Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
77.7K subscribers
27.8K photos
1.38K videos
27 files
10.1K links
የህዝብ ድምፅ
Download Telegram
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
Photo
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ  የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር፣ በቁጥጥራቸው ስር ባሉ ነፃ ቀጠናዎች የህዝባዊ ምክክር መድረኮችን በስኬት አጠናቀዋል ።

በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል በተካሄዱት በእነዚህ መድረኮች፣ የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ለማሸጋገር የሚያስችል ወጥ የሆነ አሰራርን በተመለከተ ከማህበረሰቡ እና ከአመራሮች ጋር በጋራ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

​በተለያዩ አካባቢዎች የተካሄዱ የውይይት መድረኮች ህዝቡ በነቂስ በተገኘበት በታላቅ ድምቀት ምክክሩ ተካሂዷል። ተሳታፊዎች የህልውና ትግሉን አስመልክቶ ሃሳባቸውን በነፃነት የገለጹ ሲሆን፣ የአፋብን የአንድነት አሰራር የአሸናፊነት ጉዞው የመጀመሪያ ምዕራፍ መሆኑን በአጽንኦት አረጋግጠዋል።

በዚህም በ​ግሼ ክላስተር (የላይኛው እና የታችኛው መንዝ ቀጠና) በወሎ ቤተ_አምሐራ ምኒልክ ዕዝ እና በሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ጥምረት በተዘጋጁ መድረኮች፣ በግሼራቤል ወረዳ ደል እና በኮረብቲት ቀበሌ የአርሶ አደሮች የውይይት መድረኮች ተካሂደዋል። በመድረኩም ማህበረሰቡ ከፋኖ ጎን ቆመን ስረዓቱን እናፈርሳለን እንጂ  ገዳያችንን አንመርጥም  ብለዋል።  በዕለቱ አርሶ አደሩ በአካባቢው የህልውና ትግል ሂደት ላይ ንቁ ተሳትፎ አድርጓል።

​የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ከአንድነት በኋላ እያሳየ ያለው ወጥ የሆነ አሰራር፣ ለህልውና ትግሉ ድል አድራጊነት ወሳኝ መሆኑ በመድረኮቹ በስፋት ተነስቷል። ማህበረሰቡ በነፃነት ባንጸባረቀው ሃሳብ መሰረት፣ የህዝብ እና የፋኖ አንድነት የድል ጉዞው የጀርባ አጥንት መሆኑን አረጋግጠዋል።

​"ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!"
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!"

​የአፋብን የሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ

ሚያዚያ 23/08/2018 ዓ.ም
👍1911🤯4🤬2😭2
በቋሪት የክርስቲያን ታደለ የአባት አርበኞች ሻለቃ ለግዳጅ ዝግጁ መሆኑን አበሰረ

ሚያዝያ 23/2018 ዓ.ም

የቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር አካል የሆነው  ቋሪት ወረዳ ጣሊያ ቀጠና የሚንቀሳቀሰውና በጀግናው ክርስቲያን ታደለ ስም የተሰየመው የአባት አርበኞች ሻለቃ፣ አደረጃጀቱን በማጠናከር ለማንኛውም ኦፕሬሽናል ግዳጅ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኑ ተገለጸ።
የሻለቃው አመራሮች እንደገለጹት፣ ሻለቃው በሰው ኃይልና በሥነ-ልቦና ራሱን እንዲያጠናክር ሰፊ ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። በዚህም መሰረት፦

▪️ወታደራዊአደረጃጀት፦ ሻለቃው በቲምና በጋንታ ደረጃ ስልታዊ በሆነ መንገድ ተዋቅሮ ለግዳጅ ዝግጁ ሆኗል።

▪️የአመራር ማሟላት፦ በሻለቃው ውስጥ የነበሩ የአመራር ክፍተቶችን ሙሉ በሙሉ በመሙላት፣ ግልጽ የሆነ የዕዝ ሰንሰለት ተፈጥሯል።

▪️ቅንጅታዊ አሰራር፦ ሻለቃው ከቀጠናው የዐፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 33ኛ ክፍለ ጦር 4ኛ ሻለቃ ጋር በቅርበት እንዲተሳሰር ተደርጓል።

ይህ የተጠናከረ ዝግጅት የሕዝቡን ደህንነት ለማስጠበቅና የሚሰጡትን ተልእኮዎች በብቃት ለመወጣት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተስፋ ተጥሎበታል።

©️102ኛ ኮር 33ኛ ክፍለ ጦር ህዝብግንኙነት
30👍12🔥12👏3🥰2
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
Photo
#የአሳምነው_ልጆች_በሸዋ_በአይነቱ_ለየት_ያለ_ድል_ተቀዳጁ‼️

ሚያዚያ 24/2018ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባላ ክፍለ ጦር የአገዛዙን ወራሪ ኃይል በመደምሰስ ከፍተኛ ድል ተቀዳጅቷል።

በትላንትናው ዕለት ሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም የነበልባል ክፍለ ጦር ምኒልክ ሻንበል የፋኖ አባላቶች በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ወረዳ ልዩ ቦታው በሙክየ ሀሮ ቀበሌ በሰፈረው የኦሮሚያ ሚሊሻ ላይ ድል ተቀዳጅቷል።

ይህ ሀይል እነ ሽመልስ አብዲሳ ስውር የጥፋት ተልዕኳቸውን በአማራ ህዝብ ላይ ለመፈፀም ያዘጋጁት እንደሆነ ከተያዩ የክልሉ አካባቢዎች ከተወጣጡ ከምርኮኞች አንደበት ማረጋገጥ ተችሏል።

በተጨማሪም በአካባቢው ሰፍረው በቆዩባቸው ቀናቶች በማህበረሰቡ ላይ የተለያዩ ግፎችንና በደሎችን ሲያደርሱ እንደነበርም ለጊዜው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰቦች እንዲህ በማለት አጋርተውናል።

1ኛ. ከ 70 በላይ የሚሆን የአካባቢውን ማህበረሰብ ቁጥሩን ለማሳሳት አስረዋል የት እንዳደረሳቸውም አይታወቅም ሲል ተናግሯል።

2ኛ. በአካባቢው አማራ አይኑር የተባለ እስኪመስል የተገኘውን ሁሉ ድብደባ "ዘረፋ"የሴቶች አስገድዶ ደፈራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል።

3ኛ. በስብሰባ ሰበብ ሴቶችንና ህፃናትን በመሰብሰብ ብዙ ጊዜ ምክንያቱ ባልታወቀ ነገር በመመረዝ እንዲታመሙ ተደርገዋል በዚህም መቋቋም ያቃታቸው ህፃናት እንደሞቱ አስረድቶናል።

ታዲያ በዚህ ሰቆቃና በደል ውስጥ በሀይል ለማኖር በማሰብ ከተለያየ ቦታ በአፈሳ አምጥቶ ያሰፈራቸውን ከ67 በላይ የሚሆኑ የኦሮሚያ ሚሊሻ ለወሬ ነጋሪ ሳይቀሩ በነበልባል ክፍለ ጦር በምኒልክ ሻምበል ፋኖ አባላቶች ተደምስስዋል ።

👉በእዚህም አውደ ውጊያ የተገኙ ድሎች‼️

1ኛ. 25 ክላሽ
2ኛ. 50 ካዝና
3ኛ. 150 የክላሽ ተተኳሽ
4ኛ. 25 የወገብ ትጥቅ
5ኛ. 7 ምርኮኛ
6ኛ. የተደመሰሱ 60 በላይ

በተየያዘ ዜና የኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር 3ተኛ ሰላም ሰው ሻለቃ በኦሮሚያ ክልል ሀሙሥ ገበያ አቅራቢያ ልዩ ቦታው ዘንጎ ኪዳነ ምህረት ተብሎ ከሚጠራው የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ምሸግ ላይ በመግባት መብረቃዊ ጥቃት በማድረሥ 8 ሙትና 4 ቁሥለኛ ሆኗል።

ድል ለተገፋው የአማራ ህዝብ‼️
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!

የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ

ሚያዚያ 24/2018ዓ.ም
48🔥5🤬5🙏4😢3😱2😭2
የብልፅግና የሀሰት ምርጫ ቅስቀሳና የምርጫ ካርድ እደላ ሳይሳካ ተበተነ!

ሚያዚያ:-24/2018ዓ/ም

አፋብን ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር በግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ ውስጥ ጨፍጫፊው ብልፅግና ለሚያደርገው የውሸት ምርጫ በቀን 24/08/2018 ዓ.ም ቅዳሜ ለገበያ የሔደውን ህዝብ በግዴታ የምርጫ ካርድ ውሰዱ በሚል በሶስት ቦታዎች ማለትም አዲስ ፋና ትምህርት ቤት፣ሙጃ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና መጋዘን ላይ ባዘጋጀው በግድ ካርድ ውሰዱ የሚል ህብረተሰቡን ሰላም የመንሳት ዕቅድ አስቦ ቢሰራም ጀብደኞቹ የ14ኛ ክፍለ ጦር ሰርጎ ገቦች እንዲበተንና ያሰበውን ሳያሳካ ቀርቷል።

በኦፕሬሽኑም አራት የመከላከያ አባላት ሙት ከአምስት በላይ ቁስለኛ ሆነዋል ።
በዚህ የተናደደው የአብይ ስልጣን አስጠባቂ ሰራዊት ሞርተር 120 በመወርወር መላው የግዳንን ማህበረሰብ ሲያሸብር ውሏል።ለበዓል ገበያ የሔደውን ህብረተሰብም ድንጋጤ ውስጥ እንዲገባና ከተማው ምስቅልቅሉ እንዲወጣ ሲያደርግ አርፍዷል።

ህዝብን በውሸት እያታለለ ስለምርጫ እየደሰኮረ ያለው ብልፅግና ምርጫው እንደማይሳካለት እየተረዳ በመምጣቱ ተስፋ ስለቆረጠ በግዴለሽነት ህዝብን ለመጨፍጨፍ በመዘጋጀት ላይ ያለ ይመስላል ።በመሆኑም ይህንን አስከፊ ስርዓት አምርረን በመታገል የድል ፅዋን መጎንጨት ያስፈልጋል ።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል መረጃውን የ14ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ አድርሷል ።

አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ:- 24/2018 ዓ/ም
20🥰5🤯2
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
Photo
206ኛ ኮር ከስናን ወረዳ ብቁ ወጣቶች ጋር 

በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!
በሚል መሪ ቃል በምስ/ጎጃም ስናን ወረዳ ደብር ወለቄ ቀጠና የወጣቶች መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ሚያዚያ 24/2018 ዓ.ም
=======================================
ከአፋብን በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት 206ኛ ኮር በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች የወጣቶች የውይይት መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ተካሒደዋል። የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ጫፍ ለማድረስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት የሚያስችል ሰነድ በመድረኩ ቀርቧል።

በምስራቅ ጎጃም ስናን ወረዳ ወለቄ ቀጠና እንዲሁ ህዝባዊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ወጣቶች ተሳታፊ ሁኗል።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
10👍1
ሰበር የድል ዜና!!!

በቋራ ወረዳ ቁጥር-2 ላይ የአገዛዙ ጥምር ሀይል ከፍተኛ ሽንፈትን አስተናገደ!!!

በትናንትናው እለት ሚያዚያ 23/2018 የአገዛዙ ጥምር ሰራዊት መነሻውን በሶስት አቅጣጫ ማለትም ከቁጥር-4፣ ሽንፋ፣ ቱመትና ዱባባ በማድረግ ወደ ቁጥር-1 በመጓዝ ላይ እያለ ረመጦቹ የበረሀው ፈርጦች አፋብን በላይ ዕዝ መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር ካራማራ ክ/ር በአርበኛ አጠቃ ሞገስ በተሰጠ ስምሪት፤ ጠላት ካሰበው ቦታ ቁጥር-1 ሳይደርስ ቁጥር-2 ላይ ከቀኑ 9:00_10:30 ገደማ ባላሰበው መንገድ ቀድሞ በተሰራ ኦፕሬሽን አናብስቶቹ ድል ቀንቷቸዋል።

በአማራ ህዝብ ላይ እንደ አሻንጉሊት የሚጫዎተው የአብይ አህመድ እና የምስለኔዎቹ የምርጫ መርሀግብር ድራማዊ ተውኔት ተፈፃሚነቱ የህልም እንጀራ ሆኖበት ምንም ማድረግ ሳይችል ከፍተኛ ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ ሀዘንተኛ ሆኖ ሁሉም ወደ መጣበት ሊመለስ ችሏል ሲል የካራማራ ክ/ር የህ/ግ አርበኛ ቴዎድሮስ ይግዛው ከስፍራው አድርሶናል።

በጥቅሉ ቀጠናው ላይ የአገዛዙ አሸርጋጅ ሰራዊትና የብልፅግና አሽከሮች ጥርስ የሌለው አንበሳ ሆነዋል። በየጊዜው በሚደርስባቸው ሽንፈት ፣ ሰራዊቱም በሚያዋጣው መንገድ ከአሀዱ እየወጣ እየኮበለለ፤ ለፋኖ ትጥቁን እያስረከበ በሰላም ወደ ቤተሰቡ የሚሄደው እና መሰል የስርአቱ መቃዎስ በአጉል ምኞት የአገዛዙን እድሜ ለማስረዘም የሚጣጣረው የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮችና የአብይ አህመድ ድቅሎች ከፍተኛ የራስ ምታት ላይ ይገኛሉ።

በአውደውጊያው የተገኘ ድል: በመጣበት አስር ጎማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው አስክሬኑንና ቁስለኛውን ይዞ ተመልሷል።

ኀልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!

አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር የህ/ግ
     ሚያዚያ 24/2018