ASD AJ LAH
668 subscribers
1.71K photos
192 videos
3 files
483 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
ሙገሳ ሲበዛ…
ደህና እደሩ
ህንፃህን ለማሰራት ሚሊዮን ብር መድበህ መሀንዲስ ትቀጥራለህ ፤ የምትጀምረው ንግድ እንዲሰምር ቢዝነስ ምሩቅ ትቀጥራለህ ፤ ህመምህ እንዲፈወስ ጥሩ ሀኪም ትፈልጋለህ…ታድያ የአንተ የአለማወቅ ችግር እንዲፈታ ዐሊሞችን ማመከሩን ለምን ዘነጋህ…ለምን ራስህ ፈትዋ ሰጪ አደረግክ?

ፈጅር ሰላት ላይ አንድ ዳዒ ወደራሳችን መለስ ብለን እንድናስብ ብሎ የጠየቀን ጥያቄ
ሞት ማንንም አያለያይም…መለያየት ማለት ያኔ ባለ ቀኝ እጆቹ ወደ ጀነት ባለግራዎቹ ወደጀሀነም ሲባሉ አንደኛችን ወደጀነት አንደኛችን ደግሞ ወደጀሀነም የሄድን ግዜ ነው።

አላህ መልካሙን ይግጠመን
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 2️⃣5️⃣ #ሸዋል 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በሀገራችን ታካሚዎች እና በጤና ባለሞያው መሀል የሚፈጠረውን "የንግግር ክፍተት" በመጠኑም ቢሆን እነዚህ ነጥቦች ያስተካክሉታል ብዬ አሰብኩ።

አያድርግባቹ እና ምን አልባት እናንተ ወይም የእናንተ የሆነ ሰው ከታመመባቹ እነዚህን ነገሮች ልማድ በማድረግ ብዙ ነገር ማትረፍ ትችላላቹ

1. ሁልጊዜ ሀኪማችሁን እነዚህን ጥያቄዎች መጠየቅ
👉 የተገኘብኝ በሽታ ምንድነው?
👉 በሽታው ከምን ሊመጣ ቻለ?
👉 በሽታውን እንዴት መከላከል ይቻላል?
👉 በሽታው ከሰው ወደሰው ይተላለፋል?

2. በተለይ የቀዶ ህክምና የሚደረግላቹ ሰዎች መጠየቅ ያለባቹ
👉 ከቀዶ ህክምና ውጪ ሌላ አማራጭ ህክምና አለው?
👉 የቀዶ ህክምና ባይደረግልኝ ምን ሊከሰት ይችላል?
👉 ያሉት የቀዶ ህክምና አማራጮች ምንድናቸው?
👉 የታቀደው የቀዶ ህክምና ምንድነው? እና ከተሰራ በኋላ ውጤቱ ምንድነው?
👉 የቀዶ ህክምናው ከተሰራ በኋላ ማድረግ ያለብኝ የሌለብኝ ነገሮች?
👉 ከቀዶ ህክምናው ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮች ምንድናቸው?

3. የታዘዘላችሁን የምርመራ ውጤቶች እና መድሀኒቶች በፎቶ 📸 መያዝ እንዲሁም አለርጂክ የሆነባችሁን መድሀኒት ስም ለይቶ ማወቅ።

👉 በተለይይ ለተጓዳኝ በሽታዎች ለረዥም ጊዜ በክትትል የምትወስዷቸው መድሀኒቶች ካሉ በተቻለ መጠን ስማቸውን መጠናቸውን እና አወሳሰዳቸውን ማወቅ።

4. ሁልጊዜ ሆስፒታል🏥 በተለይ ሪፈር ተብላቹ ወደ ሪፈራል ሆስፒታል ስትሄዱ 🚑 ከዚህ በፊት የነበራችሁን የምርመራ ውጤቶች እና የወሰዳችሁትን መድሀኒቶች ወይም እየወሰዳችሁት ያለ መድሀኒት ካለ ይዞ መሄድ።

