የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ANRS Water and Energy Bureau
1.68K subscribers
2.86K photos
105 videos
4 files
457 links
ይህ ቻናል የአማራ ክልል አለፍ ሲልም ኢትዮጵያ ስላሏት የውሃና ኢነርጂ ሃብቶች፣ እነዚህን ሃብቶች ለህዝባችን በፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማድረሰና ለሃገር እድገት በመጠቀም ማጠንጠኛ የሚከወኑና የሚታለሙ ትልሞች ይዳሰሱበታል።
Download Telegram
የወልዲያ ከተማ የመጠጥ ውኃና ፍሳሸ አገልግሎት ድርጅት ዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ ወጪና ጊዜ ቆጣቢ ሆኖልናል። ሌሎች የከተማው ተቋማትም ይህን ተሞክሮ ይውሰዱልን ሲሉ ደንበኞች ተናገሩ።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከደንበኞቹ የፎረምና ምክር ቤት አባላት እንዲሁም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የጋራ ምክክር አካሒዷል።

በምክክር መድረኩ የከተማዋ መብራት አቅርቦት መሻሻል በመብራት የኃይል አቅርቦት መቆራረጥ ምክንያት ይፈጠር የነበረው የደንበኞች የውኃ መስመር መቆራረጥ መሻሻሉ፤ የከተማዋን የውሃ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት እየተሰሩ ያሉ ልዩ ልዩ የፕሮጀክት ሥራዎች። በዋናው አስፋልት መንገድ ፕረጀክቶ፣ በ30 ሜትር መንገድ ሥራ ፕሮጀክትና በኮሪደር ልማት ምክንያት የሚቀየር የውኃ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት ከቴሌ፣ ከመብራት፣ ከመሠረተ ልማት መምሪያና ከመንገድ ሥራ ድርጅቶች ጋር በመናበብ የደንበኞች የውኃ ስርጭት ሲቋረጥ በቶሎ ጊዜ ሳይወስድ መሠራቱ፣ የዲጂታል ቴክኖሎጅ አገልግሎት መሰጡቱና የሀብት አጠቃቀምና አያያዝ ዙሪያ ባሉ የአሠራር ለውጦች ከእነ ተግዳሮቶቻቸው ለምክክር መድረኩ በመነሻነት ቀርበዋል።

በምክክር መድረኩ የተሳተፉት አገልግሎት ተቋሙ የውኃ ደንበኞች የቢል ክፍያን ወደ በዲጂታል ባንኪንግ በሲቢኢ ብር፣ የቴሌ ብርና በሌሎች የሞባይል ባንኪንግ አማራጮች መዘርጋቱ ወጪያችንን፣ ጊዜያችንንና የቆጠበና የሰልፍ እንግልታችንን አስቀርቶልናል ብለዋል።

ሌሎች የከተማዋ ተቋማትም ከክፍያ ጋር የተያያዙ
ስራዎችን ከኋላቀር አሠራር ወደ ዘመናዊ አሠራር ለመቀየር የውኃ አገልግሎቱን ፈለግ ቢከተሉ ጥሩ ነው በማለት የተቋሙን የአገልግሎት አሰጣጥ አወድሰዋል።
👍6👏2
በዳባት ወረዳ ወቅን ከተማ በፖምኘ ብልሽት ምክኒያት ተቋርጦ የነበረው የመጠጥ ውኃ አቅርቦት የጠላቂ ፓምፕ ቅያሬ ተደርጎለት አገልግሎት መስጠት ጀመሯል።
👏6
በአማራ ክልል የገጠር ኮሪደር ልማት አረጋዊያንንና አካል ጉዳተኞችን ባማከለ ዲዛይን በውኃና ኢነርጂ ዘርፍ የሚሰሩ የንፁህ መጠጥ ውኃና የኢነርጂ ልማቶች

💦 በሁሉም ቤቶች የእጅ የውኃ ጉድጓድ
💦 ምንጭ ማጎልበት
💦 የገጠር መጠጥ ውኃ መስመር ዝርጋታ ( RPS)

አርሶ አደሩ በቂ የሆነ የኃይል አማራጭ እንዲያገኝ ከዋናው የኤሌክትሪክ መስመር ለራቁ (Off-grid) መንደሮች

🔋 የሶላር ኃይል ማመንጫና መገልገያ ቁሶች
💡 ከባዮጋዝ ከመብራትነትና ከማብሰያነት ባለፈ ለግብርና ምርት ማሻሻያ የሚውል ባዮ ስለሪ አማራጮች
🔥 ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎችን አቅርቦትና ማሻሻያዎች

ከአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ጀምሮ እስከ ዞንና ወረዳ ባሉ አደረጃጀቶች እነዚህን የልማቱ መርሆዎች ይከተላሉ...

👥 ህብረተሰቡን ያሳተፈ፣
🏚️ ዘላቂ በሆነ የግንባታ ጥራት፣
🙏 ምቹ ለጋራ አኗኗር
🌎 ለቴክኖሎጂ ትስስር የተመቸ
👨‍🦽 ለአካል ጉዳተኞችና አረጋዊያን በተመቸ ዲዛይን

መገንባት ዋና ዋና የገጠር ኮሪደር ልማቱ ፓኬጅ የቤት ስራዎቻችን ናቸው፡፡
የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሁሉንም የውኃ አገልግሎቶች ጠቅላላ መረጃ ዳታ ቤዝ ላይ የሚያስገባ ዲጂታል የመረጃ አስተዳደር ስርዓት MIS ከ123.8 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለማዘመን ውል ተፈራረመ።

ስርዓቱ በሁሉም የሀገሪቱ ውስጥ ያለውን አጠቃላይ የዋን ዋሽ ሲስተምና የውኃ አገልግሎቶች ጠቅላላ መረጃ ዳታ ቤዝ ላይ የሚያስገባና ለድጋፍም ለቁጥጥርም አመቺ የሆነ ቀላል ስርዓት ይፈጥራል።

ውሉን የፈረሙት የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ከኤል-ሃዳር ኢንጂነሪንግ ኃ.የተ.የግ.ማ. ከ ​​e-service Africa Ltd (eSAL) ጋር ነው።

የገንዘብ ምንጩ ዋን ዋሽ ብሔራዊ ፕሮግራም ሆኖ ጥቅል ወጪው 123,826,811.38 (አንድ መቶ ሃያ ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሃያ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ አስራ አንድ) ብር ነው።
💯1
በደቡብ ወሎ ዞን የውኃና ኢነርጂ ልማት የህዝቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማሳደግ የዞኑን ሃብቶች ማልማትና ማስተዳደር የሚችል ተቋም ለመፍጠር እየተሰራ ነው፡፡

በዞኑ በያዝነው ዓመት የህብረተሰብ የውኃና ኢነርጂ ልማት ተሳትፎን ወደ 40 በመቶ ለማሳደግ ግብ ተጥሏል። በዚህ ግብ መሰረት ህዝቡ መንግስት ለፕሮጀክቶች ከሚመድበው ገንዘብ በተጨማሪ ህዝቡ በገንዘብ፣ በቁሳቁስና በጉልበት ድጋፎች በገንዘብ ብር 43 ሚሊዮን የሚጠጋ ብር አስተዋጽኦ እንዲያደርግ እየተሰራ ነው።

ባለፉት 5 ወራት ብቻም የዞኑ ህዝብ ለውኃና ኢነርጂ ልማቱ 10 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ድጋፍ አድርጓል።

የደቡብ ወሎ ዞን ውኃና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ጽጌ እንደገለጹት በየደረጃው የሚገኝ የውኃና ኢነርጂ አመራር ባለሙያው ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የህብረተሰቡን ተሳትፎ በላቀ ደረጃ በማሳደግ በዘርፉ ያለውን የፋይናንስ እጥረት መሙላትና የህዝቡን ከፍተኛ የመጠጥ ውኃና ኢነርጂ ጥያቄዎች መመለስ የሚያስችል ተቋማዊ መደላድል ላይ መድረስ አለብን ብለዋል።

