Artopian🎨
552 subscribers
238 photos
10 videos
2 files
4 links
The fear of the Lord is the beginning of wisdom.
@El_knows
Download Telegram
ያ ......ትሁቱ ሻማ
።፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨።

ያ ትሁቱ ሻማ፤
መስዋዕት ለመሆን ራሱን ባዶ ያረገ፣
ከደረቅ መሬት ለይ እንደ ስር ያደገ፣
መልክ ዉበት የሌለዉ በደዌ የደቀቀ፣
በሰዉ የተጠላ በሰዉ የተናቀ፣
ያ .....ትሁቱ ሻማ

ያ ትሁቱ ሻማ፤
ቤዛ ሆኖ ሊከፍል የሰውን ሁሉ እዳ፣
አንዳች ሳይናገር ለእሳት ሲነዳ፣
በጭንቅ ነበልባል ሲነድ በብዙ፣
እንደ ደም ሲወርድ ሲንጠባጠብ ወዙ፣
ያ .....ት ሁቱ ሻማ

ያ ትሁቱ ሻማ፤
በተከተሉት ፊት ሲሸነፍ ሲረታ፣
ምራቅ ሲተፋበት በጥፊ ሲመታ፣
ብረት ባለዉ ጠፍር በሃይል ሲገረፍ፣
ቆዳዉ ሲገሸለጥ ደሙ ሲጉረፈረፍ፣
ያ......ትሁቱ ሻማ

ያ ትሀቱ ሻማ፤
በሾህ ጉንጉን አክሊል ግንባሩ ሲበሳ፣
መስቀል ተሸክሞ ሲወድቅ ሲነሳ፣
በረዣዠም ምስማር እጅ እግሩ ሲጠረቅ፣
መጠማቱ ሲያይል አፍ ጉሮሮዉ ሲደርቅ፣
ያ...... ትሁቱ ሻማ

ያትሁቱ ሻማ፤
አልባሱ ተገፎ በ'ንጨት ሲንጠለጠል፣
በህማሙ ንዳድ ሲቃትት ሲቃጠል፣
ጅማተ አጥንቱ በ'ሳት ተለኩሷል፣
ሰዉነቱ ቀልጧል በፍም ተገማምሷል።
ያ....... ትሁቱ ሻማ

ያ ትሁቱ ሻማ፤
ከቆሰለ አካሉ ደሙ እየወረደ፣
ብርሃን ያበራልን እሱ እየነደደ፣
አበቃለት ሲሉ መቼ ቀረ ቀልጦ?!
በ ሶስተኛ ቀኑ ታይቷል ሁሉን በልጦ።

@artopian
Forwarded from Artopian🎨
--^~__/^\__¡__^~_^--

አንድ ትንሽ ማሽን በሃኪም ቤት ያለች፣
እውነታን በመስመር በርግጥ ታሳያለች።
ሰው በህይወት ካለ ዚግዛግ ገባ ወጣ፣
ደሞ ልሙጥ መስመር ሰው ነፍሱ ከወጣ።
........
አባጣ ጎርባጣ፣
ደሞ ገባ ወጣ፣
ሸለቆና ዳገት፣
ቁልቁለት አቀበት፣
ይሄ ከሌለበት፣
የምትኖረው ህይወት፣
ያውም በዚች አለም፣
እመነኝ ግድ የለም፣
ታሪክህ አበቃ፣
ሞተሃል ነው በቃ።

artopian
#repost
Forwarded from Artopian🎨
፨፨ተረቱና እውነቱ፨፨

ላልነገረ ህመሙን፣
መድሃኒት የለውም፣
ተብሎ ሲተረት፣
ምሳሌና ተረት፣
መድሃኒት ብትሻ፣
ከ'መም መፈወሻ፣
መናገር ቢያቅታት፣
ግፊያውም ቢያግዳት...
አልያም ምናልባት፣
ሰው ስለበዛባት፣
ህመሟን ለማውራት፣
ቢሆን ያሳፈራት፣
ምንም ሳትናገር፤
ጨርቁን ስትዳስሰው፣
የውስጧን የሚያውቀው፤
ህመሟን ፈወሰው።

ልክ እንደተረቱ፣
ቢሆን ኖሮ እውነቱ፣
ሚያስጨንቀን ነገር፣
ሲሆን ማይነገር፣
ማውራት ሳንችል ስንቀር፣
ምን ይውጠን ነበር?!

✏️unknown
artopian
#repost
📙 book cover design
🔸graphics
@artopian
፨፨፨፨፨፨፧።፧፨፨፨፨፨፨

የመኖሬ ሚስጥር የጥሜ መቁረጫ፣
ካሳዳጁ አዉሬ ከጠላት ማምለጫ፣
ምታነፃ 'ድፌን ምትቀይር ጠረኔን፣
መአዛህን ሰጥተህ አስወግደህ የኔን፣
ደረቅ በረሃዬን የምታረሰርስ፣
በምትገኝበት ምናፍቅ ልደርስ፣
ባጣህ የምዋትት ምባዝን ምከፋ፣
ያላንተ የማልኖር ብለይህ ምጠፋ፣
የነብሴን ባዶነት በ'ርካታ ምትሞላ፣
አንተ የ'ይወት ውሃ እኔ ደሞ ዋላ።

artopian
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM