Forwarded from ሐዋርያዊ መልሶች Chat
ዘፈን ኖርማል ነው ብለን ሳይሆን አንተ ስታነበው እንደዛ አንብበኸው ነው ሙሌ.. እስቲ መነጽሯን አውልቀህ ሞክራት ሎል
አይ ግን ያው ጤናማ ግጥም ያለው ዘፈን በራሱ ኃጢአት አይደለም..ግን ደግሞ የዓለምን ፍቅር በውስጥ ሊያሳድር ስለሚችል መዝሙር ነው መስማት ያለብን.. ዓለምን መውደድ ከእግዚአብሔር ጋር ጥል ነውና

Forwarded from ሐዋርያዊ መልሶች
አንድ ፕሮቴስታንት ወንድም እንዲህ ሲል ይተቻል..
[ ክርስቲያኖች ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ውስጥ ዘፈን አትሰሙም.. ከዚያ ስትወጡ ግን የምትሰሙ ከሆነ እንግዲያውስ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሆናችሁት በትርፍ ሰዓታችሁ ነው(ቤተ ክርስቲያን ስትሄዱ ብቻ) ]
ይሄ ወንድም የምር በተገኘበት መሸለም አለበት.. እንዲህ ያለ ብሩህ እና ታላቅ የማሰላሰል ብቃት ያለው አእምሮን ይዞ በቲክቶክ ብቻ መገደብ የለበትም.. ዓለም ላይ ላሉ ብዙ ችግሮች መፍትሄ ማምጣት የሚችል ዓይነት ሰው እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ..
እናንተ ደግሞ “ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሙቪ አናይም ስንወጣ ግን እናያለን..” እንዳትሉ ቆይ😁😁
[ ክርስቲያኖች ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ውስጥ ዘፈን አትሰሙም.. ከዚያ ስትወጡ ግን የምትሰሙ ከሆነ እንግዲያውስ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሆናችሁት በትርፍ ሰዓታችሁ ነው(ቤተ ክርስቲያን ስትሄዱ ብቻ) ]
ይሄ ወንድም የምር በተገኘበት መሸለም አለበት.. እንዲህ ያለ ብሩህ እና ታላቅ የማሰላሰል ብቃት ያለው አእምሮን ይዞ በቲክቶክ ብቻ መገደብ የለበትም.. ዓለም ላይ ላሉ ብዙ ችግሮች መፍትሄ ማምጣት የሚችል ዓይነት ሰው እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ..
Forwarded from ኪዳን ዘኢየሱስ
ዛሬ የምር በጣም አሳዛኝ ነገር ነው የሰማሁት ለነገሩ ዛሬ ብቻ አይደለም ብዙ ጊዜ በውስጥ የሚመጡልኝ መልእክቶች በክርስትና በጣም እንደሚቀረን ነው እየተረዳሁ ያለሁት ፤ ክርስትናን ሳይሆን እየኖርን ያለነው ይሁዲነትን ነው ያስብላል አንዳንዴ።
ለምሳሌ ከሰማሁት ልንገራቹ አንዲት ሴት ገና teenager እያለች ትደፈራለች በኋላ ስታድግ በቤተክርስቲያን ውስጥ በተክሊል ማግባት አትችዪም ትባላለች ፤ እንዲሁም ዲያቆን ድንግል ስለሆነ ማግባት ያለበት ከአንድ ዲያቆን ጋር ቢዋደዱ እንኳን መጋባት አትችሉም ይባላሉ።
Really? አሁን ክርስቶስ ቢወርድ ኖሮ ፈሪሳዊያንን እንደ ወቀሰ አይወቅሰንም? ቆይ ተክሊል ድንግልናን እስከ ትዳር ለጠበቁ ሽልማት ነው አልተባለም እንዴ ታድያ የተደፈረች ሴት ምን አጥፍታ ሽልማቷ ይቀርባታል? ቆይ ድንግልናን የምንመለከተው ከሥጋ አንጻር ብቻ ነው እንዴ? እንደሱ ከሆነማ ብዙ ሴቶች በተፈጥሮም ሆነ በከባድ ሥራ የማይኖራቸው አለ እነርሱስ ሊከለከሉ ነው?
