E-LMIS - ብቁ
93.5K subscribers
341 photos
17 videos
1 file
155 links
ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ
Download Telegram
ቅንጅት ለላቀ የሥራ ስኬት!

ለሃገር አቀፍ የግብርና ናሙና ቆጠራ በቴክኖሎጂ ታግዞ የተደረገው የሰው ሃይል ምልመላን በተመለከተ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር መስሪያቤታችን ከኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር በከር ሻሌ (ዶ/ር) ጋር እንዲሁም ከሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ጋር የምልመላ ሂደቱን በተመለከተ ግምገማ አድርገናል።

በሚኒስትር መስሪያቤታችን ስር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት E-LMIS ሲስተም በኩል 43,500 ሰራተኞችን ለመመልመል በታቀደው መሰረት በአምስት የሥራ ቀናት ብቻ ከ200 ሺህ በላይ አመልካች የተመዘገበ ሲሆን በቴክኖሎጂው ትሩፋት ከአድሎአዊ አሰራር የፀዳ፣ ቀልጣፋና ግዜን እንዲሁም ጉልበትን ቆጣቢ የሆነ የምልመላ ሂደስ መታየቱ በቀጣይ በቅንጅት ለምንሰራቸው ሥራዎች የላቀ የራስ መተማመንን አጎናፅፎናል።

ምልመላውን ልዩ የሚያደርገው በኢትዮጵያ ወይም በአዲስ አበባ ተብሎ የሚጠቀስ ሳይሆን በሁሉም ክልሎች ላይ እያንዳንዱን ቀበሌ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የተከናወነ መሆኑ ምልመላውን ከባድ ያደርገዋል። በዚህም መሠረት የሥራ መሥፈርቱን ያሟሉ 73,000 እጩ አመልካቾች ወደ ቀጣዩ ፈተና ተዘዋውረዋል። በቀጣይም በስልካቸው በአጭር የፅሁፍ መልዕክት በሚደርሳቸው የፅሁፍ ፈተና ለሥራው ብቁ የሆኑትን የምንለይ ይሆናል።

ይህን የቅጥር ሂደት በአነስተኛ ወጪ፣ በጣም አጭር በሆነ ጊዜ ውስጥ፣ ብቁ ሠራተኛ በዚህ ከፍተኛ የሰው ሃይል ቁጥር ልክ ማቅረብ መቻሉ በተጨማሪም ቀጣሪም ሆነ አመልካች ሳይጉላላ ጥራት ያለው አገልግሎት መሥጠት መቻሉ ትልቅ ስኬትና የሥራችን ውጤት በመሆኑ ኩራት ይሰማናል።

የሥራ ባለቤት እርስዎ ኖት!
ነሐሴ 9/2016 ግ.ም
የሥራ ማስታወቂያ!

Agri-MSMEs Development for Jobs (AMD4J) በኢትዮጵያ ውስጥ ሴቶችና ወጣቶች የሚመሩትን ቢዝነስ እና ኢንተርፕርነርሽፕ እድገትና ምርታማነት በተሻለ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የንግድ እድገት ድጋፍ እና የተጠናከረ ኢንተርፕርነርሽፕ ለማበረታታት እየሰራ ባለው ፕሮጀክት በፕሮጀክት ኮኦርድኔተር፣ በፕሮክሩትመንት ኦፊሰር፣ በፕሮጀክት ፋይናንስ ኦፊሰር እና በአካውንቲንግ ክለርክ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

በተጠቀሰው የሥራ መደብ ለመወዳዳር በቅድሚያ በሥራና ክህሎት ሚኒስትር በለማው የኢትዮጵያ ሥራገበያ መረጃ ሥርዓት E-LMIS ተመዝግቦ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመሥጠት የሠራተኛነት መለያ ቁጥር የያዘ መሆን ይጠበቅበታል።

