Channel name was changed to «ባይራ የተቀናጀ የልማት ድርጅት Bayra Developmental Organization»
ባይራ የተቀናጀ የልማት ድርጅት በኢፌዲሪ ሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ እውቅና ፈቃድ ያገኘ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት ሲሆን: በደቡብ ክልላዊ መንግስትና አዲስ አበባ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ነው።
ይህ ድርጅት ማህበረሰብ እውቀቶችና እሴቶች በሳይንሳዊ መንገድ ተደግፈው ከተደራጁ ለችግሮች ዘለቄታዊ መፍትሄ ይሰጣሉ ብሎ ያምናል። ስለሆነም ማህበረሰብ በቀል እውቀቶችና እሴቶችን በጥናትና ምርምር በማስደገፍ በሀገራችን ብሎም በአፍሪካ ለሚታዩ ዘርፈ ብዙ ችግሮች የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረብና ወደ ውጤት መቀየር ዋናው አላማ አድርጎ የተነሳ ድርጅት ነው።

በጋሞ 4ሺ 500 ዓመት ያስቆጠረ “ባይራ” የተሰኘ የጥንተ ሰው ቅሬተ አካል ተገኘ
🍊🍊🍊🍊🍊🍊🍊🍊
“ባይራ” የተሰኘ የጥንተ ሰው ቅሬተ አካል ተገኘ ጋሞ በተባለ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ስፍራ ሞጣ በሚባል ዋሻ እድሜው 4ሺ 500 ዓመት የሚገመት የጥንተ የሰው ቅሪተ አካል መገኘቱን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣኝ አስታወቀ። ከግኝቱ ላይ በጥንቃቄ በተወሰደ ናሙና በአፍሪካ በዕድሜ ከፍተኛ የሆነውን የዕድሜ ዘረ መል አወቃቀር ማወቅ ተችሏል። የግኝቱን ስያሜ በተመለከት የጥናት ቡድኑ የተገኘበትን የጋሞ ማህበረሰብ ቋንቋ መሰረት ባደረገ ሁኔታ “ባይራ” ብሎ የሰየመው ሲሆን ትርጉሙም የበኩር ልጅ እንደማለት ነው።
እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ በ2011 በካተሪን አርተር የሚካሄደው የዘርፈ ብዙ የጥናትና ምርምር ቡድን በጋሞ ማህበረሰብ የሀገር ሽማግሌዎች መሪነት የሞጣ ዋሻን የጎበኘ ሲሆን በወቅቱም በሰበሰቧቸው መረጃዎች መሰረት ሌሎች ባለሙያዎችን በማካተት በ2012 በከፊል ባደረገው ቁፋሮ “ባይራ” የተባለውን ቅሪተ አካል ማግኘት ችሏል።”ባይራ” ከ30 እስከ 50 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ ኖሮ የሞተ የአዋቂ ወንድ ቅሬተ አካል እንደሆነ በጥናቱ መረጋገጡን የቅርስ ጥናንትና ጥበቃ ባለስልጣን ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ለመቀላቀል፦ https://telegram.me/bayradevelopmentalorganization

Telegram
ባይራ የተቀናጀ የልማት ድርጅት Bayra Developmental Organization
ባ/የተ/ል/ድ በደቡብ ክልላዊ መንግስትና አዲስ አበባ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ የልማት ማህበር ነው
በእንሰት አዘገጃጀት ሂደት ለዘመናት ማህበረሰቡን ስያሰቃይ ለኖረው አሰልች የህይወት ውጣ ውረድ በቴክሎጂ መፍትሄ እንዲያገኝ ያደረገ ተቋም፡- የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት!
............................................................................................................
የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በርካታ ለሀገርና ለህብረተሰባችን ጠቃሚ እና ችግር ፈቺ የምርምርና የቴክኖሎጂ ስራዎችን በማከናወንና ለውጤት በማብቃት በርካታ ርቀቶችን በመጓዝ ላይ ይገኛል፡፡ ከሚያከናውናቸውና ድጋፍ ከሚያደረግላቸው የምርምር ፕሮጀክቶች ውስጥ ‘’Innovative Enset Technology for gentle processing, value added products, safe storage and longer shelf life’’ የሚል ፕሮጀክት ይገኝበታል፡፡
ይህንኑ ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ካሳሁን ተስፋዬ እና ከፍተኛ የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች በእንሰት አዘገጃጀት ህደት ላይ እየተሰራ ያለውን በኤሊክትሪክ እና በነዳጂ መስራት የሚችሉ ዘመናዊ የእንሰት መፋቂያ፤ መጭመቂያ፤ መቁርጫ ማሽን በአርባ ምንጭ ከተማ ዶርዘ የምርምር ጣቢያ በመገኘት የምርምር ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ደረጃ ገምግሟል፡፡