አተ-ተቅዋ
66 subscribers
26 photos
5 videos
15 links
በአላህ ፍቃድ እንድንማማርበት ታስቦ የተከፈተ ቻናል ሲሆን መጥፎ ከተናገር ልታርሙን ጥሩ ከተናገር እናተንም ነፍስያችንን ለማስታወስ ነው ::

ጥሩ ከተናገርን ከአላህ እና ከመልክተኛው ነው መጥፎ ከተናገርን ከነፍሲያ እና ከሸይጣን ነው !!!

ስለምታነቡልን ዋጋቹ ጀነት ይሁን!!!
Download Telegram
قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا

«በላቸው፡- እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፤ አላህ ኃጢአቶችን ሁሉ ይምራልና።»
😢1
وَالَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا اصْرِفْ عَنَّا عَذَابَ جَهَنَّمَ ۖ إِنَّ عَذَابَهَا كَانَ غَرَامًا
«እነዚያም «ጌታችን ሆይ! የገሀነምን ቅጣት ከእኛ መልስልን፤ ቅጣቷ የማይለይ ሞት ነውና» የሚሉ።»
❤1
⚠️መውሊድ በዲን ላይ የተጨመረ የፈጠራ ተግባር ነው❗️

ረሱል (▫️) እንዲህ ብለዋል፦

﴿فإنَّ خَيْرَ الحَديثِ كِتابُ اللهِ، وَخَيْرُ الهُدى هُدى مُحَمَّدٍ، وَشَرُّ الأُمُورِ مُحْدَثاتُها، وَكُلُّ بدْعَةٍ ضَلالَةٌ،﴾

“ከንግግር ሁሉ በላጩ የአላህ መፅሐፍ ነው። ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። ከነገሮች ሁሉ መጥፎው መጤዎቹ ናቸው። ፈጠራ ሁሉ ጥመት ነው።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 867
በትዕግስት ጠብቅ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿يُسْتَجَابُ لِأَحَدِكُمْ مَا لَمْ يَعْجَلْ، يَقُولُ : دَعَوْتُ فَلَمْ يُسْتَجَبْ لِي﴾

❝አንዳችሁ የምታደርጉት ዱዓችሁ ተቀባይነት ያገኛል እሳካልቸኮላችሁ ድረስ። መቸኮል ማለት፦ ዱዓ አድርጌ ነበር ተቀባይነት አላገኘልኝም ማለቱ ነው። ❞

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 6340
‎وَاتَّقُوا يَوْمًا تُرْجَعُونَ فِيهِ إِلَى اللَّهِ ۖ ثُمَّ تُوَفَّىٰ كُلُّ نَفْسٍ مَّا كَسَبَتْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

«ወደ አላህ የምትመለሱበትንና ከዚያም ነፍስ ሁሉ የሰራችውን (ምንዳ) ሙሉ ሆና የምታገኝበትን፣ እነሱም የማይበደሉበትን ቀን ተጠንቀቁ።»
وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ ۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَارُ

«አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ነገር የዘነጋ አድርገህ አታስብ፤ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ ወደሚፈጡበት ቀን ብቻ ነው።»
يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْأَهِلَّةِ ۖ قُلْ هِيَ مَوَاقِيتُ لِلنَّاسِ وَالْحَجِّ

«ከአዲሶቹ ጨረቃዎች ይጠይቁሃል፤ «እርሷ ለሰዎች (የጊዜ) ማወቂያዎችና ለሐጅ (መቁጠሪያ) ናት» በላቸው።»

ሱረቱል በቀራህ (2:189)
يَسْأَلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ ۖ قُلْ مَا أَنفَقْتُم مِّنْ خَيْرٍ فَلِلْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَابْنِ السَّبِيلِ
«ምን እንደሚያወጡ ይጠይቁሃል «ከበጎ ነገር የምታወጡት ለወላጆች፣ ለቅርብ ዘመዶችም፣ ለየቲሞችም፣ ለምስኪኖችም፣ ለመንገደኛም ነው» በላቸው።»
ሱረቱል በቀራህ(2:215)
❤1
ሚዲያ ላይ: የበግን ለምድ የለበሱ ተኩላዎች ብዙ ናቸው!፣ ትዳር ላይ የውሃ አረፋት የሆኑ።  የአንዳድ ሰዎች ቃል እኛ ዘንድ በንፋስ ጀርባና በወራጅ ውሃ ደረት ላይ ሊፃፍ ነው የሚገባው። በተለይ ሚድያ ያገነናቸው የመጥፎ ባህሪ ባለቤቶች የሆኑትን።

አንዲት ሶሓባ ነበያችንን ስለትዳር ስታማክራቸው..."እሱኮ! ዱላውን ከትካሻው አያወርድም" ያሉት ሶሓባ ነበር ፣ ሶሐባኮ ነው። ግን ትዳር ረቂቅ ነው!!....ሰለፊይ ነኝ ብሎ ምግባር የጎደለው፣ ሴቶችን መቀያየር ግብሩ ያደረገ፣ ቅዳሜ አግብቶ እሁድ ለመፍታት የማያመነታ...ርህራሄ የጎደላቸው ብዙ ወንድሞች አሉን!። አብራው የሚያኖር ባህሪ ከሌለው ትዳራቸው ጤዛ ነው የሚሆነው!። የትዳር ሳይንስ ከመቅራት ከማስቀራት ምናምን ረቀቅ ይላል… “ዲኑንና ስነምግባሩን የምትወዱለት ከመጣ ዳሩት” ያሉት ረሱል ናቸው...።

✍አብደረህማን አማን
👍1
يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ ۖ قُلْ فِيهِمَا إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَا أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا«


ከመጠጥና ከቁማር ይጠይቁሃል፤
«በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢአትና ለሰዎች ጥቅሞች አልሉ፤ ኃጢአታቸውም ከጥቅማቸው የበለጠ ነው» በላቸው።
ሱረቱል በቀራህ
(2:219)
አንድን ሰው ቤት ዘግተንበት ከዓለም ሁሉ ብናቋርጠው ሪዝቅ በየት በኩል ይደርሰዋል? ብለው አንድን ዓሊም ጠየቁ።
"ሞት በሚደርሰው በኩል" ብለው መለሱላቸው።
በሰብር ኑሩ። ሪዝቃችሁ እንደ አጀላችሁ ይመጣልና!

Copy
❤1
የሰዎችን ጥፋት እንደ ጌታ ሆናቹ የራሳችሁን ጥፋት እንደ ባርያ ሆናቹ አትመልከቱ በወንጀል የተፈተኑ ሰዎችን ስታዩ እዘኑላቸው። አሏህ ከዛ ስለጠበቃችሁም አመስግኑት !!!

           ኢማሙ ማሊክ
👍2
ከአላህ የሆነ ሰላም.... ለዚያ አባቱን አጥቶ ለተወለደው.. እናቱን በምጥ ላላስጨነቀው ጨቅላ
ከአላህ የሆነ ሰላም... ለዚያ የብርሀን ዘውድ የኑር አበባ... ለእይታ የሚያሳሳ በመወለዱ ኸልቁን ላስደሳ ተአምረ ብዙ...
ከአላህ የሆነ ሰላም.... ባልዳበረ አካሉ የልጅ ገላው ተቀዶ በመልአክት ልቡ ለታጠበው
ከአላህ የሆነ ሰላም.... ከሸይጧን ውስወሳ ተጠብቆ ከፅዩፍ ምግባር ርቆ ላደገው ጥቡቅ
ከአላህ የሆነ ሰላም.... በታማኝነቱ ሲወደስ በሸጋ ምግባሩ ሲሞገስ ላደገው ወጣት💚✨️

الهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد 🤎
➢ያማረ ውዴታ ማለት አላህ
ለመላኢኮች ባለ ጊዜ ነው
" እገሌን ወድጀዋለሁና ውደዱት "
🥰1
አስቸኳይ‼️

​በእጃችን ላይ ያሉትን ቁርአኖች በሚቀጥሉት 3 ቀናት ውስጥ ተገቢው ቦታ አድርሰን ማጠናቀቅ እንፈልጋለን። ስለዚህ
1, አዲስ አበባ ውስጥ የቁርአን እጥረት ያለበት ወይም ተማሪዎቹ ቁርአን መግዛት የማይችሉበት መድረሳ/መርከዝ የምታውቁ ካላችሁ እባካችሁን አሁኑኑ ጠቁሙን! (ለቅርቦቹ አስቀድመን ሰጥተን መጨረስ ስለምንፈልግ ቅድሚያ ለአዲስ አበባና ዙሪያዋ እንሰጣለን)።

​2, ከአዲስ አበባ ውጭ ለሆናችሁ፦ ኑራኒያ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያስፈልጋቸው ቦታዎች ካሉ አሁኑኑ ጠቁሙን፤ እናደርሳለን!
​ቦታዎችን ለመጠቆምና ለበለጠ መረጃ
👉 @arisalah_admin
👍1
"ሁለት ነገሮችን ዘወትር አስታውስ: ሁለት ነገሮችን ደግሞ ፈጥነህ እርሳ::

