ASD AJ LAH
753 subscribers
1.74K photos
195 videos
3 files
493 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 2️⃣1️⃣  #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ዛሬ ፈጅር ሰላት በኋላ ሸይኻችን ተነሱና ከናንተ መሀል አላህ ይቀበለውና ተራዊህን ሰግዶ ለተሀጁድ ተነስቶ ሰግዶ ደክሞት ሲያበቃ ፈጅር እንደሰገደ ዑምራ እና ሀጅ ለማድረግ ያለ ምንም ወጪ መካ የመሄጃ እድል ቢሰጠው ደከመኝ ዛሬ አልሄድም የሚል ይኖራልን ብለው ጠየቁን በአንድ ድምፅ የለም መለስን። ይኖራልን በማለት አከታትለው ሶስቴ ጠየቁን እኛም የለም አልናቸው። ይሄኔ የሚከተለውን ሀዲስ ነገሩን እና ሰጋጁን ማህበረሰብ ባለበት እንዲቀመጥ አደረጉት።(የኔ አይነቱን ደግሞ በሼም አስቀመጡት)

{من صلى الفجر في جماعة ثم قعد يذكر الله حتى تطلع الشمس، ثم صلى ركعتين، كانت له كأجر حجة وعمرة } قال رسول الله { تامة، تامة، تامة }رواه الترمذي وحسنه
አነስ ኢብን ማሊክ ባወሩት ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም እንዲህ ይላሉ"የፈጅር ሰላትን በጀማዐ የሰገደ ከዚያም ፀሀይ የጦር ዘንግ ርዝመት ያህል ከፍ እስክትል አላህን እያወሳ የተቀመጠ ከዚያም ሁለት ረከዐ የሰገደ ልክ የዑምራ እና የሀጅን አጅር ያህል ያገኛል"ረሱል አስከትለው ምን አሉ"የተሟላ የሆነ ሀጅ እና ዑምራ…የተሟላ የሆነ ሀጅ እና ዑምራ…የተሟላ የሆነ ሀጅ እና ዑምራ"
ቲርሚዚይ ዘግበውታል

https://t.me/asdajlahh
Forwarded from Hanan Federalist (Han Fed)
#Notcoin - ጥቂት ነጥቦች
.
.
.
👌 #Tab እያደረጉ #Notcoin መሰብሰብ ሌሊት 6:00 ላይ ያበቃል::

👌 እስከ አሁን ባለው ከ10 ሚሊየን በታች የሆነ #Notcoin ከቴሌግራም አካውንት ወደሌላ የቴሌግራም አካውንት ማስተላለፍ አይቻልም:: ነገር ግን 10 ሚሊየን ወደ #NFT ከተቀየረ ከዋሌት ወደ ዋሌት ማስተላለፍ ይቻላል::

👌 በተደጋጋሚ እንደገለጽኩት የሰበሰባችሁት #Notcon 10 ሚሊየንም ቢሞላ ባለበት ሁኔታ ገንዘብ አይደለም:: ገንዘብ የሚሆነው #ወደብሎክቼይን ሲወሰድ ወይም #ወደNFT ሲቀየር ነው:: ሲቀየርም ልዩ መለያ ተሰጥቶት በኔትወርክ ላይ ቦታ (Space) ስለሚይዝ የአገልግሎት ክፍያ ይጠየቅበታል:: እስከ አሁን ባለው 10 ሚሊዮኑን ለመቀየር 0.06 #Ton ይከፈላል:: ነገር ግን 1 ton ወስዶ መልስ ስለሚሰጥ ሲቀየር ዋሌታችሁ ቢያንስ 1.1+ Ton ሊኖራችሁ ግድ ይላል::

👌 ዋሌታችሁ ላይ ተገቢው #Toncoin ሳይኖራችሁ ወይም 10 ሚሊዮን ሳይሞላ ለመቀየር መሞከር ከነጭራሹ ሊጠፋ ይችላል::

