Arba Minch University
20.7K subscribers
18.5K photos
66 videos
1.14K files
924 links
The official telegram channel of Arba Minch University
Download Telegram
የበዓል መልካም ምኞት መግለጫ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ፣ በመላው ዓለም ለምትገኙ ለዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ምሩቃን እንዲሁም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለትና የትንሣኤ በዓላት በሠላም አደረሳችሁ እያለ በዓላቱ የሰላም ፣ የጤናና የደስታ እንዲሆኑ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

መልካም በዓል !
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓልን ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጋር አከበሩ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓልን ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጋር ዛሬ ሚያዝያ 12/2017 ዓ/ም በድምቀት አክብረዋል፡፡

ከፍተኛ አመራሮቹ ተማሪዎች ከወላጆቻቸው ርቀው በትምህርት ላይ ስለሚገኙ ብቸኝነት እንዳይሰማቸው ለማድረግ በዓሉን በጋራ ማክበር ማስፈለጉን ጠቁመው አመራሮቹ ለተማሪዎች፣ ለወላጆቻቸው፣ ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብና ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ የበዓል መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ ፕሬዝደንት ዶ/ር ቦጋለ ገ/ማርያም፣ የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ተክሉ ወጋየሁ፣ የአስተዳደርና ልማት ም/ ፕሬዝደንት ፕ/ር ጳውሎስ ታደሰን ጨምሮ ሌሎች የዩኒቨርሲቲው መካከለኛ አመራሮች በካምፓሶች ተገኝተው በዓሉን ከተማሪዎች ጋር አክብረዋል።

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት