AWACH SACCOS Ltd.
38.2K subscribers
3.23K photos
40 videos
8 files
752 links
ኅብረት ሥራ ማህበራችን የሚያከናውናቸው ተግባራት
የቁጠባ እና የብድር አገልግሎት
አነስተኛ የብድር መድህን አገልግሎት
የትምህርት ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት

+251-11-557-97-98
+251-11-557-88-89
+251-11-557-98-99
+251-11-868-47-44
saccawach@gmail.com
https://www.facebook.com/AWACHSACCOS
@awachsaccos
Download Telegram
አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር 23ኛውን የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች መደበኛ ጉባኤ አከናወነ!

👉 ሀምሌ 27 ቀን 2016 ዓ.ም አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች 23ኛውን መደበኛ ጉባኤ በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል አካሂዷል፡፡
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የኅብረት ሥራ ማህበሩ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መስፍን ገ/ስላሴ በ2016 በጀት ዓመት ኅብረት ሥራ ማህበሩ በ2016 በጀት ዓመት ከምንጊዜው የተሻለ የስራ አፈፃፀም ማስመዝገቡን በመግለፅ ለዚህም ውጤት የስራ አመራር ቦርድ አባላት ተሳትፎና የአመራርነት ድርሻ ቀላል የማይባል መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተያያዘም የስራ አመራር ቦርዱ በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸውን ተግባራት በዝርዝር ለጉባኤው በማቅረብ ለተገኘው ውጤት ለኅብረት ሥራ ማህበሩ አባላት፣ ለሰራተኞች፣ ለቁጥጥር ኮሚቴ አባላት ፣ ለኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮምሽን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በተያያዘም የኅብረት ሥራ ማህበሩ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን ሸለመ በአሜሪካን ሀገር በቦትሰን ስቴት በዓለም አቀፉ የ2024 የዓለም የገንዘብ ቁጠባና ብድር ምክር ቤት (WOCCU) ኮንፍረንስ ላይ የሀገራችንን ባንዲራ በብቸኝነት ይዘው በጉባኤው ላይ በመቅረብ በክብር ማቅረባቸውን በመግለፅ፤ አዋጭ በኅብረት ሥራ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደረገ ባለው ተሳትፎና እንደሀገር እያበረከተ ባለው አስተዋፅዖ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡
👉 በተያያዘም አቶ ዘሪሁን የኅብረት ሥራ ማህበሩን የ2016 በጀት ዓመት ሪፖርት ለጉባኤው በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርታቸውም ላይ በ2016 በጀት ዓመት ኅብረት ሥራ ማህበሩ በተለያዩ የሀገሪቷ ክልልሎች 4 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን መክፈቱን፣ ከአባላት 4 ቢሊየን ብር በላይ ቁጠባ በመሰብሰብ አጠቃላይ የቁጠባ መጠኑን ከ9.4 ቢሊየን ብር በላይ ማድረስ መቻሉን፣ ለ7882 አባላት ከ6.4 ቢሊየን ብር በላይ ብድር በመስጠት እስካሁን ለ38,398 አባላት ከ15.2 ቢሊየን ብር በላይ ብድር መስጠት መቻሉን፣ በኅብረት ሥራ ማህበሩ ጥሩ የብድር አመላለስ መኖሩን እና አጠቃላይ ኅብረት ሥራ ማህበሩ በአለም አቀፍ የፋይናንስ መለኪያዎች ደረጃ አንፃር ሲቃኝ በሁሉም መለኪያዎች አስተማማኝ አቋም ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አቶ ዘሪሁን አያይዘውም ኅብረት ሥራ ማህበሩ በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ ካፒታሉ 2.3 ቢሊየን ብር እንዲሁም ጠቅላላ ሀብቱ 11.8 ቢሊየን ብር ማድረስ መቻሉን በመግለፅ ኅብረት ሥራ ማህበሩ በሾላ ገበያ እና በልደታ አከባቢ ላይ ባሉት ሁለት ቦታዎች ላይ የግንባታ ስራ ለመጀመር በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አቶ ዘሪሁን ኅብረት ሥራ ማህበሩ ከምንጊዜውም በተሻለ ከሀገር ውስጥ አልፎ በተለያዩ የአለም ክፍሎች ከሚገኙ ኅብረት ሥራ ማህበራት ጋር የልምድ ልውውጥ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ በመግለፅ በበጀት ዓመቱ በሶስት አህጉራት (በአፍሪካ፣ በአሜሪካ እና በአውሮፓ) ላይ በመዘዋወር ልምድ እና ተሞክሮዎችን ከመለዋወጥ ባለፈ በ2030 ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ኅብረት ሥራ ማህበር ሆኖ ማየት የሚለውን ራዕዩን በተጨባጭ እያሳካ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
👉 በኅብረት ሥራ ማህበሩ የቁጥጥር ኮሚቴ ሰብሳቢ በዶ/ር ዮሴፍ ቤኮ አማካኝነት የቁጥጥር ኮሚቴ ሪፖርትም የቀረበ ሲሆን የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ደግሞ በኅብረት ሥራ ማህበሩ የስትራቴጂክ አመራርና ግብይት የስራ ክፍል ኃላፊ በአቶ ገረመው አማረ አማካኝነት ቀርቧል፡፡ ጉባኤው በቀረበው የ2016 በጀት ዓመት ሪፖርት፣ በቁጥጥር ኮሚቴ ሪፖርት፣ በ2017 በጀት ዓመት እቅድ እንዲሁም ሌሎች በተነሱ አጀንዳዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርጎ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡
👉 በመጨረሻም የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮምሽን የኅብረት ሥራ ፋይናንስ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ዱፌራ በመዝጊያ ንግግራቸው አዋጭ በየዓመቱ እያስመዘገበ ያለው እድገት አስደሳች መሆኑን በመግለፅ እንደሀገር በገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር ደረጃ የአዋጭ ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
👍579🙏5👏4
👏5👍31🙏1