ASD AJ LAH
755 subscribers
1.73K photos
194 videos
3 files
487 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ0️⃣9️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ረመዷን - 10

እንደው እንደዋዛ ሮጠን 10ኛው ቀን ላይ ደረስን ቢባል ማን ያምናል ወዳጆቼ? ዐጃኢብ ነው ብቻ….
ቀናት እንግዶች ናቸው፤ ይመጣሉ ይሄዳሉ፣ ይዘይሩናል ያልፋሉ፡፡ የመጡት ለዘላለም ከኛ ጋር አይቆዩም ፡፡
በኢስላም እንግዳ ክቡር ነው፤  በየዓመቱ በዓመት ለአንድ ወር ያህል የሚዘይሩን የረመዷን ቀናት ደግሞ የበለጠ የተከበሩ ናቸው፡፡ እንዴት እያስተናገድናቸው ይሆን?
የረመዷንን ቀናት አከበርን የሚባለው አላህ በሚወደውና በሚፈቅደው መልኩ ስናስተናግዳቸው ነው፡፡ ቁርኣን ስንቀራባቸው፣ ተራዊህ ስንሰግድባቸው፣ ዚክር ስናዘወትረባቸው፣ ሶደቃ ስናበዛባቸው፣ መልካምነትን ስንላበስባቸው ነው፡፡

የረመዷን ቀናት አላህ (ሱ.ወ.) ዕድሎችና ቦነሶች ናቸዉና ተጠቀሙባቸው ብሎ የላከልንን የተከበሩ ቀናት ናቸው ፡፡ ዘጠኙ ቀናት እንዴት አለፉ በረቢ?፡፡

 መልካሞቹ የአላህ ባሮች ባለፉት ቀናት እየተቆጩ ለሚመጡት እየሳሱ እዚህ ደረሱ፡፡

በርግጥም ረመዷን የምር የሆነ ምርጥ ወዳጅ ነው፤ ተጠቀሙብኝ ብሎ በረከቱን ሁሉ ሳይሰስት ዘርግፎ ሠጠን፡፡
ጀሊሉ በቀሩት ቀናት ይበልጥ ወደ ልቦናቸው ተመልሰው ተጠቃሚ ከሚሆኑት ያድርገን፡፡

Afdel
📅#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 1️⃣0️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
Be different😓
ተራዊህ በኋላ ቁኑት የሚያደርጉ ኡስታዞች ግን ለእኛ ወጣቶች አላህ የትዳር በርን እንዲከፍትልን ዱዐእ ማድረግ አለባቸው ከምር'😇
የቻልከዉን ያህል ተገኝ

አንዳንዴ በተራዊሕም ይሁን የግዴታ ሶላት ላይ የት እንደሄድክ ሳታውቅ የኢማሙን ተክቢራ እና ማሰላመት ከሀሳብህ ያነቃህ ይሆናል። አላህ ይዘንልን- ያለ ማስተዋልና ያለ ማስተንተን እንደ እንጨት ቆመን የምንሰግዳቸው ሶላቶች ብዙ ናቸው። ታድያ በዚህ ጊዜ ሁሉ በአካል እንጂ በሀሳብ ሶላት ላይ መገኘት አልቻልኩም ብለህ ሶላትህን አትተው። የቻልከዉን ያህል ለመገኘት ጣር። ከሶላቱ አምስት ይሁን አሥር ፣ ሀያ ይሁን ሰላሳ፣ ሀምሳ ይሁን ሰባ እጅ የሚፃፍለት አለ። ሰው ሆኖ ከሶላቱ መቶ በመቶ የሚፃፍለት አለ ለማለት ይከብዳል። መዳኛህ ነዉና ሶላትህን አጥብቀህ ያዝ። ሕይወት በሁሉም መስክ ትግል ናትና በተሻለ ሁኔታ ለመገኘት ታገል።

©
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 1️⃣1️⃣  #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ረመዷን-11


እንግዳ የሚበዛበት ቤት አላህ የሚወደው ቤት ነው ይላሉ።
ለትንሽ ትልቁ ልድሃ ሀብታም ሚከፈትን ቤት የሰዉም ሆነ  የመላእክት ዱዓ አይለየዉም። የአላህ ችሮታም አይጎድልበትም።
እንግዳ እቤት ሲገባ በረከትና የአላህ እዝነት አብሮት ይገባል።
እንግዳው ብዙ ችሮታዎችን ይዞ ይመጣል፣ ወንጀልም አጥቦ ይሄዳል።
"በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳዉን  ያክብር።" ብለዋል የአላህ መልዕክተኛ ሶ.ዐ.ወ።

ፆመኛን ያስፈጠረ የሱን ያህል እኩል ምንዳ ያገኛል።
©
{أَنَا عِنْدَ ظَنِّ عَبْدِي بِي}
{እኔ ባርያዬ በጠረጠረኝ ቦታ ነኝ}ቡኻሪ

ቀኖቹ አንድ አይነትቢሆኑም እንኳን ሁኔታዎች ​​ተለዋዋጭ ናቸው፣ፍላጎትህ ላይ ለመድረስ መፍትሄው ሚስጥር ቢሆንም።አንድ ቀን ግን አላህ በምትጠብቀው መልካም ነገር ያበስርሃል...
ጌታችን አላህ ዕጣ ፈንታን በቅጽበት ይለዋውጣል፣ ምቾትም ከመከራ ልብ ውስጥ ይፈጠራል፣
በአላህ ላይ መልካምን እንጅ አትጠርጥር!
©

اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
መልካም ስራቸው ከሚበዛላቸው፣ ጊዜያቸውን ከሚጠቀሙት፣ በኸይር ከሚያሳልፉት፣ ለወንጀላቸው መሀርታን ከሚያገኙት፣ በጀነት ከሚበሰሩት ሰዎች መሀል የምንሆንበት ወዶ በላካቸው እዝነቱን በእርሳቸው ባሳየን ወዱ ነብያችን የበዛ ሰለዋት ምናወርድበት በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ በቲላዋ በተሳኩ ምኞቶች በጀባሩ ራህመት የታጀበ የተዋበ ምርጥየ ጁምዐን ተመኘሁ።

https://t.me/asdajlahh
ረመዷን - 12
****

ተቀምጦ መስገድ ሽንፈት የሚመስለው፤ አንካሳ ሆኖ በአንድ እግሩ ለተራዊሕ ቀጥ ብሎ የሚቆም አየሁ።
ጤናማና ጠንካራ ሆነው ጀርባዬን፣ እግሬን እያሉ በየሰበቡ ሶላት አቋርጠው የሚወጡትን አየሁ።
ከዚያም ራሴን ታዘብኩ፣
እንዲህም አልኩ ...
ሰው በኢማኑ ልክ ለሶላት ይቆማል ፣
ሰው በኢማኑ ልክ አላህን ያወሳል፣
ዒባዳ ላይ የሚያፀናው አካላዊ ሳይሆን ኢማናዊ ጥንካሬ ነው፣
ሰው በኢማኑ ልክ ዲኑ ላይ ይፀናል።

አዎ ... ሰው ለአላህ ፍራቻ ባለው ልክ አላህን ይታዘዛል ።
ሰው ዉስጡ በያዘው ኢማኑ ልክ ፊቱ ይርሳል፣ እንባው ይፈሳል፣ ልቡ ይርዳል፣ አካሉ ይርበተበታል።
ሰው በኢማኑ ልክ እዝነቱ ይበዛል ፣
ሰው በኢማኑ ልክ ቁርአን ይከፍታል ፣
ሰው በኢማኑ ልክ መስጂድ ይመላለሳል ፣
ሰው በኢማኑ ልክ ምጽዋት ይሠጣል ፣
ሰው በኢማኑ ልክ ወንድም እህቶቹን ይወዳል፣
ሰው በኢማኑ ልክ ሥነምግባሩ ያምራል።
ወዳጆቼ !
ኢማን ምኞት አይደለም ሥራ ነው፣
ኢማን ምላስ አይደለም ተግባር ነው።
አላህ እውነተኛ ኢማን ይስጠን።

©Abx
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 1️⃣2️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ስምህ በሰዎች ዘንድ መታወቁ አልያም ስራዎችህ ሰዎች ዘንድ አጀንዳ መሆናቸው ለአኼራ ስኬትህ ያን ያህል አስፈላጊ አይደለም።

وَرُسُلًا لَّمْ نَقْصُصْهُمْ عَلَيْكَ

“...ባንተ ላይም ያልተረክናቸውን መልክተኞች (እንደላክን ላክንህ)..” ቁርአን 4፥164

በሰዎች ዘንድ የማይታወቁ አሏህ ﷻ ዘንድ ግን የሚታወቁ በርካታ ነብያት አሉ። አሏህ ዘንድ ለመታወቅ በርትቶ መስራት ትልቁ ስኬት ነው። የፍጡራን ሙገሳና እውቅና እዚህው ምድር ላይ የሚቀር ትርጉም አልባ ቅጽበት ነው። በምድር ባይታወቁም በሰማይ ከሚታወቁት አሏህ ያድርገን..!

مجهولون في الأرض معروفون في السماء،!

©
ከጎኑ የሚሰግደውን ሰው የለቅሶ ሲቃ በመጠኑም ሰምቶ ነበርና ሲጨርሱ ወደሱ ዘወር ብሎ "ምን ያክል ትርጉሙ ቢገባህ ነው እንዲህ ያስለቀሰህ?" አለው ሰውየውም በትካዜ "የቁርአኑ ትርጉሙ አልገባኝም፤ ያስለቀሰኝም እሱ ነው" አለው። ለስንቱ የዱንያ ሀጃ በርካታ ስራዎችንና ሳይንሶችን ለብዙ አመታት ያጠናው ጭንቅላታችን የአሏህን ቃል ግን ትርጉሙን እንኳን አለማወቁን ማሰብ እንዴት ሀዘን ይፈጥራል?

ያሕያ
ረመዷን - 13
***

እጅግ ከሚገርሙኝ አባባል መካከል " መከተል የፈለገ እነኚህን የሞቱትን ይከተል። በሕይወት ያለ ሰው ፈተናው አይታመንም ።" የሚለው ይገኝበታል ።

አባባሉ ትልቅ አስተዉሎትን ይፈልጋል። ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ ናቸው ይህን ያሉት ተብሏል።
"የሞቱት" የተባሉት ደጋጎቹ የአላህ ባሮች ሶሐቦች ናቸው። እነርሱ ደግ ሥራ ሠርተው ለሌሎችም ምሳሌ ሆነው አልፈዋል ። እስከመጨረሻ ድረስ በዲን ፀንተው ለአምላካቸው አላህ ሱ.ወ. ታምነው ኖረው መቃብር ወርደዋል። ስለዚህ መከተል እነርሱን ነው። ቢከተሏቸው ያዋጣሉ ። አብነት ቢያረጓቸው ወደ መልካም መጨረሻ ያደርሳሉ ።
በሕይወት ያለ ግን ምኑ ይታመናል ወዳጆቼ። እስካልሞተ ድረስ የሰው ፍፃሜው አይታወቅም። እየኖረ እያለ ነገ ድንገት አቋሙን ሊቀይር ይችላል ። ስንቱን አየን እኮ!። ትናንት ብርቱ የነበረ ኡስታዝ በዱንያ አልያም በሌላ ምክንያት ዛሬ ሲደክም። ጠንካራ አቋም የነበረው ሲሸረሸር። የተውሒድ ሰው የነበረ ሲያደገድግ። የሱና ሰው የነበረ በቢድዓ ሲዞር። ኅጢአት ይሸሽ የነበረ ምን ችግር አለው ብሎ ሲዳፈር።

ወዳጆቼ!
ሰዉን ዐይናችን እያየ ዱንያ፣ ሥልጣን፣ ጥቅም፣ ዝና ... አቋሙን ሊያስለዉጠው ይችላል። ስለሆነም በሕይወት ያለ አይታመንም ። ሰው በያዘው መልካም አቋም ላይ የሚታመነው ሞቶ መቃብር ሲወርድ ብቻ ነው። ያኔ የሚለውጠው አቋም አይኖረዉም።
ስለዚህ ኡስታዝ በሉት ሸይኽ፣ እኔም ሆንኩ ሌላ ማንም ይሁን ማን .. ሰዉን ፍፁም በሆነ መልኩ አመኑ፣ ከትከተሉ ። ራሣችሁንም በርሱ ላይ አትጣሉ። አድናቆታችሁን ቀንሱ። ነገ ቢሰንፍ፣ ቢደክም፣ አቋሙን ቢለዉጥ ... እንዳትደነግጡ ያግዛችኋል።

አንድ ነገር ልምከራችሁ
ስትቀመጡ፣ ስትነሱ፣ ስትገቡ፣ ስትወጡ ...

ዐለይከ ረበና ቢሑስኒልኺታሚ ..ን አንጎራጉሩ።
የጠፉት እንዴት እንደጠፉ ሳይሆን ነጃ የወጡት እንዴት እንደወጡ መርምሩ።

©Abx
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 1️⃣3️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ለሶላት የውጭ ድምፅ ማጉያ መጠቀም
~
ሶላት ዒባዳ ነው። ዒባዳችን ከእልህና መሰል አጉል ስሜቶች ፀድቶ በኢኽላስና በንፁህ መንፈስ ሊፈፀም ይገባል። ድምፅን በሶላት ከፍ ማድረግ በቦታው ሲሆን የተወደደ ነው። አልፎ በእንቅልፍ ሰዓት ሰዎችን እስከሚረብሽ ሊደርስ አይገባም። አንዳንድ አካባቢ ከሶላትም አልፎ መዝሙር ከፍተው እንደሚያውኩ ሰዎች መንዙማ ለቀው የሚያውኩ አሉ። ኢስላም ይህንን አይፈቅድም። "እነሱስ እንዲህ እያደረጉ አይደል?" የሚል ማመሀኛ እልህ እንጂ ማስረጃ አይደለም። ደግሞም እነሱ አይደሉም ምሳሌዎቻችን። በረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ሌሊት ለተሀጁድ የሚነሱ ወገኖች የውጭ ድምፅ ማጉያዎችን ሲጠቀሙ ሰፈሩን እንዳለ ነው የሚያውኩት። ጉዳዩ አላህን በመፍራት ሰከን ብሎ ማጤን ይሻል። ሰፈር ጎረቤት ቢታወክም እንጮሃለን እያስባለን ያለውን ምክንያት ረጋ ብለን እናዳምጠው። ምናልባት አንዳንዶች ጋር "በዚያ ሰዓት እተኛለሁ የሚል ይረበሽ። ሙሉ የሰፈሩ ህዝብ ተነስቶ ይስገድ" የሚል ስሜት ወለድ ሙግት ካለ ስሜታችሁን ተቆጣጠሩ ከማለት ውጭ ይሄ ምላሽም የሚግገባው አይደለም። ብቻ ደጋግሜ የምለው አላህን እንፍራ። የታመመ ይተኛ። መተኛት የፈለገም ይረፍ። አሁን ያለው ግን ሌላው ቀርቶ መስጂዶች በሚቀራረቡባቸው አካባቢዎች ባጎራባች ያሉ ሰጋጆች ሶላታቸው እስከሚረበሽ እየደረሰ ነው።
ከዚህ በፊት አንዳንዶች "ቁርኣን እንዴት ይረብሻል?" የሚል የህፃን ክርክር ሲያስነሱ ነበር። የሚረብሸው ለከት ያለፈው ድምፅ ነው። መስገዳችንን አገር እንዲያውቅልን ማወጅ የለብንም። ለኢኽላስ የቀረበው በልክ የሆነው ስራ ነው።

እንዲያውም በተሀጁድ ብቻ ሳይሆን #በሌሎችም ሶላቶች የውጭ ድምፅ ማጉያዎችን መጠቀም ክልክል ነው ይላሉ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ። ይሄውና:

ጥያቄ:- “ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የመስጂድ ኢማሞች የውጭ ድምፅ ማጉያዎችን መጠቀም አብዝተዋል። ድምፅ ማጉያዎቹ በአብዛኛው ሚናራ ላይ የሚሆኑ ሲሆን በጣም ከፍ ያለ ድምፅ ይጠቀማሉ። በዚህ ድርጊት የተነሳ ድምፅ ከፍ በሚደረግባቸው ሶላቶች ጊዜ ከፊል መስጂዶች በቁርኣን ንባብ ጊዜ ድምፅ ማጉያዎችን ስለሚጠቀሙ ሌሎቹን ይወሰውሳሉ። እና ድምፅ ከፍ በሚደረግባቸው ሶላቶች ጊዜ የድምፅ ማጉያዎችን መጠቀም ብይኑ ምንድነው?

የሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ ምላሽ እንዲህ የሚል ነበር:-

ድምፅ ከፍ በሚደረግባቸው ሶላቶች ጊዜ ድምፅ ማጉያዎችን ከሚናራ ላይ መጠቀም ክልክል ነው። ምክንያቱም በአቅራቢያ ባሉ ነዋሪዎች እና መስጂዶች ላይ መረበሽ አለበትና። ኢማሙ ማሊክ ረሒመሁላህ በዘርቃኒይ ሸርሕ ላይ እንደሚገኘው ሙወጦእ (178) ላይ በ (باب العمل في القراءة) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየሰገዱ ከነበሩ ሰዎች ዘንድ ወጡ። በቁርኣን ድምፃቸው ከፍ ብሏል። በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉ:-
"إن المصلي يناجي ربه فلينظر بما يناجيه به ولا يجهر بعضكم على بعض بالقرآن"
“ሰጋጅ ከጌታው ጋር ነው የሚንሾካሾከው። ስለዚህ የሚንሾካሾክበትን ይመልከት። አንዳችሁ በሌላው ላይ በሶላት አይጩህ። አቡ ዳውድ (1332) (رفع الصوت بالقراءة في صلاة الليل ) በሚል ርእስ ስር ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየላሁ ዐንሁ በዘገቡት የአላህ መልእክተኛ ﷺ በመስጂዳቸው ኢዕቲካፍ አድርገው ነበር። በቁርኣን ሲጮሁ በሰሟቸው ጊዜ መጋረጃውን ገልጠው እንዲህ አሉ:-
"ألا إن كلكم مناج ربه فلا يؤذين بعضكم بعضاً، ولا يرفع بعضكم على بعض في القراءة ، أو قال في الصلاة"
“ንቁ! እያንዳንዳችሁ ከጌታው ጋር ነው እየተንሾካሾከ ያለው። ስለሆነም አንዳችሁ ሌላችሁን አያስቸግር። በቁርኣን ንባብ / በሶላት አንዳችሁ ሌላችሁ ላይ አይጩህ።” [መጅሙዑ ፈታዋ ኢብኒ ዑሠይሚን: 13/74-96]

በተጨማሪም እንዲህ ብለዋል:-

“ሶላቶችን ከሚናራዎች ላይ በድምፅ ማጉያዎች ማስተላለፍ ጠያቂው እንዳለው በየቤታቸው ያሉ ሰዎችን መወስወስ ነው። የግል ዚክሮቻቸውንና ተስቢሖቻቸውን ማናጋት ነው። ምናልባትም ከዚህ ጊዜ ውጭ ማረፊያ ያጡ የተኙ ሰዎችንና ህመምተኞችን መረበሽ ሊኖርበትም ይችላል።
በተጨማሪም ከዚህ ድምፅ ባጎራባች ላሉ መስጂዶች መረበሽና መወስወስ አለበት።” [ኑሩን ዐለ ደርብ:176]

የሁለቱንም ፈትዋዎች ይዘት ሙሉውን ስላላቀረብኩ የፈለገ ምንጩን ተከትሎ ያንብብ።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ረመዳን 19/1442፤ ሚያዚያ 23/2013)
ረመዷን - 14
***

አዎ አሁንም ቢሆን ዝም አትበሉ፣ አትዘናጉ፡፡ ረመዷንን እንደ ትልቅ ዕድል ተጠቀሙበት፡፡ ያሳሰባችሁን ማንኛዉም ነገር ሁሉ ለፈጠራችሁ አምላክ ለአላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ ንገሩት፡፡ እሱ ጉዳያችሁን ይፈታል፣ አይቻልም ተብሎ የሚታሰበዉን ሁሉ ያገራል፡፡

አንዳንድ ዱዓ እኮ ምላሽ ለማግኘት ረመዷንን ይጠብቂል። አንዳንዱ የናንተን እጅ ማንሳት ብቻ እየጠበቀ ይሆናል፡፡
እጃችሁን ወደ አላህ አንሱ አትፍሩ፣ አትፈሩ፣ አታመንቱ፣ አትቅጠሩ፣ አመቺ ጊዜ አትጠብቁ፡፡

አንድ ሰው ብዙ እንዲሳኩለት የሚፈልጋቸው ሓጃዎች እያሉት እንዴት ይሰንፋል! እንዴት እጁን አጣጥፎ ይቀመጣል!!፡፡

ብቸኝነት ያደከማችሁና መልካም ትዳር የምትናፍቁ፣ ጉዳያችሁ ከዓመት ዓመት መልስ ሳያገኝ የተንከባለለ አሁንም ወደ ተጠጉ፣ ከአላህ ጋር አውሩ፡፡
ሪዝቅ የጠበባችሁ፣ ድህነት ያዋረዳችሁ አላህ ሆይ ሪዝቄን አስፋ በሉት፡፡ ያሳሰባችሁን ማንኛዉንም ነገር ሳትፈሩ ሳታፍሩ ለምኑት፣ ጠይቁት፣ ተማፀኑት፡፡ ረመዷን አላህ በብዛት ባሮቹን የሚቀበልበት ወር ነው፡፡ ከተቀበላቸው ትሆኑ ዘንድ በርቱ ተስፋ አትቁረጡ።

©Abx
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 1️⃣4️⃣  #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
በዙሪያህ ያለውን ሁሉንም ነገር ለመረዳት አትሞክር። አንዳንድ ጉዳዮችን አለመረዳት ነው የሚሻለው። አንዳንዴ ነገሩን በመረዳትህ የሚመጣብህ የልቦና ቀውስና አንደበትህ ላይ የሰዎች ስም መመላለስ ብቻ ነው። …  በቃ ምናገባኝ ማለት አስፈላጊ ነው። በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ!

©fuad
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 1️⃣5️⃣ #ረመዳን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