ህልምህን ኑረው_Live your dream
1.81K subscribers
537 photos
48 videos
21 files
1.16K links
የቻናል አላማ ሰዎች ራዕያቸውንና አላማቸውን ለይተው በማወቅ ለተፈጠሩበት መልካም ስራ ማዋልን እና አስተሳሰባቸውን በመለወጥ የሚፈልጉትን ህልም እንዴት ማሳካት እንደሚችሉ ፣ የአሸናፊነት ልማድ፣የአእምሯችንን ሚስጥራዊ አሰራር የምናውቅበት እና የስኬታማ ሰዎች ተሞክሮም እናቀርባለን።
ዩቱዩቭ: https://www.youtube.com/@Live_Your_Dream2112
https://t.me/Attitudeplc
Download Telegram
"የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር መቃቃር የጀመረው  ራሱን ከተፈጥሮ ሁሉ የበላይ አድርጎ መመልከት ሲጀመር ነው።ለዚህም መነሻ ምክንያት የክርስትና አስተምህሮ ነው።"
ብሩህ አለምነህ

በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ሰፊ ዘመናትን የያዙት የባርያ ንግድ፣ ቅኝ ግዛት፣ የተለያዩ ዓይነት ባርነቶችና የሴቶች ጭቆናዎች ሁሉ መንስኤያቸው የሰው ልጅ መቆጣጠርንና ጥቅምን ዓላማው ባደረገ አስተሳሰብ መመራቱ ነው፡፡ አንድን ነገር “መቆጣጠር” ካሰብክ ራስህን የዚያ ነገር አካል አድርገህ ማሰብህን አቁመሃል፡፡ “መቆጣጠር” የሚለው ሀሳብ የሚመጣው ራስህን ከዚያ ነገር ለይተህ ስታየው ነው፡፡

እናም አውሮፓውያን በዚህ መንገድ ተጉዘው ራሳቸውን ከተፈጥሮ ገነጠሉ፤ ራሳቸውን ከተፈጥሮ መገንጠል ብቻ ሳይሆን ተፈጥሮን ለሰው ልጅ መጠቀሚያ ብቻ የተፈጠረ አድርገው እንዲቆጥሩት አድርጓቸዋል፡፡ በዚህ አስተሳሰብ ላይ ተመስርተውም የፈጠሩት ሃይማኖት (ክርስትና)፣ የካፒታሊዝም ስልተ ምርት፣ ፍልስፍናና ሳይንስም ተፈጥሮን ይበልጥ እንደመጠቀሚያ እና ሜካኒካል በሆኑ ክስተቶች የተሞላ አድርገው እንዲያስቡት አድርጓቸዋል፡፡ ለምሳሌ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሄር ምድርን የሠራት፣ እንስሳትንና እጽዋትንም የፈጠራቸው ለሰው መጠቀሚያነት እንደሆነ ይናገራል፤
“እግዚአብሄርም አለ፡- ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር፤ የባሕር አሣዎችንና የሰማይ ወፎችን፤ እንሳሳትንና ምድርን ሁሉ፤ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ፤”
(ዘፍ 1፥ 26)

​"አላህ በሰማያትና በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ ያስገዛላችሁ፤ ግልጽና ድብቅ የሆኑትንም ጸጋዎቹን በፊታችሁ ላይ ያፈሰሰላችሁ መሆኑን አታዩምን?"
(ቁርአን 31፥20)

እንደዚህ አይነት መንፈሳዊ አስተምህሮ እንደ ታሪክ ምሁሩ Lynn White, Jri አመለካከት፣

"የሰውን ልጅ ራሱን ከተፈጥሮ የተገነጠለና የተለየ፤ የፍጥረታት ሁሉ ማዕከልና የሁሉም የበላይ አድርጎ እንዲመለከት በማድረግ ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ "

በሃይማኖታዊ አስተምህሮው ከተፈጥሮ ራሱን የገነጠለው አውሮፓ “ተፈጥሮን መቆጣጠርና ማስገበር ” በሚል መርህ ወደሚመራው ካፒታሊስታዊ ስልተምርት ተሸጋገረ፡፡ ካፒታሊዝምም የገበያ ውድድርን በማፋፋምና ከፍላጎት በላይ የሚጠቀም ማህበረሰብን በመፍጠር ተፈጥሮ ላይ የመጨከኑና ከመጠን በላይ የመበዝበዙን መንገድ አጠናክሮ ገፋበት፡፡ እንደ አዲሶቹ ማርክሲስቶች አመለካከት ግን የካፒታሊዝም ጦስ የሰውን ልጅ ከተፈጥሮ በመገንጠል ብቻ አያበቃም፤

"ካፒታሊዝም የሰውን ልጅ ከተፈጥሮ ብቻ ሳይሆን ከራሱ ሰውነትም ገንጥሎታል፡፡ ካፒታሊዝም የሰውን ልጅ ሃይል በገበያ ብዙ ትርፍ ሊያመጣ እንደሚችል ኢንቨስትመንት በመቁጠር ሰውነትን ወደ ሸቀጥነት ቀይሮታል፡፡"

እናም ወደ ሸቀጥነት የተቀየረው ሰው ለተፈጥሮ የሚያዝንበት ህሊና አጣ፡፡

የጥንቱና የምዕራብያውያን ፍልስፍና ዋነኛ ትኩረቱ ሰው ከሚኖርበት አካባቢና ከዲበ አካላዊው (ከሰማያዊው) ዓለም ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያስስ ነበር፡፡ እውነትንና እውቀትን፤ ውበትንና የሕይወት ትርጉምን ሁሉ በዚህ ሂደት ውስጥ ለማግኘት ይሞክር ነበር፡፡ ይሄም ሂደት  ከተፈጥሮ ጋር የነበረውን ጥብቅ ቁርኝት የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ የጥንቱ አውሮፓዊነት ከተፈጥሮ ጋር መቃቃር የጀመረው ግን ራሱን ከተፈጥሮ ሁሉ የበላይ አድርጎ መመልከት ሲጀመር ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ትምክህታዊ አመለካከት እንዲይዝ ካደረጉት አስተምህሮቶች ውስጥ ዋነኛው ደግሞ ክርስትና ነው፡፡

" የሰማያት ሰማይ ለእግዚአብሔር ነው፤ ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።"
መዝሙረ ዳዊት 115፥16

ክርስትና (እና እስልምና) እግዚአብሄር ምድርን ለሰው ልጅ መጠቀሚያ እንደፈጠረ በማስተማር የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር የነበረውን ህብረትና ጓደኝነት ቆረጡት፡፡ አውሮፓዊነትም በዚህ የክርስትና አስተምህሮ ተጠልፎ ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ግንኙነት ከሁለንተናዊ ህብርነት ወደ ገዥና ተገዥ፣ ጨቋኝና ተጨቋኝ፣ መለኮታዊና አለማዊ ወደሆነ “ቁጥጥር እና ጥቅም”ን ታሳቢ ወዳደረገ የሁለትዮሽ ግንኙነት ተቀየረ፡፡ የኒውተን ሜካኒክስ እንዲሁም የሆብስ፣ የላሜትሪ እና የዴካርት ፍልስፍናዎች መሰረታቸው ይሄው በሰውና በተፈጥሮ መካከል ያለው የበላይነትና የበታችነት የሁለትዮሽ ግንኙነት ነው፡፡

እነሱ የሚመኩበት “የምክንያታዊነት” እና “ተፈጥሮን በመቆጣጠር የማስገበር” አካሄድ መጨረሻ ላይ የምድራችንንና አጠቃላይ የሰውን ልጅ ህልውና የከፋ አደጋ ላይ ጣለው፡፡ አውሮፓዊነት ከተፈጥሮ ጋር የነበረውን የስሜት ቁርኝት ትቶ የተጓዘበት መንገድ መጨረሻው ተፈጥሮን በማምከን የሰውን ልጅ ለከፋ አደጋ ዳረገው፡፡

✍️ ብሩህ አለምነህ

📌አሁኑኑ ይ🀄🀄ሉን
በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን
🎯🎯🎯🎯🎯🎯

🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን
SUBSCRIBE ያድርጉ

ዩቱዩብ:
https://www.youtube.com/@Asfaww

ቲክቶክ:
https://tiktok.com/@asfaw_motivation
ፌስቡክ:  https://www.facebook.com/attitudease

ቴሌግራም: 
https://t.me/Attitudeplc


  ለግል ለአስተያየትዎ:
https://t.me/LYDAse1

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
ስራ-ፈት አትሁኑ!

ለምንም ነገር እራሳችሁን ካልሰጣችሁ በሁሉም ነገር መረበሻችሁ አይቀርም። ስራፈትነት ከውጤት አልባነት በዘለለ ብክነትንም ያስከትላል። የማይረባ ሃሳብ መነሻው ከስራፈት አዕምሮ ነው። ስራ ፈቶ መቀመጥ ለማንም ከባድ አይደለም፣ ማንንም የሚፈትን አይደለም። ስራፈት መሆንን መምረጥ መብት ነው፣ ህይወት ግን ለስራፈቶች ቦታ የላትም። እንኳን ያለስራ ተቀምጦ ይቅርና ቀኑን ሙሉ እየሰሩም ህይወት ክብደቷን አትቀንስም። መጥፎ ሀሳቦች የሚቆጣጠሩን መቼ ይመስሏችኋል? በቀላሉ ለሱስና ለአሉታዊ ልማዶች የምንጋለጠው መቼ ይመስላችኋል? በእርግጥም ያለስራ የምናሳልፈው ጊዜ ብዙ ሲሆን ነው። የሰው አዕምሮ በስራና በፈጠራ ሀሳቦች ካልተወጠረ በቀላሉ ለውዳቂና ጥቃቅን ሀሳቦች መጋለጡ አይቀርም። ሁሌም እድገት በሌለው ኋላቀር ሀሳብ ስትሞሉ ልባችሁ እየደነደነ፣ ግዴለሽና ተስፋቢስ እየሆናችሁ ትመጣላችሁ። ስራ ገቢ ከማምጣቱም በላይ የህሊና እረፍትን ይሰጣል። ያለምንም ስራ ቁጭ ብሎ መዋልና እራስን በስራ መወጠር የሚሰጡት የህይወትና የሀሳብ ነፃነት እኩል አይደለም።

አዎ! ስራ-ፈት አትሁኑ! አዕምሯችሁን በሚያሳድጓችሁ ሀሳብና ስራ ወጥሩ፣ ነፃነትን በሚነፍጓችሁ ብዙ ነፃና የእረፍት ጊዜያት ህይወታችሁን አትሙሉ። የተገደበ እረፍትና የተገደበ የስራ ሰዓት ያስፈልጋችኋል። ስራፈት አዕምሮ የሰይጣን መነሃሪያ ነው። ሰይጠናን እንደፈለገው ይመራዋል፣ የፈለገውን ያስደርገዋል፣ ያሰኘው ነገር ውስጥ ይከተዋል። ስራፈት ስትሆኑ ሰይሰን ብቻ ሳይሆን የሰውም መጫወቻ ትሆናላችሁ። ይብዛም ይነስም ስራ በእራሱ ክብር ነው፣ አንድ መዋያና አዕምሮን ማሳረፊያ ነገር ማግኘት በእራሱ ስኬት ነው። ምንም ቢሆን ካለመስራት መስራት ይሻላል፣ የማይረባ ሀሳብ ከማሰብ ጠቃሚና ህይወት ቀያሪ ሀሳብን ማሰብ ይሻላል። ሁን ብላችሁ እራሳችሁን ጫና ውስጥ ክተቱት፣ ስራፈት በመሆን በማያሳድጋችሁ ምቾት ውስጥ አትቀመጡ። ወጣ በሉ፣ እራሳችሁን ፈትኑት፣ አቅማችሁን መዝኑ፣ እውቀታችሁን በተግባር ግለጡት። ተቀምጦ መናን ከሰማይ መጠበቅ አያዋጣም። ምንም ቢሆን መናው እስከሚወርድበት ቦታ መጓዝ የግድ ነው። "ሳይሰሩ የሚበሉ እጆች የተረገሙ ይሁኑ" እንደሚል መፅሀፍ ቅዱስ እራሳችሁን የወጣት ተጧሪ አታድርጉ።

አዎ! ጀግናዬ..! ተንቀሳቀስ፣ ዞር ዞር በል፣ ለእድገትህ መሱዓትነት ለመክፈል ተዘጋጅ። አርሶ፣ ዘረቶ፣ አርሞ፣ አጭዶ፣ ወቅቶ ሰብሉን ለገበያ የሚያቀርበውን የብርቱውን ገበሬ ታታሪነት ተመልከት። መስራት ብቻ ሳይሆን ጠንክሮ መስራት በራሱ ዲኤንኤው (DNA) ውስጥ ነው። ማንነቱን ለስራ አሳልፎ ሰጥቷልና በቀላሉ የማይሰበር ጠንካራ ልብ አለው፣ የእጆቹን ስራ ፈጣሪው እንደሚባርክለት ከልቡ ያምናል፣ ፅናቱና ታታሪነቱ እንደሚከፍለው ያውቃል። ስራ ስትፈታ እጆችህ የሰይጣን መጠቀሚያ ይሆናሉ። ለመብላት መዝረፍ ትጀምራለህ፣ ስራፈትነትህን ለመርሳት ወደ ሱስ ትገባለህ፣ በአጭር ጊዜ ገንዘብ ለማግኘት ወንጀልን ጨምሮ የተለያዩ አቋራጭ መንገዶችን ትጠቀማለህ። ስራ አትናቅ፣ ከሚያስገኝልህ ገንዘብ በላይ የሚሰጥህን የሰራተኝነት ነፃነት አስብ። ስራ እየናቁ ተንቀው የቀሩ ብዙ ሰዎች አሉ፣ ስራ እየመረጡ ምራጭ ሆነው የቀሩ ብዙ ሰዎች አሉ። ዛሬ በገቢው ያነሰ ስራን ብትሰራ ሁሌም እርሱን እየሰራህ አትኖርም። የሰው ልጅ ምንም ሰርቶ ምንም ገቢ ቢያገኝ አጠቃቀሙን ካወቀበት በሂደት እራሱን ማሳደጉ አይቀርም። ጠንቃቃ ሁን፣ ስራህን አክብር፣ ልብና አዕምሮህን አስገዛለት፣ ጠንክረህ ስራ የነገው ህይወትህንም ዛሬ እራስህ ወስን።

📌አሁኑኑ ይ🀄🀄ሉን
በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን
🎯🎯🎯🎯🎯🎯

🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን
SUBSCRIBE ያድርጉ

ዩቱዩብ:
https://www.youtube.com/@Asfaww

ቲክቶክ:
https://tiktok.com/@asfaw_motivation
ፌስቡክ:  https://www.facebook.com/attitudease

ቴሌግራም: 
https://t.me/Attitudeplc


  ለግል ለአስተያየትዎ:
https://t.me/LYDAse1

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
"ውድድሩን የማሸንፈው በስታዲየም ውስጥ ብርሃን ባለበት አይደለም፤ ድሉ የሚወሰነው ከዓይን  ጠባቂዎች ርቆ በለሆሳስ በሚደረግ ትጋት፣ በባዶ ጂም ውስጥ በለፋሁባቸው ሰዓታት ውስጥ ነው።"  ሙሀመድ አሊ
የሁለቱ ተኩላዎች ታሪክ (The Two Wolves)።
🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣
አንድ አረጋዊ የቼሮኪ (Cherokee) ጎሳ መሪ ለልጅ ልጁ ስለ ሕይወት እያስተማረው ነው። "በውስጤ ትልቅ ውጊያ እየተካሄደ ነው" አለው ለብላቴናው። "በሁለት ተኩላዎች መካከል የሚደረግ በጣም አስፈሪ ውጊያ ነው። አንደኛው ክፉ ነው — እሱም ቁጣ፣ ቅናት፣ ሃዘን፣ ጸጸት፣ ስግብግብነት/ስስት፣ ትዕቢት፣ እራስን ማዘን፣ የጥፋተኝነት ስሜት፣ ቅያሜ፣ የበታችነት ስሜት፣ ውሸት፣ የሀሰት ኩራት፣ የበላይነት ስሜት እና እራስ ወዳድነት (ego) ነው።"

በመቀጠልም እንዲህ አለ፦ "ሌላኛው ደግሞ ጥሩ ነው — እሱም ደስታ፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ተስፋ፣ መረጋጋት፣ ትህትና፣ ደግነት፣ ለሰዎች በጎ መሆን/ቸርነት፣ የሌሎችን ስሜት መረዳት (empathy)፣ ልግስና፣ እውነት፣ compassion (ርህራሄ) እና እምነት ነው። ይህ የውስጥ ውጊያ በአንተም ውስጥ እየተካሄደ ነው — በሌሎች ሰዎች ሁሉ ውስጥም ጭምር።" የልጅ ልጁም ስለ ነገሩ ለአንድ ደቂቃ ያህል ካሰበበት በኋላ አያቱን "ታዲያ የትኛው ተኩላ ነው የሚያሸንፈው?" ብሎ ጠየቀው። አረጋዊው የቼሮኪ መሪም በቀላሉ "የምትመግበው" ሲል መለሰለት።

ይህ ታሪክ የንቃተ ህሊናን (awareness) ኃይል በግልጽ ያሳያል። የትኛውን ተኩላ መመገብ እንዳለብህ ከመምረጥህ በፊት፣ መጀመሪያ በውስጥህ ሁለት ተኩላዎች እንዳሉ ማወቅ (ነቅቶ ማስተዋል) ይኖርብሃል። መኖራቸውን፣ ረሃባቸውን እና በውስጥህ የሚያሳድሩትን ተፅዕኖ ማስተዋል አለብህ።

1️⃣ የማንነትህ ቀራፂ እራስህ ነህ፦ በሁላችንም ውስጥ ጨለማና ብርሃን አለ። የሚያሸንፈው ግን ዕድል ሳይሆን አንተ ትኩረትና ጉልበት ሰጥተህ በየቀኑ የምትመግበው ስሜት ነው።

2️⃣ "የመመገብ" ኃይል፦ በቂም እና በቁጣ ላይ ስታተኩር ክፉውን ተኩላ ታጠነክረዋለህ። በምስጋና፣ በይቅርታና በደግነት ላይ ስታተኩር ደግሞ መልካሙን ተኩላ እያሳደግከው ነው።

3️⃣ ንቃተ ህሊና (Awareness)፦ በውስጥህ ውጊያ እንዳለ መጀመሪያ ካላስተዋልክ፣ የትኛውን መመገብ እንዳለብህ መምረጥ አትችልም። ሁሌም ስሜቶችህ ከመምራትህ በፊት ቆም ብለህ አስተውላቸው።
📌 ጥያቄ ለእናንተ፦ ዛሬ በሃሳባችሁና በድርጊታችሁ እየመገባችሁት ያላችሁት የትኛውን ተኩላ ነው?

📌አሁኑኑ ይ🀄🀄ሉን
በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን
🎯🎯🎯🎯🎯🎯

🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን
SUBSCRIBE ያድርጉ

ዩቱዩብ:
https://www.youtube.com/@Asfaww

ቲክቶክ:
https://tiktok.com/@asfaw_motivation
ፌስቡክ:  https://www.facebook.com/attitudease

ቴሌግራም: 
https://t.me/Attitudeplc


  ለግል ለአስተያየትዎ:
https://t.me/LYDAse1

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
🛑 #የዘገየ_ትክክለኛ_ውሳኔ... ራሱ ሌላ ስህተት ነው! (The Law of Timing)

"አንድን ውሳኔ በትክክለኛው ጊዜ ካልወሰንከው፣ በኋላ ላይ መቶ በመቶ ትክክለኛ ቢሆን እንኳ ዋጋ የለውም፤ ምክንያቱም ጊዜው አልፏል።"

ብዙ ሰው በሕይወቱ ስህተት ላለመሥራት በሚል ሰበብ አንድን ነገር ለማድረግ ለወራትና ለዓመታት ያስባል። "ሁሉንም ነገር አጥንቼና እርግጠኛ ሆኜ ነው የምወስነው" ይላል። እውነቱ ግን ይህንን ነው፦ "ፍጹም የሆነውን ቀን ለመጠበቅ ስትል የምታዘገየው እያንዳንዱ ትክክለኛ ውሳኔ፣ ዕድሉ ካለፈ በኋላ ምንም ዓይነት ውጤት ስለማያመጣ በራሱ ትልቅ ስህተት ነው።"

ስኬት የሐሳብ ጥራት ብቻ አይደለም፤ የስሌትና የሰዓት (Timing) ጉዳይም ጭምር ነው።

ልክ ከ3 ዓመት በፊት መጀመር የነበረብህን አንድ የዲጂታል ቢዝነስ ወይም ኢንቨስትመንት፣ ዛሬ ላይ ቆመህ "አሁን በሚገባ አጥንቼ ገባሁበት" ብትል እንኳ ያኔ ልታገኘው የምትችለውን ትልቅ የዕድገት ማዕበልና ጥቅም አታገኘውም። ውሳኔው ዛሬም ትክክል ሊሆን ይችላል ፤ ሰዓቱ ግን ስህተት ነው። በጦር ሜዳ ላይ ጥይት ካለቀ በኋላ የሚተኮስ እጅግ ምርጥ ኢላማ እንደማይጠቅመው ሁሉ፣ ዕድሎች ካለፉ በኋላ የሚወሰን "ትክክለኛ ውሳኔ" የቁጭት መሸፈኛ ጭምብል ብቻ ነው።

ፍጽምና ወጥመድ ነው፦ ሁሉንም ነገር አውቄ እጀምራለሁ ስትል ጊዜው ይቀድምሃል። ፍጹም ዝግጁ ለመሆን አትጠብቅ ፤ ውሳኔህን ዛሬውኑ አውጅ።
የፍጥነት ዋጋ ከፍ ያለ ነው፦ በዘመናዊው ዓለም ውስጥ ቀስ ብሎ በትክክል ከሚራመደው ይልቅ፣ ፍርሃቱን ተቋቁሞ በፍጥነት ወስኖ ስህተቱን በመንገድ ላይ የሚያርመው ቆራጥ ሰው ቀድሞ ግቡ ላይ ይደርሳል።
ጊዜ ዕድልን ይበላል፦ ዛሬ ያመነታህበትና ወደኋላ ያልከው ዕድል፣ ነገ ሌላ ሰው ቀድሞህ ወስኖበት ታሪክ ሲሠራበት ማየትህ አይቀሬ ነው።

ታላላቅ የዓለማችን መሪዎችና ባለሀብቶች በሙሉ መቶ በመቶ እርግጠኛ እስኪሆኑ የጠበቁ አይደሉም፤ የጊዜን ውድነት ተረድተው "አሁንኑ" በሚል ፍጥነት የወሰኑ ጀግኖች እንጂ። አንተስ? ዛሬም ውሳኔህን በማዘግየት ላይ ነህ?

