ቀን 01/08/2017 ዓ.ም
ውድ የአርዲ ዩዝ አካዳሚ ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ ፡-
ጉዳዩ፣ የ3ኛው ሩብ አመት ማጠቃለያ ፈተና ፕሮግራምና ሌሎች መርሃ ግብሮች
ለ2017 ዓ.ም በወጣው የትምህርት መርሃ ግብር መሰረት የ3ኛው ሩብ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ከ ሚያዚያ 06/2017 እስከ ሚያዚያ 09/2017 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል ፡፡
1. የ3ኛው ሩብ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ከኬጂ እስከ 3ኛ ክፍል ከሰኞ ሚያዚያ 06 /2017 እስከ ረቡዕ ሚያዚያ 08/2017 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ከ4ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በፈረቃ ማለትም ሰኞ እና ረቡዕ እንዲሁም ማክሰኞ እና ሀሙስ የሚፈተኑ ይሆናል። ማጠቃለያ ፈተና በሚሰጥባቸው ቀናት ት/ቤት ክፍት የሚሆነው ለግማሽ ቀን ሲሆን የኬጂ ተማሪዎች እስከ 6፡00 ሰዓት እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች 6፡20 ድረስ ይቆያሉ ።
2. የትምህርት አገልግሎት ክፍያ ፡ የሚያዚያ ወር ፣ የመጨረሻው የሩብ ዓመት የትምህርት ቤት ክፍያ እንዲሁም የሰርቪስ ክፍያ ያላጠናቀቃችሁ ወላጆች የማጠቃለያ ፈተና ከመድረሱ በፊት ከፍላችሁ እንድታጠናቅቁ እየገለፅን ውዝፍ ክፍያዎች ያላጠናቀቁ ተማሪዎች ፈተና ላይ መቀመጥ እንደማይችሉ እናሳውቃለን፡፡
3. የጥናት ፕሮግራም፡- የመጨረሻ ፈተና በሚሰጥበት ቀን ማለትም ረቡዕ ሚያዚያ 08 ቀን 2017 እንዲሁም በፈረቃ ለሚፈተኑም ረቡዕ እና ሀሙስ የጥናት ፕሮግራም አይኖርም ። በሌሎቹ ቀናት ግን የጥናት ፕሮግራሙ በተለመደው መንገድ እስከ ቀኑ 8 ፡00 ሰዓት ድረስ ይቀጥላል። አርብ ሚያዚያ 03/2017 ዓ.ም የጥናት መርሃ ግብር የሚሰጥ ይሆናል፡፡
4. የፈተና መመለሻ ቀን ፡- የ4ኛው ሩብ ዓመት ትምህርት የሚጀምረው ማክሰኞ ሚያዚያ 14/2017 ሲሆን ለተማሪዎች የፈተና ወረቀት የሚመለስ ይሆናል፡፡
5. አመታዊ የስፖርት ፊስትቫል፡- ተማሪዎች በእውቅት ብቻ ሳይሆን በአካልም ጤናማ እና የዳበረ ስነ ልቦና እንዲኖራቸው የሚያስችሉ ስፖርታዊ ውድድሮች ከፍተኛ ፍክክር በመላበስ ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡ ሀሙስ ሚያዚያ 09 /2017 ዓ.ም የ2017 ስፖርታዊ ውድድር የመዝጊያ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም ተማሪዎች እለቱን በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድር ስለሚያሳልፉ ት/ቤት የሚቆዩት ለግምሽ ቀን አስከ 06፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል፡፡ በዕለቱ የስፖርት አልባሳት ለብሰው መምጣት ይችላሉ፡፡

አንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን
ት/ቤታችን ዛሬ ቀን 14/08/2017ዓ.ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት በተዘጋጀው የሳይንስና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ሥራ እግዝቢሽን ዉድድር በ ICT ዘርፍ ተማሪ ለዊ ኤፍሬም 1ኛ እና ፀደኒያ አማረ 2ኛ በመሆን ስላሸነፉ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን ፤ ተቋማችን ክፍለ ከተማውን በመወከል በከተማ ደረጃ የሚዘጋጀውን የእግዝብሽን ዉድድር በቀን 16/08/2017 ዓ.ም ተሳተፊ ይሆናል፡፡
ትምህርት ቤታችን በማዘር አርዲ ቅርንጫፍ ያቋቋመው የስቴም ሴንተር ፍሬ ጅማሮ ማየታችንን በቀጣይ ተማሪዎቻችን በአገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እንድንገፋበት ስንቅ እና ጉልበት ሆኖናል፡፡
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ደስ ብሎናል ፡፡

ውድ የአርዲ ተማሪ ወላጆች /አሳዳጊዎች
ጉዳዩ፡-የትምህርት አገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ውይይት ቀን መራዘሙን ስለማሳወቅ
በ18/08/2017 ዓ.ም ተጠርቶ የነበረው የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ውይይት /ስብሰባ/ መንግስት በሰጠን መመሪያ መሰረት ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን እንገልፃለን፡፡