ASD AJ LAH
759 subscribers
1.78K photos
197 videos
3 files
508 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
የአላህ ጊዜ ሁሌም ትክክል ነው። የእርሱ ቃልኪዳን ሁልጊዜም እውን ነው። ባሮቹ ሲበደሉ ዝም ብሎ የሚመለከት አምላክ የለንም። አማኞች አቅም ሲያጡ፤ ለአዕምሮ የሚከብዱ ተጨባጮች ውስጥ ሲገቡ የሚዘነጋቸው ጌታ አይደለም።

አላህ አይረሳም! ❤️‍🩹

ጌታችን የባሮቹን ህመም ረሺ አይደለም። ረቢ በዳዬችን የሚበቀል አምላክ ነው። የአሳማሚ ቅጣት ባለቤት ነው!

ጀሀነም ሐቅ ነው!
ጌታችን ፊት መቅረብ ሐቅ ነው!
ሁሉም የስራውን የሚያገኝበት የሒሳብ ቀን'ም ሐቅ ነው!

የዛኔ ግን ቅጣቱም ሆነ ሽልማቱ ጊዜያዊ አይደለም። የዛኔ የትኛውም አምባገነን መሪ ጭፍ*ጨፋውን በሚዲያ ሽፋን ለመደበቅ አይሞክርም። ዳኛው አላህ ነዋ! የዛኔ ማምለጫ አይኖርም! ቆዳን በጣም አክሳይ በሆነው ሰቀር ውስጥ የመማቀቂያ ዘላለማዊ ህይወት ይጀምራል! ወላሂ የዛኔ ማምለጫ በፍፁም አይኖርም!

እነዚህ አረመኔዎች ምድር ላይ የበሉት ነፍስ፤ ያፈሰሱት የጨቅላ ደም የዛኔ ይከፍላቸዋል! እስከዛ ደግሞ በዚህች ትንሽ የዱንያ ቆይታቸው እረፍት ያለ ኑሮን አይሰጣቸውም። በቅዠት የተሞሉ ለሊቶች፤ በፍርሃት፤ በጭንቀት የተረበሹ ልቦችን ይለግሳቸዋል! ምክንያቱም አላህ በባሮቹ ድርድርን አያውቅም! እንዴት'ስ ዝም ይላል?! በእውነቱ ጌታችን ረሺ አምላክ አይደለም። 🙌🏽

እኛም እስከዛ "ሐስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል!" እንላለን! ... የትኛውም ቃል፤ የትኛውም መፈክር፤ የትኛውም የተስፋ ቃል ከዚህ በላይ ሊያጠነክረን አይችልም! ቁስላችንን በቅርቡ ያሽርልን ዘንድ ምላሳችን ላይ እናዘውትረው ኢንሻአላህ! ❤️‍🩹
#Nadia