ተወዳጁ ዳኛ ፍራንክ ካፕርዮን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። በርኅራኄው እና በመልካም ዳኝነቱ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነት ያገኘው ፍራንክ ካፕርዮን በተወለደ በ88 ዓመቱ በPancreatic Cancer ህይወቱ አልፏል።በ60 ዓመት የትዳር ህይወታቸው ከባለቤቱ Joyce Caprio ጋር 5 ልጆችን የወለዱ ሲሆን 7 የልጅ ልጆችን እንዲሁም2 የልጅ ልጅ ልጆችን ማየት ችለዋል።
ደግነቱ እና እውነተኛነቱ በብዙዎች ልብ ህያው ሆኖ ይኖራል።
ከፍራንክ ካፕርዮ ተጠቃሽ ንግግሮች መካከል
"Every small act of kindness I give creates a better world and better me"
"We rise by lifting others"
"Kindness is the one gift that costs nothing,but means everything.Give it freely specially when it is hard"

❤3
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የህግ እና አስተዳደር ትምህርት ክፍሉን በቅርቡ ህይወታቸው ባለፈው ታዋቂው ዳኛ ፍራንክ ካፕሪዮ ስም ሰየመ፡፡
ከሁለት ሳምንታት በፊት በ88 ዓመታቸው ህይወታቸው ያለፈው፤ ዳኛ ፍራንክ ካፕሪዮ ዓለም አቀፍ ተወዳጅነትን ያተረፉና በሚያሳዩት ርኅራሄ "መልካሙ ዳኛ" የሚል ስም የተሰጣቸው ነበሩ።
የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ነሐሴ 27/2017 ዓ.ም የተቋሙን የህግ እና አስተዳደር ትምህርት ቤት በስማቸው ሰይሞላቸዋል።
የዩኒቨርሲቲው የህዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ መሐመድ አህመድ ውሳኔው "ዩኒቨርሲቲ እና ፍትህ ዓለም አቀፍ በመሆናቸው" የተደረሰ ነው ብለዋል።
"… የእርሳቸው ህያው ሥራ፣ የእርሳቸው ርኅራሄያዊ ፍትህ ለዩኒቨርሲቲያችን፣ ለተማሪዎቻችን እንዲሁም ለአካባቢው ማኅበረሰብ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለን ነው" ሲሉ ለስያሜው ምክንያት አቅርበዋል።
የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መሐመድ ኡስማን (ዶ/ር) "የዳኛ ፍራንክ ካፕሪዮ የህይወት ዘመን ሥራ በተማሪዎቻችን ለመቅረፅ የምንጥረው የፍትህ፣ ክብር እና አገልግሎት ዕሴት ተምሳሌት ነው" ብለዋል።
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደም የሉሲን ቅሪተ አካል ባገኙት ፕሮፌሰር ዶናልድ ጆሀንሰን ስም የማኅበረሰባዊ እና ሰብዓዊነት ትምህርት ክፍልን መሰየሙ ይታወቃል። #ቢቢሲአማርኛ
©tikvahuniversity