👌 ወደNFT ሳይቀየር እስከመቼ መቆየት እንደሚችል፣ ከ10 ሚሊየን የሆነው እንዴትና በስንት ክፍያ እንደሚቀየር ወደፊት ሲገለጽ አሳውቃችኋለሁ::

👌 ዛሬ ከቀኑ 10 እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ የማስታወቂያ ፓኬጆች (earn ላይ) ስለሚኖሩ ተጠባበቁ፤ መልካም እለተ እሁድ ይሁንላችሁ🙏🙋
የሸይኽ አዘይን ምክትል ኢማም የሆኑት ሸይኽ ሲራጁዲን መድረኩን…

#መወሰኛይቱ
ሰዐቱ 11:58 ላይ ያሳያል…ዱንያን ፍለጋ በጠዋቱ ስራ ወዳለበት ሩጫ ላይ የተሰማራንን 13ተሳፋሪዎች ይዞ ዱንያን ፍለጋ የወጣ አንድ ሹፌር መኪናውን ያሽከረክር ይዟል

#ከስብ

አላህ ሆይ የልባችንን መሻት አደራ🤲
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 2️⃣2️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
I can't
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ 2️⃣3️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
📅#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 2️⃣4️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ለራስህ ጥቅም ብሎ የሚጠራህ ሙአዚን ብቻ ነው
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 2️⃣5️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
عن ‏ابن حجر رحمه الله تعالى أنه قال: "إن تمني زوال رمضان من الكبائر". قال بعض العلماء معلقًا على كلام ابن حجر: "ولعله إذا كان بغضًا للعبادة فربما يخشى منه الكفر".(الجواهر شرح الاربعين )

ይህ ንግግራቸውን አያይዘው አንድ ዓሊም “ምናልባትም ይህን የተመኘው ዒባዳውን በመጥላት ከሆነ ኩፍር ይፈራበታል” ብለዋል !!!
አል ጀዋሂር ሸርሐል–አርበዒን
____
አላሁም’መ ሰሊምና መዓ ሳሊሚን 🤲
©አብዱ ረዛቅ

اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
መልካም ስራቸው ከሚበዛላቸው፣ ጊዜያቸውን ከሚጠቀሙት፣ በኸይር ከሚያሳልፉት፣ ለወንጀላቸው መሀርታን ከሚያገኙት፣ በጀነት ከሚበሰሩት ሰዎች መሀል የምንሆንበት ወዶ በላካቸው እና እዝነቱን በእርሳቸው ባሳየን ወዱ ነብያችን የበዛ ሰለዋት ምናወርድበት በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ በቲላዋ በተሳኩ ምኞቶች በጀባሩ ራህመት የታጀበ የተዋበ ምርጥየ ጁምዐን ተመኘሁ።

https://t.me/asdajlahh
💕ኢላሂ

የፆምነውን ፆም ተቀበለን፣ ያጓደልነውን በእዝነትህ ሸፍንልን፣ መልካም ስራዎቻችን ሁሉ ተቀበለን🤲

ሃያሉ ጌታችን ሆይ

የረመዳን ወር ፆም የፍርዱ ቀን ላይ ለኛ የሚመሰክርልን እንጂ በኛ ላይ የሚመሰክርብን አታድርግብን🤲🤲🤲

🥰ለይለቱል ቀድር ትገኝባቸዋለች ተብለዉ ከሚጠበቁት 10 ቀናቶች መካከል ጐደሎ ቀናቶች ይበልጥ ይጠበቃሉ፤ከእነዚህ ቀናቶች የዛሬዉ አንዱ ነዉናራሳችንን እናበረታታ ዱአ እናብዛ።መልካም ኢፍጣር በዱአ አስታዉሱ🙏
   
ረመዳን 27
በሱጁደ ቲላዋ ላይ ኢማሙ ምን ላይ እንዳለ ያላወቀ ሰው ምን ያድርግ?
~
በቁርኣን ውስጥ በሶላት ውስጥም ይሁን ከሶላት ውጭ በሚቅቀሩ ጊዜ ሱጁድ የሚወረድባቸው 15 አንቀፆች አሉ። በርግጥ ሱጁዱ ግዴታ አይደለም። ነገር ግን ኢማሙ ሱጁድ ከወረደ መከተሉ ግዴታ ነው።
በሶላት ውስጥ ኢማሙ እነዚህን አንቀፆች ቀርቶ ተክቢራ ሲያደርግ እሱን በእይታ መከታተል የማይችሉ ሰዎች (በተለይም ሌላ ክፍል ውስጥ የሚሆኑ ሴቶች) ኢማሙ ሩኩዕ ላይ ይሁን ወይም ሱጁድ ላይ ይሁን ለመለየት የሚቸገሩበት ጊዜ አለ። በዚህን ጊዜ ምን ያድርጉ?

1ኛ፦ ኢማሙ ሱጁድ ወርዶ ሳለ ተከታዩ ሩኩዕ ከመሰለው

1.1. ኢማሙ ሱጁድ ወርዷል። ተከታዩ ግን ሩኩዕ መስሎት እንዳጎነበሰ ከሩኩዕ ሳይነሳ ኢማሙ ሱጁድ ላይ መሆኑን ካወቀ ኢማሙን ይከተላል። ወደ ሱጁድ ይወርዳል።
1.2. ኢማሙ ሱጁድ ላይ እንደነበር ያወቀው ከተነሳ በኋላ ከሆነ ኢማሙን ተከትሎ ያጠናቅቃል። ሱጁዱ ግዴታ ስላልሆነ ምንም ማድረግ አይጠበቅም።

2ኛ፦ ኢማሙ ሩኩዕ ላይ ሆኖ ሳለ ተከታዩ ሱጁድ ከወረደስ?

2.1. ኢማሙ ሩኩዕ ላይ እንደነበር ካወቀ ተከታዩ ከሱጁድ ተነስቶ ቀጥ ብሎ ከቆመ በኋላ አጠር አድርጎ ሩኩዑን በመፈፀም ይከተለዋል። ሆን ተብሎ የተፈፀመ ስህተት ስላልሆነ ምንም ማድረግ አይጠበቅበትም።
2.2. ተመልሶ ሩኩዑን ሳያስገኝ ከቀረ ግን ሩኩዕ የጎደለው አንዱ ረከዐ ስለማይቆጠር መጨረሻ ላይ አንድ ረከዐ ይጨምራል።

ከዚህ ሁሉ ግን ኢማም የሆነ ሰው የተከታዮቹን ሁኔታ ከግምት ቢያስገባ ጥሩ ነው። የኢማሙን ተግባር ማየት የማይችሉ በመሆናቸው የተነሳ ሰዎች ሊሳሳቱ እንደሚችሉ ከገመተ ወይ ሱጁድ በሌላባቸው አንቀፆች ቢብቃቃ ወይ ደግሞ ሱጁደ ቲላዋውን ቢተወው የተሻለ ነው። ወሏሁ አዕለም።

IbnuMunewor
ዘካተል ፊጥርን የሚመለከቱ ነጥቦች
~
1- ምንነቱ፦ ሙስሊሞች ከዒደል ፊጥር በፊት ለችግረኞች የሚሰጥ የእህል / የምግብ ሶደቃ ነው።
2- ሑክሙ፦ በሚችል ሰው ላይ ግዴታ ነው። [አልቡኻሪይ፡ 1503] [ሙስሊም፡ 984]
3- በማን ላይ ነው ግዴታው?
3.1. በትንሽ በትልቁ፣ በሴት በወንዱ፣ በሁሉም ሙስሊም በሆኑ የቤተሰብ አባላት ቁጥር የሚወጣ ሶደቃ ነው።
3.2. ገና ያልተወለደ ፅንስ እዚህ ግዴታ ውስጥ አይገባም።
3.3. አንድ ሰው የሌሎችን ዘካተል ፊጥር (ለምሳሌ ከሱ ጋር ያልሆኑ ቤተሰቦቹን ወይም የአገልጋዮችን) ማውጣት ይችላል። ግን እንደሚያወጣላቸው ማሳወቅ ይገባል።

