ASD AJ LAH
762 subscribers
1.79K photos
197 videos
3 files
512 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እናንተው ይህን ጮማ ዜና ሰማችሁልኝ ወይ ¿

የወራሪዋ እስራኤል የሴኩሪቲ ሚኒስቴር የሆነው ልበ ደረቁ ኢትማር ቤንግቪር (Itamar Ben-Gvir) ላይ በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ በሚታየው ከፍተኛ የሆነ የመኪና አደጋ እንደደረሰበት እየተዘገበ ይገኛል። አላህ ሂዳያ ካልሰጠው እድሜውን አሳጥሮ ይገላግለን።
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 1️⃣8️⃣ #ሸዋል 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
እናት ስለወለድኳችሁ ይቅርታ የምትልበት ጘዛ ያለችበት አለም ላይ እኛም እየኖርን እንደሆነ ሳስበው…
የጎንደሩን ጭፍጨፋ የደገፉ እና ያስተባበሩት አባ ዩራኒየም ወደ በፊቱ የሀላፊነት ቦታቸው መመለሳቸውን ሀሩን ሚድያ ዘግቦ አየሁት
ASD AJ LAH
የጎንደሩን ጭፍጨፋ የደገፉ እና ያስተባበሩት አባ ዩራኒየም ወደ በፊቱ የሀላፊነት ቦታቸው መመለሳቸውን ሀሩን ሚድያ ዘግቦ አየሁት
በሚያዝያ 18/2014 የጎንደር ጭፍጨፋ ወቅት በግጭት ሰባኪነታቸውና በሀሰተኛ መረጃቸው የሚታወሱት ሊቀ ኅሩይ አባ ዮሴፍ ደስታ ወደ ቀድሞ ሀገረ ስበከታቸው መመለሳቸው ተገለጸ

ሀሩን ሚዲያ፥ ሚያዝያ 18/2015

በጎንደር ሙስሊሞች ላይ በተፈጸመው ጭፍጨፋ በወቅቱ በግጭት ሰባኪነታቸውና በሀሰተኛ መረጃቸው የሚታወሱት የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ የነበሩት ሊቀ ኅሩይ አባ ዮሴፍ ደስታ በፈጸሙት መሠረት የለሽ ውንጀላ ሳቢያ በወቅቱ ከቤተ ክርስቲያኗ እንዲሁም ከሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ውግዘት አስተናግደው ነበር። በዚህም ሳቢያ እስካሁኑ ወቅት ድረስ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ ሲሰሩ ቆይተዋል። በወቅቱ ተናግረውት የነበረውና የጎንደር ሙስሊም 500 ሚሊየን ብር የሚገመት ዩራኒየም ቦንብ እያብላላ መሆኑን የገለጹበት መንገድ በብዙ ሰው ዘንድ እጅግ ያስገረመና ያነጋገረ እንደ ሀይማኖት መሪነታቸውም ትዝብት ውስጥ የጣላቸው ክስተት ነበር።

አሁን ግን በጥያቄያቸው መሠረት ቀድሞ ይሰሩበት ወደነበረውና ከሙስሊሙ ጭፍጨፋ ወቅት ጋ ተያይዞ ስማቸው በጥቁር መዝገብ ወደሚታወስበት የጎንደር ሀገረ ስብከት በስራ አስኪያጅነት መሾማቸውን ለማወቅ ተችሏል። በዚህም ምክንያት ከቀድሞ ማንነታቸውና አሁን ካለው የክልሉ የሰላም ሁኔታ ጋ ተደማምሮ በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ዘንድ ትልቅ ስጋት መፈጠሩን የአካባቢው ሙስሊሞች ገልጸውልናል። ግለሰቡ ከተለመደው የግጭት ጠማቂነት ባህሪያቸው በመነሳት በአካባቢው ያለውን ግጭት እንዳያስፋፉትና በሙስሊሙ ዘንድ ያለውን ግፍም በማንሰራፋት እሳቱን እንዳያፋፍሙት ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው ሙስሊሞቹ ጨምረው ገልጸዋል። ሰላም ወዳድ የአካባቢው ነዋሪ ሁሉ ይህንን ጉዳይ በአንክሮ በመከታተል ከዚህ በፊት ያለፈውን አይነት አደገኛ ክስተት እንዳይደገም የበኩሉን ጥረት እንዲያደርግም ህዝበ ሙስሊሙ አበክሮ ጠይቋል።

© ሀሩን ሚዲያ
የስነልቦና አማካሪ:- ለሚስትህ አንድም ቀን አበባ ገዝተህላት አታውቅም ለምን?

