Apostolic Answers Ethiopia
22 subscribers
4 photos
8 videos
1 link
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይሄ ጊዜ ትዝ ይላችኋል አይደል.. መሠረት ደፋር ስታሸንፍ ምስለ ፍቁር ወልዳን ካሜራ ፊት አውጥታ ለዓለም ሁሉ እመቤታችንን ስታሳይ..

ያኔ በዓለም አቀፍ ደረጃ ክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ ደስ አላቸው.. ያው ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ካቶሊክን ጨምሮ ማለት ነው..

አሁን ደግሞ እኛ ሃገር የቲክቶክ አዋርድ ላይ አንዳንድ ልጆች ሲያሸንፉ የወላዲተ አምላክን ስም መጥራታቸው ለአንዳንዶች የሚጨንቅ ሆኗል እና ያሳዝናል..

ሰው አባቱን ወይም ወንድም እህቱን አለያም እናቱን ቢጠራ ምንም ችግር አይኖረውም.. እናቱን ማርያምን ግን ከጠራ ያበሳጫል.. እዛ መድረክ ላይ እኮ እየሰበኩ አይደለም እነዚህ ልጆች.. ያው ፍቅራቸውን እየገለጹ ነው እና ይግለጹ በጣም ደስ ይላል..

@Apostolic_Answers
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኧረ በጌታ ስም😁😁

ስግጥ ፍምስ
ስግጥ ንግሥ
😭😭

እዚ ኮመንት ስዘጋ በውስጥ መጡብኝ
ኢየሱስ አሁንም ድረስ በሰማይ አብን ይለምነዋል(ይጸልያል) እንዴ..??

በውስጥ የደረሰኝ ጥያቄ ነው..

ጌታችን በምድር ሳለ ጸልዩዋል ወደ አብ ማልዷል.. ግን ደግሞ ልክ እንዲሁ አሁንም በሰማይ የጸሎት እና ልመና ድርጊት እየተካሄደ ነው እና ምልጃ ምንለውም እሱን ነው የሚል ትምህርት በቤተ ክርስቲያን ደረጃ በየትም ቦታ አላውቅም.. ጌታ ኢየሱስ በምድር ላይ የሰራው ሥራ ለዘላለም ሕያው ነው.. ለዘላለም ሕያው የሆነው ደግሞ የማይለወጥ ክህነት ስላለውና በአብ ቀኝ አሁንም ድረስ ተቀምጦ ስለሚኖር ነው.. ስለዚህም ስለሁላችን ሞቶ የተነሳው ጌታ በአብ ቀኝ አለና በእርሱ የተሰራው ሥራ ሁሌም የሚያገለግል ነው..

ስለዚህም በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ “ይጸልያል” የሚለውን ቃል የተጠቀሙ ሊቃውንት ቢገኝ እንኳን በምድር ላይ የሰራው ሥራ ሕያው መሆኑን ከማመልከት አንጻር ይሆናል እንጂ አሁንም የቀረ ጸሎት ያለ ይመስል እየደጋገመ እየጸለየ ይኖራል የሚለው ከክርስትና ራቅ ያለ መሰለኝ😁😁

ምንም ሆነ ምን ግን ከምን አንጻር እንደተጠቀሙት እናያለን እንጂ እንዲሁ ቃላት እየመዘዝን የራሳችንን አስተምህሮ ማለትም አሁንም ጌታ በአብ ፊት እየተማጸነ ነው የሚል ትምህርት መመስረት ከባድ ይመስለኛል..

- በፕሮቴስታንቶቹ እንኳን ለምሳሌ እነ ካልቪን የኢየሱስን ምልጃ ሲያስረዱ በመስቀል ላይ ሞቶ ከዚያም መነሳቱን እንጂ አሁን ላይ ይለምናል ማለት አይደለም እያሉ ነው..(commentary on romans 8:34)

- በካቶሊካውያን ዘንድም የምልጃን አሳብ ሲያብራሩ የጌታ መካከለኛነት እንደሆነና በመስቀሉ ሥራ የተከናወነ እንደሆነ ሲያስሰቀምጡ የቅዱሳንን ግን ጸሎት ልመና ብለው ይለዩታል(catholic encyclopedia, intercession(mediation)

ኢየሱስ በሰማይ ይለምናል የሚለው ቃል የቤተ ክርስቲያን ልምድም እንዳልሆነ ይናገራሉ(George haydock, comm. On romans)

- በግብጽም እነ አቡነ ሺኖዳ የጌታችንን አስታራቂነት ሲያብራሩ ከመስቀሉ ሥራ አንጻር ያደርጉትና ጸሎት ልመናን ግን ለይተው ለቅዱሳን ይሰጣሉ..(comparative theology, on intercession)

- የኛ ሃገር ሊቃውንትም ይማልዳል የሚለውን ሲያብራሩ በእለተ አርብ በመስቀል ላይ በሠራው ሥራ ለዘላለም ስለሚያስታርቅበት እንደሆነ ነው የሚያስቀምጡት(የሮሜም የዕብራውያንም አንድምታ ትርጓሜ)

@Apostolic_Answers
ከብዙ ማመንታት በኋላ የተጻፈ ነው.. ያው አስቸጋሪ ነገሮችን እያስተዋልን ስለሆነ..