📌አሁኑኑ ይ🀄🀄ሉን
በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን
🎯🎯🎯🎯🎯🎯

🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን
SUBSCRIBE ያድርጉ

ዩቱዩብ:
https://www.youtube.com/@Asfaww

ቲክቶክ:
https://tiktok.com/@asfaw_motivation
ፌስቡክ:  https://www.facebook.com/attitudease

ቴሌግራም: 
https://t.me/Attitudeplc


  ለግል ለአስተያየትዎ:
https://t.me/LYDAse1

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
#የሰው_ልጅን_የሚለውጡ_ልማዶች !!

1. ​የአቶሚክ ልማዶች (Atomic Habits)፦ ትናንሽና ተከታታይነት ያላቸው ለውጦች በረጅም ጊዜ ውስጥ ትልቅ ውጤት ያመጣሉ።

2. ​በማንነት ላይ ያተኮረ ልማድ (Identity-Based Habits)፦ ልማድን ለመቀየር "ምን ማግኘት እፈልጋለሁ?" ከሚለው ይልቅ "ምን ዓይነት ሰው መሆን እፈልጋለሁ?" በሚለው ላይ ማተኮር።

3. ​አራቱ የባህሪ ለውጥ ህጎች (The Four Laws)፦ ማንኛውንም ልማድ ለመገንባት ግልጽ ማድረግ፣ ማራኪ ማድረግ፣ ቀላል ማድረግ እና አርኪ ማድረግ።

4. ​ልማድ መደራረብ (Habit Stacking)፦ አዲስ ልማድን ቀድሞ በነበረና በለመድነው ልማድ ላይ መጨመር።

5. ​አካባቢን ማስተካከል (Environment Design)፦ ለጥሩ ልማዶች ግልጽ የሆኑ ምልክቶችን በአካባቢያችን ማዘጋጀት

6. ​የሁለት ደቂቃው ህግ (The Two-Minute Rule)፦ ማንኛውንም አዲስ ልማድ ሲጀምሩ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ሊያልቅ በሚችል ቀላል ስራ መጀመር።

7. ​የማይመች ማድረግ (Make it Difficult)፦ መጥፎ ልማዶችን ለማቆም በመንገዳችን ላይ እንቅፋቶችን መፍጠር። አጫሽ ከሆንክ ለማጨስ በማይመች ቦታ መዋል።

8. ​ልማድን መከታተል (Habit Tracking)፦ የምናደርጋቸውን ስራዎች መዝግቦ መያዝ ስኬታማነታችንን እንድናውቅ ይረዳናል።

9. ​ወዲያውኑ የሚገኝ እርካታ (Instant Gratification)፦ አእምሯችን ለወደፊት ከሚገኝ ጥቅም ይልቅ አሁን ለሚያገኘው ደስታ ቅድሚያ ስለሚሰጥ፣ ለጥሩ ልማዶች አነስተኛ ሽልማቶችን ማዘጋጀት።

10. ​መሰላቸትን ማሸነፍ (Goldilocks Rule)፦ ልማዶች በጣም አስቸጋሪ ወይም በጣም ቀላል ሳይሆኑ፣ ተግዳሮት ያለባቸው ሲሆኑ ይቀጥላሉ።

📖  "Atomic Habits"
✍️ጄምስ

📌አሁኑኑ ይ🀄🀄ሉን
በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን
🎯🎯🎯🎯🎯🎯

🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን
SUBSCRIBE ያድርጉ

ዩቱዩብ:
https://www.youtube.com/@Asfaww

ቲክቶክ:
https://tiktok.com/@asfaw_motivation
ፌስቡክ:  https://www.facebook.com/attitudease

ቴሌግራም: 
https://t.me/Attitudeplc


  ለግል ለአስተያየትዎ:
https://t.me/LYDAse1

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
የዝሆኑ ሰንሰለት (The Elephant Rope)
🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣
አንድ መንገደኛ በጎዳና ሲያልፍ አንድ ግዙፍ ዝሆን በአነስተኛ ገመድ ብቻ እግሩ ታስሮ ቆሞ አየ። ዝሆኑ ሰንሰለት አልታሰረም። በስተጀርባውም የሚታሰርበት የብረት አጥር የለም። ዝሆኑ በቀላሉ ገመዱን በጥሶ ማምለጥ እንደሚችል ግልጽ ነበር። ነገር ግን ለመሞከር እንኳን አይፈልግም።

መንገደኛው ግራ በመጋባት የዝሆኑን አሰልጣኝ
"ይህ ግዙፍ እንስሳ እንዴት በዚህች ደካማ ገመድ ብቻ ተይዞ ለመሰብሰብ አይሞክርም?"

ሲል ጠየቀው።
አሰልጣኙም ፈገግ ብሎ እንዲህ አለው፦ "ዝሆኖቹ በጣም ትናንሽ ልጆች እያሉ የምናስራቸው በዚህችው ገመድ ነው። በዚያ እድሜያቸው ገመዱን ለመበጠስ አቅም አልነበራቸውም። ሲያድጉና ግዙፍ ሲሆኑም በውስጣቸው
'ይህችን ገመድ መበጠስ አልችልም'

የሚል እምነት አብሮአቸው ያድጋል። አሁንም ገመዱ ሊያስራቸው እንደሚችል ስለሚያምኑ መቼም ቢሆን ለማምለጥ አይሞክሩም።"

💡 የታሪኩ ዋና መልዕክት፦
ብዙዎቻችን በሕይወታችን ልክ እንደዚህ ዝሆን ነን። ድሮ በልጅነታችን ወይም ቀደም ሲል በነበረን ውድቀት ምክንያት "አልችልም" የሚል የገደብ እምነት (Limiting Belief) በውስጣችን እንፈጥራለን። ትልቁ ሰንሰለት ያለው እግራችን ላይ ሳይሆን አእምሯችን ውስጥ ነው።

📌 ጥያቄ ለእናንተ፦ እናንተስ ዛሬ እንዳታድጉ አምክኖ የያዛችሁ የአእምሮ "ገመድ" የትኛው ነው?
The Overview effect

ለዘመናት የሰው ልጅ አእምሯዊና ስነ ልቦናዊ መዋቅር በወሰኖች፣ በጥበቃዎችና በክልከላዎች ግንብ የታጠረ ነበር። ማንነታችንን የምንተርከው በካርታዎች ላይ በሰፈሩ የድንበር መስመሮች፣ በጎሳና በፖለቲካ የጎራ ክፍፍሎች፣ እንዲሁም በጠበቡ የማህበረሰብ ቡድኖቻችን ጭፍን ወገንተኝነት (tribal biases) ነው። ሁላችንም እንደየምርጫችን የተሰነጠቀ መስታወት ይዘን ያንን የያዝነውን ስባሪ ብቻ ሙሉው ሰማይ አድርገን የመቁጠር ስህተት ውስጥ እንወድቃለን። ነገር ግን ከዚህ ከከበበን የዕለት ተዕለት ውክቢያ ወጣ ብሎ በጥቁሩና ማለቂያ በሌለው የህዋ ባዶነት ውስጥ ይህንን የሰው ልጅ የስባሪ አስተሳሰብ በአንድ ቅፅበት የሚያክም፣ የአመለካከት አድማስን ሙሉ በሙሉ የሚገለብጥ አንድ አስደናቂ ስነ ልቦናዊ ክስተት አለ፤ እርሱም {ኦቨርቪው ኢፌክት} (The Overview Effect) ይባላል።

​ይህንን ፅንሰ ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ ያፈለቀው የህዋ ፈላስፋው ፍራንክ ኋይት ሲሆን፣ ክስተቱም ጠፈርተኞች መሬትን ከህዋ ምህዋር ላይ ሆነው በሚመለከቱበት ጊዜ የሚገጥማቸውን ጥልቅና ስር-ነቀል የአእምሮና የንቃተ-ህሊና መለወጥ የሚገልፅ ነው። ይህ የፕላኔታችንን ውበት ዝም ብሎ በአድናቆት መመልከት ብቻ አይደለም፤ ከዚያ በላይ የሆነ የሰው ልጅን መኖርና ምንነት ዳግም የሚመረምር ህልውናዊ መናወጥ (existential rupture) የሚፈጥር ነዉ።

መሬትን ከሩቅ፣ ከናኘው የአፅንፈ-ዓለም ፀጥታ ውስጥ ሆኖ መመልከት ሁሉንም ነገር አቅፎ የያዘን አንድ ወጥና የተሟላ ስርአት እንደማየት ነው። እዚያ ላይ የፖለቲካ ድንበሮች፣ የብሄር ክፍፍሎች ወይም ቀጠናዊ አጥሮች የሉም። የሰው ልጅ በጥቃቅን ነገሮች ተከፋፍሎ የሚኖርበት ያ አሮጌ ቅዠት በአንድ አፍታ ይበራል፤ በእርሱም ምትክ ፍፁም የሆነው ሁለንተናዊ አንድነት ጉልህ ሆኖ ይታያል።

ይህ ክስተት አእምሯችንን ነገሮችን ለያይቶና ነጣጥሎ ከማየት ወደ አጠቃላይ ስርአታዊ ውህደት እንዲሸጋገር ያስገድደዋል። በምድራዊ ህይወታችን የሰው ልጅ አስተሳሰብ በአብዛኛው የሚመራው {እኛ እና እነሱ} በሚል የጎራ ክፍፍል ነው። ይህ ደግሞ በዝግመተ-ለውጥ ሂደት ውስጥ ራሳችንንና ቡድናችንን ለመጠበቅ ከአባቶቻችን የወረስነው አሮጌ አሻራ ነው። ነገር ግን ይህ ክስተት ያንን ጥንታዊ መዋቅር ሙሉ በሙሉ ያፈርሰዋል።

የ{እኛ} የሚለውን ትርጉም አስፍቶ የአፅንፈ-ዓለሙን የመጨረሻ ጫፍ እንዲነካ ያደርገዋል። ይህ ታላቅ ሽግግር በሶስት ዋና ዋና አእምሯዊ ለውጦች ውስጥ ያልፋል። በመጀመሪያ፣ ከህዋ ምህዋር ላይ ሆነው ሲመለከቱ በሰዎች ታሪክ ውስጥ ለብዙ ጦርነቶችና እልቂቶች ምክንያት የሆኑት ፖለቲካዊ መስመሮች ሙሉ በሙሉ የማይታዩና የሌሉ ይሆናሉ። በምድር ላይ በደም የተፃፉት ድንበሮች ውቅያኖሶችን፣ ከባቢ አየርንና አህጉራትን ብቻ ከሚያውቅ ፕላኔት አንፃር ሲታዩ ምንኛ የሞኝነትና የከንቱነት ማሳያ መሆናቸው በግልፅ ይጋለጣል።

