔ ትውስታ ብቻ አልነበረም። አንተ በሄድክ ግዜ ከእኔ ጋር የቀረህ አንድ ክፍል ነህ።ከሞት በሃላ እዚህ ምድር የሚቀረኝ እኔን የሚያስታውሰኝ ሰው አለመኖር ነው።ስለዚህ ይህን ደብተር እዚው እተወዋለሁ።ማንም ካገኘው ስለ ህመሜ ብቻ እንዳያነብ።እኔ የተሰበርኩ ልጅ ብቻ አልነበርኩም።እኔ ፍቅርን የታደልኩ ልጅ ነበርኩ።የተስፋ ቀናት ነበሩኝ።ህልሞች ነበሩኝ።ደስታዋች ነበሩኝ።አላህን ማመሰግንበት ሙሉ አካል ነበረኝ።እና አንድ ቀን ሰው ከልቡ የሚያስታውሰኝ ከሆነ…ያ ለእኔ በቂ ነው።

ሚሻል መርየም ገርገራ ውስጥ የምትወደውን ዲህያ በጀነት አይታው ይሁን ፈገግ ብላ የሞተችው? የሞተ ገላዋ ህያው የመሰለው የልቧን ምኞት አጊንታ ይሁን? ብሎ ለደቂቃ የመርየምን ፈገግ ያለ ውብ ጀናዛ አስታወሰ።በእርግጥ አላህ ለባሮቹ የማይሰስት የማያልቅበት ባለፀጋ ነው።

ሚሻል የመርየምን ደብተር ሲያነብ እስከመጨረሻው ገፅ ድረስ ምንም አላቋረጠም።
የዲህያን ፍቅር፣የዲህያን ሞት፣የመርየምን ህመም፣ብቸኝነቷን፣እንባዋን፣ትዕግስቷን፣ፍቅሯን
እና በመጨረሻ… የሞቷን ቅርበት።ሚሻል የመጨረሻውን የተጻፈ ገፅ አነበበ።ከዚያ ቀጣዩን ገፅ ገለጠ።ባዶ ነበር።ምንም ቃል የለም።ምንም ፊደል የለም።ምንም የእንባ ምልክት እንኳን የለም።ሚሻል ገፁን ለረጅም ጊዜ ተመለከተ።ደብተሩን እስከመጨረሻው ገለጠ።ከዚያ ወደ ኋላ መለሰው።የመርየም ታሪክ በዚህ ባዶ ገፅ ላይ እንደቆመ ነበር።መርየም መጨረሻዋን ለመጻፍ አልሞከረችም።ሚሻል ጣቱን በባዶው ገፅ ላይ አሳረፈ።ዓይኖቹ በእንባ ሞሉ።ባዶው ገፅ ለሚሻል ከማንኛውም ቃል በላይ ይናገር ነበር።መርየም
ታሪኬ እዚህ አላበቃም።የምትለው ይመስለዋል።እና ያኔ ሚሻል የመርየም መጽሐፍ እንዳልተጠናቀቀ ተረዳ።እሷ የመጨረሻውን ገፅ ባዶ ትታው ነበር።ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው ከሞተ በኋላ የሚተወው ታሪክ አንድ ቀን በሌላ ሰው ህይወት ውስጥ ይቀጥላል።

እና ያ ነበር…ቀሪው ገፅ

ይቀጥላል..
@bintsumi
❤4
Audio
MediaConvert
ቀሪ ገፅ
[ሱሚ ማማይ]

ጎደለ ታሪክሽ? የት ጋ ነው መቅረትሽ?
አፈር ገባ ስጋ አካልሽ
መኖር ያዘ ትላንት ግብርሽ
ሳትጠጋ ንፁህ ፍቅሯን
ሳትጀምር የትዳር ቀኗን
የእሷን ነገ ሞት ቀደመ
የህልሟ አልጋ እንቅልፍ ሾመ
ማይታቀፍ ባዳ ገላ
ከእነ ፍቅሯ አፈር በላ
እንደ ፉጢማ በእቅፉ ባትበረታ
ፃፈች ፍቅር ጀነት ገብታ
ለድሎቱ ዱዕ ልካ ለጀነቱ ከፍላ ዘካ
ሁረል አይን እንዳይነካ በመሰሰት ቅናት ታካ
ናፈቀችው ሞትን ይዛ
ተከተለች ሀዘን መዛ
እንደ አልይ
ጀናዛውን አልታቀፈች
ዜናው ከብዷት አለቀሰች
ትችል ነበር..
ስንቱን ሀዘን
ትችል ነበር
ስንቱን ማጣት
እሱ ሲሆን ምን ሊውጣት?
እንደ አልይ
ግዙፍ ሸክም አላስቆማት
የእሱ ሬሳ አቅል ነሳት
እንደ አልይ
እንዳልቻለው የእሷን ገላ
ስትሸከም ጅስሟ ላላ
እንደ አልይ
ከቀብሯ ጎን እንዳነጋ
የእሷ መኖር በሞት ረጋ
ቀሪ አላት በታሪኳ
በእሱ መኖር የሚተካ
ጀነት አላት ምትናፍቀው
ከእሱ ጋራ ምትኖረው።
@bintsumi
🥰4❤2
ቀሪ ገፅ
[ሱሚ ማማይ]
ክፍል ሀያ ሶስት
******