5. በተቻለ መጠን የጤና ታሪካችሁን ስለሚያውቀው ክትትላችሁን በአንድ ሀኪም ቢያደርጉ ይመረጣል።

ታዲያ እነዚህን ከላይ የጠቀስኳቸውን ነጥቦች ልማድ ማድረግ ለታካሚዎች ከምታስቡት በላይ
👉 ያላግባብ ከሚደረግላቹ ተደጋጋሚ ምርመራዎች
👉 ያላግባብ ከሚታዘዝላቹ ተደጋጋሚ መድሀኒቶች እንዲሁም
👉 ከአላስፈላጊ ወጪ እና የጊዜያቹ መባከን ይጠብቃቹሀል።

👉 እንዲሁም ለጤና ባለሞያው በቀላሉ የጤና ታሪካችሁን እንዲረዳ እና ተገቢውን ምርመራ እንዲሁም ህክምና በጊዜ እንድታገኙ ይረዳቹሀል ማለት ነው።

👨‍⚕️ ዶ/ር ዮናታን ከተማ: በቅዱስ ፓውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህፃናት ቀዶ ህክምና ሬዚደንት ሐኪም
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
" የኦንላይን ፈተናው በተመረጡ 25 ከተሞች ይሰጣል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ 25 ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ገልጿል።

ተፈታኝ ተማሪዎች በኦንላይን ለሚሰጠው ፈተና እንዲዘጋጁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከሁሉም ክልሎች በተመረጡ 25 ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።

በወረቀት ከሚሰጠው ፈተና ጎን ለጎን የሚሰጠው የኦንላይን ፈተና ተማሪዎች ከቦታ ቦታ ሳይጓጓዙ በየአካባቢያቸው #ቤተሰቦቻቸው_ጋር_እያደሩ ፈተናውን ይወስዳሉ ሲሉ አሳውቀዋል።

ወ/ሮ አየለች ፤ ተማሪዎች ለፈተናው እንዲዘጋጁ፣ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ፣ ወላጆችንም ልጆቻቸውን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር እስካሁን ፈተናው በኦንላይን የሚሰጥባቸውን 25 ከተሞች በዝርዝር ይፋ አላደረገም።

የኦንላይን ተፈታኞች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ደጋግመው እንዲለማመዱ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 2⃣6⃣ #ሸዋል 1⃣4⃣4⃣5⃣
ይህ ሀላል ነው ይህ ሀራም ነው ብሎ የሚነግርህ የሚንሺካሾክልህ ድምፅ ውስጥህ ካለ አደራህን ይህን ድምፅ እንዳታጣው።

ነጂብ መሕፉዝ
የዛሬውን ውሎህን በአላህ መልእክተኛ ላይ ሰለዋት በማውረድ ጀምረው
..አንዳንድ መከራዎች ፈተናዎች ምንነታቸውን እንጂ የሚፈጥሩት ስሜት የሚገለፅ አይደለም..በዝምታ ውስጥ የሚብላላ እና የሚፋጅ ረመጥ ነው..እሷም ከዚህ የተለየ አልገጠማትም ሰው መሆን ጋር ተያይዞ የሚመጣው ስንኩልና እሷም ጋር ደርሷል ውስጧን ዳብሷታል ወደፊት ያለችው ቀርቶ አሁኗ ባላሰበችው አቅጣጫ ሲጓዝ ወደ መስመሩ ለመመለስ እየታገለች ነው በስስ ፈገግታ የታጀበ ፊት ግን ተለይቷት አያውቅም አዎ እንደነበረችው መቆየት ነበረባት በሷ ፅኑ ወኔ ፀንተው የሚኖሩ ነፍሶች በዙርያዋ አሉና ጌታዋን ስታማርር አትገኝም ለጠያቂዎቿ ሁሉ መልሷ "አልሐምዱሊላህ" ነው

..በአንዱ ቀን ስትብከነከን አጠገቧ ደረስሁ..ከጥሞናዋ ላናጥባት አልፈለኩም..ድምፅ ሳላሰማ አጠገቧ ተቀመጥኩ..ከጥቂት ቆይታዎች በኋላ እንደመባነን አለችና ሰላምታ አቀረበችልኝ..ያ የሚያስደንቀኝ ሰላማዊ ፈገግታ ፊቷ ላይ አለ ምን አይነት አቻቻል ነው ብዬ ተገረምኩ..የራሴን ደካማነት እና ባዶነት ከሷ ፈገግታ ላይ ሸከፍኩ..ምን ሲያብከነክናት እንደነበር ጠየቅኳት..ከጥቂት የዝምታ ቆይታዎች በኋላ ፊቷን ልትጠልቅ በምታዘቀዝቀው ፀሓይ ሰጥታ ..
"..አሏህ ግን የእዝነቱ ረቂቅነት አይገርምህም..?!» ስትል ንግግሯን ጀመረች..
«ሸሽቸው አልራቀኝም..ቀርቤው አላጣውም..ለምኜው አላሳፈረኝም..ሀቁን አጓድዬ አልተወኝም..ሳምፀው አላባረረኝም..ሳማርረው አልተወኝም..በመሐሉ መንገድ ስስት ደሞ በተለያዩ ፈተናዎች ወደሱ ይጠራኛል..እኔ በፈተናዎቼ እፅናናለሁ..የሚወደውን እንጂ አይጣራምና..»ብላ ንግግሯን ገታች..ትናንሽ አይኗቿ እንባን አዝለው የፀሃዩ ነፀብራቅ ሲያርፍባቸው ሉል ይመስላሉ..በረጅሙ ተነፈሰች..ከዚያም ፈገግ እያለች እንዲህ ስትል ንግግሯ ላይ አከለችበት
«..አላህዋ ለኔ የዋለውን ለማን ዋለ?! የሚለው ነው ከሐሳቤም ገዝፎ ይዞኝ የጠፋው..»

ነሲም ሚራዥ
ASD AJ LAH
እነfatherዎች ሽምግልና ሄደው ሲሰክሱ ሳክስ 1 ልጃችሁን ካልሰጣችሁን አንቀመጥም…😅 #ሸዋል
ሳክስ 2

ልጅየው ደህና ጀንጅኖ ያሳመናትን ሊያጭ ሽማግሌ ቢልክ ሽማግሌዎቹ "ባይገርማችሁ ከልጆቼ በላይ ነው ምወዳት"😅
አይተዋት ራሱ አያውቁም እኮ🤣

#ሸዋል
ASD AJ LAH
ሳክስ 3 የልጅት ወላጆች ቀድመው በልጃቸው ውሳኔ ተስማምተው ሳለ "እስኪ የዛሬ አስር አመት ኑ!"😅 #ሸዋል
ሳክስ 4

ባል ሚሆናትን ብቻ ከመመኘታቸው ጋር "ልጁ ምን አለው? በምንድን ሚያስተዳድራት? ምንድን ነው የሚያበላት"

ሽማግሌዎቹ "አይዞት የ……አባት ምን ቢያጣ የሚያበላት አሳር አይጠፋውም"😓

#ሸዋል
ASD AJ LAH
ሳክስ 4 ባል ሚሆናትን ብቻ ከመመኘታቸው ጋር "ልጁ ምን አለው? በምንድን ሚያስተዳድራት? ምንድን ነው የሚያበላት" ሽማግሌዎቹ "አይዞት የ……አባት ምን ቢያጣ የሚያበላት አሳር አይጠፋውም"😓 #ሸዋል
ሳክስ 5

የልጅት አባት "ልጁ ዲኑ ላይ እንዴት ነው? "

ሽማግሌዎች" የዱሀ እና የለይል ሰላትን ጨምሮ በቀን 7 ግዜ ይሰግዳል ባይገርማችሁ በየቀኑ መስጂድ እግራቸውን አስፍተው እየቆሙ መስጂድ ከሚያጣብቡ እና የውሀ ቧንቧ ከሚሰብሩት መሀከል ነው"



የልጅት አባት ወድያውኑ ኦ😮

#ሸዋል
ሁለተኛዬን ሽማግሌ ሆኘ ልድረው የሚፈልግ ካለ በውስጥ ያናግረኝ ስለነበረን ቆይታ ከልብ አመሰግናለሁ በሌላ ሳክስ እስክንገናኝ መልካም አዳር

#ሸዋል
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 2⃣7⃣ #ሸዋል 1⃣4⃣4⃣5⃣