Al EHSAN አል_ኢህሳን
182 subscribers
417 photos
45 videos
2 files
662 links
የቻናሉ አላማ
1 ባለን አቅም እስልምናን በአግባቡ ለኡማው ማድረስ
2 ሙስሊሞችን በድናቸውም ይሁን በዱኒያ እውቀታቸው የነቁ እንድሆኑ መገፋፋት
3 ለወጣቶች ምክር
4 በልዩ መልኩ ሴቶችን ማንቃትና ሌሎቹም አለማዊና መንፈሳዊ ት/ቶች ይገኙበታል።

ውድና የተከበራቹ የአል ኢህሳን ቻናል ቤተሰቦች ሆይ ውብና ማራኪ የሆኑ ሀሳብ አስተያያታቹ እንዳይለይን

ለአስተያት @S1u9l
አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇
Download Telegram
👇👇👇


በጣም የሚገርም ወንድማማችነት

ሰለፎች ዘንድ
👇


ከቀደምት ሰለፎች መካከል አንድ ሰው ወደ ጓደኛው ቤት ይሄዳል።
ጓደኛውም ምነው በዚህ ሰአት መጣህ? ይለዋል። "እሱም አራት መቶ ዲርሃም አለብኝና ክፈልልኝ" ይለዋል ።
ጓደኛውም ቤቱ ይገባና አራት መቶ ዲርሀም መዝኖ ይሰጠዋል።
ከዘም ወደ ቤቱ ገብቶ ማልቀስ ይጀምራል ሚስቱም ማልቀሱን ስታይ ገንዘቡን የሚትፈልገው ከሆነና መስጠት የማትችል ከሆነ ለምን የለኝም ብለህ ምክንያት አታቀርብም ነበር? አሁን ማልቀስህ ምን ያደርግልሃል ? አለችው

እሱም በጣም የሚገርምና ልብን የሚነካ ንግግር ተናገራት 👇

👉እኔ እኮ የማለቅሰው ወንድሜ ቤቴ ድረስ መጥቶ ቸግሮት ችግሩን እስኪነግረኝ ድረስ ወንድሜ የሚኖርበትን ሁኔታ ባለማወቄ ነው ኣላት

📚 አት-ተብሲራ 2/263
ዛሬ እኛና እነሱ ዬት ነው ያለነው ሰዎች? እኛም አሁን ከነሱ ጀነት ለመግባት እናስባለን? አላህ በእዝነቱ ይድረስልን እንጂ ከባድ ነው

https://t.me/B1e9h
አንዘርቱኩሙ ናር
አህመድ አደም
አዋጅ አዋጅ አዋጅ

ወላሂ አው ጀሃነም በጣም ያስፈራል አላህ ሁላችንም ጀሃነም ከመውረድ ይጠብቀን አደራ ሁላችንም እናድምጠው እንዳታልፍ

ሸይሃችን አህመድ አደም አላህ ይጠብቅልን

https://t.me/B1e9h
☞  ተራራን  መውጣት የፈራ, ሁሌ በሸለቆ  ውስጥ  ይኖራል❗️

☞ አኬራን የዘነጋ ሰው , በዱንያ ፍቅር እንደተጠማ ይሞታል !

☞" በኢልም ጥላ ስር ጥቂት ሰዓታትን መታገስ ያቃተው ሰው እድሜ ልኩን በጃሂልነት ጥላ ሰር ይኖራል❗️"

https://t.me/B1e9h
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህንን የሸይኹን መልዕክት በምገባ አድምጡት በተለይ እህቶች

ሸይኽ አብዱረዛቅ አልበድር

https://t.me/B1e9h
​​አስባቹታል ግን‼️

#ፍቅር በነፃ
#አየር በነፃ
#ንስሀ በነፃ
#የዘላለም_ህይወት በነፃ
------------------------------
#መጠጥ በክፍያ
#ዝሙት በክፍያ
#ጭፈራ_ቤት በክፍያ
#ሺሻ_ጫት በክፍያ

‼️እንዴት ከፍለን ገሀነም እንገባለን
እናስብ ወገን!!!

https://t.me/B1e9h
ጥብቅ ማሳሰቢያ ኡዲህያ ለምታርዱ በሙሉ👇



ዛሬ ዕሮብ ዙል-ቀዕደ ቀን 28 ነው ።
ይህ ማለት ደግሞ ምናልባት ወሩ በ29 ካለቀ የወሩ መጨረሻ ነገ ሐሙስ ሊሆን ይችላልነ

የወሩ መጨረሻ ነገ ሐሙስ ከሆነ ደግሞ ቀጥሎ የምጠቅሳቸውን ነገሮችን ኡዱሒያ ለሚያደርግ ሰው ማስወገድ ስለማይፈቀድለት ከአሁኑ ቅድመ ጥንቃቄ ማደረግ ይኖርበታል 👇

1 ፀጉር መቁረጥ
2 ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር
3 ጥፍሩን መቁረጥ
4 የብብትና የብሊት ፀጉርን ማስወገድ የፈለገ ሰው ከነገ ከሐሙስ ማሳለፍ የለበትም

👉ነብዩ ሰለላሁ አለይሒ ወሰለም እንዲህ ብሏሉ 👇

የዙል-ሒጃ ወር የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት ስገቡ ከእናንተ አንዳቹ ኡዱሒያን ማድረግ ከፈለገ ከፀጉሩም ይሁን ከሰውነቱ ምንም ነገር እንዳይነካ።

አደራ ይህንን አሳሳቢና አስቸኳይ መልዕክት ለሁሉም ሙስሊሞች በማሰራጨት ሙስሊሞችን ከስህተት እንታደግ

https://t.me/B1e9h
የዘንድሮ ወርቃማዎቹ የዙል-ሒጃ የመጀመሪያ ቀናት መቼ ይጀምራሉ?

ዛሬ ዕለተ ረቡዕ በኢትዮጵያ አቆጣጠርግንቦት 28, 2016 E.C. ነው። በኢስላማዊ ካላንደር (በሂጅሪያ) አቆጣጠር ደግሞ ዙል-ቂዕዳህ 28, 1445 H.C. ነው። በፈረንጆቹ ጁን 05, 2024 G.C. ነው።

የዙል-ቂዕዳህ ወር በ29 ቀናት ከተጠናቀቀ ከነገ በኋላ ጁሙዓህ ግንቦት 30, 2016 ይጀመራሉ። የዙል-ቂዕዳህ ጨረቃ 30 ከሞላች ግን ወርቃማዎቹ የዙል-ሒጃ 10 ቀናት ቅዳሜ ሰኔ 01, 2016 E.C. ይጀመራሉ። በኸይር ለማሳለፍ ከወዲሁ ዝግጁ እንሁን።

https://t.me/B1e9h
አስርቱ የዙልሒጃ ቀናት ||
ኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ

NesihaTv

https://youtu.be/tKFIPtXKcno

https://t.me/B1e9h
➡️ ሶስት ትላልቅ ወንዞች

ኢብኑል ቀይም ረሂመሁላሁ እንዲህ ይላል :-
" ለወንጀለኞች በዱንያ ላይ ከወንጀላቸው የሚፀዱባቸው ሶስት ትላልቅ ወንዞች አሏቸው
እነዚህ ወንዞች ካላፀዱአቸው የቂያማ ቀን በጀሀነም ወንዝ ነው የሚፀዱት


1. የተውበተ አንነሱሁ ወንዝ
2. ሀጢያትን የምታብሰው የመልካም ስራ ወንዝ
3. ወንጀልን የሚያጥብ የሙሲባ ወንዝ
አላህ ለባሪያው መልካም ከሻለት ከእነዚህ ወንዞች በአንደኛው ያስገባዋል ንፁህ የተጥራራ ሆኖ ወደ ቂያማ ከወረደ አራተኛ ማፅጃ አያስፈልገውም "

መዳሪጁ ሳሊኪን ( 1/64)

https://t.me/B1e9h
በሃገረ ሳዑዲ ዐረቢያ የወርሃ ዙል-ሒጃህ ጨረቃ ዛሬ ሐሙስ ስለታየች ነገ ጁሙዓህ ግንቦት 30, 2016 E.C. የዙል-ሒጃህ ወር የመጀመሪያው ቀን ይሆንና ወርቃማዎቹ የዙል-ሒጃህ 10 ቀናት ከነገ ይጀምራሉ። ስለሆነም ቅዳሜ ጁን 15, 2024 (ሰኔ 08, 2016 E.C.) የዕለተ ዐረፋህ ቀን ሲሆን እሁድ ጁን 16 (ሰኔ 09) ዒደ-ል-አዽሓህ ይሆናል። አላህ በሰላም ያድርሰን

እነዚህን ወርቃማ ቀናቶች በዒባዳህ ለማሳለፍ ከወዲሁ ዝግጅት አድርጉ። ቀናቶቹን ከምታሳልፉባቸው ዒባዳዎች መካከል፤ ጾም፣ ዚክር፣ ቁርኣን መቅራት፣ ሶደቃ፣ ለቻለ ሰው ሐጅና መሰል በጎ ተግባራትን ማከናወን ይገኙበታል። አላህ ያበርታን።

ሌሎችንም አስታውሱ!


https://t.me/B1e9h
👉  የዒደል አድሓ ተክቢር

     የዒደል አድሓ ተክቢራ ዙል ሒጃ ከገባበት ቀን ( የዙል ቂዕዳ ወር አልቆ የዙል ሒጃ ጨረቃ ከታየበት ጊዜ ) ጀምሮ እስከ አያሙ ተሽሪቅ መጨረሻ ድረስ ይፈቀዳል ። ይህ ልቅ የሆነው ተክቢራ ( በማንኛውም ሳአተ የሚባለው ) ሲሆን የተገደበው ወይም ከሶላት በኋላ የሚባለው ደግሞ የዙል ሒጃ 9ኛ ቀን ፈጅር ሶላት ላይ ተጀምሮ የመጨረሻው አያመ ተሽሪቅ ዐስር ሶያት ላይ ያበቃል ። ወሩ የዚክርና የመልካም ስራ ስለሆነ ከተክቢራ እንዳንዘናጋ እንጠቀምበት ።

https://t.me/B1e9h
ይህ ምልክት ነመስቲ ይባላል ። የሂንዱስ እምነት ተከታዮች የሰላምታ ምልክት ነው ።
ሂንዱሶች በአላህ መኖር የማያምኑ ከሀዲያን ናቸው ። በዚህ ምልክት የሚፈልጉበት መልእክት በውስጤ ያለው አምላክ ባንተ ውስጥ ያለውን አምላክ ሰላም ይለዋል የሚል ነው ።
የሁለቱ መዳፎች መጣመር በኔና ባንተ ውስጥ ያሉት አምላኮች ተጣምረዋል አንድ ሆነዋል የሚል እምነት አላቸው ። ይህ ኩፍር መሆኑ ግልፅና የኢስላምን አስተምሮ የሚፃረር የወሕደቲል ውጁድ ዐቂዳ ነው ። እኛ ሙስሊሞች ከእንደዚህ አይነት ምልክት የተብቃቃን ነን ።
አላህን ስንለምን ሁለቱ መዳፎቻችንን ዘርግተን ገጥመን በዚህ መልኩ " 🤲 " ነው መሆን ያለበት ። ለዚህም የሚከተለው የአላህ መልእክተኛ ንግግር መረጃችን ነው ።
قال النبيﷺ :
« اذا سألتُم الله فأسألوهُ بِبُطونِ أكفِّكُم ولا تَسألوهُ بظهورها »
الالباني صحيح أبي داود

https://t.me/B1e9h
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ስለ አስሩ የዙል ሒጃህ ቀናት አጭር ማስታወሻ!

ከነሲሓ ቲቪ

ሼር በማድረግ ሌሎች እንዲጠቀሙበት ያስተላልፉ!

https://t.me/B1e9h
ለነገህ ምን አዘጋጅተሃል?

አዎ ለቀብር ጨለማ !!
ለቂያማ ጭንቀት !!
በሲራጥ ለማለፍ !!
አላህ ፊት ቁመን ስንጠየቅ ላለው ጭንቀት !!
በጥቅሉ ከሞት በሗላ ላለው ሂወታችን  ምን አዘጋጅተናል?

አላህ (ሱብሓነሁ ወተዐላ) እንድህ ይላል:-

{ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَلْتَنظُرْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ لِغَدٍ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ }

« እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡ » [ሐሽር (18)]

https://t.me/B1e9h
ኢማም አቡ ሃቲም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ👇


" ከንግድ ሁሉ ትርፋማው፦ አለህን ማውሳት ነው።

" ከንግድ ሁሉ ኪሳራው ፦ ሰውን ማውሳት ነው።


📚 በህጀቱል መጃሊስ 86

👉ልብ በሉ! ሸይኹ ለምን ይህን ያለ ይመስላቹሃል? ምኖደውን ሰው/አሰሪያችንን/አንድ ታወቂ ሰውን ብዙ ግዜ እናወሰዋለን ነገር ግን እኛ ለሱ ትዝም አንለውም ብንለውም ምንም አያደርግልንም
★አላህ ግን ባወሳቹኝ ቁጥር አወሳቹሃለው ብሎናል ከዚህም አልፎ በጀማዓ ስናወሳው ከመላኢካዎች እንደምያወሳን ነግሮናል
ታድያ ማነው ያተረፈው ማነው የከሰረው?

https://t.me/B1e9h
ነጋዴ ትርፍ በሚታፈስበት ወቅት ከተዘናጋ መቼ ሊያተርፍ ነው⁉️
በነዚህ ቀናቸውም ሌሊታቸውም በተባረኩ የዙልሒጃ ወርቃማ ቀናት እንጠቀምባቸው። ጾም መጾም፣ ሶደቃ መሰደቅ፣ ዚክር ማብዛት፣ ቁርኣን መቅራት… ኸይር ነገር ላይ ሁሉ እንበርታ። አላህ ያግራልን!

https://t.me/B1e9h
የቀለበት አደራረግ

ሴት ልጅ የወርቅም ይሁን የብር ቀለበት በፈለገችው ጣት ላይ ማድረግ ትችላለች። ነገር ግን ቤት ውስጥም ይሁን ከቤት ውጪ ስትሆን ጌጧን ባዕድ/አጅነቢይ ወንድ እንዳያይ ጌጡን መሸፈን ግዴታ ይሆንባታል። ይህም የቁርኣን ህግና ትእዛዝ ነው።

ወንድ ልጅ ግን የወርቅ ቀለብት ማድረግ አይችልም።
ከወርቅና ከብረት ውጪ ካሉ ነገሮች የተሰራ (የብርም ይሁን ሌላ) ቀለበት ሲያደርግ በመጨረሻው ትንሹ ወይም ከሱ ቀጥሎ ባለው ጣት እንጂ በመሃለኛው ረጅሙ ጣት፣ ከሱ ቀጥሎ ባለው ሌባ (አመልካች) ጣትና አውራ ጣት ላይ ለወንድ ልጅ ቀለበት ማድረግ አይቻልም።
በተለይ በመሃለኛው ረጅሙ ጣትና ቀጥሎ ባለው አመልካች ጣት ላይ ቀለበት ማድረግን ነቢዩ صلى الله عليه وسلم
በግልጽ ከልክለዋል።
ከመሆኑም ጋር ብዙ ወንዶች በነዚህ ጣቶች ቀለበት ሲያደርጉ ይታያል።
ዲናችንን እንወቅ! እውቀት ብርሃን ነው፤ አላዋቂነት ጨለማ ነው።

ኡስታዝ አሕመድ ኣደም

https://t.me/B1e9h
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በከዓባ ዙሪያ “ጠዋፍ” የመራችው ህጻኗ ልጅ

በሳዑዲ አረቢያ መካ የሃጅ ስነስርዓት በሚረግበት ሰዓት በከዓባ ዙሪያ “ጠዋፍ” የመራችው ህጻኗ ልጅ የበርካቶችን ቀልብ ስባለች።

ከእሲያ የሄደችው ህጻኗ ልጅ በአባቷ ትክሻ ላይ ሆና ጠዋፍ ስትመራ የነበረ ሲሆን፤ ሃጃጆችም ልጅ ሲከተሉ ነበር።

https://t.me/B1e9h
👌🟩አስቸኳይ መልእክት ለአረፋ ወደ ገጠር ተጓዦች በሙሉ


بسم اللّه الرحمن الرحيم. الحمد للّه رب العالمين، والصلاة والسلام على أشرف الأنبياء والمرسلين، نبيّنا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين، ومن تبعهم بإحسان إلى يوم الدين.
اما بعد
ለዒድ አል አድሃ)(አረፋ) ገጠር እናትና አባቶቻችሁ ጋር ለመሄድ ያሰባቹ ውድ እህትና ወንድሞች ጥቂት ማስታወሻዎቼ ለናንተ
👇👇👇👇👇👇👇
1 ስትሄድ እነሱን በቻልከው መጠን አስደስተህ ለመመለስ ሞክር ልብ በል የምታስደስታቸው ዱንያዊ ቁሳቁስ ስለያዝክ ብቻ አይደለም
የመጀመሪያ የሄድክ ቀን እነሱን አንጀታቸው የሚያርስ ቃላቶችን ተጠቅመህ አስደስታቸው አብሽር በላቸው ችግርህ; ጭንቀትህ አትንገራቸው  ከጎናቸው አትራቅ ገላቸውን እግራቸውን እጠባቸው ቀጣይ አረፋ ኢንሻአሏህ ሃጅ አስደርጋቸዋለሁ በላቸው ባትወስዳቸው እንደወሰድካቸው ይሰማቸዋል ደስታቸው ይፋፋል ደሞም አላህ ያሳካልህ ይሆናል ከልብህ በላቸው።

2 ከሽርክና ቢዳዓ ደጋግመህ አስጠንቅቃቸው ልብ በል አሁን ዱንያው ቁሳቁስ በመግዛት ብቻ የሚደሰቱት ሁሉ ጊዜያዊ ነው ተውሂድን እንዲረዱ ካላስረዳሃቸው ዘላለማዊ ደስታን ያጣሉ እና ይህ ላንተ ፀፀት ነው የመጀመሪው ሃቃቸው ያለብህም ይህን በማስረዳት ነው በሚገባቸው ቋንቋ ከሽርክ የሚያስጠነቅቁ ሙሃደራዎችን በሚሞር ጭነህ ከሬዲዮ ጋር ይዘህላቸው ሂድ።

☘️3.ለዝየራ ብለህ የምትሄድም ሆነ እዚህ የምትቀመጥ እባክህ ባለህ ነገር አትሰስትባቸው 1000 ብር ካለህ ጫቱን ተወውና 800 ለነሱ ስጣቸው ወላሂ አትጠራጠር
800000000.......  አድርጎ አሏህ ይተካልሃል

🔻አስበህ ታውቃለህ ግን እናትህ እኮ አንተ እዚህ በስልክ ካርድ የምታጠፋው 50 ብር ለማግኘት ነው ሰው ቤት እንሰት ስትፍቅ የምትውለው
አባትህ እኮ ያ በካርድ የምታወጣው 100 ለማግኘት ነው ጠዋት 2:00 ወጥቶ 11:00 ድረስ ሰው ጓሮ የሚያርሰው እና እጁ የተሰነጣጠቀው
እና ትንሽ አታስብም ኪስህ ውስጥ 1000 ይዘህ 500 ለጫት ስታወጣው‼️‼️‼️
ወላሂ እንባ እየተናነቀኝ ነው ይህን መልእክት ያካፈልኩህ


አንተ እዚ ሰው ለመጋበዝ ትሽቀዳደማለህ እሷ እዛ ተርባ ለ 50 ብር ወገቧ ሰው ቤት እንሰት እየፋቀች ተጣሞ ወላሂ ልብ ይነካል
እስቲ ይህን መልእክቴ ካነበብክ በኋላ ወደራስህ ተመለስ
አባትህ እስክታድግ ለዚህ አብቅቶሃል በተራህ አሳድገወኸ እናትህ እስከዚህ እየሸናህባት አሳድጋሃለች አሁን እስቲ በተራዋ አሳድጋት ከኪሱ ብር አይለይ እቤቱ ከቦርሳዋ አንተ እያለህ ብር አትጣ እሷ በቃ  ሰው ቤት መንከራተት ይብቃት።


4.እህቴ ሆይ ለበአል ለዝየራ ብለሽ ወላጆችሽ ጋር ሄደሽ በበአሉ እራሱ አንቺ ቁጭ ብለሽ እሷ እናትሽ ሁሉንም ሰርታ አቀራርባልሽ ቁጭ ብለሽ የምትበዪ ከሆነ ወሏሂ ሰጋሁልሽ !! እሺ መቼ ነው ከድካሟ የምታርፈው?? ስለዚህ ነቃ በይ እስከትመለሺ ድረስ እሷን በክብር ቁጭ አድርገሽ ጎንዋን አሳርፊላት ኻድሚያት አለሁልሽ በያት አብሽር በያት ገላዋን እጠብያት ልብሷን እጠቢላት ፀጉርዋን አበጥሪላት ፏ አድርገሽ ሙሽራ አስመስለሽ ቁጭ አድረገሻት አዘዥኝ በያት ከዛም በመቀጠል ወናውና አንገብጋቢው አንቺም ከቢዳዓና ከሽርክ አስጠንቅቂያት።

5. ለአረፋ ቤተሰብ ዝየራ ብላችሁ እዚም እዛም ቤት ስትዞሩ ውላቹ አድራችሁ የራሳቹ እቤት የሆነች ደቂቃ ብቻ ገባ ወጣ የምትሉ ደሞ በጣም የሚገርም ነገር ነው ለምንድነው የሄድኩት ብላችሁ እስቲ እራሳችሁን ጠይቁ
ኡሚና ባባ እኮ አይናችሁን ትኩር ብለው ጠግበው ሊያዩዋችሁ እንኳን ሳያገኟቹ በ3 ተኛ ወይም በ4ተኛ ቀን ልትሰናበታቸው አጠገባቸው ትሄዳላቹ ይህ ከሆነ
ወላሂ በጣም ልብ የሚሰብር ነገር ነው
ስለዚህ ወንድሜ ልትዘይራቸው ሄድክ አይደል በቃ ካጠገባቸው አትራቅ አጫውታቸው ;አማክራቸው  የቀጣዩ አረፋ እኮ ልታገኛቸውም ላታገኛቸውም ትችላለህ አሏህ ሃያታቸው ከመልካም ስራ ጋር ያርዝመው እንጂ አስበኸዋል እና ቆም ብለህ አስብበት።


6.ሲያማክሩህ ከልብህ ሆነህ አውራቸው ስልክ እየጎረጎርክ አታውራቸው ;አታመናጭቃቸው ;አትገላምጣቸው።

☘️6. እህቴ ሆይ ለዝየራ ብለሽ ሄደሽ የወንጀል በር መክፈቻ ከመሆን ተጠንቀቂ እራስሽን ገላልጠሽ አትሂጂ የሰፈር ልጅ ነው በሚል እዚና እዚያ ከአጅ ነቢ ጋር አትጃጃይ ይባስ ብሎ ውሎሽም አዳርሽም የሰፈር ልጆች ናቸው ብሎ ከነሱ ጋር ማድረግስ ምን ይሉት ቂልነት እንደሆነ አይገባኝም ።

☘️7.ስትሄዱ ጊዜ መኪና ውስጥ አላህን ልትፈሩ ይገባል ያ ሁሉ መንገድ በተክቢራ በአዝካር በቂርአት እንደዚሁም ሙሃደራ ቁርአን በማድመጥ ልታሳልፈው ልታሳልፊው ይገባል ።
አስተውለሃል በዛ ሁኔታ ሆነህ አላህን ብትገናኘው??
በተቃራኒው ደሞ እየቃምክ በዘፈን ሰክረህ ከአጅ ነቢ ጋር እየተጃጃልክ ያ አጅሬው ሞት ከተፍ ቢል ??ስለዚህ ቆም ብለህ አስብ!
አሏህ እንዲህ ይላል

وَمَا تَدْرِي نَفْسٌ مَّاذَا تَكْسِبُ غَدًا ۖ وَمَا تَدْرِي نَفْسٌ بِأَيِّ أَرْضٍ تَمُوتُ ۚ

"ማንኛይቱ ነፍስም ነገ የምትሠራውን አታውቅም፡፡ ማንኛይቱ ነፍስም በየትኛው ምድር እንደምትሞት አታውቅም"።


☘️8.እህት ሚስት ያለህ ሆይ ለብቻዋ አትልቀቃት አንድ መህረም ከሷ ጋር አድርግላት።

☘️9. ከሄዳችሁ በኋላ መጥፎ ነገር ስታዩ ለመከልከል ሞክሩ ምክንያቱም ገጠራማው ማህበረሰብ ላይ ወላጆቻችን  አብዘሃኛው በለማወቅ ነውና የሚፈፅሙት።

🌿10.በቻልከው መጠን ኸይር የተባለ ነገር ሁሉ አድርገህላቸው ምርቃታቸው ለመቀበል ታገል ምርቃታቸው ጠብ አይልምና በግልፅ ታየዋለህ

🌲11.ተሳስተህም እንኳን ሚያስከፋቸው ነገር ላለማድረግ ጥረት አድርግ ወላሂ ወቢላህ ወተሏህ የበደልካቸው እንደህ
ሆነ እርግማናቸው ያጠፋሃል ፊ ዱንያ ወል አኺራህ የሰው በታች ያደርገሃል ሲቀጥል ጀነት በማን እግር ስር ነች??? መልሱን ተውቁታላችሁ አይደል?? አሁንም አትጠራጠር ምታመናጭቃቸው ከሆነ ምትገላምጣቸው ከሆነ ምትበድላቸው ከሆነ አንተ በቀን የፈለግከውን አማርጠህ እየበላህ እነሱ ተርበው እንደሆነ ወላሂ ለራስህ ፍራ !!!

☘️12.እህት ወንድሞች ኖሯቹህ ለነሱ ልብስ እንደዚሁም ሌላ ቁራቁስ የምትገዙ ምን አይነት ልብስና እቃ መግዛት እንዳለባችሁ እወቁ ! ታናሽ እህት ካለህ ለሷ ጥብቅ ያለ ጉርድ ቀሚስ የምትገዛላት ከሆነ ታናሽ ወኔድም ኖሮህ ለሱ ቡጭቅጥቅ ያለ የምእራባውያን ልብስ የምትገዛለት ከሆነ ወደ ጥፋት ልትመራቸው እንደወረድክ አስበው ስለዚህ መፍትሄው ልንገርህ
እህት ካለችህ ጅልባብ ግዛላት ከውስጥ የሚለበስ ግዛላት ጫማ ግዛላት ወንድም ካለህ ጀለቢያ ቀሚስ ጥምጣም ኪታብ እና ሰፋ ያለ ሱሪ ጃኬት ግዛለት


☘️13.የመጨረሻው ጥቆማዬ
ለምንድነው የምሄደው ብላችሁ ኒያችሁን አሳምሩ።

አሏህ ይበልጥ አዋቂ ነው።

ታናሹ ወንድማችሁ አቡሰልማን (አብዱል ዓሊም )ነኝ
እናንተም ባነበባችሁት እኔም በፃፍኩት ተጠቃሚ ያድርገን
ዙል ሂጃ 4/1445
ሰኔ 4/10/2016

وصلى الله على نبينا محمد وآله وصحبه وسلم


https://t.me/B1e9h
🔪
    የኡዱሕያ መስፈርቶች!!

1ኛው, ከቤት እንስሳ መሆን አለበት።
እነርሱም
          
  ግመል
            
  ከብት
            
   በግ

         እና

  ፍየል
   

2ኛው, በሸሪዐ ለተገደበው እድሜ መድረስ አለበት።
        
🍖 ግመል ከሆነ   👉👉  5 ዓመት
        
🍖  ከብት  ከሆነ  👉👉  2 ዓመት
         
🍖  ፍየል  ከሆነ   👉👉  1 ዓመት
          
🍖  በግ    ከሆነ   👉👉 6 ወር የሞላው         


3ኛው, ከነውር (ከዓይብ) የጠራ መሆን አለበት።
      
🛑 ግልፅ  ከሆነ መታወር
       
🛑 ግልፅ  ከሆነ በሽታ
        
🛑 ግልፅ  ከሆነ አንካሳነት
          
🛑 መቅኔ የሌለበት ከሆነ ከሲታማነት


  አንድ ሰው ኡዱሒያ ማረድ ከፈለገ በሚያርደው እንስሳ ላይ ከተጠቀሱ ነውሮች መጥራት አለበት።



🛖ቅርጫ ማድረግ የፈለገ ሰው……

    በግ ወይም  ፍየል ከሆነ ለ1 ሰው ብቻ
    በሬ  ለ7ወይም ግመል ከሆነ ለ10 ሰው መካፈል ይቻላል።

https://t.me/B1e9h