ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ Balderas for Democracy
3.4K subscribers
875 photos
12 videos
2 files
70 links
Political party
Download Telegram
/
ለሀጫሎ ሁንዴሳ የተሰጠው ክብር፣ በግፍ ለተጨፈጨፉት የወለጋ አማራዎች በሁሉም መስፈርቶች ቢያንስ እንጂ የሚበዛ አይደለም።

ህዝብ ታዝቧል—-የኢትዮዽያ ህዝብ የህሊና ብቻ ሳይሆን የተግባር ምላሽ ይሰጣል!
/
#ኢትዮጵያ
#ዜና ለመከላከያ የቀረበ ጥሪ!

# የወደቁ አስክሬኖችን መከላከያ እንዲቀብርላቸው በወለጋ ከጅምላ ጭፍጨፋው የተረፉት ጠየቁ!!
/
በምዕራብ ወለጋ በመንግሥት አካላት ከሚታገዘው ኦነግ-ሸኔ ጭፍጨፋ የተረፉ አማራዎች፤ በርካታ የጭፍጨፋው ሰለባዎች ከሁለቱም ኃይማኖቶች አስተምሮ ውጭ በአንድ ጉድጓድ መቀበራቸውን ተናገሩ።

ይህ አልበቃ ብሎ፣ ጉድጓዶችን ለመቆፈር ከፍተኛ ጉልበትና ጊዜ የሚጠይቅ ሲሆን፣ በኤክካቬተር ለመቆፈር ቢሞክሩም፣ የአካባቢም የመንግሥት ባለሥልጣናት "የመንግሥትን ገፅታ ይበላሻል" በማለት እንደከለከሏቸውና የሚችሉትን ያህል በእጅ እየቆፈሩ እንደቀበሩ ገልፀዋል።

ሆኖም፣ ቀብረው ሳያጠናቅቁ ገዳይ ታጣቂዎች ደርሰው ጥቃት በመክፈት ከፊል ቀባሪዎችን ረሽነዋቸዋል፤ ከፊሎች ደግሞ አምልጠው ወደ ምስራቅ ወለጋ እና ሆሮጉድሩ ወለጋ ሄደዋል። በመሆኑም፣ የወዳደቁ አስክሬኖችን የሀገር መከላከያ ሰራዊት እንዲቀብርላቸው ጠይቀዋል።

"መከላከያ በፊት እንደተከበብንና ከጭፍጨፋ እንዲያድነን ጠይቀነው ነበር። ነገር ግን አልደረሰልንም። አሁን ቢያንስ አስክሬናቸው የወዳደቁ ቤተሰቦቻችንን አፈር ያልብስልን። ማዳን ባይችል በመቅበር እንኳን ይተባበረን" ብለዋል ከጅምላ ጭፍጨፋው ያመለጡ አማራዎች።
/
#ኢትዮጵያ
#ዜና የችግኝ ተከላው ተቃውሞ ገጥሞታል!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “መንግስት በሰላም ስልጣን እንዲለቅ" ጠየቁ!
/
በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ተከታታይ ጅምላ ጭፍጨፋ በመቃወም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና መምህራን ዛሬ አርብ ሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም.በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።

ተቃውሞውን የጀመሩት የፋሲል፣ ቴዎድሮስ እና ማራኪ ካምፓሶች በተመሳሳይ ጊዜ በመውጣት በጥምረት ነው።

ገዥው ፓርቲ እያካሄደ ያለውን የችግኝ ተከላ ዘመቻ በጎንደር ከተማ ውስጥ ለማስጀመር ቤት ለቤት ቅስቀሳ በማድረግ ላይ እያለ ነበር ተቃውሞው በድንገት የፈነዳው። ኗሪዎችም የችግኝ ተከላ የቤት ለቤት ቅስቀሳውን ባለመቀበል ተቃውሟቸውን ገልፀዋል።

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እየተደረገ ባለው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ "ፋኖ ዛሬም ነገም ወደፊት፣ ብልፅግና ወደ ኋላ፣ መንግሥት በሰላም ና በፍቅር ሥልጣኑን ይልቀቅ፣ እኛም ያልተገደልነው ወለጋ ስላልተገኘን ነው" የሚሉ መፈክሮች ተደምጠዋል።

