Al EHSAN አል_ኢህሳን
179 subscribers
405 photos
43 videos
2 files
621 links
የቻናሉ አላማ
1 ባለን አቅም እስልምናን በአግባቡ ለኡማው ማድረስ
2 ሙስሊሞችን በድናቸውም ይሁን በዱኒያ እውቀታቸው የነቁ እንድሆኑ መገፋፋት
3 ለወጣቶች ምክር
4 በልዩ መልኩ ሴቶችን ማንቃትና ሌሎቹም አለማዊና መንፈሳዊ ት/ቶች ይገኙበታል።

ውድና የተከበራቹ የአል ኢህሳን ቻናል ቤተሰቦች ሆይ ውብና ማራኪ የሆኑ ሀሳብ አስተያያታቹ እንዳይለይን

ለአስተያት @S1u9l
አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇
Download Telegram
ከሰለፎች መካከል የዐረፋህ ቀን ሲደርስ ዱዓእ አደርግበታለሁ ብለው ወሳኝ ጉዳያቸውን ቋጥረው የሚይዙ ነበሩ። አላህ ካደረሰን ይህ ድንቅ ቀን የፊታችን ቅዳሜ ነው። በተለይ ከሰዓት በኋላ በተለይም ከዐስር በኋላ ሁሉንም ጉዳያችንን ትተን ከወዲሁ ጊዚያችንን በማመቻቸት ወሳኝ ጉዳዮቻችንን ይዘን ለአላህ «ያ ረብ!» ለማለት እንዘጋጅ።

ከአላህ ውጭ ለማንም የማንነግራቸው፣ ብንነግራቸውም ሰዎች በአግባቡ የማይረዱን፣ ውስጣችንን የሚያብሰለስሉን ስንትና ስንት የታፈኑ እምቅ ስሜቶችና ጭንቀቶች አሉብን አይደል! በተለይ ደግሞ ሙእሚን ዱንያን እንደምንም ቢያልፋትም አኺራው ወሳኝ ነውና ሁሉንም ጉዳያችንን ለርሱ ለማመልከት እንዘጋጅ። አላህ ያግራልን።

https://t.me/B1e9h
ውድ ተከታታዮቻችን😍

እንኳን ለኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሰዎ!

በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የመተሳሰብ እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!

ኢድ ሙባረክ!

https://t.me/B1e9h
Audio
የዒድ አል-አዽሐህ አከባበር ስርዓት
በኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ

https://t.me/B1e9h
የእኛ የሙስሊሞች ዒዶች…

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: - "የዓረፋ እና የእርዱ  እለት እንዲሁም የተሽሪቅ (ከዙል‐ሒጃ ወር 11ኛው፣ 12ኛው እና 13ኛው) ቀናት የእኛ የሙስሊሞች ዒዶች ናቸው፤ እነሱም የመብላት እና የመጠጣት ቀናት ናቸው።" ( አቡዳውድ ዘግበውታል አልባኒም ሰሂህ ብለውታል)

በዚህ ሐዲስ ውስጥ እነዚህ አምስት ቀናት ማለትም  ከዙል‐ሒጃ ወር 9ኛ፣ 10ኛው፣ 11ኛው፣ 12ኛው እና 13ኛው ቀናት ለሙስሊሞች ከሐጅ ስርአት ጋር ተያይዞ አላህ ለዚህ ቀጥተኛ እምነት ስለመራቸው በልዩ ሁኔታ እንዲደሰቱባቸው፣ የተለያዩ አላህና መልእክተኛው የደነገጓቸውን የአምልኮ አይነቶች በመፈፀም አላህን ሊገዙባቸው፣ እርሱን ሊያመሰግኑባቸው እና ሊያልቁባቸው የተለዩ የዒድ ቀናት መሆናቸውን እንረዳለን። ስለሆነም ዘጠነኛውን ቀን ሐጅ ላይ ላልሆነ ሰው መፆሙ ሲበረታታ፤ አስረኛውን ቀን መፆም ለሁሉም የተከለከለ ይሆናል። ከዚያ በኃላ ያሉትን የተሽሪቅ ቀናት ሐጅ ላይ ላልሆነ ሰው መጾሙ የማይፈቀድ መሆኑን ዑለማዎች ገልፀዋል።

አላህን እርሱ በሚፈልገው መልኩ በመልእክተኛው መንገድ ከሚገዙት ያድርገን!

ጣሀ አህመድ


https://t.me/B1e9h
          🔷   አያሙ ተሽሪቅ

    ከዒደል አድሓ ( የውሙ ነሕር ) ቀጥለው የሚመጡት ሶስት ቀኖች አያሙ ተሽሪቅ በመባል ይታወቃሉ ። እነዚህ ቀኖች ሙስሊሞች እየበሉና እየጠጡ አላህን የሚገዙባቸው ቀኖች ናቸው በእነዚህ ቀኖች በፆም አላህን መገዛት ክከልክል ነው ።  ይህን አሰመልክቶ የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – እንዲህ ይልሉ : –

عن نبيشة الهذلي أن النبي–  صلى الله عليه وسلم – قال :
(أيام التشريق أيام أكل وشرب وذكر الله) أخرجه مسلم
" አያሙ ተሽሪቅ የመብያና የመጠጫ እንዲሁም አላህ የሚታወስባቸው ቀኖች ናቸው ። "
وفي رواية للإمام أحمد
(من كان صائماً فليفطر فإنها أيام أكل وشرب) .
صحيح مسلم.
" ፆመኛ የሆነ ሰው ያፍጥር እነዚህ ቀኖች የመብያና የመጠጫ ቀኖች ናቸው ። "

   ከእነዚህ ሐዲሶች የምንረዳው በእነዚህ ቀኖች መፆም ክልክል መሆኑ ነው ። ምናልባት ሐጅ ላይ ሆኖ ሀድይ የሌለው ከሆነ አስር ቀን መፆም ይኖርበታል ። ሶስቱን ቀኖች እዛው ፆሞ ሰባቱን ቀኖች ወደ ቤተሰቦቹ ሲመለስ ይፆማል ። ሶስቱን ቀኖች በአያሙ ተሽሪቅም ቢሆን መፆም ይችላል ቀደም ብሎ ካልፆመ ። ከዚህ ውጪ ሌላ ሰው በእነዚህ ቀኖች መፆም አይችልም ። መብላትና መጠጣት ሙባሕ የነበረ ሲሆን በእነዚህ ቀኖች ግን መሰራት ያለበት ዒባዳ ይሆናል ። በመሆኑ ከእርዱ ቀን ማግስት ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት  ድረስ በዒድ ይካተታሉ መፆም አይፈቀድም ። በእነዚህ ቀኖች አላህን መዘከር በጣም ትልቅ የዒባዳ አካል ነው ። አላህ ያግራልን ።

https://t.me/B1e9h
«አባት የመጀመርያም የመጨረሻም የሆነ ብቸኛ ልጁን ሊድር ድል ያለ ሰርግ ደግሶ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆቹን ጠርቶ የምሳ ግብዣውን እየተዟዟረ ይመለከታል።

‹‹ማን ቀረ ማን መጣ›› የሚለውን በትኩረት እየተመለከተ ሳለ የቅርብ የግድግዳ ጎረቤቱን ከእይታው ያጣዋል። ግራ በመጋባት እየተዟዟረ ቢመለከትም ጎረቤቱንም ሆነ የጎረቤቱን ልጆች ሊያይ አልቻለም።

‹‹የልብ ወዳጄ በዛሬ ቀን እንዴት ከጎኔ ይጠፋል›› እያለ በንዴት ስሜት በመብሰልሰል ላይ ሳለ ድንገት የጎረቤቱ ልጅ ብቅ አለ ና በፍጥነት ትንሽ ምግብ ቀማምሶ ትቶ ወጣ።

ይህን ትዕይንት የተመለከተው ደጋሽ በንዴት ተብከነከነ። የአባቱ በደስታው ግዜ አለመገኘት ሳያንሰው ልጁ መጥቶ በምግቡ አላግጦ መውጣቱ አበሳጨው።

በዚህ መሀል የሙሽራው አጃቢዎች ሙሽራውን ይዘው ወደ ሙሽሪት ቤት ጉዞ ሊጀምሩ መኪናቸውን ማንቀሳቀስ ሲጀምሩ ምግቡን ቀማምሶ በፍጥነት የወጣው የጎረቤቱ ልጅ ሙሽራውን ለማጀብ ከግቢ መኪናውን ይዞ ይወጣል።

አባት ተበሳጨ፣ ንዴቱን መቆጣጠር ቢያቅተው በቁጣ መንፈስ ተሞልቶ ወደ ጎረቤቱ ልጅ በመሄድ፦‹‹አባትህ ጎረቤቴ ሁኖ ደስታዬ ላይ አልተገኘም፣ ታላላቅ ወንድሞችህም እንደዝያው፤:ታድያ አንተ ምን አስበህ ነው በምግብ አላግጠህ ትተህ የወጣኸው?  አሁን ተመለስ ያንተን አጃቢነት አንፈልግም›› ብሎ መለሰው። ልጁም እቤቱ ገባ፤ ሰርገኛዎችም ሙሽራውን ይዘው ወደ ሙሽሪት ቤት አቀኑ።

በመጨረሻም አጃቢዎች ሙሽሮችን ይዘው ወደ ቤት በመግባት የደስታቸው ተካፋይ ከሆኑ በኋላ ቀኑ ሲጨልም ሁሉም ተበታትኖ ሰርግ ቤቱ በሙሽሪት እና በሙሽራው ጭር አለ።

አባት አሁንም በጎረቤቶቹ ንዴት እየተብሰለሰለ ነው። ድንገት ከመሸ ያለ ወትሮው የጎረቤቱ ጊቢ ተከፈተ። የሙሽራው አባት እየተመለከተ ነው።

የጎረቤቱ ልጆች በትከሻቸው አስክሬን ተሸክመው ከቤታቸው ሲወጡም ተመለከተ። ፍፁም ዝግታ እና እርጋታም በሚስተዋልበት እርምጃ ልጆቹም ይራመዱ ጀመር።

የሙሽራው አባት ጠጋ አለ። ፦‹‹ምንድነው? የማንን አስክሬን ነው የተሸከማችሁት ›› ሲልም ጠየቃቸው።

‹‹አባታችን ጠዋት ሙቶ ነው፤ ሲሞትም በሱ ለቅሶ ምክንያት ያንተ ደስታ እንዳይጓደል መሞቱን ከሰርግህ በፊት ለማንም እንዳንናገር እና ድምፅ አውጥተን እንዳናለቅስ ተናዞልን ነበር። ለዝያ ነው ድግሱ ላይ መገኘት ያልቻልነው። ›› በማለት ጀናዛ የተሸከሙ ልጆች ጉዳያቸውን አስረዱ።

ደጋሽ ተፀፀተ፦‹‹ወላሂ እኔ በሱ ቦታ ብሆን ይህን የማድረግ አቅም አይኖረኝም ነበር›› ሲልም የፀፀት እንባ ያነባ ጀመር።

በህይወታችን ችላ ያሉ እየመሰሉ በቁስላቸው ደስታችንን ላለማበላሸት ሲሉ ከአከባቢያችን የሚርቁ ሰዎችን አላህ ይዘንላቸው።»

ሰፍዋን

https://t.me/B1e9h
በከባድ ሙቀት ህይወታቸው ያለፈ ሀጃጆች ቁጥር ከ1 ሺህ ተሻገረ‼️

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የተለያዩ ሀገራትን ዲፕሎማቶችን ዋቢ አድርጎ ይፋ ባደረገው አሃዝ እስከዛሬ ድረስ 1081 ሃጃጆች ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።

እስካሁን በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት የ10 ሀገራት ዜጎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፥ 658ቱ ግብጻውያን ናቸው።

የሱዳን፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዚያ፣ ህንድ፣ ዮርዳኖስ፣ ማሌዥያና ኢራን ዜግነት ያላቸው ሃጃጆችም ህይወታቸው ማለፉን ነው አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ያስነበበው።

https://t.me/B1e9h
✍️ ብዕረ ሐኒፍ #4
🔖ኃላፊነት አለብን!

ከሺህ አራት መቶ አመታት በፊት ዓለም ሁለንተናዊ ጽልመት ያካበባት ድቅድቅ ጨለማ ነበርች።መላ ፍጥረታትን ካነበሩበት አስገኝቶ እንደምንጣፍ በዘረጋት ምድሩን ላይ ያኖራቸው ቸር እና ኃያል ጌታ ተትቶ፤የማይጠቅሙ እና የማይጎዱ ግዕዞች የሚመለኩበት ፣ ጉልበተኛው ደካማውን የሚበዘብዝበት እና የሚረግጥበት ፣ የሴት ልጅ ሰዋዊ ማንንነት እንኳን ተረስቶ ከነ ሕይወቷ የምትቀበርበት ፣ የጎሳ እና የዘር ጠብ አይሎ የተከበረው የሰው ልጅ ደም እንደዋዛ የሚፈስባት ዓለም።

አዛኙ ጌታችን አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ሰዎች እስከ አፍንጫቸው ከተዘፈቁበት ድርብርብ የጨለማ አዘቅት በእዝነቱ ሊያወጣቸው በፈለገ ጊዜ ፤ የፍጥረታት እንቁ ፣ የሰው ልጅ ሁሉ ዓይነታ የነብያት እና መልዕክተኞች መደምደሚያ የሆኑትን ሙሐመድ ኢብኑ ዐብደላህ ኢብኑ ዐብዱል ሙጠሊብን ﷺ ለመላው ዓለም የመጨረሻው ነብይ እና መልዕክተኛ አድርጎ ላካቸው።

ረሱሉላህ ﷺ ከአላህ ዘንድ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ፣ ህዝባቸውን ከገባበት የመሐይምነት ጨለማ ለማውጣት ሌት ተቀን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ወገባቸውን አስረው ለፉ ፤ ለህዝባቸው መዳን ሲሉ በርካታ መከራ እና ግፍ አዩ ፤ ከባባድ የበደል እና የጭቆና ጊዜያትን አሳለፉ ፣ በገዛ ቤጸባቸው ተገፉ ፣ ዕምብርታቸው ከተቀበረባት የሚወዷት አገር ተሰደዱ።

በርካታ ውጣ ውረዶች ከሞሏቸው ሁለት አስርት ዓመታት በኋላ ፤ የጌታቸውን መልዕክት አድርሰው ፣ ሰዎች በቡድን በቡድን ወደ እስልምና ሲጎርፉ ተመልክተው ፣ በአላህ እርዳታ ዳዕዋቸው ፣ ልፋታቸው እና ጥረታቸው ፍሬ እንዳፈራ ያስተዋሉ ጊዜ በመሰናበቻው ሐጃቸው ላይ ለባልደረቦቻቸው "የጌታዬን አደራ አድርሻለሁን?" ብለው ጠየቁ። ሰሐቦቻቸውም "አዎን አድርሰዋል" አሉ።እሳቸውም "አላህ ሆይ መስክር !" አሉ።

የነብዩ ባልደረባ እንዲሆኑ አላህ የመረጣቸው ሰሐቦችም ከነብያቸው የተረከቡትን አደራ ጠብቀው ለቀጣዩ ትውልድ አስተላለፉ ፣ በኢስላም ዳዕዋ አገራትን ከፈቱ ፣ በርካቶችን ከጨለማ ወደ ብርሃን አወጡ።ከሰሐቦች ይህን ትልቅ አደራ የተቀበሉት ሰለፎቻችንም ዲኑን በማስተማር እና በማሰራጨት ለቀጣዩ ትውልድ የማሸጋገር ኃላፊነታቸውን ተወጡ።እንዲህ እንዲህ እያለ በየዘመኑ የነበሩ ዑለማዎች እና ደጋግ የአላህ ባሮች ዲኑን ለማስጠበቅ እና ለቀጣዩ ትውልድ ለማሸጋገር ከባባድ መስዕዋትነትን ከፍለው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማበርከት እስልምናን ከትውልድ ትውልድ እንዲሸጋገር አደርጉ።

ዛሬም የዚህን ዘመን የዲን ኃላፊነት መሸከም በዚሁ ዘመን እየኖርን ያለነው ሙስሊም ማህበረሰቦች ኃላፊነት ነውና እንደየ አቅማችን እና ችሎታችን የበኩላችንን አስተዋጻኦ ለዲኑ ማበርከት የእያንዳንዳችን ግዴታ ነው። በመማር ፣ በማስተማር ፣ ኢስላማዊ የትምህርት ማዕከላትን በማቋቋም ፣ ኢስላማዊ የዳዕዋ እና የትምህርት ስራዎችን በሀሳብ ፣ በጉልበት ፣ በቁሳቁስ እና በገንዘብ በመደገፍ ያለብንን ኃላፊነት መወጣት ይኖርብናል!

አላህ ባለን አቅም እና በተሰማራንበት የስራ ዘርፍ ያለብንን የዲን ኃላፊነት የምንወጣ ባሮች ያድርገን! አሚን!

https://t.me/B1e9h
ባለ ትዳሮች ሆይ ይህ ተራ ወሬ ነው!

🔅ባልና ሚስት በጸብም ይሁን በሰላም በተለያዩ ምክንያቶች ለምንም ያክል ጊዜ ተራርቀው ቢኖሩ ባል በራሱ ወይም በወከለው ሰው ኒካሕ እስካላወረደ ወይም ሚስት በፍርድ ቤት እስካልተፈታች ድረስ በአካል ተራርቀው ስለቆዩ ብቻ ኒካሕ ፈጽሞ አይወርድም።
ይህ ከመሆኑ ጋር ብዙ ሰዎች "3 ወር፣ 6 ወር ወዘተ ተራርቃችሁ ስለቆያችሁ ኒካሕ እንደ አዲስ እሰሩ ተባልን..." ይላሉ!
ይህን አላህም ይሁን መልእክተኛው እንዲሁም የፊቅህ ሊቃውንት (ዑለማኦች) አላሉም።

🔅ስለዚህም ባልና ሚስት በስራም ይሁን በሌላ ምክንያት፤ በስምምነትም ይሁን በጸብ ለወራትም ይሁን ለዓመታት ተራርቀው ቢቆዩ በመራራቃቸው ወይም ተለያይተው በማሳለፋቸው ብቻ ኒካሕ እንደማይወርድ አውቀው ዳግም ኒካሕ ማሰር ሳያስፈልጋቸው ህይወታቸውን አብረው መቀጠል ይችላሉ።

💥የአላዋቂዎች ወሬ እንዳያደናብረን ዲናችንን አስቀድመን እንወቅ! እንማር።

ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም


https://t.me/B1e9h
'
ኢብኑ አቢ ለይላ እና ሁለቱ ሴቶች (የሴቶች ሴራ)


አንዲት አሮጊትና ወጣት ሴት ተካሰዉ በዘመኑ ታዋቂ ወደነበረዉ ቃዲ ኢብኑ አቢ ለይላ ይሄዳሉ

ዳኛዉ መጀመሪያ ማን ይናገር አለ አሮጊቷ አንቺ ተናገሪ አለች ወጣቷም የሁለታችንም እኔ እናገራለሁ ከተሳሳትኩ ትመልሰኛለች አለች


ከዚያም አንተ ቃዲ ሆይ! ይህች አጠገቤ ያለችዉ አሮጊት አክስቴ ነች አባቴ ሲሞት የቲም አድርጎ እሷ ጋ ተወኝ እሷም ባማረ አስተዳደግ አሳደገችኝ በዚህም እንደ እናቴ ስለሆነች እናቴ በማለት ነዉ የምጠራት አለች

ዳኛዉም ከዚያስ አላት

እድሜዬ ለትዳር ሲደርስ የአጎቴ ልጅ ለትዳር  ጠየቀኝ አክስቴም በትዳር አጣመረችን

በጣም እንዋደድ ነበር እኔ ለሱ እሱም ለኔ ብቻ እንደተፈጠርን ከአለም ሌላ እንደሌለን እናስብ ነበር።

ከሶስት አመታት በፍቅር የተሞላ ትዳር በኋላ  የባሌን መልካምነት ስትመለከት ሃብቱም እየሰፋ ሲመጣ ለልጇ ተመኘችዉ

ከዚያም ያማረ ልብስ አልብሳ አስዉባ ወደ ባሌ አስገባቻት እሱም ሲያያት ወደዳት አክስቴም ይህችን ልጄን  እንዳጋባህ  አንድ መስፈርት አለኝ አለችዉ ምን እንደሆነ ሲጠይቃት የመጀመሪያዋ ሚስትህን (የወንድሜን ልጅ)  ሃላፊነት በእጄ ልታረግና ፍቿን እኔ ልሰጣት አለችዉ

እሱም ተስማማ በሰርጉ ቀይ ወደኔ መጥታ ባልሽ ልጄን አግብቷታል ያንቺም ጉዳይ በእጄ አድርጎታል አናም ተፈትተሻል አለችኝ በሌሊትና በረፋድ ፈት ሆንኩ

ከአጭር ጊዜ በኋላ ለረዥም አመታት ሌላ ቦታ የቆየዉ ባሏ ከመንገድ ተመለሰ ታዋቂ ነጋዴ ነበር (ገጣሚም ነዉ ተብሏል)  ስለኛ ሲጠይቃትም እኔ አግብቼ እንደተፋታሁ ልጁም እንዳገባች ነገረችዉ እሱም የመዘየር ሃቅ  አለብኝ በማለት ሊጠይቀኝ መጣ

በዚህ ጊዜ የአክስቴ ባል ሆይ! ታገባኛለህን? አልኩት እሱም መስማማቱን ገለፀልኝ

ነገር ግን አንድ መስፈርት አለኝ እሱም የሚስትህን ጉዳይ  በኔ እጅ ልታደርግ  አልኩት እሱም ተስማማ

ከዚያም ለአክስቴ ባልሽ ያንቺን ጉዳይ በእጄ አድርጎታልና ከርሱ አፋትቼሻለሁ በማለት መልእክት ላኩላት። ከዚያም አገባሁት አክስቴም ፈት ሆነች
አንተ ቃዲ ሆይ!  አላህ እድሜህን ያስረዝመዉና  በዚህ መልኩ አንድ እኩል ሆንን አለች

በዚህ ጊዜ ቃዲዉ በሚሰማዉ ነገር ደንግጦ በመቆም ያአላህ! አለ  እሷም ገና ታሪኩ አልጀመረም ተቀመጥ አለችዉ

እሺ ቀጥይ አላት

ባሌ ከትንሽ የትዳር ቆይታ በኋላ ሞተ እኔም ንብረቱን ወረስኩ

ታዲያ በዚህ ጊዜ አክስቴ መጥታ ለብዙ ዘመናት ለንግድ ሲሄድ ርቀቱን የታገስኩ ልጁን ያሳደግኩ እኔ ነኝ ከዚህ ሃብት ሃቅ አለኝ ብላ ዉርስ ጠየቀች  እኔም እኔ የባሌ ሃብትና ሃቄ ነዉ  አንቺ ከዉርሱ ምን አገባሽ አልኳት

ኢዳዬ ከተጠናቀቀ በኋላ አክስቴ ልጇንና በዉርስ ጉዳች እንዲያሸማግለን የድሮ ባሌን የአሁን የአክስቴ ልጅ ባል ይዛ መጣች።

ወጣቷ ትረካዋን ትቀጥላለች

ከዚያም የድሮ ባሌ ሲመለከተኝ ያሳለፍናቸዉን ጊዜያት አስታወሰ ድጋሚም ከጀለኝ

እኔም ትመልሰኛለህን? አልኩት  መስማማቱን ገለፀልኝ እኔም ግን አንድ መስፈርት አለኝ እሱም የአክስቴን ልጅ ጉዳይ በእጄ ልታደርግ አልኩት። በመስፈርቴ ተስማማ ለአክሰቴ ልጅ ተፈትተሻል አልኳት።

በዚህ ጊዜ ቃዲዉ ኢብኑ አቢ ለይላ እጁን ጭንቅላቱ ላይ አድርጎ ጥያቄዉ የታለ 😳 አለ

አክስትም ተነስታ አንተ ቃዲ ሆይ!  ይህ እንደ ሸሪዓ ሃራም አይደለምን? እኔና ልጄ ፈት ሆነን ይህች ሴት ሁለት ባልና ዉርስ የምትወስድ? አለችዉ

ቃዲዉም በዚህ ዉስጥ ሃራም ነገር አላየሁበትም አንድ ወንድ ሁለት ጊዜ አግብቶ ሁለት ጊዜ መፍታቱና ዉክልና መስጠቱ ምኑ ላይ ነዉ ሃራምነቱ? አለ 

ከዚያም በዘመኑ ከአባሲያዎች የነበረዉ ዋሊ መንሱር ጋር ሄዶ ታሪኩን አጫወተዉ

መንሱርም ከሳቁ ብዛት እግሩን ከመሬት ያማታ ነበር ከዚያም እንዲህ አለ "ቃተለላሁል አጁዝ ለወንድሙ ጉድጓድ የቆፈረ ራሱ ይወድቅበታል ይህችን ግን ባህር ላይ ወደቀች

https://t.me/B1e9h
📨20(ሐያ)ወንድማዊ ምክር ለውዷ እህቴ

①,በተውሒድ ላይ አደራ! ሽርክን እና ቢደዓን በያይነታቸው ራቂ!!
②,, ሁሌ ቤት ውስጥ መቀመጥ ምርጫሽ ይሁን።ወጣ ወጣ አትበይ!!
③,,ተቅዋን(አላህን መፍራት) የውስጥ መዋቢያሽ ካደረግሽ ሀያእን ደሞ ውጫዊ መዋቢያሽ አድርጊው!!
④,,ከ ወንዶች እና ከካፊር ሴቶች ጋ ያለሽ ግንኝነት በጣም አስፈላጊ ሆኖ እስካላገኘሽው ድረስ ራቂ!!
⑤,,ሒጃብሽ ሰፋ ያለና ረዘም ያለ ይሁን!!
⑥,,አካሄድሽ ረጋ ያለና አደብ የተላበሰ ይሁን!!
⑦,,በየቀኑ ብታጠፊ በየቀኑ ወደ አላህ ተመለሺ!!
⑧,,በአለባበስሽና በሥነምግባርሽ ለሌሎች ሴቶችና ለሴት ልጆችሽ ምሳሌ ሁኚ!!
⑨,,ያልተፈቀደልሽን ባዕድ ወንድም ሆነ ሊያገባሽ የሚፈቀድለትን የቅርብ ዘመድ አትጨብጭ!!
10,,ከላይ አላህን ሳይታዘዙ፤ ዉስጤ ንፁህ ነው አላህን ፈራለሁ ማለት ቅጥፈት ነው!!
①①,ከባዕድ ወንድ ጋር ስታወሪ መቅለስለስ፤ በሽ?ታ ያለበትን በሽታውን መቀስቀስ ነውና አደብ ይኑርሽ በንግግርሽ…!!
①②,መስመር እየሳቱ የሚመስሉ የስልክ ወሬዎችንና ቻቶችን ከወድሁ ቁረጪ!!
①③,እየተኳኳሉና እየዘለሉ አላህን እና መልዕክተኛዉን እወዳለሁ ማለት ዉሸት ነውና… ነሽዳ እና መሰል ኮተቶችን ራቂ!!
①④,ሒጃብና ኒቃብ እየለበሱ መጥፎ መሥራት የኢስላምን ንጽሕት ሙስሊምን ሥም ጭምር ማጠልሸት ነውና… በቻልሽው አቅም አደብ ይኑርሽ!!
①⑤,በሐራም መንገድ ገንዘብም ሆነ ትዳር ባገኙት አትቅኚ ፍፃሜው አያምርም እና!!
①⑥,- ፀጉርሽን አትጎዝጉዢ(ከፍ አድርገሽ አትሰሪው) አትቀጥይውም፣ሽቶም ሆነ ዶድራንት ተቀብተሽ አትውጪ!!
①⑦,ስትስቂ በስሱ፤ ሰታወሪ ድምጽሽ ዝቅ ይበል!!
①⑧,በሥራ ቦታ እና በት/ት ቤት  ከሰዎች ጋር ባለሽ ግንኙነት ቀይ መስመር ይኑርሽ!!
①⑨,, ከእህቶችሽ ጋር ተግባቢ እና ትህትና ያለሽ ሁኚ!!
20,,የሸሪዓ እውቀትን በመፈለግ ላይ አደራ እስካሁን ለጠቀስኩት ምክሮች መሰረቱ ነውና!!
منقول
https://t.me/B1e9h
«ለአላህ ብቻ ብሎ በኢኽላስ የሚሰራ ሰው ልክ በአሸዋ መንገድ ላይ እንደሚሄድ ሰው ነው። የእርምጃው ድምፅ አይሰማም፣ ፋናው ግን ይታያል።»

ኸይር ሥራችን ትንሽ ነው፤ ለዚችሁ ስራችን ኢኽላስ ይኑረን፣ ትንሹን ያበዛዋልና!
ኢኽላስ ከሌለው ከንቱ ድካም ነው።

https://t.me/B1e9h
ከዘረፋ ወደ ታላቅ ኢማምነት
❴በአንዲት የቁርአን አንቀፅ በመስራት የተገኘ ታላቅ ክብር❵

ከታቢዒዮች መካከል ታላቅ መሪ የሆኑት ፉዶይል -አላህ ይዘንላቸውና- ጸጸት ከማድረጋቸው በፊት ግማሽ የሆነውን ህይዎታቸውን ያሳለፉት በዘረፋ ተግባር ወይም በሽፍትነት ነው፡፡ አርባ አመት እስኪሞላቸው ድረስ የአካባቢው ህብረተሰብ በጣም ይሰጋቸው ነበር፡፡ “ሲየር አዕላም አን’ኑበላእ” በተባለው ኪታብ ዘህብይ -ረሂመሁሏህ- የእርሳቸውን የጸጸት ታሪክ እንደሚከተለው ይገልጹታል፡፡ ለጸጸት ምክንያት የሆነቻቸው አንዲትን ሴት በማፍቀራቸው ምክንያት እንደሆነ ይወሳል፡፡ ወደሴትዮዋ ቤት ለመድረስ አጥር ላይ
ሲወጡ በአጋጣሚ የሚከተለውን የቁርኣን አንቀጽ የሚቀራ ሰው አደመጡ
፡፡
۞ أَلَمْ يَأْنِ لِلَّذِينَ آمَنُوا أَن تَخْشَعَ قُلُوبُهُمْ لِذِكْرِ اللَّهِ
“ለነዚያ ለአመኑት ለአላህ ተግሳጽና ከቁርኣንም ለወረደው ልቦቻቸው ሊፈሩ….
አልቀረበምን?”

📚 [ ሱረቱ አል-ሐዲድ - 16 ]

“ጌታየ ሆይ አዎ ቀርቧል” የሚል መልስ ሰጡ፡፡ ከዚያም ካሰቡት አላማ ተጸጽተው ተመለሱ፡፡ ያኔ እርሳቸው በተጸጸቱበት ወቅት መንገደኞች “እንለፍ አንለፍ? ፉዶይል ቢዘርፈንስ?” በማለት ጭንቀት ውስጥ እንደነበሩ በታሪክ ተዘግቧል፡፡
ፉዶይል የሚከተለውን ተናገሩ፡- ((አስተነተንኩ፣ ሙስሊሞች እኔን ይሰጋሉ፣ እኔ ግን በሌሊት ወንጀል ለመፈጸም እንቀሳቀሳለሁ፣ እኔን ወደዚህ አላህ አላመጣኝም ጸጸትን ለእኔ ሽቶልኝ እንጅ፤ አላህ ሆይ! እኔ ወደአንተ ተጸጽቻለሁ፤ በህይዎት እስካለሁ ድረስ ካዕባን መጎራበት ለእኔ ከጸጸቴ መካከል አንዱ ነው፡፡))
📖 ሲየር አዕላም አን ኑበላእ፡ 8/423

ፉዶይል ከዚህ ዓለም በሞት እስኪሰናበቱ ድረስ መካ ውስጥ አላህን ይገዙ ነበር፡፡ ከመካ ዑለሞች የሐዲስ የተለያዩ የፊቅህ እውቀቶችን ቀስመዋል፤ ሐዲስ ሀፍዘዋል፡፡ ለዚህ ነው ሙስሊሞች የተፍሲር፣ የሐዲስና የፊቅህ መጽሐፎችን ገልጠው ሲያነቡ የዚህን ታላቅ ኢማም ስም ዘወትር የሚያስተውሉት፡፡ አንዲት አንቀጽ የፉዶይልን ህይዎት ከከባድ አመጸኝነት ወደ ደጋግ የአላህ ባሪያነት ቀየረች ፤ የኢማሞች ሁሉ ኢማም አደረገች፡፡

https://t.me/B1e9h
ዩሱፍ ጉድጓድ ውስጥ ጠብቋል፣
ኢብራሂም እሳት ውስጥ ጠብቋል፣
አዩብ ህመሙ እስኪሻለው ድረስ ጠብቋል፣
ዩኑስ በዓሳ ነባሪው ሆድ ውስጥ ጠብቋል።

በመጨረሻም ለሁሉም የመጣውን ፈረጃ እናውቃለን።

አላህ እንድትጠብቅ ካደረገህ ታድለሃልና አሁንም ሳትቸኩል ታገስ።

https://t.me/B1e9h
ሐሰነ-ል-በስሪይ (ረሒመሁ-ል'ሏህ) «ዱንያን ቸልተኛ ያደረገህ ነገር ምንድነው?» ሲባሉ፦

√ ሪዝቄን ማንም እንደማይወስድብኝ አወቅኩኝ፤ ልቤ ተረጋጋልኝ፣

√ ሥራዬን ማንም እንደማይዘሰራልኝ አወቅኩኝ፤ ትኩረት ሰጥቼ ሠራሁኝ፣

√ ጌታዬ እንደሚጠባበቀኝ አወቅኩኝ፤ በወንጀል ልቀጣጨው ፈራሁኝ፣

√ ሞት እንደሚጠብቀኝ አወቅኩኝ፤ ጌታዬን ለመገናኘት ስንቄን ተሰነቅኩኝ!

https://t.me/B1e9h
እንደ ዑማ ከስረናል 🥲
*
ትላንትናው እለት በሳዑድ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሀጫሉ ደጋፊ እና የቴድ አፍሮ ደጋፊ በመሆን ሲከራከሩ ከቆዩ ቡሃላ ክርክራቸው ወደ ጭቅጭቅ አልፎ ወደ ፀብ በማምራት እርስ በርሳቸው በጩቤ ተወጋግተው ሁለቱም ህይወታቸው አልፏል።

እጅግ የሚገርመው ምናቸውም ለማይታወቅ ለዱኒያ አይሆን ለአኼራ ለማይጠቅሙ #ዘፋኝ የተገዳደሉት ሁለቱም ሙስሊሞች ሱሆኑ በነዚህ ልጆች ምክኒያት ወደ 20 የሚሆኑ በህንፃው አካባቢ የሚኖሩ ልጆች ተሰብስበው ታስረዋል።

ነገ ከአላህ ፊት የተገዳደሉበትን ምክኒያት ምን ብለው ይናገሩ ይሆን ⁉️

ኻቲማችነን አሳምረው የሚባለው ይህ ነው።

በነዚህ ልጆች ምክኒያት በዚያ አካባቢ የሚኖሩ አረቦች የሀበሻ ሰራተኛ አንፈልግም በማለት እያሰናበቱም እንደሆነም እየተወራ ነው

እንደዚህም አለ ፡ የራሳቸውን ህይወት አጥተው ፡ የሚረዷቸውን ቤተሰብ እና ልጆቻቸውን በትነው አልፎም ለሌሎች ጓዶቻቸውም ጦሱ ተረፋቸው።

እህቴ ሆይ ፡ ወንድሜ ሆይ ወደቀልባችሁ ተመለሱ
የሄዳችሁበትን አላማ አትዘንጉ።

ጭራሽ በኛ ላይ ሀራም የሆነ ሙዚቃ መስማቱ አልበቃ ብሎ ለነዚህ ኻዒኖች ፡ በአላህ ላይ ላመፁ ዘፋኞች ጠበቃ ሆኖ እዚህ ደረጃ መድረስ እውነትም ከስረናል።

https://t.me/B1e9h
በተዘጋብህ በር አትፀፀት

ከፊት ለፊትህ የተዘጋውን በር ከጀርባው ያለውን አደጋ ብታውቅ ኖሮ፤ ማማረርህን ትተህ በመዘጋቱ አላህን በብዙ ታመሰግነው ነበር።

https://t.me/B1e9h
የሙሐረም ወር ጨረቃን በተመለከተ…

«የሳዑዲ ዓረቢያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባወጣው መግለጫ መሰረት

በሳዑዲ ዓረቢያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጨረቃን ሁኔታ ለመከታተል በተየሰየመው ችሎት በዛሬው እለት ጁሙዓህ ዙል–ሒጃህ 29/1445 አመተ ሂጅራ ጁላይ 5/2024 ከመግሪብ በኋላ ተሰይሞ በተለያዩ ከተሞች ካሉ ፍርድ ቤቶች እና ጨረቃን ለመከታተል የተመረጡ ኮሚቴዎች ጨረቃ ባለመታየቷ ነገ ቅዳሜ ጁላይ 06/2024 ዙል–ሒጃህ ወር 30ኛው ቀን ሲሆን እሁድ ጁላይ 07/2024 የሙሐረም ወር(1446 አመተ ሂጅራ) መጀመሪያ ቀን ይሆናል።

በዚህም መሰረት የዚህ አመት ዓሹራእ (ከሙሐረም 10ኛው) ቀን ማክሰኞ ጁላይ 16 ይሆናል ማለት ነው።

አላህ በመልካም ስራ ከሚሽቀዳደሙት ያድርገን!»

©: ጣሃ አሕመድ (ዙል–ሒጃህ 1445)

https://t.me/B1e9h
- መስጂድ ሄደ። በሰላት መሀል ስልኩ በሙዚቃ ጥሪ በተደጋጋሚ ጮኸ። ሰጋጆች ገላመጡት። ኢማሙም “በቤቱ ውስጥ አሏህን አትፈራውም እንዴ? ቁጣውን ቢያወርድብህስ” ዓይነት ሃይለቃል ተናገረው። ተሸማቀቀ። ወደ መስጂድ መመለስ አልፈለገም።

ወደ ሌላኛው ሰዎች ዓለም አቀና። እጆቹ ጫቱን አይፋቱትም። ሺሻና  መጠጥም ከአጠገቡ አይለዩም። የመጠጥ ብርጭቆው ድንገት ቢሰበርበት  “አይዞህ አትደንግጥ ደንበኛችን” ይሉትና ካስከፈሉት ይከፍላል። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የመጠጥ ቤት ዘበኛ ሆነ። 

አላህን ፈልገው የመጡ ሰዎችን በመጥፎ አይን የምታዩ ቅዱስ ነን ባዮች እረፉ። የርሱን መሀርታ ፈልገው እንጂ እናንተን ለማስደሰት ብለው ወደ ቤቱ አልመጡም። (ቁጣቹህን በልኩ ግሩት!)

“አበስሩ አታስበርግጉ” ረሱለላህ!!

https://t.me/B1e9h
ዓሹራን የመጾም ትሩፋት

🔅ቡኻሪይ እንደዘገቡት ዐብዱሏህ ኢብን ዐባስ ረዲየሏሁ ዐንሁ የዓሹራን ጾም አስመልክተው ሲናገሩ የሚከተለውን ብለዋል (ነቢዩም ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለ እንደ ዓሹራ ቀንና እንደ ረመዷን ወር ሆን ብለው <በጉጉት ጠብቀው> ሲጾሙ አይቻቸው አላውቅም! )
ብለዋል ነቢዩም፥
( የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል(ያስሰርዛል) ብዬ አሏህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ ) ብለዋል።

🔅አንድን ቀን በመጾም የዓመት ወንጀል መማር ለሙእሚኖች ታላቅ የአሏህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ስጦታ ነው እድሉም ለሁሉም ክፍት ነው መሽቀዳደም እና መወዳደር ያማረው ሰው በሙሉ እንዲህ አይነቱ የኸይር ስራ ሜዳ ላይ ይሽቀዳደም!
🔅የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል ያሰርዛል በቀላል ስራ ይህን የሚያህል ምንዳ የሚገኝ ሆኖ ሳለ ብዙ ለአኼራቸው ግድ የለሽ የሆኑ ሰዎች እድሉን ችላ ሲሉ እንመለከታለን፤አዱኒያዊ ጥቅም ቢሆን ግን አይዘናጉም ነበር፤ አልፎም እድሉ ላይ በመሻማት ይፋጁ ነበር ግን {አብዛኞች የሰው ልጆች አያውቁም} አርሩም 6

የዓሹራእ ጾም ሙሐረም ስንተኛው ቀን ላይ ነው?...
የዓሹራእ ጾም ማለት የሙሐረም ወር 10ኛው ቀን ላይ ሲሆን ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድ ቀን (9ኛውን ወይም 11ኛውን) ቀን ጨምሮ መጾም ይመረጣል ምክንያቱም ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ዓሹራን ሲጾሙና ሷሓባዎችም እንዲጾሙት በመከሯቸው ጊዜ አይሁዶች የሚያከብሩት ቀን እንደሆነ ለነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሲነግራቸው የሚከተለውን ብለዋል፤ ( አሏህ ካለ የሚመጣው ዓመት ላይ 9ኛውንም ቀን እንጾማለን ) ብለዋል ከዚህም በመነሳት ዑለማዎች ዘጠነኛውንም ቀን መጾም ሱና ነው ብለዋል።