👍2❤1
<<ጥቂት ስለ መዉሊድ>>
የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመውሊድ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!!!
የመዉሊድ በዓል በአብዛኛው(በሁሉም ዘንድ አደለም) ሙስሊም አማኝ የሚከበር የነቢዩ መሐመድ የልደት ቀን መታሰቢያ ነዉ።የመዉሊድ በዓል በእስልምና አቆጣጠር በሦሥተኛዉ ወር በቀን 12 ይከበራል።ነቢዩ መሐመድ የእስልምና እምነት መስራች እና የአላህ መልእክተኛ እንደሆኑ በቁርአን ተጽፏል።የእስልምና እምነት መሠረቱም 'አላህ ብቸኛ አምላክ ነዉ መሐመድም መልእክተኛው ነዉ' የሚል ሲሆን መሐመድ የመጨረሻው ነቢይ እንደሆነ ይታመናል።ሙስሊሞች ለነቢዩ መሐመድ ትልቅ ክብር እና ፍቅር አላቸዉ።ለዚህም አብዛኞቹ የመሐመድን ልደት በየቤታቸው፣መስጊድ በመሄድ እና ስለ መሐመድ የሚናገሩ የቁርዓን ክፍሎች በማንበብ ያከብሩታል።የተወሰኑ ሙስሊሞች የመሐመድን ልደት(መዉሊድ) በዓል መከበር እንደሌለበት ይከራከራሉ።ለዚህም የሚያነሱት ሀሳብ
1.በቁርዓን የመሐመድን ልደት አክብሩ የሚል ስለሌለ ሲሆን እንደ እስልምና ማንም በቁርዓን ከተቀመጠዉ ዉጪ አዲስ ሀሳብ(ሥርዓት) መፍጠር አይችልም።እንደ እስልምና በመልእክተኛዉ በመሐመድ ያልተነገረ ወደ አላህ የሚያደርስ መልካም ነገር የለም።መዉሊድ ሰዎችን ወደ አላህ የሚያቀርብ መልካም ነገር ነዉ የሚል ካለ ይኽ መልእክተኛዉን መሐመድን መክሰስ ነዉ-መልካም የሆነዉን ለሰዎች አልገለጸላቸዉም ያስብላልና።
2.ክርስቲያኖችን መምሰል ስለሆነና በቁርዓን ደግሞ በግልጽ ክርስቲያኖችን አትምሰሉ ተብሎ ተነግሯልና።ክርስቲያኖች የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት ስለሚያከብሩ እነሱን መምሰል አይገባም ብለዉ ያምናሉ።(ሙስሊሞች ከክርስቲያኖች ለመለየት ሲሉ በርካታ ልዩነቶችን እንደሥርዓት ደንግገዋል)
3.ከአላህ ሌላ ምስጋና ለማንም አይገባም የሚለዉን የእስልምና መሠረት የሚጥስ ስለሆነ።በመዉሊድ ጊዜ ስለ መሐመድ የሚዘመሩ መዝሙራት፣ የሚነገሩ ታሪኮች፣ነብዩን እርዳታ መጠየቅ በጸሎት(ዱአ) ከልካቸዉ ያለፉ ሲሆኑ ይኸንን አስተምህሮ ይጥሳል ብለዉ ስለሚያምኑ።መዉሊድን በአደባባይ ማክበር በ1207 A.D የተጀመረ ሲሆን በዓሉ ይፋዊ(Official) ሆኖ መከበር የተጀመረዉ በኦቶማን ቱርክ ሥርወ መንግስት በ1588 A.D ነዉ።የመዉሊድ በዓል መከበር አለበት የለበትም የሚለዉ በእስልምና አከራካሪ ከሆኑ ጽንሰ ሀሳቦች አንዱ ነዉ።መዉልድ በቱርክ፣በግብጽ እና በሌሎች አስላሚክ ሀገራትና በሌሎች ሙስሊሞች በርከት ብለዉ ባሉበት ሀገራት ብሔራዊ በዓል ሆኖ የሚከበር ሲሆን ኳታር እና ሳዉዲ ዓረቢያ ግን መዉልድ እንዳይከበር ተከልክሏል።

🥰3❤1
እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሠላም እና በጤና አደረሳችሁ!!!
አዲሱ ዓመት የሠላም፣የፍቅር፣የመግባባት ዓመት እንዲሆንልን ቻናላችን ይመኛል!!!!

የዩናይትድ ስቴትስ የትምህርት አውደ ርዕይ ነገ መስከረም 10/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሔዳል፡፡
መድረኩ በአዲስ አበባ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ EducationUSA አማካሪ ማዕከል እና በዓለም አቀፉ የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት (ICS) ትብብር የተዘጋጀ ነው፡፡
ከ30 በላይ የዩናይትድ ስቴትስ ዩኒቨርሲቲዎች በመድረኩ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡
ነገ ጠዋት ከ3:00-9:00 ሰዓት አዲስ አበባ International Community School (ICS) ካርል አደባባይ አካባቢ በሚካሐየደው አውደ ርዕይ ለመሳተፍ ይመዝገቡ 👉 https://forms.gle/xKZ3ZnscnTvMkZ1j9
ለቅድመ ምረቃ እና ድኅረ ምረቃ ተማሪዎች በነጻ ለመሳተፍ ክፍት የሆነው መድረኩ፤ በዩናይትድ ስቴትስ ትምህርታቸውን ለመከታተል ፍላጎት ላላቸው ጥሩ አጋጣሚ መሆኑ ተገልጿል፡፡
@tikvahuniversity

የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለደመራ በዓል እና ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን!!
🥰3
#የጤናባለሙያዎች🙏
የ21 ዓመት እድሜ ያላት እንስት እርጉዝ የመውለጃዋ ጊዜ ደርሶ መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ዋና ከተማ እንዳስላሰ-ሽረ የሚገኘው ስሑል አጠቃላይ ሆስፒታል ትደርሳለች።
ወደ ሆስፓታሉ የተጓዘችው የአስገደ ወረዳ ከሚገኝ ራህዋ የተባለ የገጠር ቀበሌ ገበሬ ማህበር በመሆኑ ድካምና የነበረባት ደም መፍሰስ ተደራርቦ ህይወት የሚቀማ አደጋ ተደቀነባት።
በዚህ ሰዓት ሃኪሞቹ ቀዶ ህክምና እንደሚያስፈልጋት ወስነው መጣደፍ ጀመሩ።
ይሁን እንጂ በሆስፒታሉ ለአደጋ ጊዜ ተብሎ ተጠራቅሞ በደም ባንክ የተቀመጠ ደም ባለመኖሩ እንዲሁም ለወላጅ እናቷ ደም የሚለግስ የቅርብ ሰው ባለመኖሩ ምክንያት ሃኪሞቹ ጥረታቸው መና ሊቀር ሆነ።
እናም ቀዶ ህክምናውን የሚያከናውነው የሆስፓታሉ የእናቶችና የህፃናት ሃኪም ዶ/ር ኣርኣያ ወለገብርኤልና የፋርማሲ ባለሞያዋ ሲ/ር ምፅላል አብርሃ ደም ለመለገስ ወስነው አደረጉት።
ቀዶ ህክምናው ተከናወነ ፤ እናቲቱ ደም ተለገሰላት ፤ ራሷና የወለደችው ህፃን በአሁኑ ሰዓት በበጎ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።
የወላጅ እናት ቤተሰቦች ፥ " ሃኪሞቹ መንታ ሰብአዊነት በመፈፀም አራስ እናቲቱንና የወለደችውን ህፃን ታድገዋል ፤ ረጅም የአገልግሎት ጊዜ ከመልካም ጤና ጋር እንመኝላቸዋለን " ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
©tikvahethiopia

" የስኮላርሺፑን የሙሉ አመት የትምህርት ወጪ የሩሲያ መንግሥት ይሸፍናል " - ሩሲያን ሃውስ
የሩሲያ መንግስት በማንኛውም የትምህርት መስክ በሩሲያ ትምህርት የመከታተል ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ስኮላርሺፕ ማመቻቸቱን አሳውቋል።
ስኮላርሺፑ የሩሲያ መንግስት ለ155 የባችለር፣ ማስተርስ እና ፒ ኤች ዲ ተማሪዎች በማንኛውም ፊልድ እንዲማሩ የፈቀደው ነው።
ባለፈው አመት ለ100 ተማሪዎች ተፈቅዶ የነበር ስኮላርሺፕ በዘንድሮ አመት ቁጥሩ ወደ 155 ተማሪዎች ከፍ የተደረገ ሲሆን እንደ አመልካቾች ብዛት የሩሲያ መንግስት ቁጥሩን ከእዚህም ከፍ ሊያደርገው እንደሚችል የሩሲያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።
የሩሲያ የሳይንስ እና ባህል ማዕከል ወይም በአዲሱ ስያሜው ሩሲያን ሃውስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፤ የስኮላርሺፑ ሙሉ የትምህርት ክፍያ በሩሲያ መንግሥት የሚሸፈን መሆኑን ገልጾ የጉዞ ትኬት እና የኢንሹራንስ ወጪዎችን ብቻ በአመልካቾች የሚሸፈን ይሆናል ብሏል።
የትምህርት ሂደቱ የቆይታው ጊዜ ለባችለር አራት አመት ለማስተርስ ሁለት አመት እንዲሁም ለ ፒ ኤች ዲ አመልካቾች እንደ ትምህርቱ አይነት የቆይታ ጊዜያቸው የሚወሰን ይሆናል ተብሏል።
ስኮላርሺፑን አሸንፈው የሚሄዱ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ከመጀመራቸው በፊት ለአንድ አመት የቋንቋ ትምህርት የሚማሩ ሲሆን እንደ ሩሲያን ሃውስ መረጃ ስኮላርሺፑ የሙሉ የትምህርቱን እና የቋንቋን አንድ አመት ቆይታ ያካተተ ነው።
ተማሪዎች ካመለከቱ በኋላ ለስኮላርሺፑ ብቁ የሆኑትን የማጣራት ሂደት የመጀመሪያው ዙር በሳይንስ ማዕከሉ ከተከናወነ በኋላ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ዙር የማጣራት ሂደቶች በሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች እና በሚመለከታቸው አካላት የሚከናወን ይሆናል።
ለስኮላርሺፑ የማመልከት ሂደት ሴፕቴምበር 15 የተጀመረ ሲሆን እስከ ጃንዋሪ 15 የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል።
በሩሲያ የሳይንስ እና ባህል ማዕከል የስኮላርሺፑ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ናድር መሃመድ " የራሺያን ስኮላርሺፕ እንዲሳካ እናደርጋለን እያሉ ብር የሚቀበሉ ኤጀንሲዎች እያየን ነው " ያሉ ሲሆን በስኮላርሺፑ ዙሪያ ህጋዊ ሰውነት ያለው እና የሚያስተባብረው የሩሲያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል ብቻ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አተባባሪው አመልካቾች ለማማከር እና ለተጨማሪ መረጃ ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰአት ወደ ማዕከሉ በመደወል መረጃ በነጻ ማግኘት እንደሚችሉ ገልጸዋል።
ለስኮላርሺፑ ለማመልከት መሟላት ያለባቸው ነገሮች ምንድን ናቸው ?
ፓስፖርት አስፈላጊ ቢሆንም ስኮላርሺፑን ለማመልከት አስገዳጅ አይደለም።
በቀበሌ ወይም በፋይዳ መታወቂያ ማመልከት ይቻላል።
የአመልካቾች የ9 ፣ 10 ፣ 11 እና 12 የትምህርት ማስረጃቸው እንዲያስገቡ ይጠየቃል።
አሁን 12 ክፍል እየተማሩ ያሉ አመልካቾች እስካመለከቱበት ጊዜ ያለውን የትምህርት ማስረጃ አስገብተው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት ደግሞ ሲደርስ መስገባት ይችላሉ።
ለማስተርስ አመልካቾች ዲግሪ እና ግሬድ ሪፖርት አስፈላጊ ነው (ዲግሪው ያልደረሰለት ቴምፖራሪውን ማስገባት ይችላል)።
ለፒ ኤች ዲ አመልካቾች የሪሰርች ፕላናቸው ምን እንደሆነ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን አስገዳጅ ባይሆንም ፕብሊሽ የተደረገ የጥናታዊ ጽሁፍ ቢኖራቸው ይመከራል።
ባለፈው አመት ስኮላርሺፑ የተሰጠው 50 በመቶ ለባችለር ዲግሪ ፣ 30 በመቶ ለማስተርስ ዲግሪ እና 20 በመቶ ለፒኤች ዲ ዲግሪ ቢሆንም ይህኛው ስኮላርሺፕ እንደ አመልካቹ ቁጥር ብዛት ፐርሰንቱን ሊሸጋሸግ ይችላል።
ጥሩ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች የመመረጥ እድላቸው ሰፊ ነው በመሆኑ ቢያመለክቱ ይመረጣል።
ጥሩ ውጤት የሌላቸው ተማሪዎች የስኮላርሺፑ የውድድር ሂደት የተማሪዎችን የትምህርት መረጃ በማስተያየት የሚከናወን በመሆኑ በአንዳንድ ትምህርቶች ጥሩ ውጤት ካላቸው ተማሪዎች የተሻሉ ሆነው ቢገኙ ባላንስ ስለሚያደርግ ማመልከት ይችላሉ።
ስኮላርሺፑን https://www.education-in-russia.com ሊንክ በመጠቀም ቋንቋውን ወደ እንግሊዝኛ በመቀየር ማመልከት ይቻላል።
ለተጨማሪ መረጃ ወደ ሩሲያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል በEmail - ethiopia@rs.gov.ru
ወይም n.mokhammed@eth.rs.gov.ru
እንዲሁም በስልክ ቁጥር 251 11 155 1343 ማግኘት ይቻላል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

ሳያነቡ አይፈርሙ
━━•✦•━━
በ400 ዓ.ም. ተወልደው በ450 ዓ.ም. የሞቱት የምሥራቅ ሮማ ንጉሥ የነበሩት ዳግማዊ ቴኦዶሲውስ ማንኛውንም ነገር በሚፈርሙበት ጊዜ ምን እንደተጻፈበት ሳያነቡ ዝም ብለው ይፈርሙ ነበር።
ይህን ነገር የምትመለከት እህታቸው ፑል ቸሪያ አድራጎታቸውን ትቃወም ነበር።
"ሁልጊዜም እያነበብህ፣ ጉዳዩ እየገባህና እያመዛዘንህ ፈርም" ስትላቸው
"ምን አደጋ ይመጣል ብለሽ ነው?" ይሏታል።
በእንዲህ ዓይነቱ ነገር የተናደደችው እህታቸው
የሚል ደብዳቤ ጽፋ ከንጉሡ ጠረጴዛ ላይ አኖረችው።
ንጉሥ ቴኦዶሲውስም ከቢሯቸው እንደገቡ ያን የመገደያቸውን ደብዳቤ ሳያነቡ ፈርመው አስቀመጡት። ነገሩን ትጠባበቅ የነበረችው እህታቸው ደብዳቤውን ወዲያውኑ አንስታ ስታነብላቸው ንጉሡ ደነገጡ።
"ከእንግዲህ ወዲያ ሳላነብ እንዳልፈርም መልካም ትምህርት አስተማርሽኝ" ብለውም እህታቸውን አመሰገኑ።
━━━━━━━━
© ጳውሎስ ኞኞ

"እስከ አሁን የገዛሁት ይበቃኛልና እኔን ገድላችሁ ሌላ አንግሡ።"
የሚል ደብዳቤ ጽፋ ከንጉሡ ጠረጴዛ ላይ አኖረችው።
ንጉሥ ቴኦዶሲውስም ከቢሯቸው እንደገቡ ያን የመገደያቸውን ደብዳቤ ሳያነቡ ፈርመው አስቀመጡት። ነገሩን ትጠባበቅ የነበረችው እህታቸው ደብዳቤውን ወዲያውኑ አንስታ ስታነብላቸው ንጉሡ ደነገጡ።
"ከእንግዲህ ወዲያ ሳላነብ እንዳልፈርም መልካም ትምህርት አስተማርሽኝ" ብለውም እህታቸውን አመሰገኑ።
━━━━━━━━
© ጳውሎስ ኞኞ
#ጥቆማ
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ነርሲንግ ትምህርት ቤት አዲስ ገቢ (ፍሬሽማን) የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የትምህርት ዕድል አመቻችቷል።
የትምህርት ዕድሉ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ነርሲንግ ትምህርት ቤት ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፋቲማ የጤና ኮሌጅ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
ትምህርት ቤቱ የ2018 ዓ.ም አመልካቾችን መቀበል የጀመረ ሲሆን፤ ዘንድሮ ለ 45 አመልካቾች ቅበላ ይደረጋል ተብሏል።
ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም የማመልከቻ ቅፁን ይሙሉ 👇
https://docs.google.com/forms/d/1LV7AZ8XiXU22ipLMIH9NMzWi3kCVwgTDJrBtSp5p0aE/edit

Google Docs
Jimma University School of Nursing
Welcome to Jimma University (JU), a leading public higher education institution in Ethiopia. The Jimma University School of Nursing is collaborating with Fatima College of Health Sciences (FCHS) from the United Arab Emirates (UAE) to enhance nursing education…
❤2
#Japan
የጃፓን ከፍተኛ ፍርድቤት በሀገሪቱ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን በህገመንግስት ከለከለ።
ፍርድ ቤቱ አዲሱን ህግ በ2026 የመጀመሪያ አመት ላይ ተፈፃሚ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
የሀገሪቱ ህገመንግስት አንቀጽ 24 " ትዳር በሁለቱ ፆታዎች (ሴት እና ወንድ) መግባባት ላይ ሲደረስ ይፈፀማል " ይላል።

