Arba Minch University
20.7K subscribers
18.5K photos
66 videos
1.14K files
926 links
The official telegram channel of Arba Minch University
Download Telegram
ለዩኒቨርሲቲው የቴኒስ ስፖርት ታዳጊዎች ፕሮጀክት የትጥቅ ድጋፍ ተደረገ

የኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን ለዩኒቨርሲቲው የቴኒስ ስፖርት ታዳጊዎች ፕሮጀክት የትጥቅ ድጋፍ አድርጓል፡፡ በዕለቱ በፕሮጀክቱ እየሠለጠኑ ከሚገኙ የታዳጊ ወላጆች ጋርም ምክክር ተካሂዷል፡፡

የፕሮጀክቱ ዋና አስተባባሪ፣ ኢንተርናሽናል የቴኒስ ዳኛና የስፖርት ሳይንስ መምህር አብረሃም ደርባቸው የኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን ላደረገው የማልያ ድጋፍ ምሥጋናቸውን አቅርበው አርባ ምንጭና አካባቢው በስፖርቱ ዘርፍ ምቹና ጠንካራ አቅም ያለው አካባቢ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በቴኒስ ስፖርት በሀገር ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ ታዳጊዎችን ለማፍራት ይሰራልም ብለዋል፡፡

የጋሞ ዞን ስፖርት መምሪያ ተወካይ አቶ ዮሐንስ ዘለቀ እንደገለጹት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተግባራዊ የሚሆነው ፕሮጀክት በቴኒስ ስፖርት የሠለጠኑ ታዳጊዎችን ከማፍራትና ሀገሪቱ በስፖርቱ የተሻለ እውቅና እንዲኖራት ከማስቻል አንጻር የራሱ ሚና ይኖረዋል። ፕሮጀክቱን ከማስጀመር አኳያ የባለድርሻ አካላት ተነሳሽነት የሚበረታታ መሆኑን የገለጹት አቶ ዮሐንስ የቴኒስ ስፖርት አሁን ላይ ዓለም ዓቀፍ ውድድሮችን በተከታታይ በማዘጋጀት የሀገሪቱን ገጽታ በመገንባት፣ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ከማሳደግ አንጻር እንዲሁም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ከማሻሻል አንጻር ጉልህ ድርሻ ያለው መሆኑን አመላክተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት
AMU SIFA JOB-FEET Enset Project Holds Internal Mid-Term Review Meeting

Arba Minch University (AMU) SIFA JOB-FEET Enset project team members have held mid-term review meeting with its internal partners at AMU, Main Campus on April 23rd, 2025.

Teklu Wegayehu (PhD), vice president for research and cooperation, in his opening remarks, said, we have understood the impact and importance of cooperative projects and the opportunities that they brought to our institution. Briefing on AMU-SIFA JOB-FEET project is different from other projects by its objective of job creation for disabled youth and women, by its scope covering three regions: Central Ethiopia, Sidama and South Ethiopia which are known by Enset crop production and by its theme of end to end focus on Enset crop from producing disease free seedling to the use of by products to market value, Dr. Teklu highlighted. This internal meeting is to review our achievements and challenges that we faced during the accomplishment of two milestones of project preparation and market analysis; having the experiences, team members got oriented to accomplish the next two milestones of market validation and evaluation and closing, he underscored.

Wondwossen Jerene (PhD), project PI, said, this meeting is aimed to share the achievements and challenges faced during last seven months while implementing the first and second milestones, review the progress together and direct the team members to play their roles effectively in the next two milestones, he noted.

Addisu Fekadu (PhD), Enset technologies innovator, project member and coordinator, presented key points on project achievements and challenges whereas Wondwossen Jerene (PhD) presented highlights on project management and reporting.

Finally, the team members discussed the issues based on the presentations including executives from finance and procurement of AMU, TVET and Lucy Enset P.L.C.

For more Information Follow us on:-


Website - https://www.amu.edu.et/
Telegram - https://t.me/arbaminch_university
Facebook - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
YouTube - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

Public and International Relations Executive
በፕሬዝደንት ጽ/ቤት ሥር የሚገኙ የሥራ ክፍሎች የ3ኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ተገመገመ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት በሥሩ የሚገኙ ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤቶችን የ2017 በጀት ዓመት የ3ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ዛሬ ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም ገምግሟል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ከአምላክነሽ ደሳለኝ በመድረኩ በሥራ ክፍሎቹ በሩብ ዓመት በቁልፍና ዝርዝር ተግባራት ታቅደው የተሠሩ ሥራዎች ፣ ጠንካራ አፈጻጸሞች፣ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች በዝርዝር ቀርበው መገምገማቸውን ገልጸው ድክመት የታየባቸው ጉዳዮች ደግሞ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶባቸው እንዲሠሩና ተሻሽለው እንዲቀርቡ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቁመዋል።

ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ግምገማው ሥራዎችን ትኩረት ሰጥቶ በጥራት ለመሥራትና ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጡንን ቁልፍ ተግባራት በወቅቱ ለመፈጸም የሚረዳ መሆኑን ገልፀዋል።

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት