የጥበብ አርበኞች
238 subscribers
61 photos
4 videos
9 files
9 links
ሀሳብን ይዘን ስለ እሳቤዎቻችን በነፃነት ልናወጋ.....ከተለያዩ ምልከታዎች አንፃር....ግርምቶቻችንን ትዝብታችንን...ያስተዋልናቸውን ሁነቶች ልንጋራ..ብእራችንን በሀሳብ ሞረድ ስለን የጥበብ አርበኞች ለመሆን ለመፍጨርጨር እነሆ ተነሳን.....እንኳን መጣችሁ😊😊😊።

ኢትዮጵያዊነትን ተላብሰን ስለ አንድነት እንዘምር።
Download Telegram
ውዶቼ ልባችሁ በየትኛውም ሁነት በየትኛውም ንግግር በተደጋጋሚ እንዲሸረሸር አትፍቀዱ.....የሆነ ቀን ልትደርሡ ካሰባችሁበት ማንነት እንዳትደርሡ ትደክማላችሁና።

አደራ ልባችሁን ጠብቁት።😊😊😊

ሰላም ለልባችሁ።😊😊😊
❤4👍3🔥1
እያየነው አደገ በሚለው ንግግራቸው ውስጥ ስንቱን እንዳሳለፍን ያውቁልን ይሆን???
❤8🔥5💯1
የተወደዳችሁ......አለመታየታችሁን ውደዱት....ስለ እናንተ ጉብዝና ስለ እናንተ ውበት ስለ እናንተ አለባበስ ስለ እናንተ ሀብት ስለ የትኛውም ነገራችሁ አለመወራቱ ሰላማችሁ ይሁን.......ራሳችሁን ለማሳየት ብላችሁ too much አትልፉ.....

እወነተኛ የሆነ እና ለሠዎች እይታ ተብሎ ያልተገነባ ሸግዬ ማንነት አላሳየውም ብትሉ እንኳ መታየቱ አይቀሬ ነው.......ራሳችሁን ብቻ ሁኑ😊😊😊

ሰላማችሁ ይብዛልኝ😊😊😊

ሰናይ ውሎ😊😊😊
❤16🔥1
የጥበብ አርበኞች pinned «የተወደዳችሁ......አለመታየታችሁን ውደዱት....ስለ እናንተ ጉብዝና ስለ እናንተ ውበት ስለ እናንተ አለባበስ ስለ እናንተ ሀብት ስለ የትኛውም ነገራችሁ አለመወራቱ ሰላማችሁ ይሁን.......ራሳችሁን ለማሳየት ብላችሁ too much አትልፉ..... እወነተኛ የሆነ እና ለሠዎች እይታ ተብሎ ያልተገነባ ሸግዬ ማንነት አላሳየውም ብትሉ እንኳ መታየቱ አይቀሬ ነው.......ራሳችሁን ብቻ ሁኑ😊😊😊 ሰላማችሁ ይብዛልኝ😊😊😊…»
ተወለደ....አደገ.....አገባ....ወለደ....አረጀ.....ሞተ ለመባል ብቻ ወደዚች ምድር ተልከናል ብዬ አላምንም እኔ እንደ ሀሳብ።

ሁላችንም መጀመሪያ ከእናታችን ማህፀን ስንወጣ አሁን ያለን የትኛውም ማንነት አብሮን አልተወለደም።

ሌባ የወለደችም ጨዋ የወለደችም እኩል ስለ ልጇ ትጨነቃለች እንደሚለን ተረት......ዛሬ ላይ በክፋታቸው የሚታወሱትም በመልካምነታቸው የሚሞገሱትም የሆነ ቀን ላይ ንፁህ ሆነው ተወልደዋል....

በመወለድ እና በመሞት ውስጥ ምርጫ የሚባል ነገር አለ.......አቅል የሚባል ነገር የተሰጠን ደግሞ መምረጥ እንድንችል ነው...

የትኛውን እንምረጥ???...... ተወለደ አደገ ሞተ ብቻ መባልን ወይስ ተወለደ አደገ ለዚች አለም ይሄን አበርክቶ ሞተ መባልን...

ምርጫው የእኛ ነው።
መምረጥ እንቻል የዛሬው መልዕክቴ ነው።

ለመታረም ዝግጁ ነኝ።
ሰናይ ቅዳሜ😊😊😊

✍️ እስማኤል አሰለፍ አየለ
❤8🔥2
አሁንን ኑሩትማ ውዶቼ......ትላንት ባሳለፍነው መልኩ ሆኖ አለፈ......ነገ ገና መጪ አለም ነው ያውም እንኑርበት አንኑርበት የማናውቀው የተስፋ አለም......ትላንት ያለፈ ከሆነ ነገ መጪ ከሆነ ሁለቱም በእጃችን አለመሆናቸው እሙን ነውና ያለንን በሚገባ እንወቅ.....ውዶቼ ያለን አሁን ነው....ነገ ትላንት ብለን የምናወራው የዛሬ አሁናችንን ነው......

አሁናችሁን ኑሩት....
እየኖርን....😊😊😊

ሸጋ ምሽት

ቤታችንን ለወዳጆቻችሁ ሼር እያደረጋችሁ አሳድጓት😊😊😊
❤13
የጥበብ አርበኞች pinned «አሁንን ኑሩትማ ውዶቼ......ትላንት ባሳለፍነው መልኩ ሆኖ አለፈ......ነገ ገና መጪ አለም ነው ያውም እንኑርበት አንኑርበት የማናውቀው የተስፋ አለም......ትላንት ያለፈ ከሆነ ነገ መጪ ከሆነ ሁለቱም በእጃችን አለመሆናቸው እሙን ነውና ያለንን በሚገባ እንወቅ.....ውዶቼ ያለን አሁን ነው....ነገ ትላንት ብለን የምናወራው የዛሬ አሁናችንን ነው...... አሁናችሁን ኑሩት.... እየኖርን....😊😊😊…»
Forwarded from የሃሳብ ጠብታዎች💧 (Nesru)
✨
👏6
የሃሳብ ጠብታዎች💧
✨
ይቺን ቤት ተቀላቀሏት...በብዙ ታተርፋላችሁ😊😊😊
🥰2
Forwarded from የሃሳብ ጠብታዎች💧 (Nesru)
🍂

ካስተዋልነው አፈጣጠራችን በራሱ የሚነግረን ነገር አለ ። ብዙዙ ማዳመጥና ትንሽ ማውራት እንዳለብን የጆሯችንና የምላሳችን አፈጣጠር የሚነግረን ይመስለኛል ። ምክንያቱም 2 ጆሮ 1 ምላስ ነው ያለን ። ብዙ ነገር የሚሰጠን ሃጃው ብዙ ሲሆን ነው ። ሰዎችዬ ስናዳምጥ ብዙዙ ፤ ስናወራ  ደግሞ ትንሽ ይሁን ። ብዙዙ የተሰጠን ምን አለ ሌላስ ? ብዙ ጤና ? ብዙ ህመም ? ብዙ ጊዜ ? ብዙ ችግር ? ብዙ ገንዘብ ? ብዙ ጉልበት ? ብዙ ምን አለን ሰዎችዬ !? ያለምክንያት የበዛ እንዳይመስላችሁ ። ከመብዛቱ ጀርባ  የያዘው ምስጢር አለው ። አብዝተህ የሰጠኸኝ ለምንድን ነው ? ብላችሁ ጌታችሁን ጠይቁት ። በጥያቄያችሁ ውስጥ መልሱን ታገኙታላችሁ ። ሰዎችዬ ከህይዎት ተማሪ መሆን ጥሩ ነው ! እንማርማ😊...


መልካም ህይዎት✨



@fezekir_fe
🥰5❤2
ተው ተው ተው እንጂ ወገን ላስብበት እንዴ ሀይ😊😊😊


ልማድ ሆኖብን የሆነ ሰው ዝም ብሎ የሆነ ነገር ላይ እያተኮረ እያብሰለሰለ ስናይ " ምን እያሰብክ ነው manye.....ኧረ አንቺ ምንሼ ነው ብዙ አታስቢ......ምንድን ነው እህቴ በዚህ እድሜሽ እንደዚ ማሰብ " ብቻ ብዙ ብዙ እንላለን...

ሰዎች ነን እኮ ውዶቼ....ማሰብ አለብን " ምን ማድረግ እንዳለብን....ምን ማውራት እንዳለብን.....የት እና መቼ ሁነቶች ላይ መገኘት እንዳለብን...ስለ ጤናችን...ስለ ትምህርታችን...ስለ ስራችን...ስለ ቤተሰባችን...ስለ እምነታችን....ስለ ነጋችን...ስለ.....ስለ.....ስለ.......ወ.ዘ.ተ ልናስብ ግድ ይለናል።

አብዝቶ መጨነቅን እና ማሰብን ግን እየለየን......መጨነቅ ማሰብ አይደለም እሺ የተወደዳችሁ....

እናማ የዛሬው መልዕክቴ እኛም እናስብ ሌሎችም ያስቡ ዘንድ እንፈቅድ ( አታስቡ ማለት ሳይሆን አስቡ ይልመድብን ) ነው።

ሀሳባችሁን አጋሩን።
ለመታረም ዝግጁ ነኝ😊😊😊

✍️ እስማኤል አሰለፍ አየለ
❤8👌3🥰2👍1
"የኔ ልጅ " አሉኝ....." አቤት አባቴ "...

" ሰውን ስትወድ ያለ ቅድመ ሁኔታ ውደድ እሺ....ሰውን ስትወድ በምላሹ ምንም ላላገኝ ብለህ ውደድ....ሰውን ዝምምም ብለህ ውደድ እሺ😊😊😊 "
❤2
Channel photo updated
ቤታችንን ለጓደኞቻችሁ ሼር እያደረጋችሁ አሳድጓት.....ብዙ ብዙ አዳዲስ ነገሮችን ይዘን እንመጣለን።
❤1
ዛሬ ሰርግሽ ነው !!😓

አለምሽ ነው!!

ወትሮም ውበት የደፋበት ፊትሽ ተሽሞንሙኖ ከሩቅ ያንፀባርቃል፣ሁሉም እየደጋገመ በቻለው ልክ ውበትሽን እና ማማርሽን ሊገልፅልሽ ይባክናል.....ዛሬ ቀንሽ ነው!
ከዚያ ሁሉ ሰው መሀል ጎልተሽ የምትታዪው አንቺ ነሽ.....በዛ ሁሉ ጫጫታ ውስጥ የፊትሽ ርጋታ የተሸበረ ልብን ያሰክናል.....

አዎ አንቺ እንደዛ ነሽ በጫጫታ መሀል  ማረፊያ የምትሆኚ፣ በድቅድቅ ሀዘን ወስጥ ሰላም የምታለብሺ ሙሉ ሴት ነሽ!!!

በየትኛው ሰአት በየትኛው ቦታ ማን መሆን እንዳለብሽ ታውቂያለሽ!!ለመጣው ሁሉ አታሸረግጂም ለበደለሽ ሁሉ ፊትሽን አታዞሪም!!!

አንቺ ካለሽ በቦታው ደስታ እና ሳቅ ይደራል.....በሄድሽበት፣ባለፍሽበት ሰላምን ብቻ ትዘሪያለሽ.....ከቋጥኝ የከበደው ችግር አንቺ ስተኖሪ የላባ ያክል ይቀላል.....አንቺ እንደዛ ነሽ በቃ!!!

ይሄው ዛሬም በደስታሽ ቀን ከሩቅ ሆኜ አየሁሽ፣ነጩ ቀሚስ የበለጠ አሳምሮሻል....ለወትሮው የምትጠቀልዪው ዞማ ፀጉርሽ በትካሻሽ ላይ ተዘናፍሏል....ሰው ሁሉ ፈዞ ያይሻል...በአንድ እይታ አትጠገቢም....በሙሉ አይን እንዳትታዪ ታሳሺያለሽ....

በዚህ ሁሉ ጥድፊያ ውስጥ አንቺ ተረጋግተሻል፣በጩኸት ውስጥ ተክዘሻል....ምን እያሰብሽ ይሆን?

ቃልሽ ታውሶሽ ይሆን?

ትዝ ይልሻል?በዚህ ቀን ላተክዢ ፣በዚህ ቀን ልታብጂ፣በዚህ ቀን ብዙ ልቶኚ ቃል ገብተሽ ነበር.....እኔ ግን አረሳሁትም.....በዚህ ቀን አብሬሽ ልሆን፣ወንድነቴን ትቼ ከሴት ሚዜዎችሽ ጎን ተደርድሬ ላጅብሽ ቃል ገብቼ ነበር.....አየሽ እኔ ቃሌን አላጠፍኩም ባታይኝም ከጎንሽ ነኝ........እንደሌሎች ተጠግቼ ውበትሽን ላደንቅልሽ፤መልካም ምኞቴን ልገልፅልሽ ባልታደልም ከሩቅ ሆኜ ቃሌን ለመጠበቅ እየሞከርኩ ነው......

ለኔ ጊዜ ሁሌም ከጎኔ ነበርሽ፣ጭንቀቴን አዳምጠሽ ለመፍትሄ ላይ ታች ብለሻል....የተበላሸ ማንነቴን ለመቀየር ራስሽን ዝቅ አድርገሽ በማይገባሽ እየዋልሽ ታግለሻል......የወደኩ ጊዜ አበርትተሽ አንስተሽኛል.....ልብን በሚሰርቅ ፈገግታሽ፣ክፋት በሌለው ንፁህ ልብሽ ሸሽገሽኛል.....አየሽ እኔ ግን ለደስታ ቀንሽ እንኳን ጎንሽ ልሆን አልቻልኩም.....ከሩቅ አይሻለሁ እንደተከዝሽ ነሽ!!

ዘፈኑ ጀመሯል

ሙሽራዬ ሙሽራዬ የወይን አበባዬ ....ሙሽራዬ፣ሙሽራዬ የወይን አበባዬ

እውነትም ሙሽራ ፣አንቺ ዛሬ አይደለም ሙሽራ የሆንሽው....አንቺ ሁሌም ሙሽራ ነሽ!
አንቺ በህይወት ውስጥ ዳግም የማትከሰች ፣በዚህ አለም ድጋሚ የማትበቅዪ የሁልጊዜ ሙሽራ ነሽ!!

አንቺ ጋር ያስቀመጥኩት ፣ከኔ ጋር ያኖርኩት ብዙ እኔነት አለኝ.....ታሪኬ ነሽ....ተነግረሽ የማታልቂ፣ተዘርዝረሽ የማታበቂ...ሁሌም አዲስ፣ሁሌም ትእንግርት የሆንሽ ሙሽራዬ......

በይ መልካም ህይወት....ቃሌን ጠብቄያለሁ!ያው ባልሽ መጣ ...እጅሽን ያዘሽ....አሁን ልሂድ!!

ከልብሽ የሰጠሺኝ መልካምነት፣ያለስስት ያስታቀፍሽኝ የማያልቅ ፍቅር ለቀረው ዘመኔ ስንቅ ነው!!!.....ሂጂ ወደ ጎጆሽ....ሂጂ ወደ አዲሱ ህይወት ....ፈቅጄያለሁ፣ቅር አይለኝም......የሰጠሽኝ ይበቃኛል፣ያስታቀፍሽኝ ያኖረኛል....ሂጂ፦ልሂድ
❤4
Forwarded from የሃሳብ ጠብታዎች💧 (Nesru)
🍂


አንዱ አፍቃሪ ለልቡ ሴት የሚያምር መልክ ፣ የሚያምር ልብ ፣ የሚያምር ፈገግታ ፣ የሚያምር ስብእና ሲባል አእምሮዬ መልክሽን ፊቴ ላይ አምጥቶ ድቅን ያደርግልኛል ፤ ሁሉንም ያየውት ባንች ነው አላት... ልቡ ልቧን ወዶት የለ !? ልብ ልብን ሲወድ ደግሞ ዓይን ነውርን አይመለከትም ።  መስመሩን ካለፉ ወዲያ ዝም ብሎ መውደድ ፣ ዝምም ብሎ ማፍቀር ፣ ዝምም ብሎ መደናገር ነው ። ይሄ ፍቅር የሚሉት ነገር አደናጋሪ አይደለ !?

ፍቅር ጀባ🫶




መልካም እሁድ✨


@fezekir_fe
🥰7❤1
ምሳ የበላሁትን ሽሮ እያጣጣልኩ ፈጣሪዬን እያማረርኩኝ ወደ ታክሲ ገባሁ.....አልሞላም ነበር እና በመስኮት ሳስተውል ከተደፋ የአትክልቶች ትራፊ ላይ አቮካዶ አንስቶ ቆሻሻውን እያራገፈ የሚበላ ህፃንን አየሁ...

" እንደዚህም አለ ለካ " አልኩት ራሴን..... በልቦናዬ ፈጣሪዬን አመሰገንኩ።

አሁን ካለንበት ሁኔታ በጣም በብዙ የከፋ የማናስበው ሁኔታ ላይ ያለ እልፍ ሰው አለ እና እናመስግን...

ሰላም ለልባችሁ።
❤12
አይን አይኗን በስስት እያየ እንዲህ አላት
" ላንቺ ያብቃኝ..ከኔ ደስታ ያንቺን እንዳስቀድም......አትሁኚብኝ አንድም"

አጂብ መታደሏ😊😊😊
❤7😁3🔥1
ትምህርት ከብዙ ሁነቶች ትገኛለች ውዶቼ።

ዛሬ በአንፊልድ የተደረገውን የአርሰናል እና የሊቨርፑልን ጨዋታ አይቼ ስወጣ ምን አስተዋልኩኝ መሰላችሁ።

አንዳንድ ፍላጎቶች አንዳንድ ምኞቶቻችን አንዳንድ ልፋቶቻችን የምርም ውጤታቸው የሚታየው በጊዜ ሂደት በጊዜ ቆይታ ውስጥ ነው።

ይሄን ያልኩበት ምክንያት ዛሬ አርሰናል አንፊልድ ላይ ጨዋታን ማሸነፍ የቻለው ከ14 አመታት በኋላ በመሆኑ ነው።

ብዙ እየለፋን ብዙ እየጣርን ብዙ እየሞከርን ውጤታችን የታለ እያልን ይሆናል ብዙ እየታመምን ብዙ እየተፈተንን ብዙ እያሳለፍን መቼ ነው ፈረጃው እያልን እያሰብንም ይሆናል። ጊዜ ለሁሉ መልስ አለው ከእኛ የሚጠበቀው ትዕግስትን መላበስ ነው።

በእርግጥም ጊዜ ለሁሉ መልስ አለው።

ከመታገስ ጋር በርቱልኝ።

ትዕግስት ለልባችሁ።😊😊😊
❤10