በአንዲት ሴት ላይ እኮ መደፈር ከባድ የሆነ አካላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ ጉዳት ነው የሚያደርሰው ፤ አንድ አንድ ሴቶች ጭራሽ ወንድ የተባለ ፍጡርን የሚጠሉ አሉ ፤ ራሳቸውን እንደ ረከሱ ያያሉ ፣ እንዲሁም long lasting trauma ነው የሚከተላቸው ፣ ጭራሽ የእኛ ማኅበረሰብ ደግሞ የራሳቸው ጥፋት እንደሆነ አድርገው ነው ጣታቸውን ወደ ተጠቂዎቹ ሴቶች የሚጠቁሙት።
ታድያ ቤተክርስቲያን በዚህ ጊዜ ማረፊያ መሆን ሲገፋት ጭራሽ ቤተክርስቲያንም ስታገል ምኑን ከማኅበረሰቡ ተለየች? ምኑን የክርስቶስ ልብ ኖራት? አስቡት ያለ ፈቃድሽ አንድ አረመኔ ጨካኝ ወንድ ስለ ተጫወተብሽ ረክሰሻል ተክሊል አይገባሽም ስትባል? ጭራሽ እኮ ዲያቆን ክህነቱ ንጹሕ ነው ታረክሺዋለሽ ካገባሽ ነው የተባለችው። I don't even have the words to describe my anger ብቻ ቤተክርስቲያናችን በጣም የተማሩ ንስሐ አባቶች እንደሚያስፈልጓት ነው የተረዳሁት በዚህ ታሪክ ብቻ ሳይሆን በብዙ ታሪኮች ፤ በተለይ ሴቶች እኅቶቻችን ላይ የሚደርሰው ግፍ ከባድ ነው። ጌታ ይታደገን ብቻ ምን ይባላል።
የሚጠፋ እንደዚህ አይነት ነገር ምናልባት ስለማልጽፍ

Forwarded from ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
ትንሽ እንጨዋወት መሰለኝ 😁
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ በእርሱ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች ትንሹም ፣ ትልቁም ከባድ ነገረ መለኮታዊ ርዕሶችን ባገኙት ቦታ ሲወያዩ ተመልክቶ :- “ሥነ መለኮት ለሁሉም አይሆንም ስለዚህ በብዙ ልንጠነቀቅ እና ራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል።” በማለት ገሰጻቸው።
Meanwhile የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን በ 21 ኛው ክፍለ ዘመን የሚወያዩባቸው ርዕሶች :- “ቡና መጣጣት ኃጢአት ነው ወይስ አይደለም ? የቴዲ አፍሮን ዘፈን መስማት ኃጢአት ነውን ? አሳ ጾም አለው ወይስ የለውም ?”😭😭
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ እንደው ምን ሊለን የሚችል ይመስላችኋል ?
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ በእርሱ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች ትንሹም ፣ ትልቁም ከባድ ነገረ መለኮታዊ ርዕሶችን ባገኙት ቦታ ሲወያዩ ተመልክቶ :- “ሥነ መለኮት ለሁሉም አይሆንም ስለዚህ በብዙ ልንጠነቀቅ እና ራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል።” በማለት ገሰጻቸው።
Meanwhile የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን በ 21 ኛው ክፍለ ዘመን የሚወያዩባቸው ርዕሶች :- “ቡና መጣጣት ኃጢአት ነው ወይስ አይደለም ? የቴዲ አፍሮን ዘፈን መስማት ኃጢአት ነውን ? አሳ ጾም አለው ወይስ የለውም ?”😭😭
Forwarded from ኪዳን ዘኢየሱስ
መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ በቂ ነውን?
አንድ ሰው ለመዳን የሚያስፈልጉትን እውቀቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማግኘት ይችላልን? ማለትም ኹሉም እውቀቶች በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይገኛሉ ለማለት ሳይኾን ለመዳን የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ዶግማዊ እውቀቶች ግልጽ በኾነ መንገድ (explicitly) ወይም ግልጽ ባልኾነ መንገድ (implicitly) ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማግኘት ይቻላል?
አይቻልም ብላችሁ የምትከራከሩ አንድ ወጥመድ ውስጥ ትገባላችሁ እርሱም ለመዳን የሚያስፈልጉ እውቀቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት እንደሚቻል መጽሐፍ ቅዱስም ኾነ የጥንት ቤተክርስቲያን አባቶች ጽፈዋል የቤተክርስቲያን አባቶችማ ከዚህም ገፍተው ስለ ዶግማዊ ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ጠቅሰን ካላስተማርናችሁ አትቀበሉን ሲሉ ጽፈዋል እስቲ ጥቂት ምሳሌ እንመልከት:
John 20 አማ - ዮሐንስ
30: ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤
31: ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል። (ኹሉ ነገር አልተጻፈም ለእምነትና ለሕይወት በቂ የኾኑት ነገሮች ግን ተጽፈዋል)
2 Timothy 3 አማ - 2ኛ ጢሞቴዎስ
15: ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል።
16-17: የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።
Gregory of Nyssa
Irenaeus of Lyons
Athanasius of Alexandria
እነዚህን ካየን ይብቃንና እነዚህ ማስረጃዎች የሚያረጋግጡልን ለመዳን የሚያስፈልጉ ዶግማዎች በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት እንደምንችል ነው። ይህ ማለት ታድያ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ በቂ ነውን? የሚለውን ጥያቄ ስንመለከት "በቂ" የሚለው ቃል ምን ማለት ነው የሚለውን መገምገም አለብን። እኛ መጽሐፍ ቅዱስ ለመዳን የሚኾኑ እውቀቶችን በሙሉ ይዟል ነገር ግን እነዚህን እውቀቶች በጽሑፍ ደረጃ ነው እንጂ የያዘው ለእነዚህ እውቀቶች contextኡን የያዘው የቤተክርስቲያን ትውፊት ነው እንላለን (The Church is the active agent of infallibility )፤ ይህን Material sufficiency of Scripture ብለን ልንጠራው እንችላለን። ዶግማዎቻችን እንዳለ የሚወጡት ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው ለእዚህ መጽሐፍ ግን infallible በኾነ መንገድ ትርጓሜ የምትሰጠው ቤተክርስቲያን ናት። በአጭሩ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ቢያንስ implicitly እንኳን የሌለ ዶግማ የለንም።
ይህን በምሳሌ ለመረዳት መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ሕንፃ የሚሠራበት blue print ነው ፣ ሕንጻው ደግሞ የቤተክርስቲያን ዶግማዋ ነው blue printኡ ላይ የሌለ ነገር አይሠራም ነገር ግን blue printኡ ብቻውን ሕንፃ አይኾንም context የሚሠጠው የቤተክርስቲያን ትውፊት ያስፈልጋል።
በመጨረሻም ይህ ማለት መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የማይገኙ ትውፊቶች የለንም ማለት አይደለም ይልቅስ ዶግማ የኾኑ ትውፊቶች መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የማይገኙ የሉንም ማለት ነው።
@KidanZeIyesus

"What then is our reply? We do not think that it is right to make their prevailing custom the law and rule of sound doctrine. For if custom is to avail for proof of soundness, we too, surely, may advance our prevailing custom; and if they reject this, we are surely not bound to follow theirs. Let the inspired Scripture, then, be our umpire, and the vote of truth will surely be given to those whose dogmas are found to agree with the Divine words." (Dogmatic Treatises, Book 12. On the Trinity, To Eustathius.)
“Let the inspired Scriptures then be our umpire, and the vote of truth will be given to those whose dogmas are found to agree with the Divine words.” (On the Holy Trinity, NPNF, p. 327)
Irenaeus of Lyons
We have learned from none others the plan of our salvation, than from those through whom the Gospel has come down to us, which they did at one time proclaim in public, and, at a later period, by the will of God, handed down to us in the Scriptures, to be the ground and pillar of our faith. (Against Heresies, 3.1.1)
Athanasius of Alexandria
These are fountains of salvation, that they who thirst may be satisfied with the living words they contain. In these alone is proclaimed the doctrine of godliness. Let no man add to these, neither let him take ought from these. For concerning these the Lord put to shame the Sadducees, and said, ‘Ye do err, not knowing the Scriptures.’ And He reproved the Jews, saying, ‘Search the Scriptures, for these are they that testify of Me.’ (Festal Letter 39, 6–7)
“Vainly then do they run about with the pretext that they have demanded Councils for the faith’s sake; for divine Scripture is sufficient above all things.” ( Letter, De Synodis, Par. 6; 296)
እነዚህን ካየን ይብቃንና እነዚህ ማስረጃዎች የሚያረጋግጡልን ለመዳን የሚያስፈልጉ ዶግማዎች በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት እንደምንችል ነው። ይህ ማለት ታድያ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ በቂ ነውን? የሚለውን ጥያቄ ስንመለከት "በቂ" የሚለው ቃል ምን ማለት ነው የሚለውን መገምገም አለብን። እኛ መጽሐፍ ቅዱስ ለመዳን የሚኾኑ እውቀቶችን በሙሉ ይዟል ነገር ግን እነዚህን እውቀቶች በጽሑፍ ደረጃ ነው እንጂ የያዘው ለእነዚህ እውቀቶች contextኡን የያዘው የቤተክርስቲያን ትውፊት ነው እንላለን (The Church is the active agent of infallibility )፤ ይህን Material sufficiency of Scripture ብለን ልንጠራው እንችላለን። ዶግማዎቻችን እንዳለ የሚወጡት ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው ለእዚህ መጽሐፍ ግን infallible በኾነ መንገድ ትርጓሜ የምትሰጠው ቤተክርስቲያን ናት። በአጭሩ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ቢያንስ implicitly እንኳን የሌለ ዶግማ የለንም።
ይህን በምሳሌ ለመረዳት መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ሕንፃ የሚሠራበት blue print ነው ፣ ሕንጻው ደግሞ የቤተክርስቲያን ዶግማዋ ነው blue printኡ ላይ የሌለ ነገር አይሠራም ነገር ግን blue printኡ ብቻውን ሕንፃ አይኾንም context የሚሠጠው የቤተክርስቲያን ትውፊት ያስፈልጋል።
በመጨረሻም ይህ ማለት መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የማይገኙ ትውፊቶች የለንም ማለት አይደለም ይልቅስ ዶግማ የኾኑ ትውፊቶች መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የማይገኙ የሉንም ማለት ነው።
@KidanZeIyesus
Forwarded from ኪዳን ዘኢየሱስ
ኢየሱስ ይወዳችኋል
ብዙ ጊዜ ዕቅበተ እምነት ላይ ብቻ ስናተኩር የክርስትናን ዋና መሠረትን እንዘነጋለን። ዕቅበተ እምነት በጣም አስፈላጊ ነገር ቢኾንም እኛ ሰዎች ግን በአመክንዮ የታጠርን ብቻ አይደለንም አንዳንድ ጊዜ ሰው "ክርስትና ለምን እውነት እንደኾነ 10 አሳማኝ ምክንያቶችን" የሚል ሙግት ላይፈልግ ይችላል ይልቅስ የፈለግነውን ተዋስኦ ብናቀርብ የምንናገረው ነገር ወደ ልቡ ውስጥ ካልገባ ደረቅ እውነት ብቻ ይኾንበታል።
ሐዋርያት ወደ ዓለም ዳርቻ የተላኩት ወንጌልን ሊሰብኩ ነው εὐαγγέλιον - የምስራች ማለት ነው። እግዚአብሔር አንድያ ልጁን አሳልፎ እስኪሰጥ ዓለምን እንዲሁ ወዷል ፤ ወልደ እግዚአብሔር ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ኃጢአታችሁን በመስቀል ላይ ተሸክሞ እንዲሁ በጸጋው ድናችኋል እያሉ የምስራቹን መልካም ዜና ወደ ዓለም እየሰበኩ አሰራጩ። በእርግጥ ከእነርሱ ስነ አመክንዮን እየተጠቀሙ የተጠበቀው መሢሕ በእውነትም ኢየሱስ እንደኾነ የክርስትናን እውነታ መጽሐፍ እየጠቀሱ ሞግተዋል ይህም ዐቃቤ እምነት ያደርጋቸዋል። ነገር ግን ዐቃቤ እምነት ብቻ አልነበሩም የምስራቹ ወንጌል ሰባኪያን ናቸው እንጂ።
አሁን ላይ ከኦርቶዶክሳዊያን ወገን ጥሩ የዕቅበተ እምነት ሥራዎች እየተሠሩ ነው በዚህም እንደሰታለን። ነገር ግን ከፕሮቴስታንት አንድ መማር ያለብን ነገር አለ የወንጌል ሥርጭት። ወንጌል ዕቅበተ እምነት ብቻ አይደለም ለተጨነቁት መድኃኒት ላጡት ይኸው መድኃኒት ብሎ መስበክ ነው ፤ ደስታ ለራቃቸው ኹል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ እያሉ ማስደሰት ነው ፤ ፍቅር ለራቃቸውም ኢየሱስ ይወዳችኋል ስለ ኃጢአታችሁ ሞቶላችኋል እያሉ ማጽናናት ነው።
በእርግጥም ፍቅር የኾነው ኢየሱስ ይወደናል ስለዚህ በፍቅሩ እንኑር ፍቅሩንም ለኹሉም እናጋራ ፤ ደቀ መዛሙርቱ መኾናችን የሚታወቀው በምናቀርባቸው ሙግቶችና ባለን እውቀት ደረጃ ሳይኾን ከፍቅራችን የተነሣ ነውና!