ሚሻል ከልጅነቱ ጀምሮ አላህን ለማወቅ አልሞከረም።እምነትን በስም እንጂ በልቡ ላይ አልተሸከመም።አዛን ወደ አላህ ቤት የሚጠራው ድምፅ አልነበረም።
ሰዎች በዱዕ እጃቸውን ወደ ሰማይ ሲያነሱ እሱ በጥያቄያቸው ላይ ይገረማል።እንደ እሱ ጉዞ ሕይወት የሚጀምረው የሚያበቃውም እዚህ ዓለም ላይ ነበር።
<እውነት ፈጣሪ ከኖረ ለምን ችግር ተፈጠረ?>ይላል። ነገር ግን ለጥያቄዎቹ መልስ ከመፈለግ ይልቅ አላህን መካድ ቀላል ሆነለት።እሱ በሁሉም ነገር ውስጥ ሲፈልገው የኖረውን ሰላም አላህ ዘንድ መገኘቱን አላወቀም።የመርየምን ማስታወሻ ካነበበ ወዲህ ግን የገባው ነገር ለአላህ ያላትን ቅርበት ነው።አመስጋኝነቷ ልቡን አለሰለሰው።መርየም በህመሟ ውስጥ ሳይቀር አላህን ማመስገን አልሰነፈችም።እሱ ግን በማማረር የዘነጋው የፀጋ ጥፍጥና በዛበት።

ሚሻል አሁን ያለበት የቤቱ ክፍል ማብራት ጠፍቶ ጨለማ ነው።ከሌላው ግዜ በተለየ መልኩ ከብቸኝነት ይልቅ የሰማይ እና የምድር ሰራዊት ካለው አምላኩ ጋር የልቡን ጥሪ ማውጋት ጀመረ።ለመጀመሪያ ጊዜ የልቡን ጨለማ በብርሀን መለወጥ ፈለገ።የክፍሉን ማብራት አበራ።ለልቡ ብርሀን ውዱእ አደረገ።ገላውንም ታጠበ።ወደ ጌታው ሊቆም መስገጃውን ዘረጋ።ሚሸል በሰላቱ ላይ
“አላህ ሆይ ረያንን መልስልኝ” አላለም
“አላህ ሆይ፣ ሕይወቴን ለውጠው” ብሎ አልጠየቀም።የፀፀት እንባው በሱጁድ ላይ ወረደ።
“አላህ ሆይ…
አንተ እያለህ ከአንተ ውጪ ያለን በሙሉ ፈለግኩ።አንተ ስትጠብቀኝ እኔ ራቅኩኝ።ስትሰጠኝ አመፅኩኝ።ስትከለክለኝ ተቆጣሁ።የሰጠሀኝን ስትወስድብኝ ተነጫነጭኩ።ዛሬ አንተ ሳትኖር እኔ ምንም እንደሆንኩ ተረዳሁ ይቅር በለኝ…”
“አልሐምዱሊላህ…”

ይህ ቃል ከቀናት በፊት ለሚሻል ዳገት ነበር።አሁን ግን ሕይወት ሆነው።ሚሻል አላህን አገኘ።እና ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ያጣውን ከመቁጠር ይልቅ ያለውን ማመስገን ጀመረ።እናም በዚያ ቅጽበት ሚሻል ለመጀመሪያ ጊዜ ከአላህ ሊሸሽ የሚችልበት ቦታ እንደሌለው ተረዳ።
ከሰዎች ሊሸሽ ይችላል።ከትዝታ ሊሸሽ ይችላል።ከፍላጎቱ ሊርቅ ይችላል።ግን ከፈጣሪው ሊሸሽ አይችልም።ዳግም እጆቹን ወደ አላህ አነሳ።ለአላህ ለመቅረብ ሱጁድ ወረደ።ግንባሩ መሬት ነካ።ድምፅ ሳያወጣ ከጌታው ጋር ማውራት ጀመረ።
“አላህ ሆይ…
እኔ ለዓመታት ከአንተ ሸሽቻለሁ።አንተ ግን አልተውከኝም።አንተን ስክድ የሰጠሀኝን አልነጠቅከኝም።አንተን ስረሳ አንተ ግን አልተውከኝም።እኔ እንጂ አንተ አልራቅከኝም።ሰዎችን ተከትዬ ደከምኩ።ፍቅርን ተከትዬ ደከምኩ።የእራሴን ፍላጎት ተከትዬ ደከምኩ።አሁን ግን ወደ አንተ ብቻ ለመመለስ መጥቻለሁ።ወንጀሌ ብዙ ነው.......ግን ከአንተ አንድ እዝነት አይበልጥም።ስራዬ ብቻ በሚፈርድልኝ እለት እዘንልኝ።
አላህ ሆይ...የምወደውን የምፈልገውን ነገር እንድትሰጠኝ አልጠይቅህም።ችግሬን፣ምሬቴን ከሕይወቴ እንድታስወግድ አልጠይቅህም። ብቻዬን ግን እንዳትጥለኝ እለምንሃለሁ።
በተሰበረ ልብ፣በብዙ ኃጢአት፣በብዙ ፀፀት ወደ አንተ እመጣለሁ።
አላህ ሆይ…እኔን እንደ ጥፋቴ አትመልከተኝ።እንደ ምሕረትህ ያዘኝ።
እኔ ወደ አንተ ለመምጣት ዘግይቻለሁ።ዘውታሪ አድርገኝ።ክፍት የሆነውን የእዝነትህን በር አታስረሳኝ ይቅር በለኝ…
እንባው ግንባሩ ያረፈበትን መስገጃ አረጠበው።ፀፀቱ ቃል አልነበረውም።ፍርሀት፣እፍረት፣ድንጋጤ፣ተስፉ የቀላቀለ ስሜት ልቡን ተሰማው።ሰለ እራሱ ለአፍታ ሲያስብ ኩምሽሽ አለ።ልቡ ከበደው።
<ጌታዬ በእዝነትህ..እያለ እንባው ከአፍንጫው ውሀ ጋር ተቀላቅሎ ወረደ።ስቅስቅ ብሎ አነባ።ድምፁ ከክፍሉ አልፎ ይሰማ ነበር።ለእሱ የእሱ ሁኔታ ግድ አልሰጠውም የእሱ ጭንቀት አላህ ይምረኝ ይሁን? የሚለው ነበር።

አልሐምዱሊላህ…”

ያ ነበር የሚሻል የፀፀት እንባ።ከአመታት ርቀት በሃላ ወደ አላህ የተመለሰበት እንባ ነበር።ከዚያ ቀን ጀምሮ ሰላት ለእሱ ከአለም ወደ አላህ የሚመለስበት በር ሆነው።
በፊት እንዲህ ይል ነበር፦
“ለምን አላህ?”አሁን ግን፦
“አልሐምዱሊላህ… ለሁሉም አላህ አለ”
ያኔ ነበር ሚሻል በእውነት የተለወጠው።ሚሻል ተውበቱን ሲያስብ
“እኔ አላህን አላገኘሁትም…
እሱ ነው እኔን ያገኘኝ”ይላል።

አላህ ባሮቹን ሲምር ያለፈውን የማይቆጥር ጌታ ነው።ለዚህ ምስክር ከከሀዲ ሰይፍ ወደ እራሱ ሰይፍ የቀየረው የጀግናው ሰሀባ ካሊድ ታሪክ በቂ ነው።አላህ ሲቆጣ የትኛውም ትልቅ ተግባር አይበግረውም።ለዚህ ምስክር የኑህ ጎስቋላ መርከብ እና ትልቁ ተራራ በቂ ነው።አላህ በዳዬች የተመኩበትን ተራራን የሚያክል ግዙፍ ነገር በማዕበል አፍርሶ መርከቧን ግን በእሱ ትዕዛዝ አማኝ እንደያዘች ያለምንም መናወጥ በሰላም ተጉዛለች።

ይቀጥላል
@bintsumi
የመጨረሻው ክፍል መች ይለቀቅ? 'ቀሪ ገፅ' ሊያልቅ አንድ ክፍል ብቻ ቀረው 🥺
ቀሪ ገፅ
[ሱሚ ማማይ]
ክፍል ሀያ አራት
የመጨረሻ ክፍል
****

ሚሻል በመርየም ማስታወሻ ሰበብ የህይወቷን ገፅ በቀላሉ እየገለጠ አነበበ።ህመሟ፣ማጣቷ፣ምስጋናዋ ተጋባበት።የእሷን ማስታወሻ ሌሎች እንዲያነቡት ዘንድ ማሳተም ፈለገ።ይህን ሀሳብ ለማጠናከር ፉአድን ማማከር እንዳለበት አሰበ።ግዜ ሳይፈጅ ፉአድን አግኝቶ ሰለመፃፉ ያለውን ሀሳብ በዝርዝር ነገረው።ፉአድ በሚሻል ሀሳብ ተስማማ።ሚሻልም ፉአድ እሺ ሰላለው ተደሰተ።

ሚሻል መርየም ሀሳቡን እንደተቆጣጠረች ወደ ስራው ገባ።ቀመር ለሰርግ ዝግጅቷ ፍቃድ ጠይቃ ስራ አቁማለች።ዙሊሊ ብቻዋን በመስተንግዶ ተወጥራለች።በእረፍት ሰዕት ሚሻል እና ዙሊሊ ጥግ ላይ አብረው ተቀመጡ።ሚሻል እና ዚሊሊ የጎን ወሬ ጀመሩ።ዙሊሊ <ሚሻል በንግግሬ እናም በሁኔታዬ ካስቀየምኩህ ይቅርታ ነገሮች የገቡኝ በቅርብ ነው>አለችው ።
<እኔ እድሜ ለቀመር ተረድችሻለው ባይሆን ሳይዘገይ መንቃትሽ አሪፍ ነው>አላት ሚሻል።
<በፊት እንደዚህ አልነበርኩም መቼ በእራሴ ኩራት ይዞኝ እንደተኮፈስኩ አላውቅም አድናቆት ልቤን አውሮታል ይህም አሁን የገባኝ በፈይሰል ምክኒያት ነው>አለች በፈገግታ።
<እንዴት?>አላት።በቀመር ተደጋጋሚ ጉትጎታ ፈቅ ያለለችው ዙሊሊ በቅርብ በአወቀችው ሰው በመቀየሯ እየተገረመ።

ዙሊሊ ሀሳቧን እየቀጠለች<የሆነ ግዜ ላይ ከዶክተር ጋር ገና ብዙ ሳንግባባ በፊት ነጭ እና የሚያምር ቀሚስ ገዝቶ እንደ ስጦታ ሰጠኝ ስጦታ ሰለምወድ ተቀበልኩት ስጦታው ያምራል ግን ቤት ወስጄ ስለበሰው የማይሆን ቦታ ላይ ውበቱን በሚሰርቅ መልኩ ተቀዷል ተናደድኩ መልበስ ሰለፈለኩኝ ስፌት ቤት ወሰድኩት በነጋታው ፈይሰል ወደዚህ ምግብ ቤት መጣ አስጠርቶኝ አጠገቡ ተቀመጥኩ ሰለልብሱ ጠየቀኝ እንከኑን ደብቄ እንደሚያምር ነገርኩት ልብሱን ለምን እንዳለበስኩት ሲጠይቀኝ እንደተቀደደ እና ለማሰፋት መስጠቴን ስነግረው ይሄን ሁሉ አቅዶ እና አስቦ እንዳደረገው ነገረኝ>አለች።የንግግሯን መጨረሻ ማወቅ ሰለፈለኩ እንድትቀጥል<እንዴት?>አልኳት።
ዙሊሊም የፈይሰልን ሀሳብ እየደገመች።<አንቺም እንደዛ ልብስ ውብ እና ውበትን ምትጨምሪ ሴት ነሽ ነገር ግን ሰዋች አንቺን መልበስ ከአንቺ ጋር መቆየት ቢፈልጉም እንኳን አይችሉም ሁሉም ቀዳዳሽን እንጂ መጠገንሽን ሰላላሰበ ይርቅሻል የሆነ ቦታ ላይ ውበትሽ ተቀዷል መጀመሪያ አንቺን ያወቅኩሽ በቅድሚያ ሰለአንቺ በተደጋጋሚ ከሰዋች በመስማቴ ነው ልክ ሳይሽ ከነገሩኝ በላይ ውብ ነሽ አይኔ ላይ ሳይሆን ልቤ ላይ እንድትቀሪ ሰለፈለኩ እኔም ልክ አንቺ መልበስ ፈልገሽ እንዳደረክሽው ሁሉ ላክምሽ ፈለኩ>አለኝ። አለች ዙሊሊ በፈገግታ ፈይሰል ያላትን እየደገመች።
<እንዴት ሲል አሰበው በአላህ!? ዙሊሊ ኮራሁበት አንበሳ! እኔ እኮ ብዙ ግዜ ስታወሩ አያችሁ ነበር>አለ ሚሻል በፈገግታ።
ዙሊምም<በሰዕቱ ንግግሩ አልገባኝም እንደውም በፊት ለፊቱ ሰምቼው ሳበቃ ሙድ ስይዝበት ነበር እሱ ግን ደጋግሞ መከረኝ በስብዕናው ስማረክ እና የእኔ እንዲሆን ስመኝ ግን አዳመጥኩት የንግግሩ ውበት እና መደጋገም ጠጣር ኩራቴን ደረመሰው መስታወት ፊት ቆሜ እራሴን ከላይ ሳይሆን ወደውስጥ አየሁት እራሴን ለእራሴ መምረጥ ከበደኝ ከዛም በጠየቀኝ መሰረት ልብሱ ለመሆን ተሰፋሁ>አለች ንግግሯን በሀፍረት እያቋረጠች።
ቆንጆዋን ዙሊሊ በመቀደሙ ቢያዝንም በነገረችው ነገር ተደሰተ።ቀመር እንዳለችው ዙሊሊ የሚቀየር ስስ ማንነት አላት።ሚሻል እና ዙሊሊ ብቻቸውን በመግባባት ለደቂቃዋች ቁጭ ብለው ስያወሩ ይህ ቀን የመጀመሪያቸው ነው።ዙሊሊ ሳቅ ስትል የሚጨፈነው ትልቅ አይኗ ልብ ያሞቃል።እስካሁን ያላሳመነው አነጋጋሪ ውበቷ ዛሬ ይበልጥ ገኖ ታየው።ውበት አካል ላይ ያለ ነገር ግን ውስጥ ላይ የሚፈጠር መንፈስ ነው።ከዙሊሊ ጋር የልብ ልብ በሳቅ እያወሩ የስራ ሰዕቱን ጨረሱ።
ሚሻል ከስራ በሃላ ፉአድ እንዳለው መርየም እና ረያን ያደጉበት ማደጎ በመሄድ ሰለመርየም ለመፃፍ የተሟላ መረጃ ጠየቀ።የሚያምር ሰፊ ግን ብቸኝነት ሚነበብበት ግቢ ነው።ሰለ መርየም የጠየቀው ሰው አቧራውን እያራገፈ በዶሲ የተሸገ ወረቀት መክፈት ጀመረ።ከዶሲ ውስጥ አንድ አባት ልጁን አቅፎ የተነሳውን የቁም ፎቶ ያለበትን ወረቀት አቃበለው<አባቷ ነበር እሱ እዚ ካመጣት በሃላ ሆን ብሎ በታቀደ የመኪና አደጋ ሞቷል እናቷ ስትወልዳት ነው የሞተችው ሰለ መርየም ባጣራነው መልኩ ሰለቤተሰቧ ያገኘነው ከዚ በላይ ፍንጭ የለም....>ሰውየው እያወራ ነው።የሚያየውን ማመን ያቃተው ሚሻል ግን ፎቶውን ካየ በሃላ መስማት አቁሟል።<አባቷ ከዚህ በፊት ሌላ ሚስት እንደነበረው እሷም እንደ መርየም እናት ስትወልድ እንደሞተች ሰምተናል ምንአልባት መደጋገሙ የፈጠረበት ጫና እራሱን እንዲያጠፋ የገፋፋው ነገር ይመስለኛል...>ሰውየው ቀጥሏል...ሚሻል የፎቶውን ጀርባ እየገለባበጠ ባለማመን ያየዋል።ፎቶው የቆየ ነበር። ጠርዙ ተቀዶ፣ቀለሙ ደብዝዟል። ነገር ግን በፎቶው መሀል የቆመውን ሰው ፊት ግን…ሚሻል በደንብ ያውቀዋል።የተረሳ ግን የማይጠፋ ፊት ነው።የልጅነቱ ማስታወሻ።የቤተሰብ የመጨረሻው ምስል።የሚሻል አባት።ሚሻል ድንገት የጠፋውን የአባቱን ፊት ከ ሀያ አመታት በሃላ ዳግም በፎቶ ሲያየው አልረሳውም።እጁ ተንቀጠቀጠ።
<ይሄ…>ድምፁ ከጉሮሮው አልወጣም።ሰውየው የሚሻልን ሁኔታ ሲመለከት።<ምን ሆነ?>አለው።
ሚሻል ፎቶውን ወደ ላይ ከፍ አንዴ ዝቅ አደረገ።አባቱ በፎቶው ላይ ሕፃን ልጅ አቅፏል።ልጅቷም መርየም ነች።
<ይሄ ሰው እርግጠኛ ነህ አባቷ ነው?>አለ ዝግ ባለ ድምፅ።
<እንዳለን መረጃ አዎ እሱ ነው እዚህ ያመጣት.... ፎቶውንም ያገኘነው ልብሷ ውስጥ አስቀምጦላት ነበር እኛ ወላጅ አልባ የሆኑትን ህፃናት ብቻ ነው ምንቀበለው እሱ እዚህ ግቢ ላይ የሚታወቅ ሰው ሰለሆነ በሰዕቱ እንደ አደራ ነበር የተቀበልነው>
ሚሻል ዝም አለ።በአእምሮው ውስጥ የአባቱ ፊት ተመላለሰ።እሱ በልጅነቱ ብዙ ጊዜ አባቱን የጠየቀው ጥያቄ ታወሰው።
<አባዬ፣ እኔ ብቻ ነኝ ልጅህ?>
አባቱም የሚሰጠው መልስ ተመሳሳይ ነበር።<አንተ ብቻ ነህ የእኔ>
ሚሻል ዓይኖቹን ጨፈነ።<አንተ ብቻ ነህ…>ያ ቃል አሁንም ልቡን አቆሰለው።
<ለምን አባ?>አለ በውስጡ።
ሚሻል እንደገና ፎቶውን ተመለከተ።አባቱ ሕፃኗን አቅፎ ፈገግ ብሎ ነበር።ያ ፈገግታ ሚሻል በልጅነቱ ካየው ፈገግታ ጋር አንድ ነበር።አእምሮው አንድ ነገር እንዲያምን እየጮኸ ነው።እሱ ግን አልፈለገም።
<አይሆንም…>አለ በቀስታ።ሰውየው ሌላ ፋይል እያወጣ<በዚህ ፋይል ውስጥ የልጅቷ የአባት ስም ተጽፎአል>
ሚሻል ወረቀቱን ተቀበለ።አይኖቹ በስሙ ላይ አረፉ።አብዱልሰላም አህመድ።የሚሻል አባት ስም።ወረቀቱ ከእጁ ሊወድቅ ተቃረበ።
<እሷ…>እጆቹ በላብ ተሞሉ።<እህቴ…>
ቃሉ ከአፉ ተበተነ።ሰውየው ዝም አለ።ሚሻል ፎቶውን እንደገና ተመለከተ።በአባቱ እጅ ላይ ያለችው ሕፃን።መርየም.....የመርየም ማስታወሻ።ዓይኖቹ በእንባ ተሞሉ።

<እኔ… እኔ ነኝ…>ቃሉን ለመጨረስ ተሳነው።<እኔ ወንድሟ ነኝ።>የሚሻል ጉልበት ተንቀጠቀጠ።በዚያ ቅጽበት የመርየም ማስታወሻ ውስጥ ያነበባቸው ቃላት በአእምሮው ተመላለሱ።
<አንድ ቀን ቤተሰብ ይኖረኛል…>
<አንዳንድ ጊዜ የማላውቀውን ሰው ናፍቄ እውቃለሁ…>
<.....የወንድም ከለላ ፈለግኩ>
ሚሻል ፊቱን በድንጋጤ በእጆቹ ሸፈነ።የመርየም እያንዳዱ ያነበበው የእሷ ህይወት በቅፅበት ውስጥ እንደ ስዕል ታየው።ለ ሀያ አመት ያስፈልጋት ለእሱም ታስፈልገው ነበር።
<እኔ ነበርኩ…ቅርቤ ነበረች >አለ።
❤2
ሚሻል የመርየምን ምኞት ለማሳካት ነበር ወደዚህ ግቢ የመጣው።ነገር ግን ያነበበው የአንዲት ልጅ ታሪክ ብቻ አልነበረም።የማያውቃት ግን የስጋ አካሉ እህቱ ነች።በህይወት እያለች ሊያቅፋት እየፈለገገ ነበር ግን መርየም ሀጂነብይነት ተሰምቷት የራቀችው እህቱ ሆነች።ሚሻል በፎቶው ላይ ያለችውን ትንሿን መርየም እያየ እና ማስታወሻ ላይ ያደገችው ትልቋን መርየም እያሰበ እንባውን ማቆም አልቻለም።
“መርየም…”

አንዳንድ ሰዎች ከህይወታችን መጀመሪያ ወይም መሀል ላይ አይገኙም ምን አልባት በመጨረሻ ገፅ ላይ ይመጣሉ።እና ሚሻል የመርየም የመጨረሻ ገፅ ነበር።

ሚሻል ወደ ቤቱ ተመልሶ የመርየምን ማስታወሻ እስከ መጨረሻ ገፅ ገለጠው።የመጨረሻው ገፅ ባዶ ነበር።ምንም ቃል የለበትም።ምንም ነጥብ የለበትም።ምንም ሰላምታ የለበትም።ብቻ ባዶ ገፅ።ሚሻል ጣቱን በወረቀቱ ላይ አሳረፈ።እሷ ለምን ባዶውን እንደተወችው አላወቀም።የምትናገረው ነገር አልነበራትም? ወይም…ምናልባት ለመናገር የሚበቃ ጊዜ አልነበራትም?
እሱ በድን እንደሆነ ለጥቂት ሰከንዶች ባዶውን ገፅ ተመለከተ።ከዚያ አንድ መስመር ጻፈ።
“መርየም… እኔ ወንድምሽ ነኝ።”
እንባው በወረቀቱ ላይ ወደቀ።ቀለሙም በእንባው ፈሳሽ ተሰራጨ።ሚሻል ብዕሩን እንደገና አነሳ።ሌላ ነገር ሊጽፍ ፈለገ።
“ይቅርታ” ሊል ፈለገ..
“እወድሻለሁ” ሊል ፈለገ...
“ለምን አላገኘሁሽም?” ሊል ፈለገ...
ግን አንዳቸውም ቃላት በቂ አልነበሩም።ብዕሩን አስቀመጠ።የመርየምን ማስታወሻ ዘጋው።ከዚያም ባዶ ቤቱ ውስጥ ድምፁን ከፍ አድርጎ
<<ሁሉንም ገፅ አነበብኩ…አንቺን ግን ዘግይቼ አወቅኩሽ>>
አልጋው ላይ በጀርባው የተንጋለለው ሚሻል እንባው ጉንጩን ተደግፎ በሁለት ጎን ወረደ።
ሚሻል ለመጀመሪያ ጊዜ ሊያቅፋት ሊያወራት ሊቀርባት የማይችላትን ቤተሰብ እህት አገኘ።እህቱም ብትቆይ ለመኖር ምታቅድለትን ወንድም ተለያየች።ሁለቱም ተገናኙ አንዱ ለስንብት፣ ሌላው ለትዝታ።እና በመካከላቸው የቀረው ነገር…አንድ ባዶ ገፅ ብቻ ነበር።

መርየም ለእሱ የማያውቃት ድጋሚ የማያገኛት አንዷ እህቱ ነች።ቀብሯን ለመዘየር እንጂ እጇን ለመያዝ አልታደለም።ሚሻል በእሱ እድሜ ያሳለፈውን ክስተት በድጋሚ በህሊናው ላይ መላለሰ።ብዙም ሳይቆይ ከሀሳብ መንገዱ ላይ በትንሽ እጇ የሸሚዙን ጫፍ አጥብቃ የያዘችው የረያን ልጅ ኢናያ አስቆመችው።እሱ እና ረያን በወደቁበት አላህን ባመፁበት ስህተት መሀል የተፈጠረች እምቡጥ አበባ መሰለችው።ይባስ ሲልየእራሱን መልክ የደገመችው እና የእኔ የሚል ስሜት የፈጠረችበት ትንሽ አበባ ቀለሟ ፈፅሞ ከረያን ሆነ ከባለቤቷ ጋር አይገናኝም።ሚሻል በዛን ቀን አንዴ ብቻ ነው ያያት ግን አልረሳትም።
ኢናያን እያስታወሰ ልጄ ትሁን ብሎ አሰበ?

ይህ ታሪክ ስለ ሰዎች መገናኘት እና መለያየት ብቻ አልነበረም።ስለ ፍቅርም ብቻ አልነበረም።ሁሉም ሰው በሌላ ሰው ሕይወት ውስጥ አንድ ገፅ አለው።

አንዳንዶች በእንባ ፣ አንዳንዶች በፍቅር፣ አንዳንዶች በጥላቻ፣አንዳንዶች በተስፋ፣አንዳንዶች በምስጋና፣አንዳንዶች በፅናት፣አንዳንዶች በደስታ፣አንዳንዶች በመኖር፣አንዳንዶች በመሞት በሰው ገፅ ላይ አሻራን ያሳርፋሉ።የመርየም በመጨረሻ ያልተጻፈ አንድ ገፅ…ለአንባቢያን የተተወ ገፅ ነው።ቀሪው ገፅ ባዶ እንደማይሆን በማሰብ ለሚሻል እንደተሰጠው ሁሉ ለአንባቢ፣ለእናንተ የእራሳችሁን ታሪክ ለመጻፍ የተሰጠ ቦታ ነበር።

ሀሳቡ ቢቀጥልም ልብ ወለዱ እዚህ ጋር አበቃ…ነገር ግን ቀሪውን ገፅ እናንተ ሙሉት።

ተፈፀመ❤️።
❤3
ባለ ቀለም
[ሱሚ ማማይ]

መኖር የጀመረው
የቀለም አሻራ
አንዱ ለአንዱ
ምልክት ሲሰራ
ዝብርቅርቅ ምስሎች
መልክን ይዋጃሉ
ያረፉ ቀለሞች
ሰውን ይመስላሉ

አንተ ባለቀለም
አንቺ ባለቀለም
መልክ አልባ ልጅነት
ለዘላለም የለም
ሁሉም ሰዕሊ ነው
ሁሉም መልከኛ ነው
ቀለም ተቀብሏል
መኖር የጀመረው
ሁሉም እንደ ወጉ
በቀለም ሲዋጉ
ዝብርቅርቅ መስመሮች
ጠልፈው እንዳይጥሉ
ከውበት አፉተው
መኖር ሳይከልሉ
መስታወት ላይ ቁሙ
ድብዝዝ ካለ ምስሉ
አላህዬ በሉ
አያልቅበት ቀለም
መልክን ለማበጀት
አጥፍቶ ይሰራል
መፍጠር ሲችልበት

ቀሪ ምስል አለ
ሰውን የማይሞላ
ከገፁ ማማር ላይ
የሚከተል ጥላ
አንተ የእኔ ጉድለት
አንቺ የእኔ ጥረት
መልኬን ላበጃጀው
ምልክት ስሩለት

ሁሉም መልከኛ ነው
ሁሉም ባለ ቀለም
አወል ነው ሲፈጠር
ቀለም ለዚህ አለም
ፃፍ ሲባል ጀመረ
ጥበብን ፈጠረ
አንብብ ሲባል ቆመ
ፍርድን አስተማረ

አንተ ባለቀለም
አንቺ ባለቀለም
ከአላህ የተዋስነው
ቀለም አላለቀም
የእጃችን አሻራ
ስሜት አልፈጠረም?

@bintsumi
❤3
Audio
MediaConvert
❤1
አረ ወገን ሚስጥር ወጥቷል😀የሻይ ፍቅሬን ማን ነግሮት ይሁን?🤔....

ብቻ ምን ለማለት ነው በዚህ ከቀጠሉ እኛ ሰዋች የ AI ጀምዕ ቡና መጠጫ መሆናችን አይቀርም።ሀሜት ጀምረዋል ወገን!

የእኔን ቁጣ እንደ ሻይ ጠጥቷል😭እናንተም እየጠጣችሁ🤣
😁4❤1
[ሱሚ ማማይ]

ቀስ..
ሸርተት..
ቁልቁል መፈናጠጥ
በጨዋታ ማምለጥ
ወድቆ መንገዳገድ
በከፍታ መንገድ

መቼ ነበር
ከደጁ ላይ የቀረሁት
በስንፍና ያረፈድኩት
በልማዴ የታከትኩት
መቼ ነበር የሸሸሁት

ቀላል ነበር አላህ ማለት
አላስቻለኝ ደጁ መቅረት
እንዳልነቃው በእሱ ጥሪ
ጠናኝ መዋል ከፈጣሪ
እሱን ይዤ ዳገት ወጣሁ
መቆም ስችል በእራስ ኮራሁ
ተንሸራተትኩ ከከፍታ
አላቆመኝ የእኔ እርዳታ
ጠናኝ መልመድ በከፍታ
ካደኝ ጉልበት ለእኔ ፈንታ
አልታዘዘኝ አካል ደሜ
ከፈጣሪ አሳድሜ
አልበረታሁ በመውደዴ
ጠጠለፍኩኝ በእራስ ፍርዴ

ያኔ ሳለሁ በከፍታ
ቁልቁል ቆሜ ስበረታ
ፈራጅ ነበርኩ በሰው ገላ
ከጌታው ጋር በተጣላ
እገረም ነበር በሰው ተድላ
ከሰይጣን ጋር በሚጉላላ
ዳገት ጠንቶኝ ስቀር ቁልቁል
ገባኝ መቻል እንዳልሆነ በሰው በኩል

@bintsumi
❤3🔥1
Audio
MediaConvert
❤3
Audio
MediaConvert
@bintsumi
ነይ ማ 😍
❤4🥰1
ሱሚ፡ እንቆቅልሽ?

Members፡ ምን አውቅልሽ?
ሱሚ፡ ሊያዩኝ አይችሉም፣
ሊይዙኝም አይችሉም
ነገር ግን ያጡኛል ...who am i?

members....?

ሽልማት የለውም ጭብጨባ ሰላለው ሞክሩ ማ 🤔
👏3