State of Amhara (ነጣ የዐማራ መንግስት)
436 subscribers
64 photos
5 videos
15 links
Download Telegram
ዐማራው ሞት ለዐማራ ብሔርተኝነት ፤ ድል ኢትዮጵያ አንድነት ቢልም የሞት ዘመን ቢያስረዝም እንጅ የሚያገኘው ፖለቲካዊም ሆነ ፤ ዐማራዊ ትርፍ የለውም ‼️

በጸረ ሴማዊ እንቅስቃሴ ወቅት በአውሮፓ የሚኖር ይሁዲ ሁሉ የግድያ ምልክት ተሰጥቶት ነበር። ያ የግድያ ምልክት ድሬይፉስ የሚባል የሚባልሰው ላይ ደረሰ። ድሬይፉስ በፈረንሳይ የሚኖር ይሁዲ ነበር አሉ። ይሁዲነቱ ለጥቃት አጋለጠው። ያለ ጥፋቱ “ከውጭ ከጀርመን ጋራ ተመሳጥረሃል” ተባለ። "ከጀርመን ጋር ተመሳጥረሃል" ያሉት በይሁዲነቱ ሊገድሉት ምክንያት ሲፈጥሩለት ነው። ከቀናትም በኋላ የነበረዎ ማዕርግ ተገፈፈ፣ በአደባባይ ተዋረደ፣ ተገረፈ። ድሬይፉስ ግን “ንጹህ ነኝ፥ ንጹህ ነኝ የማውቀው ነገር የለም ብሎ ማለ። ያምኑት ዘንድም "ድል ለፈረንሳይ” እያለ እጁን ዘረጋ። ግን ምን ያደርጋል ይሁዲ ነው። ምንም ቢል ከጸረ ሴማዊ አሳዳጆች አይተርፍም። በከንቱ ጉንጩን አለፋ ! እውነቱን የሚሰማው አልነበረም።

በጸረ ሴማዊ እንቅስቃሴ ወቅት በአውሮፓ የሚኖር ይሁዲ ሁሉ የግድያ ምልክት ተሰጥቶት ነበር። ያ የግድያ ምልክት ድሬይፉስ የሚባል የሚባልሰው ላይ ደረሰ። ድሬይፉስ በፈረንሳይ የሚኖር ይሁዲ ነበር አሉ። ይሁዲነቱ ለጥቃት አጋለጠው። ያለ ጥፋቱ “ከውጭ ከጀርመን ጋራ ተመሳጥረሃል” ተባለ። "ከጀርመን ጋር ተመሳጥረሃል" ያሉት በይሁዲነቱ ሊገድሉት ምክንያት ሲፈጥሩለት ነው። ከቀናትም በኋላ የነበረዎ ማዕርግ ተገፈፈ፣ በአደባባይ ተዋረደ፣ ተገረፈ። ድሬይፉስ ግን “ንጹህ ነኝ፥ ንጹህ ነኝ የማውቀው ነገር የለም ብሎ ማለ። ያምኑት ዘንድም "ድል ለፈረንሳይ” እያለ እጁን ዘረጋ። ግን ምን ያደርጋል ይሁዲ ነው። እውነቱን የሚሰማው/የሚቀበለው አልነበረም።

ድሬይፉስ ይሄን ሁሉ ማንነታዊ ጥቃት ሲያስተናግድ፣ ማንነቱን ክዶም "ድል ለፈረንሳይ" ቢል ከጸረ ሴማዊ አዳኞች መትረፍ ከልቻለም። ይህን ጊዜ አንድ ጋዜጠኛ ግን ሁነቱን ይከታተል ነበር። ጋዜጠኛው ቴዎዶር ሄርጽል ነው። ይህ ይሁዲ ሲዘለፍ፥ ሲሰደብና ሲዳፋ ይህ ጋዜጠኛ ይሁዲ ሁነቱን ይከታተል/ ይመለከት ነበር። ከሁሉም በላይ ከተሰነዘሩ ስድቦች መካከል “ሞት ለአይሁድ” የሚለው ከጋዜጠኛው ከቴዎዶር ሄርጽል አእምሮ ውስጥ ሳይወጣ አቃጨለበት። "ሞት ለአይሁድ" የሚለውን ድምጽ ከሰማ በኋላ ሄርጽል እጁን አጣጥፎ አልተቀመጠም። ይበልጥ ግን ለአይሁድ ሀገር ምሥረታ ተጋ። ተሳዳቢዎች ባይኖሩ፥ የድሬይፉስ መዋረድ ባይኖር ይህ ታላቅ ጽዮናዊ ስለ አይሁድ ሀገር ባላሰበና በተዘናጋ ነበር። ከድሬይፉስ ፍርድ በኋላ በሁለተኛው ዓመት ሄርጽል በባስል የመጀመሪያውን የጽዮናውያን ሸንጎ ስለ ማካሄዱ እንዲህ ሲል ማስታወሻውን ከተበ። “በባስል የአይሁድን ሀገር መሠረትኩ። ዛሬ ይህን በጉልህ ብናገር፥ በሁሉም ዘንድ በሳቅ ይመለስልኝ ይሆናል። ምናልባት በአምስት ዓመት ውስጥ፥ በርግጥም በሀምሳ፥ ሁሉም ይህን የዛሬ ንግግሬን ይረዳል። ለአይሁድ ሀገር ምስረታ በጽናት መነሳት አለብን ይሄን ካላደረግን በህይወት ለዘር አንተርፍም” ሲል ንግግሩን ቋጨ።

ቴዎዶር ሄርጽል ይሄን ጉባኤው 1897 አደረገ። እሥራኤል ደግሞ በ1948 ዓ.እ ተመሠረተች። ከሀምሳ አንድ ዓመት በኋላ ማለት ነው። ይህ ሰው ትንቢተኛ ነው ይሉታል። በቤተ መንግሥቱ ግድግዳ የዚህ ትምቢተኛ ፎቶና ስም ተሰቅሏል፣ ከሀገሪቱ ብሔራዊ መዝሙር ከፍ ተደርጎ ይዘመራል። ያ ቀልድ የሚመስለው የቴዎዶር ሄርጽል ንግግር ይሄው እውን ሆነ።

ዐማራ በዐማራ ፖለቲካ ላይ የማይጸና ከሆነና በራሱ የፖለቲካ እግር ካልቆመ "የዐማራ ብሔርተኛ" ነኝ የሚለውን ቀልድ ፤ ቀልዱም በዐማራ ህዝብ ላይ መቀለድ ነው !
1
ዐማራን ዐማራ የማድረግ ፖለቲካ የዐማራ ብሔርተኝነት ሲባል የሚገነባውም በፖለቲከኛ ዐማራዎች ሳይሆን በብሔርተኛ ዐማራዎች ነው ‼️

የዘር ማጥፋት ድርጊት በዓለም ላይ ከጀመረ ብዙ ምዕተ ዓመታትን እንዳስቆጠረ የታሪክ ድርሳናት ይናገራሉ። የዘር ማጥፋት ድርጊት በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ወንጀል ሁኖ ከተመዘገበ ግን ገና አንድ መቶ ዓመት እንኳን አላስቆጠረም። በዓለም አቀፍ መድረክ ዘንድ የዘር ማጥፋት (Genocide) ወንጀል ነው ተብሎ ስያሜ የተሰጠው ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ነው። የዘር ማጥፋት ድርጊት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፊት በላቲን አሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ፣ በአፍሪካ ውስጥ ሲፈጸም ነበር። ይሄ የዘር ማጥፋት ድርጊት ግን በዓለማቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ወንጀል ተደርጎ አልተሰየመም ነበር።

ምንም እንኮን የአይሁድ ጭፍጨፋ የዓለም የመጀመሪያው የዘርር ጭፍጨፋ ድርጊት ባይሆንም። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜአይሁድን ከመላው አውሮፓ ለማጽዳት የተፈጸመው ድርጅት በዓለምአቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ "ከባድ ወንጀል" ተብሎ እንዲተረጎም ተደርጓል። በአይሁድ ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ድርጊት የዘር ማጥፋት "ወንጀል" (Genocide) እንደሆነ በመግለጽ የጻፈው የመጀመሪያው ሰው አይሁዳዊው የፖላንድ ተወላጅ ጠበቃ ራፋኤል ለምኪን የተባለ ሰው ነው። ይህ ሰው ከናዚዎች ጭፍጨፋ ለማምለጥ ወደ አሜሪካ ሲሄድ በ1944 ሲዊድን ሆኖ "Axis Rule in Occupied Europe" የሚል መጽሐፍ ጽፎ ነበር። በዚህ መጽሐፉ ላይ በአይሁድ ህዝብ ላይ የተፈጸመው ድርጅት የዘር ማጥፋት ወንጀል አንደሆነ በማያሻማ ቃል ገልጿል።

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ጥቂት የጀርመን ናዚ ባለስልጣናት ተይዘው በኑመምበርግ ውስጥ ለፍርድ ሲቀርቡ ጉዳዩ በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲታይ ጠበቃ ለምኪን በየፍርድ ቤቱና በየችሎቱ ሀሳብ መስጠትና መከራከር ጀመረ። ይሁን እንጅ ጉዳዩን ያስቻሉት ዳኞች የናዚ ባለስልጣናትን በጦር ወንጀል ክስ ለመክሰሰ ወሰኑ። ጠበቃ ለምኪን ግን ያለአንዳች ተስፋ መቁረጥ ጫና በማድረግና ደጋግሞ ይግባኝ በማለት በተባበሩት የዓለም መንግስታት ማህበር ጀሮ አንዲሰጠውና በአይሁድ ላይ የተፈጸመው ድርጊት የዘር ማጥፋት ወንጀል ተብሎ እንዲተረጉምና ውሳኔ እንዲያገኝ፣ በመጪው ዘመንም እንደዚህ አይነት ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ ማንቂያ፣ ከተፈጸሙም ወንጀሉ በዚህ እንዲታይ መስፈሮቶችን አርቅቆ የዘር ማጥፋት ወንጀል በዓለምአቀፍ ማህረሰብ ዘንድ በ1948 "ከባድ ወንጀል" ተደርጎ እንዲደነገግ አስቿለ።

የዘር ጭፍጨፋ በዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ "ወንጀል" ተደርጎ ሲደነገግ ፥ ማሟላት ያለባቸው ተብለው የተዘረዘሩ አንቀጾች አሉት። ያም ሁኖ አንድ አንድ ሀገራት ከዚህ ቀደም የፈጸሙት የዘር ጭፍጨፋ ተብሎ ሊወሰድ የሚችል ወንጀል ሊሆን ስለሚችል አንቀጾች እንዲጠቡ እንደተደረጉ ይነገራል።

የዘር ጭፍጨፋን ወንጀልን የሚጠቁሙና ለዘር ጭፍጨፋ ወንጀል የሚያበቁ ቅድመ ድርጊቶች ውስጥ በሚዲያ፣ በሀገሪቱ ሊቃውንት፣ በመንግስት አካላት የሚደረጉ ስብዕናን የማዋረድ ድርጊት (de-humanization) ትልቁን ስፍራ ይይዛል። የዘር ጭፍጨፋ (Genocide) በአንድ ቀን ጀምበር የሚከናወን ሳይሆን ለረጅም ዓመታት ተደብኖ የሚኖር ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ ለዘር ጭፎጨፋ ይመች ዘንድ ልዩ መልክት የተሰጠውን ዘር በቀላሉ እንደ ሰደድ እሳት የሚበላ፣ ሁሉም ቦታ የሚዳረስ ነው። የዘር ጭፍጨፋ ቀስ በቀስ የሚያድግ ድርጊት (heeling-killing process) ነው። የረጅም ጊዜ ዕቅድ ተይዞ የዘር ማጥፋት ድርጊት መሆኑ ሳይነቃ አንድ በአንድ ምልክት የተሰጠውን ዘር እየገደሉ መጨረስ፣ የመንግስት ሚዲያንና አካላትን ተጠቅሞ የሞት ምልክት የተሰጡ የአንድ ዘር አባላት ቀስ በቀስ ቦታውን ለሸው እንዲሰደዱ ማድረግ የዘር ማጥፋት ድርጊት መኖሩን የሚጠቁሙ ናቸው። የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ "ስንች ሰው ሞተ?" የሚል መስፈርት የለም።

ብዙ የዘር ማጥፋት ድርጊት የታየባት ዓለም ሁሉን ጀሮ ዳባ ልበስ ብላ ኑራ ፤ በ1948 በይሁዳዊው ጠበቃ ራፋኤል ለምኪን አማካኝነት እንደዚህ አይነት ድርጊቶች ከቅድመ እንቅስቃሴ ጀምሮ እስከ ድህረ ጭፍጨፋ በየፈርጁና በየመስፈርቱ ሰንዷ የዘር ማጥፋት ወንጀልን "ምህረት አልባ ከባድ ወንጀል" በማለት በይና አልፋለች።

ዐማራ ላይ በመልክም፣ በተግባርም፣ በቁጥርም ከቅድመ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፥ ከድህረ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ከተፈጸሙ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ተከናውኗል። እስከአሁኗ ሰዓት ድረስም እየተፈጸመ ነው። ዐማራ በየሚዲያው፣ በየመንግስት መስሪያ ቤቱ፣ በየባህላት አዳራሹ ሁሉ ክብሩ፣ ስብዕናው ዝቅ ተደርጎ ተሰድቦ፣ ተዋርዷል። ከአገዳደሉ እስከ አቀባበሩ ድረስ ተዋርዷል። ዐማራ ላይ የተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ ወንጀል ተደርጎ ካልተቆጠረ ሌሎችማ ምንም ናቸው። ዐማራ በማይጨክንበት የጨከነውም ለዚህ ነው። ዐማራው ላይ የተፈጸመው ወንጀል የሚዳኘው የዓለማቀፋዊ ህግ አግባብ ነው። ፍርድ ቤቱም የተባበሩት የዓለም መንግስታት ፍርድ ቤት ነው። በሀገር ውስጥና በተወሰኑ የፖለቲካ ቡድኖች የሚያልቅ የጓዳ ውስጥ ወንጀል አይደለም። በስልጣን ርክክብም የሚካስ አይደለም። የግድ በወንጀሉ ሃላፊነት የሚወስድ አካል እና የዓለማቀፉ ማህበረሰብም በዐማራ ላይ የተፈጸመው ድርጊት አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል መሆኑን መገንዘብ አለበት። መገንዘብ ብቻም ሳይሆን እያወቁም ይሁን ሳያውቁ ዐማራን ለማጥፋት በሚደረግ ዘመቻ ከመሳሪያ ማቀበል ጀምሮ እስከ ፕሮፓጋንዳ የሰሩ የአውሮፓ፣ የአፍሪካ፣ የየመካከለኛወ ውምስራቅ ሀገራት በድርጊታቸው መጸጸት አለባቸው።
ይሄ የሚሆነው ግን በተባበሩት የዓለም መንግስታት ጫናና ፍላጎት አይደለም። እንደ ጠበቃ ራፋኤል ለምኪን አይነት ባሉ ጀግናና ዓላማ ያላቸው የዐማራ ልጆች ነው።

ዐማራ ላይ የዘር ማጥፋት ድርጊት እንዳይቆም/እንዳያበቃ፣ ወንጀሉም በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዳይዳኝ የሚያደርጉት የራሳችን ሰዎች ዐማራዎች ናቸው። በተለይም አታጋይ ነን ባይ ግለሰቦች። "ሽማግሌ በምክሩ አርበኛ በሰናድሩ" ብለው በዐማራ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በሽምግልና፣ በድርድር፣ በስልጣን ርክክብ ለመጨረስ የሚያልሙ አሉ። እንደ አዎንታዊ ምክንያት ብለው የሚያነሱት ደግሞ "ሰው ለወዳጁ ጫጩት ያርዳል" የሚል የአንድነት ፍቅር ሁነው ለኢትዮጵያ አንድነት ዐማራው ቢታረድም አይቆጨንም የሚል ነው። ዐማራ በተፈጸመበት ልክ ከጸነፈ ወችንም ወንጀሉ ላይ የሚጠብቅ ከሆነ .. ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ላትቀጥል ትችላለች፣ ከዚህ ሁሉ ከባህርዳር ዘንባባ ቆርጠን ፍቅርን ሰብከን "ስለአንድነት፣ ስለአብሮነት እና ስለፍቅር ብለን ሁሉን ተውነው ፤ ከዚህ በኋላ ሰላም ወርዷል" ብለው ታቦት አውጥተው ወይንም ከአባገዳ ዋርካ ስር መታረቅን የመሰለ የለም የሚሉ ናቸወ።

የዐማራ ትገል ወይንም ብሔርተኝነት መሰረታዊ መነሻው፦
1. በማንነቱ ላይ የተፈጸመው ዘር ተኮር ጭፍጨፋ።

2. ዐማራ ለማጥፋት ዐማራን ሀገር አልባ ለማድረግ የተደረገበት የእርስት ወረራ።

3. የዘር ፍጅቱን ተከላክሎ የዐማራን ትውልድ ማስቀጠልና ዐማራ ዳግም ለዘር ጭፍጨፋ ድርጊት ሰለባ አንዳይሆን ለማድረግ ጠንካራ ዐማራ መፍጠርና የዐማራን የዘር ፍጅት የሚከላከል ዐማራ ወዳድ ስርዓተ መንግሰትና ሀገር መትከል ነው።
👍1
መነሻችን መድረሻችንም ነወ፦ መርህ ማለት ሊታለፍ፣ ሊታጠፋ፣ ሊሻርና ሊነካ የማይገባው አደገኛ መስመር ማለት ነው። ይሄ ነው መርሃችን።

የዐማራ ትግል ከመነሻችን አንዱ ርስት ሲሆን መዳረሻችን የዐማራን ታሪካዊ ርስት እንደገና መመለስ ነው። ይሄ መዳረሻችን ነው። በኢትዮጵያ አዳራሽ ደማቅ ቀለም ተቀብቶ የዘር ማጥፋት ድርጊት የተፈጸመበት፣ ምልክት የተሰጠው ዐማራ መፍትሔ ብሎ የሚያስባቸው ከብአዴን ልብና አእምሮ ጀምሮ እስከ እያንድአንዱ ዐማራ ይለያያሉ። በዚህ የዘር ማጥፋት ድርጊት ውስጥ ያለው ዐማራ "የህልውና ጥያቄ" አለብኝ ብሎ ሲጠይቅ አይኖርም። አሁን መልስ ሊሰጥ እየታገለ ነው። አንድአንዱ የዐማራን ትግል የዐማራ የህልውና ጥያቄ ጀሮ እንዲያገኝ ማድረጊያ አድርጎ የሚቆጥረው አለ። ህልውናው የሚከበርበት መፍትሄ እየፈለገ ነው። እሱንም ራሴው እመልሰዋለሁ ብሎ ገብቷል። ከእነዚህ መፍትሄዎች ውስጥ አንዱ ዐማራ ለመጭው ረጅም ዘመን ህልውናው ተከብሮ እንዲኖር "ሀገረ መንግስት መገንባት" አለበት የሚል ነው።

ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ አንድ ጹሁፍ ሲዘዋወር ተመለከትኩ። ይሄም ጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ እንደ ይሁዲው ጠበቃ ራፋኤል ለምኪን ይሆናል ብለን ከምናስባቸው ሰዎች ውስጥ አንዱ ነወ። ይሁን እንጅ ሰሞኑን "መነሻችን ዐማራ መድረሻችን ዐማራ የሚባል ርባና ቢስና የማይጨበጥ ነገር" የእንደማያስቡ ተናግሯል። ጠበቃ አስረስ ለፖለቲካ ንግግር (political correctness) የሚባል ነገር ስላለ ይሆናል ይሄን የተናገረው። "መነሻችን ዐማራ መድረሻችን ዐማራ" በሚለው ንግግር ላያምንበትም ይችላል። እሱ ግለሰባዊ መቅቱና እምነት ወይንም አስተሳሰቡ ነው። ነገር ግን ስህተቱ "መድረሻችን ዐማራ" የሚለው ንግግርም ሆነ ዓላማ ርባና ቢስና የማይጨበጥ እንደሆነ ደፍሮ መናር ነበረበት ብዬ አላምንም። ምክንያቱም ለዚህ ዓላማ ከጎኑ ሁነው የወደቁ፣ እየተዋደቁ ያሉ ኃይሎች አሉ። በሚሊዬን የሚቆጠር ወጣት ይሄን ሀሳብ እንደሚናፍቀው ከመናፈቅም ባሻገር ዋጋ እየተከፈለበት እንዳለ፣ በአዳኝነትም የሚከተሉት እንዳሉ ግምት ውስጥ ማስገባት ነበረበት። ክፍፍል በበዛበት ፋኖ ሌላ ክፍፍል አንፈጥርም በሚል ጭምት ሀሳብ እንጅ አንድ ክፍለ ጦር ለዚህ ሀሳብ እስከ ፍጻሜና ቀራኒዮ ድረስ የሚዘልቅ የፋኖ ኃይል ማዋለድና ማቆም የሚቻልበት ሁኔታ ነበረ። መሬት ላይ ይሄ ኃይል ያለና ለዚህም የፋኖን አንድነት የሚጠብቅ፣ አሁን ላይ ይሄን ማንሳት ከአለው ክፍፍል ጋር ተደምሮ ሌላ መጓተት እንደሚያመጣ ታስቦበት የተራዘመ እውነት ነው።
ይሄ ባይሆን እንኳን ይሄን ትልቅና የዐማራ የህልውና ጥያቄ አካል፣ ጥያቄም ብቻ ሳይሆን መልስ ሰጪ ሀሳብ በዚህ ደረጃ ለፖለቲካል ኮሬክትነስ ሲባል "ርባና ቢስና የማይጨበጥ" በማለት ሊገለጽ የማይገባው ነበር።

ነገ ሌላ ቀን ነው እያደርርን እናያለን !
State of Amhara (ነጣ የዐማራ መንግስት)
Photo
እስማኤል ቃኒ እንደ ኢሊያሁ ኮህን ‼️
ህልውና እንደዚህ ነው !

ሁሌም የእስራኤልና ከማህጸናቸው የወጣው የሞሳድ ነገር እንዳስገረመኝ ነው። ይሄ እኔን ብቻ ሳይሆን ጠላቶቻቸውንም ከመጥላታቸው ባሻገር ማስገረሙ እንዳለ ነው።

ከዚህ የምንማረው ስለህልውና ትግል ቁልፍ ሚስጢር ነው። የህልውና ትግል እንደዚህ ነው። የህልውና ትግል ምን ይመስላል ካላችሁ የእስራኤል ጽዮናዊ ትግልን ይመስላል ነው መልሱ። ስለህልውና ትግል በልኩ የሚታገሉ እንስሳትና እስራኤላውያን ናቸው። የእኛው ማስመሰልና የፖለቲካ ንግድ ነው !

ንቦችን ተመልከቱ፡ ማራቸውን ብትነኩ ወይንም ወደ ቀፎው ተጠግታችሁ ጥላችሁ ቢከብዳቸው ወይንም ጠረናችሁ ቢሸታችሁ ተጠራርተው ያለርህራሄ ነድፈው ያባርሯችኋል። ሌሎችም እንስሳት ከንብ ከፍተው ይከላከላሉ ያጠቃሉ፤ ልዩ ስፍራ ይይዛሉ !

በአልችልም ባይነት የሚጠቁት እጽዋት ናቸው። እጽዋት እንቅስቃሴ ያቸው ውጫዊ ባለመሆኑ ተንቀሳቅሰው ማምለጥ ወይንም መዋጋት አይችሉም። ምርጫቸው ጡንቻቸውን አጠንክረው ማልቀስ (irritate) ማድረግ ብቻ ነው። የዐማራ ብሔርተኝነትም እንደ እጽዋት ያለ ትግል ነው። ፖለቲካዊ ተራምዶ የለውም !

ለማንኛውም ወደ ጉዳዬ ልግባ። ሰውየው እስማኤል ቃኒ ይባላል። የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ጓድ ከፍተኛ ብርጋዲየር ጀነራል ነው። በ 20 ዎቹ መጀመሪያ ላይ የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ቡድንን ተቀላቅሎ  በተለያዩ ምድቦች አገልግሏል። 1980-1988 በተደረገው የኢራን-ኢራቅ ጦርነት የኢራንን ጦር እየመራ በጀብድ ተዋግቷል።

ጥር 3, 2020 በኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ አማካኝነት በአሜሪካ ጥቃት የተገደለውን የቀድሞውን የኢራን የጦር አዣዥ ሱሌይማንን ለመተካት አዲስ አዛዥ ሁኖ ተሹሟል። በካሜኒ አማካኝነት ይህ ሰው ከጠባቂዎች ውስጥ “በጣም ያጌጡና ክብር ካላቸው አዛዦች” መካከል አንዱ በመባል በልዩ ዝናና ክብር የሚገባው እንደሆነ ተወድሶ በ 1997 የIRGC ዋና አዛዥ ሁነው ተሾሙ ። 

በመጨረሻም እስራኤል-የአረቡ ዓለም ለአንድ አመት ገዳማ እያደረጉ ባሉት ጦርነት የእስራኤሉ ሞሳድ የኢራን፣ የሂዝቦላ፣ የሃማስ ከፍተኛ የፖለቲካና ወታደራዊ አዛዦች እስከ ቤት ጓዳቸው ገብቶ እየገደላቸው ነው። ይሄ ግድያ ያስደነገጣቸው የኢራን ባለስልጣናት በኤሊያሁ ኮህን ጊዜ እንደሆነው እርስ በእርስ ሲጠራጠሩ እስማኤል ቃኒ የእስራኤል የስለላ መረብ የሞሳድ ኤጀንት ሁኖ አገኙት። በከባድ ምርመራ ውስጥ እያለ እስማኤል በልብ ድካም ራሱን ስቷል። ራስ አሳሳቱ በራሱ ሞሳድ በቅርብ ርቀት በሪሞት ኮንትሮል እያደረገው ነው ብለዋል።

ለማንኛውም ገድሉ ኤሊያሁ ኮህንን ካስናቀ ፕሮፋይል እንቀይራለን። ከሞሳድ ሙሉ መረጃውን በፍለጋ ላይ ነን።

የህልውና ትግል እንደዚህ ነው !!
👍1
ጠላቶቻችን በጭካኔ ከራያ እስከ ወልቃይት፣ ከዛም መሀል ከመተከል እስከ ደራ ዐማራን እያረዱ፣ ወገኔ ተነካ ብሎ የሚነሳ ዐማራ ሲጠፋ፣ ሸዋን "የመኳንንት ዘር፣ የገዥ መደብ" እያሉ ፈርጀው ነጣጥለው መቱት። የአርበኛ ዘር እየተመረጠ ፣ ጀግናና ደመ ሞቃቱ ዐማራ እየታነቀ ተበላ። ያኔ ጠላቶቻችን የልብ ልብ ተሰምቷቸው። ዐማራን ሱሪውን አስፈትተነዋል፣ እኔዳይነሳ አድርገይ ቀብረነዋል፣ በየስብሰባው ገለን የቀበርነውን ዐማራ አታንሱብን እያሉ ተዘባበቱብን። ጸያፍ ስድብ ዐማራን በእብሪት አዋረዱት። የክልሉን ዐማራ የብሄረ ብሔረሰቦች ብለው አፈራረሱት። ዐማራን በእየምክያቱ በታተኑት። አንዱ ለአንዱ ስጋት እንዲሆን ምክንያት ፈጠሩለት።

የክልሉን ውስጥ ዐማራ ከበታተኑት በኆላ አቅም ሲያጣ ከክልሉ ውጭ ያለውን ይተዟዟሩ በግፍ፣ በጭካኔ አርደው ቀገደል ጣሉልት። እስከ ነብሱ በገደል ወረወሩት። እሷት ለቀቁበት። በቁም ሲጠግቡ፣ ከማህጸን የዐማራን እናት ሆድ እየቀደዱ ጽንስ አስወረዱ። ህጻን አዛውንት ሳይሉ ዐማራን በተገኘበት ሁሉ ተሳዳጅ፣ ተቅበዝባዥ አደረጉት። It's never forgotten !! Never !!

የነቃ ዐማራ ሲፈጠር፣ ግፉን የሚቃወም ግለሰብ ሲወጣ እየጠበቁ ገደሉት። በሞቱም ዐማራን ሰደቡት። ተዘባበቱበት። ከዚህ በኋላ ዐማራ ስጋት አይሆንም፣ በሱሪው ላይ አሸንተነዋል፣ ብለው እንደ ህዝብ ሰደቡን። በእየማጎሪያ ቤቱ ያጎሩትን ዐማራ "ሽንታም ዐማራ" እያሉ አጥን ድረስ ዘልቆ የሚሰማ ማንነታዊ ጥቃት አደረሱበት። በማናለብኝነት ደብዛው የጠፋው ዐማራ ሀገሩ ይቁጠረው። በልጅነት ዕድሜያ ያየሁት ሰቆቃ እልቅፍ የሚነሳ፣ እረፍት የሚያሳጣ ነበር። እንደአሁኑ እንኳን ሳይገባኝ።

እነ ፕሮፌሰር አስራትን ገድለው፣ እነ ጎቤ መልኬን ገድለው፣ እነ ሰጠኝን ገድለው፣ እነ አሳምነውን ገድለው፣ እነ አስቻለውን ገድለው አጥንት የሚሰብር ስድብ ሰድበውናል። የዐማራን ሞራል ይገድላል፣ ተስፋ ያስቆርጣል ያሉትን ሁሉ ከጅሜላ እስር እስከ ጅምላ ግድያ ፈጽመዋል። አይራሩልንም ! ሲበዛ ጨካኞች ናቸው።

የቀጠለው ጭካኔያቸው፣ የማጥፋት ጽኑ ዓላማቸው አሁንም ዐማራን በጭካኔ እየገደሉ፣ ለመግደልም እየሰሩ ነው። አብይ አህመድ ዘመናዊ ኦነግ + ህወሓት ነው። ዐማራን ሰብረነዋል የሚለውን ለማረጋገጥ ሞራል፣ ቅስሙንም ለመግደል በርትቶ እየሰራ ያለ ነው። የአሁኑ ዘመናዊ የፖለቲካ ትጌል ይህ ነው። ተቀናቃኝህ በጭራሽ ሌላ ጊዜ ስጋትህ እንዳይሆን ፤ ትጥቁን ብቻ ማስፈታት ሳይሆን፣ ወኔውንም ማስፈታት፣ አካሉን መግደል ብቻ ሳይሆን ስነልቦናውንም መግደል የሚል ነው። አብይ ለዚህ ተግቶ እየሰራ ነው። የዐማራ ፋኖ መሪዎችን ከእኛዎች ብአዴኖችና የብአዴን ተፈጥሮ ተጨምሮበት ከፋፍሎ፣ ሊፈመሪዎችን ሊገድል አሉበት የተባለውን መንደር፣ ጫካ በድሮን እየደበደበ ነው። ያለ የሌለ አቅሙን ተጠቅሞ መሪዎችን ለመግደል እየጣረ ነው። በተለይ አርበኛ ዘመነ ካሴን ለመግደል ጥረት እያደረገ ነው። በዚህ ሶስት ነገር ይሳካልኛል ብሎ ነው።

1. ሰሞኑን በባህርዳር ስብሰባቸው እንዳሉት "አውራው ከተመታ መንጋው ይበተናል" በሚል ነው።

2. ዐማራዊ ልዩነትና የጎጥ አጀንዳ ያስነሳልኛል በሚል ሲሆን

3. አርበኛ ዘመነ ካሴን መትቼ ዐማራን ትጥቁን አስፈትቼ፣ ቅስምና ስነ ልቦናውን ሰብሬ አጠፋዋለሁ በሚል ነው።

ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት ስጋት የሆነባቸውን ዐማራ ገድለው ዐማራን "መቼም አይችልም፣ አቅም አሳጥተን ሰብረነዋል" ብለው ሊዘባበቱ፣ በጭቃኔ ሊገድሉን፣ የከፋም ሊፈጽሙብን በማሰብ ነው።

ስለሆነም፦ አንድ መሆን፣ መሪን መጠበቅ፣ መሪውችም የፎቶ ሾው መቀነስ ይኖርባቸው ዘንድ የሚጠቁም ነው !
👍4
State of Amhara (ነጣ የዐማራ መንግስት)
Photo
የዐማራ ፋኖ ትግልና የዐማራ ወጣት በጸረ ዐማራ ኃይሎች አፈሳ ነገር ‼️
ለሁሉም የዐማራ ፋኖ ኃይሎች‼️

እንደ ብሔርተኝነት እንቅስቃሴ በዚህ ወቅት ይሄን ዜና መስማት ለዐማራ የብሔርተኝነት ትግል ትልቅ የልብ ስብራት ነው። ይሄን አጋጣሚ መደበኛ ውጊያ እያደረገ ያለው ጠላት፣ ተራ የሚጠብቀው ጸረ ዐማራ ኢትዮጵያኒስት ኃይል እየተጠቀሙበት ነው። የውጩና የቀጠናው ፖለቲካዊ ሀገራትም ቢሆን የዐማራ ትግል በረግረግ ጭቃ የተያዘ ወይንም ሰማጭ መርከብ አድርገው መሳላቸው ማሳያ ይሆናል።