4- ምን ያህል አቅም ባለው ላይ ነው ግዴታ የሚሆነው? ለራሱም ለቤተሰቡም ለዒድ ሌሊትና ቀን የሚበቃ ቀለብ ባለው ላይ ግዴታ ነው።
5- ለማን ነው የሚሰጠው? የእለት ጉርስ ለሌለው ድሃ።
5.1. ዘካ እና ዘካተል ፊጥር የሚሰጠው ለሙስሊም ብቻ ነው። ሌሎች ሶደቃዎችን ሙስሊም ላልሆኑ አካላት መስጠት ይቻላል።
5.2. ሑክሙን ባለማወቅ ወይም የሚግገባው አካል ስለማያገኙ ለሰራተኞቻቸው ዘካተል ፊጥር የሚሰጡ ሰዎች አሉ። ሰራተኞቻቸው የማይገባቸው ከሆኑ የተሰጣቸውን ለሚግገባቸው አሳልፈው መስጠት ይኖርባቸዋል።

6- የሚሰጡ የእህል / የምግብ አይነቶች፦ ተምር፣ ዘቢብ፣ አይቤ እንዲሁም በሃገር በአካባቢው ለቀለብነት የሚውሉ፣ ረዘም ላለ ጊዜ ሳይበላሹ መቆየት የሚችሉ የእህል / የምግብ አይነቶች ሁሉ ይገባሉ። ምክንያቱም "ከምግብ አንድ ቁና" የሚል ሐዲሥ አለና። [አልቡኻሪይ፡ 1508] [ሙስሊም፡ 985] በዒዱ እለት መመገብ የሚችሉት አይነት ቢሆን ተመራጭ ነው።
7- መጠኑ፦ አንድ ቁና (ሷዕ) ነው። በአራቱ ኸሊፋዎች ዘመን በዚህ መልኩ ነው ሲፈፀም የኖረው።
7.1. በራስ ፈቃደኝነት ጨምሮ ቢሰጥ ይቻላል።
7.2. የሚሰጠው መጠን በኪሎ ግራም:- በሐዲሥ የመጣው በስፍር ስለሆነ የክብደት መለኪያ ስንጠቀም እንደ እህሉ አይነት መጠኑ ይለያያል። ወደ ኪሎ ሲቀየር ዱቄት ላይ 2.5 ኪሎ አቅራቢያ ይመጣል። ይሄ የአንድ ሰው መጠን ነው። 10 ቤተሰብ ያለው ሰው 25 ኪሎ ማለት ነው።

8- ጊዜው፦ ግዴታ የሚሆነው የረመዷን ወር የመጨረሻ እለት ተጠናቆ የዒዱ ሌሊት ሲገባ ነው። ልብ በሉ! በኢስላማዊው አቆጣጠር የአንድ እለት ቀዳሚው ክፍል ቀኑ ሳይሆን ሌሊቱ ነው።
8.1. ከዒድ ሶላት ማሳለፍ አይፈቀድም። ረስቶ በጊዜው ያላወጣ ሰው ሲያስታውስ ቢሰጥ ወንጀል አይኖርበትም። አውቆ ወይም ችላ ብሎ ወቅት ካሳለፈ ግን ወንጀል ላይ ወድቋል። ቢሆንም ግን የድሃ ሐቅ ስለሆነ ወቅቱ ቢያልፍም ሊያወጣ ይገባል።
8.2. ተቀባዩ በመራቁ የተነሳ በእለቱ ለማድረስ የሚቸገር ሰው "የት ላድርግልህ?" ብሎ ይጠይቅና ከወከለበት ቦታ ያደርግለታል። በዚህን ጊዜ በእለቱ ባይወስድም ችግር የለውም።
8.3. አስቀድሞ መስጠት ይቻላል? ለሚሰበስቡ አካላት አንድ ቀን ሁለት ቀን ቀድሞ መስጠት ይቻላል። ከዚህ ውጭ በጊዜው መስጠት እየተቻለ ቀደም ብሎ መስጠት አይገባም። ነገር ግን በእለቱ ለመስጠት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲኖሩ ትንሽ ቀደም ብሎ መስጠት ይቻላል። እንዲሁም በውጭ ሃገራት ያሉ ሰዎች ለሚሰጥላቸው አካል ቀደም ብለው መላክ ይችላሉ። ወኪሉ ግን በተቻለ መጠን ወቅቱን መጠበቅ አለበት።
9. ከቤተሰብ ርቃችሁ ለምትገኙ ተማሪዎች ወላጆቻችሁ ዘካተል ፊጥር የማያወጡላችሁ ከሆነና የማውጣት አቅሙ ካላችሁ ዘካተል ፊጥር ማውጣት እንዳትረሱ።
10. አስገዳጅ ወይም አንገብጋቢ ሁኔታ ካልገጠመ በስተቀር በገንዘብ ማውጣት አይቻልም። ዝርዝሩ በቀጣይ የሚታይ ይሆናል ኢንሻአላህ።

IbnuMunewor
አጭር ማስታወሻ ስለ ዱዓእ
~
ዱዓእ ተቀባይነት ያገኛሉ ተብለው በሚታሰቡ በላጭ ሰዓቶች ላይ ከፍ ላሉ ጉዳዮች ትኩረት እንስጥ።
* አላህ ቀልባችንን እንዲያስተካክልልንና ዲን ላይ እንዲያፀናን። የነብዩ ﷺ ዱዓእ በብዛት እንዲህ የሚል ነበር፦
يا مُقلِّبَ القلوبِ ثبِّت قلبي على دينِكَ
“አንተ ልቦችን ገለባባጭ ሆይ! ልቤን በዲንህ ላይ አፅናልኝ።”
* በየትኛውም ዲናዊ ጉዳይ ለተሻለው እንዲመራን። ነብዩ ﷺ የሌሊት ሶላታቸውን በዚህ ዱዓእ ነበር የሚከፍቱት
اللَّهُمَّ رَبَّ جِبْرَائِيلَ، وَمِيكَائِيلَ، وإسْرَافِيلَ، فَاطِرَ السَّمَوَاتِ وَالأرْضِ، عَالِمَ الغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ، أَنْتَ تَحْكُمُ بيْنَ عِبَادِكَ فِيما كَانُوا فيه يَخْتَلِفُونَ، اهْدِنِي لِما اخْتُلِفَ فيه مِنَ الحَقِّ بإذْنِكَ؛ إنَّكَ تَهْدِي مَن تَشَاءُ إلى صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ.
“አንተ የጂብራኢል፣ የሚካኢል፣ የኢስራፊል ጌታ የሆንከው፣ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ የሆንከው፣ የሩቁንም የቅርቡንም የምታውቀው አላህ ሆይ!ባሮችህ ሲወዛገቡበት በነበረው ነገር አንተ ትፈርዳለህ፡፡ ከሐቅ ለሚወዛገቡበት ነገር ምራኝ፡፡ አንተ የፈለግከውን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትመራለህና፡፡” [ሙስሊም]
* ወንጀላችንን ምሮ ከእሳት እንዲጠብቀን፣ ጀነትን እንዲያድለን:- የሙስሊም ትልቁ ሃሳብ ጭንቀቱ ይሄ ነው መሆን ያለበት።
اللَّهمَّ إنِّي أسألُك الجنَّةَ وأعوذُ بِك منَ النَّارِ
"አላህ ሆይ! እኔ ጀነትን እለምንሀለሁ። ከእሳትም ባንተ እጠበቃለሁ።"
* የአላህን ይቅርታ ለማግኘት መትጋት። እናታችን ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ ለነብዩ ﷺ ለይለተል ቀድር መሆኑን ካሰብኩ ምን ልበል ስትላቸው የጠቆሟት ዱዓእ ይሄ ነበር፦
اللَّهمَّ إنَّكَ عفوٌّ، تُحِبُّ العفوَ فاعفُ عنِّي.
"አላህ ሆይ! አንተ በርግጥም ይቅር ባይ ነህ። ይቅር ማለትን ትወዳለህ። ስለሆነም ከኔ ይቅር በለኝ።”
* ለዚክር፣ ለምስጋና፣ ላማረ የዒባዳ አፈፃፀም እንዲወፍቀን
اللهمَّ أعني على ذكرِك وشكرِكَ وحسنِ عبادتِكَ
"አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ አንተን በሚመስገን እና አንተን ባማረ መልኩ በመገዛት ላይ አግዛኝ።"
* ለወገኖቻችንም እንዲሁ የጠመሙትን እንዲያቀናልን፣ የሞቱትን እንዲምርልን፣ ለወላጆቻችን እንዲያዝንላቸው፣ በሃገራችን፣ በፊለስጢን፣ በሱዳን፣ በሊቢያ፣ በሌሎችም ቦታዎች መከራ ላይ ያሉትን ከፈተና እንዲያወጣልን፣ ሰላም እንዲሰጠን ዱዓእ ልናደርግ ይገባል።
* ባጠቃላይ በዱንያም በኣኺራም መልካሙን እንዲያድለን ጠቅላይ ጠቅላይ ዱዓኦችን መምረጥ መልካም ነው። ነብዩ ﷺ ያዘወትሯቸው ከነበሩ ዱዓኦች ውስጥ አንዱ እንዲህ የሚል ነበር፦
اللَّهُمَّ رَبَّنَا آتِنَا في الدُّنْيَا حَسَنَةً، وفي الآخِرَةِ حَسَنَةً، وقِنَا عَذَابَ النَّارِ.
"አላህ ሆይ! በዱንያም መልካምን፣ በኣኺራም መልካም ስጠን። ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን።"
IbnuMunewor
ጘዛ

