ግጥም በ ኤዶምገነት
1.15K subscribers
57 photos
2 videos
65 links
ግጥም ብቻ ቤተሰብ ይሁኑ።

የቻናላችንን የመወያያ ግሩፕ ለማግኘት
https://t.me/slegtmenawga

tiktok.com/@edom_ge

ኤዶምገነት @Edom_Ge
Download Telegram
ጀግና ነኝ እኮ አፍቃሪሽ
አቻ የለኝ ሽገዳይ፣
አንችን ነው የምጠብቅ
አስቢበት ላልከኝ ጉዳይ፤
.
.
ምላሽ አገኘሁለት
ለተናገርከው ጥኡም ቃል፣
ጦር እና ጋሻን ታጥቆ
ባዳም ተከፍሎት ይጠብቃል፣

ጀግንነትህን ያዘው
እዚያው ካንተጋ ይቅር፣
ለእኔ....
የገደለልኝ ሳይሆን
የሞተልኝ ነው ፍቅር።


#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
አውጣኝ

ሳያስተምረኝ ስህተቴ፣
ሳያበረታኝ ጉልበቴ፣
ሄወቴን ቁማር አሲዤ፣
በጡዘት ንውዘት ፈዝዤ፣
ባጓጉል ተስፋ ስዳክር፣
በማይጥም ደስታ ስሰክር፣
እያየሁ በጭፍን ስመራ፣
ከፅልመት ብርሀን ስፈራ፣

አካሌ አጉል ሲዝናና
ጥርሶቼ በግፍ ሲስቁ፣
ሳይገጥመኝ መሬት ስንጥቁ፡
ገብቻለሁኝ ከጉድጓድ
ወድቄአለሁኝ ከጥልቁ፣

መተናነስን አለመድኩ
መንበርከክ በፈጠረኝ ፊት፣
ነገሩ ተበለሻሸ
ሆነብኝ ውሀ በወንፊት፣
መዳኛየንም አላውቅም
ብልሀት የለኝም ዘዴ፣
መተህ ካላወጣኸኝ
እዚሁ መሞት ነው ግዴ፣

ጭልምልምልም ሲልብኝ
ሂወት መንገድ ሲያሳጣኝ፣
እጆችህን ዘርጋና
በፈርጣማው ክንድህ አውጣኝ።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
**
እንደኔ ፍቅር እየናፈቀ፣
ማነው በቤቱ የተደበቀ?

መንገዱን ብቃኝ ወጥቼ ድንገት፣
ይመላለሳል እደሰው ክህደት፣
አደባባዩን ሞልቶት ማስመሰል፣
ወግ ባህል ሆኗል...
ባመኑት ወዳጅ ደጋግሞ መቁሰል፣

ታዲያ...
በክደት አለም ታማኝ ከምሻ፣
ትሻለኝ የለ የቤቴ ዋሻ?

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha

.
ኪሳችሁ ሳይሞላ....
ለመጨመር አልማዝ ለመሰብሰብ እንቁ፣
ለሌለው ማካፈል መስጠትን እወቁ።
.
.
አለች እናቴ!!!


#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
መልካም የደመራ በዓል!

@Samuelalemuu
.
ከ'ድሜዬ እኩል እያደገ
በስተቴ እየፋፋ፣
የሀጢያት ሸክም አጎበጠኝ
የሚያድነኝ ሀኪም ጠፋ፤

አይሰፈር እንደብዙ
እንደጥቂት አይቆጠር፣
ከሰማዩ እየራቁ በክብደቱ
ቁልቁል ማጠር፤

ኦ.... አምላኬ
በቃሽ በለኝ
አንተ አይደለህ የማታልፈኝ፣
የሀጢያት ሸክሜን አውርድና
በማደሪያህ አሳርፈኝ።።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
ይቅናው ከማለት ውጭ
...
ትቶኝ ሄደ በዬ
አልታጠብኩም በእንባ፣
አምናለሁኝ እና
ከፍቶት በሄደው በር
ሌላ እንደሚገባ።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
አንዳንዴ....

የራስን ህመም ደብቆ
ማከም የሰው በሽታ፣
የውስጥን ጩኸት አምቆ
ማድመጥ  ሌላ ኮሽታ፣
ሆኖ አለመገኘት
የተናገሩትን ቃል፣
ውስጥን እያበገነ
ከላይ ከላይ ያስቃል!!

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
ስሚኝ እማ

አንችን ለሚል
ለወዳጅሽ አታርፍጂ፣
ቀን አይለፍ
ሳያምርብሽ ፈጥነሽ ሂጂ፣
ሀበሻ እና ቀጠሮ
እያልሽ አትቀልጅ፣

አትልበሽ አትኳኳይ
ካዘገየሽ ሁሉም ይእቅ፣
እንዲህ ስል ነው
ያረፈድኩት
ሲጠበቀኝ ንፁህ ፍቅር።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
🥰ሰላም ሰዎች🥰🥰🥰🥰
ለመጀመሪያ ጊዜ በቲክቶክ መጥቻለው😊
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
follow me👇

https://vm.tiktok.com/ZMhSUJ9c9/
**
አልፎ ክረምት ሄዶ በጋ፣
ማጡ ድጡ ሲዘነጋ፤
ጨለማውን ቀን አቅልሞት፣
መራራውን ሳቅ አጥሞት፤
ያለፈ አምና ሆኖ መዝገብ፣
ሲነበነብ ሲደጋገም፣
ተረት ቢመስል የገፈፈ፣
አይረሳውም ያሳለፈ።


#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
**
ከፀባዩ የሚገርመኝ
ምክንያቱን የማላቀው፣
ትግስቱ አልቆ ሲበሰጫጭ
ተረጋግቶ የሚስቀው፣

እንዴት ቻለ...
ብክንክንክን.. ያረገውን
የንዴት ጥግ ያን ትኩሳት፣
በፈገግታ እያበረደ
እንዳልነበር ባንዴ መርሳት?

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
""
ተወው አትጨነቅ
ለአለም እልፍ ጓዝ፣
ይልቁን ተጠንቀቅ
ለራስህ ስትጓዝ፣

አይተህ ስትዝናና
የምድርን ስፋት፣
ችላ ያልከው ጠጠር
እንዳይሆን እንቅፋት!

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
""
ያንተ ነበርኩ እድሜ ልኬን፣
ሰውቻለው ውበት መልኬን፣
ድካም ጥጉን እስከምስት፣
አገለገልኩ ያለ ስስት፣

አንተን ወዶ ኑሮን መግፋት፣
ደስ እንዲልህ ሁሌ መልፋት፣
ራሴን መርሳት እንዳይከብደኝ፣
ፍቅርህ በልጦ አስገደደኝ፣

ሳቅህ ሳቄ ቢሆነኝ ነው
የደከምኩት ያለ ፋታ፣
መሄድ ካሻህ ደህና ሰንብት
አትታሰር በውለታ፣
ካዘኔታህ በዘለለ
ካልቻልክብት እኔን መውደድ፣
ስለራሴ ልኑር ደሞ
ሰላም ግባ መልካም መንገድ።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
#ተጣልተናል_እኮ
.
እንደማንመለስ ምለን በታቦቱ፣
ንግግር ካቆምን አልፈዋል ወራቱ፣
ኧረምን ወራቱ አመታቱም ነጉዷል፣
ሌላ ወድጃለው እሱም ሌላ ወዷል፣

ግና....
ቁልምጫ በሚሉት እዳ ተለክፌ፣
ሙሉ ስሙን መጥራት አለመደም ኣፌ፣
ተጣብቆብኝ አንዴ የቁልምጫው ነገር፣
ስለሱ ስጠየቅ ለሰዎች ስናገር፣
ውዴ፡ ማሬ፡ ፍቅር፡ ላለማለት ስጥር፣
ይቀድመኛል ኣፌ ባስታዎስኩት ቁጥር።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
ጥለሽኝ ስቴጂ
ጩአት እሪታዬን እንደምን ላምቀው?
አስጩኦ አይደለም ወይ?
ሰይጣን የሚለቀው?

#Rediet_aseffa