አባል ለመሆን የሚያበቁ መስፈርቶች
• በሕግ መብቱ ያልተገፈፈ፣
• ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነው፣
• ከአባላት ጋር ተመሳሳይ ፍላጐትና ዓላማ ያለው፣
• የአእምሮ ህመምተኛ ያልሆነ፣
• በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አራጣ አበዳሪ ያልሆነ፣
• ጥሩ ባህሪ ኖሮት በኀብረት ሥራ ማህበሩ መርህ የሚያምን፣
• የኅብረት ሥራ ማህበሩን የመተዳደሪያ ደንብ የተቀበለ፣
• በኅብረት ሥራ ማህበሩ የሥራ ክልል ውስጥ የሚኖር ወይም የሚሰራ፣
• በሌላ ተመሳሳይ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የኀብረት ሥራ ማህበር ውስጥ አባል ያልሆነ።

ሪፖርተር ጋዜጣ በረቡዕ ኅዳር 10 ቀን 2012 ዓም. እትሙ ምን እየሰሩ ነው በሚለው አምዱ ስር ከአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበር መስራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ሸለመ ጋር ሰፋ ያለ ውይይት አድርጓል በውይይቱ ላይም አቶ ዘሪሁን ከተናገሩት ንግግሮች መሀል ‹‹የሕግ ማዕቀፎች ቢመቻቹ በአገሪቱ የሚታዩ መሠረታዊ ችግሮችን በኅብረት ሥራ ማኅበራት መፍታት ይቻላል››የሚለውን እንደ ርዕስ ይዞ ቀርቧል ፤ሙሉ ዘገባውን ለመከታተል የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ https://www.ethiopianreporter.com/article/17353
የአዋጭ የ2012 ዓ.ም ዓምስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱ አበረታች መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታኅሳሥ 18 ቀን 2012 ዓ.ም
አዋጭ ባለፉት ዓምስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ በዋናው መ/ቤት ታኅሣሥ 18/2012 ዓ.ም ከጠቅላላ ሠራተኞቹ ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ በዚህም የኦፕሬሽን ዘርፍ፣ የፋይናንስና ሲስተም አስተዳደር በተለይ አዲስ ስለጀመረው የኮር ባንኪንግ ትግበራ፣ የሰው ሀብት እና ሌሎችም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶች ተካተው የቀረቡ ሲሆን በሁሉም ዘርፍ ያለፉት ዓምስት ወራት የተሻለ የሥራ አፈፃፀም እንደታየበት በሪፖርቶቹ ተገልጿል፡፡ ኅ/ሥ/ማኅበሩ እስካሁን ከ1ቢሊዮን ብር በላይ ለ7 ሺሕ አባላት ብድር ሰጥቷል፡፡ የብድር አመላለስ ኹኔታውም 99.63% ነው፡፡ አዋጭ ከአባላቱ ጋር ያለው ግንኙነት ጤናማና ውጤታማ እንደሆነና በቀጣይም በኹሉም ዘርፍ ጠንክሮ በመሥራት የስኬት ጉዞውን አጠናክሮ እንዲቀጥል የኅ/ሥ/ማኅበሩ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ሸለመ ለሠራተኞች መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

If you like the video press the thumb up button and subscribe to our YouTube channel, follow us on Facebook and Telegram.