ASD AJ LAH
668 subscribers
1.71K photos
192 videos
3 files
483 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
ASD AJ LAH
Photo
አንዳንድ ሰዎች እልም ጥፍት ብለው ይቆዩና ድንገት መጥተው ሳይቆዩ በድጋሚ እልም ጥፍት ይሉባቹሃል ። አላህን የሚፈሩት (ተቂይ) የሆኑት ላላችሁ ኒዕማ ማሻ አላህ ብለው ለገጠማችሁ ችግር እንደናንተው ተጨንቀው በዱዓ ያስቧቹሃል ። ዳግም የሚመጡትም ከነገሩ ጋር ቀጥለዋል ወይስ ተፈርጀዋል የሚለውን ለማወቅ ሲሆን ሌሎቹ ምን ላይ እንደሆናችሁ ለማወቅ ብቻ ነበር ወደ እናንተ የሚመጡት ። « በልጠውኛል ? ፣ ከእኔ የተሻለ ህይወት ላይ ናቸውን » ይህን ለማወቅ ብቻ 🙂

***
ይጠግኑልኝ ይሆን ብላችሁ የነገራችኋቸውን ስብራት ይባስ እንዳይጠገን አድርገውት ይሄዳሉ ። ህመማችሁን ፣ ችግራችሁን ዋጥ አድርጋችሁ :- « እንዳይደብራችሁ ! አልወደቅንም ፣ አልተሰበርንም አንላችሁም ; ከወደቅንበት ግን አልቀረንም እንደተሰበርን አልኖርንም አላህ አንስቶናል ። ነፍሳችንን ለአላህ ሰጥተናል በሏቸው ። መኽሉቅ ዘንድ ኻሊቁን እንዳንከስ አደራ ። የሰብር ትርጉም ይህ ነውና በምስጋና ቻል በማድረግ እንለፍ ።

አብዱ ረዛቅ

መልካም ውሎ
ሰውነታቸው በጥይት አካላቸው በእሳት አሩር እየተጠበሰ "አላሁ አክበር" የሚለውን መፈክር ደግመው ደጋግመው የሚያሰሙ ፅኑዎች

ሞት ሲያንዣብብ ከበራቸው በ"ላኢላሀ ኢለላህ" ህይወታቸውን የሚቋጩ ልጆቻቸው ከስማቸው ይልቅ የጌታቸውን ስም እንዴት መጥራት እንዳለባቸው የሚያውቁ ትውልዶች

አዎ
መላእክት ክንፎቻቸውን የዘረጉባት ሀገር የተባረከች የፍልስጤም ምድር። የእምነት ጽናትን የጨበጡ ፍጡሮች መፍለቂያ እንደ አለት የጠነከረ እምነት ባለቤቶች
ኢማን ኢማን የሚሸትበት ወንድ ተፀንሶ ጀግና የሚወለድባት የሙጃሂዶች መፍለቂያ

እናንተ የፍልስጤም ህዝቦች ሆይ ታገሱ


Mahi mahisho
ከሶፍ ውጭ ለብቻ መቆም
~
ሶፍ ሳይሞላ ለብቻ መቆም ክልክል ነው። ነብያችን ﷺ እንዲህ ይላሉ፦
እንዲህ ብለዋል፦
لا تصح صلاة المنفرد خلف الصف
"ከሶፍ ኋላ ተነጥሎ ለሚሰግድ ሰው ሶላት የለውም።" [አሕመድ፡ 15862]

ስለዚህ:-
1- ሶፍ ያልሞላ ከሆነ ለብቻ መቆም በጥብቅ የተከለከለ ነው።
2- ሶፉ የሞላ ከሆነ፣ ዘርዘር ብለው በመሰለፋቸው ሳያስቸግር የሚያስገባው ክፍተት ካገኘ አጠጋግቶ ይግባ።
3- የሚያስገባው ክፍተት ከሌለ ብቻውን ቆሞ ይሰግዳል። አላህ እንዲህ ይላል፦
{ فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ مَا ٱسۡتَطَعۡتُمۡ }
"አላህንም የቻላችሁትን የክል ፍሩት።" [አተጋቡን፡ 16]

ከዚህ ውጭ ሶፍ ላይ ያለን ሰው ወደ ኋላ መሳብ አይቻልም። ምክንያቱም ይህንን የሚደግፍ ሶሒሕ ማስረጃ የለምና። በዚህ ላይ የሚጠቀሰውም ሐዲሥ ደካማ ነው። በዚያ ላይ ከሶፍ አውጥቶ ወደ ኋላ መጎተት ጥፋቶች አሉበት።
* ሰውን መወስወስ አለበት።
* የሚሳበውን ሰው የተሻለ ደረጃ ካለው ፊተኛው ሶፍ ዝቅ ማድረግ አለበት።
* የፊተኛው ሶፍ ላይ ክፍተት መፍጠር አለበት። ይህም በጥብቅ የተከለከለ ነው። አዋቂው አላህ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል
IbnuMunewor
ማን ያውቃል
በሕይወትህ ፈጽሞ ያላሰብከው መልካም ነገር ሊፈፀም ጫፍ ደርሶ ይሆናል። አትመለሰ፣ ተስፋ አትቁረጥ።

ABX
በቀን 3 ጊዜ የምትበሉ ሰዎች ምን አስባችሁ ነው? ሀሰን አል በስሪ (ረህመቱላሂ አለይህ) በቀን 3 ጊዜ ለሚበላ ሰው ቤተሰቦቹ መኖ ቤት ይገንቡለት ብለዋል:: አስቡበት:: ምግብ ቀንሱ:: ለሀገር ኢኮኖሚ እድገትም ሆነ ነፍስ ከአላህ ጋር በሚኖራት ግንኙነት ወደ አላህ ቀረብ እንድትል ትልቅ አስተዋፅዖ አለው:: ሆድ ሲሞላ ጭንቅላት ባዶ ይሆናል ይባልስ የል¿

Mohammadammin
ከፊልም የተወሰደ ምስል ነዋ የሚመስል…ይህ በገሀዱ ዐለም በኛዋ ውድ ሀገር ፈለስጢን የተፈፀመ ውድመት ነው። አላህ ብስራቱን ቅርብ ያድርግላቸው
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ 2⃣8⃣ #ሸዋል  1⃣4⃣4⃣5⃣
ከእለታት ባንዱ ቀን ... የባግዳዱ 'ጠቢብ-ዕብድ' ባህሉል እና ሰይዱና ጁነይድ ተገናኙ ... ሰይዱና ጁነይድም ከ'እብደቱ' ባሻገር ያለውን ጤንነት የተገነዘቡ ነበሩና ምክር እና ተግሳፅ ይሰጣቸው ዘንድ ጠየቁት ... ባህሉልም "አንተ እኮ እውቅ አሊም ነህ የኔ ምክር አያሻህም" በማለት መልስ ሰጠ ... ሰይዱና ጁናይድ ግን እንዲመክራቸው አጥብቀው ወተወቱት ...
*
ባህሉልም ... "እንግዲያውስ ስለ ሶስት ነገሮች እጠይቅህና በትክክል  ከመለስክልኝ ምክር እለግስሀለሁኝ" አለ ... በመቀጠልም "እንዴት መናገር እንዳለብህ ፤ እንዴት መብላት እንዳለብህ እና እንዴት መተኛት እንዳለብህ ታውቃለህን? " ሲሉ ጠየቁት ... ሰይድና ጁነይድም "እነዚህንማ ጠንቅቄ አውቃለሁ ...  ስናገር - በትሁት እና በለዘብተኛ ድምፅ ... ነጥቡ ላይ አተኩሬ እናገራለሁኝ የምናገረውን ሰው ቀልብም ላለመሰበር እጅጉን ተጠንቅቄም አስረዳለሁኝ ፤ ስበላ - በቅድሚያ  እጄን እታጠባለሁኝ ... ከመጀመሬ በፊት ቢስሚላህ ብዬ የአላህን ስም አወሳለሁ ... ስመገብ በአግባቡ አኝካለሁ ስጨርስ ደግሞ አልሃምዱሊላህ እላለሁ ፤ ስተኛ - ከመተኛቴ በፊት ውዱዕ አደርጋለሁ ... ንፁህ ነገር መልበሴን  አረጋግጩ  በሸሃዳ አሳርጋለሁኝ " አሉት
*
" ጥሩ! አለ ባህሉል ... "የምታወራው ነገር ውሸት ከሆነ በለዘብታ እና በትህትና ማውራትህ ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል ... የንግግር ዋናው ነጥብ ንግግሩ እውነት መሆኑ ላይ ነው ... ስትበላም በተከለከለ እና ሐራም በሆነ ምግብ ላይ የአላህን ስም ማወሳትህ ትርጉም የለውም ... ከሁሉም አስቀድሞ የምትበላው ምግብ ከሐራም ፣ ከየቲም ሀቅ ፣ ቧሏ ከሞተባት ሴት ሀቅ እና ከሰዎች ሀቅ የጠራ መሆኑ ማረጋገጥ ነው ወሳኙ አደብ ... ስትተኛም ቢሆን ልብህ በምቀኝነት ፣በክፋት እና በሙስሊም ወንድምህ ጥላቻ ተሞልቶ ... በውዱዕ እና በመኝታ ዚክሮች ታጅበህ መተኛትህ  ፋይዳ የለውም ... በንፁህ ልብ የተኛ ነው  ሙዕሚን ሆኖ አነጋ የሚባለው ... ገባህ! እነዚህ ናቸው መሰረታዊ ጉዳዬች የተቀሩት የእነዚህ ተከታዬች ናቸው" ሲል የጠቢብ ምክሩን ለገሳቸው
*