በሁለተኛ ደረጃ፣ ተመልካቹ ሰፊና ሁለንተናዊ ወደሆነ ማንነት ይሸጋገራል። ከዚያ በኋላ ግለሰቡ ራሱን የአንድ የተወሰነ ሀገር ዜጋ ወይም የአንድ ጠባብ ርዕዮተ-ዓለም አራማጅ አድርጎ ማየት ያቆማል። ይልቁንም በጥቁሩ ህዋ ውስጥ እየተጓዘች ያለች በውስጧ ህይወትን ያቀፈች አንዲት ደካማና ውብ የጠፈር መንኮራኩር አካልና ተጓዥ አድርጎ ራሱን ይቆጥራል፤ ይህንን {መርከባዊዋ-መሬት ንቃተ ህሊና} (Spaceship Earth) እንለዋለን።

በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ፣ በግለሰቡ {እኔነት} እና በውጪው ዓለም መካከል ያለው ጠንካራ አጥር መፍረስ ይጀምራል። የአፅንፈ-ዓለሙ ግዙፍነት በአእምሮ ውስጥ ጥልቅ የሆነ ትህትናንና የመገረም ስሜትን ይፈጥራል። በዚህ ጊዜ ምድራዊና ጥቃቅን የሆኑት የዕለት ተዕለት ጭንቀቶቻችን በጠቅላላው ስርአት ውስጥ ቀልጠው ይጠፋሉ፤ በእነርሱም ምትክ ለዚህች ፕላኔትና በውስጧ ላለው ህይወት ሁሉ ጥልቅ የሆነ የመጠበቅና የመንከባከብ ኃላፊነት ይተካል።

ይህ ስነልቦናዊ ክስተት የሰዉ ልጆች ምን ያህል መሻሻል የሚችል {progressive} የሆነ ዝግመተ-ለዉጣዊ የስነ ልቦና አጥሮች እንዳሏቸዉ በዉል ማረጋገጥ የቻለም ጭምር ነዉ።
መጽሐፍ ማንበብ በሰዎች ሕይወት፣ አስተሳሰብና ስኬት ላይ ታላቅ አዎንታዊ አስተዋፅኦ አለው::

የሚያነቡ ሰዎች ከማያነቡ ሰዎች የዕውቀት አድማሳቸው ሰፊና ጥልቅ ሲሆን አስተሳሰባቸውም የበሰለ ነው።  መጻሕፍትን ባነበቡ ቁጥር ወደ ተለያዩ ዓለማት የመጓዝ፣የሰዎችን ሕይወት የመረዳትና ጥልቅ ጥበብን የመቅሰም ዕድል ያገኛሉ። ንባብ የቃላት እውቀታቸውንና የንግግር ክህሎታቸውን ከማሳደጉም በላይ፣ ለማንኛውም ችግር ምክንያታዊና ስልታዊ መፍትሔ እንዲፈልጉ ይረዳቸዋል። እነዚህ ሰዎች በራስ መተማመናቸው ከፍተኛ ነው፤ምክንያቱም በውስጣቸው የማይነጥፍ የዕውቀት ስንቅ አላቸው። ንባብ ለእነሱ አእምሯቸውን የሚያድሱበት፣ ጭንቀትን የሚቀንሱበትና ሁልጊዜም ራሳቸውን የሚያውቁበት የብርሃን ጎዳና ነው። በአጭሩ፣የሚያነቡ ሰዎች ትላንት ከነበሩበት የተሻሉ ለመሆን በየቀኑ የሚተጉ የሕይወት መሐንዲሶች ናቸው።

የማያነቡ ሰዎች በአንጻሩ ዕውቀታቸውና አመለካከታቸው በአካባቢያቸው በሚሰሙትና በሚያዩት ጥቂት ነገሮች ላይ ብቻ የተገደበ ይሆናል። ዓለም በየቀኑ በሚፈጥራቸው አዳዲስ እውነታዎችና የዕድገት ለውጦች ውስጥ በፍጥነት የመራመድ ዕድላቸው ጠባብ ነው። ንባብን ሕይወታቸው ያላደረጉ ሰዎች ለአድልዎ፣ለተሳሳቱ መረጃዎችና ለወሬ የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፤ ምክንያቱም ነገሮችን በምክንያትና በማስረጃ የማመዛዘን ልምዳቸው አልዳበረም። ይህም በሰዎች ላይ ጥገኞች እንዲሆኑና የራሳቸውን ጠንካራ አቋም እንዳይገነቡ ያደርጋቸዋል። አእምሯቸውን በአዲስ አስተሳሰብ ሳያድሱ ስለሚኖሩ፣ የሕይወት እይታቸው አሰልቺና ከተለመደው አስተሳሰብ የማይወጣ የመቀጨጭ ዕጣ ፈንታ ይገጥመዋል። የንባብ ልምድ በብርሃንና በጨለማ መካከል እንዳለው ዓይነት የሕይወት ልዩነትን ይፈጥራል።

📌አሁኑኑ ይ🀄🀄ሉን
በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን
🎯🎯🎯🎯🎯🎯

🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን
SUBSCRIBE ያድርጉ

ዩቱዩብ:
https://www.youtube.com/@Asfaww

ቲክቶክ:
https://tiktok.com/@asfaw_motivation
ፌስቡክ:  https://www.facebook.com/attitudease

ቴሌግራም: 
https://t.me/Attitudeplc


  ለግል ለአስተያየትዎ:
https://t.me/LYDAse1

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
“ሰዎች የምትናገትሩን ነገር ሊጠራጠሩ ይችላሉ፣ የምታከናውኑትን ነገር ግን ከማመን ውጪ ምርጫ የላቸውም” ይባላል!

እውነተኛ ማንነት፣ ስም፣ ተቀባይነትም ሆነ ዝና የሚገነቡት ድርጊቶቻችን እንጂ የምናወራቸው ወሬዎች፣ የገባናቸው ቃል ኪዳኖች ወይም የምንሰጣቸው ማብራሪያዎች አይደሉም።

ሰዎች የተናገርነውን ሊረሱት ወይም በሐሳባችን ላይ ጥርጣሬ ሊያድርባቸው ይችላል፤ ነገር ግን አንድን ነገር ጀምረን ስንጨርሰው እናን ከማመን ውጪ ምንም ምርጫ እንዳይኖራቸው ያደርጋል።

·       ታማኝ ነኝ እያልን፣ ግን የምንዋሽ ከሆነ፣ ሰዎች የሚያምኑት ድርጊታችንን እንጂ የምንናገረውን አይደለም።

·       ጎበዝ ሰራተኛ ነኝ እያልን፣ ግን ኃላፊነትን የምንሸሽ ከሆነ፣ ቃላቶቻችን ዋጋ ያጣሉ።

ዘወትር ጨዋትን፣ ሥርዓትን እና ታማኝነትን የምናሳይ ከሆነ፣ ሰዎች በእኛ መተማመን ምንም ሌላ ማብራሪያ አይፈልጉም።

በመሪነት ቦታ ላይም ቢሆን ሰዎች በቃላት ከምንሰጠው መመሪያ ይልቅ ዘወትር በተግባር የምናሳያቸውን ነገር ይከተላሉ።

ወጥነት (ተመሳሳይ ትክክለኛ ድርጊትን ማዘውተር) ተዓማኒነትን ይፈጥራል። የአንድ ጊዜ መልካም ተግባር ሰዎች አድንቀውት ያልፋሉ፡፡

በሰዎቹ ላይ ዘላቂ ተጽእኖ የሚያመጣው ግን ደጋግመን የምናደርጋቸው ነገሮች ናቸው።

በዛሬዋ ቀን፡- ሰዎችን በቃላችን ለማሳመን ከመሞከር ይልቅ፣ የምናምንባቸውን እሴቶች መኖርን፣ የተናገርናቸውን ነገሮች መፈጸምንና ወጥ የሆነ ማንነትን ማሳየትን እንለማመድ፡፡

ይህንን ካደረግን በጊዜ ሂደት፣ ተግባሮቻችን ከማንኛውም ንግግራችን በላይ ጮክ ብሎ መናገር ስሚጀምር ተጽእኗችን እየሰፋ ይሄዳል።

ምንጭ :ዶ/ር ኢዮብ
📌አሁኑኑ ይ🀄🀄ሉን
በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን
🎯🎯🎯🎯🎯🎯

🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን
SUBSCRIBE ያድርጉ

ዩቱዩብ:
https://www.youtube.com/@Asfaww

ቲክቶክ:
https://tiktok.com/@asfaw_motivation
ፌስቡክ:  https://www.facebook.com/attitudease

ቴሌግራም: 
https://t.me/Attitudeplc


  ለግል ለአስተያየትዎ:
https://t.me/LYDAse1

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
ልባችሁን ተከተሉ!

የሁለት ሃሳብ ግጪት መሃል ብትሆኑ፣ ግራመጋባት ፋታ ቢነሳችሁ፣ ምርጫ ቢበዛባችሁ፣ ከዚህም ከዛም ጫናዎች ቢያይሉባችሁ፣ ወደህም ወዲያም ለመሔድ ብትቸገሩ፣ በጭንቀትና ስጋት ካላችሁበት ስፍራ መንቀሳቀስ ቢሳናችሁ ምንም ከማድረጋችሁ በፊት ቆም ብላችሁ ውስጣችሁን አዳምጡ፣ ልባችሁ የሚመራችሁን አቅጣጫ ተመልከቱ፣ ከስሜታችሁ በላይ ሚዛናዊው አዕምሯችሁ ወዳዘነበለበት አዘንብሉ። በህይወት መንገድ ግራ መጋባት፣ አጣብቂኝ መሃል መውደቅ፣ ከቀረቡት አማራጮች የተሻለውን ለመምረጥ መቸገር ያለና ወደፊትም የሚኖር ነው። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥ ልባችንን ማዳመጥ የተሻለውን አማራጭ ያቀርብልናል። ሃሳብ ሁሌም አለ፣ ስሜት ዘወትር ይቀያየራል፣ ማንም ይጨነቃል፣ ያወጣል ያወርዳል መጨረሻው ግን ከሁለት አንዱ ነው። ወይም አንዱን  ይወስናል ወይም ከሁሉም አማራጮች ሳይሆን ይቀራል። 

አዎ! ጀግናዬ..! በስሜትህ እየተገዛህና የውስጥ ፍላጎታህን እያዳፈንክ የምትጓዝ ከሆነ፣ ለውጫዊ ጫናዎች እራስህን አሳልፈህ ከሰጠህ፣ ለጊዜያዊ ጥቅም ቅድሚያ ከሰጠህ የአጣብቂኝ ብዛት፣ የሃሳብ ዥረት፣ የጭንቀት መዓትና የግራመጋባት አባዜ ሊለቅህ አይችልም። በስሜታዊነት ከምትፈታው ችግር በላይ የምትፈጥረው ችግር ይበዛል፣ የልብ መሻትህን ወደጎን እያልክ በውጫዊ ተፅዕኖ ብትመራ ትክክል ከምትሆነው በላይ የምትሳሳተው መንገድ ይበዛል። እራስን ማወቅ ከጫናዎች ነፃ ያወጣሃል፣ እራስህን ባወከው ልክም በተግባር ሚዛናዊና የልብ መሻትን ያማከለ ውሳኔ መወሰን ለተሻለው ምርጫ ያበቃሃል። በህይወትህ ውስጥ ያለውን ምርጫ የተባለውን ትልቁን የእግዚአብሔርን ስጦታ በጥንቃቄ ተጠቀም።

አዎ! ልባችሁን ተከተሉ፣ ውስጣችሁን አዳምጡ፣ ከስሜታችሁ በላይ ሚዛናዊው የአዕምሮ ሃሳባችሁ ላይ አተኩሩ፣ ለጭንቀትና ለፍረሃት ከሚዳርጓችሁ አማራጮች በላይ ምንም እንኳን የተለየ ዋጋ ቢያስከፍሏችሁም ውስጣዊ ሰላማችሁን የሚያረጋግጡና የሚያረጋጓችሁን አማራጮች ምረጡ። ከምንም በላይ የውስጥ ፍላጎታችሁን አስቀድሙ፣ ከማንም ተፅዕኖ በላይ እራሳችሁን አዳምጡ። ማንም ቢወስንላችሁ ሃላፊነቱን አይወስድላችሁም፣ ማንም ቢመርጥላችሁ ምርጫውን አስታኮ ለሚመጣው አደጋ እራሱን አሳልፎ አይሰጥላችሁም። አጣብቂኝ ውስጥ ብትገቡ፣ ግራ ቢገባችሁ፣ ለውሳኔ ብትቸገሩ ተረጋጉ፣ ከማንም በላይ እራሳችሁን ለማወቅ ሞክሩ፣  ውስጣችሁን አዳምጡ፣ ፍላጎታችሁን በጥልቀት መርምሩ፣ ለልብ መሻታችሁ ቅድሚያ ስጡ፣ በጥበብ በማስተዋል ህይወታችሁን ምሩ፣ ሰላማዊና አስደሳች ህይወትንም ኑሩ።

📌አሁኑኑ ይ🀄🀄ሉን
በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን
🎯🎯🎯🎯🎯🎯

🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን
SUBSCRIBE ያድርጉ

ዩቱዩብ:
https://www.youtube.com/@Asfaww

ቲክቶክ:
https://tiktok.com/@asfaw_motivation
ፌስቡክ:  https://www.facebook.com/attitudease

ቴሌግራም: 
https://t.me/Attitudeplc


  ለግል ለአስተያየትዎ:
https://t.me/LYDAse1

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
. . . አንድ ወጣት ወታደር ነው አሉ። ብዙ ስኬቶችን ወደ አስመዘገቡ ጄኔራል ዘንድ ሄዶ ስለሕይወት ልምዳቸው እንዲነግሩት ይጠይቃቸዋል። «አለቃዬ! ለመሆኑ የስኬትዎ ምስጢር ምንድነው?»

የጄኔራሉ ቤት በብዙ ኒሻኖችና ሽልማቶች የተንቆጠቆጠ ነው። ወታደሩ የጄኔራሉን ሽልማቶች አይቶ እየቋመጠ «እኔም እንደርስዎ ስኬታማ ለመሆን እፈልጋለሁ፤ እባክዎ ይምከሩኝ?» ይላቸዋል። ይኽን ጊዜ ጄኔራሉ ወጣቱን ወታደር ለሦስት ደቂቃ ያህል አተኩረው ካዩት በኋላ አንድ ትዕዛዝ ይሰጡታል። ትዕዛዙ ላይ ላዩን ሲታይ ቀላል የሚመስል፣ ነገር ግን ሕይወቱን ሊያሳጣ የሚችል ትዕዛዝ ነበር።

በውኃ የተሞላ አንድ ብርጭቆ አንስተው ከሰጡት በኋላ፤ በአገጫቸው ከቤቱ በቅርብ ርቀት ወደሚገኝ የወታደር ማሰልጠኛ እየጠቆሙ፤ «ሂድና ያንን የማሰልጠኛ ሜዳ አምስት ዙር ዞረህ ተመለስ። ታዲያ ከዚህ ብርጭቆ ላይ ጠብታ ውኃ መፍሰስ የለበትም፤ 'ስናይፐር' ይዞ የሚከታተልህ ወታደር እመድባለሁ፤ ከብርጭቆው ውኃ ሲፈስ ከተመለከተህ ይተኩስብሃል።» አሉት።

ለወጣቱ ያልጠበቀው ዱብ ዕዳ ነበር...። በተሰጠው ትዕዛዝ ተደናግጦ አንዴ ብርጭቆውን፤ አንዴ ጄኔራሉን ሲመለከት ቆየና እየፈራም ቢሆን የሞት ሞቱን ተነሳ፤ ትዕዛዙን ሊፈፅም። ዓይኑን ከብርጭቆው ላይ ሳይነቅል በጥንቃቄ እየተራመደ እንደምንም ማሰልጠኛው ደረሰ።

ከዚያም ቀስ በቀስ አንድ ዙር፤ ሁለት ዙር ሦስት ዙር፤ ሲሄድ መንገዱ እየቀለለው መጣ። በዚህ መልኩ ቀጣዮቹን ዙሮች በደንብ ራመድ እያለ፤ ፍጥነቱን እየጨመረ ሄዶ አንዲት ጠብታ መሬት ሳትነካ ዙሩን ጨርሶ ጄኔራሉ ዘንድ ደረሰ። ልክ እንደደረሰ የጄኔራሉ ጥያቄ ቀጠለ.......፤

«ለመሆኑ እነዚያን ቆነጃጅት ኮረዶች ራቁታቸውን ሲደንሱ አይተሃቸዋል?» አሉት።

«አላየኋቸውም ጌታዬ» ሲል ወጣቱ መለሰ።

«ከማሰልጠኛው አጠገብ ያሉትንስ ስፖርተኞች ሲደባደቡ አላየሃቸውም?»

«አዎ ጌታዬ አላየኋቸውም!»

«ከዚያ ከዓሳ ቤቱ የሚወጣው የዓሳ ጥብስስ አልሸተተህም?»

«እንዲያውም ... አልሸተተኝም!»

. . . ይሄን ጊዜ ጄኔራሉ ወጣቱን ለአፍታ ትክ ብለው ከተመለከቱት በኋላ፤ «አየህ! ዓላማህ ላይ ስታተኩር ስኬታማ ትሆናለህ፤ ሕይወትህንም በከንቱ አታጣም። አሁን ምክሬን ጨርሻለሁ፤ መሄድ ትችላለህ።» ብለው አሰናበቱት።
..............................
ጠሚ ዐ.አ


መልእክቱን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎች ይማሩበት ዘንድ #share ማድረግን አትርሱ!
--------------------------

📌አሁኑኑ ይ🀄🀄ሉን
በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን
🎯🎯🎯🎯🎯🎯

🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን
SUBSCRIBE ያድርጉ

ዩቱዩብ:
https://www.youtube.com/@Asfaww

ቲክቶክ:
https://tiktok.com/@asfaw_motivation
ፌስቡክ:  https://www.facebook.com/attitudease

ቴሌግራም: 
https://t.me/Attitudeplc


  ለግል ለአስተያየትዎ:
https://t.me/LYDAse1

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🦅 የሁለቱ ንስሮች ታሪክ እና የአስተሳሰብ እስራት!

አንድ ንጉሥ በስጦታ መልክ ሁለት በጣም የሚያምሩ የንስር ግልገሎችን ያገኛል። ንጉሡም ንስሮቹን አሰልጥኖ ትልቅ ደረጃ እንዲያደርሳቸው ለአንድ ባለሙያ ይሰጣል።
ከጥቂት ወራት በኋላ አሰልጣኙ ወደ ንጉሡ መጥቶ እንዲህ ይላል፦ "ንጉሥ ሆይ! አንደኛው ንስር በከፍታ ላይ እየበረረ ሰማዩን እያደመቀው ነው። ሁለተኛው ንስር ግን ከመጣበት ቀን ጀምሮ ከተቀመጠባት የዛፍ ቅርንጫፍ ላይ ፍንክች ሊል አልቻለም። ለመብረር ፈጽሞ ፈቃደኛ አይደለም።"

ንጉሡም በሀገሪቱ ያሉትን ጠቢባን ሁሉ ጠርቶ ንስሩን እንዲያበሩት ቢያዝም ማንም ሊያስነሳው አልቻለም። በመጨረሻም አንድ ቀላል አርሶ አደር መጥቶ ንስሩን በአንድ ጀምበር ሰማይ ላይ እንዲበድር አደረገው!
ንጉሡ ተገርሞ አርሶ አደሩን ጠየቀው፦ "እንዴት ይሄንን ተአምር ልታደርግ ቻልክ?"
አርሶ አደሩም ፈገግ ብሎ፦ "በጣም ቀላል ነው ንጉሥ ሆይ! ንስሩ ተጣብቆባት የነበረችውን እና መብረር እንዳይችል የያዘችውን የዛፍ ቅርንጫፍ ቆረጥኳት። ከዚያም የሚይዘው ሲያጣ ክንፎቹን ዘርግቶ መብረር ጀመረ" አለው።

📌 ወዳጄ ሆይ!
አብዛኞቻችን ልክ እንደዚሁ ንስር ነን። በውስጣችን ትልቅ የመበልጸግ፣ የመለወጥ እና የፋይናንስ ነጻነት የማግኘት እምቅ አቅም (Potential) አለን። ነገር ግን አዲስ ነገር ለመጀመር ካለን ፍርሃት የተነሳ "ደሞዝ" የምትባለውን ወይም "የለመድነውን አሮጌ የኑሮ ክበብ" የምትባለውን የዛፍ ቅርንጫፍ አጥብቀን ይዘናል።

ፍርሃትን ሰብረህ ቅርንጫፏን ካልቆረጥክ በውስጥህ ያለውን ታላቅ የመብረር አቅም ፈጽሞ አታውቀውም!
ጸጥታ እና እርጋታ

በአንድ ገጠራማ አካባቢ ማያ የሚባሉ በጣም የረቀቀ አዕምሮ ያላቸው ሽማግሌ አባት ይኖሩ ነበር። በአንድ ወቅት ይኖሩበት የነበረው አካባቢ በከባድ ድርቅ፣ ጎርፍ እና በብዙ ማህበራዊ ውጣ ውረዶች ይታወቅ ነበር። ነገር ግን ማያ ምን ጊዜም በጸጥታ እና በእርጋታ የተሞላ ሕይወት ይኖሩ ነበር።

አንድ ቀን አንድ ወጣት በእጅጉ ተጨንቆ ወደ እሳቸው መጣና እንዲህ አላቸው

"አባቴ አገራችን በችግር ተመታለች አየሩ ይከብዳል፣ ሰዎች ይለወጣሉ፣ ነገ የሚሆነውን አናውቅም። በዚህ ሁሉ አለመረጋጋት ውስጥ እንዴት እንዲህ ሊረጋጉ ቻሉ ?  እኔስ እንዴት ተራጋግቼ ልኑር ? ልቤ በጭንቀት ተወጥሯል አላቸው፡፡

ማያ አጭር ፈገግታ አሳዩና ወጣቱን ይዘው ወደ ግዙፍ ተራራ እና ወደ አንድ የውሃ ወንዝ ወሰዱት።

ከዚያም አንድ ከባድ ድንጋይ አንስተው  ወንዙ ውስጥ ወረወሩት።  ድንጋዩ ገብቶ ውሃው ተረጨ፣ ሞገዱም ተነሳ፤ ነገር ግን ተራራው ግን ምንም ሳይንቀሳቀስ ባለበት ጸንቶ ቆመ።

ሽማግሌውም ወጣቱን እንዲህ አሉት፦

ልጄ ይህ ወንዝ መቀየር የማይችሉት ነገሮች ምሳሌ ነው። የሰውን ሐሳብ፣ የአየር ሁኔታውን፣ የጊዜን መለዋወጥ እና የውጭ ዓለምን ሁኔታዎችን መቆጣጠር አንችልም።
እነሱ ልክ እንደ ወንዙ ሁልጊዜ ይፈሳሉ፣ ይለዋወጣሉ፣ አንዳንድ ጊዜም አውሎ ነፋስ ይሆናሉ።