ኖሬአለሁ . . . !
(I shall not live in vain)
አንዲት ፍጡር ካዳንሁ
ባዘን የምትደማ፣
ኖሬአለሁ እላለሁ
ምንም ሳላቅማማ፣
ውጋት የሰቀዛት
አንዲት ነፍስ አግኝቼ፣
ከስቃይ ባወጣት
እጆቼን ዘርግቼ፣
ወይም አንዲት ድምቢጥ
ከመሬት አንስቼ፣
ጎጀዋ ባስቀምጥ
እስትንፋስ ዘርቼ፣
ምንም አላፍርበት
ኖሬአለሁ ለማለት።
✍ ኤሚሊ ዲክንሰን (1830 - 1886)
ትርጉም ➢ መንግሥቱ ወልደ ማርያም
(I shall not live in vain)
አንዲት ፍጡር ካዳንሁ
ባዘን የምትደማ፣
ኖሬአለሁ እላለሁ
ምንም ሳላቅማማ፣
ውጋት የሰቀዛት
አንዲት ነፍስ አግኝቼ፣
ከስቃይ ባወጣት
እጆቼን ዘርግቼ፣
ወይም አንዲት ድምቢጥ
ከመሬት አንስቼ፣
ጎጀዋ ባስቀምጥ
እስትንፋስ ዘርቼ፣
ምንም አላፍርበት
ኖሬአለሁ ለማለት።
✍ ኤሚሊ ዲክንሰን (1830 - 1886)
ትርጉም ➢ መንግሥቱ ወልደ ማርያም
#SocialMedia🚫
በአውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የማህበራዊ ሚድያ እንዳይጠቀሙ እገዳ ተደረገ።
ሀገሪቱ እንደ ቲክቶክ፣ ኢንስታግራም፣ ዩቲዩብ፣ ፌስቡክ እና ሬዲት ባሉ መድረኮች ላይ ታዳጊዎች የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች እንዳይኖራቸው የሚከለክል ህግ ተግባራዊ አድርጋለች።
የማህበራዊ ሚድያ ኩባንያዎች ይህንን አዲስ ህግ ካላከበሩ እስከ 49.5 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል፡፡
የሃገሪቱ መንግስት እገዳው ከማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በታዳጊ ልጆች ላይ የሚደርሱ ስጋቶችን ለመቀነስ ያለመ ነው ብሏል።
ህጉ ስራ ላይ መዋሉን ተከትሎ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከ16 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ከሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች በቀጥታ እንዲወጡ/እንዲወገዱ ተደርገዋል።
አውስትራሊያ ውስጥ የትኞቹ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሕጉን እንዲተገብሩ ይገደዳሉ ?
እንደ:-
- ቲክቶክ፣
- ዩትዩብ፣
- ኢንስታግራም፣
- ፌስቡክ፣
- ስናፕቻት፣
- ሬዲት፣
- ኤክስ (የቀድሞ ትዊተር)፣
- ትዊች፣
- ኪክ፣
- ትሬድስ የመሳሰሉ የማህበራዊ ሚድያ መተግበሪያዎች ከ16 ዓመት በታች ያሉ ልጆች አገልግሎት እንዳያገኙ የማድረግ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡
ዋትስአፕ ፣ ሜሴንጀር፣ የኢሜል አገልግሎቶች ፣ የኦንላይን ላይ ጨዋታዎች እና የተለያዩ ትምህርታዊ መሳሪያዎች ከእገዳው ነፃ ሆነዋል፡፡
የእገዳው ግቡ ምንድነው?
- ልጆችን ከሳይበር ጥቃት ፣ ማዋረድ ፣ ከክፉ ሃሳቦች ፣ ስድብ መከላከል፡፡
- የልጆችን የአእምሮ ጤና መጠበቅ፡፡
እገዳው እንዴት ይሰራል?
መተግበሪያዎቹ የዕድሜ ማረጋገጫ እርምጃዎችን ይወስዳሉ። ለምሳሌ ፡- የፊት ዕድሜ ግምት ፣ የዶክመንት ማጣራት ፣ ሌሎች ምክንያታዊ የሆኑ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ (ከ16 ዓመት በታች ልጆች አካውንት እንዳይከፍቱ ያላቸውንም እንዳይጠቀሙ)።
በእርግጥም ኩባንያዎቹ ህጉን ተግባራዊ ያደርጋሉ?
ትልልቆቹ ኩባንያዎች ህጉን ለመተግበር ተስማምተዋል። እንደ ሜታ (ፌስቡክ ፣ ኢንስታግረም እና ትሬድስ ) እንዲሁም ቲክቶክ ተጠቃሚዎችን ማሳወቅ ፣ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆችን አካውንት ማስወገድ ጀምረዋል፡፡
ኤክስ (የቀድሞ ትዊተር ) በይፋ እንዴት ተግባራዊ እንደሚያደርግ አልገለፀም ፤ ነገር ግን ኩባንያው ህጉን የግድ ተግባራዊ እንዲያደርግ በመንግስት በዝርዝር ከተቀመጡት የማህበራዊ ሚዲካ ኩባንያዎች መካከል ነው።
ኒውዚላንድ፣ ዴንማርክ እና ማሌዥያን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት መንግስታት የአውስትራሊያን አካሄድ ለመተግበር እያጤኑ ነው።
አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ በህግ የከለከለች ቀዳሚ ሀገራ ሆናለች።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ነው ያሰባሰበው።
#TikvahEthiopia

ታኅሣሥ ፲፪ ምን ይከሠታል ?
ይህ መረጃ በኢትዮጵያ የስነ-ከዋክብት ተመራማሪ በሆኑት በዶ/ር ሮዳስ ታደሰ የተሰጠ ሳይንሳዊ ትንበያ ሲሆን፣ ከሥነ-ፈለክ (Astronomy) አንጻር ሲታይ ፍጹም ትክክልና የሚከሰት ክስተት ነው።
በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ታኅሣሥ 12 (በፈረንጆቹ December 22) "Winter Solstice" ወይም የክረምት መለወጫ ተብሎ የሚጠራው ዕለት ነው። ዶ/ር ሮዳስ ያስተላለፉት መልዕክት የሚከተሉትን ነጥቦች ያጠቃልላል፦
* የቀኑ ርዝመት፡ ይህ ዕለት በሰሜናዊው የዓለም ክፍል (ኢትዮጵያን ጨምሮ) የዓመቱ አጭሩ ቀን ነው።
* የሌሊቱ ርዝመት፡ በአንጻሩ የዓመቱ ረጅሙ ሌሊት የሚመዘገብበት ወቅት ነው።
* ምክንያቱ፡ መሬት በዝንባሌዋ (Axial tilt) ምክንያት ከፀሐይ ርቃ የምትገኝበት የመጨረሻው ነጥብ ላይ በመድረሷ ነው።
ለምን እውነት ይሆናል? (ሳይንሳዊ ማብራሪያ)
ይሁን እንጂ ዶ/ር ሮዳስ ማህበረሰቡ ስለ ተፈጥሮ ክስተቶች ግንዛቤ እንዲኖረው ለማድረግ የሚጠቀሙበት ሳይንሳዊ ሃቅ ነው።
* የፀሐይ ጉዞ፦ ፀሐይ በደቡባዊ ንፍቀ ክበብ (Tropic of Capricorn) ላይ ቀጥታ ስለምታርፍ፣ ለእኛ ለሰሜናዊያኑ ብርሃኗ አጭር ሰዓት ብቻ ይቆያል።
* ቀጥታ ተፅዕኖ፦ ነገ እሑድ ፀሐይ ዘግይታ ትወጣለች፤ ቀድማም ትጠልቃለች። ይህም "ቶሎ ይመሻል" የተባለበትን ምክንያት ያረጋግጣል።
ማሳሰቢያ፦ ነገ እሑድ ታኅሣሥ 12 ቀን፣ ቀኑ አጭር በመሆኑ ለስራና ለጉዞ የምታቅዱ ሰዎች ጊዜያችሁን በአግባቡ እንድትጠቀሙ ይመከራል። ፀሐይ ቀድማ ስለምትጠልቅ የምሽቱ ጨለማ ረጅም ይሆናል።
ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ

❤1
#Opportunity_Alerts📣
🚀Calling Young African Creatives: Join AU Logo Design Competition 2027🚀
✨Are you an African creative aged 18–24 with a passion for graphic design, art, branding, or digital creativity? The African Union Commission is inviting young creatives across Africa to design the official logo and visual identity for the AU Theme of the Year 2027.
What You’ll Gain:
🔹Certificate of recognition
🔹Official recognition through AU platforms
🔹Training opportunities
🔹Opportunity to participate in the AU Summit
🔹Winning logo used as the official visual identity throughout 2027
🔹Prize:
🥇$5,000 for 1st place
🥈$2,000 for 2nd place
🥉$1,000 for 3rd place
Who Can Apply:
🔸Citizens of any African Union Member State
🔸Aged 18–24 on the deadline
🔸Students, designers, artists, digital creatives and innovators
🔸No formal design qualification required
🔸Individual applicants only
🔸One entry per applicant
🔸Generative AI is NOT permitted & the logo must be original and human-created
📍Location: Open across Africa
🔗Apply: https://au.int/en/newsevents/20260829/call-entries-calling-young-african-creatives-logo-competition-au-theme-year
Deadline: October 23, 2026