የዐማራ ፋኖ በየትኛውም ጠርዝ ያለው ፖለቲካዊ አይኑን እያጎላ የዐማራን ህልውናዊ ጥቅም እየዘነጋው ይመስላል። የዐማራ ወጣቶች አፈሳ የዐማራ የህልውና ጉዳይ ነው። ይሄ ወጣት በየትኛውም የጦር ግንባር ሰለባ የሚሆን ፤ በሁለተኛም የራሱን የዐማራ ህዝብ የሚጨፈጭፍ የምሳር መግጠሚያ እጀታ በመሆን ሊያገለግል የተመረጠ ነው። ይሄ ሁለቴ ሞት ነው።

የዐማራ ፋኖ አብዛኛው ቀጠናዎችን ከገጠር እስከ ከተማ ተቆጣጥሯቸዋል። ፋኖ ይሄን ባደረገበት ቀጠና የጠላት ኃይል የዐማራ ወጣቶችን አፍሶ የራሱ ወታደር ሊያደርጋቸው አይገባም። የወጣቶችና የማህበረሰቡ የራሱ የሆነ ድክመት ነው ብንል እንኳን ፤ እኛ የህልውና ታጋዮች ይሄን የራሱ ጉዳይ ብለን የምንተወው አይሆንም። በቅድሚያ ፋኖ ያልነቃውን ሰፊ ማህበረሰብ ማንቃት፣ በጥርጣሬና በአሉባልታ እንዲሁም መጥፎ ምሳሌ በሆኑ የፋኖ መሪዎች የራቀውን አቅርቦ፣ ልቡን አማሎ የዐማራ ወታደሮች እንዲሆኑ ሰፊና ወጥ የሆነ ፕሮግራምና ስልት አውጥቶ ሊሰራበት ይገባል። ሁለተኛው ደግሞ ተቋርጦ ቀርቶ፣ ፋኖም በአስቸኮይ ስራውን ሳይሰራ ቀርቶ በዐማራ ወጣት ላይ የሚደረግን አፈሳ፣ በዐማራ ህልውና ላይ የተቃጣ ሰይፍ አድርጎ በመቁጥር በወታደራዊ ኦፕሬሽ የማስመለስ ስራ መስራት ይኖርበታል !

በዚህ በእኛው የፖለቲካና የብሔርተኝነት ድክመት ህዝባችን ዋጋ ሲከፍል፣ ተገዶ የገባን የዐማራ ቀጣት የጠላት ወታደርም ስበን ስናስከዳና ስናጠቃ አንኖርም !!

ፋኖ አላሰለጥነው ሲል ጠላት በሰፊው በር ገብቶ እየተጠቀበት ነው። ይሄን ለማድረግ የተቀናጀ ስራ መስራት ይኖርብናል። ፋኖ ወጣቶችን ስልጠና ሰርቶ የዐማራ ዘብ ለማድረግ የቅድሚያ ፍላጎት፣ ተነሳሽነትና ዓላማ የሚጠይቅ ሁኖ ፤ ይሄን ለማድረግ ሰፊ የሆነ የፋይናንስ አቅም የሚጠይቅ ነውና በዛ እንተጋገዛለን !
👍1
አሁን በዚህ ሰዓት የጠላት ኃይል መነሻዉን ከፍኖተ ሰላም እና ከደንበጫ በማድረግ በአንጎት የደገራ በኩል ከፍተኛ ኃይል እና ዙ 23 በመያዝ ወደ ዋድ የዘለቃ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል!!!

ለወገን ኃይል መረጃ እናድርስ ‼️
👍4
ስለዐማራና ዐማርኛ ጥንታዊነት ‼️

1. የነገስታትና የአማልክት ስሞች

የነገስታት ስሞች፤

በፑንት የንጉሰ ነገስት መንግስት ዘመን ከ2800 ዓ.ዓ ገደማ ጀምሮ የነገሱ የግብጽ ነገስታት ከፑንት ጋር ጥብቅ የንግድ ትስስር ነበራቸው። በዚህም የንግድ ትስስር ከፑንት ከርቤ፣ ቀረፋ፣ ሙጫ እጣን፣ የሰጎን እንቁላልና ላባ፣ የድብ ቆዳ፣ ዝንጀሮ፣ አህያ፣ ኮርማ፣ በሬ፣ የአውራሪስ ቀንድ፣ የወርቅ የብርና የነሃስ እቃዎች እንዲሁም የመድሃኒት እፅዋቶች እና ሌሎችም ነገሮች ጭምር ይላኩ ነበር።

የግብጽ ንግስት የሆነችው ሃትሸፕሱት (1504-1482) 5 የንግድ መርከቦች ወደ ፑንት ልካ የነበረ ሲሆን በአንዱ መርከበኛ ተስሎ በግብጽ በአንድ ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚገኘው የስዕል መረጃ፥ ከ1500 ዓ. ዓ ገደማ "ፐረሁ" በተባለ ንጉስና "አጪ/አጢ" በተባለች ንግስት የሚተዳደሩ በእርሻና በንግድ ሙያ የሰለጠኑ፣ በገጠርና በከተማ የሚኖሩ፣ የተፈጥሮ አማልክትና ቤተ መቅደስና ካህናት ያሏቸው ፑንታዊያን ተብለው የሚጠሩ በቀይ ባህር ምዕራባዊ ጠረፍ የሚገኙ ጥንታዊ ሰዎች እንደነበሩ ይገልፃል።

የንግስቷ ስም "አጪ/አጢ" አማረኛ ስለመሆኑ አያጠራጥርም። በዚህ የአማርኛ ስም ላይ የፑንታዊያን መኖሪያ ተብለው የተሳሉት ጎጆ ቤቶች አሰራራቸው አማራ በሚኖርበት በሰሜን ኢትዮጵያ ካሉት ቤቶች ጋር አንድ አይነት ሆነው መገኘታቸው እንዲሁም በግብጽ ከጌቶቻቸው ጋር ከተቀበሩ ዝንጀሮዎች በተወሰዱ የDNA ናሙናዎች ዝንጀሮዎቹ ዝርያቸው አማራ በሚኖርበት በሰሜን ኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ መሆኑ የአማራንና የአማርኛን ጥንታዊነት ያረጋግጣል።

በዳማት የንጉሰ ነገስት መንግስት ዘመን (1000 - 10 ዓ.ም?) የስልጣኔ አሻራዎች ብዙ ሲሆኑ የዳማትን መንግስትና ስልጣኔ የሚመለከቱ የድንጋይ ላይ ጽሁፎች ዋነኛዎች ናቸው። የድንጋይ ላይ ጽሁፎቹም በየሀ፣ መጠራ፣ ከስከሴ፣ ሀውልቲ፣ አዲቀዋህ፣ አዲገለሞ፣ እንዳጭርቆስ ነው የተገኙት። የተገኙት የድንጋይ ላይ ጽሁፎች 13 አጫጭር የነገስታት ዜና መዋዕሎች ሲሆኑ የተፃፉትም በዳማታውያን በራሳቸው ቋንቋና በሳባ ቋንቋ ነው። በዜና መዋዕሎቹ ላይ የነገስታት ስሞች፣ የአማልክት ስሞችና ሌሎችም ነገሮች የሰፈሩ ሲሆን ከሰፈሩት የነገስታት ስሞች መካከል "ለመነ" ይገኝበታል።

ንጉስ ለመነ በዜና መዋዕሉ "የዳማታውያን፣ የሳባውያን፣ የአበራውያን የቀዮችና የጥቁሮች ንጉሥ ሲል ግዛቱ የሚያቅፋቸውን ህዝቦችና የግዛቱን ስፋት ገልጿል። የንጉሱ ስም "ለመነ" አማርኛ ብቻ ነው። ትርጉሙም ግልፅ ነው። 
በአክሱም የንጉሰ ነገስት መንግስት ዘመን (10 ዓ.ም - ?) ፤ ከአክሱም ነገስታት መካከል ትንሽ የማይባሉት ስማቸው አማርኛ መሆኑ ነው። አግባ፣ ጉም (ገርስም) ፣ አስጎምጉም፣ ለትም፣ ተላትም፣ አይዙር፣ አስፈሪ፣ ፍሬ ሠናይ፣ አርፍድ፣ ውድም አስፈሪ፣ ግርማ አስፈር፣ ባህር፣ ወሠን ሰገድ፣ ለአብነት ሊጠቀሱ ይችላሉ። እነኝህ ስሞች ደግሞ ቅልብጭ ያለ ትርጉም ያላቸው አማርኛ ቃላት ናቸው።

የአማልክት ስሞ፤

በድንጋይ ላይ ተፅፈው በተገኙ የዳማታ ነገስታት 13 አጫጭር ዜና መዋዕሎች ላይ ከተጠቀሱት ብሔራዊ አማልክት ስሞች መካከል "ሸመነ" ይገኝበታል። "ሸመነ" ደግሞ አማርኛ ነው። ትርጉሙም ግልፅ ነው።

የጽሁፍ መረጃ፤

ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ200 - 130 ዓ.ዓ ባለው ጊዜ ከውስጥ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚኖሩ ህዝቦች የሚናገሩት አማርኛ የሚባል ቋንቋ እንደነበረ ድርሳን ላይ የተፃፈ መሆኑ።
በአክሱም የንጉሰ ነገስት መንግስት ዘመን የሕዝቡ የዕለት ከዕለት ቋንቋ ከመሆን አልፎ ሠራዊቱና መኳንንቱ በግዕዝና አማርኛ ይገለገሉ የነበረ መሆኑ ። በአክሱም የንጉሰ ነገስት መንግስት ዘመን፥ አክሱማውያን ማለትም የግዙፉ የአክሱም አውራጃ ነዋሪዎች የአማርኛ ተናጋሪዎች ስለመሆናቸውና አውራጃው ርስታቸው መሆኑ። ዘራቸው ከቤጃ ዘላኖች የሆኑት "ነገደ ትግረ" የአክሱምን መንግስት ወርረው ከመዲናው ስለማባረራቸው እና በዚህ ጊዜ ትግርኛና "ነገደ ትግሬ" ስለመፈጠሩ። ይህም ማለት ትግርኛም ሆነ ነገደ ትግሬ ከ8ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ ነው የተፈጠረው።

የአርኪኦሎጅ መረጃ፤  የስነ ልሳን ባለሙያው አምሳሉ ጥንታዊ የድንጋይ ላይ ጽሁፎች ስለመገኘታቸው አብራርቷል።

መደምደሚያ፦ አማራ የፑንት፣ የዳማት፣ የአክሱም፣ የአዳፋ፣ የሸዋ፣ የደዋሮ፣ የወጅ፣ የበጌምድርና እንደገና ድጋሚ ወደሸዋ የተመለሰው የሸዋ የንጉሰ ነገስት መንግስት ባለቤት የሆነ ባለደማቅ ታሪክ ህዝብ ሲሆን አማርኛም ከ5-6 ሺህ ዓመታትን ያስቆጠረ የዳበረ ቋንቋ ነው።

ከየትኛውም ወገን ይሁን በዐማራና በዐማራነት ላይ የሚቀልድ፣ ትርክትና ታሪክ የሚያጣምም ግለሰብም ዬሁን ቡድን ለፍርድ መቅረብ ይኖርበታል። በተለይም በዐማራ የብሔርተኝነት ትግል ውስጥ በፋኖ መዋቅር ከፍተኛ አመራር ሁኖ እንደ የቆዬ ሞላ አይነቱ ላይ ተገቢውን እርምትና ማስተካከያ መውሰድ ያስፈልጋል።

                  ዋቢ መጽሐፍት (References)

1. Sergew H. Selassie, Ancient and Medieval Ethiopian History to 1270, 1972, pp. 22-23.

2. J. Doresse, Histoire Sommaire de la Corne Orientale de L Afrique,   pp. 47-56; Pankrust, Economic history, pp. 5-6.

3.  Ibid, Inscriptions Sudarabiques, pp. 387 - 389.

4. ተክለ ፃድቅ መኩሪያ፣ ኑቢያ-አክሱም-ዛጉዬ

5. Agatarcus (Ago), Pen tes Eryth - as thalasses (on the Erythraean sea)

6. ፈለቀ ገርማሚ፡ ባሻህ ውረድ፡ ገለበው ሰንጎጎ፣ የትግሬ-ቤጃ ማንነት፣ ገ. 5-6።

7. ዶ/ር ፈለቀ ገርማሚ: አቶ ባሻህ ውረድ: አቶ ገለበው ሰንገጎ፣ የትግሬ ቤጃ ማንነት፣ ገጽ. 7 እና 9።

8.ዶ /ር ምስጋናው ታደሰ፣ ከቤተ አማራ እስከ ወሎ

https://www.facebook.com/Amharanism2514
👍2
ከአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ) የተሰጠ መግለጫ

ኢትዮጵያዊው ኤዲ አሚን ዳዳ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፅመው ጭፍጨፋ የሕዝባችንን ትግል አይቀለብሰውም!!!
መንግሥት መር ጭፍጨፋው በሕዝባዊ የፋኖ ትግል ይቀለበሳል!!!

