ASD AJ LAH
760 subscribers
1.8K photos
197 videos
3 files
513 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብ (ኦንላይን) ከሚሰጥባቸው ከተሞች አንዱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስለመሆኑ ተሰምቷል።

ይህን ተከትሎ የፈተና ቅድመ ዝግጅት ተግባራት ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ ሲካሄድ ውሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊው ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፤ " የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በከተማው በኦንላይን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው " ብለዋል።

ለፈተናው ኮምፒዩተሮች፣ ላፕቶፖችና ታብሌቶችን ጨምሮ ሌሎች ግብአቶችን የማሟላት ስራ ተጀምሯል ተብሏል።

የግል ትምህርት ቤቶች ለፈተናው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ከወዲሁ እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ማሳወቁ ይታወሳል።

ሙሉ በሙሉ ፈተናው በኦንላይን ባይሰጥም  በተመረጡ ከተሞች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የቀሩት ተማሪዎች በተለመደው ሁኔታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በወረቀት ይፈተናሉ።

እስካሁን በየትኞቹ ከተሞች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች ፈተናውን በኦንላይን ይወስዳሉ የሚለው አይታወቅም። በምን አግባብ ተማሪዎቹ እንደሚመረጡም ለጊዜው በይፋ የሚታወቅ ነገር የለም።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia