አንዋር መረጃ / Anwar Mereja
192 subscribers
47 photos
3 videos
1 file
28 links
🎤 አንዋር መረጃ / Anwar Mereja
ሙስሊሙን ኡማ በተመለከተ እውነትን መርሁ አድርጎ የሚሰራ የመረጃ አውታር ስራውን ጀምረ ።
ግንቦት 4/2015
قل الحق እውነትን ተናገር
Download Telegram
ذهب الضيوف وبقي الأهل
እንግዶች ሄዱ ቤተሰቦች ቀሩ
የእኛው መጅሊስ የሙስሊም ሴቶችን የአለባበስ ጉዳይ መፍታት ተስኖት ይህው እነሱ ከተቋም ተቋም እርቃናችንን ሁነን አንማርም በማለት ድምፃቸውን ለማሰማት እየተንከራተቱ ይገኛሉ ።

መጅሊሱ ግን ከቀን ቀን ጉዳዮችን የማስፈፀም አቅሙ እየተዳከመ እየተሟጠጠ አሁን በድድ ብቻ የቀረ ጥርስ ማብቀል ያልቻለ ተቋም ሁኖ እየቀጠለ ነው።

በብዙ መለኪያዎች መጅሊሱ ጠንካራ ተቋምነቱን እያጣ የመንግስት አሎሌ ሁኖ ሂድ ሲባል የሚሄድ ቁም ሲባል የሚቆም የተጠመዘዘ ነፃ ያልሆነ ተቋም ሁኖል።

የአሁኑ መጅሊስ ከሀጅ ውጭ ሌላ ስራ አለውን?
የወለጋ ሙስሊሞች

ባለፈው እሁድ በተካሄደው ደማቅ እና ህዝበ ሙስሊሙ ለዲኑ ያለው ጥልቅ ፍቅር ለቁረአን ያለው ከፍተኛ ውዴታ አዋቂ ወጣት ሳይል በሴቱም በወንድም በኩል በገፍ በመውጣት ቁረአንን አልቋል የከፍታ ማማላይ አስቀምጧል የክብር እንግዶችንና መሪዎቹን በሰላም ሸኝቶ ወደ ቤቱ በሰላም ተመልሷል።
🥰1
ኢትዮጲያ 'ትግራይ' የአክሱም ሙስሊሞች

ፍትህ ፍትህን በማለት ዘመናት ተሻግሯል የመንግስታት ለውጥ ቢኖርም የሙስሊሙን ሙሉ መብት ለመተግበር ግን የእምነት አጫጥር ፖለቲካ ህዝበ ሙስሊሙን ለተሟላ መብት ሳይታደል ጊዚያቶች አሁንም እየነጎዱ ይገኛሉ።
ሸዋል 4 ቀን ቀርቶታል።
ሀንዞለቱ ቢን አረቢእ አልተሚሚ

ከነብያችን ሙሃመድ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ወህይ ከሚፅፉላቸው አንጋፋ ፀሃፊዎች መካከል ማለትም ከእነ ዘይድ ቢን ሳቢት: ከአልይ ቢን አቢጧሊብ ከእነ ኡስማን ቢን አፋን እንዲሁም ሙአውያ ቢን አቢሱፍያን ከመሳሰሉ ታላላቅ ሱሃቦች መካከል ይጠቀሳል።
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
ቁርአንን ከመፃፍ በተጨማሪ የዘካን ገንዘብ የተለያዩ ሶደቃዎች ጭምር በመዝገብ እንዲያዝ በማድረግ ለሚከፋፈሉ ሰዎች በአግባቡ እንዲደርስ ያደርግ ነበር።
ቀድመው እስልምናን ከተቀበሉት መካከልም ሲሆን ነብያችን ሙሃመድ ሶለሏሁ አልይሂ ወሰለም የእስልምናን መልዕክት ወደ መላው አለም /ለንግስታቶች መልእክትን እንዲፅፍ ያደርጉትም ነበር።
ከወህይ ፀሀፊዎች መካከል በማይገኙ እለት ምትክ ሁኖ ክፍተቱን በመሸፈን ፀሀፊ ሁኖም ያገለግላል። ፀሀፊው ሀንዞላህ ተብሎም ይጠራ ነበር።


ነብያችን ሙሃመድ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም በታማኝነቱ:በፍትሀዊነቱ እንዲሁም በአሏህ ያለው ፍራቻ አማካኝነት ለአምባሳደርነት(ልኡኩንት) ጭምር ይመርጡት ነበር :ማህተማቸውን ሳይቀር ሰጠውታል።
በአንዳድ መዛግብ እንዲህም ይሉት እንደነበር ተገልፆል።
*الزمني واذكر كل شيء أنافيه) .‏
 
ከእኔ ጋር ቆይ :እኔ ያለሁበትን ሁሉ ፃፍ(መዝግብ) ተብሎ ተገልፆል።
🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙
የመካ መከፈት ጊዜ በጦርነቱ ምክንያት በመካ አካባቢ የተገደለችን ሴት ተመለከቱ ሀንዞላንም ጠርተው ወደ ጦር መሪው ኻሊድ ቢን ወሊድ ህፃናትንና ሴቶችን እንዳይገደል  መልእክት ልከውት ነበር።

ከመካ ቀጥሎ ወደ ጧኢፍ ሲሄዱ ከ ከተማው አቅራቢያ ከሶሃቦቻቸው ጋር ካምፕ መስርተው ነበር ።
ወደ ጧኢፍ ሰዎች የሰላም ስምምነት ያደርግ ዘንድ ሀንዞላን ይልኩታ ሀንዞላም እንደደረሰ አግተው ሊገድሉት ፈለጉ በእዚህን ጊዜ ሀንዞላን ማን ነፃ ያወጣል ብለው ለባልደረቦቻቸው ጥያቄ ይጠይቃሉ በእዚህን ጊዚ አጎታቸው አባስ ቢን አብዱል ሙጦሊብ ጥያቄውን ተቀብለው ወደ ታገቱበት ቦታ(ምሽጋቸው) በፍጥንት በመሄድ ከጠላት እንጅ አስጥለው በመሄድ ላይ እያሉ ከሆላ ዲንጋይ ይወረውሩባቸው ነበር በእዚህ ነብያችን ሙሃመድ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም "እንደዚህ ያሉትን ተከተሉ:እንደ እርሱ ያሉት" ያሉትን ብለው ታሪካዊ ንግግር ተናግረዎላቸዋል።
☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️
በአሏህ መንገድ ላይ በመታገል ግንባር ቀደም ጀግና ነበር በቃድስያ ዘመቻ በመሪነነት በጀግንነት ተዋግቷል።

ኡመር ቢን ኸጧብ ሰእድ ቢን አቢወቃስ ወደ ኢራቅ ፍርስን ለመጋፈጥ ልከውት ነበር።
ሱሃቦችንም በክፍል ክፍል ማለትም ለሰባት ክፍሎች እንዲከፍል በፅሁፍ አዘውት ነበር እያንዳዱ ክፍልም መሪ እንዲመድብ ጭምር ታዞ ነበር።
ሰእድም በታዘዘው መሰረት አደረገ
ሶስተኛውን ክፍል የተሚሚ አሰድ: የኸغጠፋን ና የሃዋዚን ጎሳዎችን ነበሩ ከመካከላቸው የተሚም ጎሳ የሆኑት ሀንዞለቱ ቢን ረቢእን መሪ አድርገው ሹመዋቸል።

በኸሊፋው ኡስማን ቢን አፋን ረዲየሏሁ አንህ  ጊዜ ኡስማንን የሚሰድቡ ሰዎችን በተመለከቱ ጊዜ እኔ ኡስማን ከሚሰደቡበት ሀገር አልኖርም በማለትና ፊትናን ለመራቅ ወደ አሁኗ ቱርክ ቆስጠንጠኒያ ሄዱ።
በአልይ ቢን አቢጧሊብ ረዲየሏሁ አንሁ የኸሊፋነት ጊዜ የግመል ቀን ጦርነት ላይም ሳይሳተፉ ቀሩ ።