ኢየሱስ ይወዳችኋል!

ታቦትና መሠውያ
መምህር ዘበነ ከ5 ቀን በፊት በሠራው Video ላይ እንድ ነገር መናገር ፈለኩ። ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመቅናት የተነሣ ታቦትና ጽላት ያለን ከዓለም እኛ ብቻ ነን ሌሎቹ ኦርቶዶክሳውያን ያላቸው Altar (መሠውያ) ወይም Lord's Table (ጠረጴዛ) ብቻ ነው። እኛ ግን ከመሠውያ በተጨማሪ አሠርቱ ትእዛዛት የተጻፈበት ጽላት እንዲሁም የብሉይ ኪዳን የቃልኪዳኑ ታቦት አለን። መሠውያ የምንለውም ሥጋውና ደሙ የሚሠዋበት ሳይኾን ድርገት ሲወርድ ለምእመናን የሚቀርበበት ነው ይለናል።
ይህ ግን የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ፍጹም ኦሪታዊት የሚያስመስል አደገኛ ትምህርት ነው። ቤተክርስቲያን አሠርቱ ትእዛዛት የተጻፈበት ጽላትም ኾነ የብሉዩ የቃልኪዳን ታቦት የላትም። ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ አንድ ላይ አዲስ ቤተክርስቲያን እንዴት እንደሚከብር ሲናገር አሠርቱ ትአዛዛት ስለተጻፈበት ጽላትም አያነሳም እንዲሁም ጽላቱ ስለሚቀመጥበት የቃልኪዳን ታቦት አላነሳም ይልቅስ "የመሠውያውን ታቦት በዘይት ያክብሩት ... በመሠዊያው ላይም ይቀድሱ ... ወደ መሠዊያው ቦታ ይስገዱ" እያለ ታቦት እና መሠዊያ የሚባሉትን ቃላት በተለዋዋጭ የክርስቶስ ሥጋና ደም ስለሚሠዋበት ቅድስት ጠረጴዛ ይናገራል ነገር ግን ድርገት ሲወርድ ሥጋወ ደሙ የሚቀርበበትን ንዋይ አንድም ቦታ መሠዊያ አይለውም ፣ ጠረጴዛም አይለውም። ይህ የጌታ ሥጋና ደም የሚቀርበበት ታቦተ ምሥዋዕ ደግሞ የሚገኘው በኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን የክርስቶስ ሥጋና ደም እውነተኛ መሥዋዕት ነው ተብሎ በሚያምኑ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ነው።
ይህ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ከዓለም ልዩ ለማድረግ ተብሎ ኦሪታዊት ለማስመሰል የሚደረገው ሙከራ መቆም አለበት።

ስለእኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው
ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ ይማልዳል ስንል የክርስቶስ ምልጃ አንድ ጊዜ ቀርቦ ለኹልጊዜ ይሠራል ማለታችን ነው። ቅዳሴ አትናቴዎስ ቁጥር 144 ላይ " ወልድ ሆይ እንደ ታመመ ሰው አሰምተህ ተናገር ኤልማስ ላማ ሰበቅታኒ በል። በአፋቸውም ውስጥ እያለ አባ አባቴ ሆይ ሥጋዬን የበሉትን ደሜን የጠጡትን ማራቸውም ይቅር በላቸው በል" እያለ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ በታላቅ መቃተት ያቀረበው ምልጃ ዛሬም በሥጋውና ደሙ ገና በአፋችን ሳለ እንደሚሠራልን ያስገነዝበናል። የክርስቶስ ምልጃ ፍጹም ነው እንደ ብሉይ ኪዳን ሊቃነ ካህናት በየዓመቱ መደጋገም አይጠበቅበትም አንድ ጊዜ ባቀረበው ምልጃ ዘለዓለም ሊያድነን ይችላል "ስለ እነርሱም ሊማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል" እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ።
እንዲህ ያለ ከፍ ያለ የታመነ ሊቀ ካህናት በሰማይ አለን ለኃጢአታችን ሥርየት አንድ ጊዜ ባፈሰሰው ደም ዛሬም ይምረናል "ሊቀ ካህናት ዘይቀውም ሎሙ ለቅዱሳን በደብተራ ስምእ እንተ እግዚአብሔር ተከላ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ-እግዚአብሔር በተከላት ምሥክር ድንኳን ውስጥ ለቅዱሳን የሚቆምላቸው ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው" እንዲል አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ። አንድ ጊዜ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በደሙ ገብቷል እኛም የክርስቶስን ደም አንድ ጊዜ በማቅረብ ተቀድሰናል እስከ ሕይወት ፍጻሜያችንም እንቀደሳለን ምልጃው ድግግሞሽ የማይስፈልገው አንድ ጊዜ ለዘለዓለም የቀረበ ፍጹም ነውና!
በአብ ዘንድ የታመነ ጠበቃ አለን ለኃጢአታችን ብቻ ሳይኾን ለዓለም ኹሉ ኃጢአት ሥርየት አንድ ጊዜ የቀረበ አስታራቂ በአብ ቀኝ አለን ልያውም በድካማችን የሚያግዘን ፈተናችንን ኹሉ የተፈተነ ሊራራልን የሚችል ሊቀ ካህናት በሥራው ኹሉ የታመነ ነው ወደ እርሱ እንቅረብ ከኃጢአታችን ኹሉ በቅዱስ ደሙ ያነጻናልና!

አንድ ወንድም አንዲት እህት ላይ በዩትዩብ ሄደባት አሉ😁😁 ጀለስ እኮ ያኔ ከእኔ ጋር በተያያዘ ሚዲያው ላይ ውዝግብ በተነሳበት ወቅትም ምንም በማያውቀው ነገር ትንሽ ተናግሮኝ ነበር.. እና በዛው የተወሰኑ ሰዎችን አምጥቶ ቪዲዮ ሲሰራ ነበር እና ተሳስቼም ከሆነ ጌታ ይቅር ይበለኝ ግን በቃ እሱ ኮንተንት ነው የሚያደርግህ😁😁 ያው ግን ሰው ነኝና ተሳስቼ ተረድቼውም ሊሆን ይችላል
ስለ ቅድስና ከተወራ ግን እኛ ሁላችን አምላክ ያለን ሕዝቦች ነን.. ያውም ኢየሱስን የመሰለ ጌታ ነው ንጉሳችን.. ስለዚህም አምላክ እንደሌለው ሰው እንዲሁ ልንኖር አይገባም.. ይሄ የማንንም ልብ ስለማላውቅ ማንንም ስህተት ወይም ትክክል ለማለት አልደፍርም.. አንድ የማውቀው ነገር ግን አምላክ እንደሌላቸው ሕዝቦች አንኖርም
ስለ ቅድስና ከተወራ ግን እኛ ሁላችን አምላክ ያለን ሕዝቦች ነን.. ያውም ኢየሱስን የመሰለ ጌታ ነው ንጉሳችን.. ስለዚህም አምላክ እንደሌለው ሰው እንዲሁ ልንኖር አይገባም.. ይሄ የማንንም ልብ ስለማላውቅ ማንንም ስህተት ወይም ትክክል ለማለት አልደፍርም.. አንድ የማውቀው ነገር ግን አምላክ እንደሌላቸው ሕዝቦች አንኖርም
Forwarded from ሐዋርያዊ መልሶች
ኧረ አንዱ ወዳጄ ምን ቢለኝ.. ለአንድ መምህር ስለ እኔ አጋጣሚ ሆኖ አንስቶባቸው ምን ቢሉት..?? “ያ በሡሪ ቁረቡ የሚለው ልጅ”😭😭
ኧረ መምህርዬ እኔ እንደዛ አላልኩም ይሄ ከኔ ይራቅ😭😭 እኔ ያልኩት ውጭ ላይ ባለ ሕይወቷ ቀለል ያለ ሱሪ ብትለብስም ከቁርባን ግን አትቅሪ ነው.. ለምሳሌ ስፖርት ስትሰራም በቀሚስ አይሆን መቼስ አይደል.. ብቻ ግን ያው ውጭ ባለው ሕይወቷ ነው.. የዛን ቀንማ ፏ ብላ በቀሚስ ነው እንጂ.. ከቻለች ነጭ ቀሚስ ከሌላትም ያው ያለውን😁😁

❤1
Forwarded from ሐዋርያዊ መልሶች