ከዩኒቨርሲቲው ማስተማሪያና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሠራኞች እና የሕክምና ባለሙያዎች ጋር ትውውቅና ምክክር ተካሄደ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግንቦት 21/2017 ዓ/ም ከዩኒቨርሲቲው ማስተማሪያና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አዲስና ነባር የአስተዳደር ሠራተኞች እና የሕክምና ባለሙያዎች ጋር የትውውቅ እና የምክክር መርሐ ግብር አካሂዷል።
የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ደስታ ጋልቻ አዲስ ሠራተኞች ከነባር ሠራተኞች፣ ከሕክምና ባለሙያዎች እና ስፔሻሊስቶች እንዲሁም ሌሎች አመራር አካላት ጋር ትውውቅ ማካሄድ እና በቀጣይ ለማኅበረሰቡ ጤና መሻሻል ሊከናወኑ በታቀዱ ተግባራት ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ እና ምክክር ማካሄድ የመርሐ ግብሩ ዋና ዓላማ መሆኑን ገልጸዋል።
"እንደ ዜጋ ሀገሪቱ ከእኛ ብዙ ትጠብቃለች'' ያሉት ዶ/ር ደስታ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በመለየት እና በመሙላት ለተሻለ ነገ በትጋት መሥራት የሚጠበቅ መሆኑን አስገንዝበዋል። የሆስፒታሉ የቦርድ ኮሚቴ መቋቋሙን እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ለመሆን በሚያደርገው ጉዞ ሆስፒታሉን የተሻለ የገቢ ምንጭ እና በሜዲካል ቱሪዝም ዘርፍ የልኅቀት ማዕከል ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑንም አክለዋል።
የኮሌጁ የጤና ትምህርትና ሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር እንዲሁም የአጥንት ቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ዶ/ር ብርሃኑ አንዳርጌ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ሥራ ባሻገር በቂ ምርምር እና ማኅበረሰብ ተኮር ተግባራት ለማከናውን ቀዳሚና ተመራጭ መሆኑን ገልጸው ተቋሙን ለተቀላቀሉ አዲስ ሠራተኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
''ጠንካራ ተቋም የተሻለ የሰው ኃይል እና ዕውቀት ይጠይቃል" ያሉት ዶ/ር ብርሃኑ በቂ ዝግጅት ማድረግ፣ ሙያዊ ሥነ ምግባር መከተል፣ ተነሳሽነት እንዲሁም በትብብር መጓዝ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። የተሻለ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት እና የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎችን በመስጠት በትኩረት የሚሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
የሕክምና ትምህርትና አገልግሎት ጥራት ማሻሻያና ኢኖቬሽን ኮርፖሬት ዳይሬክተር ረ/ፕሮፌሰር ስንታየሁ አበበ እና የሆስፒታሉ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይርዳው ተቋሙን በተቀላቀሉት ሠራተኞች መደሰታቸውንና ለተቋሙ የተሻለ ግንባታ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
የመርሐ ግብሩ ተሳታፋዎች የዩኒቨርሲቲው አካል በመሆናቸው መደሰታቸውንና በትምህርት ያገኙትን ዕውቀት በተግባር በማዋል የተቻላቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Telegram
Arba Minch University
The official telegram channel of Arba Minch University