ሐበሻ ኢስላሚክ ሚድያ
2.15K subscribers
697 photos
85 videos
78 files
1.49K links
قال الله تعالى ( وَلَا تَلْبِسُوا الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُوا الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ )البقرة (42)

አሏህ በእርግጥም አለ፦[እውነትን በውሸት አትሸፍኑ እናንተ እውነታውን እያወቃቹህ]

ምንጭ፦«ሱረቱ አል–በቀራህ አንቀፅ /42/


በኡስታዝ ሐምዛ
[አሰዱሏህ]
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
♦️ فضل قراءة قصة المولد
๏ የነብዩን የውልደት ቀን ታሪክ መቅራት የሚያስገኘው ትሩፋት፥

قال السيوطي في كتاب "الوسائل في شرح الشمائل": "ما من بيت أو مسجد أو محلة قرئ فيه مولد الرسول إلا حفت الملائكة بذلك المكان وعمهم الله بالرحمة. والملائكة يدعون لهم بالخير. وما من مسلم قرئ في بيته مولد النبي إلا رفع الله  القحط والوباء والحرق والآفات والبليات والنكبات والبغض والحسد وعين السوء واللصوص عن أهل ذلك البيت. فإذا مات هون الله عليه جواب منكر ونكير. وكان في مقعد صدق عند مليك مقتدر. لأنه يظهر الحب والفرح لسيدنا محمد صلى الله عليه وسلم.


๏ ኣል–ኢማሙ ኣ·ስዩጥዩ እንዲህ ይላሉ፦

"የነብዩ ዓለይሂ ሶሏቱ ወሰላም መውሊድ የተቀራበት የሆነ የትኛውም ቤት፣መስጂድ አልያ አካባቢ የለም  መላኢካ የከበበችው እንዲሁ አሏህ ራህመቱን ያወረደባቸው ቢሆን እንጂ።መላኢካዎች በደጋግ ነገራቶች ፀሎት ያደረጎላቸው ይሆናሉ።አንድም ሙስሊም ቤት መውሊድ የተነበበ አይሆንም አሏህ ከዛ ቤት ድርቅን፣በሽታን፣መንደድን፣ ጥፋቶችን፣አደጋዎች፣ጭንቀቶችን፣ጥላቻን፣ምቀኝነትን፣መጥፎ አይንን እንዲሁ ሌባን ከዛ ቤተሰብ ያነሳላቸው ቢሆን እንጂ።ያ ሰው ቢሞት አሏህ የነኪይርና ሙንከርን ጥያቄ ያገራለት ይሆናል።ምንም የማይሳነው ቻዩ ጌታ አሏህ ይህን ሰው አመፀኞች በማይሆኑበት የእውነተኞች የመቀመጫ ቦታ  ላይ ያደርገዋል።ምክነያቱም በመልዕክተኛው የውልደት ቀን  ውዴታን እንዲሁ ደስታውን ይፋ ስላወጣ"።

ምንጭ፦<ኣል–ወሳኢል ፊ ሸሪሒ ኣ·ሸማኢል>።

HAMZA
..........ASEDULLAH
14🥰4👍1
عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضِيَ اللهُ عَنْهُ خَادِمِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: " إِنَّ أَقْرَبَكُمْ مِنِّي يَوْمَ الْقِيَامَةِ فِي كُلِّ مَوْطِنٍ أَكْثَرُكُمْ عَلَيَّ صَلَاةً فِي الدُّنْيَا، مَنْ صَلَّى عَلَيَّ فِي يَوْمِ الْجُمُعَةِ وَلَيْلَةِ الْجُمُعَةِ قَضَى اللهُ لَهُ مِائَةَ حَاجَةٍ، سَبْعِينَ مِنْ حَوَائِجِ الْآخِرَةِ وَثَلَاثِينَ مِنْ حَوَائِجِ الدُّنْيَا ". أخرجه البيهقيُّ (شعب الإيمان)

اللَّهُمَّ صلِّ وسلِّم على سيد الأنبياء محمد وعلى آله وصحبه وسلم

☞የነቢዩ ﷺ ኻዲም "አነስ ኢብኑ ማሊክ" ረዲየሏሁ ዓንሁ እንዳስተላለፉት መልዕክተኛው ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል አሉ፦

«በየትኛውም ቦታ በትንሳኤው ቀን ለኔ ቅርቡ በዱንያ ሳለ በኔ ላይ አብዝቶ ሶለዋት ያወረደው ነው።በጁሙዓህ ሌሊት (ኸሚስ ማታ)እና በእለተ ጁሙዓህ በኔ ላይ ሶለዋት ለሚያወርድ አሏህ መቶ ጉዳዬችን ያሳካለታል፣ሰባ ያክሉ አኼራዊ ጉዳይ ሲሆኑ ሰላሳው የዱንያ ሃጃ ነው። አሏህም ለዚሁ ጉዳይ ከመላኢካዎቹ ይመድባል፣ በህይወት ያሉት ለሟቾች የሚልኩትን ስጦታ(ዱዓ፣ኢስቲግፋር፣ ቁርአን፣ሶደቃ) ወደ ቀብራቸው እንደሚያስገባላቸው ሁሉ ያስገባላቸዋል። በኔ ላይ ሶለዋት ያወረደውን ሰው ስም፣ዘርና ጎሳውን ሳይቀር መላኢካው ለኔ ይነግረኛል፣እኔም ነጭ ብራና ላይ አሰፍረዋለሁ»

ምንጭ፦(፣ሹዐቡል ኢይማን ሊል’በይሃቅይ)

Hamza
asedullah
👍96
√ ምልከታ ይሻል! ሙዚቃ ሓላል ነው የሚሉ ሰዎች አልያ ይህን የመሰለ ነገር ስናይ የነብዩ ዓለይሂ ሶሏቱ ወሰላም እውነተኝነት የበለጠ ውስጥህ ላይ በበለጠ መልኩ እያደገ ብሎም እየጎላ ይመጣል።

دليل من الحديث على تحريم الموسيقى المحرمة
√ ከነብዩ ሓዲስ ሙዚቃ ክልክል እንደሆነ ማስረጃው፦
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
"صوتانِ ملعونانِ في الدُّنيا والآخرةِ مزمارٌ عندَ نعمةٍ ورنَّةٌ عندَ مصيبةٍ".

⇏ የአሏህ መልዕክተኛ ዓለይሂ ሶሏቱ ወሰላም እንዲህ ይላሉ፦"ሁለት ድምፆች በዱንያም በቀጣይኛው ዓለምም የተረገሙ ናቸው።
የደስታ ግዜ ዋሽንት መንፋትና የአደጋ ግዜ ሆን ብሎ መጮህ"።ናቸው።

عَنْ أَبِي عَامِرٍ الْأَشْعَرِيِّ رَضِيَ اللهُ عَنْه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: "لَيَكُونَنَّ مِنْ أُمَّتِي قَوْمٌ يَسْتَحِلُّونَ الْحِرَ وَالْحَرِيرَ وَالْخَمْرَ وَالْمَعَازِفَ" أَخْرَجَهُ الْبُخَارِيُّ

⇏ ከኣቡ ዓሚር ኣል–ኣሽዓርይ እንደተዘገበው የአሏህ መልዕክተኛ ዓለይሂ ሶሏቱ ወሰላም እንዲህ አሉ፦"ከኡመቴ የሆኑ ዝሙትን፣ሓሪይር መልበስን¹፣አስካሪን መጠጣት እንዲሁ የሙዚቃ መሳርያን የሚፈቅዱ የሆኑ ሰዎች ይመጣሉ"።

ምንጭ፦ኣል–ኢማሙ ኣል ቡኻርይ።

ማለትም፦ለወንዶች።
ነገር ግን ሴቶች መልበስ ይበቃላቸዋል።

HAMZA
...ASEDULLAH
13
☜ قيل للإمام الشافعى: يا إمام دلنا على واجب وأوجب ؟ وعجيب وأعجب ؟ وصعب وأصعب ؟ وقريب وأقرب ؟
๏ ኣል–ኢማም ኣ·ሻፍዕይ እንዲህ በመባል ተጠየቁ፦"ኢማም ሆይ ግዴታ ስለሆነብን እንዲሁ የበለጠ ግዴታ ስለሆነብን? አስገራሚ ስለሆነው እንዲሁ እጅጉን በጣም አስገራሚ ስለሆነው? ከባድ ስለሆነው እንዲሁ እጅጉን ከባድ ስለሆነው? ቅርብ ስለሆነው እንዲሁ እጅጉን በጣም ቅርብ ስለሆነው ነገር ይንገሩን" በማለት የጠየቋቸው ግዜን እርሳቸውም እንዲህ በማለት መለሱ፦…

قال: واجب الناس أن يتوبوا ولكن ترك الذنوب أوجب ...
√ [ሰዎች ንስሃ ሊገቡ ዘንዳ ግዴታ ሲሆን: ሓጢያትን መተዋቸው ደግሞ የበለጠ ግዴታ ይሆንባቸዋል]።