1. ለፕሮጀክት ኮኦርድኔተር
መስፈርት
-በዴቨሎፕመንት ኮርሶች ወይም በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ወይም በተዛማጅ ሞያዎች ማስተርስ ዲግሪ ያለው።
-በትንሹ የ10 አመት የስራ ልምድ በፕሮጀክት ማኔጅመንት፣ በፕሮጀክት አስተባባሪነት፣ በኢንተርፕራይዝ ዴቨሎፕመንት ወይም MSME ላይ በአጋዥነት ያለው

2. በፕሮክሩመንት ኦፊሰር
መስፈርት
- ማስተርስ በፕሮክሩመንት ወይም በሰፕላይ ማኔጅመንት ፊልድ
- የሥራ ልምድ በትንሹ የ6 አመት የሥራ ልምድ ያለው

መስፈርት ለፕሮጀክት ፋይናንስ ኦፊሰር
-ማስተርስ ዲግሪ በአካውንቲንግ ወይም አካውንቲንግ ኤንድ ፋይናንስ ወይም ፋይናንስ እና ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ወይም ቢዝነስ ማኔጅመንት
- በትንሹ የ8 አመት የሥራ ልምድ ያለው

3. ለአካውንቲንግ ክለርክ
መስፈርት
- በአካውንቲንግ ዲግሪ ያለው
- በትንሹ የ4 አመት የሥራ ልምድ ያለው

ደሞዝ:- በመስሪያቤቱ የደሞዝ ስኬል መሰረት
የሥራ ቦታ:- በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በፕሮጀክት ትግበራ ክፍል ውስጥ
ፃታ:- አይለይም ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ
ተፈላጊ ሰራተኛ:- አንድ
ሥራው በኮንትራት ለ12ወራት የሚቆይ ሲሆን እንደ ሠራተኛው የሥራ ችሎታ እና ብቁነት የሚሻሻል ይሆናል።

መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች የሥራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት ማስረጃችሁን እስካን አድርጋችሁ ከታች በተቀመጠው ኢሜል ማስገባት ትችላላችሁ።

yseid85@yahoo.com/tseget26@gmail.com


ይህንን የሥራ ማስታወቂያ እና መሰል ተጨማሪ የሥራ እድሎችን ለመጎብኘት lmis.gov.et ይጎብኙ!

የሥራ ባለቤት እርስዎ ኖት!
ማስታወቂያ!
ከሲውዲኑ ሜልዮን ካምፓኒ!

በሥራና ክህሎት ሚኒስትር የለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ELMIS በሰለጠና በከፊል በሰለጠነ የሠው ሃይል ወደ ውጪ ሃገራት ለሥራ እያሰማራ ይገኛል።

በዚህም መሠረት በሰለጠነ የሰው ሃይል ከሲውዲንና ከኖርዌይ የሥራ እድሎች ወደ ሲስተሙ እየገቡ ይገኛሉ። በመሆኑም የሲውዲኑ ሜልዮን ካምፓኒ ባቀረበው የሠራተኛ ጥያቄ መሠረት በሲስተሙ ላይ መሥፈርቱን አሟልታችሁ ለተገኛችሁ ዜጎች አጭር የፅሁፍ መልዕክት በሥልክ ቁጥራችሁ አድርሰናል።

ይህ የደረሳችሁ መልዕክት ላይ ያለው ሊንክ ምንነትና እና በምን መልኩ ይህንን ሂደት መጨረስ እችላለሁ የሚል ጥያቄ ሊፈጠር ስለሚችል ይህ ቪዲዮ የፅሁፍ መልዕክቱ ለደረሳችሁ ይሆናል።

ይህ መልዕክት የሚደርሰው በ lmis.gov.et ላይ ለተመዘገበ ብቻ በመሆኑ ያልተመዘገባችሁ አሁኑኑ ተመዝግባችሁ የሥራ እድሎቹ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ስንል እናሳውቃለን።

ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ!
💼የሥራ ባለቤት እርስዎ ኖት!
🌏በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ መረጃ አገልግሎት የሥራ ቅጥር ሂደት ለተነሱ ጥያቄዎች የተሰጠ ማብራሪያ!