በሙአውያ ቢን አቢሱፍያን ረዲየሏሁ አንሁ ኺላፋነት ዘመን ውስጥ በ52 አመተሂጅሪያ በቆስጠንጢንያ ጦርነት ሲሳተፍ ሸሂድ ሁነው ከእዚህ አለም በሞት ተለዩ ።
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴

ከእዚህ በታች ታዋቂ ሃዲሳቸውን በዝርዝር አቅርበነዋል።

يروى أنه مر (بأبي بكر) يوماً وهو يبكي فقال : (أبو بكر) مالك يا (حنظلة) فقال : نافق (حنظلة) يا (أبا بكر) نكون عند (رسول) الله صلى الله عليه وسلم يذكرنا (بالنار والجنة) كأنا رأي عين فإذا رجعنا (عافسنا) النساء والضيعة (يعني مداعبته أهله وعياله) .
❖ فقال : (أبو بكر) فو الله إنا لكذلك انطلق بنا إلى (رسول) الله صلىالله عليه وسلم فلما رآه (رسول) الله صلى الله عليه وسلم .
❖ قال : (مالك يا حنظلة) .
❖ قال : نافق (حنظلة) يا (رسول) الله نكون عندك تذكرنا (بالنار والجنة) كأنا رأي عين فإذا رجعنا (عافسنا الأزواج والضيعة) ونسينا كثيراً .
❖ فقال : (رسول) الله صلى الله عليه وسلم (لو تدومون على الحال التي تقومون بها من عندي لصافحتكم الملائكة في مجالسكم وفي طرقكم وعلى فرشكم) ولكن يا (حنظلة) ساعة وساعة)
አንድ ቀን አቡበክር ረ.ዐ በመንገድ ላይ እያለፍ ሀንዞላን እያለቀሰ አገኙት።
ምን አጋጠመህ ብለው ጠየቁት?
ሀንዞላም አለ : ሀንዞላ ሙናፊቅ ሁነ አቡበክር ሆይ ነብዩ ዘንድ ሁነን ስለ ጀነትና ጀሀነም ባስታዎሱ ን ጊዜ በአይናችን እንደምናየው እንሆናለን
ሰእሳቸው ተለይተን ወደ ቤተሰቦቻችን ስራችን በተመለስን እለት በስራችንና ከቤተሰባችን በምናደርገው ጨወታ እንረሳዋለን አላቸው።

በእዚህም ጊዜ አቡበክረርም ረ.ዐ በአሏህ ይሁንብኝ እኛም እነደዚሁነን ብለው ወደ ነብያች እንሂድ ብለው ተነሱ

ሀንዞላም የአሏህ መልእተኛ ሆይከአንቱ ጋር ሁነን በምታስታውሱን ጊዜ እንደምናየሁ ሁነን እንቆያልን ወደ ቤተሰቦቻችንና ስራዎቻችን ስንመለስ ብዙውን እንረሳለን አላቸው።

ነብያችንም ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ አሏቸው
"እናንተ ከእኔ ጋር በሆናችሁበት ሁኔታ ሁል ጊዜ ብትቆዩ ኑሮ መላዕክት በመቀመጫችሁ: በመንገዳችሁና በአልጋዎቻችሁ እየመጡ ይጨብጧችሁ ነበር ሀንዞላ ሆይ ሰአት ሰአት ማለትም ከፊሉን ጊዜ ለኢባዳ ከፊሉን ደግም ለአለማዊ ነገር አሉት"

اللهم صلي على محمد
4
ዛሬ ጁሙአ ነው
አንዱ እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ:

``ከሰው ሁሉ ደስተኛ ማነው?``

እሱም እንዲህ ሲል መለሰ

``ሰዎችን ደስተኛ የሚያደርግ ሰው።``
አሏህ ሶስት ነገራቶችን ውብ ብሎ ገልፆቸዋል።

❤️ውብ ትዕግስት
❤️ውብ መለየት
❤️ውብ ይቅርታ

ውብ ትዕግስት ማማረር የሌበት ማለት ነው።

ውብ መለየት ያለ ጉዳት መለየት ማለት ነው።

ውብ ይቅርታ ያለ ቅሬታ ይቅር ማለት ነው።

የቁርአን ምእራፎችን ከእነ አያ ትርጉማቸው በcomment box ላስቀመጠ የ50 ብር ካርድ ተሸላሚ ይሆናል።
ከአባታችን ነብዩሏህ ኢብራሂም ዱአዎች መካከል:
﴿وَاجْنُبْنِي وَبَنِيَّ أَنْ نَعْبُدَ الْأَصْنَامَ﴾
ጌታየ እኔንና ልጆቼን ጣኦት ከማምለክ ጠብቀን።
﴿هُمُ الْعَدُوُّ فَاحْذَرْهُمْ﴾
المنافقون
'' እነርሱ(ሙናፊቆች የኢስላምና የሙስሊሞች ) ጠላቶች ናቸው። ስለ ሆነም ተጠንቀቃቸው።'' አል-ሙናፊቁን
ከመስለሙ በፊት ቦክሰኛ የነበረው ሱሃባ
ሩካነህ ቢን አብዱየዚድ ቢን ሃሺም ቢን ሙጦሊብ አልቁረሺይ

* እጅግ ብርቱ ጉልበተኛ በጃሂልያ ጊዜ በመካ ሙሽሪኮች መካከል በጉልብቱ የሚመካ ማንም ጉልበተኛ ነኝ ባይ እሱን ማሸነፍ ያልቻለ ታዋቂ ቡጠኛ ከነብያችን ሙሃመድ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ጋር በዘር ሀረግ የሚገናኘው ሩካነህ ቢን አብዱየዚድ ጋር በአጭር ማስታወሻ ክፍል ሰድረናዋል።

ታሪኩ ነብያችን ነብይ ሁነው ከመላካቸው በፊት የተከሰተ ነው። ይለናል ሩካናህ ቢን አብዱየዚድ

"እኔና ነብዩ ሙሃመድ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም የአቡ ጧሊብ የበግ መንጋዎችን እየጠበቅን በነበርንበት ጊዜ እሳቸውንም ለመጀመሪያ ጊዜ ተዋወኳቸው።

አንድ ቀን እንዲህ ብለው ጠየቁኝ

ከእኔ ጋር ልትታገለኝ ትችላለህ?
እኔም አንተ አልኩት?

እርሳቸውም
አዎ እኔ አሉኝ

እኔም
በምን ውርርድ አልኳቸው?
እርሳቸውም
በአንዲት በግ

ከእዚያም ተጣላን አሸነፉኝ በጓንም ወሰዱ።

ለሁለተኛ ጊዜ ግብዣ አቀረቡልኝ
እኔም በድጋሚ ተቀበልኩ አሁንም አሸነፉኝ ሁለተኛዋንም በግ ወሰዱብኝ።

ከእዚያም ወደ ግራና ቀኝ ተመለክቱ ።

እሳቸውም ምን ሁነሃል አሉኝ?

አንድ አንድ እረኞች እንዳያዩኝ ብየ ነው እንዳይዳፈሩኝ ብየ መለስኩላቸው እኔም በሀገሬ እጅግ ብርቱ ነኝ።'

እርሳቸውም ለ3ተኛ ጊዜ ልትጣላኝ ትፈልጋለህ?አንተም አንዲት በግ ታገኛለህ አሉኝ።

እኔም አዎ አልኳቸው ።

ለሶስተኛ ጊዜ አሸነፉኝ ሌላም በግ ወሰዱብኝ።

እኔም ወደ አባቴ አብዱየዚድ ቤት ልሄድ ነው ።ሶስት በጎች ወሰድክብኝ ። እኔ ከቤተሰቦቼ ብርቱ ነኝ ብየ አስብ ነበር።

እርሳቸውም
ለ4ተኛ ጊዜ ትሞክራለህ አሉኝ?

እኔም
በቃኝ አልኩኝ

በጎችን እመልስልሃለሁ በለው መለሱልኝ።

ከእዚያም ብዙ ሳይቆይ ወህይ ይወርድላቸው ጀመረ እኔም ወደ እሳቸው በመሄድ እስልምናን ተቀብልኩ። ረዲየሏሁ አንሁ

ከእዚያ በስደት ወደ መዲና አቀና እዚም ለነብያችን ደጋፊና ተከላካይ በመሆን አገልግሎ እንዲሁም ትዳር መስርቶ የዚድ አብኑ ሩካናህ የተባለ ልጅ ወልዶ በሙአውያ አስተዳደር ጊዜ ነብያችን ከሞቱ ከ 31 አመት በሆላ በ42ተኛው አመት ሂጅርያ ከእዚህ አለም በሞት ተለየ።
ስራውን አሏህ ይቀበለው። አሚን
ከሁለት ቀናት በኋላ የሚገባው የተከበረው የዙልሂጃወር
وَالْفَجْرِ * وَلَيَالٍ عَشْرٍ﴾
"በንጋት እምላለሁ:በአስሩም ለሊቶች"
ሱረቱል ፈጅር

ብዙ ሙፈሲሮች 10 የዙልሂጃ የመጀመሪያ ቀኖች ናቸው ብለዋል።]

لِّيَشْهَدُوا مَنَافِعَ لَهُمْ وَيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ فِي أَيَّامٍ مَّعْلُومَاتٍ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّن بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ ۖ فَكُلُوا مِنْهَا وَأَطْعِمُوا الْبَائِسَ الْفَقِيرَ

ለእነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ (ይመጡሃል)፡፡ ከርሷም ብሉ፡፡ ችግረኛ ድሃንም አብሉ፡፡

ኢብኑ አባስ ሲፈስሩ በታወቁ ቀናቶች ማለት 10 የዙልሂጃ ቀናቶች እንደሆኖ ገልፀዋል።

ነብያችን ሙሃመድ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል :

''መልካም ስራ በእነዚህ ቀናት ከሚወደድበት የበለጠ ቀን የለም''።

በእነዚህ ቀናቶች የሚተገበሩ መልካም ስራዎች:

- ተክቢራ الله اكبر ማብዛት
- ተህሊል لا اله الا الله
- ተስቢህ
- እስቲግፋር
- ቁርአን ማንበብ
-ሶደቃ
ከላይ ያሉ መልካም ስራዎችን በማዘውተር ቀናቶችን በኢባዳ እንድናሳልፍ ለማስታወስ እንወዳለን።
3
🌙🌙የሙሃረም ወር ደረጃ

እነሆ 1448ኛው አመተ ሂጅሪያ (አዲሱ አመት) ከገባ ቀናቶች አንድ ሁለት እያሉ ዛሬ 8ኛው ቀን ላይ እንገኛለን።

አሏህ በተከበረው ቃሉ ካከበራቸው  4ቱ ወራቶች ውስጥ አንዱ ሁኖ እናገኘዋል።

ነብያችን ሙሃመድ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል።
" ከረመዷን ፆሞ በሆላ ተወዳጅ የሆነው ፆም በሙሃረም ወር የሚፆም ፆም ነው ብለዋል"።

እንዲሁም የሙሃረም 10ኛው ቀን   መፆም ያለፈው አንድ አመት ትናንሽ ወንጆሎች እንዲሰረዙ ተስፋ ይደረግበታልም።
ብለዋል

ነገ 9ኛውን ቀን ጨምረን በመፆም ከአይሁድ የዘልማድ ፆም እንድንለይ ነብያችን አስተምረዉናል።

የፆሙ ምክንያት ከታሪክ ማህደር

ነብያችን ሙሃመድ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ወደ መዲና በሄዱ ጊዜ አይሁዶቹ የአሹራን ቀን ሲፆሙ አገኟቸው። ለምን እንደሚፆሙ በጠየቋቸው ጊዜ " ይህ አሏህ ነብዩሏህ ሙሳንና ህዝባቸውን ከፊርአውን ያዳነበት ቀን ነው አሏቸው"።
ከዚያም ነቢዩ ﷺ፦
«نحن أحق بموسى منكم»
“እኛ ከእናንተ ይልቅ ለሙሳ ቅርብ ነን።”
ብለው የዓሹራን ጾም ጾሙ እና ሰዎችም እንዲጾሙ አዘዙ።
https://t.me/anwarmereja
👍2