መሳሪያውን እንደጨበጠ ከሰማይ የወረደ ሚሳኤል ቢያነደውም ከሰውነቴ የቀረ አካል እስካለ ድረስ ከትግል ፈቀቅ አልልም የሚል የሚመስል እጅ

አላህ በጀነት ያስደሳው
አላህ ለኛም የክብር ሞት የሆነውን ሸሂድነትን ይወፍቀን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከጘዛ ሰማይ ስር

{ تَبَارَكَ ٱلَّذِی جَعَلَ فِی ٱلسَّمَاۤءِ بُرُوجࣰا وَجَعَلَ فِیهَا سِرَ ٰ⁠جࣰا وَقَمَرࣰا مُّنِیرࣰا }

ያ በሰማይ ቡሩጆችን ያደረገና በእርሷም አንጸባራቂን (ፀሐይ) አብሪ ጨረቃንም ያደረገ ጌታ ክብሩ በጣም ላቀ፡፡

{ وَهُوَ ٱلَّذِی جَعَلَ ٱلَّیۡلَ وَٱلنَّهَارَ خِلۡفَةࣰ لِّمَنۡ أَرَادَ أَن یَذَّكَّرَ أَوۡ أَرَادَ شُكُورࣰا }
እርሱም ያ (ያመለጠውን ሥራ) ማስታወስን ለሚፈልግ ወይም ማመስገንን ለሚፈልግ ሰው ሌሊትንና ቀንን ተተካኪ ያደረገ ነው፡፡

{ وَعِبَادُ ٱلرَّحۡمَـٰنِ ٱلَّذِینَ یَمۡشُونَ عَلَى ٱلۡأَرۡضِ هَوۡنࣰا وَإِذَا خَاطَبَهُمُ ٱلۡجَـٰهِلُونَ قَالُوا۟ سَلَـٰمࣰا }
የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት፣ ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሩዋቸው ጊዜ ሰላም የሚሉት ናቸው፡፡

ሱረቱል ፉርቃን 61-63
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 2️⃣7️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
" በአላህ እምላለሁ ከአቡበክር የተሻለ ሥራ ፈጽሞ አልሠራም”

ዑመር ቢን አል-ኸጣብ (ረዐ) ምንም መልካም ብሰራ አቡበክርን (ረዐ) አልደርስም ያሉበትን ሁለት ታሪክ ሲያብራሩ

አቡበክር ከፈጅር ሰላት በኋላ ወደ መዲና ዳርቻ በመውጣት ለሰዓታት ትንሽ ደሳሳ ጎጆ ቤት ከገባ በኋላ ወደ ቤታቸው መሄዳቸው ትኩረቴን ስቧል
ከዚህ ደሳሳ ጎጆ ቤት ካለው ሚስጥር በስተቀር አቡበክር የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ አውቅ ነበር።

ቀናት ቢያልፉም የሙእሚኖች ኸሊፋ አሁንም ይህንን ደሳሳ ጎጆ ቤት መጎብኘት አላቆሙም

አቡበክር ውስጥ ገብቶ ምን እንደሚሰራ አላወቅም ነበርና አቡበክር ከደሳሳው ጎጆ ከወጡ በኋላ ወደ ቤቱ ለመግባት ወሰንኩ

በጎጆ ውስጥ ያለውን ነገር በአይኖቼ ማየት እና አቡበክርም ከፈጅር ሰላት በኋላ የሚያደርጉትን ማወቅ ጓጉቼ ነበር

ወደዚህች ትንሽ ጌጆ ቤት ገባሁ በእርጅና ምክንያት መንቀሳቀስ የማትችል እና ማንም ጥሪት የሌላት አሮጊት ሴት አገኘው
እሷም ዓይነ ስውር ነበረች

ባየሁት ነገር ተገረምኩ አቡበክር ከእዚች ዓይነ ስውር አሮጊት ጋር የነበራቸው ግንኙነት ሚስጥሩ ምን እንደሆነ ለማወቅ ፈልጋ እንዲህ ስል ጠየቅኳት
"ይህ ሰውዬ እዚህ ቤትህ ውስጥ ምን ያደርጋል?"
(አቡበከር አል-ሲዲቅ ማለታ ነው)
አሮጊቷ ሴት መለሰች፡-
" ወላሂ አላውቀውም ይሄ ሰውዬ በየማለዳው መጥቶ ቤቴን ያጸዳል ከዛም ምግብ አዘጋጅቶልኝ ቃላት ሳይናገር ይሄዳል።

" አቡበክር ወደ አኼራ ሲሄዱ እኔ አይነ ስውር የሆነችውን አሮጊት ሴት እንክብካቤ ቀጠልኩ

ቃላት አልተነፍስም አቡበክር እንደሆንኩ እንዲሰማት ነበር ጥረቴ

በአንድ ወቅት ያቀርብኩላትን ቴምር እየበላች
“ጓደኛህ ሞቷል አይደል ?” በማለት ጠየቀችኝ

"እንዴት አወቅሽ?" አልኳት

እሷም “ ያመጣህልኝን ተምር ፍሬውን ሳታወጣ ነው የሰጠኸኝ" አለችኝ

ዓይኖቼ በእንባ ተሞሉ

በሌላ ጊዜ ደግሞ

የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم ምፅዋት እንድንሰጥ አዘዙን እናም በወቅቱ እኔ ትንሽ ሀብት ነበረኝ በመሆኑም በውስጤ “ዛሬ ከአቡ በክር (ረዐ) የምበልጥበት ቀን ቢኖር አሁን ነው አልኩኝ

ከሀብቴ ግማሹን ይዤ ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ ሄድኩና አቀረብኩ “ለቤተሰብህ ምን አስተረፍክ?” አሉኝ “ተመሳሳይ መጠን” አልኳቸው
ቀጥሎ አቡበክር ያለውን ሀብት ሁሉ ይዞ መጣ
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጠየቁት
“አቡበክር ሆይ ለቤተሰቦችህ ምን ተውክ?” አሉት።
አቡበከርም “አላህና መልእክተኛውን” አለ

እኔም በውስጤ “በአላህ እምላለሁ ከአቡበክር የተሻለ ሥራ ፈጽሞ አልሠራም” አልኩ።

ሱነን አል-ቲርሚዚ 3675

Bilal zayed እንደፃፈው