አስቂኝ ቀልዶችና ሌሎችም
9.7K subscribers
520 photos
140 videos
1 file
91 links
ያፈቀረን ማሳቅ ለኛ ኖርማል ነው አያሳስብም😉

#Join ያርጉና የትም

ባልተሰሙ ቀልዶቻችን ፈታ እያሉ በውብ የፍቅር ቃላቶች ይደመሙ😍

ዘፈን ግጥም ጠቃሚ ምክሮች...

ከቻልክ❤️ ፍቅርን ተናገር፣ኑር!
ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን

👉 @just_811 👉 @get_Mu

Please😊Don't Leave ችግር ካለ አናግሩን
Download Telegram
♥️ ፅናት ♥️...!!!
     .
     .
🥀..ክፍል 34..🥀
.
.

.
ለሊቱን ያቤፅም ፅናትን ፅናትም ያቤፅን በማሰብ እና ፈገግ በማለት ከዛ ደሞ በመተኛት አልፎ ጠዋት ብርሀን በፀሀይ ፈክታ ፀሀይም በብርሀን ፈክታ ለስለስ ያለች ፀሀይ ወጥታለች። የእነ ፅናት በር ተንኳኳ ፅናት ለሊቱን የተጓዘችው የፍቅር መንገድ እንቅልፏን ስለተሻማባት በጭራሽ አልሰማችም በፀሎትም ከእንቅልፏ ለመነሳት ሁነኛ ቀስቃሽ ያስፈልጋታል አልያም እንቅልፏን መጨረሰ ያስፈልጋታል። ሰአቱ 1:15 ሆኑዋል። ያቤፅ ተነስቶ በሩን ከፈተው። ሊባኖስ ነበረች። "እንዴ ጎረምሳው እንዴት መጣክ" አለችው። ያቤፅም "በምክንያት"
ብሏት ገባ። ሊባኖስም እንደመደናገር ብላ
"በምክንያት?"አለች ቃሉን እረገጥ አድርጋ። ያቤፅም ወደ ቤት ገብቶ ጥቅልል ብሎ ተኛ። ሊባኖስ ወደ ቤት ገብታ ወደ እነ ፅናት መኝታ ቤት ገባች። ፅናት እና በፀሎት ተቃቅፈው ተኝተዋል። ሊባኖስም ወደ እነሱ ተጠግታ በፍዘት ውስጥ ማየትዋን ተያያዘችው በድንገት ፅናት ከ እንቅልፍዋ ነቅታ "ደና አደረሽ ሊቦዬ ምንድነው ነገሩ በጣም ተመስጠሻል " አለቻት። ሊባኖስም "ውበታቹ እኮ ገርሞኝ ነው የኔ ልእልት በጣም ቁንጅናቹ ቱቱቱ ከአይን ያውጣቹ"
አለች። በፀሎትም እየተንጠራራች "ምንድነው ነገሩ ዛሬ ደሞ በጠዋቱ ነው የቀሰቀሳችሁኝ እንዴት አደራቹ? " አለቻቸው። ሊባኖስ እና ፅናትም "ደና አንቺ እንዴት አደረሽ አሉዋት። በፀሎትም "ደና አድሪያለው ኧረ ለነገሩ በጠዋት መነሳቴ ጥሩ ነው"ስትል ሊባኖስ ክትክት ብላ ሳቀች። በፀሎት ግራ ተጋብታ "ምነው ምንድን ነው የሚያስቅሽ ሊቦቲዬ" አለቻት። ሊባኖስም "እንዴት አልሳቅ 1:30 ተነስተሽ በለሊት እንደተነሳ ሰው ስትሆኚ" አለቻት።  ፅናትም ተደረባ ሳቀች እና "እኔም ዛሬ ማመልከቻዬ እንደተሳካ እና እንዳልተሳካ አያለው እዚሁ በሆነች ብላቹ ፀልዩ እባካቹ አለች።

........... ከ ወራቶች በኋላ..........

ዛሬ ፅናት የ 12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በድል አጠናቃ ልክ እንደምኞቱዋ ያለችበት ክልል ላይ ተመድባለች። እናም ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ በፀሎት እና ፅናት አዲስ ህይወትን ለመልመድ ያህል ፊታቸው ላይ የሚጠመጥሙትን ሻርፕ ከፊታቸው ላይ አውልቀውታል ፅናትም ወደ ዩንቨርስቲ በፀሎትም ወደ ጨርቃጨረቅ ማሰልጠኛው ሊሄዱ ነው። አዲሱን አመት በአዲስ መንፈስ ጀምረውታል። ያቤፅ ሁለት  ወር ሙሉ ሻርፓቸውን አስወልቆ መልካቸውን ማየት እስኪቀረው ድረስ ፊታቸውን እንዲያሳዩት ሲለማመጣቸው ቆይቷል። እሱም ለመጀመሪያ ጊዜ የፅናትን እና የበፀሎትን የፊት ገፅ ማየት ጓጉቶ ሳሎን ላይ እየተንጎራደደ ነው። ሊባኖስም ትልቁ ሶፋ ላይ ተቀምጣ ያቤፅን እየታዘበችው ነው። ያቤፅ አቁነጥንጦታል። ለነገሩ በእሱ የማሳመን ብቃት ነው ዛሬ ላይ ፊታቸውን ለማየት የመጓጓቱ ቀን የመጣው።

ሊባኖስ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ "እናንተ ልጆች በሉ ፈጠን በሉ"አለቻቸው። ያቤፅም ወደ ሊባኖስ ጠጋ ብሎ  አጠገብዋ ተቀምጦ "ስሚኝ እማ ሊባኖስ እስቲ በደንብ ንገሪኝ እስኪወጡ ድረስ ትናትና ፀጉሯቸውን ስታስተኩሻቸው አምሮባቸው ነበር እሺ ፅኑ እንዴት ነበረች? ፅኑ አምሮባት ነበር? የፅኑ ፊት ምን አይነት ነው?ቀይ እንደሆነች አውቃለው ግን ምን አይነት ፊት ነው ያላት? እሺ በፂስ እሱዋስ አምሮባት ነበር?" አላት። ሊባኖስ ሳቅ እየተናነቃት የያቤፅን ወሬ ከሰማች ሳቀች። ያቤፅም "እባክሽ ንገሪኝ እሺ ምን አይነት ልብስ ነው የገዛሽላቸው?" አላት።

ሊባኖስ ሳቁዋን ማቆም አቅቷታል። የመኝታ ቤቱ በር ተከፈተ ያቤፅም በፍጥነት መኝታ ቤቱ በር ላይ ሄዶ ቆመ። ሊባኖስ የያቤፅን ሁኔታ እያየች መሳቁዋን ማቋረጥ አቃታት። ያቤፅ አይኑን ማመን ተሳነው ፊት ለፊቱ የሚያያት ፀይም ፀጉሯን በአጭሩ የተቆረጠችው እና የለበሰችው ነጭ ሼፒ ቀሚስ የሰውነት ቅርፅዋን በደንብ አሳምሮ ያወጣላትን ልቅም ያለች ቆንጆ ሴት አየ። በፀሎትን አይቷት ፈዘዘ "በፂ  በፂዬ ወይኔ ጉዴ የፈጣሪ ያለ እንዴት ነው የምታምሪው" አለ አፉን ይዞ "አሁን እሺ እንዴት ነው ካንቺ አይኔን እምነቅለው የፈጣሪ ያለ እኔ ልጮህ ነው። ቆይ ምንድነው አይኔ የሚያየው ይህንን ውበት ማመን አልቻለኩም በጭራሽ አላምንም ወይኔ አምላኬ ቆንጆ ሴት በምናብህ ሳል ብባል እራሱ እንደ አንቺ ውብ አርጌ ልስላት አልችልም።" ብሎ ያለ ትንፋሽ ካወራ በኋላ መንጎራደድ ጀመረ። መንጎራደዱን ገታ አድርጎ በፀሎትን አየት ያረጋታል በፀሎትን አይቶ ፅናትን እርስት አርጓታል።

በፀሎት በዳበሳ ወደ ሶፍው ሄዳ ቁጭ ብላ "እንዴ ምንድነው ነገሩ ሊቦዬ ያቤፅ ምን ነክቶት ነው ያቤፅ በሰላም ነው?" ስትል ሊባኖስ ይበልጥ እየሳቀች "ውበትሽ ነዋ  እንዲ የሚያስለፈልፈው" አለቻት። ያቤፅ ከአጠገብዋ ተቀመጠና "ወይኔ ወይኔ ወይኔ በጣም ውብ ነሽ ቆይ ለምንድን ነው ይህንን የመሰለ ውበትሽን እስከዛሬ አሳይኝ ስልሽ እንቢ ያልሽው ወይ አምላኬ ወይ ፈጣሪ" አለ። በፀሎትም "እኔን አይተክ እንዲ ከሆንክ ፅናቴን ብታያት እራስክን ልትስት ነው እንዴ በእረግጥ ፅናቴን ለመጨረሻ ጊዜ ካየዋት አመታት ቢያልፉም በልጅነቷ እራሱ የነበራት ውበት በቃላት የሚገለፅ አደለም"አለችው በፀሎት ፈገግ ብላ።

ያቤፅም "ውይኔ አምላኬ ስትስቂ እራሱ እንዴት ነው ምታምሪው"አላት። በፀሎትም "አመሰግናለሁ ያቤፅዬ" አለች። ያቤፅ ዝም ብሎ ያያት ጀመረ። በድንገት  ፅናት "እሺ ያቤፆ እኔስ ባክህ" አለች። ያቤፅ ፈጠን ብሎ ልቡን ያዘ አይኑ ለጉድ ፈጠጠ ቀይ ከበፀሎት ረዘም ብላ ቀጠን ያለች የሚስብ የሰውነት ቅርፅ ያላት ፀጉሯ እጅግ በጣም ረዥም ከወገብዋ ያለፈ።ፈገግ አለች ልክ እንደታላቅ እህቷ በፀሎት ጉንጭዋ ስርጉድ አለ። ድድዋ የተነቀሰ ይመስላል የጥርስዋ ንጣት ለጉድ ነው ብቻ ያቤፅ በበፀሎት ከፈዘዘው በላይ ፈዞ ድርቅ ብሎ ሀውልትን ተክቷል በበፀሎት ውበት የለፈለፈው ምላሱ አሁን በፅናት ውበት ልሳኑ ተዘግቷል ቃል ማውጣትም አቃተው ይህኔ ነበር በፀሎት፣ሊባኖስ እና ፅናት በያቤፅ ከት ብለው ሲስቁበት የባነነው እና "የፈጣሪ ያለ፤ የአምላክ ያለ፤ ይህቺኛዋን ደሞ እዩልኝ ወይ አምላኬ ኧረ የልቤን ነገር አደራክን ዛሬ የልብ ድካም ሊይዘኝ ነው" አለ። ፅናትም ወደ  ያቤፅ ተጠግታ "ኣ እኔ ለእራሱ በድንጋጤክ ባሳየከው ፊት ልብ ድካም ሊይዘኝ ነው  እኮ" አለችና "እስቲ" ብላ ወደ ደረቱ ተጠግታ የልብ ምቱን አዳመጠችው እና ከት ብላ እየሳቀች "ኣኣኣኣ የ ያቤፆ ልብ በጣም እየመታ ነው እእእ የምርም በጣም ደንግጧል" አለች። ያቤፅም የፅናትን እጅ ይዞ እያያት ድምፁን ለስለለስ አርጎ በጣም ውብ ነሽ" አላት።
.
.
በየቀኑ እንዲለቀቅ አንብባቹ ስጨርሱ ላይክ ሼር አርጉ ቤተሰብ ♥️


ይቀጥላል...
❤12
♥️ ፅናት ♥️...!!!
     .
     .
🥀..ክፍል 35..🥀
.
.
.
.
ከዛም ወደ በፀሎት ሄዶ ቁጭ አለ ና ፅናትንም ስቦ አስቀምጦ ሁለቱንም አቅፎአቸው "በጣም ውብ ከውቦችም ውብ ናቹህ እኔ በህይወቴ  እንደ  እናንተ አይነት ቀርቶ ከ እናንተ በጥቂት የሚያንሱ ቆንጆዎች እራሱ አይቼ አላውቅም ደሞ እኮ ከ ፀጉሯቹ እና ከ ማጠር እና መርዘም እንዲሁም ከፊት ከለራቹ  በስተቀር ፍፁም አንድ አይነቶች ናቹህ የፈጣሪ ያለ የኔ አምላክ ልቤን ጠብቅልኝ" አለ።

ሊባኖስም ሳቀች። ፅናትም "በሉ ሰዎች ወደየ ጉዳያችን እንሂድ ዛሬ ለእኔ እና ለእህቴ አዲስ ጅማሮ ነው።በይ እህቴ ተነሺ የመኪና ክላክስ በእርግጠኝነት የእህቴ አለቃ ነው የሚሆነው በሉ እስቲ አሁን ደሞ አለቃ ተብዬው እህቴን ሲያያት ምን እንደሚሰማው እንይ" አለች። በፀሎትም "በይ ዝም በይ እህቴ ሆሆሆ እኔ እራሱ እራሴን በመስታወት ለማየት ጓጓው እኮ" አለች። ያቤፅም "እረ እንኳን አላየሽው በራስሽ ውበት ተማርከሽ ብቀሪስ ለማንኛውም ነይ እስከበር ልሸኝሽ" አለና  ከ ወገብዋ አቀፍ አርጓት የውጪው በር ላይ ደረሱ።

ያቤፅ እነ እሱ ጋር መኖር ከጀመረ ጀምሮ በፀሎትን ሁሌም ይሸኛታል። ልክ በሩን ከፍተው ሲወጡ የበፀሎት አለቃ በፀሎትን ሲያያት ከመኪናው ፈዞ ወረደ።አይኑን ከበፀሎት ሳይነቅል ወደ እስዋ ተጠጋና "እእእእ በጣም ቆንጆ ነሽ የምር አንቺ በፀሎት ነሽ" አላት። ያቤፅም "አዎዎ በፂ እኮ ናት እይዋት እይዋት እንደእዚህ ውበት እንደጉድ የፈሰሰባት ልጅ አለች ሁላችሁም ዙራቹ እይዋት" እያለ መጮህ ጀመረ።

በፀሎት ተሸማቀቀች። "ያቤፅዬ እባክህን ዝም በል ልለምንህ" አለችው። ያቤፅ ግን የበፀሎት ልመና ችላ ብሎ አሁንም መጮሁን ቀጥሏል ፅናት ምን ተፈጠረ ብላ ወደ ውጪ ለመውጣት የውጪውን በር ከፈተችው ሊባኖስም ተከትላት ወጣች። ያቤፅ ወደ ውጪ በር ዞር አለ ፅናትን አያት ወደ ፅናት ሄዶ እጇን እየጎተተ ከእህትዋ አጠገብ አስቆማትና...

"ተመልከቱ እዩ ተመልከቱ የእነዚህን እህትማማች ውበት" የያቤፅ ድምፅ የት እና የት ይሰማል እየጮኸ መናገሩን ቀጥሏል። "እንዲህ አይነት ውበት ማነው አይቶ የሚያውቅ ንገሩኛ " ካለ በኋላ ወደ በፀሎት አለቃ ዞር ብሎ "አንተ አይተክ ታውቃለክ" አለው። የበፀሎት አለቃም በድንጋጤ ስሜት ውስጥ ሆኖ ኧረ በጭራሽ"አለ። ያቤፅ እብደቱ እና ጩኸቱ ባሰበት "አቤቱ አቤቱ የፈጣሪ ያለ አቤቱ ምንድነው ዛሬ ያየውት"አለና ፀጥ ብሎ ቆየ።

የሰፈሩ ሰው ከህፃናት እስከ አዋቂ ከበቧቸው። ያቤፅ አሁን መጮሁን ትቶ ወደ በፀሎት እና ፅናት በመሄድ አንድ አንድ እጃቸውን ይዞ የምር ዛሬ ባየውት ውበት ተደምሜያለው አላቸው። በፀሎትም "ቆይ አንተ ልጅ አብደሀል  እንዴ" አለችው።

ያቤፅ ወዲያው ፈገግ ብሎ "በእዚህ ፀባዬ ነበር ልክ አንቺ አብደሀል እንዴ ብለሽ እንደጠየቅሽኝ ሳይጠይቁኝ አብደሀል ብለው እብዱ ያቤፅ ያሉኝ"አላት። ፅናትም እየሳቀች "እና እንዲ እየሆንክ እብዱ ያቤፅ ቢሉክ ምን ይገረማል"አለችው። ያቤፅም "እሱማ አይገርምም በቃ ነይ ፅኑዬ ልሸኝሽ" አላት። ሊባኖሰ"አዎ ሂዱ በሉ በፀሎቴ በይ አንቺም አታስጠብቂው አለቃሽን አንተ እብድ በል አድርሳትና አንተም ና ዛሬ እፈልግሀለው" አለችው። ያቤፅ "እሺ  እንዳልሽ በይ ነይ ቦርሳሽን ይዘሽ ፅኑ " አላት። ፅናት ፈገግ ብላ "እሺ ጌታው ያቤፅ" አለችና ቤት ገብታ  የበፀሎትንም ቦርሳ አምጥታ ሰጥታት "በይ መልካም ቀን የኔ ቆንጅዬ እህት አለቻት።የበፀሎት አለቃም "እንዴ አብራችሁን ኑ እንሸኛቹ" ሲል ያቤፅ "አይ አያስፈልግም እባክህ ዛሬ ይህቺን ቆንጆ በመንገዱ ላይ ይዣት ሽርርር ልበል ልጎርር ደረቴን ነፍቼ ልሄድ አዳሜውን ላስቀናው አይመስልክም" አለው።

አሁን ፅናት ከያቤፅ ጋር አውላላ አስፓልት ላይ እየተጓዘች ነው። ፅናት ከ ያቤፅ አይኗን አልነቀለችም የሆነ ልትለው የምትፈልገው ነገር ያለ ይመስላል። ያቤፅም እጁን በለበሰው ኮታታ ሹራብ  ከቶ እየተጓዘ ነው በሀሳብ ስምጥ ብሏል።የሆነ ሀሳብ ውሰጥ ገብቷል ።ፅናት በልብዋ ምን እያሰበ ይሆን? ለምንድነው እኔን ከ ሰው ጋር ብቻ ስሆን እያወራኝ ለብቻችን ስንሆን ምንም እማይለኝ?" አለች። ያቤፅ ያቀረቀረ አንገቱን ቀና አርጎ ፅናትን እልም ያለ ፍቅር በሚያሲዝ አስተያየት አይቷት ከዛ መልሶ አንገቱን ሰበረ። ፅናት ይህ ነገሩ ጭራሽ አይገባትም ለምን? እንዲ ትሆናለክ ብላ መጠየቅ ፈልጋለች ግን አንደበትዋ አላወራ አላት። ከያቤፅ ጎን ስትሆን ውስጧ በሀሴት ይሞላል ያቤፅም ከፅናት ጋር ሲሆን እንደዛው ግን ሁለቱም ስለሚሰማቸው ነገር መነጋገር አልቻሉም።

ፅናት ወሬ ለመጀመር ያህል "ያቤፆ" አለችው። ያቤፅም "ወዬዬ ፅኑዬ" አላት። መንገደኛው ሁሉ እያየኝ እኮ ነው"አለችው። ያቤፅም "አዎ ፅኑ ልክ ነሽ ባያዩሽ ይገርመኝ ነበር በጣም ውብ እንደሆንሽ ነገሬሻለው"አላት። እረጋ ባለ ድምፅ። ፅናትም "ታቃለክ እረጋ ስትል እብደትህ ስታብድ ደሞ እርጋታክ ይናፍቀኛል"አለችው። ያቤፅም
"ማለት ፅኑ አልገባኝም "አላት። ፅናትም ፈገግ ብላ "እስቲ እባክህ አንዴ ቀና ብለክ እያየከኝ አውራኝ ቆይ እህቴንም አለቃዋ መጥቶ መውስደ ከመጀመሩ በፊት አንዳንዴም ሳይመጣ ሲቀር ሰትሸኛት በእዚህ መልኩ ነው" አለችው። ያቤፅ ዝም ብሎ ቆመና የፅናትን ፊት እያየ "አደለም ፅኑ ከ በፂ ጋር ስሆን ቃል አይጠፋብኝም ካንቺ ጋር ስሆን ግን አሁን አሁን እምናገረው ነገር እየጠፋብኝ ነው ፅኑዬ አልቻልኩም እባክሽ የሆነ ነገር ብለሽ ገላግይኝ" አለ በውስጡ።

ፅናት ዝምታው አስፈራት "እሺ እሺ በቃ ተወው እዚህ ጋር ታክሲ ይዤ እሄዳለሁ ተመለስ ካላዋራከኝ እርምህን ዛሬ ብትሸኘኝ ያውም ደሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ጊቢ በምገባበት ቀን እንደውም በቃ ዛሬ እዛው ጊቢ ነው እማድረው አልመጣም" ብላ ወደ ዩንቨርስቲ የሚወስዳትን ታክሲ አስቁማ ሄደች። ያቤፅ ከአስፓልት ወደ እግረኛ መንገድ ተጠግቶ ቁጭ አለ። ፅናትም የያዛት ታክሲ ያዟት ከነፈ።

ያቤፅ ከቆይታ በኋላ ከሊባኖስ ጋር ቁጭ ብሉዋል።ሊባኖስ ዛሬ ፅናት እና በፀሎት ሲመጡ አንድ ነገር እናረጋለን። አለችው።ያቤፅም  "ወይ አንቺ ፅኑ እኮ አልመጣም ብላለች"ሲላት።እንዴ ለምን አለችው ምክንያቱን ነገራት። ሊባኖስም "ዝም በላት ቅርብ ነው ዩኒቨርሲቲው የ አንድ ታክሲ እና የትንሽ እግር መንገድ የቦታ እርቀት  አታስብ እሱዋን እኔ አመጣታለው" ስትለው ያቤፅ "እሺ ምንድነው እነግርሀለው ያለሽኝ?" ሲላት ሊባኖስ "መጀመሪያ እንቢ እንዳትለኝ ቃል ግባልኝ"አለችው እሺ በይ ንገሪኛ አላት። ሊባኖስም ለመናገር ተመቻችታ ያቤፅን አይኑን አተኩራ እያየችው ነው።

"እየውልክ የኔ ሚጢጢ እንደምታውቀው በተደጋጋሚ እራስዋን ትስታለች" አለችው። ያቤፅም "እና ምን" አላት። ሊባኖስም "ለማለት የፈለኩት የሆነ ጊዜ ላይ ጋሽ በሬሳ ጋር አንድ ታካሚ መጥታ ነበር እና እራስዋን በተደጋጋሚ ልክ እንደ የኔ ሚጢጢ ስታ ትወድቅ ነበር" አለችው። ያቤፅ መንጎራደድ ጀመረ "ቆይ አንቺ ሴት አብደሻል እንዴ የፈጣሪ ያለ ቆይ እና ምን ይሁን ነው ምትይው ምልክታቸው አንድ አይነት ሆኖ ነገር ግን የተለያየ በሽታ እንዳለ አታውቂም እሺ በይ ቀጥይ" አላት እጁን እያወናጨፈ እና ይበልጥ በፍጥነት እየተንጎራደደ። ሊባኖስም ማውራቷን ቀጠለች። "እኔ ለማለት የፈለኩት" ስትል ትግስት ያጣው ያቤፅ ሊባኖስ አጠገብ ቁጭ ብሎ እያፈጠጠባት  "ሆሆሆ ሊላ ለምን እምትናገሪውን ነገር አትናገሪም" አለ።


ይቀጥላል...
❤11🙏1
♥️ ፅናት ♥️...!!!
     .
     .
🥀..ክፍል 36..🥀
.
.

.
.
ሊባኖስም "እሺ ልነግርክ ነው ያቺ ልጅ ዛሬ ሞታለች" አለችው። ያቤፅ ግራ ተጋባ "ቆይ አንቺ ሴት ምን እያወራሽ ነው በፈጠረሽ አምላክ? አምላኬ ሆይ አሽሙር አደለም በለኝ ቆይ ፅናት ትሞታለች እያልሽ ነው" አላት።

ሊባኖስም "አይ እንደዛ ሳይሆን" አለች። ያቤፅ የሊባኖስን እጅ ይዞ እንባ እየተናነቀው "ቆይ ምንድነው ንገሪኛ በፈጣሪ" አላት። ሊባኖስም "እየውልክ ልጅትዋ የሞተችው እኮ በሽታውን መቋቋም ስላቃታት ነው። ደሞ የኔ ሚጢጢን በሽታውን እንድትቋቋም ለማረግ አሁን ብዙ የሚያስደስቷትን ነገሮችን ማረግ አለብን ተስማማን?" አለችው። ያቤፅም "አዎ አዎ እሺ ተስማምተናል" አላት። ሊባኖስ ፈገግ ብላ "እሺ ጥሩ ዛሬ ሁለቱ ቆነጃጂት እህትማማቾች ሲመጡ ጥሩ ጊዜ እናሳልፍለን" አለች። ያቤፅን አቅፋው
ያቤፅም "እሺ ጥሩ ግን ፅኑ አትመጣም"አላት። ሊባኖስም "እንዴ ለምን ለምንድነው እማትመጣው የት ልትሄድ አለችው" ያቤፅም የተፈጠረውን ነገራት። ሊባኖስ "ባክህ ዝም በላት ትመጣለች ጨክና አትቀርም በእኛ ብጨክን በእህቷ ጨክና አትቀረም አሁን በቃ እምንሰራውን ነገር ገዛዝቼ ልምጣ" ብላ ብድግ አለች።

ያቤፅ "እህ አብሬሽ ልሂድና እሸከምልሻለው" ሲላት። ሊባኖስ "አይ አያስፈልግም ይልቅ ደመቁ ብስኩት ልትሰራ ትመጣለች ስለዚህ እሷን ውሀ በማጋዝ አግዛት" ብላ መኝታ ቤት ገብታ ተዘጃጅታ የሳሎኑ በር ላይ እንደደረሰች ደመቁ መጣች። ሊባኖስም "ውይ ደምዬ መጣሽ እንዴት ነሽ ጀርባሽን ተሻለሽ " አለቻት።ደመቁም  "አይይይ ዛሬ አልሰራም ልልሽ ነው አመጣጤ በጣምምም አሞኛል" ስትላት።ሊባኖስ "እሺ በቃ ሂጂ ቤትሽ እረፍት አርጊ ልጅ ያቤፅ በል ና አብረከኝ በሩን ቆልፈክ" አለችው። ያቤፅም በሩን ቆልፎ ከ ሊባኖስ እና ከደመቁ ጋር ወጡ።

ሰአቱ 12:15 ሆኖዋል የእነ ፅናት ቤት ፉዋዋዋ ብሎ ቡና ተፈልቷል የተለያዩ የምግብ አይነቶች ጠረጴዛ ላይ ተደርድረዋል።ፅናትም ልክ እሷ እና ያቤፅ ተጣልተው ታክሲ ከያዘችበት ቦታ ደርሳ ከታክሲው ወረደች። የሁሉም ሰው አይን ፅናት ላይ ነው። ፅናት ልክ ትንሽ እንደተራመደች ከፊለፊቷ አንድ ሸበላ በጣም የሚያምር የጨርቅ ሱሪ በሸሚዝ እና ፍላት ጫማ አርጎ እየመጣ ነው።ፅናት በውስጧ "እሰይይ ሰው ሁሉ እኔ ላይ ሲያፈጥ እኔም እማፈጥበት ሰው አገኘው" አለች። ልጁ ወደ እስዋ እየቀረበ መጣና ከፊት ለፊትዋ ቆመ። ፅናትም አንገቷን ቀና አርጋ አይኖቹን አየቻቸው።

እሱም ትኩር ብሎ አያትና "ፅኑ" አላት። ፅናት ማመን ተሳናት ይሄ ከፊትለፊቷ የቆመው በጣም ማራኪ ቁመና እና መልክ ያለው ልጅ ያቤፅ እንደሆነ ስታውቅ "ያቤፆ" አለችው።

"ወዬ ፅኑዬ" አላት። ፅናት ፈገግ ብላ "የእውነት አንተ ነክ ፤ የእውነት አንተ ነክ ግን" አለችው። ያቤፅም "አዎ ፅኑዬ እኔ ነኝ እንዴት ነው አምሮብኛል?" አላት እጆቹን ከፍ አርጎ ፅናት ፈገግ ብላ "በጣም የኔ ሸበላ ቃል የለኝም ጨበሬ ፀጉርክ፤ችፍፍፍ ያለው ፂምህን ተስተካክለክ ያንን ኮተት ልብስ ቀይረክ እንዴት እንደምታምር ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ፊትህን በደብ ያየውት ስለተቀየርክ ደስስስ ብሎኛል"ብላ አቀፈችው። ያቤፅም ይበልጥ አጥብቆ እቅፍ አርጓት "ፅኑዬ" አላት። ፅናትም "ወዬ ያቤፆ" ስትለው "ጠዋት ላስከፋውሽ ነገር ይቅርታ እማትመጪ መስሎኝ ከፍቶኝ ነበር ነገር ግን ሊቦ ትመጣለች ብላ ተስፋ ሰጠችኝ አላት። ፅናትም ከያቤፅ እቅፍ ሳትወጣ "የምር ብቀር ታዝን ነበር?" አለችው። ያቤፅ ከእቅፉ አውጥቶ ጉንጭ እና ጉንጯን በሁለቱ መዳፉ ይዞ "በጣም በጣም ፅኑዬ እኔ ያላንቺ አልችልም" አለና ግንባሩዋን ሳማት። ይህኔ ነበር የፅናት ልብ በሀያሉ የመታው ያቤፅ ብሏት እማያውቀውን ቃላቶች ብሏት ከዛም አልፎ ደሞ ግንባርዋን ለመጀመሪያ ጊዜ በፍቅር አይን እያየ ሲስማት እንዴት ልብዋ አይመታም ይመታል እንጂ።

ፅናት ቀና ስትል ከያቤፅ አይኖች ጋር ተገጣጠሙ ያላወቀችው ሀይል መጥቶ ወደ ያቤፅ ከንፈር መራት። አይኑዋን ጨፈነች ያቤፅም አይኑን በስሱ ጨፍነው ያሉበት ቦታ ታክሲዎች በፍጥነት የሚጓዙበት እንጂ ሰው የሚያልፍበት አደለም። ልክ በከንፈሮቻቸው መካከል ትንሽ ክፍተት ሲቀር ልባቸው ለጉድ ይመታ ጀመር። በመጨረሻ ከንፈር እና ከንፈራቸው ተነካካ እና ሳመችው እሱም ሳማት።