🔅ከዓሹራ ጋር 9ኛውን ቀን መጾም ምክንያቶች አሉት ከነዚህም መሀል አንዱ 10ኛውን ቀን ብቻ መጾም ከአይሁዶች ጋር መመሳሰልን ስለሚያመጣ አንድ ቀን ጨምሮ መጾሙ ከነሱ ጋር መለያየትን ያስገኛል፤ ከጠመሙ ህዝቦች ጋር መመሳሰል በዲናችን ክልክል ከመሆኑ አንጻር እነሱን ለመቃረን ተብሎ ሸሪዓችን አንድን ነገር ማድረግ ሲከለክል ወይም ደግሞ ሲያዝ ሁሉ እናያለን ይህም ሆኖ ሳለ ግን ብዙ ሙስሊሞች አይሁድና ነሳራ ያደረጉትን ለማድረግ ሲሽቀዳደሙ እንመለከታለንል!

🔅ይህ በእንዲህ እንዳለ ምናልባት የቀን አቆጣጠር ላይ ስህተት ቢፈጠር እና የወሩ መግቢያ አሻሚ ቢሆን ሁለቱን ቀናት መጾም የዓሹራን ቀን ማግኘት ላይ እርግጠኛ ያደርጋል፤በላጩ 9 እና 10ኛውን ቀን መጾሙ ሲሆን ያልተመቸው ሰው 10 እና 11ኛውን ቀን መጾም ይችላል።እንዲሁ ዋናውን የዓሹራን ቀን ብቻ እንጂ ሌላ ተጨማሪ ቀን መጾም ያልቻለ ሰው ብቻውን መጾም እንደማይከለከል ዑለማዎች ገልጸዋል።

🔅ጁሙዓ ወይም ቅዳሜ ቀንን ለብቻው (ከፊት ወይም ከኋላ አንድ ቀን ሳይጾሙ) ነጥሎ መጾም እንደማይቻል በሐዲሶች የተገለጸ ሲሆን አጋጣሚ ዓሹራ ጾም በጁሙዓ ወይም ቅዳሜ ዕለት ቢሆን መጾም አይከለከልም።
🔅ዓሹራ ጾም ብቻ ሳይሆን ሌሎችም እንደ ቀዷ ወይም የነዝር (ስለት) እና መሰል ምክንያት ያላቸው ጾሞችንም መጾም አይከለከልም።

ዓሹራን መጾም የቱን ወንጀል ነው የሚያስምረው?
ዓሹራን መጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል እንደሚያሠርዝ ጠቅሰናል ይህ ምህረት ጥቃቅን ወንጀሎችን ነው የሚመለከተው ወይስ ከባባዶችንም ጭምር?
ይህን አስመልክተው ኢማም አንነወዊይ የሚከተለውን ብለዋል፤
" የዓረፋ ጾምም ይሁን የዓሹራ ሌሎችም ወንጀልን ያስምራሉ የተባሉ ኢባዳዎች ጥቃቅን የሚባሉ ወንጀሎችን በሙሉ ያሰርዛሉ ጥቃቅን ወንጀሎች የሌሉበት እንደሆነ በምትኩ መልካም ስራዎች ይመዘገቡለታል አላህ ዘንድም ያለው ደረጃ ይጨምራል ጥቃቅን ወንጀሎች የሌሉበት ሆኖ አንድ ወይም ከዛ በላይ ከባድ ወንጀል ያለበት እንደሆነ ወንጀሉን ያቀለዋል ብለን አሏህ ላይ ተስፋ እናደርጋለን"

ቀዷ ያለበት ሰው ዓሹራ መጾም ይችላልን?
እንደ ዓሹራ ያሉ ሱና ጾሞችን ያለምንም ጥርጣሬ ለመጾም ያለብንን ቀዷ ፈጠን ብለን ማውጣቱ ይመረጣል።ቀዳውን ሳይጾም ወቅቱ የሚያልፍ የሱና ጾም የደረሰበት ሰው በቀጣይ ለቀዳ ሰፊ ጊዜ እስካለው ድረስ ፈርዱን ቀዳ ሳያወጣ ሱና ቢጾም ችግር አይኖረውም።
🔅ከዓሹራ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ቢድዓዎች  ታላቁ የዲን መሪ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ይህን በተመለከተ የሚከተለውን ጥያቄ ተጠየቁ
"በዓሹራ ቀን ሰዎች ገላቸውን ሲታጠቡ፤ ሲኳኳሉ፤ሂና ሲቀቡ፤ልዩ ሰላምታ ሲለዋወጡና ሲጨባበጡ፤ልዩ ምግብም ሲሰሩ እና ልዩ ደስታ ሲደሰቱ ይታያል ይህ ነገር በሸሪዓችን መሰረት አለውን?" እሳቸውም ሲመልሱ {{ ይህን አስመልክቶ ከነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የተገኘ አንድም ሷሒሕ ሐዲስ የለም ሷሓቦቻቸውም ይህን አስመልክተው ያሉት ነገር የለም ቀደምት የዲን መሪዎችም አራቱም መሪዎች (ኢማም፥አቡ ሐኒፋ፣ማሊክ፣ሻፊዒ እና አሕመድ) ይሁን ሌሎችም ከነሱም ውጪ ያሉት ታዋቂ የሸሪዓ እውቀት ምንጭ የሚባሉ መጻህፍት ባለቤቶችም በዚህ ጉዳይ ከነቢዩም ይሁን ከሷሓቦች ወይም ከተከታዮቻቸው ምንም የዘገቡት ነገር የለም) ብለው መልሰዋል።
💥ከቢድዓ በመጠንቀቅ በዲኑ የተፈቀዱ ነገሮችን ብቻ በመስራት ወደ አላህ እንቃረብ!

አላህ ይወፍቀን!

ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
@ዛዱል መዓድ
🔸 🔹 🔸🔹 🔸🔹🔸

https://t.me/B1e9h