ባል:- አበባ እንደምትሸጥ አልነገረችኝም እኮ😓

ዶክተሩ🤦🏽‍♂
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል።

" በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ " ሲሉ አሳውቀዋል።

ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፤ " ፈተናው በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው " ብለዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ብለዋል።

#MoE

tikvahethiopia
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 1⃣9⃣ #ሸዋል 1⃣4⃣4⃣5⃣
ምን ይታዘዝሎት

ከእሁድ ስፖርት መልስ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ያኔ ስፖርት መስራት ምናምን የጀመርክ ሰሞን
የማታ ኢንጂነሪንግ ተምረህ ስትመረቅ የምትሰራው ህንፃ
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 2⃣0⃣ #ሸዋል 1⃣4⃣4⃣5⃣
.....የማፍቀር ዋጋው ህመም ነው.... ታመህ የምትገዛው ደስታ ፍቅር ይባላል... "..ትላንትና እና ነገ የራሳቸው ጉዳይ.." ብለህ የማለፍ ግድየለሽ ልቦናን ፈልፍለህ ትፈጥራለህ....የአወዳደቅ ጥሩ የለውም... በፍቅር መውደቅ ግን እየቆየ የሚደምቅ ጌጥ ነው...... ልደግመው ብፈልግ የማልችልበት አይነት አወዳደቅ..... በልቤ የሚያብረቀርቁ የነበሩ የማፍቀር ድፍረት አንዳንዶቹ ስወድቅ ረገፉ... .."እሷ"ውስጥ ያለ ሌላ ቀለም ውበት በምን ይገለፃል...... ይሄስ እድለኛነት አይደል?..... በኑሮህ አሻራ ላይ የፍቅር ጣት ይነካሀል...... አንተ እድለኛ ነህ... ትወዳለህ... ትርቃለህ... ሰፌድ መሳይ ጉዞ ነው ...ክብ... ግን የማይገጥም..... አንዱ ከአንዱ የሚለያይ ይመስልሀል... ግን በፍፁም.....መንገዴ አያሳፍረኝም እኔነቴ ጋር ፀብ የለኝም...... እኔ የአጋጣሚዎቼ ውጤት ነኝ... እኔ መንገዴን መስላለሁ....

ነሲም
በተለምዶ «ያራዳ ልጅ» የሚባለው ዱኒያ ላይ ከሰው ልጆች ጋር እንዴት መኗኗር እንዳለበት አውቆ የሚኖረው ነው ። እውነት ነው ይህ ሰው አራዳ ነው ። ከአራዳዎች ጋር መኗኗር ደስ ይላል ። ቀላልና ተግባቢ ናቸው ። ላይፋቸውን እንጂ የሰው ላይፍ ላይ እንቅፋት ሲሆኑ አትመለከትም ። ሀያታቸው ሁሉ «በቃ ይመቸው!» ነው ። አኼራስ ካልክ ብዙዎቹ ያራዳ ልጆች የተሸጡበት ነው ።

የፈለገ ያራዳ ልጅ ሁን ፣ በየላውንጅና ክለቡ እሷኮ ይባልልህ ፣ ሙሉ የመሃል ልጅ ምርጥዬ ናት ብሎ ይመስክርልህ አኼራ ስትሄድ ፋራ ከሆንክ ግን ምን ጥቅም ብራዘር ?!

ደባሪ ሙድ ውስጥ ገብተው የጠፉ አሉ ። ከትርፏ ላይፏ በሚለው ሙዱን ሾፈው እጥፍ ያሉም ብዙ ናቸው ። የሱስና የጨብሲ ሙዱን ፈቶ መስጂድ የጠቀለለ ብዙ ያራዳ ልጅ አለ። ላይፍን አዯት ከትርፏ ኪሳራው ስለሚያመዝን በዱኒያ በሚያኗኑራቸው ምርጥዬ ባህሪ ለአኼራ ሲከስቡ ፣ አኼራን ሲሸምቱበት ስታይ እRድና ሞልቶ ፈሰሰ ትላለህ ። ምን አለ ሁሉም እንደነርሱ አራዳ በሆነ ፣ ያራዳ ልጆች በሙሉ ምን አለበት ለአላህ በዋሉ ፣ ለረሱል ትዕዛዝ ባደሩ ትላለህ ።

ከዱኒያ ሿሿ ጠብቆ በሁለቱም ዓለም እRድናን ይግጠመን አቦ 🫡

አብዱ ረዛቅ
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ 2⃣1⃣ #ሸዋል  1⃣4⃣4⃣5⃣