ፋሽስቱና ደም የጠማው የጠራራ ጋኒን አብይ አህመድ በሕዝባችን ላይ የከፈተውን መንግሥታዊ ጦርነትና እየፈፀመ ያለውን የዘር ማሳሳት፣ የዘር ማፅዳትና የዘር ፍጅት የሰማይ አምላክ ካልሆነ በስተቀር የሰው ልጅ በተለይ ኢትዮጵያዊያን የተረዱት ጉዳይ ነው ብሎ ማሰብ ያስቸግራል። አምባገነኑ የብልፅግና ቁንጮ፣ የኢትዮጵያዊያን የዘመናችን ታላቁ መርገም አብይ አህመድ ሲፈልግ በምድር ጦር፣ ሲፈልግ በሰማይ ጀትና በሰው አልባ ድሮን ጥምረት በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን ሁለንተናዊ ፍጅት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዐይንና ጀሮ ሳይሰጠው እንደቀልድ ሁለት ዓመት እያለፈው ነው።

የአማራ ሕዝብ በታንክና በመድፍ እንዲሁም በጀትና በሰው አልባ ድሮን ጥምረት የሚጨፈጨፍበት መሠረታዊ ምክንያት የሰው ልጅ በዴሞክራሲያዊው ዓለም ሊከበሩለት የሚፈልጋቸውን ልዩና የዴሞክራሲያዊ መብቶች ስለጠየቀ አይደለም! ወይም የመንገድና መብራት፣ ፋብሪካና ዘመናዊ ከተሞች ስለጠየቀ አይደለም! ወይም በምከፍለው ግብር ልክ ልዩ ልዩ የጤናና የትምህርት ተቋማት ይከፈቱልኝ ስላለም አይደለም! የአማራ ሕዝብ የመብትና የኑሮ ማሻሻያ ጥያቄዎችን ይዞ ሳይሆን የወጣው ሰው ተብሎና ሰው ሆኖ መኖር በመከልከሉ የሕጋዊ ሰውነት እውቅናን፣ የሕግዊ ሰውነት ውክልናን እንዲሁም ተፈጥሮ በሰጠው ዘመን ውስጥ በኢትዮጵያ ምድር ላይ በሕይወት መኖር መቻልን ለመጠየቅ የወጣ ህዝብ ነው፤ መንግሥታዊ ጦርነት የተከፈተበትም ተፈጥሮ በሰጠው ዘመን ውስጥ በሕይወት መኖርን ስለጠየቀ ብቻና ብቻ ነው። የአማራ ህዝብ ጥያቄ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ውሎች ሁሉንም ሕዝብ በኢትዮጵያዊነቱና በሰውነቱ ልክ ይወቁት፣ ይዳኙት፤ እኔንም ሕጋዊ የዜግነት እውቅናና ሕጋዊ የሕዝብ ውክልና ይስጡኝ፣ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋርም እኩል ይዳኙኝ የሚል የመኖር ያለመኖር ጥያቄ ነው። በሕዝባችን ጥያቄ ውስጥ በሀገራችን መንግስት በዘራችን ምክንያት ማንነታችን ሳይከዳ፣ ማንነታችን ሳይሳሳና ሳይጠፋ በሕግ ታውቆ መኖርን፣ እኩልነትን፣ ዲሞክራሲንና ፍትሕን የምናገኝ ሲሆን ይህም የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መሠረት ነው። ኢትዮጵያዊያን ግን ልብ ያሉት አይመስልም።

የሰላም ኖቤል ተሸላሚው ሕዝብ ጨፍጫፊውና ጦረኛው አብይ አህመድ ግን እነዚህን የከበሩ የሕዝብ ጥያቄዎች የአማራን ሕዝብ በማንበርከክ ጥያቄዎቹን ድጋሜ እንዳይነሱ ማድረግ ካልሆነም የአማራን ሕዝብ ማጥፋትን ዓላማዬ ብሎ መያዙ ገሃድ የወጣ ሐቅ ነው። በአንዳንድ ፀሐፍት አምባገነኑ ሦስተኛው የዩጋንዳ ፕሬዝደንት ኤዲ አሚን ዳዳ ዘር መርጦ የሰውን ልጅ ስጋና ደም ላልተገባ ተግባር ያውላል ተብሎ እንደተጻፈው ጭራቁ አብይ አህመድን የአማራን ሕዝብ ለማንበርከክ ብሎ በከፈተው ጦርነት የአማራን ልጅ ስጋና ደም እየተመገበ ያለ ሰው በላ መሆኑን ኢትዮጵያውያንም ሆነ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ሊገነዘበው የሚገባ እውነት ነው። የአማራ ሕዝብ በማንኛውም የታሪክ አጋጣሚ በሀገሩ መሪና መንግሥት በዚህ ልክ የዘር ጭፍጨፋ ደርሶበት አያውቅም። ፋሽስቱ የጣልያን ወራሪ ክ1928 -33 ዓ.ም ካደረሰው በደል በማይወዳደር መልኩ በሕዝባችን ላይ በዚህ አምሳ ዓመት የደረሰበት በደል የላቀ ሲሆን የሀገር ልጅ በሆነው አብይ አህመድ የደረሰበት በደል ግን የሁሉ ቁንጮ ሆኖ በገሀድ የምናየው ጉዳይ ነው። የአማራን ሕዝብ ባሪያ አደርገዋለሁ ብሎ ቆርጦ የተነሳው አባገነን የገባበት ቅጀት ውስጥ ለመውጣት የሰላም ነጋሪት ቢጎሰምለትም መንቃት የሚፈልግ አይደለም።

ሰሞኑን የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ)ን የጠቅላላ ጉባዔ ዓመታዊ ስብሰባን አደናቅፋለሁ ብሎ በማሰብ አመራሮቹ በሌሉበት በደቡብ ወሎ ዞን በአምባሰል ወረዳ በጀትና በድሮን የፈፀመው የንጹሓን ጭፍጨፋ የዚህ አይነተኛ ማሳያ ነው። አማራ መሆናቸውን የማያውቁ ሕጻናት በአብይ አህመድ የግል ንብረት በሆነው አየር ኃይል አማራ ተብለው ተጨፍጭፈዋል።

በእርግጥ የተሸነፈ ስነ ልቦና ባለቤት የሆነውና የስልጣን ጥሙ ከአካሉ የሚገዝፍበት - ከአዕምሮው የሚሰፋበት ይህ የዘመኑ የአፍሪካ አባገነኖች ቀንዲል ከምድር ጦር በዘለለ ሰው አልባ አውሮፕላንና ጀት የሚጠቀመው የሽንፈት ፅዋውን እየተጎነጨ ስለሆነ ነው። ኢትዮጵያዊው ኤዲ አሚን ዳዳ በሕዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለው የዘር ጭፍጨፋ ሕዝባዊ ትግላችንን አይቀለብሰውም፤ የተከፈተብን መንግሥት መር ጦርነትም እንደሕዝብ መደራጀታችንን፣ መታጠቃችንን፣ አምባገነናዊ የብልፅግና ሥርዓትን ማስወገዳችንን አያስቀረውም። ሥርዓቱ በሕዝባችን ላይ የሚፈፅመው በደል ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ የሚያበረታን እንጅ ክንዳችንን የሚያዝለው አይሆንም።

ስለሆነም ይህንን የአብይ አህመድን ሰይጣናዊ ተግባር ለመቀልበስ በቤተ አማራ (ወሎ) የምንገኝ ፋኖዎች በቀን 14/05/2017 ዓ.ም ወደ አንድነት መምጣታችን ይታወቃል። በመሆኑም ድርጅታችን የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ) የመጀመሪያውን የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባውን በማድረግ በስኬት ያጠናቀቀ ሲሆን የማዕከላዊ ምክር ቤትንና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴውንም አዋቅሯል፤ በሥራ አስፈጻሚና በልዩ ልዩ መምሪያዎች ደረጃ የተመደቡ አመራሮችና ምደባውም የሚከተለውን ይመስላል።

1.ዋርካው ምሬ ወዳጆ --------ሰብሳቢ
2.አርበኛ ድርሳን ብርሃኔ ------ምክ/ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ
3.አርበኛ ሀብታሙ ደምሴ -----ምክ/ወታደራዊ አዛዥ
4.ኮሎኔል አባይ ባየው--------ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጅ መምሪያ ኃላፊ
5. አርበኛ በለጠ ሸጋው ------ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
5.1. ኮሎኔል ፈንታው መኩዬ ----ምክትል ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
6.ሺ ዓለቃ ያረጋል አሰፋ-----ወታደራዊ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ
6.1. አምሳ ዓለቃ ሲሳይ ገላነው---ምክትል ኃላፊ - ለሰው ሃብት አስተዳደር መምሪያ
6.2. ዶ/ር አቡበክር ሰይድ---ምክትል ኃላፊ - ለጤና ጉዳይ
7.መቶ አለቃ በሪሁን ደምሌ---ሎጂስቲክስ መምሪያ ኃላፊ
7.1.አርበኛ ሞላ ሰማው ------ምክትል ኃላፊ - ለስንቅና ትጥቅ ስርጭት
7.2. አርበኛ ኢሳይያስ መልኩ----ምክትል ኃላፊ - ለኦርዲናንስ ክፍል
7.3. አርበኛ ኑረዲን አበበ ----ምክትል ኃላፊ - ለትራንስፖርት ስምሪት
8.መቶ ዓለቃ ዮሴፍ አስማረ ---ወታደራዊ ሥልጠና መምሪያ ኃላፊ
8.1. አርበኛ ጌታቸው ሲሳይ ----ምክትል የሥልጠና መምሪያ ኃላፊ
9.አርበኛ ** ---ወታደራዊ መረጃ መምሪያ ኃላፊ
10. አምሳ ዓለቃ አደም አሊ ----ወታደራዊ ኢንዶክትሪኔሽን (ስርጸት) መምሪያ ኃላፊ
10.1.አርበኛ ሙላት አላምረው-----ወታደራዊ ኢንዶክትሪኔሽን መምሪያ ምክ/ኃላፊ
10.2.አርበኛ ተመስገን በቀለ ----የኪነትና መዝናኛ ክፍል ኃላፊ
11.አርበኛ ተሾመ ፈንታዬ -----ልዩ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
12.ኮሎኔል ሞገስ ዘገዬ -----ወታደራዊ አማካሪ
👍3
13.አርበኛ ሄኖክ አዲሴ ----ምክ/ሰብሳቢና የፖለቲካ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ
14.አርበኛ ሞገስ አበራው ----የፖለቲካ ጉዳዮች ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ
15.አርበኛ አራጋው ያለው-----የስትራቴጅክ ጉዳዮች መምሪያ
15.1.አርበኛ ፍቅር መንግስቱ----የስትራቴጅክ ጉዳዮች መምሪያ ምክ/ኃላፊ
16.አርበኛ ሽመልስ ትዛዙ -----የውጭ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ
16.1.አርበኛ አብደላ አያሌው -----የውጭ ጉዳይ መምሪያ ምክትል ኃላፊ
17.አርበኛ አበበ ቀዬ -----የአደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ
17.1.አርበኛ አሰፋ መሰለ -----የአደረጃጀት መምሪያ ምክትል ኃላፊ
18.አርበኛ አበበ ፈንታው ----የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ
18.1.አርበኛ ናትናኤል አክሊሉ ---የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ምክ/ኃላፊ
18.2.አርበኛ ምኒልክ ፈንታሁን --ሚዲያና ኮሚኒኬሸን ኃላፊ
19.አርበኛ ዚነት አደም-----የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች መምሪያ
19.1.አርበኛ አበበች ሲሳይ---የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ምክ/ኃላፊ
20.አርበኛ ደስታው መለሰ -------የጽ/ቤት ኃላፊ
20.1.አርበኛ አለባቸው ቀስቅሴ --ምክትል የጽ/ቤት ኃላፊ
21.አርበኛ ንጉስ አዳነ ----የፋይናንስና ግዥ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ
21.1.አርበኛ አማረ አያሌው --የፋይናንስና ግዥ አስተዳደር መምሪያ ምክ/ኃላፊ
22.አርበኛ ረዳ ውበቱ ----------የሐብት አፈላላጊ መምሪያ ኃላፊ
23.አርበኛ እስራኤል እሸቴ ---የሕዝብ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ
23.1.አርበኛ ፍቅሩ ፈንታ---የሕዝብ አስተዳደር መምሪያ ምክ/ኃላፊ
24.አርበኛ አክሎግ ሲሳይ-------የእቅድ ዝግጅትና ግምገማ መምሪያ ኃላፊ
25.አርበኛ ****-የመረጃና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ
25.1.አርበኛ *****-ምክ/የመረጃና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ መሆናቸውን ለሰራዊታችንና የኅልውና ትግላችንን በስስት ለሚመለከተው በአገር ውስጥና በውጭው ዓለም ለሚኖረው ሕዝባችን መግለጽ እንወዳለን።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ለትግሉ ደጋፊዎች በሙሉ፣ ለአማራ ሕዝብ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለሥራዓቱ ደጋፊዎች የሚከተለውን መልዕክት ማስተላለፍ እንወዳለን!

1. የበሰበሰውን የብልጽግና ሥርዓት በመደገፍ ወይም የሥርዓቱ አመራር በመሆን እያገለገላችሁ ያላችሁ አካላት፣ በብልጽግና መንግሥት መከላከያ ሰራዊትና የፖሊስ ተቋማት ያላችሁ መሪዎችና የሰራዊት አዛዦች ብዙ የሥራ ባልደረቦቻችሁ እንዳደረጉት የአማራን ሕዝብ የኅልውና ትግል እንድትቀላቀሉ ድርጅታችን የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ) ጥሪ ያቀርብላችኋል፡

2. ውዱ የአማራ ሕዝብ - የሥርዓቱ ሕይወት የሆነውን መንግሥታዊ መዋቅር በማፈራረስ፣ የሥርዓቱ ጠባቂ የሆነውን የብርሃኑ ጁላን ሰራዊት በማግለል ከትጥቅ ትግልህ ጎን ለጎን በሁሉም ከተሞቻችን በሕዝባዊ ማዕበል ስርዓቱን ለመገርሰስ ዝግጁ እንድትሆን እናሳስብሃለን።

3. ውድ ኢትዮጵያዊያን - አብይ አህመድ ሁሉም አባገነኖች እንደሚያልፉት በቅርብ ቀን ያልፋል! የማያልፉት ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያ ናቸው! የአማራን ሕዝብ የኢትዮጵያ አካል ነው ብሎ የሚያምን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ፋሽስቱን አብይ አህመድንና የገማውን ሥርዓቱን እንዲቃወምና ከአማራ ሕዝብ ጎን እንዲሰለፍ በአማራ ሕዝብ ስም የትግል ጥሪ እናቀርባለን።

4. በውጭው ዓለም የምትኖሩ ወገኖቻችን የሥርዓቱን ሁለንተና ለመገርሰስና ከሕዝባችን ጫንቃ ላይ ለአንዴና መጨረሻ ጊዜ አውርዶ ለመጣል የምናደርገውን ትግል በገንዘብ እንድትደግፉ፣ የዘር ጭፍጨፋውን በዲፕሎማሲና በአደባባይ ሰልፎች ለዓለም መንግሥታት፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማትና ለዓለም አቀፉ ማህበርሰብ ደጋግማችሁ እንድታጋልጡ እናሳስባለን።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ)
ወሎ፣ አማራ፣ ኢትዮጵያ፤
State of Amhara (ነጣ የዐማራ መንግስት)
Photo
"3ኛው የዓለም ጦርነት የሚነሳ ይመስልዎታል?" ተብሎ ለተጠየቀ አንድ ጥያቄ አንድ ብልህ የዐማራ ሰው እንዲህ ሲል ይመልሳል "ስለዚህ ጉዳይ ትንቢት መናገር የሚችሉት ኃያላን መንግስታት ብቻ ናቸው።" ወደ ዐማርኛ ሲተረጎም ኃይል ያለው ሁሉም አለው ነወ። ዐማራ ህልውናውን ለማስጠበቅ ኃይል እንደሚያስፈልገው አርሶአደሩም ተረድቶ ልጄን ለፋኖ ብሎ ቃል ገብቶ ልጁን ለዐማራ ወታደራዊ ኃይል ፋኖ በፈቃዱ ራስህንና ወገንህን አስከብር ብሎ ሸልሞ ሰጦታል።

በ70 እና በ 80 አመታቸው በወገባቸው ዝናር ታጥቀው የዐማራን ተራሮችና ሸለቆች፣ ቁጥቋጦዎችና ሜዳውች ላይ ሲያገሱ የሚውሉ አዛውንት አንበሶች ይሄን ኃይል ለማዋለድ ሒሳብ በመስራት ነው። ርዕዮት አይጠይቁ፣ መሪ ብቻ ክተት ለህልውናህ ብለዋል። እንደዘመናዊ ሰው ደግሞ ፖለቲከኞች ይሄን ነገር በአግባቡ ተቆጣጥሮ ወደተፈለገው ግብ ማድረስ የሚያስችል በቂ የሆህ መርከብ ማዘጋጀት ይገባቸዋል።

ይሄ በሳል ሰው ይቀጥልና ፋኖን ስለማጠያከርና የዐማራ የህልውናም የሉዓላዊነትም ጋሻ አድርጎ ስለማጠናከር እንዲህ ይላል።

በዓለም ውስጥ አብዛኛው ህዝብ ሰላም ፈላጊና የጦርነትን ጉዳት የሚሰጋ ነው። እኛ ዐማራዎችም ከሰላማዊ ሰዎች ግንባር ቀደሞች ነን። ነገር ግን ሰላምን የሚሹ ሁሉ እንደሚፈልጉት በሰላም ለመኖር አልቻሉም። እኛም እንዲሁ። ሰላምን ብንፈልገውም ሰላም መህን አልቻልነም። ብዙ ወራሪዎች፣ እብሪተኞች፣ ተንኳሾች፣ የህልውና ጠላቶች አሉ። የዓለምን ታሪክ ገጾች በብዛት የያዘው የጦርነት ታሪክ ሁሉ በወራሪነት፣ በአጥፊመት በተነሱ አጥቂዎችና ሰላምንና ነፃነትን በሚፈልጉ ተከላካዮች መካከል የተደረገ ነው። የእኛም ዕጣ ፋንታ ከዚህ የተቀዳ ነው። እኛ ዐማሮች የሚያንሰንን፣ የሚመሳሰለንንም ሆነ የሚበልጠንን ለመውረር ምኞት ኑሮን አያውቅም። ማንም እንዲደፍረን እንዲያጠቃን ግን ፈጽሞ አንፈቅድም። በዚህ ዘመን የመጣንባቸው አስከፊ የዐማራ መጠቃቶች በኢትዮጵያ ወንድሞች የሆነ በመሆኑ ከነገ ዛሬ ይተዋሉ ብለን ዝም ብለን ተወግተናል። አሁን ግን ክፉኛ ፈትኖናልና ለማስቆም ተነስተናል። ስለዚህ ማንንም ለማጥቃትና ለመውረር ሳይሆን የህልውና ጠላታችንን አጥቅቶ ዐማራን ለማስቀጠል  የምንጠቀምበት የዐማራ የመከላከያ ኃይል ፋኖ በሰፊው ማጠናከር ግዴታችን ሁኖብናል።

የእኛ ብቻ ሰላምን ፈላጊነት የአካባቢውን ወይንሕ የሀገሪቱን ሰላም ሊፈጥር እንደማይችል ያለፉት 30 +አመታት ከበቂ በላይ ማሳያም ማስረጃም ናቸው። በጎረቤቶቻችን ጦርነት ወይንም ጭቅጭቅ አንገባም። አጥፊዎቻችንን ግን ቀንዳቸውን ሰብረን ከመመለስ የተሻለ መድኀኒት እንደማናገኝላቸው ታሪክ በጥሩው መክሮ አስተምሮናል። ለዚህ ኃይላችንን ከማሰልጠን ፣ ማደራጀት፣ ከማስታጠቅ ለአፍታም ልንታቀብ አይገባም።

እኛ ዐማሮች ሰዎችን የማንነካ፣ ነፃነታችንን ግን የማናስነካ ነፃ ህዝብ (ዐምሓራ) ነነ። የማንነት ትርጉሜችን ነፃነት፣ እምቢ ባይነት ነው። የራሳችንን ሰላም እንደምንወደው ሁሉ የሰዎችንም ሰላም እናከብራለን። ከማንም ጋር ጠብ ለማጫር የተጓዝንበት መንገድ ኖሩ አያውቅም። ሲመጡብን ግን ትዕግሥት አያስፈልግም። ከልክ በላይ የሆነ የትዕግሥት መንፈስ ለማይገነዘብ የህልውና ባላጋራ ትዕግሥትን ማስናቅና ፈሪነትን በተዘዋዋሪ መንገድ ማሳየት ነው። ለዛም ነው ከሁን በቃን ያልነው። በዐማራ እግር መቆም አማራጭ የሌለው መድኀኒት ነው ያልነው።  ዐማራዎች ሆይ፡ ጠንካራና ዐማራዊ ኃይላችንን አደርጅተን ጠላቶቻችን ከእኛ የሚፈልጉትን ሁሉ ማሳጣት አለብን። ያን ጊዜ ለሰላምና ለፍቅር ይፈልጉናል። ይሄን ማድረግ አለብን። ለዚህ ወጥና የጠራ ዓላማ ላይ የቆመ ዐማራዊ ፋኖ ያስፈልገናል !

ፎቶ፡

የዐማራ ፋኖ በጎጃም ስልጠና መምሪያ
ታያቸው ብርሃኑ
👍2
የህልውና ትግል ውስጥ ያለ እውነተኛ መሪ፤ መሪ ብቻ ሳይሆን የትግሉም ህያው መገለጫ ነው። የህዝባችንን የተስፋ ክብደት መሸከም፣ ከፍተኛ ጫናን መቋቋም እና የትግሉን እንቅስቃሴ በውጫዊም ሆነ ውስጣዊ ስጋት ውስጥ እንዳይወድቅ ማረጋገጥ ያለበት ነው።

አንድ መኪና ወይንም ጀልባ ፣ አውሮፕላን ወይንም ባቡር ያለመሪ ሊቆም እንደማይችለው ሁሉ ፤ ህዝብ ያለመሪ አይነ ስውር ነው። ለዛም ነው ላለፉት 50+ አመታት ዐማራ ያለመሪ በመሆኑ ገደል ሲገባ፣ ገደል ሲጣል የኖረው ‼️

እኛ ዐማራዎች ለመሪዎቻችን ያለንን አክብሮታ ለመግለጽ ይመስላል አባቶቻችን "ስዩመ እግዚአብሔር" ብለው የሚጠሩት። ጥሩን ብለው ሳይሆን በህዝብ፣ በጳጳሳት ተሹመው !

ይሄ ሲሆን ሲያጠፋ "ስዩመ እግዚአብሔር" ስለሆነ በመሪ ላይ ማመጽ በእግዚአብሔር ላይ እንደ ማመጽ ነው አይባልም። አክብረን የማይከበረውን ነጥለን እየጣልን ዐማራን ማዳን ነው ስራችን። ምክንያቱ "ከስዩመ እግዚአብሔር" መሪ ይልቅ "ስዩመ እግዚአብሔር" ህዝብ ይበልጣል።

በዚህ ምስሌ የእኛ መሪዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው 👇👇
የፋኖ መሪዎች የፋኖን ትግል ለመምራት ከዚህ በኋላ ሊወስዷቸው የሚገቡ እርምጃዎች ላይ መጠየቅ አለባቸው።

ሀ/ ግልጽ ርዕዮተ ዓለም እና ግብ በተመለከተ የዐማራ ፋኖ መሪዎች መጠየቅ አለባቸው። "የዐማራ ህልው" የሚለው መነሻ ምክንያት እንደ ግብምና ርዕዮተዓለም ሁኖ ሊያገለግል አይችልም። አንድ የፋኖ ከፍተኛ መሪ ስለርዕዮተዓለም ሲያስረዳ "የዐማራ የህልውና ጥያቄ ነው ግባችን" ሲል ሰማሁት። ይሄ ስህተት ነው። ዛሬ ላይ ታጋዮችና የትግል ደጋፊዎች ምን ለመሆን፣ ምን ለማሳካት፣ የት ለመድረስ ነው የምንታገለው ሲሉ ጥያቄያቸው መልስ ማግኘት አለበት። ይሄን ለጠየቀ የትግል ደጋፊና ታጋይ "ለህልውናህ ነው የምትታገል" ማለት አጥጋቢ መልስ አይደለም። ምክንያቱ ደግሞ ለዐማራ ህልውና ነው የምንታገል እያሉ ፤ ለዐማራ ህልውና ግን አደጋ የሆኑ ሰዎችና ቡድኖች በርካታ ስለሆኑ።

እርስ በእርስ መከባበር ሲጠፋ፣ በየቀበሌና በየሸጡ መፎካከር ሲመጣ፣ የመሪው አቅም እየደከመ ሲመጣ፣ መሪዎች እንኳንስ የዐማራን የሀይማኖት፣ የኢትዮጵያዊነት፣ የሰፈር .... ሌሎችን ኮንፊውዥን ሊፈቱና በነገዱ ዐማራን አንድ አድርገው ሊያታግሉ ቀርቶ እርስ በእርስ በእጅ አዙር ወደ መዘላለፍና የሰፈርና የቀበሌ ሊቀመንበር አይነት ባህሪ ሲያዳብሩ ... ታጋዩና ደጋፊው መጨረሻው የት ነው ብሎ ወደ ኋላ ማፈግፈጉ አልቀረም።

ከዐማራ የእኛ ጎጥ የአንበሳውን ድርሻ ይውሰድ ከማለት ፤ ከእኛ ጎጥ ደግሞ የእኛ ቀበሌ በልዩ ሁኔታ የአንበሳውን ድርሻ ይውሰድ ማለት ላይ ደርረናል። ይሄ ከርዕዮተዓለም እና ግብ አልባነት የመነጨ ድርጅታዊ ህመም ነው። ሲጠቃለል መሪው የትግሉን የመጨረሻ ዓላማ መግለፅ እና ሁሉም አባላት እንዲረዱት እና እንዲያምኑበት ማረጋገጥ አለበት።

ለ/ የአባላትን ዲሲፕሊን ጥሰት፣ የውስጥ አንድነት ክፍተትን ለመከላከል ጠንካራ የትዕዛዝ መዋቅር መመስረት ያስፈልጋል። ሶስት መስመር ጹሁፍ እየጻፉ የሚያንገራግሩ የሻለቃና የብርጌድ አመራሮች የበዙበት ጠንካራ የትዕዛዝ መዋቅር ባለመኖሩ ነው። ማን አለብኝነት ከድርጅቱ በላይ ገኖ ወጥቷል።

የአመራር ሚናዎች፣ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች እና የአተገባበር ሰንሰለቶች በሚገባ የተገለጹ መሆን አለባቸው። ጥብቅ የስነምግባር ህግን ማዳበር፣ አባላት ተግሣጽን መከተል አለባቸው። ክህደትን ማስወገድ፣ አንጃ ፈጣሪነትንና ለዐማራ የውስጥ አንድነት የጭቃ ውስጥ እሾህነትን አጥብቆ ማስቆም፣ ቀይ መስመር ማድረግ ያስፈልጋል። አጠቃላይ የትግል የእንቅስቃሴዎችን፣ መርሆችን ያለምንም ልዩነት ማስከበር ያስፈልጋል። ይሄ ካልሆነ የተበተነ ኃይል ለዐማራ ነቀርሳ ነው። ይሄ አባላቱን ሳይሆን መሪውችን የነገ ታሪክ የሚያጠም፣ ለዐማራም የመከራ ዶፍ ማጋትም ነው።

ሐ/ ከተቻለ በአባላቱ አልሆን ሲል ደግሞ ከላይ እስከ ታች በድርጅታዊ መዋቅሩ መሰረት የጋራ ሃላፊነትን ማበረታታት ወሳኝነት አለው። ስራ አስፈጻሚው እንኳን መተማመን፣ መከባበር፣ መዋደድና አንድ መሆን አለበት። እያንዳንዱ አባል በትግሉ ላይ የባለቤትነት ስሜት ሊሰማው ይገባል። ይህም ለስኬታማነቱ የበለጠ ቁርጠኛ ያደርገዋል። ያ ማለት ግልጽ በሆነ check and balance ከአባላቱ ጀምሮ እስከ አመራሩ ድረስ የራሱ ድርሻና ሚና ቢሰጠው ጠንካራ ይሆናል።

መ/ የአንድ የፖለቲካ ትግል የጀርባ አጥንት የሚሆነው መደበኛ ስልጠና እና የፖለቲካ ትምህርት ማዳረስ ነው። ለሁሉም ማህበረሰብ ካልሆነ ግን በትግሉ ማዕቀፍ ውስጥ ላሉ አባላቱ የፖለቲካ ትምህርትና ስልጠና መስጠን ወደር አልባ ጥቅም ያለው ነው። ሁለቱም የርዕዮተ ዓለም እና ተግባራዊ ወታደራዊ/ፖለቲካዊ ስልጠና አባላት የተካኑ እና የተማሩ እንዲሆኑ ማድረግ ከዛም ባሻገር ማረጋገጥ ያስፈልጋል። Mass doesn't matter! በማዕበል አትመኩ። ማዕበል የሚያገለግለው ሰላማዊ ተቃውሞ ላይ ነው። በትጥቅ ትግል ላይ የሰለጠኑና ለዓላማቸው ሊሞቱ የተዘጋጁ ጥቂት የተደራጁ ኃይሎች በቂ ናቸው። ሒደቱ ሲጨምር ብዙሀኑ ያስፈልጋል። ለእኛ ደግሞ ዕድል ነው። ዐማራ በህብረት ነው የተነሳው። ስራው ከብዙው መምረጡ እና ያንን ዐማራ አድርጎ ማስታጠቁ ነው።

ሠ/ የፋኖ መሪዎች ዋና ትኩረት አድርገው መስራት ያለባቸው የውስጥ ግጭቶችን መከላከል ከተቻለ ማስቀረት ነው። ማስቀረት ባይቻል ሲከሰቱ ትክክለኛ መፍትሄ እየሰጡ፣ እየተከላከሉ የውስጥ አንድነትን፣ የአባላቱ መተማመንን፣ መከባበርንና ፍቅርን መገንባት ነው። መሪ የውስጥና የአባላት አለመግባባቶችን በፍጥነት እና በትክክል መፍታት አለበት። ውስጣዊ ክፍፍል አጠቃላይ የትግል እንቅስቃሴውን እንዳያዳክም፣ ተምሳሌታዊነት ትምህርት እየሰጡ እና ስነ-ልቦናዊ ጥንካሬን እየገነቡ መከላከል አለባቸው። የትግሉ ደጋፊና ታጋይ የዐማራን የህልውና ስጋት መሰረት፣ የዐማራን ህዝብ ነገዳዊ ታሪክ ማገርና የጉልላቱ ማነጫ አድርገው ድርጅቱን ማቆም፣ መጠገን፣ ማጎልበት አለባቸው።

ጠንካራ መሪ ጠንካራ ህዝብ ይወልዳል !
ዘመቻ አንድነት

ድል የደምበጫው ድል ያስመዘገበው ውጤት !
በአምባገነን መንግሥት ሥር የመኖር አንደኛው ክፉ ውጤት መንግሥታዊ ሽብርን እንደ ዕለታዊ ሁነት መቀበል ነው። ይህን ክፉ ውጤት መቀበል ለጅምላ ግድያ፣ ለጭፍጨፋ፣ እና ለዕልቂት ያለንን የቁጣ ስሜት ያደንዘዋል። አምባገነኖች ሽብርን ሁልጊዜ የሚከተለን የሕይወት ጥላ ያደርጉታል። ከጥላችን ማምለጥ የተሳነን መሆናችንንም ቀስ በቀስ ያስተምሩናል።