ኀላፊው አክለውም የምንገነባቸው ፕሮጀክቶች ሁሉ ለሴቶችና የወጣቶችን የስራ ዕድል ፈጠራ በሚያሳድግ የህጻናትን ጤና በሚያሻሽል ጥራት እንዲሁም ለአረጋውያንና አካል ጉዳተኞች ፍትሐዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በተመቸ ዲዛይንና ጥራት እንዲፈጸሙ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡
👏3👍1
በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር የሚገነቡ የንፁህ መጠጥ ውኃና ኢነርጂ ግንባታዎችን ለማጠናቀቅ ሁሉም ወረዳና ከተማ አመራሩንና ህብረተሰቡን በማስተባበር ውጤት ማምጣት አለበት።

የብሄረሰብ አስተዳደሩ ውኃና ኢነርጅ መምሪያ ያለፉት አምስት ወራትን አፈፃፀሙን ገምግሟል።

በግምገማው የመምሪያ ኃላፊው አቶ እውነቱ አወቀ ለሁሉም ወረዳዎች የውኃና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች በሰጡት አቅጣጫ መሰረት...

በእቅድ የተያዙ የንፁህ መጠጥ ውኃ ተቋማት ግንባታ ለማጠናቀቅ ሁሉም ወረዳና ከተማ በሙሉ አቅሙ አመራሩንና ህብረተሰቡን በማስተባበር ውጤት ማምጣት አለበት።

ነባር ባዮ ጋዝ ግንባታዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁና ወደ ስራ እንዲገቡ ማስቻል፣ እንዲሁም ወደ አዳዲስ ግንባታዎች በፍጠነት በመግባት ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባናል ብለዋል ኃላፊው።

ኃላፊው አክለውም ነባር የውኃ ተቋማትን በአግባቡ ማስተዳደርነ ህብረተሰቡ በባለቤትነት እንዲጠቀምባቸውም እንዲጠብቃቸው አደረጃጀት መፍጠርና ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል የሁላችንም ግዴታ ነውም ብለዋል።

በአጠቃላይ ለምንሰራቸው ስራዎች የማህበረሰብ ተሳትፎ በማሳደግ አገልግሎቶቻችን ሁሉ ክልሉ ባስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች መሰረት አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥተን መስራት ይገባናል ብለዋል።
👍4
የሰሜን ወሎ ዞን በጸጥታ ችግር ውስጥም ሆኖ ባለፉት አምስት ወራት ውጤታማ የውኃና ኢነርጂ ተግባራትን ፈጽመናል። ይህ ውጤት በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።

የሰሜን ወሎ ዞን ውሃና ኢነርጂ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የ5 ወራት በሁሉም ዘርፍ የተሰሩ ተግባራትን እቅድ ክንውን እና አፈፃፀም ገምግሟል።

በመድረኩም የወረዳ ውሃና ኢነርጂ ፅ/ቤት ኃላፊዎች ፣የከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ኃላፊዎች እንዲሁ የመምሪያው የማኔጅመንት አባላት የተሳተፉ ሲሆን በቀረበው ሪፓርት እና በሌሎች ጉዳዮችም ጭምር ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

ኃላፊዎቹ በዋናነት በዚህ ችግር ውስጥ ሁነን በአምስት ወር ውስጥ የተከናወኑ ስራዎች የሚደነቁ ሲሆን በቀጣይም በተለይ ከበጀት ምደባ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች ከተስተካከሉ እና ዞኑም እንደ እስካሁን ቀደሙ በድጋፍና ክትትል ተጨማሪ አቅም ከሆነን ከዚህም በላይ እቅዳችንን የማናሳካበት ምክንያት የለም በማለት በአስተያየትና በጥያቄ መልክ አንስተዋል።

በመጨረሻም የመምሪያው ኃላፊ አቶ ፋሲል አረጋ ሲጠቃለል በዋናነት በቀጣይ የተጀመሩ ትልልቅ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተጨርሰው ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንዲችሁ ሁሉም የየድርሻውን ኃላፊነት እንዲወጣ እንዲሁም ከተቋማት አስ/ር እና ከኢነርጂ አንፃር ሰፊ ስራ መስራት እንደሚገባና የመጠጥ ውሃ ማህበራት፣የገጠርና የከተማ ውሃ አገ/ቶች የመረጃ አያያዛቸውን እንዲያሻሽሉ እና እንዲያዘምኑ አፅንኦት ሰጥተዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ከኢንቨስትመንት ማስመለስ ጋር ተያይዞ ብድር እንዲመልሱ የተጠየቁ ውሃ አገ/ቶች በወቅቱ ብድራቸውን እንዲመልሱ የውሃ ፅ/ቤት ኃላፊዎች ክትትል እንዲያደርጉ አሳስበዋል ።
🙏6👍4
ስራዎቻችንን በጥራትና ህዝብን በማስተባበር እንሰራለን። በዚህም የውኃ ተቋማት የብልሽት መጠን ዜሮ እናደርሳለን። የህዝብ ጥያቄዎችን በጥራትና በፍጥነት ስለመመለስ እናተኩር!!

የደቡብ ጎንደር ዞን ውኃና ኢነርጂ መምሪያ ያለፉት 5 ወራት አፈፃፀም ግምገማውን ከወረዳ ውኃና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ከመምሪያው ሰራተኞች ጋር አካሂዷል።

የግምገማዊ ውይይቱ ተሳታፊ የወረዳ ውኃና ኢነርጂ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንደገለፁት የወሰዷቸውን ስልጠናዎች በመጠቀም የተቋማቸውን ግቦች ለመፈፀም ዝግጁነታቸውን ገልፀዋል። ለአሰራር የሚያስቸግሩና ዞናዊ እገዛ የሚጠይቁትን ተግዳሮቶች በዝርዝር አስቀምጠዋል።

የደቡብ ጎንደር ዞን ውኃና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ በለጠ ተስፌ እንደገለጹት በዘርፋችን ያለውን የህዝብ ፍላጎት ለመመለስ በዞኑ እየሰፈነ ያለውን ሰላም ተጠቅመን ዘመናዊ አሰራሮችን በመተግበርና ህዝቡን በማስተባበር ያስቀመጥናቸውን ግቦች ማሳካት ልዩ ትኩረት ይሰጠዋል።

ስራዎቻችንን በጥራትና ህዝብን እያስተባበርን መስራት አለብን። ይህን ስናደርግ የውኃ ተቋማት የብልሽት መጠን ዜሮ ለማድረስ የያዝነውን እናሳካለን። ትኩረታችንን ሰብስበን ይህን በቁርጠኝነት ማሳካት አለብን ሲሉም አቅጣጫ ተሰጥተዋል።

የመምሪያ ኃላፊው እንደገለጹት በወረዳዎችን አፈጻፀም ላይ የተገመገመውን የባለሞያዎች የአቅም ልዩነት መፍታት የሚያስችሉ የአቅም ግንባታ ስራዎች መሰራት አለባቸው።

በተጨማሪም የግቦችም አፈፃፀም ጉራማይሌ በመሆኑ በቅንጅትና በትብብርና የቤት ስራዎቻችንን መወጣት ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

አቶ በለጠ አክለውም በስልጠና ያገኘነውን አቅም በመጠቀም የተቋም ስራዎችን በጥራት እና በፍጥነት መፈጸም አለብን ብለዋል።
👍4💯1
‹‹አስቻይ ሁኔታዎችን ሁሉ በመጠቀም  ችግር ፈቺ ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋለ፡፡›› ወልደ ትንሳዔ /ዶር/ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአብክመ ውኃና ኢነርጂ ቢሮ አማካሪ
 
የበጀት ዓመቱ 2ኛ ዙር የአብክመ ውኃና ኢነርጂ ቢሮ የድጋፍና ክትትል ቡድን ከነገ ታህሳስ 8/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሚካሄደው የድጋፍ ፕሮግራም ኦረንቴሽን ወስዷል፡፡
 
በመድረኩ በበቂ ዝግጅት ላይ በመመስረትና  አስቻይ ሁኔታዎችን ሁሉ በመጠቀም  ችግር ፈቺ ድጋፍ ማድረግ እንደሚየያስፈልግ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአብክመ ውኃና ኢነርጂ ቢሮ አማካሪ ወልደ ትንሳዔ /ዶር/ ለቡድኑ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

በየደረጃው ያሉ የዘርፉ ተቋማት የበጀት ዓመቱ ዕቅድ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ እስከ ጥር 5 ባለው ጊዜ ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር ገምግመው ለክልላዊ መድረኩ ዝግጁ መሆን እንደሚገባቸውም አመላክተዋል፡፡

የአብክመ ውኃና ኢነርጂ ም/ኃላፊ አቶ ጥላሁን ሽመልስ በበኩላቸው፤ አቅም የሚፈጥር፣ የሚታይ፣ የሚጨበጥና ውጤት የሚያመጣ የድጋፍ ስልትን መከተል ይገባል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የድጋፍና ክትትሉን መሰረታዊ ዓላማ ማዕከል በማድረግ ለቀጣይ ስራ የሚያነቃቃና ከችግሮች በላይ ሆኖ ለላቀ ውጤት የሚያበቃ ድጋፍና ክትትል የማድረግ ትልቅ ኃላፊነት መውሰዳቸውንም ለቡድኑ አባላት ተናግረዋል፡፡ በተዋረድ ያለው መዋቅር ለሚፈጠሩ ችግሮች ሁሉ ከቢሮ መፍትሄ መጠበቅ ብቻ ሳይሆን እኔስ ምን ሰራሁ ብሎ ወደ ውስጥ መመልከትና ክፍተቶችን በራስ አቅም የመሙላት ልምምድ ማዳበር  የተገባ ነው ሲሉም አክለዋል ኃላፊው፡፡

የዞን ውኃና ኢነርጂ  መምሪያዎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣  ውኃና ፍሳሽ ድርጅቶች፣ ወረዳዎች፣ የከተማ ግብርና ኢነርጂ ቡድን ብሎም ፕሮጀክቶች በአካ እና በዙም ድጋፍ የሚደርግላቸው ተቋማት ናቸው፡፡
👏4
ለገጠር አካባቢዎች ኤሌክትሪክ ለማቅረብ ከ13 የግል ድርጅቶች ጋር ውል ስምምነት ተከናወነ።

ከዋናው የኤሌክትሪክ መስመር እጅግ ለራቁ የገጠር አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ሀይል ከሚያቀርቡ በዘርፍ ለተሰማሩ የ16 የግል ድርጅቶች ውል የማደስና ከ13 አዲስ የግል ድርጅቶች ጋር ውል ስምምነት ተከናውኗል።

በመርሃግብሩን በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ እንደተናገሩት "መንግስት በገጠር አካባቢ የሚኖረውን የህብረተሰብ ክፍል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ለዘርፉ ትኩረት ቢሰጥም የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ወሳኝና አመርቂ ውጤት ለማምጣት የሚያስችል በመሆኑ ውል ገብቶ ወደ ስራ ማስገባት አስፈልጓል ።

በ2030 የኢትዮጵያ እያንዳንዱ ሰፈር የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚ እንደሚሆን በሃገር ደረጃ የታቀደ መሆኑን ያወሱት ሚኒስትር ድኤታ ዕቅዱን ተግባራዊና ውጤታማ ለማድረግ ውል የሚያድሱም ይሁን አዲስ ውል የሚፈርሙ የግሉ ዘርፍ በከፍተኛ ሀላፊነትና በሀገር ፍቅር ስሜት ህብረተሰቡን ከጨለማና ከኋላቀርነት የማላቀቅ ስራ መስራት አለባቸው ብለዋል ።

በመርሃ ግብሩ ላይ በዘርፉ የተሰማሩና ውል የገቡ የግል ድርጅቶች ፣ የክልሎች የኢነርጂ ዘርፍ ሀላፊዎች ተሳትፈዋል ።
💯6👍4