አንድ ወንድ በተለይ መንፈሳዊ ነገር ላይ በአደባባይ እየተሳተፈ.. ግን ደግሞ ለአንቺ በውስጥ ሲያወራሽ:- “ያው እኔ እንኳን እንደው ከጠቀመ በሚለው ላገልግል ብዬ እንጂ የራሴ ላይፍ ደግሞ አለኝ እና በዛ ላይፌ ደግሞ በጣም ደካማ ነኝ.. የተወሰነ እጠጣለሁ ምናምን..” ብሎ ጀምሮ በሆነ መልኩ ከአንቺ ጋር ለመውጣት መንገድ ካመቻቸ.. በወሬ ውስጥ sexual ነገርን እንድታስቢ ካደረገ.. ወይም ደግሞ መንፈሳዊ ሰው ነው ብለሽም ራስሽም አፕሮች አድርገሽው ግን እሱ ወደ መጠጥና ዝሙት ካሻገረሽ..

እመኚኝ ይህ ወንድም ዘማ ነው። እና በርካታ እህቶች ላይ ነው እንዲህ የሚሆነው ማለት ነው.. ያው አንቺም እንደዛው ረከስ ያልሽ ከሆንሽ ሂጂበት.. የእግዚአብሔር ሴት ልጆች ግን እንዲህ ካለው የክርስቶስ ጠላት ራሳችሁን ጠብቁ.. ራሱንም ገድሎ እናንተንም ይገድላችኋልና.. ክርስቶስን እንዳትናፍቁት ተስፋችሁንም ጭምር ያጨልመዋልና..

በጣም እንደው ውስጤን ስለሚረብሸው የጻፍኩት ነው.. እኔ ደግሞ የሃገር ድክመቶች ያሉብኝ ሰው ስሆን እንዲህ መናገሬ ትእቢት እንዳይሆንብኝ ጌታ ይጠብቀኝ..

ለ3 ደቂቃ የሚቆይ
አንድ ሰው እንዲህ ሲል ሰማሁ..

“ጸሎት በግእዝ ሲሆን ይሰምራል ከአማርኛ ይልቅ.. ያው እንደ እውቀታችን በአማርኛ ስንጸልይም ቢሰማንም እንኳን ግን የአማርኛው የሰፈር ቃላት ይሆንብናል”

ኧረ አምላካችን በአማርኛ መሆኑ ብቻ ሳይሆን በአማርኛ ሆኖ እየተንተባተብን እንኳን ከልባችን ብንጸልይ ከግእዙ ባላነሰ መልኩ የሚቀበል ጌታ ነው.. በግእዝ ስለጸለይክ ብቻ ምንም የተለየ ነገር አትፈጥርም.. ከልብህ በንጽሕና ስትጸልይ ግን በየትኛው ቋንቋ ቢሆን ጆርውን ያዘነብልልሃል.. ስለዚህ ለጸሎት የሚያስፈልገው ልብ እንጂ ቋንቋ አይደለም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የምርም እንዳለውም ልጅ ኖሮት ከሆነ አሳዛኝ ነው.. ሰው ዲያቆን ሆኖ ሳያገባ ልጅ ሊኖረው አይገባም ጸያፍ ነው..

ግን ደግሞ ሊኖረው አይችልም ማለት አይደለም በስህተት ወድቆ እንዲህ ያለ ነገር ሊፈጠር ይችል ይሆናል..

ግን ደግሞ ይህንን ነውሩንና እርኩሰቱን ለመደበቅ ግን “ዲያቆን እያለሁ ጨለማ ውስጥ ስለነበርኩ ነው” ማለት በጣም አደገኛ ነው..
አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ እንዳረፈ ሰማሁ እና ሰው ነንና መቼስ በጣም ያሳዝናል.. ጌታችን እንኳን አላዛር ሲያንቀላፋ አልቅሶ ነበር..

ያው በእርግጥ ወደ ጌታ ነው የሄደው.. ጌታ ምህረት እንደሚያደርግለትና ከእርሱ ጋር እንደሚያኖረውም አምናለሁ.. ስለዚህም እርሱ በዚህ ሰዓት ውስጥ በማይነገር ደስታ ውስጥ ነው..

አያችሁ የኔ ተወዳጆች በሕይወትም ብንኖር ብንሞትም ከጌታ ጋር ነን.. ይልቁን ደግሞ ስንሞት የበለጠ ወደ እርሱ እንሄዳለን.. ስለዚህም በጌታ ሆነን ስናንቀላፋ ለኛ ጥቅም ነው.. ጳውሎስ እንዲህ ይላል:

“ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነው።” [ፊል 1:21]

የኛ ተራም በፊታችን አለና ጌታ ኢየሱስን በሕይወታችን እናክብረው..

ኪሪዬ ኤሌይሶን - ጌታ ሆይ ማረን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በመጽሐፈ ዚቅ በስህተት የገባ ነገር መኖሩን በመግለጽ አባታችን እንዲህ ይላሉ:-

ያው ስህተት ሲገኝ አባቶቻችንም እንዴት እንደሚናገሩበት ማወቅ ለምትፈልጉ ሰዎች ይሁን
አንድ ኦርቶዶክስ ከፕሮቴስታንት ጋር ሆኖ ሙስሊሞችን ሊከራከር ይገባልን..??

እሺ ጥቂት ሰዎች የጠቀየቁኝ ጥያቄ ስለሆነ ቀለል አድርጌ ግላዊ ምልከታዬን ላስቀምጥ..

እኔ ያው ሁሌም ቢሆን በራስ መሥራትን ነው ምመርጠው.. ግን ደግሞ እንደው አጋጣሚው ከተፈጠረም ይህ ነገር ሊከሰት የሚችለው ፕሮቴስታንቱ የኔን ቤተ ክርስቲያን የማይጠላና ባገኘው አጋጣሚ የማይሰድባት ከሆነ.. እንዲሁም የጌታ ቤተ ክርስቲያን መሆኗን ካመነ.. በአጠቃላይ በጣም ጥሩ ነገር ለቤተ ክርስቲያን ካየሁበት ብቻ..

ከዛ ውጪ ግን የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቤተ ክርስቲያኔን ሲሳደብ የሚውል ከሆነ ግን በፍጹም አላደርገውም.. ክርስቶስና ቤተ ክርስቲያን(ንጉሡ እና መንግሥቲቱ) ይቀድማሉ

ለ3 ደቂቃ የሚቆይ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሙስሊም ባሎች ሚስቶቻችሁን ከነዚህ ሰዎች ላይቭ አርቁ ፕሊስ..

ለምሳሌ የዚህ ሰውዬ ሚስት ከነዚህ ሰዎች ላይቭ ሰምታ ጥያቄ አብዝታ ልትፈታው ነው.. ልብ አርጉ እንግዲህ ያ ጀማ..

ለ4 ደቂቃ የሚቆይ ፖስት😁😁
"ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ" የሚለው የፕሮቴስታንቶች አሳብ አነሳሱ ያው ከቅዱሳን አንጻር አልነበረም.. እርግጥ ነው እርሱንም ሊያጠቃልል ቢችልም እንኳን ማለት ነው.. የመጀመሪያው የፕሮቴስታንቶች አሳብ እንዲህ ነው..

ሰው በኃጢአት ምክንያት ሞቷል ነጻ ፈቃዱንም አጥቷል.. ስለዚህም ሰው ለመዳን መፍቀድ እንኳን አይችልምና በፈቃዳችን ሳይሆን የምንድነው በእግዚአብሔር ቅድመ ውሳኔ መሠረት በጸጋው ብቻ በክርስቶስ ሥራ ነው.. ስለዚህም ከእኛ የሆነ ምንም ነገር የለምና ፈቃድ እና እምነትን ጨምሮ ማለት ነው.. ስለዚህም ክብሩን ሁሉ እግዚአብሔር ይውሰድ.. ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ ይሉናል።

እኔኮ የሚገርመኝ ነገር ፊት ለፊት ላይ ሲታይ ቃሉ ምናምን ውብ ነው "ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ" ሲባል.. ቀረብ ብላችሁ ስትፈትሹት ግን ብዙ ምንፍቅናዎችን አዝሎ ደግሞ ታገኙታላችሁ.. ለምሳሌ ብዙ ጴንጤዎችም ከላይ ያለውን ዓይነት የቅድመ ውሳኔ ትምህርት አይቀበሉም ግን ደግሞ "ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ" አመጣጡ ከዛ ነው።

መልካም የጌታ ቀን
ብዙ ፕሮቴስታንቶች(እናቅባለን የሚሉትም) ጋር የሚታየው አስቸጋሪው ነገር እነርሱ ካሉበት ዲኖሚኔሽን ውጪ ያለውን ነገር ብዙም ስለማያውቁት የሆነ ነገር በተነገረ ቁጥር ያልተገባ ነገርን መመለስ ይጀምራሉ..

ከበፊት ጀምሮ እንደምታስታውሱት ሉተራን ምስጢራት ላይ ያላቸውን አቋም አንስተን ስናስረዳቸው ጭራሽ ሉተር ምስጢራትን ለድኅነት ነው ብሎ አያምንም ብለው መጥተው ሲከራከሩ ታስታውሳላችሁ.. አሁን ላይ ገብቷቸው አርፈው ተቀምጠዋል.. አሁን ደግሞ "ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ" የሚለው ትምህርት እና "ጸጋ ብቻ" የሚለው ትምህርት ምን ያህል እርስ በእርሱ የተያያዘ እንደሆነና "ጸጋ ብቻ" ከሚለው ትምህርት የተነሳ እንደሆነም አያውቁምና እንደለመዱት ለጊዜው ይቃወማሉ.. ከዚያም ላይቭ ገብተን በደንብ ስንሄድበት አርፈው ይቀመጣሉ ማለት ነው..

እኛ በድኅነታችን ውስጥ እኛም ክብር ይገባን አላልንም.. ታድያ ግን "ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ" የሚለው የፕሮቴስታንቱ እሳቤ ሲያዩት መልካም ቢመስልም ቀረብ ብላችሁ ስታዩት ግን ምንፍቅናን አዝሏል ነው.. ምንፍቅናውም "ጸጋ ብቻ" የሚለው የሐዳሲያኑ ትምህርት ነው።

ድኅነትን ሙሉ በሙሉ የተቀበልነው አዎ ከእግዚአብሔር ነው በእኛ ሥራ አይደለም.. ግን ደግሞ ቢያንስ ፈቅደን ነው የዳንነው.. ድኅነቱን ለመቀበል ቢያንስ ፈቅደን "እጃችንን ዘርግተናል"😁 በጸጋ ብቻ ትምህርት ግን active will(በመቀበል እንኳን ሊተባበር የሚችል ፈቃድ) የለህም.. ወዳጄ ውስጡ ያለው የስህተት ብዛት ትልቅ ነውና እንደው ብትተወው ብዙም ያላነበብክበትን ነገር።

ባይሆን እኛ እንደ አስፈላጊነቱ ላይቭ ላይ እንሄድበታለን😁😁 ለ10 ደቂቃ የሚቆይ ፖስት
ዶግማችን የቤተክርስቲያን አባቶች ትምህርት ይሁን!

ከሰሞኑ በቤተክርስቲያናችን በሰዉ ልብ ዘንድ የተሳለ አንድ ነገር አለ እርሱም ዶግማችን ከፕሮቴስታንቶች መለየት ማስመሰል ነው። ማለትም ወደ ፕሮቴስታንት የቀረበ የመሰለን ማንኛውም ትምህርት ዶግማ እስኪመስል ድረስ ማውገዝ እንዲሁም ከእነርሱ ትምህርት ለመራቅ ተብሎ አባታዊውን ትምህርት እስከ መካድ መድረስ።

ለምሳሌ የሰሞኑን ጳጳሳት ጉዳይ ብናይ "ማርያም ቤዛ አትባልም" ያሉትን ጳጳስ ከጫፍ እስከ ጫፍ ተቃውሞ ነው የተሰማው ምክንያቱም ቤዛ አትባልም የሚሉት ፕሮቴስታንቶች ናቸው። ነገር ግን በተቃራኒው "የምንቀበለው የማርያም ሥጋ ነው" ያሉትን ጳጳስ የተቃወሙ ቢኖሩም ተቃውሞው ግን አልበረታም ለምን "ፕሮቴስታንቶች የማርያምን ሥጋ ነው ምንቀበለው ስለማይሉ" እውነት ለመናገር ፕሮቴስታንቶች እንዲህ ያለ ትምህርት ቢኖራቸው ኖሮ ከጫፍ እስከ ጫፍ ተቃውሞ እንሰማ ነበር። ይገባኛል በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ገብተን ፕሮቴስታንታዊ ትምህርት የሚያስተምሩ ተዋሕዶሶች ስለነበሩ የትኛውም ፕሮቴስታንታዊ የሚመስል ትምህርት ሲሆን ስጋት ይደቀንብናል ነገር ግን የአስተምህሮዋችን ማእከል የአባቶች ትምህርት እንጂ ፕሮቴስታንትን መቃወም ማድረግ የለብንም።

የክርስቶስ ምልጃ ጉዳይ ላይም ተመሳሳይ ነገር ነው የማየው ስለ ክርስቶስ ምልጃ ፕሮቴስታንቶች ስለሚያስተምሩ ከተሐድሶዎች ጋርም በዚህ ጉዳይ የክርክር ጠባሳ ስለነበር የትኛውም የክርስቶስን ምልጃ ያጎላ ትምህርት ስናይ ፕሮቴስታንታዊ ይመስለናል ነገር ግን የራሳችን የቤተክርስቲያን አባቶችም ሆኑ የአምልኮ መጻሕፍቶቻችን በክርስቶስ ምልጃ ትምህርት የተሞሉ መሆናችንን አንዘንጋ የክርስቶስ ምልጃ ትምህርት ኦርቶዶክሳዊ እንጂ ፕሮቴስታንታዊ አይደለም እንዳውም ከማንም ይልቅ ለእኛ የተገባ ነው አንድ ጊዜ በቀረበው መሥዋዕት በቁርባን አማካኝነት እንቀበለዋለንና ፕሮቴስታንቶች ግን ቁርባን የኃጢአት ይቅርታ የሚሰጥ የዕለተ አርቡ መሥዋዕት ነው ብለው ስለማያምኑ ለማስረዳት ይከብዳቸዋል።

እኔ ግን የመጨረሻ ነገር ልበላችሁ ለትምህርት ማንጸሪያዬ የቤተክርስቲያን አባቶች ናቸው እንጂ ፕሮቴስታንቶችን መቃወም አይደለም። ስለዚህ የቤተክርስቲያን አባቶች ያስተማሩትን በልበ ሙሉነት እኔም እናገረዋለሁ።
በአብ ቀኝ ያለ ጠበቃ

ብዙ ሰው ኢየሱስ በመስቀል ላይ ለኃጢአታችን ማስተሠርያ ከሆነ በኋላ በአብ ቀኝ ለፍርድ የተቀመጠ ዳኛ ኃጢአት ስንሠራ ለምን ሠራችሁ ብሎ የሚቆጣ ፈራጅ አድርገን እንስለዋለን ስለዚህም ኢየሱስ ተቆጪ አምላክ ስለሆነ ርኅርኅተ ህሊና በሆነችው በእመቤታችን በኩል እናገኘዋለን እሱ ፈራጅ እርሷ ግን ሩኅሩኅ አድርጎ መሳል አለ።

ነገር ግን አንድ ነገር አስታውሱ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ባለ ፍቅሩ አሁንም በአብ ቀኝ አለ ፤ በመስቀል ላይ ለኃጢአታችን ማስተሠርያ እንደሆነው አሁንሞ በአብ ቀኝ ለኃጢአታችን ማስተሠርያ ነው ለኃጢአታችን ብቻ አይደለም ለዓለም ሁሉ ኃጢአት እንጂ። ኢየሱስ በአብ ቀኝ የተቀመጠው ኃጢአት በሠራን ቁጥር ለምን ብሎ የሚቆጣን ፈራጅ ሳይሆን አንዴ ባቀረበው ምልጃ የሚያስታርቀን አስታራቂ ነው በገዛ በደሙ ወደ ሰማያት ገብቷልና! ነገር ግን የኃጢአታችን ጠበቃ በሰማያት አለ ብለን ኃጢአትን የመሥራት ነጻነት የምናገኝ አይደለም ይልቅስ በአብ ቀኝ ያለውን ጌታችንን ለመምሰል በቅድስና ሕይወት እንመላለሳለን እንጂ ደካሞች ነንና ብንወድቅም በደሙ እንነጻለን።

በእመቤታችን በኩል ወደ ጌታ መቅረብ መልካም ነው ነገር ግን ጌታን ተቆጪ አደርጎ በመሳል አይደለም "በእርሱም ዘንድ ባለ እምነታችን በኩል በመታመን ድፍረትና መግባት በእርሱ አለንና። (ኤፌ 3:12)

በመስቀሉ ላይ በታላቅ መቃተት ምልጃን በማቅረብ የወደደን ጌታ አሁንም በዚሁ ፍቅሩ በአብ ቀኝ አለ ስለዚህም ስለእኛ ይማልድልናል ፤ ከአቤል ደም ይልቅ የሚጮህ ደም ❤️

@KidanZeIyesus
በቤታችን ያለን anti-intellectualism አካሔድ ግድ ማጥራት አለብን ወገን። ማኅበረ ቅዱሳን ላይ መጽሐፍ ቅዱስ 81 ወይስ 66 በሚል ርእስ የተለቀቀ ቪዲዮ እያየሁ ተሳቅቄ ልሞት።

1. መጽሐፍ ቅዱስ 81 አድርገው የወሰኑልን በ3ተኛው ክፍለ ዘመን የነበሩ ሠለስቱ ምእት ናቸው ይላል። እኛ ግን የተገኘውን ነገር ሁሉ ያለ ጥናት ሠለስቱ ምእት ላይ ለምን እንደምናሳብብ ይገርመኛል። አንደኛ ሠለስቱ ምእት በ3ተኛው ሳይሆን በ4ተኛው ክፍለ ዘመን ነበሩ (ይህ እንኳን understandable ስህተት ነው 325 ዓ.ም ሲባል ብዙ ሰው 3ተኛው ክፍለ ዘመን ይመስለዋል) ሌላው የሚያሳቅቀው ነገር ግን 318ቱ ሊቃውንት በኒቅያ ጉባኤ የመጻሕፍትን ቁጥር የወሰኑበት ምንም አይነት ሒደት አለመኖሩ ነው። የመጻሕፍትን ቁጥር የወሰኑ ጉባኤያት ላይ ሠለስቱ ምእት ተሳትፈው አያውቁም ይልቅስ ከኒቅያ ጉባኤ በኋላ የተደረጉት የለዶቅያ ፣ የሂፖ ፣ የቅርጣግናና የሮም ጉባኤያት ናቸው የመጻሕፍትን ቁጥር የወሰኑት ነገር ግን እነዚህ ጉባኤያት 81 የመጻሕፍት ቁጥር አልወሰኑም ይልቅስ 73 መጻሕፍትን የወሰነ ጉባኤ አለ።

2. የዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ጠፍቶ ነበር ነበር ከዛ ዮሐንስ አፈወርቅ በጸሎት ተገልጦለት ዮሐንስ አፈረወርቅ ነው የመጨረሻውን "በዚህ ትንቢት መጽሐፍ የጨመረ ወይም የቀነሰ" የሚለውን አረፍተ ነገር የጻፈው ይለናል። ይህም በምንም አይነት የታሪክ ጥናት ላይ ያልተመሠረተ መላ ምት ብቻ ነው።

3. 81 መጽሐፍ ከየት መጣ የሚለውን ሲያስረዳ የዮሐንስ ወንጌል 2፡20 ላይ "ስለዚህ አይሁድ። ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፥ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን? አሉት።" የሚለውን ጥቅሶ 46 የሚለው ቁጥር 46ቱን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ያሳያል ስለዚህ እዚህ ጋር ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት 46 መሆናቸውን እየነገረን ነው ይላል። እዚህ ጋር ይገባኛል allegory or metaphor እየተጠቀምን አስተምህሯችንን ልናሳይ እንችላለን ነገር ግን allegory እንደ ማስረጃ አይቀርብም ሲጀመርም ያንን connection የሠራው ሰው መጀመሪያውኑ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት 46 መሆናቸውን ካመነ በኋላ ነው እንጂ ለማመን አይደለምና።

4. 81 መጻሕፍትን ለማሳየት የቃኤልን ሚስት ጥቅሶ ሚስቱ ማን እንደ ሆነች የሚነግረን መጽሐፈ ኩፋሌ ነው ስለዚህ 81 ትክክል ነው ይላል። ይህ ደግሞ በጣም የሚያሳቅቅ አካሔድ ነው commentary ራሱ አያስፈልገውም ነገር ግን የቃኤልን ሚስት ማን እንደሆነች ለማወቅ ቢያስፈልግ እንኳን የቃኤል ሚስት ማን እንደሆነች የሚነግረን መጽሐፍ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ ሊሆን ነው ማለት ነው? እንደዛ ከሆነ የአይሁድ ሥራዎች መካከል ሴዴር ሃዶሮት የተባለው መጽሐፍ የቃኤል ሚስት ካልማና እንደምትባል ይነግረናል ለምን መጽሐፍ ቅዱስ አይሆንም ታድያ? እንዲሁም በዚህ ሎጂክ ትክክል ቢሆን ራሱ መጽሐፈ ኩፋሌን ትክክል ያደርገዋል እንጂ 81 መጻሕፍትን አያሳይም።

5. ሌሎችም እንዲሁ አንድ አንድ መጻሕፍትን የሚያሳዩ ከመጽሐፍ ቅዱ ተጠቅሰዋል ለጊዜው እነርሱን ልተዋቸውና የመጨረሻው ሃሳብ ላይ ላተኩር "81ዱን መጽሐፍ ባልቀበል በነፍስ ያስጠይቃል ወይ?" የሚለውን ጥያቄ ሲመልስ ያስጠይቃል እንጂ በሐዋርያት መሠረትነት ላይ ታንጻችኋል ይላል ስለዚህ የሐዋርያትን አስተምህሮ ያልተቀበለ ጌታ አልተቀበለም ማለት ነው በማለት ይመልሳል። Interviewወሯ የቁጥሩን ጉዳይ ነው ብላ clear ለማድረግ ብትሞክርም መልሶ አዎ ቁጥሩም የሐዋርያት አስተምህሮ ነው በማለት ይመልሳል። ይህኛው ደግሞ ከሁሉም አደገኛ ሃሳብ ነው የመጀመሪያ "81" የሚለውን የመጻሕፍት ቁጥር ከሐዋርያት አስተምህሮ (Deposit of Faith) ውስጥ አስገብቶታል ይህ ደግሞ መሠረት አልባ ነው deposit of faith ውስጥ ለመግባት መጀመሪያ በሁል ጊዜ ፣ በሁሉም ቦታ ፣ በሁሉም አባቶች የሚታመን መሆኑን ማሳየት ግድ ይላል ነገር ግን እንደማያሟላ ግልጽ ነው ለምሳሌ 81 የመጻሕፍት ቁጥር ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ተቀባይነት እንደነበረው ማሳየት ይቻላል? ይቻላል ከተባለ burden of proof አለበት ነገር ግን ሙሉ ትምህርቱ ላይ ማሳየት አልቻለም ፣ ሁለተኛ በሁሉ ቦታ የሚታመን መሆኑን ማሳየት ያስፈልጋል ይህ ደግሞ ወዲያው ይፈርሳል ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ውጪ አይታመንምና ፣ ሦስተኛ ደግሞ በሁሉም አባቶች የሚታመን መሆኑን ማሳየት ያስፈልጋል ነገር ግን ይህንንም እንደማያሟላ ለማሳየት ብዙ መልፋት አያስፈልግም። ደግሞ የዚህኛው አቋም ትልቁ ችግር የመጻሕፍት ቁጥር 81 መሆናቸውን ማመን የመዳን ጉዳይ አድርጎታል ስለዚህ ከኢትዮያና ከኤርትራ ውጪ ያሉ አማኞች በነፍሳቸው ይጠየቁበታል ማለት ነው።

የዚህ ትችት ዓላማ ለምናምናቸው አስተምህሮዎች የተሻሉና በታሪክ ጥናት ላይ የተመሠረቱ ሙግቶችን እንድናመጣ ነው።
አስበኸዋል አንድ ሰው የደሃን ገንዘብ እየበዘበዘ አልያም በዝሙት ኃጢአት ውስጥ እየኖረ ግን ደግሞ ግጥሙ ጤናማ የሆነ ዘፈንን ኃጢአት ነው ሲል..??

እውነቱን ለመናገር እኔ ዘፈን አዳማጭ አይደለሁም.. የሚያዳምጡ ክርስቲያኖችም እንደው ቀስ በቀስም ቢሆን እየተዉት ቢሄዱ ብዬ የማስብ ሰው ነኝ.. ታድያ ግን ዘፈን ባለመስማቱ እንደሚመጻደቅ ሰው ሰነፍ ያለም አይመስለኝም በስመአብ.. ከዛ ደግሞ ጭራሽ የሚሰሙትንም ሊኮንን ይወዳል እንጂ..

ብዙ የተወደዱ ፕሮቴስታንቶች አሉ ግን ደግሞ በዛው ልክ የፈሪሳውያኑ አበዛዛቸው😁😁 በውጩ ዓለም እኮ አይከለከልም በፕሮቴስታንቱም.. ጭራሽ ማርቲን ሉተር የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው ብሎ ነው የሚያምነው ዘፈንን..

ለ10 ደቂቃ የሚቆይ
አይ የፈሪሳውያን ጠባይ ያለባቸው ሰዎች አሉ.. ቀላሉን ነገር እንደ ከባድ ኃጢአት አድርገው ያጮሁታል.. እነርሱ ግብ ምሰሶውን ተሸክመውታል.. እና ይህ ፈሪሳዊነቱ ያስጠላል..

በውጩም ዓለማት በኦርቶዶክስም ጭምር ዘፈን ከግጥሙ አንጻር የሚታይ ነገር ነው.. ግን ደግሞ ወደ መዝሙር ነው ማዘንበል ያለብን ነው.. በዓለም ፍቅር ተነድፈን እንዳንኖር
ዘፈን ኖርማል ነው ብለን ሳይሆን አንተ ስታነበው እንደዛ አንብበኸው ነው ሙሌ.. እስቲ መነጽሯን አውልቀህ ሞክራት ሎል

አይ ግን ያው ጤናማ ግጥም ያለው ዘፈን በራሱ ኃጢአት አይደለም..ግን ደግሞ የዓለምን ፍቅር በውስጥ ሊያሳድር ስለሚችል መዝሙር ነው መስማት ያለብን.. ዓለምን መውደድ ከእግዚአብሔር ጋር ጥል ነውና
አንድ ፕሮቴስታንት ወንድም እንዲህ ሲል ይተቻል..

[ ክርስቲያኖች ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ውስጥ ዘፈን አትሰሙም.. ከዚያ ስትወጡ ግን የምትሰሙ ከሆነ እንግዲያውስ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሆናችሁት በትርፍ ሰዓታችሁ ነው(ቤተ ክርስቲያን ስትሄዱ ብቻ) ]

ይሄ ወንድም የምር በተገኘበት መሸለም አለበት.. እንዲህ ያለ ብሩህ እና ታላቅ የማሰላሰል ብቃት ያለው አእምሮን ይዞ በቲክቶክ ብቻ መገደብ የለበትም.. ዓለም ላይ ላሉ ብዙ ችግሮች መፍትሄ ማምጣት የሚችል ዓይነት ሰው እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ..

እናንተ ደግሞ “ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሙቪ አናይም ስንወጣ ግን እናያለን..” እንዳትሉ ቆይ😁😁
ዛሬ የምር በጣም አሳዛኝ ነገር ነው የሰማሁት ለነገሩ ዛሬ ብቻ አይደለም ብዙ ጊዜ በውስጥ የሚመጡልኝ መልእክቶች በክርስትና በጣም እንደሚቀረን ነው እየተረዳሁ ያለሁት ፤ ክርስትናን ሳይሆን እየኖርን ያለነው ይሁዲነትን ነው ያስብላል አንዳንዴ።

ለምሳሌ ከሰማሁት ልንገራቹ አንዲት ሴት ገና teenager እያለች ትደፈራለች በኋላ ስታድግ በቤተክርስቲያን ውስጥ በተክሊል ማግባት አትችዪም ትባላለች ፤ እንዲሁም ዲያቆን ድንግል ስለሆነ ማግባት ያለበት ከአንድ ዲያቆን ጋር ቢዋደዱ እንኳን መጋባት አትችሉም ይባላሉ።

Really? አሁን ክርስቶስ ቢወርድ ኖሮ ፈሪሳዊያንን እንደ ወቀሰ አይወቅሰንም? ቆይ ተክሊል ድንግልናን እስከ ትዳር ለጠበቁ ሽልማት ነው አልተባለም እንዴ ታድያ የተደፈረች ሴት ምን አጥፍታ ሽልማቷ ይቀርባታል? ቆይ ድንግልናን የምንመለከተው ከሥጋ አንጻር ብቻ ነው እንዴ? እንደሱ ከሆነማ ብዙ ሴቶች በተፈጥሮም ሆነ በከባድ ሥራ የማይኖራቸው አለ እነርሱስ ሊከለከሉ ነው?

በአንዲት ሴት ላይ እኮ መደፈር ከባድ የሆነ አካላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ ጉዳት ነው የሚያደርሰው ፤ አንድ አንድ ሴቶች ጭራሽ ወንድ የተባለ ፍጡርን የሚጠሉ አሉ ፤ ራሳቸውን እንደ ረከሱ ያያሉ ፣ እንዲሁም long lasting trauma ነው የሚከተላቸው ፣ ጭራሽ የእኛ ማኅበረሰብ ደግሞ የራሳቸው ጥፋት እንደሆነ አድርገው ነው ጣታቸውን ወደ ተጠቂዎቹ ሴቶች የሚጠቁሙት።

ታድያ ቤተክርስቲያን በዚህ ጊዜ ማረፊያ መሆን ሲገፋት ጭራሽ ቤተክርስቲያንም ስታገል ምኑን ከማኅበረሰቡ ተለየች? ምኑን የክርስቶስ ልብ ኖራት? አስቡት ያለ ፈቃድሽ አንድ አረመኔ ጨካኝ ወንድ ስለ ተጫወተብሽ ረክሰሻል ተክሊል አይገባሽም ስትባል? ጭራሽ እኮ ዲያቆን ክህነቱ ንጹሕ ነው ታረክሺዋለሽ ካገባሽ ነው የተባለችው። I don't even have the words to describe my anger ብቻ ቤተክርስቲያናችን በጣም የተማሩ ንስሐ አባቶች እንደሚያስፈልጓት ነው የተረዳሁት በዚህ ታሪክ ብቻ ሳይሆን በብዙ ታሪኮች ፤ በተለይ ሴቶች እኅቶቻችን ላይ የሚደርሰው ግፍ ከባድ ነው። ጌታ ይታደገን ብቻ ምን ይባላል።

የሚጠፋ እንደዚህ አይነት ነገር ምናልባት ስለማልጽፍ