ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
33.8K subscribers
878 photos
12 videos
16 files
646 links
በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡
Download Telegram
#ጥር_7 - #ቅድስት_ሥላሴ

በዚህች ቀን ቅድስት ሥላሴ በኃጢአት የተገነባውን የሰናዖርን ግንብ ያፈረሱበት አንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን የገለጹበት ቀን ነው።

ሰናዖር በአሁኑ ኢራቅ አካባቢ እንደነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም ለንጉሡም በተመሳሳይ በመጠሪያነት ያገለግል ነበር፡፡ ከናምሩድ ክፋት በኋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ፡፡ ከጥፋት ውሃ በኋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በእርሳቸው "ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ፣ በዚያውም አባቶቻችንን በውኃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው" ተባባሉ፡፡ ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ ጦርም እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወረወሩ፡፡

በዚያን ጊዜ ምድር ሁሉ በአንድ ቋንቋ በምትናገርበት ወቅት፤ እግዚአብሔር የአዳም ልጆች በኃጢአት የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። እግዚአብሔርም አለ። "ኑ፥ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።" አለ ከለዳውያንም ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቋንቋዎች ተፈጠሩ፡፡ እነርሱም ስምምነት አጥተው በምድር ሁሉ ላይ ተበተኑ፡፡ ከተማይቱንም መሥራት ተዉ። የከተማዋም ስም ባቢሎን ተባለ። (ዘፍጥረት 11፥1)

በዚህም “እግዘአብሔርም አለ” አንድነታቸውን ሲያጠይቅ "ኑ እንውረድ" በማለት ሦስትነታቸውን ገልጸውልናል። ሦስትነታቸው እንዴት ነው ቢሉ፦ ሥላሴ በስም በአካል በግብር ሶስት ናቸው። የስም ሦስትነታቸው አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ በመባል ነው። የግብር ሶስትነታቸው አብ ወላዲ፣ ወልድ ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ ነው። የአካል ሶስትነታቸው ለአብ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው፣ ለወልድም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው፣ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው። የሥላሴ ገጽ አካል ፊት እንደ ሰው ነውን ቢሉ አዎን እንደ ሰው ነው ነገር ግን የሰው ውሱን ጠባብ ፈራሽና በስባሽ ነው የሥላሴ ግን እንዲህ አይደለም በሰማይና በምድር በአየርና በእመቅ የመላ ረቂቅ ህያው ባህርይ ነው (ኢሳ 66፥1)። በማለት ስንዱዋ ተዋህዶ አንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን የገለጹበትን ምስጢር ታመሳጥራለች ታስተምራለች።

የቅድስት ሥላሴ ረድኤት በረከትና ጥበቃ ከሁላችን ጋር ይሁን።

@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
#ጥር_7

#በዓለ_ሥሉስ_ቅዱስ

ጥር ሰባት በዚች ቀን በዓለ ሥላሴ የሚከበረው ስለ ሁለት ምክንያቶች ነው:: ቀዳሚው ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው ሲሆን ሌላው ደግሞ ቅዳሴ ቤታቸው ነው::

#ሕንጻ_ሰናዖር
ሰናዖር ከሺዎች ዓመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደ ነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም: ለንጉሡም በተመሳሳይ ያገለግል ነበር:: ከናምሩድ ክፋት በሁዋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ::

ከጥፋት ውሃ (ከኖኅ ዕረፍት) በሁዋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በርሳቸው "ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ:: በዚያውም አባቶቻችን በውሃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው" ተባባሉ::

ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ:: ከሕንጻው መርዘም የተነሳ በጸሐይ አብስለው በልተዋል ይባላል:: ቀጥለውም ጦር እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወርውረዋል::

መቼም የእነዚህን ሰዎች ክፋትና ቂልነት ስንሰማ ይገርመን ይሆናል:: ግንኮ ዛሬ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም እየተሠራ ያለው ከዚህ የከፋ ነው:: ቸርነቱ ቢጠብቀን እንጂ እንደ ክፋታችንስ ጠፊ ነበርን::

ርሕሩሐን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም:: የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና:: ይልቁኑ "ንዑ ንረድ ወንክአው ነገሮሙ ለከለዳውያን-ቁዋንቁዋቸው እንደባልቀው" አሉ እንጂ::

ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቁዋንቁዎች ተፈጠሩ:: እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ:: ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት:: ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው "ባቢሎን (ዝሩት)" ሲባል ይኖራል::

#ቅዳሴ_ቤት
ልክ የዛሬ 324 ዓመት አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮዽያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት (በ1684 ዓ.ም) በጐንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሰርታ ተጠናቃለች::

ጥር 7 ቀንም ሊቁ ክፍለ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን: ሠራዊት: መሣፍንትና ሊቃውንት ባሉበት ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል:: በዕለቱም ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: ኢያሱ አድያም ሰገድ ኃያል: ደግ: ጥበበኛ: አስተዋይ: መናኝ ንጉሥ ነውና::

ቤተ ሥላሴን አስጊጿታልና ከዚህ ቀን ጀምሮ ጥር ሥላሴ በድምቀት የሚከበር ሆኗል:: ነገር ግን በተሠራች በ16 ዓመቷ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል:: ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ.ም በልጁ በአፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው::

ከበዓሉ በረከት ይክፈለን

(#ስንክሳር_ዘተዋሕዶ እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን። አሜን።

( https://t.me/sinksarzetewahido )