Artopian🎨
552 subscribers
238 photos
10 videos
2 files
4 links
The fear of the Lord is the beginning of wisdom.
@El_knows
Download Telegram
🎨Acrylic on canvas
።፨።ልዩ ፍቅር።፨።

እንደበግ ተቅበዝብዤ፣
የመጥፊያዬን መንገድ ይዤ፣
ሙት የነበርኩ በሀጥያቴ፣
የማልጠቅም ምናምንቴ፣
የማስተውል አልነበረ፣
የሚገባኝ ሞት ነበረ።
እንዳይቀጣኝ በእውነቱ፣
ይቅር አለኝ በም'ረቱ፣
ይቅርታው ሳያንሰኝ፣
በደሙ ቀደሰኝ፣
እኔን እያወቀኝ፣
በጸጋው አጸደቀኝ።
ሀጥአን ለይ አለመፍረድ፣
ፃድቃን ለይ መፍረድ
በሱ ዘንድ ሁለቱ፣
የማይገመቱ።
ጻድቅ ፈራጅም ነው፣
ያረገው ይሄን ነው።
በደሌን ጠቅላላ፣
ሀጢአቴን በሞላ፣
ወረደና ከላይ፣
አኖረ ራሱ ላይ፣
ተጨነቀ ነፍሱ፣
በኔ ምትክ እሱ፣
የሰው ስጋ ለብሶ፣
በሀሰት ተከሶ፣
በደዌ ደቀቀ፣
በህማም ማቀቀ፣
በስቃይ ቃተተ፣
የመስቀል ሞት ሞተ።
ዘላለም ሚደነቅ፣
የሚያልፍ ከመታወቅ፣
ያለና ሚኖረው፣
ልዩ ፍቅር አለው።
¤፧፧፧፧¤

ክብሩን ሚያሳንሰው፣
ሚያዋርድ ሚያረክሰው፣
ውስጡ የገባ ሳይሆን፣
የወጣው ነው ከሰው፣
የፍጥረት ፈጣሪ፣
ውብ አድርጎ ሰሪ፣
አንድ ምላስ እና ሁለት ጆሮ የሰጠን፣
ከመናገር ይልቅ እንድንሰማ አብልጠን፣
ውስጠት እንዳይረክስ በሚያወጣው ነገር፣
መስማት እንጂ ፈጥኖ ዘግይቶ መናገር።
@artopian
ያ ......ትሁቱ ሻማ
።፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨።

ያ ትሁቱ ሻማ፤
መስዋዕት ለመሆን ራሱን ባዶ ያረገ፣
ከደረቅ መሬት ለይ እንደ ስር ያደገ፣
መልክ ዉበት የሌለዉ በደዌ የደቀቀ፣
በሰዉ የተጠላ በሰዉ የተናቀ፣
ያ .....ትሁቱ ሻማ

ያ ትሁቱ ሻማ፤
ቤዛ ሆኖ ሊከፍል የሰውን ሁሉ እዳ፣
አንዳች ሳይናገር ለእሳት ሲነዳ፣
በጭንቅ ነበልባል ሲነድ በብዙ፣
እንደ ደም ሲወርድ ሲንጠባጠብ ወዙ፣
ያ .....ት ሁቱ ሻማ

ያ ትሁቱ ሻማ፤
በተከተሉት ፊት ሲሸነፍ ሲረታ፣
ምራቅ ሲተፋበት በጥፊ ሲመታ፣
ብረት ባለዉ ጠፍር በሃይል ሲገረፍ፣
ቆዳዉ ሲገሸለጥ ደሙ ሲጉረፈረፍ፣
ያ......ትሁቱ ሻማ

ያ ትሀቱ ሻማ፤
በሾህ ጉንጉን አክሊል ግንባሩ ሲበሳ፣
መስቀል ተሸክሞ ሲወድቅ ሲነሳ፣
በረዣዠም ምስማር እጅ እግሩ ሲጠረቅ፣
መጠማቱ ሲያይል አፍ ጉሮሮዉ ሲደርቅ፣
ያ...... ትሁቱ ሻማ

ያትሁቱ ሻማ፤
አልባሱ ተገፎ በ'ንጨት ሲንጠለጠል፣
በህማሙ ንዳድ ሲቃትት ሲቃጠል፣
ጅማተ አጥንቱ በ'ሳት ተለኩሷል፣
ሰዉነቱ ቀልጧል በፍም ተገማምሷል።
ያ....... ትሁቱ ሻማ

ያ ትሁቱ ሻማ፤
ከቆሰለ አካሉ ደሙ እየወረደ፣
ብርሃን ያበራልን እሱ እየነደደ፣
አበቃለት ሲሉ መቼ ቀረ ቀልጦ?!
በ ሶስተኛ ቀኑ ታይቷል ሁሉን በልጦ።

@artopian
Forwarded from Artopian🎨
--^~__/^\__¡__^~_^--

አንድ ትንሽ ማሽን በሃኪም ቤት ያለች፣
እውነታን በመስመር በርግጥ ታሳያለች።
ሰው በህይወት ካለ ዚግዛግ ገባ ወጣ፣
ደሞ ልሙጥ መስመር ሰው ነፍሱ ከወጣ።
........
አባጣ ጎርባጣ፣
ደሞ ገባ ወጣ፣
ሸለቆና ዳገት፣
ቁልቁለት አቀበት፣
ይሄ ከሌለበት፣
የምትኖረው ህይወት፣
ያውም በዚች አለም፣
እመነኝ ግድ የለም፣
ታሪክህ አበቃ፣
ሞተሃል ነው በቃ።

artopian
#repost
Forwarded from Artopian🎨
፨፨ተረቱና እውነቱ፨፨

ላልነገረ ህመሙን፣
መድሃኒት የለውም፣
ተብሎ ሲተረት፣
ምሳሌና ተረት፣
መድሃኒት ብትሻ፣
ከ'መም መፈወሻ፣
መናገር ቢያቅታት፣
ግፊያውም ቢያግዳት...
አልያም ምናልባት፣
ሰው ስለበዛባት፣
ህመሟን ለማውራት፣
ቢሆን ያሳፈራት፣
ምንም ሳትናገር፤
ጨርቁን ስትዳስሰው፣
የውስጧን የሚያውቀው፤
ህመሟን ፈወሰው።

ልክ እንደተረቱ፣
ቢሆን ኖሮ እውነቱ፣
ሚያስጨንቀን ነገር፣
ሲሆን ማይነገር፣
ማውራት ሳንችል ስንቀር፣
ምን ይውጠን ነበር?!

✏️unknown
artopian
#repost