Zenzelima campus Student's union Channel
1.08K subscribers
651 photos
13 videos
51 files
115 links
We are Zenzelima Students Union, dedicated to fostering a vibrant and supportive community for all students at Bahir Dar University. Our mission is to empower students through information sharing, collaboration, and engagement in campus life.
Download Telegram
ማስታወቂያ
👉ለዘንዘልማ ግቢ ግብርና ና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ የክላስ ተወካዮች በሙሉ:-
ነገ አርብ ማለትም:-በቀን 13/02/2019 ዓ.ም  ከቀኑ 7:30AM ላይ ከግብርና ና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ምክትል ዲን ቢሮ ቁጥር 92(አስተዳደር ሕንጻ) በመማር ማስተማር ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ ስላለ ሁላችሁም የክላስ ተወካዮች በስዓቱ እንድትገኙ ለማሳሰብ እወዳለሁ።

👉ማሳሰቢያ:- ይህ ስብሰባ የሚመለከታቸው:- የግብርና ና አካባቢሳይንስ ኮሌጅ ስር ላሉ ትምህርት ክፍሎች ብቻ እና ለሚድ ኬረር ተማሪዎች ተወካይ(2nd -4th year) ነው።
ማለትም:-(DVM,BVSC,Geology&DRMSD)አያካትትም።
👉ማርፈድም ሆነ መቅረት ፈጽሞ የተከለከለ ነው።

👉ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:-0910809848 ይደውሉ።
    የዘንዘልማ ግቢ የተማሪዎች ኅብረት አካዳሚክስ ዘርፍ ተጠሪ
❤4
ሰላም ውድ የዘንዘልማ ግቢ ተማሪዎች!

ዛሬ ማለትም 17/02/2019ዓ.ም ምሽት እራት ላይ ከካፌ በራፍ በስህት ጃንጥላ ያነሳሽ ተማሪ ከዚህ በታች በምፅፍልሽ ስልክ ቁጥር ደውለሽ የባለንብረቷ እንድትመልሽ ስንል በትህትና እንጠይቃለን። በዚህ አጋጣሚ ሌሎች ተማሪዎችም በአግባቡ ንብረታችሁን እንድትይዙ ስል ማሳሰብ እፈልጋለሁ።

0930760762
📢 የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት የአመራር ምርጫ በስኬት ተጠናቀቀ! 🎓🎉

ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም ተመራቂ የሚሆኑ የተማሪዎች ህብረት አመራሮችን በመተካት በመጪው 2019 የትምህርት ዘመን የሚገለግሉ አመራሮችን ለማስመረጥ ላለፉት ሳምንታት ሲያካሂድ የቆየውን ምርጫ ዛሬ በይፋ አጠናቋል! ✨

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት የአመራረጥ መመሪያ መሠረት (40% በፈተናና በልምድ እንዲሁም 60% በተማሪዎች ፓርላማ ድምፅ) በተካሄደው ዴሞክራሲያዊ ሂደት አሸናፊ የሆኑት፡

🏆 የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት፦
👤 ተማሪ አብዮት ግብጹ (ከቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ካምፓስ)

🏆 የተማሪዎች ህብረት ምክትል ፕሬዝዳንት፦
👤 ተማሪ ሃይለማርያም ክንዴ (ከዋና ግቢ)

📍 የታዛቢዎች መገኘት፡ ይህ ታሪካዊ የምርጫ ማጠቃለያ መድረክ በከፍተኛ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣
1⃣በፕሮፌሰር ጸጋዬ ጉጂ (የተማሪዎች ዲን)፣
2⃣በዶክተር ታዬ (የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር)፣
3⃣በኮሚሽነር አበረ (የዩኒቨርሲቲው የጸጥታ እና ደህንነት ኃላፊ) እንዲሁም በመምህራን እና በፓርላማ አባላት ታዛቢነት በሰላምና በታላቅ ግልጽነት ተጠናቋል። 👏

ለአዲሶቹ የተማሪዎች ህብረት አመራሮቻችን መልካም የሥራ ዘመን እንመኛለን!
❤7
ሰላም! ውድ የዘንዘልማ ግቢ ተማሪዎች

Legese Sitotaw የሚል National Id and ATM የያዘ ቦርሳ ያገኛችሁ ተማሪዎች ከዚህ በታች ባለው ስልክ
ደዉላችሁ ቦርሳውን ለባንብረቱ እንድትመልሱ ስንል በትህትና እንጠይቃለን።

0946457531
ስለ CECOE (Coalition of Ethiopian Civil Society Organizations for Elections) ከዚህ በታች በተጠቀሰው ሊንክ በመግባት ስለ
ዲሞክራሲ፣ መልካም አስተዳደር እና የዜግነት ኃላፊነትን የሚዳስሱ አሳታፊ ኮርሶች ማለትምእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሰላማዊና አሳታፊ ማህበረሰብን ለመገንባት በሚያደርገው ጥረት ውስጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የተዘጋጁ ኮርሶች በሶስት ቋንቋ ( አማርኛ ፣ ኦሮምኛ እና እንግሊዝኛ) አሉት:: እነዚህን ኮርሶች አጠናቃችሁ ሰርተፍኬት የምታገኙበትን እድል አመቻችተዋል። እድሉን ተጠቀሙበት! ሊንኩ
👉 https://biquzega.cecoe-tools.org/

በተጨማሪም የተለያዩ መረጃዎችን እና ስልጠናዎችን በተለያዩ በተቋሙ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ከዚህ በታች በተጠቀሰው ሊንክ በመግባት መከታተል ትችላላችሁ 👇
https://linktr.ee/qr/29906878-7653-4fc8-aa5c-2e61a5f783f4