ፎቶዎቹ—-ከአሻራ ሚዲያ
/
#ኢትዮጵያ
#ሰበር

# በባህርዳር መሸንቲ ኬላ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የፅጥታ ኃይሎች ቆስሉ፣ ሞቱ!!
/
ከባሕርዳር ወጣ ብሎ፣ መሸንቲ አካባቢ ኬላ ጋር በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ የፀጥታ ኃይሎችን ጨምሮ ጉዳት ደርሷል። በተኩስ ልውውጡ ከ5 የሚበልጡ የመንግሰ‍ት ፀጥታ አባላት ቆስለዋል፣ ሞተዋል።
/
#ኢትዮጵያ
#ሰበር

በፍቼ አካባቢ የሕዝብና የጭነት ተሸከርካሪዎች ከእነ ተሳፋሪዎቻቸው ታገቱ!!
/
ከደራ ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ያሉ የሕዝብና የጭነት ተሸከርካሪዎች ከእነ ተሳፋሪዎቻቸው ታገቱ።

እገታው የተፈጸመው ከፍቼ 28 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ
ነው ።

© Roha Media
/
#ኢትዮጵያ
#ሰበር ከታጋቾቹ መካከል ብዙ አማራዎች ይገኙበታል!

# ኦነግ/ሽኔ የሕዝብና የጭነት ተሸከርካሪዎች ከእነ ተሳፋሪዎቻቸው አገተ!!
/
ከደራ ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ያሉ የሕዝብና የጭነት ተሸከርካሪዎች ከእነ ተሳፋሪዎቻቸው በኦነግ/ሽኔ ታገቱ። ከታጋቾቹ መካከል በብዛት አማሮች ይገኙበታል። ኦነግ/ሽኔ በአማራዎች ላይ የዘር ፍጅት እየፈፀመ ይገኛል።

እገታው የተፈጸመው ከፍቼ 28 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ
በምትገኘው ሂደቡአቦቴ ወረዳ፣ ወዘሚ በሚባል መንደር ውስጥ ነው። ተሳፋሪዎቹ መንገድ የጀመሩት ደግሞ፣ ከፍቼ 110 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው የደራ ወረዳ ዋና ከተማ ከጉንዶ መስቀል ነበር።

አብዛኞች ታጋቾች በኩዩ፣ በአቦቴና በወረጃርሶ ወረዳዎች መካከል ወደሚገኝና ጨለንቆ ወደ ሚባል ቦታ ተወስደዋል።

የደራ ፍቼ አዲስ አበባ መንገድ ለስምንት ወራት ያህል ተዘግቶ የነበረ ሲሆን፣ ሰራ የጀመረው በቅርቡ ነው።

ዘገባው— ሮሃ እና አሻራ ሚዲያዎች ካወጧቸው ዘገባዎች የተጠናከረ።
/
#ኢትዮጵያ
#ሰበር ልዩ ቃለ ምልልሱን በድምፅ ያድምጡ!!

በጋምቤላ ባለፈው ሰሞን በአደባባይ ከተረሸኑት መካከል ወላይታዎችና አማሮች ይገኙበታል!!
/
በጋምቤላ ሰኔ 7/2014 ዓ.ም በክልሉ በአደባባይ ከተረሸኑት መካከል "አማሮች እና ወላይታዎች አሉበት” ሲሉ የሟች ቤተሰቦች ገለፁ።

የተረሸኗቸውን አስከሬን በሲኖትራክ ጭነው ጫካ በመውሰድ በጅምላ ቀበረዋቸዋልም ብለዋል።የሟች ወገኖች “ከተረሸኑ በኋላ በወግ ወስደን እንዳንቀብር ተደርገናል”በማለት እያማረሩ ናቸው።

ጥቃቱን የከፋ የሚያደርገው፣ ቆስለው ህክምና ማግኘት ሲገባቸው ፣ ነፍሳቸው ሳይወጣ በጅምላ የተቀበሩ መኖራቸው ነው ሲሉ የሟች ቤተሰቦች በስልክ ገልፀዋል።

"ቀያዮችን ግደሏቸው" የሚል አባባል በከተማው ስላለ ፣ዛሬም ድረስ እንደለልብ ተንቀሳቅሰን ፍትህ መጠየቅ አልቻልንም፣ የተዘጉ መንገዶችም አልተከፈቱም” በለዋል።

ተጨማሪ ዝርዝር ሃሳቡን ከስር በተቀመጠው Link ቃለ ምልልስ ያድምጡ።


ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ


https://fb.watch/dSMEZBT8xr/
#ዜና በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል!!

# ስለወለጋው ጭፍጨፋ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ተማሪዎች በፖሊስ ተደበደቡ!!
/
የወለጋውን የዘር ማጥፋት ለመቃዎም የወጡ የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ተማሪዎች በፖሊስ ተደበደቡ!!

ተማሪዎቹ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያቸውን በማቅረብ ላይ ሳሉ ነበር የመንግስት ታጣቂ ኃይሎች ድብደባ የፈፀሙት።

"የአማራ የዘር ማጥፋት ይቁም፤በማንነታችን መገደል ይብቃ፣ንፁሃን እየሞቱ መማር አልቻልንም፣ስርዓቱ በቃን”እና የመሳሰሉ መፈክሮችን በመያዝ ነበር ተማሪዎቹ ድምፃቸውን ያሰሙት።

ይሁን እንጅ፣ የዘር ማጥፈፉትን "መቃዎም አትችሉም"በሚል የመንግስት ታጣቂዎች በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል።

በህክምና ላይ የሚገኙ ተማሪዎች እንዳሉ ለማዎቅ ተችሏል።
/
#ኢትዮዸያ
#ሰበር የአ/አ ዩኒቨርስቲ አማራ ተማሪዎች እየታሰሩ ናቸው!

# በዩኒቨርስቲዎች ተቃውሞው ቀጥሏል!!
/
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፤ የዘር ፍጅቱን በመቃወም ሰልፍ እድርገዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አማራ ተማሪዎች እየታሰሩ ናቸው።

ተማሪዎቹ ዛሬ ለተጨፈጨፉት ድምፃቸውን ለማሰማት ባደረጉት ጥረት ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸዋል።

አሁን ደግሞ፣ አማራ ተማሪዎች እየተለዩ እየታሰሩና እየታደኑ ይገኛሉ።
/
#ኢትዮጵያ
# ወቅታዊ መግለጫ!

# በአማራ ላይ የሚፈፀመውን ጭፍጨፋ ሁሉም የክልል መስተዳድሮች በግልፅ እንዲያወግዙ እንጠይቃለን!!
/
/
ኦህዴድ ብልፅግና ቤተ መንግሥት ከገባ ጀምሮ አያሌ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይ ግን የአማራ ህዝብ፣ ከመቸውም ጊዜ በላይ ለህልፈተ ህይወት፤ ለስደት እና ለመፈናቀል ተዳርገዋል፡፡

የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና፣ ህግን የፖለቲካ ተቀናቃኞችን ማጥቂያ አደረገው እንጅ፣ የህግ የበላይነትን ማስፈን አልቻለም።

ዜጎች ያሰ ማንም ጠያቂ ለዘመናት በኖሩበት ቀያቸው በጠራራ ፀሃይ ሲገደሉ ቆይተው፣ ባልደራስ በግምባር ቀደምነት ባደረገው ትግል፣ በአሁኑ ግዜ የዘር ማጥፋቱ እና የዘር ማፅዳቱን ዓለም በአንክሮ እየመረመረው ይገኛል፡፡ በተገኘው ውጤት ባልደራስ በእጅጉ ተደስቷል።

የኦህዴድ/ብልፅግና መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን ስልታዊ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማፅዳት ዘመቻ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በፅኑ እያወገዘ ፣ከኦህዴድ/ብልፅግና ጋር አብራችሁ የምትሰሩ ክልላዊ መስተዳድሮች እና ባለስልጣናት በታሪክ፣ በህግ እና በሞራል ተጠያቂነት እንደሚኖርባችሁ አውቃችሁ ከወዲሁ ድርጊቱን በማውገዝ የራሳችሁን እርምጃ እንድትወስዱ እያሳሰብን፣ ከዚህ መግለጫ ጋር በአባሪነት የተያያዘውን ደብዳቤ እንዲደርሳችሁ ለማድረግ ተገደናል።

ይህ ደብዳቤ የሚላክላቸዉ:-
ለአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣
ለአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣
ለሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣
ለደቡብ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣
ለጋምቤላ እና ለሌሎችም ብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት፣

ለሙሁራን፣ ለሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ለኃይማኖት ተቋማት፣ ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ለአፍሪካ ህብረት፣ ለተባበሩት መንግስታት)፡፡

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ
አዲስ አበባ
ሰኔ 20 2022
/
#ኢትዮጵያ
#መረጃ

# የሱዳን ታጣቂዎች የአርማጭሆ ወረዳን “ገላል ውሃ”
በከባድ መሳሪያ ሲደበድቡ ዋሉ!!
/
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን፣ ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ፣ የሱዳን ታጣቂዎች “ገላል ውሀ” የተባለች አካባቢን በከባድ መሳሪያ ሲደበድቡ መዋላቸውን የአካባቢው ነዋሪ የሆኑት አቶ ሲሳይ አሸብር ገልፀዋል።

ጥቃቱ ካለፈው ሰኔ 15 ጀምሮ አልፎ አልፎ ነበር። ዛሬ ጥቃቱ የተፈፀመው ከጠዋቱ 2ሰዓት እስከ 7 ድረስ ነበር ብለዋል።

ሌላው የዓይን እማኝ፣ ሱዳኖች፣ “የአገር ውስጥ አሸባሪዎች” ካሏቸው ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የአካባቢውን ባለሀብት ወደ እርሻ ስራ እንዳይገባ እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡

የምዕራብ ጎንደር ዞን አንድ የመንግስት ኃላፊ ስለጉዳዩ ተጠይቀው፣ ታጣቂዎቹ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ጅምሮ ጥቃት መክፈታቸውን አምነዋል።
/
#ኢትዮጵያ
# የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የረሃብ አድማ አደረጉ!!

# በባህር ዳር የአማራ ፋኖ ሰብሳቢ ቴዎድሮስ ጌታቸው እና ሌሎች የስራ አሰፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ታፈኑ!!
/
የየባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በወለጋ ለተጨፈጨፉ አማራዎች የህሌና ፀሎት በማድረግ የምግብ አድማ አድርገዋል።

ተማሪዎቹ የወለጋውን ጭፍጨፋ ከማውገዛቸው ባሻገር፣ ገዢው ፓርቲ ስልጣን እንዲለቅ መጠየቃቸው ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የባህር ዳር አማራ ፋኖ ሰብሳቢ ቴዎድሮስ ጌታቸው ታፍኗል።የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ሰብሳቢ ፋኖ ቴዎድሮስ ጌታቸው፣ የአማራ ህዝብ በገጠመው የህልውና ጦርነት ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ወደ ጋሸና የዘመተና የአማራ ፋኖ በባህር ዳር በጋሸና በነበረው አኩሪ ገድል የአንበሳውን ድርሻ የተወጣ ብርቱ ታጋይ ነው።
ትላንት ከምሽቱ 4 ሰዓት አፋኝ ቡድን ወደ መኖሪያ ቤቱ በመሄድ ያለምንም ምክንያት አፍነው ወደ ጣቢያ ወስደው አሰረውታል።

በተጨማሪም፣ የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ስራ አሰፈፃሚ እና አባላትን ከሌሊቱ 8:00 ሰዐት ከመኖሪያ ቤታቸው በኃይል ታፍነው ተወስደዋል። ከእነዚህ መካከል፣ ፋኖ ሀብታሙ ማንደፍሮ እና ፋኖ ማንችሎት እሱባለው ይገኙበታል።

ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ
/
#ኢትዮጵያ