አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት (ARDO) Channel
402 subscribers
4.04K photos
80 videos
4 files
745 links
አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት
Awolia Relief & Development Organization

Telegram Channel = t.me/ardoeth
Telegram Group = t.me/ardoethG
Download Telegram
ቀን እሮብ መስከረም 6/2019

👉 አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ከሳዑዲ ዓረቢያው የንጉሥ ሰልማን የሰብዓዊና ዕርዳታ ማዕከል ጋር በመተባበር ነፃ የዓይን ሕክምና በመሰጠት ላይ ይገኛል!

👉 የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ሰዒድ አስማረ እንደገለጹት ይህ ሰብዓዊ የሕክምና ፕሮግራም በንጉሥ ሰልማን የሰብዓዊ ዕርዳታ ማዕከል የገንዘብ ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን በተጨማሪም በአል-በስር ዓለም አቀፍ ፋውንዴሽን የተዘጋጀውና “ኑር” የተሰኘው ዓይነ ስውርነትን ለመከላከል ያለመ የሕክምና ዘመቻ በሳዑዲ በጎ ፈቃደኞች አማካኝነት እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል።

👉 የነፃ የአይን ሞራ ገፈፋ ሕክምና ዘመቻው ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በቀጣይ ቀናት በጅግጅጋና በወራቤ ከተሞችም እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን የሚከተሉትን ነፃ የሕክምና አገልግሎቶች በዋናነት ያካትታል፦
👉 የዓይን ሕክምና ምርመራና የመድኃኒት ድጋፍ ይሰጣል
👉 የዓይን ሞራና ሌሎች በቀዶ ሕክምና ሊታከሙ የሚችሉ የዓይን ችግሮች ላለባቸው ከ400 በላይ ታካሚዎች ነፃ የቀዶ ሕክምና ይደረጋል
👉 የእይታ ችግር ላለባቸው 1,500 ሰዎች ነፃ የእይታ ማስተካከያ መነጽር ይሰራጫል።

👉 ይህ የሰብዓዊ ድጋፍ መርሃ ግብር የዓይን ሕክምና ከመስጠት ባለፈ የበርካቶችን ተስፋና የኑሮ ጥራት ለማሻሻል የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።
የአንድ ሰው የእይታ ችግር ሲቀረፍ ተስፋው ከመታደሱም በላይ በቤተሰቡ ውስጥ ትልቅ ደስታን እንደሚፈጥር ተመላክቷል።

👉 በመጨረሻም አ.ዕ.ል.ድ ይህን ነፃ የዓይን ሕክምና ዘመቻ ላዘጋጁት አል-በስር ዓለም አቀፍ ፋውንዴሽን ለንጉሥ ሰልማን የሰብዓዊ ዕርዳታ ማዕከል ለሳዑዲ በጎ ፈቃደኞች እንዲሁም ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የላቀ ምስጋና ያቀርባል።

አ.ዕ.ል.ድ


አወሊያ ቴሌግራም
👉 t.me/awoliaschool5
12
ቀን እሮብ መስከረም 6/2019

የአወሊያ ሙስሊም ቀ.1 አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት 2019 የትምህርት ዘመን አጀማመር በከፊሉ



አወሊያ ቴሌግራም
👉 t.me/awoliaschool5
11
ለአወሊያ ኮሌጅ ነባር እና አዲስ ተማሪዎች በሙሉ!
👍7