የኢትዮጵያ አምባገነን መንግሥት የዐማራ ጭፍጨፋን፣ ሽብርን እና ግድያን አስለምዶናል። በጥይት ተደብድቦ መሞት፣ በጅምላ መጨፍጨፈ፣ እርስት መወረስ፣ ሃብት ንብረት መውደም እንደ ተራ ስታትስቲክስ እንድንቆጥር አድርጎናል። ነገር ግን አንዳንዴ ይህን ባስለመዱ አምባገነን ሥርዓቶች ውስጥ እንኳን ሳይቀር በደረጃው ከሁሉ የላቀ፣ በዓይነቱ ከሌሎች መንግሥዊ ሽብሮች ሁሉ ተነጥሎ የሚታይ፣ የህዝብን አዕምሮ እና ልብ ሰቅዞ እና ቀስፎ የሚይዝ ታላቅ መንግስታዊ ሽብር ፥ ታላቅ ፍጅት የዘር ፍጅት ይፈጸማል።

በአፓርታይድ የግፍ ሥርዓት ውስጥ በኖሩ ደቡብ አፍሪካውያን ላይ የተካሄደውን የስዌቶ ፍጅት (እ.ኤ.አ 1976) ፣ በአምባገነን ወታደራዊ አመራር ሽብሮችን ቁም ስቅላቸውን ሲያዩ የኖሩ ግብጻውያን የተፈጸመባቸውን የራባን ጭፍጨፋ (እ.ኤ.አ 2013) ፣ በብሪታንያ የኮሎኒያል አገዛዝ ግፍ እና በደል የተሰቃዩ ሕንዶች የወደቀባቸውን የአምሪትሳር ግድያ (እ.ኤ.አ 1919)፣ እና በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት የማያባራ ጥቃት ሲፈጸመባቸው የኖሩ አልጄርያውያን ላይ የወረደባቸው የፊሊፕቪል ዕልቂት (እ.ኤ.አ 1955) በተጠቀሱት አገሮች ዜጎች ከሌሎች መንግሥታዊ ሽብሮች ተለይተው የሚታዩ ናቸው። ፍጅቶቹ፣ ጭፍጨፋዎቹ፣ ግድያዎቹ፣ እና ዕልቂቶቹ ለእነዚህ ሕዝቦች ልዩ ትርጓሜ እና ሥፍራ ያላቸው የታሪክ ምዕራፎቻቸው ናቸው።

በዐማራ ህዝብ ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋም ከእነዚህ ታሪካዊ መንግስታዊ ሽብሮች ተርታ የሚመደብ ባይሆንም እንኳን የመንግስታዊ ሽብርን እስከ ዘር ማጥፋት ያለውን ደረጃ አጉልቶ ያሳየናል። መንግስታዊ ሽብር የአንድን ህዝብ ህልውና የሚገዳደር አደገኛ ሂደት ነው።አንድን ህዝብ ጦር ሰብቆ ለማጥፋት ይከብድ ይሆናል። መንግስታዊ መንበሩን ይዞ፤ በስመ መንግስት ነኝ የሚደረግ ማንነት ተኮር መንግስታዊ ሽብር ግን ለህልውና አደገኛ ነው። አውሮፓውያን በአይሁዳውያን ላይ ስም ለጥፈው በህብረት ተነስተቅ ለማኝፋት ጦር ሰብቀው ነበር። ያ ዕቅድ በተባበረ የአይሁዳውያን ክንድ መክሸፍ ችላል። የመካከለኛው ምስራቅ የታላቁ የባዛንታይን ስልጣኔ ፈር ቀዳጅ ታላቁ የኩርድ ህዝብ የጠፋበት እና ሀገር አልባ የሆነበት መንገድ ፤ ኩርዲስታን ላይ የወደቀው አደጋ ውጫዊ ሳይሆን ውስጣዊ መንግስት መር ነበር። ይጠብቀናል በሚሉት፣ መብታችንን ያስከብራል፣ ሀገራችንን ያቀናል ብለው በሚያስቡት፣ ግብር በሚከፍሉት መንግስት ጸረ ኩርድ ንቅናቄ ከውስጥ ፈንቅሎ ወጣ። ያንን ከነገ ዛሬ ይቀራል ሲሉ ጠቅልሎ እንደበላቸው አይተናል። የዐማራን የህልውና አደጋ ክፉ የሚያደርገው ጠላቱ ውስጣዊ መሆኑ ነው። "ቅድስት ሀገሬን ይመራል፣ ሉዓላዊነቴን ያስከብራል" ብሎ በሚያምነው በራሱ መንግስት ጸረ ዐማራ ሽብር እስከ ፈጽሞ ማጥፋት ዕቅድ ወጥቶለት በቅደም ተከተል ጭፍጨፋ እየተፈጸመበት ያለ ነው።

ይህ ዘመን ለዐማራው ታሪካዊ ዘመን ነው። ይህ ዘመን ነገ የዐማራ ትውልድ በዛ ዘመን እያለ የሚያወሳው ለታሪክ የሚቀመጥ ነው። የሚያሳዝነው ለሰላሳ አመታት የቀጠሉት የዐማራ ግዙፍ ጭፍጨፋዎች አንዱም አልተመዘገቡም። ጭፍጨፋው ዕቅና አላገኘም። በራሱ በዐማራም በውጭ አካላትም።

በአንድ ወቅት እ.ኤ.አ በ2014 የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች በግብጽ ራባ አደባባይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ “ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በአንድ ቀን ከተፈጸሙ ታላላቅ ግድያዎች መካከል አንዱ” ተብሎ እንደሚመደብ ዘግቧል ነበር። እንደ ድርጅቱ ዘገባ ከዚህ የራባ ግድያ ጋራ የሚወዳደሩት የቻይና ታይናሚን እና የኡዝቤኪስታን አንዲጃን ጭፍጨፋዎች ናቸው በማለት አስፍሮ ነበር። በእነዚህ ሁሉ ታላላቅ ጭፍጨፋዎች በእያንዳንዳቸው የሞተው ሰው ቁጥር ከአራት መቶ እስከ ስምንት መቶ የሚገመት ነው። የዓለም ሚዲያና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች ታላላቅ ጭፍጨፋዎች ሲል መዝግቦ አልፏቸዋል። ዐማራ ላይ የተደረገው ግልፅ እና መንግስታዊ የዘር ፍጅት ከእነዚህ ቁጥሮች ጋር ሲወዳደር የአንድ ቀኑ ይበልጣል።

የስዊድኑ ኡፕሳላ ዩኒቨርሲቲ እ.ኤ.አ ከ1946 ጀምሮ በዓለም የተፈጸሙ የተደራጁ ሽብሮችን የሚመለከት ገላጭ መረጃዎችን ያቀፈ፣ ድንቅ ዳታ ቤዝ አለው። የዊኪ ፕሮጀክት ደግሞ የዓለም ጭፍጨፋዎችን (massacres) የሚያጠናክር በየጊዜው የሚያዘምን (dynamic) የመረጃ ዴፖ አለው። የትጥቅ ግጭትን፣ ከአንድ ቀን በላይ የወሰዱ ጭፍጨፋዎችን እና ከመንግሥት ውጪ የተፈጸሙ ፍጅቶችን ወደ ጎን አድርገን ሁለቱንም ዳታ ቤዞች ስንመረምር ዐማራ ላይ የተፈጸመውን ያክል በዓለም ላይ የትኛውም ሀገር የትኛውም ህዝብ ላይ እንዳልተፈጸመ እናረጋግጣለን። ግን አየሁ ሰማሁ ባይ የለም።

ቢፓን ቻንድራ “Indian’s Struggle for Independence” በተሰኘው ታዋቂ መጽሐፋቸው የአምሪትሳርን ጭፍጨፋ በተመለከተ ሲያትቱ የሕንድን ሕዝብ ክፉኛ ድንጋጤ እና ከፍተኛ ቁጣ ውስጥ የከተተው የሟቾች ቁጥር ሳይኾን ግድያው የተፈጸመበት መድረክ መኾኑን ያወሳሉ። በዚህ ጭፍጨፋ የተገደሉት በፑንጃብ ግዛት በየዓመቱ በደማቅ ሁኔታ በሚከበረው የመኸር የእህል ምርት የምስጋና በዐል (Harvest Thanksgiving) ላይ ለመታደም የተሰበሰቡ ሰዎች ናቸው። ቻንድራ እንደሚሉት ከዚያ ጭፍጨፋ በኋላ በሕንዶች እና በብርታኒያዊ ገዢዎቻቸው መካከል ያለው ግንኙነት ፈጽሞ ተቀየረ። ሕንዶች በአገዛዙ ላይ ያለቸው ተስፋ ተሟጦ አለቀ። ታላቁ የሕንድ ጸረ ኮሎኒያሊዝም ትግል ተቀጣጠለ። አምሪትሳር በሕንድ እና በብሪታንያ የታሪክ ትምህርት ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ነው።

የዐማራን ህዝብ ወደ ቁጣና በመንግስታዊ ሽብር ቡድኑ ተስፋ ሊያስቆርጡ የሚችሉ ሁነቶች ብዙ ነበሩ። ጅምላ መቃብሮች፣ የዘር ፍጅቶች አላስደነገጡንም። አላስቆጡንም። የድል በዓሉን አድዋን አታከብርም መባሉም አላስቆጣም። ከክልሉ ውጭና ውስጥ ለሽብር ሰለባ መሆኑም አልገረመንም። ወደ አዲስአበባ እንዳትገባ መባሉም አልመሰለንም።

የዚህ ሁሉ ጣጣ መውጫ መንገድ አንድ ነው። የዐማራ ህዝብ አይኑን የሸፈነበትን "የኢትዮጵያ" መሀረብ ማውለቅ ነው። ያኔ እየተደረገበት ያለው መከራ ሳይሆን መውጫ መንገዱ እንደ በጋ ሰማይ ጠርቶ ይታየዋል!! 9 ሚሊዮን ህዝብ የተጨፈጨፈበት አንድም ሀገር አንድም ህዝብ የለም። እኛ ብቻ !!
👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የመጨረሻው እራት በግዮን ወንዝ አጠገብ !

የእኛ የዐማራዎች ማን የመሆን ትግል በወል አጠራሩ የዐማራ ብሔርተኝነት ትግል ከተጀመረ ጀምሮ የማንነት ፍለጋውና ፍቅሩ አይሎ ውስጣቸውን ንጦ አይተኬና አይረሴ ዋጋ የከፈሉ ፣ ዛሬም እየከፈሉ ያሉ እና የዐማራን ቀደምትነት ነገ ላይ ለማየት የሚጥሩ፣ የዛሬው የሰቆቃ ዘመን ፈውስ አግኝተው ነገ ላይ ህዝባቾንና ወገናችን በደስታና በሀሴት፣ በክብርና በማንነት ይኖር ዘንድ ልባቸው ላይ ስንቅ የሰነቁ፣ ክንዳቸው ላይ ተስፋ የያዙ፣ አእምሯቸው ላይ የትንሳኤ ፍታቱን ያሰሉ አያሌ ናቸው።

እንዲህ በቀላሉ የሚሆን ነገር ባይኖርም እንኳን እስከ ዓለም ጫፍ ተጉዞ የዐማራን ህልውና ለማቃነት መናኝ ዐማራ ከሆኑት ውስጥ የአንዱ ወንድማችን የበዓል ስጦታ እነሆ ዛሬ በዚህ ቀርቧል!

የመጨረሻው የዐማራ እራት በግዮን ወንዝ አጠገብ !
4