ይህ ተራራ ደግሞ የእኛ ውስጣዊ ልብ እና አዕምሮ ምሳሌ ነው። ውጭ የሚሆነውን ነገር ማቆም አንችልም ነገር ግን በውስጣችን ያለውን የሰውን ማንነት እና ጽናት መምረጥ እንችላለን።

ማያ አክለውም “ሰዎች ብዙ ጊዜ ኃይላቸውን የሚያባክኑት የማይለወጡትን ነገሮች ለመለወጥ በመጣላት ነው። ሰንሰለቱን ለመስበር ትሞክራለህ እንጂ ሰንሰለቱ የታሰረብህን እጅ መቆጣጠር ትረሳለህ”

ጥበብ ማለት ሊለወጡ የሚችሉትን ነገሮች የመለወጥ ኃይል  የማይለወጡትን ደግሞ በጸጋ የመቀበል ልብ እና ሁለቱን መለየት የሚችል ማስተዋል መኖር ነው አሉት፡፡

✍️ዮናስ

📌አሁኑኑ ይ🀄🀄ሉን
በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን
🎯🎯🎯🎯🎯🎯

🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን
SUBSCRIBE ያድርጉ

ዩቱዩብ:
https://www.youtube.com/@Asfaww

ቲክቶክ:
https://tiktok.com/@asfaw_motivation
ፌስቡክ:  https://www.facebook.com/attitudease

ቴሌግራም: 
https://t.me/Attitudeplc


  ለግል ለአስተያየትዎ:
https://t.me/LYDAse1

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
"ዕድል ማለት ዝግጅትና አጋጣሚ ሲገናኙ የሚፈጠር ነው። እውነተኛ አሸናፊዎች ዕድልን ሳይሆን ዝግጅታቸውን ያጠናክራሉ።"ሴኔካ

"በህይወት ውስጥ የሚደርስብንን ነገር ሁሉ መቆጣጠር አንችልም፤ ነገር ግን በእነሱ ላይ ላለመሸነፍ መወሰን እንችላለን።"ማያ አንጄሉ

አሸናፊነት መዳረሻ ብቻ ሳይሆን፣ በየዕለቱ የሚደረግ የትጋትና የዲሲፕሊን ጉዞ ነው።✍🏻

"አሸናፊነት ማለት በሂደቱ መደሰት እና የመጨረሻውን ግብ እስኪመቱ ድረስ እጅ አለመስጠት ነው።" — ቦብ ፕሮክተር
ጥቂት ነጥቦች ስለ አልኬሚ

የረቂቁ አልኬሚ ፍልስፍና መስራች ስሙ ሐርሜስ ትሪስሜጊስተስ (Hermes Trismegistus) ይባላል፡፡ እግዚአብሔራዊ አረዳዳችን ላይ ከቀኖና የተሻገረ ረቂቅ አምልኮአዊ ፍልስፍና ካረቀቁ ሰዎች ቀዳሚው እሱ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ግብጻዊ ቢሆንም ግሪካዊያን የሚጠቀሙባቸውን 42 የሚደርሱ መጻሕፍት የጻፋቸው እርሱ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ሰውዬው ፍጹም የላቀ ሰው ነበር፡፡

የሳይንስ፣ የሐይማኖታዊ ዕሳቤዎች፣ ሒሳብ፣ ጂኦሜትሪ፣ አልኬሚ፣ ሕክምና፣ ፍልስፍና እና አስማት የመሣሠሉ ጥበባት ሁሉ መስራች መሆኑ ይነገርለታል፡፡ ሙሴ በእስራኤል ታሪክ ታላቁ ነብይ ሆኖ እስራኤላዊያንን ከአራት መቶ ዘመናት አገዛዝ ቀንበር ነጻ ከማውጣቱ በፊት ከኢትዮጵያዊው ዮቶር ሌላ በዚሁ ጥቁር ግብጻዊ ሐርሜስ ትሪስሜጊስተስ ክትትል እና አስተምህሮ ስር እንዳደገ የሚነገር ታሪክ አለ፡፡

በሌላ በኩል በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አቆጣጠር፣ ከአዳም ስደት በኋላ ከጥፋት ውኃ  በፊት በግብጽ እንደኖረ የሚተረክም ሌላ የታሪክ ፈርጅ አለ፡፡ አንዳንዶች ትሪስሜጊስተስ  ከጥፋት ውኃ በፊት የኖረው የመጽሐፍ ቅዱሱ ሔኖክ (የቅዱስ ቁርዓኑ እድሪስ) ነው ይላሉ፡፡ ሌሎች በአንጻሩ ሔርሜስ ትሪስሜጊስተለ ፈጠራ የሆነ፣ ስያሜው ራሱ ከግሪኩ የጣዖት አምላክ ሔርሜስ እና ከግብጹ ቶት ተዳቀሎ የተገኘ ፍጹም ምናብ ወለድ ሰው ስለመሆኑ ይከራከራሉ፡፡ የዚህ ታላቅ ሰው ማንነት ላይ ዛሬም ድረስ ስምምነት የለም፡፡

የአልኬሚ ግርድፍ ጽንሰ ሀሳብ ይሄው ነው፡፡ ብረትን ሁሉ ወደ ወርቅ ምትቀይረውን ፈሳሽ መፈለግ፣ ዘለዓለማዊ ወጣት ለመሆን የምታስችለውን እጽ ማሰስ፡፡ ከኢየሱስ መወለድ በፊት ለሺህ ዘመናት የተፈራረቁት አልኬሚስቶች የሞትን መድኃኒት፣ ወይ ብረትን ሁሉ ወደ ወርቅ የምትቀይረውን ተዓምረኛ ድንጋይ ይፈልጉ ዘንድ ቃተቱ፡፡ ከእርሱ በፊት የፈለቁት የመጀመሪያዎቹ የአልኬሚ ጠቢባን ሁሉም ጽድቁም፣ ኩነኔውም፣ ጋኔሉም ያለው ውስጣችን መሆኑን ያወቁት አይመስልም፡፡

በኋለኛው ዘመን ብቅ ያሉ ክርስቲያናዊ የአልኬሚ ጠበብት እነ ሜይስተር ኤክሃርት ደግሞ መዳን ረቂቅ የአልኬሚ ሽግግር መሆኑን በተግባር ያሳየው ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ሰበኩ፡፡ እንደ እነዚሁ ክርስቲያናዊ ሚስቲኮች አስተምህሮ ፍጽምናውን መቀዳጀት የሚቻልበትን እውነተኛ መንገድ የቀየሰ መሲሁ ብቻ ነው፡፡

በእርግጥም እንደመጽሐፍ ቅዱስ ትረካዎች ኢየሱስ ራሱ አልኬሚስት ነበር፡፡ ከእናቱ ጋር በቃና ዘገሊላ በታደመበት ሰርግ ለሰርገኛው የሚቀርብ ወይን በተሟጠጠ ጊዜ ውኃውን ወደ ወይን ቀይሯል፡፡ በሌላ ጊዜ ጥቂት ቁራሽ ዳቦዎችንና ጥቂት ዓሶችን በበረከት አባዝቶ ሺዎችን መግቧል፡፡ አሁንም እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትረካዎች ሽባዎችን፣ ድውያንን ፈውሷል፡፡ ይህ ለሺህ ዘመናት የተንከራተቱ አልኬሚስቶች ሁሉ ምኞት ነበር፡፡ ብረትን ወደ ወርቅ፣ ውኃን ወደ ወይን፣ ሞትን ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት መቀየር..

ከኢየሱስ መወለድ በኋላ በመካለኛው ዘመን በተለይ በአውሮፓ የነበሩ የአልኬሚ ጠበብት ሞትን ድል የምታደርገውን ዕጽ ሀሰሳውን እርግፍ አድርገው ትተው የክርስቶስን አብነት ተከተሉ፡፡ ለእነርሱ ብረት የሆነ ሀጥያትን ሁሉ ወደ ወርቅ የሆነ ጽድቅ የሚቀይረው መንገድ እርሱ እንደሆነ አመኑ፡፡

እኛ ግን እንጠይቅ! ኢየሱስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዳይካተቱ ከተገፈተሩት መጻሕፍት አንዱ በሆነው የቶማስ ወንጌል ላይ "በውስጣችሁ ያለውን እሱን ካወጣችሁት ያድናችኋል፡፡ በውስጣችሁ ያለውን ያንን ማውጣት ካልቻላችሁ ግን መጥፊያችሁ ይሆናል፡፡"ሲለን ምን ማለቱ ነበር? (When you bring forth that within you, then that will save you. If you do not, then that will kill you.) በውስጣችን ያለው ያ ስናሰለጥነው ሊያድነን፣ ልናወጣው ባንችል ግን ሊገድለን የሚችል እርሱ ምንድን ነው?

ይህ ኃይለቃሉ በራሳችን እና በዙሪያችን የከበበን የነተበ ፈሪሳዊ ዓለም ላይ እንድናምጽ እያተጋን አልነበረምን? የራሳችን መስቀል ተሸክመን ወደ ራሳችን ቀራኒዮ እንድንዘምት፣ ልክ እንደተጋዳሊ (Hero) ከራስ ለሚልቅ ዓላማ እንድንሰለፍ እያነቃን? ዋሻ ውስጥ ተጋድሞ የጸሐይቷን መውጣት ሲጠብቅ እንቅልፍ ጥሎት ዘመናት እንደሚፈራረቁበት፣ ሳር እንደሚበቅልበት ዘንዶ በውስጣችን ያንቀላፋውን ያንን ስናነቃው፣ ስናሰለጠነው ሊያጀግነን የሚችል ደራጎን ማስደንበር እንችል ዘንድ እያተጋን?

ደራገን (Dragon - Serpent) ከአልኬሚ ጽንሰ ሐሳብ ጋር ተያይዞ የሚነሳ እሳት እንደሚተፋ፣ በክንፍ እንደሚበር የሚታሰብ የእባብ ዝርያ ነው፡፡ ነገርግን ደራጎኖች የሰው ልጅ ስነልቦናን እንደጥናት ዘርፍ ከመመስረቱ ሺህ ዘመናት በፊት ለጭቁኑ አእምሮው (shadow) መገለጫ ይሆኑት ዘንድ የፈጠራቸው ምናባዊ መመሰያዎች እንጂ በሕልውና የነበሩ ፍጥረታት እንዳልሆኑ ይታመናል፡፡

ደራጎኖች ውስጣችን የታመቀው ስናነቃው፣ ስናሰለጥነው ሊያመጥቀን ሊያስፈነጥረን የሚችል ንጹህ ንቁ ኃይል አመልካቾች ናቸው፡፡ ደራጎኖች ከመገራታቸው ከመታረቃቸው በፊት ስግብግቡን አ
እኔነት (ego) ይሸከማሉ፡፡ ደራጎኖች መጀመሪያ ከሸለብታቸው ሲቀሰቀሱ አፍራሽ፣ አደፍራሽ ናቸው፡፡ ከተገሩ በኋላ ግን የነቃውን አነ (divinity) ይመስሉታል፡፡ ሽግግሩ ዘመናትን ሊወስድ በአብዛኛው ላይቋጭም ቢችልም ቅሉ..

የደራጎኑ ጌታ ገበሬም ይሁን ሐያሲ የደራጎኑን ቁጣ ማስከን መግራቱን እስኪሰለጥንበት ሁሉንም ማተረማመሱ፣ ማፈራረሱ አይቀርም፡፡ ይህ በድራጎን የተመሰለ እምቅ ኃይል በሁላችንም ውስጥ ይገኛል፡፡ የሰው ልጅ አካል ከአፈር፣ ከአየር፣ መሬት እና እሳት ኃይለ ባህሪያት (form of energies) ተሰራ ብለናል፡፡ ደራጎኖች በአካል ላይ የሚሰለጡኑ ገዥ ኃይላት እንደመሆናቸው አካል የተሰራንባቸውን አራት ባህሪያት (ውኃ፣ እሳት፣ መሬት፣ አየር)
ይወርሳሉ፡፡

በዚህም አግባብ በሰው ልጆች እዝነ ልቦና ውስጥ አራት ዓይነት የድራገን ኃይለ ስሪቶች ይኖራሉ፡፡ ሆኖም ምንጊዜም አንደኛው ኃይለ ስሪት ገዥ (dominant) ሆኖ መውጣቱ ግዴታ ይሆናል፡፡ ገዥውን ስነ ባህሪይ ለይቶ ማወቅ ብሎም ማሰልጠን ደግሞ የተተስካከለ ስብዕና የላቀ ኃይል ያላብሳል፡፡

📖ብርሀን ጨልጦ መስከር
ደራሲ-ያዕቆብ ብርሀኑ

📌አሁኑኑ ይ🀄🀄ሉን
በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን
🎯🎯🎯🎯🎯🎯

🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን
SUBSCRIBE ያድርጉ

ዩቱዩብ:
https://www.youtube.com/@Asfaww

ቲክቶክ:
https://tiktok.com/@asfaw_motivation
ፌስቡክ:  https://www.facebook.com/attitudease

ቴሌግራም: 
https://t.me/Attitudeplc


  ለግል ለአስተያየትዎ:
https://t.me/LYDAse1

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
ሁሉም ይቀናብሃል!

አንድን ሰው የተራራው ጫፍ ላይ ብንመለከተው ሁሉም ሰው የሚቀናው የተራራው ጫፍ ላይ በመውጣቱ እንጂ በአወጣጡ አይደለም። እንዴት እዛ ይድረስ? ምንያህል ቀን ይፍጅበት? ስንቴ ወደቀ? ስንቴ ተነሳ? የማንም ጉዳይ አይደለም። ሰው የሚቀናው አስቀድማችሁ ባለፋችሁት ስቃይ ሳይሆን በስተመጨረሻ በምትጎናፀፉት ድል ነው። ብዙ ሰው ደስታችሁን ይመኛል ነገር ግን ከዛ በፊት ምንያህል ጨለማ ጊዜ እንዳሳለፋችሁ ማወቅም አይፈልግም፤ ብዙ ሰው ስኬታችሁን ይናፍቃል ነገር ግን ስኬታማ ለመሆን ያደረጋችሁት ከባድ ነገር ለማድረግ ፍቃደኛ አይደለም። ህይወት በምኞት ብቻ የምትሳካ አይደለችም። ሁሉም በየደረጃው ስራ ይፈልጋል። ህልምን ሲተኙ ብቻ መመልከትና ቆሞ የስኬታማ ሰዎችን ህይወት መመኘት አንድ ናቸው። ሁለቱም በምናብ ወደምንፈልገው ስፍራ ይወስዱን ይሆናል እንጂ በፍፁም በተጨባጭ እዛ አያደርሱንም። ዓለም የህልመኛ እጥረት የለባትም፣ ምድር የባለራዕይ ችግር የለባትም። ዋናው ችግሯ ህልሙን ለማሳካት መሱዓትነት የሚከፍል ሰው ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ሁሉም ይቀናብሃል! ትንሹም ትልቁም፣ አዋቂውም አላዋቂውም፣ ሰነፉም ብርቱውም አንተ የደረስክበትን ከፍታ ይመኘዋል። ነገር ግን ምኞት ብቻውን ግን ያንተ ስፍራ እንደማያደርሳቸው አልተረዱም። ብዙ ምርጫ ነበረህ ነገር ግን ስኬትን ብቻ መርጠሃል፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ጀምሮ ማቆም፣ ሌላ ነገር መሞከር ትችል ነበር ነገር ግን አላደረከውም። ህልምህን ከደምህ ጋር አስተሳስረሀዋል፣ ውስጥህን በማይበገር ፅኑ ማንነት አንፀሀዋል፣ መንፈስህን እስከ ጥግ አጠንክረሀዋል። ይህን ሁሉ ማደረግ የሚችል ያንተ ቦታ አይደለም አንተ ካለህበት ቦታ የሚበልጥ ቦታ መድረስ ይችላል። የትኛውም የሚያስቀና ህይወት የሚያስቀናው መጨረሻው እንጂ መጀመሪያው አይደለም። ተቀምጦ መመኘት ተነስቶ እንደመስራት ከባድ አይደለምና ብዙዎች ይመኛሉ ጥቂቶች ብዙዎች የሚመኙትን ህይወት ይኖራሉ። አንድ ጠጠር እንኳን ሳይጥሉ የተሳካ ህይወት ለመኖር መሞከር ከንቱ የሀሳብ ድካም ነው።

አዎ! አሸናፊዎች ሁሌም ያሸንፋሉ፤ ተሸናፊዎች ሁሌም ይሸነፋሉ። ከዚህ የተለየ ህግ የለም። ማሸነፍ እንደምትችል ከልብህ አምነሃል፣ ለአሸናፊነት የሚያበቃህን ስራ ሰርተሃል፣ መክፈል ያለብህን ዋጋ ከፍለሃል፣ የሚገባህን አሸናፊነት በእጅህ አስገብተሃል። ተሸናፊውም ሽንፈትን መርጧል፣ በቀላሉ ተስፋ ለመቅረት ወስኗል፣ ጀምሮ ማቆምን እጣፋንታው አድርጎታል። ከአዕምሮው ስሜቱ በልጦበታል፣ ከዘላቂው ስኬት ጊዜያው ደስታ ሚዛን ደፍቶበታል፣ ከአላማው ወቅታዊው አጀንዳ ስሜት ሰጥቶታል፣ በእቅድ ሳይሆን በስሜት ይጓዛል፣ ብዙ ይመለከታል ብዙ ያውቃል ነገር ግን ሚዛናዊ ውሳኔ መወሰን አይችልም። ይሔ ሰው አሸናፊነት ከባህር ማዶ እንዳለች ደሴት ርቆታል፣ ምኞት እንጂ እውነታው ሊሆንለት አይችልም። ህይወት ምርጫ ነች ሲባል ቀላል ምርጫ እንዳልሆነች መረዳት ያስፈልጋል። ሰው አዝኖልህ እንዲረዳህ ከፈለክ ምርጫው ያንተ ነው፤ በስራህ ተደስቶም እንዲሸልምህ ከፈለክ ምርጫው ያንተ ነው። "ምንም የለኝም፣ ምን ላድርግ? ሰው የለኝም፣ እንዴት ብቻዬን ልስራ?" ካልክ አሁንም ምርጫህ ነው። "ባለኝ ጀምሬ ላሳይ፣ ብቻዬን የምችለውን አድርጌ ውጤቱን ልመልከት" ካልክም ምርጫው ያንተ ነው። አሸናፊነትን እስከመረጥክ ድረስ ስሜትህን ጥለህ በማይናወጠው አቋምህ እንደምትመራ አስታውስ።

📌አሁኑኑ ይ🀄🀄ሉን
በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን
🎯🎯🎯🎯🎯🎯

🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን
SUBSCRIBE ያድርጉ

ዩቱዩብ:
https://www.youtube.com/@Asfaww

ቲክቶክ:
https://tiktok.com/@asfaw_motivation
ፌስቡክ:  https://www.facebook.com/attitudease

ቴሌግራም: 
https://t.me/Attitudeplc


  ለግል ለአስተያየትዎ:
https://t.me/LYDAse1

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
እራስህን ለመገምገም 5 Questions (Mid-Week Reflection)
ዛሬ ማክሰኞ ነው! የሳምንቱ አጋማሽ ላይ ከመድረሳችን በፊት እነዚህን 5 ጥያቄዎች ለራስህ ሳትዋሽ መልስ!

አብዛኛው ሰው ሳምንቱን ሙሉ በልማድ ይሮጣል ነገር ግን የት እየደረሰ እንደሆነ ቆሞ አይገመግምም። እድገት የሚጀምረው እራስን በግልጽነት በመገምገም ነው።

የጀመርከውን ሳምንት ስኬታማ ለማድረግ ዛሬ ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ እነዚህን 5 ጥያቄዎች ደብተርህ ላይ ጽፈህ መልሳቸው፦
1️⃣ በእነዚህ ጥቂት ቀናት ውስጥ ከግቤ ጋር የሚያገናኘኝ ምን አዲስ እርምጃ ወሰድኩ?
2️⃣ እስከ ዛሬ ሰዓት ድረስ ጊዜዬን በይበልጥ ያባከነው ወይም ትኩረቴን የሰረቀው ነገር ምንድን ነው?
3️⃣ በዚህ ሳምንት ለፍርሃቴ ወይም ለስነፍዝግናዬ የሰጠሁት ትልቁ ሰበብ ምን ነበር?
4️⃣ ከቀናት ውድቀቴ ወይም ስህተቴ የተማርኩት ትልቁ ትምህርት ምንድን ነው?
5️⃣ የሳምንቱ ቀሪ ቀናት የተሻሉ እንዲሆኑ ከዛሬ ጀምሮ ማድረግ ያለብኝ 1 ዋና ነገር ምንድን ነው?

