ASD AJ LAH
671 subscribers
1.7K photos
192 videos
3 files
483 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሱብሀነለዚ ዘየነ ሪጃለ ቢሊሀእ

ወንዶችን በፂም ላሳመረው ጌታ ጥራት ይገባው😅
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ከሐምሌ 6 እስከ 7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። 

መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብ (ኦንላይን) ከሚሰጥባቸው ከተሞች አንዱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስለመሆኑ ተሰምቷል።

ይህን ተከትሎ የፈተና ቅድመ ዝግጅት ተግባራት ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ ሲካሄድ ውሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊው ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፤ " የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በከተማው በኦንላይን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው " ብለዋል።

ለፈተናው ኮምፒዩተሮች፣ ላፕቶፖችና ታብሌቶችን ጨምሮ ሌሎች ግብአቶችን የማሟላት ስራ ተጀምሯል ተብሏል።

የግል ትምህርት ቤቶች ለፈተናው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ከወዲሁ እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ማሳወቁ ይታወሳል።

ሙሉ በሙሉ ፈተናው በኦንላይን ባይሰጥም  በተመረጡ ከተሞች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የቀሩት ተማሪዎች በተለመደው ሁኔታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በወረቀት ይፈተናሉ።

እስካሁን በየትኞቹ ከተሞች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች ፈተናውን በኦንላይን ይወስዳሉ የሚለው አይታወቅም። በምን አግባብ ተማሪዎቹ እንደሚመረጡም ለጊዜው በይፋ የሚታወቅ ነገር የለም።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
እነ ሚስ ሒጃብ ኢትዮጲያ ላይ እናመጣዋለን ብለው ያሰቡት ለውጥ vs ልኡል ሊዮናርድ

በአውሮፓውያኑ 1969 ሊዮናርድ ካዝሊ የሚባል ገበሬ ከሚኖርባት ሀገረ አውስትራሊያ የሚያርሳት የነበረችውን እርሻውን ራሷን የቻለች ሀገር ሆና መገንጠሏን አውጆ የራሱን ባንዲራ እና የራሱን ሳንቲም አትሞም ወደ ስራ ገባ። ራሱንም ልኡል ሊዮናርዶ ብሎ ሰየመ። በ1977 ደግሞ አውስትራሊያን ለጦርነት ጋበዟት የአውስትራሊያ ጦር በምላሹ ምንም ነገር ሳያደርግ በመቅረቱ በሀገሪቷ ጋዜጣዎች ላይ ማሸነፉን አውጇል።

ሁለቱም ህልም ብቻ
ልጅ ሳለሁ ጓደኞቼ ጋር ለመሄድ እዋሽ እንደነበር አስታውሳለሁኝ…አሁን አድጌ ደግሞ ጓደኞቼን ላለማግኘት "እቤት ስራ አለብኝ ይቅርታ! አልመጣም" ብየ እዋሻለሁኝ። ምናልባት ያ ስራ እኮ እንቅልፍ ሊሆን ይችላል
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 2️⃣2️⃣ #ሸዋል 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ትዳር ማለት ቤተሰብሽን ትተሽ የመጣሽለትን ሰው ቤተሰብሽን ለመዘየር የምታስፈቅጂበት ስርዐት ነው።

ለዚህ ስርዐት የከፈልሽው ከከፈልሽው ይበልጣልና ቤትሽን በማሳደግ ላይ አደራ።
ከዐረብኛ የተመለሰ

#ሸዋል
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 2⃣3⃣ #ሸዋል 1⃣4⃣4⃣5⃣
አንዳንዴ አብሽር የሚለው ቃል ብቻ ስሜትህን አይለውጠውም ። ከፍቶሀል አዝነሀል አጠገብህ ያሉ ሰዎች አብሽር ብቻ ይሉሀል ። የነሱ አብሽር ማለት በአንዴ ስሜትህን የሚቀይረው ይመስላቸዋል ። የሚያረጉልህ የሚሉህ ቢጠፋቸው እንደሆነ ግልፅ ነው ። ነገር ግን ስሜትህ በአንዴ እንዲቀየር ይጠብቃሉ ። ያንተን መቸገር ያንተን ማጣት ያንተን ክፉ ስሜት ውስጥ መግባት ያንተን ማዘን ከሌሎች ጋር ያነፃፅሩታል ። አንተ እንድትደሰት ሌላ የተከፋ ወይም ያዘነ ሰው ምሳሌ መሆን አለበት ወይ ? ለማዘንም ለመከፋትም የራሴ ጉዳዩች አይበቁኝም ወይ ? ትወጣለህ ትወርዳለህ ምንም የምታየው ነገር የለም ። በዙሪያዬ አሉ የምትላቸው ሰዎች እነሱ ሲፈልጉህ እንጂ አንተ ስትፈልጋቸው አታገኛቸውም ። ላንተ አንድ እርምጃ መጓዝ ይከብዳቸዋል ። በሁሉም ነገር ተስፋ ትቆርጣለህ ። በቃ አለ አይደል ድንገት የሆነ ነገር በመጣ'ና በወሰደን ብለህ ምትመኝበት ስሜት እሱ ስሜት ሲሆን አብሽር የሚለው ቃል ብቻ ስሜትህን አያስተካክለውም ።