African Union
Call for Entries: Young African Creatives Invited to Design the Official Logo and Visual Identity for the AU Theme of the Year…
The 39th Ordinary Session of the Assembly of Heads of State and Government adopted the AU Theme of the Year 2027: “AU at the Dawn of its 25th Anniversary: Leveraging the Full Potential of SAATM & New Technologies for Continental Integration.”
❤1
ሳናውቀው የስልካችን ስክሪን ላይ ብዙ ሰዓት እናሳልፋለን።ይኽም ለዓይናችን፣ለአእምሯችን፣ለማኅበራዊ ኪሂሎታችን ••• ትልቅ ተጽዕኖ አለው።በስልካችን ስክሪን ምን ያህል ሰዓት በቀን እንደምናሳልፍ፡አብዛኛውን ሰዓት የትኛውን የስልካችን መተግበርያ(app) ለምን ያህል ሰዓት እንደምንጠቀም ለማወቅ እንዲሁም ገደብ ለማስቀመጥ(ካስቀመጥነተው ገደብ በላይ ስንጠቀም Notfication እንዲያሳየን) በAndroid ስልኮች built in setting አለ።
፩ Setting ውስጥ ይግቡ
፪ Digital well being and parental control የሚል ፈልገው ይጫኑ
፫ ከዚያ በቀን ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ስልኮን እንደከፈቱ(Unlocks)፣ስንት Notification እንደተቀበሉ ጨምሮ የትኛውን App በብዛት እንደተጠቀሙ ከላይ ባለው ምስል ዓይነት ያሳዮታል።ተጨማሪ መረጃዎችን ይኽንን በመከተል ማየትና ያንኖ App የሚጠቀሙበትን ጊዜ ገደብ (Limit)ማበጀት ይችላሉ።
ከላይ ያለው ምስል(Pic) እንደሚያሳየው የዚህ ስልክ ባለበት (Oct 25) በቀን ለ8 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ያህል ስልኩን የተጠቀመ ሲሆን ለ4 ሰዓት ከ35 ደቂቃ YouTube ,ለ1 ሰዓት ከ 5 ደቂቃ ቴሌግራም እንዲሁም ሌሎችን እንደየ መጠናቸው ተጠቅሟቸዋል።29 ጊዜ ስልኩን የከፈተ ሲሆን(Unlock) 202 Notification ተቀብሏል።

Garbage in Garbage out(GIGO)
This expression is familiar in the field of computer science. It indicates that the quality of the output of the computer is determined by the quality of the input.If you feed your computer poor quality input data then you should expect poor quality outcome no matter how sophisticated your processor or Logic is.
I think this case is also the same for us humans.The things that we feed to our brains have direct influence on our personality, attitude and behavior. The movies we watch;The music's we listen to;the compliments and the criticisms we receive from others;the books we read make us who we are and who we become.The effect on our life may be either visible(when the effect is on our conscious mind) or hidden (when the impact is on our subconscious mind).The latter effect is by far more serious and stronger in that each and every tiny thing we absorbed will be written and saved in our subconscious mind so as to be printed later when the time comes.Mostly our habits,feelings and attitudes are determined by the subconscious mind,and sadly it is much difficult to unlearn and delete what we have received as input to our subconscious mind.We can't just erase it as such easily.It becomes part of your life.This is why we have to be extra cautious with what we supply to our brain.As we choose what to feed for our body we should too care about what we feed to our brain.
Ke-ay-d 2019

In Vietnam, artificial intelligence is being formally integrated into the national education system to prepare students for a technology-driven future. Beginning with the 2026-2027 academic year, the Ministry of Education and Training has mandated a new framework that includes 12 dedicated AI lessons per academic year for students across the country.
schools focus on teaching both the practical benefits of AI—such as using tools for creative illustration and problem-solving—and the potential dangers, including security risks and misinformation.