የምታስታውሳቸው፡ አላህንና ሞትን ሲሆን: የምትረሳቸው...ለሰዎች የዋልከውን መልካም ነገርና ሰዎች በአንተ ላይ የፈጸሙትን በደል ነው።”

ሉቅማን ሀኪም🥀🖤
➔ ዛሬ ላይ እጅግ በርካታ ሴቶች እንደ ቀላል ነገር የሚመለከቱት፣ ነገር ግን በአላህና በመልእክተኛው ዘንድ እጅግ የከበደና አስከፊ ከሆኑ ወንጀሎች ተርታ የተመደበ አንድ አጥፊ ድርጊት አለ፤ እርሱም አንዲት ሴት ሽቶ ተቀብታ አጅነቢይ (ባዕድ) ወንዶች ባሉበት መውጣቷ ነው።

ይህንን አስመልክቶ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንድህ ይላሉ፦
❝ማንኛዋም ሴት ሽቶ ተቀብታ፤ ሽታዋን ያሸቱ ዘንድ በሰዎች (በአጅነቢይ ወንዶች) አጠገብ ካለፈች፤ እርሷ ዝሙተኛ ናት!❞ [አቡ ዳዉድ፣ ቲርሚዚይ እና ነሳኢይ]

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሽቶ ተቀብታ የወጣችን ሴት «ዝሙተኛ ናት» በማለት የጠሯት ዝም ብለው አይደለም። ሽቶ የአንድን ወንድ የስሜት ህዋሳት የሚቀሰቅስ፣ ልቡን የሚያሸፍት እና አይኑን ወደ እርሷ እንዲያነጣጥር የሚያደርግ ገዳይ መርዝ ነው። እርሷ በወጣችበት መንገድ ሁሉ የወንዶችን ስሜት በማነሳሳት የዓይን ዝሙት፣ የልብ ዝሙትና የሀሳብ ዝሙት እንዲፈጽሙ በር ከፋች ትሆናለች፤ በዚህም ሳቢያ በፈጸሙት ወንጀል ሁሉ ሙሉ ተካፋይ ትሆናለች።አደጋው በዚህ ብቻ አያበቃም! ይልቁንም ወደ አላህ ቤት መስጂድ ለመስገድ ስትሄድ እንኳ ሽቶ ከተቀባች ሶላቷ ተቀባይነት እንደሌለው በሌላ ሐድስ ተነግሯል።

ልብ በይ! ወደ አላህ ቤት፣ ለዒባዳ እና ለሶላት ለመሄድ ሽቶ መቀባት እንዲህ የሚያስጠይቅና ሶላትን ውድቅ የሚያደርግ ከሆነ፤ ለገበያ፣ ለትምህርት ቤት፣ ለቢሮ፣ ለመንገድ እና ለሰርግ ድግሶች ሽቶ ተቀብቶ በአጅነቢይ ወንዶች ፊት መዘዋወር ቅጣቱ ምን ያህል የከፋ ይሆን?!
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
❝ በጣም የሚገርም ነገር ነው፤ ሙሳ አለይሂ ሰላም የንግግር ችግር እና የምላስ ችግር ነበረበት። ነገር ግን አላህ በቀጥታ የናገረው እሱ ብቻ ነው፣በአላህ ፊት የሚታየው ልብህ ነው እንጂ ሌላ ነገር  አይደለም።
ኢብኑ አል-ቀይም ❝በሆነ ወንጀል ሰውን ያነወረ ሰው ያንን ወንጀል ሳይሰራው አይሞትም❞ ይላሉ።

ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ ደግሞ
❝በውሻ ባሾፍ እንኳ ውሻ እንዳልሆን ብዬ እፈራለሁ፡፡❞ ይላሉ።
👍1
✍ሶስቱ ከሳሪዎች.......
======================
1ኛው, የአደን ውሻ!!
🦴ይሮጣል ይደክማል አድኖ ያመጣው ግን ለባለቤቱ ያስረክባል።

2ኛው, ስስታም ሰው!!
💸አይበላም አይለብስም ሁሌም ሲስገበገብና ሲሰበስብ ይኖርና ለወራሽ አስረክቦ ይሞታል።

3ኛው, ሀሜተኛ ሰው!!
ይፆማል ይሰግዳል ይለፋል መጨረሻ ላይ የለፋበትን ሁሉ ሲያማቸው የነበሩት መጥተው ያስረክባል።
      [ከክስረት አላህ ይጠብቀን]