ይህኔ ነበር ፅናት ያቤፅ እቅፍ ውስጥ ሆና  ከሀሳብዋ የነቃችው ያቤፅ እቅፍ ውስጥ ሆና በሰማችው የመኪና ክላክስ ነበር። ፅናት "ወይ እውነት አልሆነ ወይ ሀሳቤ ላይ አልቆየው" አለች በውስጧ የመኪና ክላክስ ወደሰማችበት አቅጣጫ እየዞረች። ባለ ክላክሱ የበፀሎት አለቃ ነበር። ፅናት የያቤፅን እጅ እየጎተተች።ከኋላ ገቢና ላይ በፀሎት አለች። መኪና ውስጥ ከገቡ በኋላ ፅናት "እህቴ እንዴት ነሽ አንተስ እንዴት ዋልክ"አለች። የበፀሎትን አለቃ እያየችው። "ደና ነኝ አንቺስ" አላት በቀኝ እጁ እያሽከረከረ በግራ እጁ ደሞ የበፀሎትን ጣቶች ከጣቶቿ አጣምሮ ይዞ። ፅናት ይህንን ስታይ ማመን አቃታት "እህቴ" አለቻት። "ወዬ የኔ ልዩ" ስትላት። "እጅሽ" አለቻት። የበፀሎት አለቃ ደንግጦ የበፀሎትን እጅ ሊለቃት ሲል በፀሎት "ቆይ" አለችና እጁን ይበልጥ አጥብቃ ያዘችው እና "የኔ እህት ፅናትዬ አትንቀልቀይ እሺ ጥያቄሽ በኋላ ይደረሳል" አለቻት።

ፅናትም "እሺ እህቴ"አለች። ድምፅዋን ቀነስ አርጋ። ከዛም በልብዋ "ምን አለበት ያቤፅም እጄን ቢይዘኝ" ብላ ተመኘች። ያቤፅ በመስኮቱ በኩል አፍጥጧል። አሁን ቤት ደረሱ። ያቤፅ ከሁሉም ቀደም ብሎ በሩን ከፈተው ፅናት "እንዴዴዴዴዴ ኧረ ጉድድ ደስ ሲል " አለች። በፀሎት ግራ ገብቷት "እንዴ እህቴ ምነው" አለች። በእዚህ ሰአት ነበር የሊባኖስ አይን የበፀሎት እና የአለቃዋን የተጣመረ እጅ ላይ አይኑዋ ያረፈው። "ኧረ ጉድድድ ዛሬ ሰርፕራይዝ አረጋለው ብዬ እራሴው ተደረኩኝ"አለች።

ፅናት እና ያቤፅ ፈገግ አሉ። የበፀሎት አለቃ ተሸማቀቀ ምክንያቱም ሊባኖስ ከተጣመረው እጃቸው አይኑዋን መንቀል ስላልቻለች።ሊባኖስ በመጨረሻ ሀሳብዋን ሰብስባ "በሉ በሉ ቁጭ በሉ"አለች። ከዛ ቤቱ ድምቅ አለ። ሊባኖስ ቡና እያፈላች ነው ሁሉም ሊባኖስ የሰራችውን ጣፍጭ ምግብ እየተመገቡ ነው በቃ ቤቱ በጣምምም ደምቋል ልክ ምግባቸውን ተመግበው ሁለተኛ ቡና እየጠጡ በፀሎት ድምፅዋን ከፈ አረጋ "ስሙኝ ዛሬ ሁለት ደስስ የሚሉ ነገሮች እነግራችዋለው"አለች። ፅናትም "እሺ እህቴ በያ ንገሪን እባክሽ" አለቻት። በፀሎት እምትናገረው ጠፍቶባት መንተባተብ ጀመረች። የሁሉም አይናቸው፤ ልባቸው እና ጆሮአቸው በፀሎት ላይ ሆኖዋል።

በፀሎት ግን መናገር አቃታት። ሊባኖስ "በያ የኔ ቆንጆ ንገሪን አታጓጊን እንጂ" አለቻት። ፅናትም በጣም ጓጉታ "እህቴ እባክሽን ንገሪን" ስትላት። ያቤፅ "ኧረ በፂ ይደብራል ምንድነው እንዲ ማጉዋጋት"? አላት።  በፀሎትም "ማጉዋጉዋት ፈልጌ እኮ አደለም  እንዴት ብዬ መግለፅ እና መናገር እንዳለብኝ ከብዶኝ እንጂ ዛሬ 2 ነገሮች እነግራችዋለው " አለችና ብድግ ብላ እጅዋን ወደ አለቃዋ ሰደደችው  እሱም ተነስቶ  እጅዋን ያዛት።
         .
         .
         .
ከ 150 like ቡሀላ ክፍል 37 ይቀጥላል...

👇👇👇
በየቀኑ እንድንለቅላቹ አንብባቹ ስጨርሱ ሼር ላይክ አርጉ ♥️
❤40👍10
#ውሾች_ይጮሃሉ_ግመሎች_ይሄዳሉ..
🐪🐪🐪 🐕 🐕
ማንም ምንም ይበል Keep going forward ! What others think about you is none of your business!

እንግሊዘኛ ትምህርትን በእስፖርት⛹‍♂ መምህር ተምሬ ይሄን ያህል እንግሊዘኛ ከፃፍኩ መደነቅ የለብኝም ታዲያ🤷‍♂
❤15🤣5😭5
ብርዱን ምክንያት በማድረግ የማቀፍ አገልግሎት እንሰጣለን ሴቶች ይበረታታሉ ለወንዶች ቦታ የለንም🤷‍♂
🤪21❤8
በአጠገቡ አንቡላንስ🚑 እየጮኸ ሲያልፍ "እዩት ይሄን አሽቃባጭ ሰው ሊያድን እኮ ነው" ያለው የሬሳ ሳጥን ሻጭ ትዝ አለኝ
🤣37❤9
ምን አለ አሁን እኔ በTelegram ቀልድ ስልክላችሁ እናንተ ደግሞ በ Money gram ብር ብትልኩልኝ😜😂
👍31🤣22❤10🆒1💘1
የሴት ልጅ እድሜና ፈተና
15 አመቷ፡ ወንድ እንዳይቀርብሽ
18 አመቷ፡ ወንድ እንዳያታልልሽ ተጠንቀቂ
20 አመቷ፡ አርፈሽ ተማሪ
24 አመቷ፡ ውጭ ውጭ አትበይ ወንድ ራሱ ይመጣል
26 አመቷ፡ አግቢ እንጂ
28 አመቷ፡ አታማርጪ
33 አመቷ፡ ቆመሽ መቅረትሽ ነው
35 አመቷ፡ አርግዘሽም ቢሆን ተጠቃለይ
38 አመቷ፡ ዝምብለሽ ከአንዱ ውለጅ
#ህዝቤ የሴት ልጅ እድሜ ለምን እንደሚያስጨንቀው አይገባኝም፡፡
🤔8❤7
ሁሌም ከእንቅልፍህ ስትነሳ ይህን አስታውስ። አንተ ተፈላጊ ሳትሆን አስፈላጊ ነህ 100%🙌
👌20
ብታዩ የዘንድሮ ተማሪዎች Facebook በጣም ከመጠቀማቸዉ የተነሳ መጽሐፍ ሲያነቡ Like እና Share button ፈላጊዎች ሆነዋል😜
👌14
ድሮ በአማሪኛ Class ከገንዘብ💵 እውቀት📚 ይሻላል ብዬ የተከራከርኩት...
💰 💰 💰
#ልጅነት_ይዞኝ_ነው_ገንዘብ_ሆይ_ይቅር_በይኝ
🤣10❤3
ከራሴ ጋር ተጣልቼ ብሎክ ላረገው Setting ውስጥ እየገባሁ ነው😂😜🤷‍♂
👍7❤2🤣1
አርጅታችሁ ጥርሳችሁን ከማጣታችሁ በፊት ሳቁበት😂🤣😅
🤣16
#ዐርብ ላይ ሆኜ #ቅዳሜን ባሰብኳት ጊዜ ተደሰትኩ😂
❤14
Online ከሌለው ቶሎ ብላቹ ካርድ ላኩልኝ
❤9
ጋንጃ ያጦዛል ብለውኝ ስሞክረው ወፍ የለም
፡
ይሀው ራሴን ሆድ ምታት ይዞኝ ልታከም ገቢዎች ጽሕፈት ቤት እየሔድኩ ነው።
🤣22
♥️ ፅናት ♥️...!!!
     .
     .
🥀..ክፍል 37..🥀
.

.
.
ፅናት "ሆሆሆሆ ኧረ ምን ጉድ ነው? በጉጉት ልትገሉን ነው እንዴ ሀሳባቹ" አለች። አጠገብዋ የተቀመጠው ያቤፅም "እስቲ ዝም በይ ልትናገር ነው" አለና በትከሻው ጎሸም አረጋት። በፀሎትም "አዎ ልናገር ነው ዛሬ 2 አስደሳች ነገሮች እነግራችዋለው" ስትል ያቤፅ "ኧረ እባክሽ በፂ ምንድነው እሱንማ ቅድም ነገርሽን አደል" አላት።
በፀሎት ክትክት ብላ እየሳቀች "ልክ ነው
ዛሬ ደስተኛ ህይወት እንድኖር ተፈቅዶልኛል የፈቀደልኝ አምላክ ነው።

ይህ እምታይውት እማፈቅረው ሰው እሱም እንደሚያፈቅረኝ ከነገረኝ ቆየ እና ዛሬ ጥያቄውን ተቀብየዋለው" አለች። ያቤፅም "አሀሀሀሀ እና በፂዬ ፍቅር ያጃጅላል አሉ በይ መልካም መጃጃል" አላትና ሳቀ ሁሉም ተከትለውት ሳቁ በፀሎትም አሜንን አለች። ነገር ግን ፅናት የያቤፅ ንግግር ውስጧን ስለረበሻት አልሳቀችም በስሱ ብቻ ነበር ፈገግ ያለችው። ያቤፅም "እሺ ሁለተኛውስ" አላት። በፀሎትም "ሁለተኛው ሁለተኛው ደሞ እኔ..." አለችና እንባዋን እያረገፈች ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች። እና ሁሉም ደነገጡ ከ አለቃዋ በስተቀር።

ፅናት ፈጠን ብላ ወደ እህቷ ሄዳ አቀፈቻት። በፀሎትም እህቷን ይበልጥ እቅፍ እያረገቻት "እህቴ" አለች።

ፅናትም"ወዬ እህቴ" አለቻት። በፀሎትም ፅናትን ከእቅፉዋ አውጥታ እንባዋን ጠራረገችና "ዛሬ አይኔ በቅርብ ጊዜ ህክምና.... "አለችና መናገር አቃታት። ፅናት የእህቷን ንግግር ሰምታ ሳትጨርሽ
"እህቴ ምን ለማለት ፈልገሽ ነው ማለቴ እኔ ያሰብኩትኝን ነበር በሆነ እምትናገሪው" አለቻት።

በፀሎትም ፈገግ ብላ "ይህ ከጎኔ ቆሞ የምታዩት ሰው የአይን ህክምና ወጪዬን ሙሉ ሸፍኖልኝ ሊያሳክመኝ እና ብርሀን ሊሰጠኝ ነው የአይን ብርሀኔን ሊመልስልኝ ነው"አለች።

ሊባኖስ "አአ ምንድነው ምሰማው"አለች።
ያቤፅም "ውይይይ የሰው ልጅ አሁን እስቲ ሊባ የምር በእዚህ ንግግር ውስጥ ያልገባሽ ነገር አለ? የለም እኮ በሉ አሁን ኑ ሁላችንም አቅፈን ጥሩ ምኞታችንን እንግለፅላት" አለና ወደ በፀሎት ሄዶ "እንኳን ደስ አለሽ ቆንጅዬዋ በፂ በይ እንግዲ ማየት ከቻልሽ በኋላ ሰውዬሽን መጀመሪያ እይው ያለ በለዚያ ግን መጀመሪያ እራስሽን በመስታወት ካየሽ ቀድመሽ በራስሽ ውበት እና ፍቅር ትወድቂያለሽ"አላት። በፀሎት ክትክት ብላ ስቃ "ጥሩ ምክር ነው ያቤፅዬ" አለቻው።  ያቤፅም "አቦ ግን አንተ ጥሩ ሰው ነክ እንደዚህ አይነት ሰው አይገኝም ትልቅ ስራ ነው የሰራከው ብራቦ"አለና አቀፈው።

የበፀሎት አለቃ "አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ" አለ።

ፅናትም "ይህን ደስታ እማ በጭፈራ ማክበር አለብን አለችና ወደ ጂፓሱ አመራች። በፀሎትም "ቆይ ሌላም ነገር አለ ወደ ካናዳ ሄጄ ነው እምታከመው እና ፅናትም ትምርትዋ አለ ስለዚህ ሊቦቲዬ ካላስቸገርኩሽ ካናዳ አብርሽኝ ልትሄጂ ትችያለሽ?" አለች። ፅናትም ወደ በፀሎት አለቃ እየጠቆመች "ቆይ እሱ አብሮሽ አይሄድም እህቴ"አለች። የበፀሎት አለቃም "አይ እኔ ትንሽ ስራ አለኝ ስጨርሽ ግን ወደ እነሱዋ እንሄዳለው"አላት።

ሊባኖስም "አሀሀሀ ገባኝ ገባኝ እሺ መቼ ነው  ምንሄደው" አለች። በፀሎትም እሚቀጥለው ሳምንት እንሄዳለን ያው በአስታማሚነት ስለምትሄድ ፓስፖርት አያስፈልግም ግን ደሞ ቢኖር አሪፍ ነበር"ስትል።ሊባኖስ "ፓስፖርት እኮ አለኝ እንደውም ካናዳም ሄጄ አውቃለው"ስትል። ያቤፅ "እኔም ሄጄ አቃለው በጣም ጥሩ ሀገር ናት"አለ። ፅናት ሊባኖሰ እና ያቤፅን እያፈራረቀች እያየቻቸው "ቆይ ምን ልታረጉ"አለቻቸው። ያቤፅ "ለጉብኝት ነበር በ15 አመቴ የሄድኩት" አላት። ፅናት "ጥሩ እሽ ሊቦ አንቺስ "አለቻት። ሊባኖስም "በልጅነቴ አባቴ ክረምት ትምህርት ሲዘጋ ይዞኝ ይሄድ ነበር"አለች።

ፅናት ፈገግ ብላ "እህህህ ለካ ሰው ሁሉ በየ ሀገሩ ይዞራል እእእእእእ አልተቻላችሁም" አለቻቸው። ሁሉም ሳቁ ፅናትም "በሉ በሉ እንጨፍራ ብላ በጂፓሱ ዘፈን ከፈተች እና ቤቱን በጭፈራ ቀወጡት በሳቅ ሞቅ አረጉት ልክ ከ ምሽቱ 4:12 ላይ የበፀሎት አለቃ ወደ ቤቱ ሄደ። ሁሉም ነበር እስከበር የሸኙት። እሱ ከሄደ በኋላ ደሞ ሊባኖስ የተቋረጠውን ቡና አፍልታ ጠጥተው ሲጨርሱ 5:05 ሆነ እና ሁሉም በየ መኝታቸው ሄደው ተኙ።

ፅናት እና በፀሎት ልክ ሁሌም እንደሚያረጉት ሊባኖስን ከመሀል አርገው ተኙ ያቤፅም ሶፋው ላይ ተኛ ለሊቱን ሁሉ በሰላማዊ እንቅልፍ አሳለፉ።

ከለሊቱ በኋላ ያሉትን ቀናቷች ያቤፅም ፅናትን እስከ ትምህርት ቤቷ በር ይሸኛታል ሲሸኛት የሚያይዋትን ወንዶች ሁሉ እየሳቀባቸው ይዝናናል ፅናትም አብራው ትስቃለች። ልክ ትምህርቱ ሲያልቅ ወደ  ካንፖስ ይሄድና ያመጣታል ሲያመጣት  ደሞ የቀን ውሎዋን ቤት እስኪደርሱ እየነገረችው ቤት ይደርሳሉ። ሊባኖስም ቤት ስለምትውል የቤቱን ስራ ሰርታ ስትጨረስ ከደመቁ ጋር ደሞ ለሚሸጡት ምግብ ይሰራሉ ከዛም ልክ 12 ሰአት ሲል ምግብ መሸጥ ይጀምራሉ። በፀሎትም ከ ፍፁም ጋር ከስራ መልስ አምሽታ 2 ሰአት ሲሆን ትመጣለች። እነ ፅናት የህይወት መንገድ በእዚህ መልኩ እያስተናገዱት ነው።

ዛሬ ማታ በፀሎት  እና ሊባኖስ
ወደ ካናዳ ሊበሩ ኤርፖርት ደርሰዋል። በፀሎት እና ሊባኖስ የበፀሎትን አለቃ ፍፁምን ፤  ፅናትን እና ያቤፅን እየተሰናበቷቸው ነው። ከሳምንት በኋላ መሆኑ ነው።እና በፀሎት ዛሬ ህይወቷ ላይ ሶስተኛ አስደሳች ለውጧን ልታደርግ ነው።

ያው የመጀመሪያው ሻርፕዋን ከፊቷ አውልቃ መንቀሳቀስዋ ነው ሁለተኛው የፍቅር ጓደኛ መያዝዋ እና ሶስተኛው ደሞ የአይን ብርሃንዋን ለመመለስ መንገድ ላይ መሆኑዋ።

ፅናት እያለቀሰች ነው። በፀሎትም እንደዛው መለያየታቸው ለትንሽ ቀናት ቢሆንም ከብዷቸዋል። ፅናት ሊባኖስን እና በፀሎትን አቅፋቸው በተራ ሳመቻቸው። ያቤፅም "በሉ በሉ ተላቀቁ እንጂ መለያየታችሁን ዘላለማዊ አታስመስሉት"አላቸው። በፀሎትም "እሺ
እሺ ያቤፅዬ በል እህቴን ላንተ አደራ ሰጥቼሃለሁ ተንከባክበክ አቆይልኝ" አለችው። ያቤፅም "እሺ አደራዬን እወጣለሁ ኧር በቃ ሂዱ" አላቸው።

ሊባኖስም "በሉ በሉ ደና ሁኑ እስክንመጣ ድረስ ተንከባከባት የሚያስፈልጋቹ ነገር ካለ ደሞ ለፍፁሜ ንገሩት ያው እሱም ወደ እኛ ይመጣል ቢሆንም ግን እስከዛ የምትፈልጉትን ነገር ጠይቁት በቃ ሰአቱ ደረሰ እኛ እንሂድ" አለችና ሊባኖስ በፀሎትን ይዛት ወደ በረራ ቦታ ሄዱ።
         .
         .
         .
ከ 150 like ቡሀላ ክፍል 38 ይቀጥላል...
👍3❤1
♥️ ፅናት ♥️...!!!
     .
     .
🥀..ክፍል 38..🥀
.
.

.
.
ፅናት አለቀሰች ያቤፅ "ፅኑ በፈጠረሽ አታልቅሺ የኔ ቆንጆ እህትሽ እኮ ለለውጥ ነው ምትሄደው" አላት። እና አቅፈዋት ፍፁም መኪና ውስጥ ገቡ። ፍፁም እየነዳ ፅናት እና ያቤፅ  ደሞ ከኋላ ቁጭ ብለው ቤታቸው ሲደረሱ ፍፁም "በሉ ቀስ ብላቹ ውረዱ ፅናት አይዞሽ አታልቅሺ በሉ ደና እደሩ " አላቸው። ፅናት እና ያቤፅም በእኩል ድምፅ እሺ ደና እደር"ብለውት ወደ ቤታቸው ገቡ።

ምሽቱን ሙሉ ያቤፅ እና ፅናት ቁጭ ብለው አመሹ። እኩለ ለሊት ላይ
ሁለቱም በተቀመጡበት ሶፋ ላይ እንቅልፍ ወስዶቸው ነጋ። ያቤፅ 12:45 ሰአት ሲል ነቃ እና ሊባኖስ ለአንዳንድ ነገር ብላ ከሰጠቻቸው ብር ላይ ወተት  እና እንቁላል ገዝቶ መጣና። እንቁላል ጠብሶ ከዛ ደሞ ወተትም አፍልቶ ካዘጋጀ በኋላ  ፅናትን ቀሰቀሳት። ፅናት ከ እንቅልፍዋ ስትነሳ ያየችውን ማመን አቃታት። "እንዴት አደረክ እንዴ ቆይ አንተ ምግብ ማዘጋጀት ትችላለህ?" አለችው።

ያቤፅም "ኣኣኣ ቆይ ታዲያ ባልችል እንዴት  አዘጋጀውት ለማንኛውም ደና አድሪያለው አንቺም ደና እንዳደረሽ ተስፍ አረጋለው በይ አሁን እረፈደብሽ ቶሎ ተነሽ እና በልተን እንሂድ" አላት። ፅናትም "እሺ መጣው" ብላ። ተጣጥባ መጣች።
ከዛም ያቤፅ እና ፅናት እንቁላሉን በእንጀራ በሉ። ያቤፅም ልክ እንደ ፅናት ዳቦ አይወድም። ሲጨርሱ ፅናት ልብስዋን ቀያይራ ወደ ካንፓስ ጉዞ ጀመሩ።