والدهر فى تصرفه عجيب وغفلة الناس عنه أعجب ...
√ [ግዜ የሚያስተናግዳቸው ነገሮች የሚያስገርሙ ሲሆን: ሰዎች ደግሞ ከዛ ነገር ዝንጉ መሆናቸው በጣሙን የሚያስገርም ነው]።
والصبر عند المصائب صعب ولكن فوات الثواب أصعب ...
√ [በአደጋ (ፈተና) ግዜ ትዕግስት ማድረግ ከባድ ሲሆን: ነገር ግን በትዕግስታችን ሰበብ የሚሰጠንን ምንዳ ማጣቱ እጅጉን የከበደ ነው]።
وكل ما تتمنى قريب والموت من دون ذلك أقرب .
√ [የምትመኘው ነገር በብዛት ቅርብ ሆኖ ታገኘዋለህ:ነገር ግን ሞት ደግሞ እጅጉን ካንተ የቀረበ ነው]።

~HAMZA
....ASEDULLAH
10
عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضِيَ اللهُ عَنْهُ خَادِمِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: " إِنَّ أَقْرَبَكُمْ مِنِّي يَوْمَ الْقِيَامَةِ فِي كُلِّ مَوْطِنٍ أَكْثَرُكُمْ عَلَيَّ صَلَاةً فِي الدُّنْيَا، مَنْ صَلَّى عَلَيَّ فِي يَوْمِ الْجُمُعَةِ وَلَيْلَةِ الْجُمُعَةِ قَضَى اللهُ لَهُ مِائَةَ حَاجَةٍ، سَبْعِينَ مِنْ حَوَائِجِ الْآخِرَةِ وَثَلَاثِينَ مِنْ حَوَائِجِ الدُّنْيَا ". أخرجه البيهقيُّ (شعب الإيمان)

اللَّهُمَّ صلِّ وسلِّم على سيد الأنبياء محمد وعلى آله وصحبه وسلم

☞የነቢዩ ﷺ ኻዲም "አነስ ኢብኑ ማሊክ" ረዲየሏሁ ዓንሁ እንዳስተላለፉት መልዕክተኛው ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል አሉ፦

«በየትኛውም ቦታ በትንሳኤው ቀን ለኔ ቅርቡ በዱንያ ሳለ በኔ ላይ አብዝቶ ሶለዋት ያወረደው ነው።በጁሙዓህ ሌሊት (ኸሚስ ማታ)እና በእለተ ጁሙዓህ በኔ ላይ ሶለዋት ለሚያወርድ አሏህ መቶ ጉዳዬችን ያሳካለታል፣ሰባ ያክሉ አኼራዊ ጉዳይ ሲሆኑ ሰላሳው የዱንያ ሃጃ ነው። አሏህም ለዚሁ ጉዳይ ከመላኢካዎቹ ይመድባል፣ በህይወት ያሉት ለሟቾች የሚልኩትን ስጦታ(ዱዓ፣ኢስቲግፋር፣ ቁርአን፣ሶደቃ) ወደ ቀብራቸው እንደሚያስገባላቸው ሁሉ ያስገባላቸዋል። በኔ ላይ ሶለዋት ያወረደውን ሰው ስም፣ዘርና ጎሳውን ሳይቀር መላኢካው ለኔ ይነግረኛል፣እኔም ነጭ ብራና ላይ አሰፍረዋለሁ»

ምንጭ፦(፣ሹዐቡል ኢይማን ሊል’በይሃቅይ)

Hamza
asedullah
8
مسألة مفيدة وهي إن كان الشخص يمشي في الجنازة يستحب أن يذكر الله تعالى سرا، يعني أن لا يجهر بالذكر إلا إذا كان سبب،
ጠቃሚ ነጥብ፦
๏ [አንድ ሰው ሬሳን ተከትሎ እየተጓዘ ከሆነ አሏህን ድምፁን ቀንሶ ማውሳቱ የተወደደ ነው።ማለትም አሏህን ሲያወሳ ድምፁን ከፍ አለማድረጉ የበለጠ ነው።ድምፁን ከፍ  ለማድረግ ምክነያት እስከሌለው ድረስ ማለት ነው]።
الفقهاء يقولون: إذا كان سبب يجهر، كان مثلا جهر الماشون في الجنازة يكون مانعا للناس من الوقوع في الغيبة،لأن بعض الناس الماشون في الجنازة يغتابون الميت.
√ ፉቅሃኦዎች እንዲህ ይላሉ፦"አሏህን ለማውሳት ድምፁን በዚህ ግዜ ከፍ ለማድረግ ምክነያት ካለው ከፍ ያድርግ።ከነዚህም ምክነያቶች መሀከል ሰዎች አሏህን ሲያወሱ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በማውሳታቸው ማቹን አልያ ሌላን ሰው በማማት የተጠመዱ ሰዎች ከዛ ስራቸው እንዲቆጠቡ ለማድረግ ከሆነ የመጠላቱ ፍርድ ይነሳል።ምክነያቱም አንዳንድ ሰዎች በዚህ ግዜ ሟቹን ስለሚያሙት ነው]።
الأَحْسَنُ لِلْمَاشِي فِي الْجِنَازَةِ أَنْ يَذْكُرَ اللهَ بِلا جَهْرٍ، إِلَّا إِذَا كَانَ سَبَبٌ لِلْجَهْرِ، فَالْأَحْسَنُ الْجَهْرُ.
وَهَذَا السَّبَبُ، هُوَ الَّذِي ذَكَرْنَاهُ، أَنَّهُ يَكُونُ حَاجِزًا لِلنَّاسِ حَتَّى لَا يَقَعُوا فِي نَحْوِ الْغِيبَةِ.
☞[ነገር ግን ሟችን ተከትሎ ለሚሄድ ሰው በላጩ ከዚህ ውጭ ማለትም ምክነያት ከሌለው አሏህን እራሱ በሚሰማው ያህል እያወሳ መጓዙ (መከተሉ) ነው።ነገር ግን ምክነያት ካለው ሲቀር በዛ ሰኣት ከፍ አድርጎ ማውሳቱ ደግሞ በላጭ ነው።የተጠቀሰውም ሰበብ እርሱን የመሰለ ከሆነ ነው ከፍ አድርጎ አሏህን ማውሳት የተሻለ ሚሆንበት ግዜ።ምክነያቱም ሰዎች ሓራም የሆነ ሀሜት ላይ ከሚወድቁ ይህ ከልካይ ስለሚሆናቸው ማለት ነው]።

HAMZA
....ASEDULLAH
7
مَا هِىَ الصَّلَوَاتُ السِّرِيَّةُ وَالصَّلَوَاتُ الْجَهْرِيَّةُ.
ድምፅ ዝቅ እንዲሁ ድምፅ ከፍ የሚደረግባቸው የሶሏት አይነቶች የትኞቹ ናቸው?

الصَّلَوَاتُ السِّرِيَّةُ هِىَ الظُّهْرُ وَالْعَصْرُ وَالصَّلَوَاتُ الْجَهْرِيَّةُ هِىَ الْمَغْرِبُ وَالْعِشَاءُ وَالصُّبْحُ وَيَجْهَرُ بِهَا الْمُنْفَرِدُ وَالإِمَامُ فِى الرَّكْعَتَيْنِ الأُولَيَيْنِ فِى قِرَاءَةِ الْقُرْءَانِ وَقَوْلِ ءَامِين. أَمَّا مَنْ أَرَادَ أَنْ يَقْضِىَ صَلاةً جَهْرِيَّةً فِى وَقْتِ صَلاةٍ سِرِيَّةٍ كَالصُّبْحِ فِى وَقْتِ الظُّهْرِ أَوْ أَرَادَ أَنْ يَقْضِىَ الصُّبْحَ قَبْلَ أَنْ يَدْخُلَ وَقْتُ الظُّهْرِ فَإِنَّهُ يُسِرُّ بِهَا.
๏ ድምፅ ዝቅ ተደርጎ የሚቀራባቸው የሶሏት አይነቶች ኣ·ዙህሩ እና አል–ዐሱር ሲሆኑ ድምፅ ከፍ ተደርጎ የሚቀራባቸው ሶሏቶች ደግሞ አል–መግሪብ፣ አል–ዒሻእ እንዲሁ ኣ·ሱብሒ ናቸው። በነዚህ ድምፅ ከፍ ተደርጎ በሚቀራባቸው ሶሏቶች ላይ ለብቻው የሚሰግድ ሆነ ኢማምም ቢሆን በመጀመርያዎቹ ሁለት ረከዐተይኒዎች ላይ ቁርኣን ሲቀራም ሆነ ኣሚይን ሲል ድምፁን ከፍ ያደርጋል ማለት ነው።ነገር ግን እነዚህ ድምፅ ከፍ ተደርጎ የሚቀራባቸውን ሶሏቶች አንዳቸው አምልጠውት ድምፅን ዝቅ ተደርጎ በሚቀራባቸው የሶሏት ወቅቶች ግዜ ላይ ቀዷእ ሚያወጣ ከሆነ ለምሳሌ የሱብሒ ሶሏትን በዙህር ወቅት የመሰለ አልያ የሱብሒን ወቅት ሶሏት ዙህር ከመግባቱ ፀሀይ ከወጣች ቡሀሏ ቀዷእ የሚያወጣ ከሆነ በዚህ ግዜ ድምፁን በመቀነስ ነው የሱብሒውን ሶሏት ቀዷእ የሚያወጣው ማለት ነው።

  وَالْمَرْأَةُ تَجْهَرُ فِى مَوْضِعِ الْجَهْرِ إِنْ لَمْ يَحْضُرْهَا أَجْنَبِىٌّ.
ሴት ልጅ ድምፅ ከፍ ተደርጎ በሚቀራባቸው ሶሏቶች ላይ ባዳ ወንዶች ከሌሉ ከፍ በማድረግ ትቀራለች።

HAMZA
...ASEDULLAH
9