ኤሊ ዔዘር
565 subscribers
742 photos
22 videos
122 links
👉👉 ኤሊ ዔዘር "እግዚአብሔር ረድኤት ነው" ማለት ነው። የአብርሃም ቤት መጋቢ ይህ ሰው በግዕዝ ኢያውብር ይባላል። ለልጁ ለይስሐቅ ሚስት ይፈልግ ዘንድ አብርሃም ወደ መስጴጦምያ የላከው አገልጋዩ ነበር።

👉👉 በዚህ መንፈሳዊ channel የእግዚአብሔርን ቃል የደጋግ አባቶች እና እናቶች ምክር ይቀርብበታል።
ራሳችን የምንመዝንበት እና ራሳችን በየቀኑ የምናሳድግበት channel ነው። @Amon0721
Download Telegram
#ሰውን_የሚጎዳው_ክፉ_ልብ_ነው!

ሰው ሆይ! የሚጎዳህ ሀብትህ አይደለም፤ ድኽነትህም አይደለም። ሰውን የሚጎዳው ክፉ ልብ ነው። ክፉ ልብ ደግሞ በሀብትም፣ ሀብት በማጣትም የሚመጣ አይደለም። ክፉ ልብ ሌሎች ክፉ ልቦችን ይወልዳል። እሳት እሳትን እየወለደ ብዙ እንጨቶችን እንደሚበላ ኹሉ ክፉ ልብም እንደዚህ ነው።

አንተ ሰው! ይህን ማወቅ ትወዳለህን? ክፉ ምግባር ወይም በጎ ምግባር በተፈጥሮ የሚገኙ አይደሉም። እነዚህ ኹለቱ ከክፉ ልብ ወይም ከመልካም ልብ የሚገኙ ናቸው።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

አምስቱ የንስሐ መንገዶች

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#ዕርገት

#በአባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ

"አሁንም በዓልን ከእኛ ጋር በዓልን እንዲያደርጉ አባቶችን እንጥራቸው። ከሁሉ በፊት አዳምን እንጥራው፡ እነሆ እግዚአብሔር ከገነት በወጣህ ጊዜ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ያለው ተፈጸመ፡ እግዚአብሔር ሥጋን ከሴት ልጅህ ለበሰ በአባቱም ቀኝ በሰማያት ተቀመጠ ይህን የወደድኸውን አምላክነት ከሴት ልጅህ በተወለደ በመለኮት ሰው መሆን አገኘኸው እንበለው። የሕያዋን እናታቸው ስለሆንሽ ሕይወት የተባልሽ ሔዋን ሆይ በሴት ልጅሽ ደስ ትሰኚ ዘንድ ነዪ፡ ሕይወትን አምጥታልሻለችና፡ በታተመ አፈ ማኅፀኗ የወለደችው እርሱ በረከትን ካገኙ ደቀመዛሙርቱ ጋር ቆማ እያየችው ወደ ሰማያዊው አባቱ ዐረገ። ዘፍጥረት ፫፥፳፪

ሄኖክ ሆይ ከእኛ ጋር በዓል ታደርግ ዘንድ ና ከሞት ፊት የሠወረህ በተሠወረች ሥፍራም ያኖረህ እርሱ ራሱን ከሥጋዊያን ሠወረ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ። የእግዚአብሔርም ወዳጅ አብርሃም ሆይ ከእኛ ጋር በዓል ታደርግ ዘንድ ና። በድንኳን ደጃፍ አጠገብ ባለ የወይራ ዛፍ አጠገብ ከአንተ ጋር የተቀመጠ የሦስት መሥፈሪያ ስንዴ ዱቄት የተጋገረ እንጎቻ የበላ አንተም ርጎና ማር የሰባ ወይፈንም ያቀረብህለት እርሱ ዛሬም ከደቀመዛሙርቱ ጋር በደብረ ዘይት ምሳ አደረገ ከምሳም በኋላ ባርኳቸው ከሴት ልጅህ በነሣው ሥጋ ወደ ሰማይ ዐረገ። ይስሐቅ ሆይ ከእኛ ጋር በዓል ታደርግ ዘንድ ና ከአባትህ ከአብርሃም ሾተል ቀንዶች በሐረግሬሳ በተያዘ በግ ደም የተቤዠህ እርሱ እንደበግ ሊታረድ መጣ ለመታረድም እጆቹን በመስቀል ግንድ ላይ ዘረጋ። በደሙም ሰይጣን የተናጠቃቸውን ተቤዣቸው ቁስላቸውም በሞቱ ቁስል ደረቀ ተነሥቶም የሰውና የመላእክት አእምሮ ወደማይደርስበት ወደ ሰማይ ዐረገ። ዘፍጥረት ፭፥፳፩ ፣፲፰፥፩-፲፭ ፣ ፳፪፥፱-፲፱

የእግዚአብሔር ሰው ያዕቆብ ሆይ ከእኛ ጋር በዓል ታደርግ ዘንድ ና እነሆ በሎዛ ከምድር እስከ ሰማይ ተተክሎ ያየኸው የወርቅ መሰላል እርሱ በደብረ ዘይት ተተከለ ቁመቱም እስከ አርያም ከፍታ ደረሰ የወልድ ሥጋ ከደብረ ዘይት ወደ ጽርሐ አርያም ከማረጉ በቀር የወርቅ መሰላል ምንድር ነው። ዘካርያስ የእግዚአብሔር እግሮች በደብረ ዘይት ይቆማሉ እንዳለ ለመባረክም እጁን በሐዋርያቱ ላይ ያኖር ዘንድ ቆመ ሰውነቱን ከመለኮቱ ክብር ያሳትፋት ዘንድ ቆመ ሰውነቱን ከመለኮቱ ክብር ያሳትፋት ዘንድ ወደላይ ከፍ ከፍ በማለት ራቃቸው ስለ ሰው ልጆች ፍቅር በምድር ላይ ያገኛት ያለፈው መከራ በቃት አሁን ግን በመለኮት ክብር ዐረገች በአብም ቀኝ ተቀመጠች። ዘፍጥረት ፳፰፥፩-፳ ፣ ዘካርያስ ፲፬፥፬ ፣ ሐዋርያት ፯፥፶፩

የእግዚአብሔር ልጅ ግን ያለመሰላል በሚንቦገቦግ ደመና ተን ዐረገ መለኮቱ ይተጋለታልና ወደ አየራትም ነጥቆታልና ኪሩቤል ሊያሳርጉት አልመጡም እርሱ ራሱ በመለኮት ኃይል አብን ተካክሎ በቀኝ በኩል ተቀመጠባቸው የማረጉም ምስጋና ለእኛ መሰላል ሆነን። ከገሊላ ሴት እንደተወለደ ባሰብን ጊዜ ወደ አባቱ እንዳረገ እናስታውሳለን። በጭኖቿ እንደታቀፈ ስናስታውሰው በአባቱ እቅፍ እንዳለ እናስባለን። በደብረ ዘይት ከደቀመዛሙርቱ ጋር እንደተቀመጠ ባሰብነው ጊዜ በመላእክቱ እልልታ እንዳረገ በወላጁም ቀኝ እንደተቀመጠ እናስታውሳለን።....

ዳግመኛም የእግዚአብሔርን ሕግ ያስተማረ ሙሴን ከእኛ ጋር በዓል ታደርግ ዘንድ ና ብለን እንጥራው በደብረ ሲና ሕግን የሰጠው እርሱ ለደቀመዛሙርቱ ሸክምን የምታቀል በዳግም ሕግ ያለውንም የርግማን ማሠሪያ የምትሽር ሕግን ሰጣቸው። ወገኖችህን ቀን በደመና ሌሊትም በእሳት ዓምድ የመራቸው በእሳት ዓምድ ወደላከው ወደ አብ ዐረገ። ዘጸአት ፴፩፥፲፰ ፣ መዝሙር ፻፬፥፵፰

ነቢዩ ዳዊት ሆይ ከእኛ ጋር በዓል ታደርግ ዘንድ ና መሰንቆ ከሚመታ ከአሳፍ ከሚዘምር ከኤማን በትንቢት መሰንቆዎች ከሚዘምሩ ከቆሬ ልጆችም ሁሉ ጋር እግዚአብሔር በእልልታ ዐረገ ጌታችንም በመለከት ድምፅብለህ አመስግን፤ ዳግመኛም ለአምላካችን መዘመርን ዘምሩ ለንጉሣችንም መዘመርን ዘምሩ ብለህ ዘምር። ከእንደገናም ዓለምን የሚገዛት ከፍ ከፍ አለ ብለህ አመስግን፤ ዳግመኛም አቤቱ በኃይል ከፍ ከፍ አልህ ኃይልህን እናመሰግናለን እንዘምራለን በል፡ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ ብለህ አመስግን በመጨረሻም ጌታ ጌታዬን አለው ጠላቶችህን ከእግርህ መረገጫ በታች እስካስገዛልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ብለህ ዘምር። ፩ዜና ፮፥፳፪ መዝሙር ፲፯፥፲ ፣፵፮፥፭ ፣ ፻፱፥፩"

(#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ - #መጽሐፈ_ምስጢር )

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#ልብ_ብለው_ያንብቡ

#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘእንዚናዙ ለንስሓ ልጁ በሰርጓ ቀን መገኘት ባለመቻሉ የላከላት ደብዳቤ

“ልጄ! ለሰርግሽ የነፍስ አባትሽ እኔ ጐርጐርዮስ ይህን ግጥም ስጦታ አድርጌ ልኬልሻለሁ፡፡ አባት ለሚወዳት ልጁ ሊሰጣት የሚችለው የተሻለው ምክርም ይህ እንደ ኾነ አምናለሁ፡፡

“ኦሎምፒያታ ሆይ፥ እውነተኛ ክርስቲያን ለመኾን ያለሽን ፍላጎት ዐውቃለሁና በደንብ አድምጪኝ! እውነተኛ ክርስቲያን እንዲሁ መኾንን የሚመኝ ብቻ ሳይኾን እንደዚያ ለመኾን ሊጥር ይገባዋል፡፡

“ከኹሉም በላይ፥ እግዚአብሔርን ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ ከእርሱ ቀጥሎም በቅዱስ ወንጌል እንደ ታዘዘው እንደ ጌታችንና መድኃኒታችን [ኢየሱስ ክርስቶስ] አድርገሽ ባልሽን ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ ስለዚህ እጠይቅሻለሁ! ጌታዋንና ፈጣሪዋን [ኢየሱስ ክርስቶስን] የማታከብርና የማትወድ ሴት በዚህ መንገድ ባልዋን እንዴት አድርጋ ልታከብረውና ልትወደው ትችላለች?

“በጋብቻሽ ውስጥ የትዳር አጋርሽ ይኾን ዘንድ እግዚአብሔር መርጦ ለሰጠሽ ባል ያለሽ መውደድ፣ ስሜትና ፍቅር እጅግ ኃያል ሊኾን ይገባዋል፡፡ ይህ ሰው አሁን የሕይወትሽ ዓይን፣ የልብሽም ደስታ ነውና፡፡

“እግዚአብሔርን እንደምትወጂው፥ ባልሽንም ያለ ቅድመ ኹኔታ ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ አንቺ ሴት እንደ ኾንሽና ታላቅ የኾነ ዓላማና ግብ እንዳለሽ፥ ኾኖም ዓላማሽና ግብሽ የቤትሽ ራስ ሊኾን ከሚገባው ባልሽ የተለየ እንደ ኾነ ዕወቂ፤ ተረጂም፡፡ ባንቺ ዕድሜ ላይ ያሉት አንዳንዶች ኹለቱም ፆታዎች እኩል [ራስ ናቸው] ብለው የሚሰብኩትን አትስሚ፤ የጋብቻንም ግዴታ [ወይም ዋና ዓላማ] አስቢ፡፡ እነዚህን ግዴታዎች [ወይም ዓላማዎች] ስታውቂ የቤተሰብሽን ተግባራት ለማከናወን እንደ ምን ያለ ትዕግሥትና ጽናት እንደሚያስፈልግሽ ታውቂያለሽና፡፡ እንደ ሚስት እጅግ ጥንካሬን ገንዘብ የምታደርጊውም በዚህ መንገድ ነው፡፡

“ወንዶች እንዴት በቀላሉ የሚቈጡ መኾናቸውን በርግጥ ልታውቂ ይገባሻል፡፡ አይችሉም፤ ብዙ ጊዜም እንደ በረኻ አንበሳ ይኾናሉ፡፡ እንግዲህ ሚስት ጸንታ ልትቆምና የነፍስ ልዕልናዋን ልታሳይ የሚገባት በዚህች ቅጽበት ነው፡፡ አንበሳን የማስለመድ ሥራ መሥራት አለብሽ፡፡ አንበሳን የሚያስለምድ ሰው አንበሳ ሲያገሳ የሚያደርገው ምንድን ነው? ከየትኛውም ጊዜ በላይ ዝም ጸጥ ይላል፡፡ በጸጥታውና በርጋታውም የአንበሳውን ቊጣ ይቈጣጠራል፡፡ በርጋታና በለሆሳስ ኾኖ ያናግረዋል፤ ይደባብሰዋል፤ በቀስታ ያሻሸዋል፤ በጥቂት በጥቂቱም አንበሳው ቊጣውን ይተዋል፡፡

“ባልሽ ስሕተት ሲሠራ በፍጹም ልትነቅፊው፣ ልትንቂው ወይም ልታስነውሪው አይገባም፡፡ በተመሳሳይ መንገድ አንድ መሥራት ያለበትን ነገር ባይሠራና ከዚሁ የተነሣም ውጤቱ ደስ የማያሰኝ ቢኾን፣ ወይም እጅግ የምትፈልጊውና አግባብ ነው ብለሽ የምታስቢውን ባያደርግ እንኳን ባልሽን መናቅ ከአንቺ ልታርቂ ይገባል፡፡ ክፉዎች አጋንንት ዘወትር ቤታችሁን ለማፍረስና የጥንዶች መንፈሳዊ አንድነትን ለመበተን እንደሚሞክሩ ዕወቂ፡፡”

( #ከገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ ከትንሿ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ የተወሰደ)

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#የካህን_ሥልጣን_ግን_በነፍስ_ላይ_ነው!!

የንጉሥ ሥልጣን በሥጋ ላይ ነው፤ የካህን ሥልጣን ግን በነፍስ ላይ ነው፡፡ ንጉሥ ይቅር ቢል የገንዘብን ዕዳ ነው፤ ካህን ይቅር ሲል ግን የበደል የኃጢአት ዕዳን ነው፡፡

ንጉሥ ያዝዛል፤ ካህን ግን ያስተምራል፤ ይዘክራል፡፡ ንጉሥ ያስገድዳል፤ ካህን ግን ነጻ ፈቃድን ያያል፡፡

ንጉሥ ቁሳዊ የጦር ዕቃ መሣሪያ አለው፤ ካህን ግን ረቂቅ (መንፈሳዊ) የጦር ዕቃ መሣሪያ አለው፡፡ ንጉሥ የጦር ዕቃ መሣሪያውን ቢሰብቅ አንገዛም ብለው ባመፁት (እንዲሁም ከወራሪዎች ሥጋውያን ደማውያን) ላይ ነው፤ ካህን ግን ውጊያው ከጨለማ አበጋዞች ከአጋንንት ጋር ነው፡፡

ስለዚህ ሥልጣነ ክህነት ከሥልጣነ መንግሥት ይበልጣል፡፡ እንዲህም በመኾኑ ንጉሥ አንገቱን ለካህናት እጅ ያጎነብሳል፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ፣ ትንቢተ ኢሳይያስ፣ ድርሳን ፬ በተረጎመበት ድርሳኑ)

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#በዓለ_መንፈስ_ቅዱስ

#ጰራቅሊጦስ

ይህች ታላቅ ዕለት ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል የሆነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለቅዱሳን ሐዋርያት፣ ለቅዱሳን አርድእትና ለቅዱሳት አንስት የተገለጠባት ዕለት ናት፡፡ እነዚህ ሁሉ በጸሎት ተግተው በሚጸልዩበት ወራት መንፈስ ቅዱስ በተከፋፈሉ የእሳት ልሳን አምሳል የወረደበት ቅዱስ ቀን ነው፡፡ አስቀድሞ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት ደብረ ዘይት በተባለ ታላቅ ተራራ ላይ ሳሉ እንዲህ ብሎ አስተምሯቸው ነበር “ኃይልን ከአርያም እስክልክላችሁ ድረስ በኢየሩሳሌም በጸሎት ቆዩ፡፡” ሉቃስ 24፥36 መቶ ሃያው ቤተሰብም በኢየሩሳሌም ሀገር በምትገኝ በቤተ መቅደስ በአንድነት ሆነው በጸሎት በመትጋት ቆዩ፡፡ 120ው ቤተሰብ የሚባሉት 12ቱ ሐዋርያት፣ 72ቱ አርድእት )አገልጋዮች) እና 36ቱ ቅዱሳን አንስት (ሴቶች) ናቸው፡፡

ከዕርገት በኋላ በአሥረኛው ቀን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት ወዳሉበት፣ በጸሎትና በምሥጋና ወደ ሚተጉበት ሥፍራ በእሳት አምሳል (ምሳሌ) ወርዶ በእያንዳንዳቸው ላይ ተቀመጠባቸው፡፡ ይሄንንም ሁኔታ ተከትሎ ምስጢር ተገለጠላቸው፣ ይፈሩ የነበሩት ሐዋርያትም ወንጌልን ለማስተማር ደፋሮች ሆኑ፣ በተለያየ ቋንቋዎች እንዲናገሩ እውቀት ተሰጣቸው፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ ተቀበሉ፡፡ ይህንን ታላቅ ኀይል እና ሰማያዊ ስጦታን የሰጣቸውን እግዚአብሔርን በታላቅ ዝማሬና እልልታ አመሰገኑት፡፡

በዚያም ዕለት በዓለ ሃምሳ የሚባለውን የአይሁድን በዓል ለማክበር ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ቁጥራቸው በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሐዋርያቱን ታላቅ የዝማሬና የእልልታ ድምፅ ሰሙ፡፡ ከመቶ ሃያው ቤተሰብ መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ጴጥሮስ የተሰበሰቡት ሁሉም እንዲሰሙት ድምፁን ከፍ አድርጎ ቃለ እግዚአብሔርን እንዲህ ብሎ አስተማራቸው፡፡ እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ እኛን የሰው ልጆችን ለማዳን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ወደ ምድር መጥቶ ከክፉ ሥራ ተመለሱ፣ ኀጢአትን አታድርጉ፣ በቅድስና ኑሩ፣ ወደ እኔም ተመለሱ ቢላችሁ፤ እናንተ ግን ምንም በደል ሳይኖርበት ገረፋችሁት፣ አንገላታችሁት፣ በመስቀል ላይም ሰቀላችሁት፡፡ እርሱ ግን እግዚአብሔር ነውና ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፡፡ እርሱ ግን አሁንም ይቅር ባይ ነውና ከኀጢአታችሁ ተመለሱ ንስሐም ግቡ፡፡ በማለት አስተማራቸው፡፡

የተሰበሰቡት ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፡፡ ምክንያቱም ሐዋርያት በፊት የሚያውቁት አንድ ቋንቋ ብቻ ነበረ፡፡ በዚህ ሰዓት ግን ሰባ ሁለት ቋንቋን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ገልጦላቸው ለሁሉም በየቋንቋቸው አስተማሯቸው፡፡ ይህንንም ድንቅ ተአምር ከተመለከቱት ብዙዎች እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ ወደ ሐዋርያትም ቀርበው አባቶቻችን እናንተ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናችሁና ምከሩን፡፡ እንደ እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆንና በቅድስና እንድንኖር ምን እናድርግ?” በማለት ጠየቁ በዚያች ቀን ቁጥራቸው ሦስት ሺ ያህል ሰዎች በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት አምነው ክርስቲያን ለመሆን ቀረቡ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፡፡ “እነሆ ሁላችሁም ንስሐ ግቡ፡፡ በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት አምናችሁ ተጠመቁ፡፡” አላቸው በዚያው ዕለትም ሦስት ሺ ሰዎች ወደ ሐዋርያት በመቅረብ ኃጢአታቸውን ተናገሩ፤ ሐዋርያትም እግዚአብሔር ይፍታችሁ እያሉ ልጅነትን የሚያሰጣቸውን ጥምቀት አጠመቁዋቸው፡፡

ከዚያ ቀን ጀምሮም በየዓመቱ ይህችን ታላቅ የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን የምትባለውን በዓለ ጰራቅሊጦስን ክርስቲያኖች በታላቅ ደስታና ምሥጋና እናከብራታለን፡፡

በጽርሐ ፅዮን የወረደው የአብ በረከት፣ የወልድ ፍቅር ፣ የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችንም ጋር ይሁን!!!

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#መንፈስ_ቅዱስ

"በሃይማኖት ሙቀት ቤተክርስቲያንን ያሞቃት የመንፈስ ቅዱስ እሳት ነው፡፡"

#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#ጾመ_ሐዋርያት/የሰኔ ጾም/

ጾመ ሐዋርያት /የሰኔ ጾም/ ማለት ሐዋርያቶች የጾሙት ጾም ማለት ነው። ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ለስብከት ከመሰማራታቸው በፊት አገልግሎታቸው የተሳካ ይሆን ዘንድ ፈጣሪያቸውን በጾም በጸሎት ተወስነው የጠየቁበት ጾም ነው። /ግብ ሐዋርያት 2፥1፣ 27፥9/

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ይህንን ጾም ሐዋርያት እንደሚፆሙት ተናግሮ ነበር። ️/ማቴዎስ. 9፥14/ ከዚህ በኋላ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው “እኛና ፈሪሳውያን ብዙ እንጾማለን ደቀመዛሙርትህ ስለምን አይጾሙም” አሉት። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዲህ አላቸው “የሙሸራው ሚዜዎች ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ አይችሉም ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል ያን ጊዜ ይፆማሉ።” በማለት የፆምን አስፈላጊነት አስረግጦ አስተምሯል። ጾም ባያስፈልግ ኖሮ ለደቀመዛሙርቱ እኔ ጾምኩላቸው ብሎ በተናገረ ነበር። መወሰድ የተባለው ደግሞ ዕርገቱ ነው።

ካረገ በኋላ በአስረኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ጾምን ጀምረዋል ይህም ጾም ሁል ጊዜ በየዓመቱ ከበዓለ ሃምሳ ማግስት ጀምሮ ይጾማል። የፍስኩም ዕለት የማይለወጥ ሲሆን ሁል ጊዜ ርዕሰ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስና ብርሃነ ዓለምና ማኀቶተ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ጳውሎስ በሚታሰቡበት ሐምሌ 5 ዕለት ይሆናል። የጾሙ ቀን ግን ሊያጥርም ሊረዝምም ይችላል። ሲያጥር 15 ቀን ይሆናል። ሲረዝምም ደግሞ 49 ቀን ይሆናል።

በወርኃ ሰኔ ስለሚጾምም የሰኔ ጾም ተባለ እኔ ሳለሁ አይጾሙም ማለቱ እርሱ ካልሞተና ካላረገ መንፈስ ቅዱስም ካልተሰጣቸው በመንፈስ ቅዱስ ባልታደሰ ሰውነት ሆኖ ሰይጣንን ድል መንሳት ስለማይችሉ ይህንን አለ። ይህንንም አባባል ሲያብራራው “ባረጀ ልብስ ልብስ ላይ አዲስ ቁራጭ እራፊ የሚለጥፍ የለም ምክንያቱም የአዲስ ቁራጭ ልብስ ኃይል ቀዳዳውን ያሰፋዋልና አዲሱንም ወይን ባረጀ አቁማዳ ረዋት የሚጨምር የለም ቢጨምሩት ግን ጋኑ ይፈነዳል ወይም ያፈሳል። በአዲስ ረዋት ቢጨምሩት ግን ምንም የሚያመጣው ችግር የለም።” ማቴዎስ 9፥16-17 በማለት ምክንያቱን በምሳሌ አስተምሯል። ሐዋርያትም በመንፈስ ቅዱስ ባልታደሰ ሰውነት መጾም ስለማይገባቸው መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ግን መጾም እንዳለባቸው ሲነግራቸው ነው። አንድም የኦሪቱ የጾም ሥርዓት ከሐዲሱ የጾም ሥርዓት የተለየ መሆኑን ሊያስረዳቸው ስለፈለገ ነው።

ይህንን ጾም የምንጾመው ሐዋርያት ጾመው ጸልየው ድል ያደረጉትን ዓለም እኛም የምናሸንፍበትን ኃይል እንዲሰጠን ፈጣሪያችንን አምላከ ሐዋርያት ተለመነን እያልን ለመማፀን ነው።

በተጨማሪም ቅዱሳን ሐዋርያትን አርአያ አድርገን የበረከታቸው ተካፋይ እንሆን ዘንድ እንጾማለን። ጾሙም በሥርዓተ ጾም መሰረት እንደ ሁሉም አጽዋማት እስከ ዘጠኝ ሰዓት መጾም አለበት። ይህንን የሐዋርያት ጾም አንዳንድ ሰዎች ሐዋርያት ጾሙት ሲባል የቄስ ጾም ነው በማለት ላለመጾም ምክንያት ሲደረድሩ ታያላችሁ አስቀድመን እንደተናገርነው የቄስ ጾም የሚባል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዘንድ የለንም። አባቶቻችን ሠልስቱ ምእትም ይህን ጾም እንጾመው ዘንድ ሥርዐት ሠርተዋል። ፍትህ መንፈሳዊ አንቀጽ15 በመሆኑም ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ይጾመዋል።

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#ከማውራት_ይልቅ_መስማትን_ምረጥ!

አባ ዮሴፍ አባ ንስጥሮስን እንዲህ ሲል ጠየቀው "እርሱን መቆጣጠር አልቻልሁምና ስለ አንደበቴ ምን ባደርግ ይሻለኛል?"

አረጋዊው ንስጥሮስም "በምትናገርበት ጊዜ ሰላምን ታገኛለህን?" ሲል ጠየቀው እርሱም "አላገኝም" ብሎ መለሰ። አረጋዊውም "ሰላምን የማታገኝ ከሆነ ስለምን ትናገራለህ? ዝም በል፣ ንግግርም በሆነ ጊዜ ከማውራት ይልቅ መስማትን ምረጥ!"

ምንጭ፦ Paradise of the holly fathers

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#በዓለ_ቅዱስ_ሚካኤል_ሚካኤል

ሰኔ 12 የሚከበርበት ምክንያት ዲያብሎስን በፈቃደ እግዚአብሔር ተዋግቶ ያሸነፈበት አምላክነትን ሽቶ በወደቀው በዲያብሎስ ምትክ ሊቀ መላእክት ሆኖ የተሾመበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ "ክብር ይግባውና እግዚአብሔር በዚህች ዕለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን ከወገኞቹ ከመላእክት ሁሉ በላይ አክብሮ ሹሞታል" ይላል ድርሳነ ሚካኤል!!!

ከዚህ በተጨማሪ ይህ ዕለት ቅዱስ ሚካኤል አፎምያን ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ በአንዲት አገር ሃይማኖቱ የቀና ታላቅ መኮንን ከሙ አስተራኒቆስ የሚባል ሰው ነበር፡፡ ሚስቱም አፎምያ ትባላለች፡፡ አፎምያ ባልዋ አስተራኒቆስ ታሞ እያለ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አስሎ እንዲሰጣት ለመነችው፤ እንዳለችው አደረገላትና ባልዋ ሞተ፡፡ ከዚህ በኋላ አፎምያ ባልዋ ያሠራላትን ሥዕል ይዛ በሃይማኖት ጻንታ ስትኖር ዲያብሎስ በተለያየ መልኩ ይፈትናት ጀመር፡፡ አንድ ጊዜ ባልቴት እየመሰለ ሌላ ጊዜ ሌላ እየሆነ ባል ማግባት እንዳለባት መከራት፡፡ መጽሐፍም ጠቀሰላት፡፡ ከንጉሡ ጋር ማጋባት እንዳሰበ ነገራት እርሷ ግን ማግባት እንደማትሻ እግዚአብሔርን እያገለገለች ኖራ ማለፍ እንደምትፈልግ ነገረችው፡፡ ዲያብሎስ ግን ፈተናውን እያባሰ እያባሰ መጣ፡፡ በመጨረሻ ግን በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል አሳፍራ አዋረደችው፡፡

የሰኔ ሚካኤል ዕለት ዲያብሎስ ዳግመኛ ሊፈትናት መጣ፡፡ ሚካኤል ነኝ አላት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ሰይጣን ራሱ የብርሃን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣል››/2ቆሮንቶስ .11፥13/ እንዳለ በዚህን ዕለት የቀረባት ራሱን ለውጦ የብርሃን መልአክ መስሎ ነበር፡፡ አፎምያ ግን አስተዋይ ስለነበረች ‹‹የብርሃን መልአክ ከሆንክ የመስቀል ምልክት ያለበት በትርህ ወዴት አለ?›› አለችው፡፡ በኛ በመላእክት ዘንድ የመስቀል ምልክት አይደረግም አላት፡፡ እርሷም ስለ ተጠራጠረችው የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ልታመጣ ወደ ሥዕል ቤቷ ስትገባ ዘለለና አነቃት፡፡ አፎምያ ጮኸች፤ ቅዱስ ሚካኤልም ፈጥኖ ደርሶ አዳናት ዲያብሎስንም አዋረደላት፡፡

ዲያብሎስ አፎምያ ያሰበችውን ጸጋ ሆኖ የተሰጣትን ኑሮ ትታ በተለየ ዓለም እንድትኖር እንደ መከራት በእኛም ሕይወት እንዲህ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በጋብቻ ወቅት ምንኵስናን እንድናስብ' በዕርቅ ሰዓት ጥላቻ እንዲሰማን' በሰላም ጊዜ ጦርነትን' በጾም ጊዜ ምግብን' በትዕግሥት ጊዜ ቁጣን በመረጋጋት ጊዜ አድመኝነትን በውስጣችን ሊያኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ እንደ አፎምያ በእምነትና በምግባር ጸንተን በማስተዋል ልንኖር ይገባል፡፡ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት አይለየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏

ምንጭ፦ ሐመር 1995 ግንቦት/ሰኔ

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#ሰኔ_12

#ዕረፍቱ_ለቅዱስ_ላሊበላ_ኢትዮጵያዊ

(ለዝክር ያኽል) ...ንጉሥ ወቅዱስ ላሊበላና ሚስቱ መስቀል ክብራ ኑሯቸው እንደ አብርሃምና እንደ ሣራ በፍቅርና በሃይማኖት ነበር። ሆኖም በጊዜው የነበረው ንጉሥ በሐሰት ምስክር ስላስገረፈው ላሊበላ "ድሮስ ከሰው ምን አለኝ" ብሎና ተቆጥቶ ሊመንን ተነሣ። መስቀል ክብራም "ባሌ መንኖ እኔ ምን ልሆን" ብላ በፍቅር ተከተለችው። በዓት መሥርተው በትኅርምት መኖር ጀመሩ።
መልአከ ዑቃቤው ቅዱስ ገብርኤል ተገለጠለትና "ተነሥ ወደ ኢየሩሳሌም ልውሰድህ" አለው። ላሊበላም "እሷስ?" አለ መስቀል ክብራን ትቶ ላለመሔድ። "ለእርሷ ሚካኤል አለላት" አለው መልአኩ።

ቅዱስ ገብርኤል ላሊበላን በአምሳለ ወሬዛ መርቶ ኢየሩሳሌም አደረሰው፤ ቅዱስ ሚካኤልም በአምሳለ ወሬዛ መስቀል ክብራን መርቶ የሴቶች ገዳም አድርሶ በአደራ አስረከባት። ላሊበላ ኢየሩሳሌምን ተሳልሞ ፣ በማየ ዮርዳኖስ ተጠምቆ ፣ በረከትንና ቃል ኪዳንን ተቀብሎ ወደ መስቀል ክብራ በመልአኩ ታቅፎ ተመለሰ።

ወንድሙ ንጉሥ ገብረ መስቀል ንግሥናውን ትቶ በእግዚአብሔር ጥሪ ሲመንን ላሊበላ ነገሠ። ከ20 በላይ አብያተ ክርስቲያናትን በመላ ሀገራችን አሠራ፤ የቅድስና ሕይወቱ ታላቅ ነው።

ክብሩ እንደ ቅዱስ ጳውሎስና እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ተብሎ የተመሠከረለት ኢትዮጵያዊው ንጉሥ ወቅዱስ ላሊበላ በቅድስና ሕይወቱን መርቶ ሰኔ 12 ዐረፈ።

በረከቱ ከኹላችንም ጋር ይሁን!

#ሕሊና_በለጠ✍🏻✍🏻✍🏻

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#ባሕራን

ባሕራን ማለት ከባሕር የተገኘ ማለት ነው፡፡ የባሕራን ሕይወት፣ መኖር፣ ክብር፣ ታሪክ ከመጀመሪያው ጀምሮ እስከ ዕለተ ዕረፍቱ ድረስ ያለው በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ተአምር ላይ የቆመ ነው፡፡

ይህም በመጽሐፈ ስንክሳር እንደተጻፈው በሰኔ 12 ቀን ይዘከራል፡፡ በአንዲት አገር እግዚአብሔርን የሚፈራ ደግ ክርስቲያን ሰው ነበረ፡፡ በየወሩም የቅዱስ ሚካኤልን ዝክር አያቁዋርጥም ነበር፡፡ በተለይም ኅዳር 12 ቀን እሥራኤልን ከምድረ ግብጽ መርቶ መና እያወረደ ውኃ እያፈለቀ በምደረ በዳ የመገባቸውን፣ ቀን በዓምደ ደመና ሌሊት በዓምደ ብርሃን እየመራ የለበሱት ልብስና የእግራቸው ጫማ ሳያልቅ፣ ከጠላቶቻቸው እየሰወራቸው እና ድልን እንዲቀዳጁ አደረገ አርባ ዓመት ሙሉ በመንገዳቸው የጠበቃቸውን፣ የመራቸውን፣ የረዳቸውን፣ የመገባቸውን እያሰበ በቃል ኪዳኑ ታምኖ፣ ድኆችን በቤቱ ሰብስቦ ይዘክር ነበር፡፡
እንዲሁም በሰኔ 12 ቀን ስለ ሰው ልጆች በአምላክ ዙፋን ፊት ቀርቦ ከእሳት መጋረጃው ውስጥ ገብቶ ምህረትን የሚለምንበትን ቀን አስቦ ዝክሩን በደማቅ ሥነ ሥርዓት ያደርግ ነበር፡፡

የሚሞትበትም ቀን በደረሰ ጊዜ ለሚስቱ ይህንን መልካም ሥራ እንዳታቁዋርጥ ወር በገባ በ12 ዝክሩን እንድታደርግ በተሌም ዓመታዊ በዓሉን ባላት ነገር መታሰቢውን እንድታደርግ እና እርሱ በአካለ ሥጋ ቢለያትም ቅዱስ ሚካኤል በነገር ሁሉ እንደሚረዳት ጎረቢታቸው ባለጸጋው ሰው በሀብቱ እየተመካ ይተናኮላቸው ስለነበር የእርሱን ክፋት የእነሱን መልካምነት የሚውቅ እግዚአብሔር እንደሚጠብቃት፣ ቅዱስ ሚካኤልም እንደማይለያት እና እንደሚረዳት አስተምሮዋት በክብር አረፈ፡፡ እሱ ካረፈ በኋላ ጠቂት እንደቆየች ማርገዙዋን አወቀች፤ ከመሞቱ በፊት ፀንሳ ነበርና፡፡ የመውለጃዋ ጊዜም ደርሶ በምጥ ተጨንቃ ሳለች ረዳቴ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ተጨንቄአለሁና ድረስልኝ ካንተ በቀር ሌላ የሚያጽናናኝ ወገን ዘመድ የለኝምና ባሌ ሲሞት የሰጠኝ ዋስ ጠበቃዬ እንተ ብቻ ነህ ብላ ለመነች፡፡

ቅዱስ ሚካኤልም ልመናዋን እንዳቀረበች እንደ ዓይን ጥቅሻ ፈጥኖ ደረሰና ያለችበትን ቤቱን በብርሃን መላው፡፡ ወዲያውኑ በሰላም ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ እጅግ ደስም አላት መልአኩም ደስ የሚያሰኝ የሚያጽናና ድምጹንም አሰማት፡፡ እንዲህም አላት አይዞሽ ይህ ያማረ ልጅሽ ባጠገብሽ ያለውን የባለጸጋውን ሀብት ሁሉ ይወርሳል፡፡ አንቺም ከድህነት ኑሮ ትላቀቂያለሽ ሙሉ ሀብቱን ንብረቱን ባሪያዎቹን ሳይቀር ትወርሳላችሁ ደስ ብሏችሁም በሰላም ትኖራላችሁ አላት፡፡

ይህንን ሲል የመልአኩን ድምጽ ያ ክፉና ጨካኝ ባለጸጋ ሰምቶ ስለ ነበረ ተጨነቀ፡፡ ህጻኑም ጡት በተወ ጊዜ ያ ባለጸጋ ልጅሽን ስጪኝና እኔ ሀብት ስላለኝ ነገር ግን ወንድ ልጅ ስለሌለኝ ላሳድገው ላንቺም ሃያ ወቄት ወርቅ እሰጥሻለሁ ይላታል እሷም ስለ ሃያ ወቄት ወርቁ ደስ ብሏት ልጁዋን ሰጠችው እሱ ግን በቁመቱ ልክ ሳጥን አሰርቶ በሌሊት ባሪያዎቹ ወስደው ከባህር እንዲጥሉት አደረገ፡፡

ያ ሳጥን ለሃያ ቀናት ጉዞ ያክል እያንሳፈፈ ወስዶ ካንዲት አገር ወደብ ዳርቻ ተፋው፡፡
በዚም በጎች የሚጠብቅ አንድ ሰው ባሕር የተፋውን ሳጥን አየና ወደ ቤት ወሰደው፡፡

ሳትኑ ተቆልፎ ነበርና በምን ልክፈተው እያለ ሲያስብ ልቡናውን አሳሰበውና ሳጥኑን ከቤት አስቀምጦ ወደ ባሕሩ ዳርቻ ሄደ በዚያም ዓሣ የሚያጠምደውን በኔ ስም መረብህን ጣለውና የምትይዘውን ዓሣ ትሰጠኛለህ እኔም ዋጋውን እሰጥሃለሁ ይለውና ትልቅ ዓሣ በመረቡ ይያዛል፡፡

ዓሳውን ይዞም ወደ ቤቱ ገባ ማታም ለእራት ሊያዘጋጀው ዓሳውን ሲጠብስ በዓሳው ሆድ ቁልፍ አገኘ፡፡ ያንን ቁልፍ የሣጥኑን ቁልፍ ቢሞክርበት ከፈተለት በሣጥኑ ውስጥም ያን የሚያምር ልጅ በማግኘቱ እጅግ ደስ አለው፡፡ ቀድሞውንም ልጅ አልነበረውምና ያን የመሰለ ልጅ እግዚአብሔር እንደሰጠው እያሰበ ደስ ብሎት አሳደገው፡፡ ስሙንም ከባህር አግኝቼዋለሁ ሲል ባሕራን አለው፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን ያ በሳጥን አድርጎ በባሕር የጣለው ባለጸጋ ለንግድ ወደ ሩቅ አገር ሲጉዋዝ መሸበትና ወደ አንዲት መንደር ቀርቦ አሳድሩኝ መንገደኛ ነኝ ለማደሬም ጠቀም ያለ ገንዘብ እሰጣችኋለሁ ይልና ባሕራን እንደ ልጅ ሆኖ ካደገበት ቤት ለማደር ይፈቀድለትና ይገባል፡፡የቤቱ ባለቤትም ልጁን ባሕራን እያለ ሲጠራው ይሰማና እንዴት ልጅህን ስሙን ባህራን ብለህ አወጣህለት ይለዋል እሱም ከባህር ስላገኘሁት ነው ይልና ታሪኩን ያጫውተዋል፡፡

ያ በለጸጋም ይደነግጥና መቼ ነው ይህ የሆነው ይለዋል ከሃያ ዓመት በፊት እንደሆነ ሲነግረው የራሱ ጉድ እንደሆነ በማወቁ ሌሊቱን ሙሉ ሲጨነቅ ሲያስብ ያድራል፡፡ ሲነጋም ወደ አደረበት ቤት ባለቤት ቀረብ ይልና እባክህን ለሥራ የሚያስፈልገኝን ዕቃ ከቤቴ ረስቼ መጥቻለሁና ልጅህን ልላከው ለአንተም ሃያ ወቄት ወርቅ እሰጥሃለሁ፡፡ ለልጅህም የሚያስፈልገውን ሁሉ አደርግለታለሁ ይለዋል፡፡ እሱም ይፈቅድለትና ባሕራን ይጠየቃል፡፡ ባህራንም እጅግ ቅን እና ታዛዥ ልጅ ነውና እሺ ብሎ አባቱ እንዳለው ለዚያ ባለጸጋ ይታዘዛል፡፡

ባለጸጋውም “ይህ ባህራን የተባለ ልጅ ይህችን ደብዳቤ ይዞ እንደመጣ ወዲያው ሰው ሳያይ ግደሉትና ጉድጉዋድ ውስጥ ጣሉት የሚል ጽሑፍ ጽፎ እሱና የሀብቱ አሳዳሪ ብቻ የሚተዋወቁበትን የምሥጢር ምልክት ወይም ፊርማ አኑሮ ሰጠውና በመንገድ ላይ ማንም ቢያገኝህ ይህቺን ደብዳቤ እንዳታሳይ ይለዋል፡፡

ባህራንም ሲጉዋዝ ሰንብቶ ከተላከበት አገር ሊደርስ የአንድ ቀን ጉዞ ሲቀረው በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠ ጎልማሳ አገኘውና ሰላምታ አቀረበለት ባህራንም ሰላምታውን ተቀበለ ያ ጎልማሳም በእጅህ የያዝከው ምንድን ነው እስኪ አሳየኝ ይለዋል፡፡ባሕራን ግን መንገድ ላይ ለማንም አታሳይ ተብሎ ስለ ነበር ለጊዜው ለማሳየት ፈቃደኛ አልሆነም ነበር ነገር ግን ያ ጎልማሳ ደጋግሞ ስለጠየቀው እሺ በእጅህ ላ እንዳለ አሳየኝ አለውና ሲያሳየው እፍ ቢልበት ጽሑፉ ተለውጦ “ይህ ደብዳቤውን የያዘ ባሕራን የተባለ ልጅ እናንተ ጋር እንደደረሰ እና ደብዳቤውን እንዳነበባችሁት ወዲያውኑ አንድ ልጄን አጋቡት ሀብት ንብረቴን ሁሉ አውርሱት በባሪያዎቼ ላይ ሁሉ አዛዥ ይሁን እኔ ቶሎ አልመለስምና አትጠብቁኝ” የሚል ሆነ፡፡

ያ ጎልማሳም ባሕራንን ሞትህ በሕይወት ቀይሬልሃለሁና አሁን በሰላም ሂድ መልክትህን አድርስ ብሎት ተሰወረው፡፡ ባህራንም እንደ ታዘዘው ለማድረግ ወደ ተላከበት ቤት በተሰጠው ምልክትና አድራሻ መሠረት ገባ እንደገባም ደብዳቤውን አንብበው ደስ አላቸውና ድል ያለ ሠርግ ሠርገው የባለጸጋውን አንዲት ልጃገረድ ልጁን በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በሥርዓተ ተክሊል አጋቡት ሀብቱን ሁሉ አወረሱት በንብረቱ ሁሉ አዛዥ ናዛዥ ሆነ፡፡

አርባ ቀን ሙሉ ሲጨፈር ሲበላ ሲጠጣ ያ ባለ ጸጋ ከሄደበት ተመልሶ ወደ መንደሩ ሲቀርብ የከበሮ፣የእልልታ፣ የዝማሬ እንዲሁም ባህላዊ ሽለላ ይሰማና ምንድን ነው የምሰማው ብሎ ይጠይቃል፡፡ ደብዳቤ ጽፈህ ልጄን ዳሩለት ሀባቴንም አውርሱት ብለህ የላከው ልጅ እንዳዘዝከው ተድሮ ሀብትህን ሁሉ ወርሶ ይኸው ሲበላ ሲጠጣ ሲጨፈር ዛሬ አርባ ቀን ሞላው ብለው ነገሩት፡፡ እርሱም ደንግጦ ከፈረሱ ወድቆ በድንጋጤ ሞተ፡፡


@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#አባ_ገሪማ (ይስሐቅ) መደራ

#ሰኔ_17

አቡነ ገሪማ የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሮም ውስጥ ነው። ወላጆቻቸው መስፍንያኖስና ሰፍንግያ እግዚአብሔርን የሚወዱ የሮም ከተማ ንጉሥና ንግሥት ነበሩ። ልጅ በማጣታቸው እመቤታችንን ለመኑ።

እመ ብርሃንም ደግ ፍሬ ሰጠቻቸው። ስሙን ይስሐቅ ብለው አሳደጉት። ገና በልጅነቱ አባቱ ድንገት በመሞቱ ይስሐቅ በዙፋኑ ተተክቶ ነገሠ። ለ7 ዓመታት ሕዝቡን በፍትሕ እያስተዳደረ መጻሕፍትንም እያጠና ኑሯል።

አንድ ቀን ግን ከግብፅ በርሃ የተላከ ደብዳቤ ደረሰው። ላኪው አባ_ዸንጠሌዎን ሲሆኑ መልዕክቱ "ምድራዊ ንግሥና ምን ያደርግልሃል? ይልቁኑስ በሰማይ ለዘለዓለም እንድትነግሥ ወደ በርሃ ና" የሚል ነበር።

ንጉሥ ይስሐቅ አላመነታም ሌሊት ተነስቶ ወደ ፈጣሪው ጸልዮ በለበሳት ልብስ ብቻ ዙፋኑን ጥሎ መነነ። ድንገት ግን ቅዱስ_ገብርኤል ደርሶ በቀኝ ክንፉ ነጥቆ ግብፅ አባ ዸንጠሌዎን በዓት ላይ አኖረው።

እርሳቸውም ተቀብለው ፍኖተ አበውን አስተምረው አመነኮሱትና ዘጠኝ ሁነው ወደ ኢትዮዽያ መጡ። ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ብዙ ሲሰሩ አንዱና ታላቁ አባ ይስሐቅ (ገሪማ) ናቸው። ሰውነታቸውን በገድል ቀጥቅጠውት ቆዳና አጥንታቸው ተጣብቆ ነበር።

አንድ ቀን አባ ይስሐቅ በልቶ ቀደሰ ብለው ነግረዋቸው አባ ዸንጠሌዎን አዘኑ። ልምከር ብለው "ልጄ ይስሐቅ የሰማውብህ ነገር አለና ሰዎችን አርቅልኝ" አሉ። አባ ይስሐቅ ግን "ሰዎች ብቻ አይደሉም ዛፉም እንጨቱም ገለል ይበል" ቢሉ የቤተ ክርስቲያኑ አጸድ አንድ ምዕራፍ (800 ሜትር) ተጠራርጎ ሸሸ።

ይሕንን የተመለከቱት አባ ዸንጠሌዎን "ወልድየ_ይስሐቅ_ገረምከኒ (ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ) አሏቸው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮም "አቡነ_ገሪማ" ተብለው ቀሩ፡፡

አቡነ ገሪማ ወደ መደራ ሲሔዱ እነዚያ የሸሹ ዛፍና ድንጋዮች "ገሪማ ለእኛም ግሩም ነህ" እያሉ በዝማሬ ተከትለዋቸዋል።

ጻድቁ ወንጌልን ገዳማትን ከማስፋፋት ባለፈ ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል፦

1.ስንዴ ጠዋት ዘርተውት በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር "በጽባሕ ይዘርዕ ወበሠርክ የአርር" እንዲል።
2.ጧት የተከሉት ወይን በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር።
3.አንድ ቀን ምራቃቸው ቢወድቅ ጸበል ሆኖ ዛሬም አለ።
4.ብዕራቸው ወድቃ አብባ አፍርታለች።
5.አንድ ቀን ድርሳን እየደረሱ ሊመሽ በመሆኑ ፀሐይን አቁመዋታል።

ከእነዚህ ሁሉ ዘመናት በኋላ ጌታችን ተገልጦ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ሰጣቸው። "ስምሕን የጠራ መታሰቢያህን ያደረገ እስከ 12 ትውልድ እምርልሃለሁ። አንተ ግን ሞትን አትቀምስም" ብሏቸው ተሰወረ። ያን ጊዜ መላእክቱ በሠረገላ ጭነው እየዘመሩ ብሔረ_ሕያዋን አድርሰዋቸዋል፡፡

dn_yordanos ✍🏻✍🏻✍🏻

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#ላንተ_ከሰጠሁህ_ትጠፋለህ!

ሁለት ሰዎች በአንድ ጉዳይ አብረው ይጸልያሉ። አንደኛው ጸሎቱ ተመለሰለት፣ አንደኛው ሳይመለስለት ቀረ። በዚህ ጊዜ ጸሎቱ ያልተመለሰለት፡- “ጌታ ሆይ ሁለታችንም እኩል ጸለይን ለእርሱ ሰጥተኸው ለእኔ የከለከልከኝ ለምንድን ነው?” አለው። እግዚአብሔርም፡- “ለእርሱ ባልሰጠው ይጠፋል፣ ላንተ ከሰጠሁህ ትጠፋለህ” አለው።

እግዚአብሔር ከራሳችን በላይ እኛን ያውቀናል። ለአንዳችን በመስጠት፣ አንዳችንን በመከልከል ዕድሜያችንን ያረዝመዋል። መስጠቱም መንሣቱም ሁለቱም ለፍቅር ነውና ስለሆነልን ስለሚሆንልንና ስላልሆነልን ነገር ሁሉ ተመስገን ማለትን አንርሳ፡፡

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም (ህንጸተ ቤተክርስቲያን)

ሰኔ ሃያ አንድ በዚች ዕለት የአዳምና የዘሩ ድኅነት የተደረገባት አምላክን የወለደች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የታላቁ በዓል መታሰቢያና በዓለም ሁሉ የቤተ ክርስቲያን መታነፅ መታሰቢያ ነው። ከሁሉ አስቀድሞ ያቺ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያት ዘመን ብቻዋን ታነፀች።

ይኸውም ጳውሎስና በርናባስ በአሕዛብ ውስጥ በሰበኩ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ከሰዎች ቤቶች በቀር ቅዱስ ቊርባንን የሚቀበሉበት ቤተ ክርስቲያንም አልነበራቸውም ነበር። ስለዚህም ወደ ጴጥሮስና ወደ ሐዋርያት ሁሉ ስለ ቤተ ክርስቲያን መታነፅ ጉዳይ እየለመኑ መልእክትን ላኩ።

ሐዋርያትም እንዲህ ብለው መለሱላቸው ክብር ይግባውና ያለ ጌታችን ፈቃድ እኛ ምንም ምን አንሠራም። ነገር ግን የምንሠራውን እስኪያስረዳን ድረስ ወደ እግዚአብሔር እየጸለዩና እየማለዱ አንድ ሱባኤ ይጾሙ ዘንድ ወደ ሃይማኖት የተመለሱ አሕዛብን እዘዙአቸው እንዲህም አዘዙአቸው።