©Fuad Yasin
ሸዋል ላይ አገባለሁ ብሎ ያቀደውን ጀለስህን ስታስታውስ
አሁንኮ የወደፊት ሚስትህ "የወደፊት ባሌ በእውቀት የበለፀገ: በገንዘብ የሞላለት: መልካም ስነ-ምግባር መታወቂያው የሆነ ሰው ነው::" በሚል ሀሳብ ውስጥ ልትሆን ትችላለች:: አንተም በሀሳብ የወደፊት ሚስቴ "ሲያዟት እሺ የምትል: ለእኔም ሆነ ለቤተሰቤ የማትጎረብጥ: ልጆቼን በዲናቸውም ሆነ በዱንያዊ ነገሮች ኮትኩታ የምታሳድግ ናት::" እያልክ ይሆናል::

ግን አንተ የት ነህ? አንቺስ የት ነሽ? ለዚህ ስብዕና እየተዘጋጃችሁ ነው? ያም ሆነ ይህ የአላህ ሰላም በእናንተ ላይ ይሁንና ደህና እደሩ!

©
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 2️⃣9️⃣ #ሸዋል 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
አዲስ አበባ ላይ ይህንን ባነር ይዘው "ሲሰብኩ" የነበሩ ሰዎችን ፖሊስ እንዳሰራቸው እዚህ መንደር ሲዘዋወር አየሁ። ትምህርቱ ለሀይማኖተኛ አይደለም ለቄሳርም እንደሚያስደነግጥ የሚያስተዛዝብ ነው። የክርስትናው አለም አምላክ "ይቅር ባይነቱን" አክቲቬት ሊያደርገው ዘንድ የሚፈስ ደም ማየት ይፈልጋል። የአንተ ንስሀም ሆነ በጸጸት ከሀጥያትህ መራቅህ እግዚአብሔር እንዲምርህ የሚያደርግ ሚና የላቸውም። ብቻ ደም አቅርብለት እንጅ ስርየቱ ይረጋገጥልሀል። ከዚያ በኃላ የፈለግከውን ሀጥያት ብትሰራም "በጸጋው ድነሀልና" ከልካይ የለብህም። ካንተ ጭምትነት ይልቅ ለእግዚአብሔር የሚፈሰው ደም የበለጠ ያስፈልገዋል። ትምህርቱን ለመቀበል አይደለም ለመስማትም ይረብሻል..!

___
https://t.me/Yahyanuhe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
▣ የተማሪዎች ፈተና ራሱ እንደዚህ አይታረምም😁!


®Sαlαh Responds 🎙
#የኔ እይታ 51

አላህ ሲፈልግ.....

ህይወታችን ውስጥ በጣም ብዙ ተሳክተው ልናያቸው የምንጓጓላቸው ጉዳዮች አሉን። ጉዳዩን እጅግ በጣም ከመፈለጋችን ብዛት ተሳክቶ ለማየት ብዙ የምንደክምለት፣ አቅመቢስነታችንን አውቀን ሁሉን ቻይ አምላካችንን እርዳታውን የምንለምንለት፣ አቅማችንን ሁሉ አሟጠን ለብዙ አመታት የምንለፋለት፣ሰበባችን ብቻ በቂ እንዳልሆነ በማወቃችን ጉዳዩን ወደጌታችን አስጠግተን ውጤቱን በጉጉት የምንጠብቅለት ከባዱ ሀጃችን!
ያ ልባችንን ያስጨነቀው፣ ያ ተሳክቶ ለማየት የምንጓጓለት ፣ ያ የደስታችን መገኛ እንደሆነ ያመንበት ሀጃችን.....
ያ ሀጃችንን አላህ ለኛ እንደሚጠቅም እና ጊዜው እንደደረሰ ሲወስን ወደ እኛ የሚመጣበት ፍጥነት ያስገርማል። ሰርፕራይዝ ተደርጋችሁ ታውቃላችሁ?
ካወቃችሁ የሚያስደስታችሁ ነገር የናንተን ምንም አይነት ልፋት ሳይፈልግ በሌሎች ልፋት ውስጥ አልፎ እናንተ ጋር ያልተጠበቀ ደስታ ሁኖ ሲመጣ ያለውን ስሜት ምን አልባት በደስታ የሚፈስ እምባችሁ እንጂ ሌላ ምንም አይገልፀውም! ይህ በሰው ሰርፕራይዝ መደረግ የሚፈጥረው ስሜት ነው።
ሰርፕራይዝ የሚያደርግህ አላህ ሲሆን የጉዳዩን ትልቀት እና ውበት እንዲሁም ሂወትህ ላይ የሚፈጥረውን ለውጥ አስበው.........
አላህ ያ ሀጃህ ላንተ እንደሚጠቅም ከወሰነ እጅን አፍ ላይ በሚያደርግ ፍጥነት ያስደምምሀል። ብቻ እርሱ ይፈልግ ያኔ በ ك እና በ ن መካከል ባሉ ቃላት ብቻ ለአመታት ያስጨነቀህን ጉዳይ ፈፅሞት ታገኘዋለህ።
  አላህ እስኪፈልግ ሶብ'ሩ.....

©rehima
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 0⃣1⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣5⃣
ደመናው ሲጠቋቁር ነጎድጓዱ ሲያጉረመርም ዝናቡ ሊያለቅስ ሲል ነበር የዐስር ሰላትን ልሰግድ አለምባንክ በሚገኘው ሙስዐብ መስጂድ የታደምኩት። ኢማሙ እያሰገዱን ሰላታችን ካጋመስን ወዲህ ጥቁሩን ደመና መሸከም በቃኝ ያለው ሰማይ ዶፍ ዝናብ ያወርድ ጀመር…ኢማሙ በተረጋጋ መንፈስ ሰላታችን አስጨርሰውን ምእመኑ አዝካሩን በሚያጠናቅቅበት ግዜ ከመስጂዱ አወለ ሰፍ ሁለት እድሜያቸው በሀያዎቹ መጀመርያ ላይ መሆናቸው የሚያስታውቅ ወጣቶች ብድግ ብለው ቁርዐን ይዘው ያካፋፍሉ ጀመር…
ይህ አይደለ ትርፍ…ይህን የመሰለ አንድ እንኳን ወጣት እያለ ኢንሻአ አላህ አንወድቅም…አላህ ንግዳቸውን ትርፋማ ያድርገው
በዚህ ሌሊት ስንት ሰው ወደ አኼራ ተሻግሮ ይሆን ? ይህችን ንጋት ሳይታደል ከሞት የተገናኘ ስንት ይሆን ? እኔና አንተ ግን አንግተናል :: እኔና አንቺ ግን አንግተናል :: ለምን ? አላህ ስለፈቀደ ማለት ነው :: ምስጋና ይድረሰው :::

ሁሉም ነገር ለእርሱ "ኩን ፈየኩን!" ነው :: ስለዚህ ባደለህ ንጋት ውስጥ መልካም ነገርን ይወፍቅህ ዘንድ ጠይቀው :: ትላንት ያገኘኸውን አይነት ብቻ ሳይሆን አገኘዋለሁ ብለህ የማታስበውን እንኳ ስጠኝ በለው :: በሩን ደጋግመህ አንኳኳ :: አዕምሮህ አንተ አትችልም ብሎ የሚነግርህን ነገር በሙሉ ጠይቀው :: ምክንያቱም እርሱ የአለማት ጌታ ነው :: እሱ የተዓምራት ሁሉ ባለቤት ነው :: እሱ "ሁን!" ብሎ ነገሮችን ሁሉ እንዲሆኑ የሚያስችል ጌታ ነው ::

አላህ በመልካም ነገሮች surprise ያድርጋችሁ

©

اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
በምድር እና በሰማይ ተወዳጅነትን የምታገኙበት…መልካም ስራቸው ከሚበዛላቸው፣ ጊዜያቸውን በኸይር ከሚያሳልፉት፣ ለወንጀላቸው መሀርታን አግኘተው በጀነት ከሚበሰሩት ሰዎች መሀል የምንሆንበት ወዶ በላካቸው እና  እዝነቱን በእርሳቸው ባሳየን ወዱ ነብያችን የበዛ ሰለዋት ምናወርድበት በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ በሰላት በቲላዋ በተሳኩ ምኞቶች በጀባሩ ራህመት የታጀበ የተዋበ ምርጥየ ጁምዐን ተመኘሁ።

https://t.me/asdajlahh
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 0️⃣2️⃣ #ዙልቀዓዳ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