Artopian🎨
551 subscribers
238 photos
10 videos
2 files
4 links
The fear of the Lord is the beginning of wisdom.
@El_knows
Download Telegram
Digital illustration(adobe draw)
''ይቅር አትበለኝ''
፨፨፨፨፨፨፨፨፨


ሚከፍለውን መክሊት አጥቶ የተቸገረ፣
እልፍ እዳ ያለበት አንድ ሰው ነበረ፣
ጌታው ሀብቱን መቁጠር በወደደ ዕለት፣
ይህንን ባለ'ዳ ይዘው አመጡለት።
ሚስት እናት ልጆቹ ያለው ሁሉ እንዲሸጥ፣
እዳውን እንዲከፍል ንጉስ ትዛዝ ሲሰጥ፣
ባርያውም የጌታው እግር ስር ወደቀ፣
ጊዜ እንዲሰጠው አጥብቆ ጠየቀ።
እንዲህ ሲማጸነው ንጉስ አዘነለት፣
ዕልፍ ዕዳውን ሁሉ ራራና ተወለት።
ግን ያ ባርያ ወጥቶ ከባልንጀሮቹ፣
ጥቂት እዳ ያለውን አነቀው በ'ጆቹ።
የሱ ባልንጀራ ከፍልሃለው ቢለው፣
ትንሽ እንዲታገስ ብዙ ቢለምነው፣
እርሱም አልወደደም ፈጽሞ ሊምረው፣
እዳውን እስኪከፍል በወህኒ አኖረው።
ዕልፍ ዕዳው በሞላው ባርያው ተትቶለት፣
የወንድሙን እዳ መተው ጭንቅ ሆነበት፣
ይህንን ሲሰማ ንጉሱ ባለበት፣
የማረውን ሁሉን ተወው ሰረዘበት፣
''ክፉ ባርያ'' ብሎት ጌታው ባንደበቱ፣
አሳልፎም ሰጠው ለሚያሰቃዩቱ።
ም'ረት ያገኘ ሰው እዳ የተተወለት፣
ለወንድሙ ይቅርታ ግን ማያረግለት፣
''አባታችን ሆይ'' ሲል ጸሎቱ ሚሆነው፣
''ይቅር እንደማልል ይቅር አትበለኝ ነው።''

@artopian
Work in progress🙃...with colored ball point pens for the very first time
1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
My first acrylic painting on canvas🎨
🔘Size (60*80)cm
🔘title- ''yeselam liguam''
🤔መስቀል አንደበት ቢኖረው ምን ይነግረን ነበር?
፨፨፨፨፨፨


ከመስቀሉ አንደበት 🗣

"ባይነ ህሊናዬ የኋሊት ገስግሼ፣
በትዝብት በቁጭት ያኔን አስታውሼ፣
የርግማን ምልክት የሆንኩ ከፍጥረቴ ፣
የተከወነውን ላውራ ባንደበቴ።

ሰው ያላከበረው ፈጽሞ የተናቀ፣
ከቶ የተጠላ ደዌንም ያወቀ፣
ራሱን ባዶ ያረገ ከሰማይ ወረደ፣
በከብቶች ማደሪያ በረት ተወለደ።
ለሁሉ ደቀቀ ለሁሉ ታመመ፣
የብዙውን በደል ሀጢአት ተሸከመ፣
የ'ጆቹ ፍጥረት ግን ልባቸው ደንድኖ፣
ማስተዋል ጎድሏቸው ክፋታቸው ገኖ፣
በሀሰት ከሰውት ተላልፎ ተሰቶ ፣
ንጹኹ ሊታሰር በርባን ግን ተፈቶ፣
"ስቀለው ስቀለው" አሉት ጲላጦስን፣
አልቀበል ብለው ጠልተው ክርስቶስን።
ጲላጦስም ገርሞት የሀሰት ክሳቸው፣
እጆቹን ተጣጥቦ ሊገድሉት ሰጣቸው።
እየዘበቱበት ቀይ ልብስ አልብሰውት፣
አይኖቹን ሸፍነው በጥፊ መተውት፣


ትንቢት ተንብይ ሲሉ ተዘባበቱበት፣
የሾህ አክሊል ጎንጉነው ራሱ ላይ ደፉበት፣
በመቃ እየመቱት ጎሰሙት ተፉበት::
ብረት ባለው ጠፍር ገርፈው አቁስለዉት፣
ከሁለት ወንበዴዎች መሀል ለይ ሰቅለውት፣
እሱ ግን ይቅር ባይ ምህረት የወደደ፣
አመጻቸውን አይቶም ለህዝቡ ማልደ።

"ክርስቶስ አይደለህ አድነህ ራስህን
እስቲ እኛንም አድን እንየው ሀይልህን።"

ሲል አንዱ ወንጀለኛ ህዝቡም ሲተባበር፣
ግን ደሞ ሌላኛው መልሱ እንደዚህ ነበር።
" እኛስ በድለን ነዉ እሱ ምን በደለ፣
ክፋትን ሳይሰራ ነው የተሰቀለ።"

የተረገመን ነዉ በኔ ሚሰቅሉቱ፣
ተብሎም ተጽፏል ይሄ ነው እውነቱ።
የአማልክት አምላክ ጻድቁ ቅዱሱ፣
እርግማን የሆነው ለሁሉ ነው እሱ።

በተማሪዎቹ ፊት ረቡኒ በሚሉት፣
አልባሱን ገፈውት በርቃኑ የሰቀሉት፣
ማን እንደሚወስድ- አውቀው ሊካፈሉ፣
እጀ ጠባቡ ለይ እጣ ተጣጣሉ።

ተጠማው ሲላቸው በደከመ ድምጹ፣
መች ልባቸው ራራ ይብሱን አመጹ።
በሰፍነግ ሆምጣጤ አረስርሰው ሰጡት፣
ደሞ ብለው ብለው ጎኑን በጦር ወጉት።
የተረገመን ነው በኔ ሚሰቅሉቱ፣
ተብሎም ተጽፏል ይሄ ነዉ እውነቱ፣
የአማልክት አምላክ ጻድቁ ቅዱሱ፣
እርግማን የሆነው ለሁሉ ነው እሱ።''

@artopian
"The tongue is like a sharp knife: it kills without drawing blood. "

#Learn_how_and_when_to_use_it.

#inktober #inktober2020 #blade #prompt5

@artopian
🐭 #rodents have a pair of upper & a pair of lower teeth that never stop growing.They must chew on things constantly to wear their teeth down & survive.

#inktober2020 #rodent
@artopian