የኢትዮጲያ ስታትስቲክ መረጃ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት በሃገራችን ለሚያከናውነው የግብርና ናሙና ቆጠራ መረጃ ለመሰብሰብ 43,500 ሰራተኞችን ቅጥር በE-LMIS በኩል ፈፅሟል።
አጠቃላይ የሰራተኞች ቅጥር ሂደት በምን መልኩ ተከናወነ?

ተመልምለው የፅሁፍ መልዕክት ደርሷቸው ፈተና የተፈተኑ እያሉ ያልተመለመሉና የፅሁፍ መልዕክት ያልደረሳቸው አልፋችኋል የሚል መልዕክት ደርሷቸዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ገለፃ ቢደረግ።

በቀጣይ በዚህ ሲስተም ሠራተኛ የሚቀጥሩ ድርጅቶች በምን መልኩ ተጠቃሚ ይሆናሉ? አጠቃላይ የሲስተሙስ ፋይዳ ምንድን ነው? ለሚሉት ጥያቄዎች ከE-LMIS ኦፕሬሽናል ማናጀር ኤርሚያስ ተክሉ የተሰጡ ማብራሪያዎችን ይህንን ሊንክ ተጭነው ይመልከቱ።
: https://www.youtube.com/watch?v=jxncalnuCcY
🌏በውጪ ሃገር ስራ ስምሪት ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎችን ምላሽ ማግኘት የምትችሉበት ልዩ ፕሮግራም በNBC!

⚡️እንዴት እንመዝገብ?
⚡️እንዴት የውጪ ሃገር ስምሪቱ ላይ መሳተፍ እንችላለን?
⚡️የውጪ ሃገር ሥራ ሥምሪት ሥልጠና የት ይገኛል? የሥልጠና አሰጣጡስ ምን ይመስላል?
⚡️የውጪ ሃገር የሥራ ስምሪት ከዜጎች ደህንነት እና ጥቅም አኳያ ፋይዳው ምን ያህል ነው?
⚡️ከዚህ ቀደም የነበረውን የውጪ ሃገር ጉዞ ስርዓት በምን ያህል ደረጃ ቀላል አድርጎታል? እና የመሳሰሉ የብዙ ጥያቄዎችን ምላሽ የምታገኙበት ልዩ ፕሮግራም በNBC ቀርቦላችኋል።

አሁኑኑ ይህንን ሊንክ በመንካት ሥለ የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (ELMIS) በጥልቀት ይወቁ!

https://youtu.be/HxmJuHLm-1E?si=mkvXe7rJEDwi_qFH


ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ!
💼የሥራ ባለቤት እርስዎ ኖት!
🌏በዚህ ወር የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት እድል እንዳያመልጥዎት!! ይፍጠኑ!!

በሥራና ክህሎት ሚኒስትር በቀረበው የውጪ ሃገር ስራ ሥምሪት ዜጎች ደህንነታቸው ተጠብቆ መብትና ጥቅማቸው ተረጋግጦ መሥራት የሚችሉበት መንገድ ተመቻችቷል።
ይህ እድል በሰለጠነም በከፊል በሰለጠነም የሰው ሃይል በብዙ የሞያ ዘርፎች ማለትም፡
•  የቤት ውስጥ ተንከባካቢ ነርስ (ዲፕሎማ/ በጤና ኤክስቴንሸን ያለፉ)
•  ሹፍርና፣ (የአጭር ቀናት upskill certify በመሆን)
•  ምግብ አብሳይ፣ (በዘርፉ የሰለጠነና ሰርተፊኬት ያለው) (ልምድ ያላቹ የአጭር ቀናት upskill certify)
•  ሴኪዩሪቲ፣ (በዘርፉ የሰለጠነና ሰርተፊኬት ያለው ውይም በህግ አስከባሪ ተቋማት ውስጥ ያለፈ)
•  አስተናጋጅ (በዘርፉ የሰለጠነና ሰርተፊኬት ያለው)(ልምድ ያላቹ የአጭር ቀናት upskill certify)  እና ሌሎች የሞያ ዘርፎችን ያካተተ ሲሆን ዜጎች የአንድ ወር ግዜው ሳያመልጣቹ በፍጥነት በ www.lmis.gov.et ምዝገባ በመጨረስ የእድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ!! እንዳያመልጥዎ!!

ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ!
💼የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
ድህረ-ገፃችንን ይጎብኙ ይመዝገቡ  :https://lmis.gov.et

💼 ቴሌግራም ፡ https://t.me/bequelmis1

📢 ሊንክደን   : https://www.linkedin.com/company/86463026/admin/feed/posts/

🎥 ዩቲዩብ ፡: https://www.youtube.com/channel/UCiIzqvMmVHMH9g61rc9nX7Q
🌍💫ለግል ማሰልጠኛ ተቋማት እና በዘርፉ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር በውጪ ሃገር ስራ ስምሪት የዜጎችን ደህንነት፣ መብት እና ጥቅም አስጠብቆ ወደ ተለያዩ ሃገራት እያሰማራ ይገኛል። በመሆኑም ዜጎች ከሃገር ሲወጡ ሠልጥነው በሚሄዱበት ቦታ ብቁ ሆነው መገኘት እንዲችሉ በሃገር ውስጥ ሥልጠናዎችን ሲያመቻች ቆይቷል።
ነገር ግን በአሁን በጥቅል የመንግስት እና የግል የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ስልጠና ተቋማት ብዛት አነስተኛ መሆኑን ተከትሎ ከውጪ ሃገራት እየመጣ ያለው የሰው ሃይል ፍላጎት/ጥያቄ በየግዜው መጨመር በማሳየቱ በተለይ ነርስ፣ ሹፍርና፣ የቤት ውስጥ ተንከባካቢ ነርስ፣ ምግብ አብሳይ፣ ሴኪዩሪቲ፣ አስተናጋጅ ዘርፎች ሚንስቴር መስሪያ ቤታችን ወደዚህ ስራ ያልገባቹ የግል ማሰልጠኛ ማዐከላትን እንድትገቡ እንዲሁም በዘርፉ መሳተፍ ለምትፈልጉ ባለሃብቶች ይህንን ትልቅ እድል እንድትጠቀሙ እያልለ ከሚነስቴር መስሪያ ቤታችን የሚፈለግ ማንኛውንም ድጋፍ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናችንን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!

ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ!
ድህረ-ገፃችንን ይጎብኙ ይመዝገቡ  :https://lmis.gov.et

💼 ቴሌግራም ፡ https://t.me/bequelmis1

📢 ሊንክደን   : https://www.linkedin.com/company/86463026/admin/feed/posts/

🎥 ዩቲዩብ ፡: https://www.youtube.com/channel/UCiIzqvMmVHMH9g61rc9nX7Q
🌍💫በE-LMIS የE-Learning አገልግሎት መምህራን ወደ ሲስተሙ እንዴት ኮርስ መጫን እንደምትችሉ ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ እየነካችሁ የማሳያ ቪዲዩውን ተመልከቱ።

https://youtu.be/NweE1EHicsI?si=SVqUxVZ8vBDTtN2g
የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪትን በተመለከተ ለሚነሱ ጥያቄዎች ነፃ የስልክ መሥመር ይጠቀሙ!

በሥራና ክህሎት ሚኒስትር የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት የዜጎችን ደህንነት፣ መብትና ክብር አስጠብቆ ወደ ተለያዩ ሃገራት እያሰማራ እንደሆነ ይታወቃል። በመሆኑም የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪትን በተመለከተ መጠየቅ የሚፈልጉትን ማንኛውንም ጥያቄ ☎️9138 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ማቅረብ እንደሚችሉ እንገልፃለን!

የሥራ ባለቤት እርስዎ ንዎት!
Agency-Active-Countries - Agncy-Active-Countries.csv (1).pdf
286.1 KB
🌏በውጪ ሃገር ስራ ስምሪት የህጋዊ ኤጀንሲዎችን ዝርዝር ለምትፈልጉ በሙሉ!

በሥራና ክህሎት ሚኒስትር የውጪ ሃገር ስራ ስምሪት ዜጎች መብታቸው፣ ደህንነታቸው እና ክብራቸው ተጠብቆ እየተሰማሩ እንደሆነ ይታወቃል። ለዚህ ህጋዊ የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት lmis.gov.et ብላችሁ በመመዝገብ አቅራቢያችሁ በሚገኝ የአንድ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ሄዳችሁ የባዩሜትሪክስ መረጃ ሰጥታችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ በሞያ ዘርፋችሁ የአጭር ግዜ ሥልጠና በመውሰድ የብቃት ማረጋገጫ (COC) ካገኛችሁ የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት እድሉን ለመጠቀም ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘረውን ህጋዊ ኤጀንሲዎች በማግኘት ፕሮሰሱን መጀመር ትችላላችሁ!

በዚህ የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት ከፓስፓርት፣ ሜዲካል ምርመራና የሥልጠና ክፍያ ውጪ ምንም አይነት ክፍያ የማይከፈል ነፃ መሆኑን አውቃችሁ ተጨማሪ ክፍያ የሚጠይቋቹ ኤጀንሲዎች ካጋጠሟቹ pfs.mols.gov ላይ ወይም በ9138 ነፃ የሥልክ መስመር ጥቆማ መስጠት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
ማስጠንቀቂያ‼️

ለሥራ ወደ ውጪ ሃገራት መጓዝ ለምትፈልጉ በአጭር ግዜ ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት እናደርሳለን የሚሉ በተለይ ወደ ካናዳ እንልካለን እያሉ በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ስምና ሎጎ በመጠቀም ማስታወቂያ እያሰራጩ በማታለል ተግባር ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ተበራክተዋል።

በመሆኑም በሥራና ክህሎት ሚኒስትር የቀረበው የውጪ ሃገር የሥራ ስምሪት ከፓስፓርት፣ የሥልጠና እና የሜዲካል ምርመራ ውጪ ምንም አይነት ክፍያ የሌለው ሙሉ ነፃ መሆኑን ተገንዝባችሁ ቅድመ ክፍያ እየጠየቁ ከሚያጭበረብሩ ግለሰቦች እራሳችሁን እንድትጠብቁ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ያሳስባል።


በተያያዘ በዚህ የውጪ ሃገር ስራ ስምሪት እድል ለመጠቀም lmis.gov.et ብላችሁ ሲስተሙ ላይ ከተመዘገባችሁ በኋላ አቅራቢያችሁ በሚገኝ የአንድ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመሄድ የባዩሜትሪክስ መረጃ በመስጠት ሥልጠና መጀመር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ!
💼የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
ድህረ-ገፃችንን ይጎብኙ ይመዝገቡ  :https://lmis.gov.et

💼 ቴሌግራም ፡ https://t.me/bequelmis1

📢 ሊንክደን   : https://www.linkedin.com/company/86463026/admin/feed/posts/

🎥 ዩቲዩብ ፡: https://www.youtube.com/channel/UCiIzqvMmVHMH9g61rc9nX7Q
🌍ኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ E-LMIS ምዝገባ ተጀምሯል!

በሥራና ክህሎት ሚኒሰትር በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት ሁሉም በሃገር ውስጥ የሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በስሩ የሚገኙ ሰራተኞችን በE-LMIS ስርዓት ላይ እያስመዘገቡ ይገኛሉ። የኢንዱስትሪ ፓርኩ ሰራተኞቹን በማስመዝገቡ የሚያገኛቸው ጥቅሞችም:-

ኢንዱስትሪ ፓርክ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽዎ ከሚያበረክቱ ሴክተሮች መካከል በቀዳሚነት ተጠቃሽ ሲሆን በሁሉም ክልል እና ከተማ መስተዳደር ስር በተለያየ የሙያ ዘርፍ ላይ ዜጎችን በማሰማራት ለብዙኅን የስራ እድል መፍጠር ችሏል። በመሆኑም በስሩ የሚሰሩትን ሰራተኞች የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር መ/ቤት ባበለጸገው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ በባዮሜትሪክስ የታገዘ ምዝገባ በማድረግ፤ የሁሉንም ሰራተኞች የት/ት ዝግጅት፣ የስራ ልምድ፣ ያላቸውን ክህሎት እንዲሁም የሰራተኞቻቸውን ማንኛውም ከስራ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች በአንድ ቋት ስር ማግኘት እንዲቻል ይረዳል። ይህም እንደ ሴክተር ከሰራተኛ አስተዳደር ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ችግሮች ቁልፍ መፍትሄ በመሆን ዘርፉን በተሻለ መንገድ ለመምራት እና ለማስተዳደር የሚያስችል አቅምን ይሰጣል።
ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ!
💼የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
ድህረ-ገፃችንን ይጎብኙ ይመዝገቡ :https://lmis.gov.et

👍 ፌስቡክ : https://www.facebook.com/profile.php?id=61555705001836

💼 ቴሌግራም ፡ https://t.me/bequelmis1

📢 ሊንክደን : https://www.linkedin.com/company/86463026/admin/feed/posts/
🌏በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ለወጣቶች የቀረበ ልዩ ዕድል!

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የራሳቸውን ሥራ መሥራት ለሚፈልጉ እንዲሁም ሥራ በመፈለግ ላይ ላሉ ወጣቶች የራሳቸውን ሥራ ብቻ ሳይሆን ተደራጅተው መሥራት የሚችሉበትን ትልቅ ዕድል አመቻችቶ እንሆ ይልዎታል።

ይህ ዕድል በገንዘብ፣ በሥልጠና እና በቦታ ከክልልና ከከተማ መስተዳደሮች ጋር በህብረት በተቀናጀ መንገድ የሚሰራ በመሆኑ እንዳያመልጥዎ አሁኑኑ E-LMIS ስርዓት ውስጥ በመግባት መረጃችሁን በመሙላት በሚላክላችሁ የፅሁፍ መልዕክት የሳይኮሜትሪክ ምዘና ወስዳችሁ በወሰዳችሁት የምዘና ውጤት መሰረት ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በመሆን ብድር እስከማመቻቸት የደረሰ እድል ስለተመቻቸ እንድትጠቀሙ ስንል እንገልፃለን።

በቅድሚያ ግን lmis.gov.et ላይ ተመዝግባችሁ የባዩሜትሪክስ መረጃ
በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር ካገኛችሁ በኋላ በፅሁፍ መልዕክት በሚላክላችሁ ሊንክ በመግባት የሳይኮሜትሪክ ምዘና ወስዳችሁ ስትጨርሱ የዚህ እድል ተጠቃሚ ትሆናላችሁ።

ይህንን መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የእድሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያድርጉ።

ይመዝገቡ  :https://lmis.gov.et

👍 ፌስቡክ  : https://www.facebook.com/profile.php?id=61555705001836

💼 ቴሌግራም ፡ https://t.me/bequelmis1

📢 ሊንክደን   : https://www.linkedin.com/company/86463026/admin/feed/posts/

🎥 ዩቲዩብ ፡: https://www.youtube.com/channel/UCiIzqvMmVHMH9g61rc9nX7Q