Artopian🎨
552 subscribers
238 photos
10 videos
2 files
4 links
The fear of the Lord is the beginning of wisdom.
@El_knows
Download Telegram
፨፨፨፨

በህይወት ጎዳና ለኑሮው ሲዳዳ፣
ወድቆ ሲቀር ስንቱ በወረርሽኝ ሜዳ፣
መኖር በሞት ጥላ ሂደቱ ሲዛነፍ፣
የሰው ነፍስ በዋዛ እንደ ቅጠል ሲረግፍ፣
ቀባሪ አስቀባሪ የሚሆን ሲጠፋ፣
ሚታየው ሚሰማው ቀን በቀን ሲከፋ፣
ስልጡን ባለጸጋ ሃያላን ነን ያሉ፣
ሚጨብጡት ሲያጡ ሽንፈት ስር ሲውሉ፣
ጠቢባን ምሁራን ሊቃውንት ስመጥር፣
ማወቅ ሲሳናቸው የ ኮቪዱን ሚስጥር፣
አይን ሲንከራተት ተራራ ሲወጣ፣
አወይ ጣር ሰቀቀን ረዳት ከየት ይምጣ?
......
ሰማይና ምድርን በቃሉ የፈጠረው፣
ረዳትማ እሱ ያለና ሚኖረው።
የሀገሬ ድንኳን እጅግ ተጨንቃለች፣
እግዚኦ ማረን ብላ እጇን ዘርግታለች።
ጎልያድ በጠጠር የመውደቁ ነገር፣
አምላክ በ'ስራኤል ዘንድ እንዳለ ሊነገር።
በኛም ዘንድ ኤሎሄ መኖሩ ይታወቅ፣
ይ' ባይን ማይታይ በጾም ጸሎት ይውደቅ።
፨፨፨፨

ሃና መለሰ
@artopian
@artopian
Forwarded from Amazing arts🤡 (Mek A)
Forwarded from Blen arts🎨📃 (Blen m)
--^~__/^\__¡__^~_^--

አንድ ትንሽ ማሽን በሃኪም ቤት ያለች፣
እውነታን በመስመር በርግጥ ታሳያለች።
ሰው በህይወት ካለ ዚግዛግ ገባ ወጣ፣
ደሞ ልሙጥ መስመር ሰው ነፍሱ ከወጣ።
........
አባጣ ጎርባጣ፣
ደሞ ገባ ወጣ፣
ሸለቆና ዳገት፣
ቁልቁለት አቀበት፣
ይሄ ከሌለበት፣
የምትኖረው ህይወት፣
ያውም በዚች አለም፣
እመነኝ ግድ የለም፣
ታሪክህ አበቃ፣
ሞተሃል ነው በቃ።

@artopian
፨፨ተረቱና እውነቱ፨፨

ላልነገረ ህመሙን፣
መድሃኒት የለውም፣
ተብሎ ሲተረት፣
ምሳሌና ተረት፣
መድሃኒት ብትሻ፣
ከ'መም መፈወሻ፣
መናገር ቢያቅታት፣
ግፊያውም ቢያግዳት...
አልያም ምናልባት፣
ሰው ስለበዛባት፣
ህመሟን ለማውራት፣
ቢሆን ያሳፈራት፣
ምንም ሳትናገር፤
ጨርቁን ስትዳስሰው፣
የውስጧን የሚያውቀው፤
ህመሟን ፈወሰው።

ልክ እንደተረቱ፣
ቢሆን ኖሮ እውነቱ፣
ሚያስጨንቀን ነገር፣
ሲሆን ማይነገር፣
ማውራት ሳንችል ስንቀር፣
ምን ይውጠን ነበር?!

✏️unknown
@artopian
Channel photo updated
1
"ማነው?" ሲሉ
፨፨፨፨፨፨
"አምላክ የምትይው የታለ ቆይ እሱ?
ማነው? አላየነው" ሲሉ እየተነሱ
እኔም የምሰጠው ከውስጠት ከነፍሴ
ማልፀፀትበት ይኸውና መልሴ።
የሁሉ መገኛ የፍጥረት መሰረት
መነሻ የሌለው መድረሻ አልባ ጅረት
ሁሉም ቦታ አለ ታችም ሆነ እላይ
ምድር መረገጫው ዙፋኑ ነው ሰማይ
ባህሪ ፀባዩን የሱነቱን ሚስጥር
ለማውቅ በጣሩ በፈለጉ ቁጥር
ባይመረመርም ርቆ እንኳ አድማሱ
አልፋና ኦሜጋ የቅርብ ነው እሱ
ሞቶ የማዳኑን የፍቅሩን ቀመር
ከራሱ በስተቀር ማን ገልጦት ሲጀመር
በየለቱ አዲስ ከቶ ማይለመድ
ደመናት ለይ ሚሄድ ውሃ ለይ ሚራመድ
አይደለም በቃላት ልገልፀው በ ሆሄ
ከመታወቅ ያልፋል ማንነቱ ኤሎሄ።

@El_knows

💥@artopian
የኖረው ሲሞት ነው

፨፨፨፨፨፨፨፨
ነፍሱ ከስጋው ላይ
ያኔ ሳትለያይ
እስትንፋሱ ሳለ
በምድር እያለ
አልን በ'ይወት አለ።
ሚጠይቀው ጠፍቶ
ዘመድ ወዳጅ አጥቶ
ኖሮ በሰቀቀን
ከለታት አንድ ቀን
ያቺ አንድ ነፍሱ
ስትጠፋ ከሱ
ሲበድን አካሉ
''ወይኔ ሞተ'' አሉ
ከዛም እንዳረፈ
በ'ድር ተለፈፈ።
ሰው ተሰበሰበ
ቤት ጊቢው ጠበበ
መሞቱን ሲሰማ መኖሩን የረሳ
የሟች ባህሪውን አስታውሶ አወሳ
ስራው ተነገረ
ስሙ ተዘከረ
ታድያ ነፍሱ እያለ 'አለ' ማለት ምነው?
አልገባንም እንጂ የኖረው ሲሞት ነው።

2005 ዓ.ም
@El_knows