ASD AJ LAH
753 subscribers
1.72K photos
194 videos
3 files
486 links
ካነበብኩት…
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
{ قَالَ یَـٰۤإِبۡلِیسُ مَا لَكَ أَلَّا تَكُونَ مَعَ ٱلسَّـٰجِدِینَ }
(አላህም) «ኢብሊስ ሆይ! ከሰጋጆቹ ጋር የማትኾን ላንተ ምን ምክንያት አለህ» አለው፡፡

{ قَالَ لَمۡ أَكُن لِّأَسۡجُدَ لِبَشَرٍ خَلَقۡتَهُۥ مِن صَلۡصَـٰلࣲ مِّنۡ حَمَإࣲ مَّسۡنُونࣲ }
«ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከግም ጭቃ ለፈጠርከው ሰው ልሰግድ አይገባኝም» አለ፡፡

{ قَالَ فَٱخۡرُجۡ مِنۡهَا فَإِنَّكَ رَجِیمࣱ }
(አላህ) አለው «ከርሷም ውጣ፡፡ አንተ የተባረርክ እርጉም ነህና፡፡»

{ وَإِنَّ عَلَیۡكَ ٱللَّعۡنَةَ إِلَىٰ یَوۡمِ ٱلدِّینِ }
«ባንተ ላይም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ እርግማን አለብህ፡፡»

ሱረቱል ሂጅር 32-35

Good night with good dreams 😴😴😴
የረመዿንን 30 ቀናት የፆመ በአላህ ፍቃድ ሙሉ ረመዿንን እንደፆመ ተደርጎ ይቆጠርለታል😉
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ 2️⃣4️⃣ #ሻዕባን 1⃣4⃣4⃣5⃣
ጅል አይሙት ሊያጫውት
ASD AJ LAH
የረመዿንን 30 ቀናት የፆመ በአላህ ፍቃድ ሙሉ ረመዿንን እንደፆመ ተደርጎ ይቆጠርለታል😉
ድሮስ 30ቀን ፆሞ አላህ ብሎ እንደፆመ ላይቆጠር ነው እንዴ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
{ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَیۡكُمُ ٱلصِّیَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِینَ مِن قَبۡلِكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَتَّقُونَ }
እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡

ሱረቱልበቀራህ 183

Good night😴😴😴
📅#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 2️⃣5️⃣ #ሻዕባን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ወንዶች ሆይ! ውዱእ እንዳታደርጉ ሚከለክላችሁን ቦርጭ አይስጣችሁ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
{ قَالَا رَبَّنَاۤ إِنَّنَا نَخَافُ أَن یَفۡرُطَ عَلَیۡنَاۤ أَوۡ أَن یَطۡغَىٰ }
[«ጌታችን ሆይ! እኛ በእኛ ላይ ክፋት በመሥራት መቸኮሉን ወይም ኩራትን መጨመሩን እንፈራለን» አሉ፡፡

{ قَالَ لَا تَخَافَاۤۖ إِنَّنِی مَعَكُمَاۤ أَسۡمَعُ وَأَرَىٰ }
(አላህም) አለ «አትፍሩ፡፡ እኔ በእርግጥ ከእናንተ ጋር ነኝና፡፡ እሰማለሁ፤ አያለሁም፡፡

ሱረቱ ጠሀ 45-46

Good night 😴😴😴
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 2️⃣6️⃣ #ሻዕባን 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣
ቀን ፀሀይ ስለሚሆን ብየ እምለብሰው እያለኝ በነጠላ ሸሚዝ ለስራ የወጣሁትኝ እኔ ከእኔ እድሜ እኩያ የሆነ ወጣት ቅዝቃዜውን ትንሽ እንኳ ከተከላከለልኝ ብሎ ባለችው አንዲት በየቦታው በተቀደደች ቲሸርት ውስጥ በብርድ ምክንያት የሚንቀጠቀጥ እጁን ከ'ቶ ሪዝቁን ፍለጋ ሲወጣ አይቸ ካላመሰገንኩኝ ምን ይሻለኛል

አልሀምዱሊላህ
ASD AJ LAH
Photo
" እስካሁን በተጓዝኩበት የህይወት መንገድ ፡ ነገሮች ሁሉ አልጋ በአልጋ ( bed of roses ) ብቻ ሆነውልኝ እዚህ አልደረስኩም ። ከልጅነቴ ጀምሮ በብዙ ህመምና የጤና ችግር ውስጥ አልፌያለሁ ።

ሆኖም  እናትና አባቴ ፡ ሁሌም ከጎኔ ሆነው ፍቅርና ድጋፋቸውን ስለሰጡኝ  እዚህ ደርሻለሁ "

ከላይ ያለው ንግግር.  . ሰሞኑን አለምን ጉድ ባስባለ ሰርግ የተዳረው አናንት  አምባኒ ፡ በሰርጉ እለት የተናገረው ነው ።
....
አናንት አምባኒ የቢሊየነር ልጅ ብቻ ሳይሆን ፡  ከአርባ ቢሊየን ዶላር በላይ፡  ሀብት በማካበት እሱ ራሱም ቢሊየነር  የሆነ. ..  ከጤና በስተቀር በምድር ላይ መግዛት የማይችለው ነገር የሌለ  ቱጃር ወጣት ነው ። ሆኖም ከልጅነት እድሜ ጀምሮ በያዘው ክፉ የአስም ህመም ምክንያት ብዙ ተሰቃይቷል ።
.....
steroids የአየር መተላለፊያ እብጠትን በመቀነስ ፡ በአስም ህመም መተንፈስ ላቃታቸው ሰወች ፡ እንደ መፍትሄ ሆኖ የሚያገለግል መድሀኒት ቢሆንም ፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሰውነት ክብደትን የመጨመር ባህሪ አለው ።
እናም አናንት  ከዚህ ህመም ጋር ሲታገል በመኖሩ ፡ በየጊዜው የሚወስደው መድሀኒት ክብደቱን እንዳይቆጣጠር አድርጎት ቆይቷል ።
...........
በአንድ ወቅት እንደውም 208 ኪሎ ይመዝን ነበር ፡ ሆኖም ይህ ወጣት ከህመሙ ጋር እየታገለም ቢሆን የአመጋገብ ስታይሉን ቀይሮ ፡ በየቀኑ እስከ 20 ኪሎ ሜትር ወክ እያደረገ ፡ በአንድ አመት ከስድስት ወር ውስጥ 108 ኪሎ ቀንሶ ክብደቱ 100 ኪሎ ማድረስ ችሎ ነበር ።
( በዚህ ምስል ላይ የሚታየውም ክብደት ከመቀነሱ በፊትና በኋላ ያለው ልዩነት  ነው ።
........
እና የሰውነቱ መወፈር የተከሰተው ብዙዎች እንደሚያስቡት መክሳት ስላልፈለገ ሳይሆን ፡ ህመሙ በሚሰማው  ወቅት በሚወስደው መድሀኒት እና ተያያዥ በሆኑ ምክንያቶች ነው ።
....
አንዳንዴ ከሩቅ የምናያቸው ሰወች ፡ ህይወት አልጋ በአልጋ ብቻ የሆነችላቸው ይመስለናል ግን አይደለም ።
በነገራችን ላይ  በቀደም እለት አናንት አምባኒ በሰርገኞቹ ፊት ፡ ወላጆቹን ለማመስገን ሲል ፡ ይህንን የጤናውን ጉዳይ በተመለከተ ሲናገር ቢሊየነሩ ሙኬሽ አምባኒ  ( ልጁ ያሳለፈውን አስቸጋሪ ሁኔታ ያውቃልና )  እንባውን መቆጣጠር አቅቶት ሲያለቅስ ታይቷል ።
...
( ስለዚህ  እጅግ ትሁት እና ከሁሉም ጋር ተመሳስሎ ፡ የመኖር ችሎታ ያለው ፡ ወጣት ቢሊየነርና ፡ ቤተሰቡ ፡ ለሌላው ተሞክሮ ሊሆን የሚችል የህይወት ስታይል የሚከተሉ ናቸውና ፡ በሌላ ፅሁፍ እንመለስባቸዋለን )
.....
ድህነት ክፉ ነው ፡ አስከፊ ነገር ነው ድህነት  ።   በተቃራኒው ደግሞ ፡ ሀብታም መሆን ደስ ይላል ። ሆኖም አንዳንዴ ሀብትህ የማይገዛልህ ነገር አለ ። ይህ ነገር ጤና ይባላል ።

እና. . ሀብታም ለመሆን እንመኝ ፡ ከተቻለም ለመሆን እንሞክር ፡ በዋነኝነት ግን ጤነኛ ስለሆንን እናመስግን ።

Wasihun
ወደዚያ ተግባር እንደማትመለስ ለአላህ ቃል ገብተህ ቃልህን አፈረስክ ኣ?

ያኔ አስጠልቶሽ አልመለስበትም እንዳላልሽ ዛሬ ህሊናሽ ፈቅዶልሽ ሁሉንም ረስቶ ሳለ ተመለስሽበት ኣ?

ዱንያ ላይ ካሉ መጥፎ ስሜቶች ውስጥ ነው ያለሽዋ? ራስሽን በጣም ጠልተሽው እየወቀስሽው ነዋ ?

አብሽሪ እህቴ ድጋሚ ወደጌታ:ሽ ተመለሽ ድጋሚ ቃል ግቢ!…ግን እንደ ዛሬው ቶሎ ቃልህን አታፍርሽ ከቃልህ ከዛሬው የበለጠ ጊዜ ለመቆየት ሞክር…ቀስ በቀስ የነበርሽበትን ትጠዪዋለሽ።

ትልቁ ክስረት ማለት ባሪያው ከሱ ወንጀል ለመመለስ በጌታው እዝነት ተስፋ የቆረጠበት ነው።
©jabir

በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡(ሱረቱ ዙመር 53)

اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
ወዶ በላካቸው እዝነቱን በእርሳቸው ባሳየን ወዱ ነብያችን የበዛ ሰለዋት ምናወርድበት በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ በተሳኩ ምኞቶች በጀሊሉ ራህመት የታጀበ የተዋበ ምርጥየ ጁምዐን ተመኘሁ

https://t.me/asdajlahh
🗓 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 2️⃣7️⃣ #ሻዕባን 1⃣4⃣4⃣5⃣
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
I ወላሂ! ወቢላሂ! ወተላሂ! ረመዷንን ሳይጠቀምበት ያለፈበት ማንም ሰው  ዑዝር የለውም!
ሸይኽ ሱዑድ ሹረይም
ዝሆኖቹ የዓመቱን ወርቃማ ሰዓታት ይዘርፉን ይሆን !?
★★★

ኢማሙ ማሊክ እንደወትሮው የነብዩ _ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም_ መስጂድ ውስጥ ተቀምጠው ሀዲስ ያቀራሉ...
በዙሪያቸው ያሉ ደረሳዎቻቸውም ትምህርቱን በትኩረት እየተከታተሉ ነው...ድንገት ያልተለመደ ድምፅ ተሰማ፡-
"ትልቅ ዝሆን፣ትልቅ ዝሆን …" የሚል…

ከዚህ ቀደም የመዲና ሰዎች ዝሆን አይተው አያውቁምና ዝሆን በማየታቸው የተፈጠረው ወከባ አይደንቅም ነበር።

የኢማሙ ማሊክ ደረሳዎች በሙሉ ዝሆኑን ለማየት እየተጣደፉ ኢማሙን ጥለዋቸው ሄዱ ...ከያህያ ቢን የሕያ አልለይሲ በስተቀር።

ኢማሙም የሕያን " ዝሆኑን ለማየት አብረሀቸው ለምን አልሄድክም፣ ወይስ ዝሆን ላንተ አዲስ አይደለም?" ሲሉ ጠየቁት።

እርሱም " መዲና የመጣሁት የርሶን ዒልም ለመቅሰም እንጂ ዝሆን ለማየት አይደለም " ሲል መለሰ።

ይህን ክስተት በደንብ ካጤንነው ወደ መዲና ለምን እንደመጣ እና አላማው ምን እንደሆነ ከተሰብሳቢዎቹ ጠንቅቆ የሚያውቀው አንዱ ብቻ ሆኖ እናገኘዋለን፤ ስለዚህ አልተዘናጋም፣ ትኩረት ሊያስቱ በሚችሉ አማላይ ነገሮች አልተሸነገለም።

በዚህም ምክንያት ኢማሙ ያህያ ቢን ያህያ አል-ለይሲ የኢማሙ ማሊክን አል-ሙወጠእ የተሰኘውን የሐዲስ ኪታብ በመዘገብ ልዩ ቦታ የሚሰጣቸው ሆነው እናገኛቸዋለን።

ሌሎች ጎደኞቹ የነበሩ ተማሪዎችን በተመለከተ ግን ታሪክ አልጠቀሳቸውም።

በእኛ ጊዜም የዝሆኑ ታሪክ ይደገማል...ነገር ግን በተለያዩ ምስሎች...እና በተለያዩ መንገዶች...በተለይ በረመዷን።

በረመዷን ሁለት አይነት ሰዎች አሉ፡–

1ኛ/ ግቡን ወስኖና ለይቶ... በረመዷን ውስጥ ማሳካት የሚፈልገውን ጠንቅቆ የሚያውቅ፤

2ኛ/በተለያዩ የዝሆን አይነቶች የተጠመደ... ፊልሞች፣ ገደብ የለሽ እንቅልፍ፣ ጫት እየቃሙ ማምሸት እና ሌሎች የዚህ ዘመን ዝሆኖች.. ‏ስለዚህ ከዘመኑ ዝሆኖች እንጠንቀቅ
የዓመቱን ወርቃ ሰዓት ይዘርፉናልና።

ረመዷን ከሪም!

ነስሩ ኸድር
ከረመዿን በፊት የመጨረሻውን ጁምዐ አንዴት ሆነን እያሳለፍነው ይሆን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ውብ_ውሎ
#ድንቅ_እሁድ
#መጋቢት_አንድ
#ሚሊኒየም_አዳራሽ
#ሁለት_ቀናት

ሁላችንም እሁድ  3:00 ሚሊንየም አዳራሽ ነሲሓ ኮንፈረንስ ላይ እንገናኝ