©
ለነገሮች በምትሰጠው መልካም ጥርጣሬና ለሰዎች በምትመኘው መልካም ነገር ተጠቃሚ ትሆናለህ... አሲያ አለይሃ ሰላም የፊርዓውን ባለቤት ሙሳን ዐለይሂ ሰላም ህፃን ሆኖ ከባህር ላይ ሲያነሱት "

قُرَّتُ عَيْنٍ لِّي وَلَكَ ۖ لَا تَقْتُلُوهُ عَسَىٰ أَن يَنفَعَنَا أَوْ نَتَّخِذَهُ وَلَدًا
«ለእኔ የዓይኔ መርጊያ ነው፡፡ ለአንተም፡፡ አትግደሉት፡፡ ሊጠቅመን ወይም ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጀላልና» አለች፡፡
በነበራት መልካም ጥርጣሬ ምክንያት ሙሳ ልጇ ሆነ፣እሱን በምከተሏ ነብይዋ ሆነ ወደ ጀነትም መራት..ከጀነት በላይ ምን አለ?

ነቢ ሙሳ ውሃ ያጠጣጣላቸው እነዚያ አባታቸው ሷሊህ የሆነው ሴቶች አንዷ ለአባቷ "

يَا أَبَتِ اسْتَأْجِرْهُ ۖ إِنَّ خَيْرَ مَنِ اسْتَأْجَرْتَ الْقَوِيُّ الْأَمِينُ
«አባቴ ሆይ ቅጠረው፡፡ ከቀጠርከው ሰው ሁሉ በላጩ ብርቱው ታማኙ ነውና» አለችው፡፡"
ለሙሳ ኸይር በመመኘቷ ምክንያትም ሙሳን የማግባት እድል አገኘች።
©

اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
በምድር እና በሰማይ ተወዳጅነትን የምታገኙበት…መልካም ስራቸው ከሚበዛላቸው፣ ጊዜያቸውን በኸይር ከሚያሳልፉት፣ ለወንጀላቸው መሀርታን አግኘተው በጀነት ከሚበሰሩት ሰዎች መሀል የምንሆንበት ወዶ በላካቸው እና  እዝነቱን በእርሳቸው ባሳየን ወዱ ነብያችን የበዛ ሰለዋት ምናወርድበት በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ በሰላት በቲላዋ በተሳኩ ምኞቶች በጀባሩ ራህመት የታጀበ የተዋበ ምርጥየ ጁምዐን ተመኘሁ።

https://t.me/asdajlahh
« ሰለዋት ማለት ያዋጣል
ከችግር ቶሎ ያወጣል »

እውነት ነው በዳዒሙ ሹም ላይ ሰላትና ሰለዋት ማውረድ ከጭንቅ ፣ ከድህነት ፣ ከልፍስፍስነት ፣ ከበሽታና ሀሜት ከተሰኙ ችግሮች ያወጣል ። ሪዝቁ እንዲሰፋ ፣ ፊቱ እንዲያበራ ፣ መንፈሳዊም አካላዊ ጥንካሬ እንዲኖረው የሚሻ ሰው ሰለዋትን ያበዛል ። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላን ማውሳት በነብዩ አለይሂ ሰላት ወሰላም ላይ ሰለዋት ማውረድ የቀደምት አበዎች ፣ የደጋጎች ፣ የዐሪፎች ፣ የመሻይኾች ምግባር ብቻ ሳይሆን የአላሁ ተዓላና የነብዩ አለይሂ ሰላም ትዕዛዝ ነውና ። የመረጣቸውና የተመረጡት በዚህ ተጠምደዋል ።

«… እርሱን ተዉት ; አላህና መልዕክተኛውን ይወዳል!» ወዷቸው ያላቀውና ያወሳቸውስ…?

ዐለይሂ አፍደሉ ሰላት ወሰላም 💚

አብዱ ረዛቅ
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 2️⃣4️⃣ #ሸዋል 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
የተላከልኝን ቴክስት ከአንድ ሳምንት በኋላ አልሀምዱሊላህ ደህና ነኝ ብየ በመመለስ ላይ
ሙገሳ ሲበዛ…