እራስህን በየቀኑ እና በየሳምንቱ አጋማሽ በገመገምክ ቁጥር በሕይወትህ እና በሥራህ ላይ ሙሉ ቁጥጥር ታገኛለህ።

👉 ይህንን የራሳቸውን እድገት መገምገም ለሚፈልጉ እና ስኬታማ እንዲሆኑ ለምትመኛቸው 5 ሰዎች Share አድርግላቸው! 🚀
የሕይወት ታሪክ፦ ከዕለታት አንድ ቀን በትንሽ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ አዛውንት ነበረ። አዛውንቱ በሕይወታቸው ውስጥ ብዙ አስቸጋሪ ጊዜያትን አሳልፈዋል። ነገር ግን ሁልጊዜ በፊታቸው ላይ ፈገግታ አይጠፋም ነበር።
አንድ ቀን የ መንደሩ ወጣቶች "አያቴ፣ በሕይወትዎ ውስጥ ያጋጠመዎት ሁሉ አስቸጋሪ ሆኖ ሳለ እንዴት ሁልጊዜ ሰላማዊና ደስተኛ መሆንቻሉ?" ብለው ጠየቋቸው።
አዛውንቱም ፈገግ ብለው እንዲህ አሉ፦ "ሕይወት እንደ ወንዝ ፍሰት ናት፤ ድንጋዮችና እንቅፋቶች ያጋጥሟታል። ነገር ግን ወንዙ ጉዞውን አያቆምም። እኔም የተማርኩት ነገር ቢኖር ያለፈውን ማዘን ወይም ስለ ነገ ከልክ በላይ መጨነቅ ሰላማችንን እንደሚወስድብን ነው። በየቀኑ የሚሰጠንን አዲስ ቀን በጥሩ መንፈስ መቀበልና ለሌሎች በጎ ማድረግ የሕይወት ትልቁ ምስጢር ነው
#አሁንም_አልረፈደም ! #Share


እኔ ማንም አይደለሁም ፤ እራሴንም ከሌላው ለማወዳደርና እሻላለሁ ብዬ ለመናገር ሞራሉም ብቃቱም የለኝም፡፡ ግን ግን ሰው ነኝና አንዳንድ ሁኔታዎች ይገርሙኛል፤ የሚገርመኝንና የምታዘባቸውን ነገሮች ለሌላው ባካፍል መመጻደቅ አይሆንብኝም፡፡ ህይወት ትምህርት ቤት ናት ፤ በህይወት ትምህርት ቤትነት ያወቅነውን ወይም የታዘብነውን ለሌሎች ማሳወቅና ማካፈል ሞራላዊ ግዴታም ጭምር ነው ብዬ አምናለው፡፡ ይህንን ጽሑፍ ከእዚህ መንፈስና አንድምታ ተረድታችሁልኝ እንድታነቡ አስቀድሜ ላሳስባችሁ እወዳለሁ፡፡

ተወልጄ ባደጉበት አካባቢ አንድ “አፒዮ” የሚባል ሰው ነበር፡፡ አፒዮ የቀን ሰራተኛ ሲሆን ፤ ለቤት መስሪያ የሚሆን እንጨት ከተቆረጠበት እስከሚፈለግበት ቦታ ድረስ በትከሻው ተሸክሞ ደከመኝ ሳይል የፈጀበትን ጊዜና ቀን ያህል ቢፈጅበትም እንጨቶቹን ተሸክሞ እያመላለሰ ከምር በተባለበት ስፍራ ይከምራል፡፡ ለድካሙ ዋጋ ብር አይቀበልም ጥቂት ዝርዝር ሳንቲምና ምግብ ብቻ በቂው ነው፡፡ አፒዮ እኔ እስከማውቀው ድረስ ዘመድ የለውም እንዲሁም በአካባቢው መኖሩን እንጂ ከየት እንደመጣ ማንም አያውቅም፡፡ ከሰው ጋር አይነጋገርም በአጠቃላይ ከማኅበራዊ ህይወት የተገለለ በእራሱ ዓለም የሚኖር ሰው ነው፡፡ ቤት የለው ፤ አንዲት ቃል ትንፍሽ አይል ብቻ ዝም ብሎ የጸጥታን ባህር የሚቀዝፍ ለሰውም ለራሱም ባይተዋር የሆነ ምስኪን ሰው፡፡ ቢርበው ራበኝ ብሎ ምጽዋት አይጠይቅም ፤ ውሃ ቢጠማው እሩቅ ተጉዞ ወንዝ ሄዶ ይጠጣል እንጂ ከማንም ጋር ግንኙነት መፍጠር አይፈልግም፡፡ የቀን ስራ ሰርቶ የሚያገኛትን ሳንቲም በድሪቶ ልብሱ ላይ ይቋጥራል፡፡ በላዩ ላይ ያለው ልብስ ድሪቶ ቢመስልም ብዙ ገንዘቦችን ቋጥሮ ይገኛል፡፡ “ግን አፒዮ ዘመድ ፤ ሚስትና ልጅ የለው ገንዘብ ምን ሊያደርግለት ያጠራቅማል?” ልጆች ሳለን ብዙዎቻችን የምንጠይቀው ጥያቄ ነበር፡፡ ታዲያ ምስኪን አፒዮ በዓመት ወይም በሁለት ዓመት አንዴ በከተማው ማዘጋጃ ቤት ጸጥታ አስከባሪዎች በግድ (አፒዮ እንደ ዝምተኛነቱ ሳይሆን አንድ ሰው አጠገቡ ደርሶ በመተናኮል ገንዘቡን ሊዘርፈው ቢነሳሳ ዘውትር ከአጁ በማትለው ቀመጥ እንካ ቅመስ ብሎ ያስገባለታል፡፡) ይያዝና ድሪቶ ልብሱ ከላዩ ላይ ይገፈፍል በእራፊ ጨርቆች የቋጠራቸው ሳንቲሞች ይፈታሉ ፤ ጸጉሩ ይቆረጣል ፤ አዲስ ጥብቆና ልብስ ይገዛለታል (ቀሪው ገንዘቡ ምን እንደሚደረግበት ፈጣሪ ይወቀው!)፡፡ እርሱ ግን በዚህ ምንም ደስተኛ አይሆንም እንዲሁም ለምን ንብረቴን ነካችሁብኝ ብሎ ያዝናል ፤ ይተክዛል ከፍ ሲልም ያለቅሳል፡፡ በአዲስ ገጽና ልብስ ለጥቂት ሳምንታት ከቆየ በኋላ ቀስ በቀስ አዲስ ገጽታውና ልብሶቹ እያደፉ ወደ ቀድሞ ማንነቱ ይመለሳል፡፡ እኔ እስከማውቀው ድረስ ህይወቱ በእንዲህ ቀጥላለች አሁን ይኑር አይኑር ባለውቅም፡፡

በአዲስ መስመር ሃሳባችንን ስናጠናክር በስራና በትምህርት ገበታ ብዙ አፒዮችን አውቃለው፡፡ እነኚን ከዋናው አፒዮ የሚለያቸው የተማሩ የሚባሉ ፤ በአንጻሩ የተሻለ ገቢ የሚያገኙ ናቸው፡፡ ነገር ግን በትክክል ከታየ ህይወታቸው ከአፒዮ የሚለይበት ምንም መስመር የለውም፡፡ በአፒዮ ላይ ምንም መፍረድ አንችልም ምክንያቱም ለሰው ቀርቦ የማያዋየው ወይም ሌሎቻችን ልንረዳው ያልቻልነው ብዙ ግላዊ ሚስጥሮችና እንቆቅልሾች ይኖሩታል፡፡ እነኚህን ግን ምን ልላቸው እንደምችል አላውቅም (ልፈርድባቸው ሳይሆን የህይወት ትርጉም ለእነሱ ምንድን ናት የሚለውን ለማንሳት ያህል ነው፡፡) ይሰራሉ ማንም የሚያገኘውን (አንዳንዴ እንዲሁም ከማናችንም በላይ ያገኛሉ) ደመወዝ ያገኛሉ፡፡ ብዙዎቹ ከማኅበራዊና ዘመድ የተገለሉ ናቸው፡፡ ነገር ግን ገንዘብ ማጠራቀም ትልቁ ስራቸው ነው፡፡ ለምን ገንዘብ ያጠራቅማሉ ለማለት አይደለም ገንዘብ ልንገለገልበት እንጂ ሊገለገልብን አይገባም፡፡ ልብሳቸውንና ገላቸውን አይታጠቡ አንዲት ልብስ እላያቸው ላይ እስኪወይብና እስኪያረጅ ማልያ አድርገው ይለብሳሉ፡፡ ትንሽ ገንዘብ አውጥተው ምግብ ለመብላት ለገንዘባቸው ይሳሱለታል፡፡

ብቻ እዚህ ልገልጸው የማልችላቸው ነገሮችን ሁሉ አይባቸዋለው፡፡ ባልፈርድባቸውም ያሳዝኑኛል ገንዘብ አስፈላጊ ነው ነገር ግን ገንዘብ ብቻ አያኖረንም፡፡ እንደው ይቅር ምንም አታውጡ ማኅበራዊ ህይወትን እንኳን እንጋራ ሲባሉ አሻፈረኝ የሚሉ፡፡ እራስን እየበደሉ ገንዘብ ማጠራቀም አሁንም ማጠራቀም፡፡ ይህ በእውነት ጤነኝነት አይደለም ለዚህ ነው ዓለም ዓቀፉ የጤና ድርጅት “አለመታመም ጤነኝነት አይደለም” ብሉ ጤናን በተለያየ አኳሃን የሚተረጉመው፡፡

የሚገርመው ነገር እነኚህ ሰዎች ገንዘባቸውን አጠራቅመው ኋላ ላይ ጤናቸውን በገንዘብ ለመሸመት ለዘመናት ያጠራቀሙትን ገንዘብ ለህክምና ያውሉታል፡፡ “የቆጣቢን ይበላል ቆርጣሚ!” እንደሚባለው አስቀድመን ያልተንከባከብነውን ጤና በኋላ ላይ ገንዘብ ብቻ አይታደገውም፡፡ ድህነት አስቀያሚ ነገር ነው ክብርንና ማንነትን ያዋርዳል ነገር ግን የሚበላ የሚጠጣ ሳይጠፋቸው ከድህነት ጠለል በታች የሚኖሩ ሰዎች በፍጹም የጤነኝነት አይደለም፡፡ ሰው ምግብ ካልበላ ውሃ ካልጠጣ እንዴት ነው የሚኖረው ፤ ለነገስ ብለን የምናጠራቅመው ገንዘብ ነገ እንደሚያኖረን እንደምን እርግጠኛ እንሆናለን!?

ከስነ-ልቦና አንጻር ከተመለከትነው ይህ እራሱን የቻለ ትልቅ ችግር ነው፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች በገንዘብ እጦት ምክንያት ብዙ መሰረታዊ ጉዳዮቻቸው ሳይሟሉ ካደጉ በኋላ ዘመን ያንን የማጣትን ዘመን ለመበቀል ሲሉ እራሳቸውን እየቀጡ ገንዘብ ማጠራቀምን ትናንትን እንደማሸነፊያ መንገድ አድርገው ሊወስዱት ይቻላሉ፡፡

ያለነን ነገር ሁሉ ደፍፍተን ዛሬን ብቻ እንኑር ማለትም አደጋ አለው፡፡ ዛሬን በአግባቡና በመጠኑ በመኖር ነገን ማለም ብልህነት ነው፡፡ ሰው እንደ ፀሐይ ነው በጊዜ ጀምበር ይወጣል በጊዜ ጀንበር ይጠልቃል፡፡ ጀንበር ወጥታ ለመጥለቅ እንደ ወቅቶች ሁኔታ ቢለያይም ቢያንስ አስራ ሁለት ሰዓት ያህል ይፈጅባታል ሰው ግን የራሱን ህይወት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ጀንበሩ በእጁ ላይ ነች፡፡ የህይወት ጀንበር ከመጥለቋ በሚፊት እራስን መንከባከብ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ማለት ማንም ሌላውን ይምሰል ወይም የሌላውን ኑሮ ይኑር ሳይሆን በአቅሙ ለመኖር ይብላ ይልበስ ሳይቸግረው እራሱን በእራሱ ቀጥቶ አያጥፍ ለማለት ነው፡፡ በገዛ እጅ እራስን አጎሳቅሎ የተጠራቀመን ገንዘብ ለህክምና ከማውጣት ጀምበር ከመጥለቋ በፊት መንቃት፡፡ ሻሎም!

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)


📌አሁኑኑ ይ🀄🀄ሉን
በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን
🎯🎯🎯🎯🎯🎯

🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን
SUBSCRIBE ያድርጉ

ዩቱዩብ:
https://www.youtube.com/@Asfaww

ቲክቶክ:
https://tiktok.com/@asfaw_motivation
ፌስቡክ:  https://www.facebook.com/attitudease

ቴሌግራም: 
https://t.me/Attitudeplc


  ለግል ለአስተያየትዎ:
https://t.me/LYDAse1

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!