ከቤታቸው ከወጡ ጀምሮ እስከ ታክሲ መያዣው ቦታ ያቤፅ እያወራ ፅናት ዝም ብላ ነው የደረሱት። ልክ ታክሲ መያዣ ቦታው ላይ ሲደርሱ እና ቆመው ታክሲ ሲጠብቁ ግን  ያቤፅ  ተበሳጭቶ "ቆይ ምንድነው ፅኑ ኡፍ ፅኑ ኡፍ ዛሬ ደሞ እኔን ብቻ ለማስለፍለፍ ነው እንዴ አቅደሽ ከቤት ከወጣን እዚህ እስከምንደረስ ድረስ ያልቀለድኩልሽ ቀልድ የለም አንቺ ግን ሰትሄጂ ሰው ከአጠገብሽ ያለ እራሱ አይመስልም" አላት። ፅናት ፈገግ አለች። ያቤፅ "ስለዚህ ዛሬ ሊያስቅሽ እና ሊያዝናናሽ የሚችለው የኔ ብስጭት ብቻ ነው?" አላት።  ፅናትም"ባክህ ተወኝ ዛሬ ምንምምምምም መናገር ለእራሱ አልፈልግም " አለችው።

ያቤፅም "ስለዚህ ዛሬ በቃ  አትሂጂ" አላት። ፅናትም "እሺ የሆነ ቦታ እንሂዳ" አለችው። "አዎ አስታወሽኝ በይ ነይ ጥሩ የድብርት ማስለቀቂያ ቦታ  አለኝ" አላት። "የምርህን ነው እሺ ውሰደኛ" አለችው። ያቤፅም "እሺ ፅኑዬ በይ ነይ እዚሁ ቅርብ ነው በእግራችን እንሄዳለን" አላት። ትንሽ ከተጓዙ በኋላ ትልቅ የህፃናት መጫወችቻ ስፍራ በጣም ብዙ መጫወቻ ያለበት ቦታ ሲደረሱ። "በይ ግቢ" አላት። ፅናት "እንዴ እዚህ ነው?" አለችው። ያቤፅ ፈገግ ብሎ
አዎ ብሎ ወደ ውስጥ ትኬት ቆርጠው ገቡ።

ያቤፅ "ፅኑ ነይ ዥዋዥዌው ላይ ቁጭ በይ" አላት። ፅናትም ቁጭ አለች። ያቤፅ ቀበቶውን እንዳትወድቅ ካሰረላት ቡኋላ ከኋላዋ ሆኖ መጀመሪያ በቀስታ ከዛ ደሞ በሀይለኛው  እየገፋት እያለ ፅናትም ከጭንቀቷ እና ከድብርቷ እየተላቀቀች መጣች። ከዛ  ዥዋዥዊውዊውን መግፋት አቆመ ፅናት ልክ ያቤፅ መግፋት ሲያቆም በእራስዋ መንዠዋዠው ጀመረች። ከዥዋዥዌው ወርዳም እረጅም ሰአት ሸርቸቴው ላይ ከዛም ደሞ ከ ያቤፅ ጋር ሚዛን ላይ መሽሎክልኪያው ላይ ተጨወተች።

ፅናት ስለደከማት ወደ ቤት እንሂድ ብላ ወደ ቤት እየተመለሱ " ያቤፆ አመሰግናለሁ እሺ ስማኝማ የጭንቀት ማላቀቂያ አለኝ ስትለኝ ማለቴ ልውድሽ ስትለኝ ልክ ፊልም ላይ እንደምናየው ጫካ ውስጥ ወስደክ ወይም ጭር ያለ ቦታ እና ተራራ እሚታይበት ቦታ ወስደክ ጮክ ብለሽ ጩሂ ልትለኝ መስሎኝ ነበር አለችው" ያቤፅም "በቃ እንግዲ አሁን ደሞ አንቺ በተራሽ አውሪ እኔም በተራዬ ዝም ብዬ ብድሬን ልመልስ " አለና በውስጡ( በልቡ)  ፈገግ አለ። ፅናት "አታወራም እንዴ" አለችው" ያቤፅ ፀጥ ፅናት "አንተ ምን ሆነካል" ያቤፅ አሁንም ፀጥ...

ፅናት የያቤፅ ዝምታ አናደዳት "ኡፍፍ እንግዲህ ጀመረክ ቆይ ምን ልሁን ብለክ ነው ልክ እኔ ከድብርቴ ስላቀቅ አንተ ዝም እምትለው" ያቤፅ ጥሎት ቀደም ብሎ መራመድ ጀመረ። ፅናት በንዴት ጨሰች። ያቤፅ እየሳቀ ነው። ፅናት "አንተ ቆይ ምን ነክቶክ ነው?" አለችው።ያቤፅ ዝም ፅናት ይበልጥ በንዴት "ያቤፅ" አለችው። ያቤፅ እርምጃውን ገታ እና ዞር አለ። ፅናት በንዴት አይን እያየችው እንባዋ እረገፈ። ያቤፅ ደነገጠ "እንዴ ፅኑ በእናትሽ በምትወጅው ሁሉ ልለምንሽ ስታለቅሽ ማየት አልችልም ፅኑ እባክሽን አታልቅሺ" ብሎ ሁለቱን እጆቿን በእጁ ያዛቸው። ያቤፅ ፅናትን አያት እራሱን መቋቋም አልቻለም ጎትቶ ወደ ደረቱ አስጠጋት ፅናት ክው አለች ምክንያቱም የያቤፅ ደረት ከደረትዋ ተጠግቶ የልብ ምቱም ይሰማት ነበር። ያቤፅ ጥብቅ አርጎ አቀፋት።

ፅናት በልብዋ "ልክ እንደ ባለፈው ሀሳብ ባልሆነ ፤ ሀሳብ ከሆነም እረጅም ሰአት ባልነቃው" ብላ ተመኘች። ያቤፅ ፅናትን ከእቅፉ ሳያወጣት ይበልጥ እያቀፋት "ፅኑ ፅኑዬ እባክሽ ልለምንሽ ሁለተኛ ያቤፅ ብለሽ እንዳጠሪኝ"አላት። ፅናት ዝም አለች። ምክንያቱም በሚያፈቅሩት ሰው እቅፍ ውስጥ ሆኖ ሰው ሊሰማው የሚችለውን ስሜት እያጣጣመች ስለነበር ፤ ያቤፅን እስዋም አቅፋው ነበር።

ያቤፅ ፅናትን ያቀፈ እጁን ለቀቀው ፅናትም ለቀቀችው ከዛም ከ አገጭዋ ቀና አርጓት "ፅኑ" አላት። ፅናት የያቤፅን አይን አተኩራ እያየችው "ወዬ"አለችው። ያቤፅ እየተንተባተበ "ፅኑ እኔ" አላት። "አንተ ምን ያቤፆ" አለችው። በተዳከመ ድምፅ ከዛም ፅናት እራስዋን ሳተች። ያቤፅ ደገፋት ፅናትም እራስዋን ስታ ወደቀች። ያቤፅ "እርዱኝኝኝ ብሎ ጮኸ..

አንድ ባለ ላዳም "ምንነው ምን ተፈጥሮ ነው አይዞህ ተረጋጋ ና አግዘኝ እናስገባት"አለው። ያቤፅም ከባለ ላዳው ጋር ተጋግዞ ላዳ ውስጥ አስገቧትና ባለ ላዳው ቅርብ ወደሚገኘው አነስተኛ ክሊኒክ ወሰዳት። ፅናት የነቃችው አንድ ግሉኮስ ጨረሳ ነበር። ባለ ላዳውም ትንሽ ቆይቶ  ያቤፅን "በል አይዞክ ምንም አትሆንም በጣም በአስቸኳይ መሄድ አብኝ" ብሎ ሄድዋል። ያለ ማቋረጥ  "ይቅር በይኝ በፂ ይቅር በይኝ ሊባ እያለ ፅናት ግሉኮስ ጨረሳ እስክትነቃ ደረስ እየተንጎራደደ ነበር።
         .
         .
         .
ከ 150 like ቡሀላ ክፍል 39 ይቀጥላል..
❤1👍1
♥️ ፅናት ♥️...!!!
     .
     .
🥀..ክፍል 39..🥀
.
.

.
.
በመጨረሻም ዶክተሩ መጥቶ  "ገብተክ ልታያት ትችላለክ" አለው። ያቤፅ ተንገብግቦ ገባና "ፅኑዬ እባክሽን ይቅር በይኝ፤ ፅኑ እባክሽን ልለምንሽ ይቅር በይኝ" አላት። ፅናት ፈገግ ብላ "ምን አረከኝ ያቤፆ በጣም ስደሰትም እኮ አንዳንዴ እራሴን እስታለው" አለችው።
ያቤፅ ግራ ተጋብቶ "ማለት አልገባኝም ፅኑ እየቀለድሽብኝ ነው እንዴ" አላት። ፅናትም "አይ እንደሱ ሳይሆን እኔ" ስትል በሩ ተከፈቶ ዶክተሩ መጣና አሁን መውጣት  ትችያለሽ"። አለና አልጋው ጠረዝ ላይ የተቀመጠውን ያቤፅ ጀርባ መታ መታ እያረገ "አይዞህ ይገባኛል የሚያፈቅሩት ሰው አንድ ነገር ሲሆን እንኳን ቅርብ ሆነክ እሩቅ ብትሆንም ይሰማሀል" አለው። ፅናት የያቤፅን መልስ ጠበቀች ምክንያቱም ያቤፅ ሰው ያልሆነ ነገር ሲናገር ካየ ስለሚናገር ነው። ያቤፅ ግን ዝም ነበር ያለው ዶክተሩም ከክፍሉ  ወጣ።

ያቤፅም ፅናትን ቀስ እያለ ወደ ቤት ደግፎ እና ተንከባክቦ አደረሳት። ቤት ከገቡ በኋላ ያቤፅ ፅናትን ወደ መኝታ ቤት  አስገብቶ አልጋዋ ላይ አመቻችቶ ካስተኛት በኋላ ከሳሎን እሱ ለብሶት የሚተኛውን ፎጣ አምጥቶ "ፅኑዬ ይሄ ይሻልሻል ብዬ ነው። በይ እረፍት አርጊ ብሎት ከመኝታ ቤት ወጣ።

ፅናት ልክ ያቤፅ እንደወጣ ፎጣውን ወደ አፈንጫዋ አስጠግታ አይኗን ጨፈነች እና እንቅልፍ ወሰዳት።

ለብዙ ሰአት ከተኛች በኋላ ስትነቃ ያቤፅ አልጋው ፊት ለፊት በወንበር ተቀምጦ እያያት ነበር። ፅናት ስታየው ፈገግ አለች።
ያቤፅም ፈገግ አለላት። "ፅኑዬ" አላት።  "ወዬ ያቤፆ" አለችው። ያቤፅ ባዘነ ፊት እና ድምፅ "አስከፋውሽ አደል?" አላት። እጁን ወደ እስዋ እየሰደደ። ፅናትም እጁን ይዛ ጎተት አረገችው ያቤፅም የፅናትን እጅ ተከትሎ አልጋው ጠረዝ ላይ ተቀመጠና አይን አይኑዋን እያየ "ፅኑዬ" አላት። "ወዬ" ስትለው። "እሺ አሁን ምን ላርግልሽ" አላት። ፅናትም "ተረት ንገረኝ"
አለችው። ያቤፅም "እንዴ ፅኑዬ ተረት እኮ  ለህፃናት ነው ይልቅ ታሪክ ልንገርሽ" አላት።

ፅናት ፈገግ ብላ እያየችው  ድምፅዋን ለስለስ አርጋ "እና ለምን እንደ ትልቅ ሰው ካየከኝ" አለችና ዝም አለች ከዛም በውስጥዋ "ለምን ፍቅረኛሽ ልሁን ብለክ አትጠይቀኝም" አለች። ያቤፅ "ምነው ዝም አልሽ ጨረሽዋ" አላት። ፅናት ፈገግ ብላ "ማለቴ ለምን የህፃናት መጫወቻ ቦታ ይዘከኝ ሄድክ" አለችው። ያቤፅም "ፅኑዬ እኔ እኮ እዛ ቦታ ይዤሽ የሄድኩት ላስረዳሽ የምፈልገው ነገር ስለነበር ነው። ህይወትን በጨዋታ ማሳለፍ እንዳለብሽ እንድትረጂ ነው አላት። ፅናት "ማለት አልገባኝም ያቤፆ" አለችው። ያቤፅም ተመቻችቶ ከተቀመጠ በኋላ የፅናትን እጅ በሁለት እጆቹ መሀል አረጎ አጥብቆ ይዟት "እየውልሽ ፅኑዬ መጫወቻ ቦታው ውሰጥ ስንገባ የህይወት አዳራሽ ውስጥ እንደገባሽ አስቢው መጀመሪያ ዥዋዥዊው ላይ ተቀመጥሽ እና እኔ በገፋውሽ መጠን ስትንዠዋዘዊ ነበር የሆነ ሰአት ላይ መግፋቴን ሳቆም በራስሽ ሀይል መንዠዋዠው ጀመርሽ። በራስሽ እንድትንዠዋዠዊ የተውኩሽ እየቆየሽ ስትሄጂ የኔ አንቺን መግፍት ስላላረካሽ ነበር" አላት።

ፅናትም "እንዴ ታዲያ ይህን ከሂወት ጋር ምን ያገናኘዋን" አለችው። ያቤፅም ፈገግ ብሎ "ምን መሰለሽ ፅኑዬ ይህንን ወደ ህይወት ስናመጣው ደሞ የህይወት መንገዳችንን ሰው በመጠነልን መጠን ለትንሽ ጊዜ ልንኖር እንችላለን ልክ አሁን አንቺን ለተወሰነ ደቂቃ እንደገፋውሽ ነገር ግን ልክ አንቺ የኔ መግፋት እንዳላረካሽ እና ይበልጥ ከፍ ማለት እንደፈለግሽው በህይወትሽ ውስጥም ያሉ ሰዎች ጊዜ በገፍ ቁጥር አንቺ መንሳፈፍ በምፈልጊው መጠን ላያንሳፍፉሽ ይችላሉ። ማለቴ ፅኑዬ ለምሳሌ ቅድም በዥዋዥዊው ላይ ስትጫወቺ በጣም ከፍፍ ብለሽ ነበር ነገር ግን እኔ ብሆን እየገፋው እንደዛ በሀይል ያንዠዋዠውኩሽ በእርግጠኝነት ትፈሪ ነበር ይህ ደሞ ሰው ከምንም በላይ እራሱን እንደሚያምን ያሳያል" አለ።

ፅናት "እሺ ሌሎቹስ" አለችው። ያቤፅም "ሌሎችም ትርጉም አላቸው። ሚዛን ስንጫወት ካስተዋልሽ እኔ ከፈ ለማለት የግድ አንቺ ዝቅ ማለት አለብሽ ይህ የህይወትን ውጣ ውረድ እና ምን ጊዜም አንዱ ዝቅ ሲል ሊላው ከፍ እንደሚል ማንም ዝቅ ወይም ከፍ ብሎ እንደማይቀር እና ህይወት ጣእም እንዲኖርው ደስታ እንዲኖረው የግድ ከፍ እና ዝቅ ማለት እንዳለብን ያሳያል።

ሊላው እሽክርክሪት ነው አለም ነው ብለሽ ውሰጅው ለመሽከርከር የተቀመጡት ደሞ ሀገራት ናቸው። እና ሁሉም የደረሱት ቦታ  ሁሉም ይደርሳል ማለት የፈለኩት ለምሳሌ አንቺ ከአንዱ ወንበር ፊት ለፊት ብቅቆሚ ተቀምጠው የሚሽከረከሩ ሰዎች ሁሉ አንቺ ጋር ይደርሳሉ። ባንቺ ሲያልፋ አንቺ እሳት ከሆንሽ ሁሉም ይቃጠላሉ ከዛም ቀዝቃዛ ከሆንሽም አንቺን መንካታቸው አይቀረም ነገር ግን እኔ ተቃጥያለው ሊላው አይቃጠል ብሎ መፍትሄ  የሚፈልግ  ተሽከርካሪ ጋር  ሲደርስ ሁሉም ነፃ ይወጣል እሱም ተመልሶ ሲመጣ በነፃነት ባለፈበት መንገድ ያልፋል። እና ፅኑዬ ህይወትን ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ መረዳት አለብን ይህንን ነበር ላስረዳሽ የፈለኩት" አላት።

ፅናት "ውይ በጣም ጥሩ አለምን ጥሩ አርገክ ነው የተረዳካት የእውነት በጣም ጎበዝ ነክ ግን ከማንም ሳትሰማ እራስክ በእይታ የተረዳከው ነው?" አለችው። ያቤፅም "አዎ ፅኑዬ" አላት።

ፅናት በዝምታ ያቤፅን ማየት ጀመረች በፍቅር አይን  ድምፅዋንም ለስለስ አድርጋ "ቅድም ልትለኝ የነበረው ነበር" አለችው። "ያቤፅ በፅናት አይኖች ተካዳክሟል "ቅድም ልልሽ የነበርው ነገር " አላት። ፅናትም "አዎ ንገረኝ" አለችው። "ፅኑ" አላት። ወዬ አለችው። ግንባር ለግንባር ተላተሙ። "አፍቅሬሻለው የኔ ብቻ ሁኚ" አላት። ፅናት ከዛ በኋላ ቃላት ሳታወጣ ወደ ያቤፅ ከንፈር ተጠጋች እሱም ተጠጋት ሳመችው እሱም ሳማት መላቀቅ አልቻሉም አቃታቸው። ማውራት እራሱ አልፈለጉም እና በስሜት መናርን መርጠዋል።

ሳያስብት ከደቂቃዎች በኋላ የፍቅርን ልፍያ ተላፍተው ጨርሰው ተቃቅፈው ተኝተዋል። ፅናትም ያቤፅን ያቤፅም ፅናትን ለማውራት አልቻሉም ፅናት ከተንተራሰችው የያቤፅ ደረት ላይ ቀና ስትል ያቤፅ በእጁ መለሳት። ፅናት ፈገግ ብላ እዛው የያቤፅ ደረት ላይ ተኛች። ያቤፅ  በፍርሀት ድምፅ ቀስ ብሎ "ፅኑዬ" አላት። ፅናትም "ወዬ"አለችው። "ይቅርታ አድረጊልኝ" አላት። "ለምኑ"አለች ድምፅዋን እረጋ አርጋ። "ፅኑ አሁን ለተፈጠረው ነገር በእርግጥ እማልክደው ሀቅ እንደማፈቅርሽ ነው። ገና 19 አመትሽን ቀጣይ ወር  ነው የምትይዢው ግን እኔ ዛሬ እራሴን መቆጣጠር አቃተኝ ፅኑ አፈቅርሻለሁ" አላት። ፅናትም "እኔም በጣም አፈቅርሀለው የኔ ፍቅር" አለችው። ያቤፅ ደነገጠ "ማን ማነው ያልሽኝ" አላት። "የእኔ ፍቅር ነው ያልኩክ" አለችው። ያቤፅ ደስ አለው "ደግመሽ ደጋግመሽ በአሁኑ አጠራር ጥሪኝ እባክሽ ጥሪኝ " አላት። ፅናትም "ያቤፆ የእኔ ፍቅር ያቤፆ የእኔ ፍቅር አፈቅርሀለው" አለችው እና ቀና አለች እና ከ ያቤፅ አይን ጋር አይኖቿ ተገጣጠሙ በድጋሜ የፍቅርን ትግል አከናውነው ሲጨርሱ በድካም ዝለው ተኙ።

         .
         .
         .

ከ 50 like ቡሀላ ክፍል 40 ይቀጥላል...
❤3👍1
♥️ ፅናት ♥️...!!!
     .
     .
🥀..ክፍል 40..🥀
.
.

/

.
.
አመሻሽ 12:45 ላይ ያቤፅ ከ እንቅልፉ ተነሳና የሳሎኑ በረዳ ላይ መንጎራደድ ጀመረ። በደስታ ስክር ብሎዋል በሊላ በኩል ለፅናት አዝኖላታል ወደ መኝታ ቤት ገባ ፅናት ተኝታለች። ከጎኑዋ ሄደና ጋደም ብሎ እስዋን ማየት ጀመረ አይኑ በእንባ ተሞልቷል። ትንሽ ቆይታ ፅናት ከ እንቅልፍዋ ነቃች። የያቤፅን በእንባ የተሞሉ አይኖቹን እና በእንባ የረጠቡ ጉንጮቹን አየቻቸው። ፅናት እጅዋን ወደ ያቤፅ ሰደደችና እንባውን እየጠረገችለት። "ምነው? ምን ሆነካል?" አለችው። ያቤፅም "ምንም" አላት። ፅናትም "ንገረኝ አትዋሸኝ" አለችው። ያቤፅም "የደስታም የሀዘንም ለቅሶ ነው የማለቅሰው" አላት። ፅናት ግራ ገባት። "እንዴ ቆይ ምን እያልክ ነው በፈጠረክ" አለችው። ያቤፅም " ፅኑዬ እባክሽን የተፈጠረውን ነገር ለእነ በፂ እንገራቸው" አለ። ፅናትም "አይ አይሆንም ለሁሉም ጊዜ አለው" አለችው። ያቤፅ "ለነገሩ ምንስ ብዬ እናገራለው በፂዬ ሊቦዬ እባካችሁን ይቅር በሉኝ እንደ አይናችሁ ብሌን እምታይዋትን ልጅ ያለ ደንቡ እና ስርአቱ ቀሚስዋን ተዳፍሪያለው እና እንዲህ ማለቱም አሳፋሪ አደል ፅኑዬ" አላት።

በሩ ተንኳኳ ደመቁ ነበረች። ፅናት ማነው ብላ ልትነሳ ስትል መነሳት አቃታት። ያቤፅም "አንቺ አትነሺ ተኚ ደመቁ ናት እምትሆነው እኔ አናግራታለው"አለና ሄደ።

በሩን ከፈተው እንዳለውም በሩን ሲከፍት ደመቁ በር ላይ ነበረች።"አቤት ደመቁ" አላት። ደመቁም "እንዴት ናቹህ ጠዋት ስመጣ የላችሁም አሁንም ስመጣ ያላችሁ አልመሰለኝም ግን ድምፃችሁን ሰምቼ ነው ዛሬ አጋዥም ስላላገኘው ብዙ አልሰራሁም ቆይ ለፅናት ላስረዳት የት ናት"  አለችው። ያቤፅ "ትንሽ አሙዋት ተኝታለች"አላት። ደመቁም "ቆይ እስቲ ልያት" አለችና ወደ መኝታ ቤት ሄደች። ፅናት ደነገጠች። "እንዴ ደሜ" አለች። ደመቁም "ወዬ ምንሽን አሞሽ ነው እስቲ ብድግ በይ አለቻት" ፅናት በድንጋጤ ክው ብላ ቀረች።

ደመቁ ወደ እሷ  ተጠግታ "እስቲ" ብላ እጇን ወደ ፅናት ግንባር ሰደደችው።ፅናት "ደና ነኝ ደምዬ ትንሽ ሰውነቴን አሳስሮኝ ነው" አለቻት ደመቁም "ትኩሳም የለሽም በይ ተነሽና ተጣጠቢ ይለቅሻል እስክትነቃቂ እኔ ኩሽና ለገላሽ ውሀ ላሙቅልሽ እና ገላሽን በሙቅ ውሀ ስትታጠቢ ይለቅሻል እኔ እንዲ ሲያረገኝ በሙቅ ውሀ ስታጠብ ደና እሆናለሁ አንቺም ደና ትሆኛለሽ" አለቻት። ያቤፅም "አዎ ጥሩ ሀሳብ በይ አሁን ሂጂና ውሀ ጣጂላት" አላት። ደመቁም "እሺ በይ ተነሺ ብላ ፅናት የለበሰችውን ብርድ ልብስ እና አንሶላ ልትገፋት ስትል። ያቤፅ እና ፅናት ደመቁ ብለው ጮሁ። ደመቁም ተደናግጣ "እንዴ ምነው" አለች። ያቤፅም ሂጂና ውሀ አሙቂላት ሊላውን እኛ እንወጣዋለን" አላት። ደመቁም "እሺ" ብላ ወደ ኩሽና ሄደች።

የውጫ በር ተንኳኳ ያቤፅም "ፅኑ ቀለል ያለ ልብስ ለብሰሽ ሳሎን ቁጭ በይ" አላት። ደመቁ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ "ያቤፅ እስቲ እባክህ በር ክፈት " አለችው። ያቤፅም "እሺ" ብሎ በር ሊከፍት ሄደ። ፅናት በዝግታ ከ አልጋዋ ተነስታ ልብስ ቀያየረች እና ሳሎን ቁጭ አለች። ትንሽ ቆይቶ ያቤፅ መጣ "ፅኑ ደና ነሽ" አላት። "በጣም አሞኛል ያቤፆ" አለችው። ያቤፅም "እሺ ፅኑዬ ተረጋጊ እሺ ደና ትሆኛለሽ" አላት። "እሺ ያቤፆ ቆይ የት ሄደክ ነው የቆየከው?" ስትለው "በር ተንኳኩቶ ስከፍት ፓስቲ እና እፖቲቶ ገዢዎች ነበሩ እና ለእነሱ እየሸጥኩኝ ነበር" አላት። ደመቁ መጣች። "በይ ፅናትዬ ተነሽ ወደ መታጠቢያ ቤት" አለች። በር ተንኳኳ ደመቁም "ያቤፅ እኔ ፅናትዬን ወደ መታጠቢያ ቤት ልውሰዳት ምግብ የሚገዙ ሰዎች ነው የሚሆኑት" አለችው ያቤፅም "እሺ"አለና ሄደ።ደመቁ "በይ ተነሽ የኔ ቆንጆ አለቻት። ፅናት "እሺ" ደሜ አመስግናለው ብላ ብድግ ልትል ስትል መቆም እና መራመድ አቃታት። ደመቁ "እንዴ መራመድም አትችይም እንዴ ቆይ ልርዳሽ አለችና ወደ ፅናት ሄደች። እና ፅናትን ደገፈቻት። ሶፋው ላይ ደም አየች የፅናትን ልብስም አየችው ደም ነክቶታል ደመቁ "እንዴ ፅናትዬ ልብስሽ እና ሶፋው እኮ ደም ነክቶታል አሀ እንደዛ ነው ነገሩ" አለች። ፅናት ደነገጠች። "ምን ማለት ነው ምን ለማለትስ ፈልገሽ ነው" አለቻት።ደመቁም "አይይ አንቺ ልጅ እኛ ሁሉን አልፈን ነው እዚህ የደረስነው"አለች። ፅናት "አልገባኝም ቆይ ምን ለማለት ፈልገሽ ነው በፈጠረሽ አለቻት። "ደመቁም ከ ያቤፅ ጋር የተፈጠረ ነገር አለ አደል?" አለቻት።

ፅናት ደነገጠች "እንዴ ቆይ ምን እያልሽኝ ነው" አለቻት።  ደመቁም ነይ ለማንኛውም አቅምም የለሽም ገላሽን እያጠብኩሽ ሁሉን ነገር እናወራለን" ብላ ደግፋ ወደ መታጠቢያ ቤት ወሰደቻት።

ደመቁ ፅናትን "መጣው ፎጣ ላምጣልሽ" ብላ ወደ መኝታ ከመሄድዋ በፊት የሶፏውን ትራስ ገለበጠችው እና  ወደ መኝታ ቤት ገብታ የአልጋ ልብሱን  አነሳችው ያቤፅ አጮልቆ እያያት ነው።

ደመቁ በደም የተበላሸውን አንሶላ አይታ ጭንቅላቷን ይዛ "አቤት አቤት ቅሌት ገና ልጆች ናቸው ምን አስቸኮላቸው" አለች። ያቤፅ ደንግጦ በፍጥነት ከቤት ወጣ። ደመቁም ፎጣ ይዛ  ወደ ፅናት ተመለሰች።

ደመቁ ፅናትን እያጠበቻት "ስሚኝ እስቲ ግን ፈልገሽው ነው እዚህ ውስጥ የገባሽው ገና ልጅ ነሽ በዛ በላይ" አለቻት። ፅናትም "እምትይው አንዱም ነገር አልገባኝም" አለቻት። ደመቁ አተኩራ ፅናትን እያየቻት "እንዴ ቆይ የማይዋሽ እና የሚዋሽ ነገር እወቂ እንጂ እንዲ  አቅምሽን ስተሽ እና በደም ተጨማልቀሽ ያለሽውን ምክንያት እማላውቅ ይመስልሻል" አለቻት።ፅናት እያለቀሰች "እየውልሽ ለማንም ምንም እንዳትይ ይህ ነገር ባይፈጠር ደስ ይለኝ ነበር  ያቤፅም እንደዛው ግን ሳናስበው ነው ሁሉም ነገር የሆነው እባክሽ ተረጅን"አለቻት። ደመቁም "ምን ብዬ ለማን እናገራለሁ ይከብዳል"አለች።

በዝምታ ገላዋን ካጠበቻት በኋላ ደግፋ ፎጣ አረገችላትና ወደ መኝታ ቤት ወሰደቻት። ከሻንጣውም ልብስ አወጣችና የሚያስፈልጋትን ነገሮች ሁሉ አርጋላት ወደ ሳሎን ወስዳ ትልቁ ሶፋ ላይ አስተኛቻት። ወደ መኝታ ቤትም ተመልሳ የቆሸሸ አንሶላ እና ብርድ ልብሱን አውጥታ ዘፈዘፈችው። ፅናት ተሸማቀቀች የደመቁ አይን ማየት አቃታት።

ደመቁ ፅናትን ግንባርዋን ስማ "በይ አይዞሽ ፈጣሪ ያቃል ደሞ አዲስ አንሶላ እና ብርድ ልብስ ቀይሬልሻለው" ብላ ጥላት ሄደች። ደመቁ የውጪውን በር ከፍታ እንደወጣች ያቤፅ በፍጥነት ወደ ፅናት ሄደ። ፅናት ያቤፅ በሩን እንደከፈተ "የት ነበርክ ያቤፆ" አለችው። ያቤፅም በማመልከቻ ጣቱ መሀል ጭንቅላቱን እያከከ ደመቁ መኝታ ቤት እንዳያት እና ያለችውን እንደሰማ ነገራት። ፅናት "በቃ አትጨነቅ ና ቁጭ በል አለችው እና እግሯን ሰበሰበችለት። እሱም እግሯን ስትሰበስብ ያለው ክፍተት ላይ ቁጭ አለ። ፅናት እግሯን ያቤፅ ታፋ ላይ አረገች።

ያቤፅ "ፅኑዬ" አላት "ወዬ" አለችው
"ታሪክ ልንገርሽ" አላት። ፅናት " እሺ በል ንገረኝ"አለችው። ያቤፅም ከዛ በፊት ሁለት ማለት እምፈልጋቸው ነገሮች አሉ" አላት።
ፅናት "እሺ"አለችው።
         .
         .
         .

/


ከ 50 like ቡሀላ ክፍል 41 ይቀጥላል...
🤣5❤3👍1