በሱባዔውም ፍጻሜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጸላቸው ሐዋርያትንም ሁሉ ከየአገሮች ሁሉ እስከ ፊልጵስዮስ በደመና ሰበሰባቸው ከእርሳቸውም ጋር ጳውሎስና በርናባስ ነበሩ ጌታችንም ባረካቸው እንዲህም ብሎ ነገራቸው "ይቺ ዕለት በእናቴ በማርያም ስም በአራቱ ማእዘነ ዓለም አብያተ ክርስቲያናት እንድታንፁ የፈቀድኩባት ናት።"

ይህንንም ብሎ ከከተማዋ በስተ ምሥራቅ በኲል አወጣቸው የቤተ ክርስቲያኒቱንም ቦታና መሠረቷን ወሰነላቸው ከእርሳቸውም ጋራ የእግዚአብሔር ኃይል ነበረ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃዋ እስከ ተፈፀመ ድረስ ደንጊያዎች በሐዋርያት እጆች ውስጥ ይለመልሙ ነበረ ጌታችንም ነዋየ ቅድሳቷን አልባሳትዋንና መሠዊያዋን አዘጋጀ።

ከዚህ በኋላ ጌታችን እጁን በጴጥሮስ ራስ ላይ ጭኖ በአራቱ ማእዘነ ዓለም ውስጥ "አርሳይሮስ" ብሎ ሾመው ይህም "ሊቀ ጳጳሳት" ማለት ነው። ለሐዋርያት አለቃ ጴጥሮስ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የጳጳሳት አለቃ ይሆን ዘንድ ይገባዋል ይገባዋል ይገባዋል እያሉ ሰማያውያን መላእክትና ምድራውያን ሰዎች ሦስት ጊዜ አሰምተው ተናገሩ።

ከዚህም በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን የቊርባኑን ቅዳሴ ሥርዓት ያከናውኑ ዘንድ ለሕዝቡም ሥጋውን ደሙን ያቀብሏቸው ዘንድ አዘዛቸው እንዲህም የሚል አለ ራሱ መድኃኒታችን ቀድሶ ሥጋውንና ደሙን ለሐዋርያት አቀበላቸው። እንዲህም አላቸው በዚች ቀን የእጃቸውን ሥራ እንዳይሠሩ ሕዝቡን ሁሉ እዘዙአቸው ይኸውም በሰኔ ወር ሃያ አንድ ቀን ነው።

ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን ከእርሳቸው ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። ከዚያችም ቀን ጀመሮ አባቶቻችን ሐዋርያት በዓለሙ ሁሉ ውስጥ አምላክን በወለደች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን የሚያሳንፁ ሆኑ።

በቂሣርያው ሊቀ ጳጳሳት በባስልዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን በሠራ ጊዜ በውስጡ የእመቤታችን የማርያምን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ሠሌዳ ፈለገ ሰዎችም በአንድ ባለጸጋ ዘንድ ስለ አለ አንድ መልካም ሠሌዳ ነገሩት።

ቅዱስ ባስልዮስም ሠሌዳውን እንዲሰጠው ወደ ባለጸጋው ላከ ባለጸጋውም ይህ ሠሌዳ ለልጆቼ ነው አለ እንጂ ፈቃደኛ አልሆነም። ከዚያም አልፎ በመድፈር በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብ ቃል ተናገረ ወዲያውኑም በድንገት ወድቆ ሞተ ልጆቹም ፈሩ ያንንም ሠሌዳ ከብዙ ወርቅና እንቊ ጋራ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ አምጥተው የአባታቸውን በደል ያቃልልለት ዘንድ ለመኑት።

ቅዱስ ባስልዮስም ያንን ሠሌዳ ወስዶ የእመቤታችንን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ለሠዓሊ ሰጠው። እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም በሌሊት ራእይ ለቅዱስ ባስልዮስ ተገለጸችለት ሥዕሏንም በዚያ ሠሌዳ ላይ እንዳይሥል ከለከለችው። ከዐመፀኛ ሰው እጅ ወስዶታልና። እጅግም ያማረ የእመቤታችን ሥዕሏ የተሣለበት የሁለት ደናግልም ሥዕል ያንዲቱ በቀኝ ያንዲቱ በግራ ሆኖ የተሣለበት ቀይ ሠሌዳ ያለበትን ቦታ ነገረችው።

ቅዱስ ባስልዮስም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ አመለከተችው ወደዚያ ቦታ ሔደ ያንንም ሠሌዳ አገኘው ወደዚያች ቤተ ክርስቲያንም በታላቅ ደስታ አመጣው።

ከዚህም በኋላ ዳግመኛ በአንድ ጣዖት ቤት ሁለት ምሰሶዎች እንዳሉ አስረዳቸው እነርሱንም አምጥቶ በመቅደሱ ፊት ለፊት እንዲአቆማቸው በላያቸውም ሥዕሏን እንዲያኖር አዘዘችው።

ቅዱስ ባስልዮስም እነዚያን ምሰሶዎች ያመጣቸው ዘንድ ሔደ መሠርያኑም ሊከለክሉት ፈለጉ ጌታችንም ኃይላቸውን ደመሰሰ እነዚያንም ምሰሶዎች አምጥቶ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው በላያቸውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕሏን አስቀመጠ እግዚአብሔርም ከእነዚያ ምሰሶዎች በታች የውኃ ምንጭ አፈለቀ በውስጥዋም የሚታጠብ ሁሉ ከአለበት ደዌ ሁሉ የሚድን ሆነ።

እንዲሁም ከእመቤታችን ማርያም ሥዕል በሽተኞችን ሁሉ የሚፈውስ የዘይት ቅባት ፈሰሰ ይህ ሁሉ የሆነ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በከበረችበት በሰኔ ወር በሃያ አንድ ቀን ነው።

በዚያችም ቀን እንዲህ ሆነ አንዲት ሴት መጥታ ታጠበች ወዲያውኑም ሁለመናዋ በለምጽ ተሸፈነ ቅዱስ ባስልዮስም ወደርሱ አስቀርቦ በእርሷ ላይ የሆነውን ጠየቃት እርሷም የእኅቷን ባል እንደወደደችና እኅቷን በመርዝ ገድላ እንዳገባችው ነገረችው። ቅዱስ ባስልዮስም ታላላቅ ሦስት ኃጢአቶችን ሠራሽ ግን ወደ እግዚአብሔር ንስሐ ግቢ ምንአልባት በደልሽን ይቅር ይልሽ እንደ ሆነ አላት በዚያን ጊዜም ምድር ተሠንጥቃ እንደ ዳታን ዋጠቻት እርሷ የረከሰች ስትሆን ወደ ቤተ ክርስቲያን መግባትን ደፍራለችና።

እኛ ሁላችን የክርስቲያን ወገኖች አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለከበረች ድንግል ማርያም ለመታሰቢያዋ መንፈሳዊ በዓልን ልናደርግ ይገባናል ሰለ እርሷ ለአዳምና ለሁላችን ለልጆቹ ድኅነት ሆኖአልና ይህንንም በዓል ለማድረግ የሚተጋ የተመሰገነ ነው።

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#መጥምቀ_መለኮት_ቅዱስ_ዮሐንስ

#ሰኔ_30

ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ


ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ። ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለፈልደ እግዚአብሔር የሰገደው ነው። ይህም በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው። በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጐረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው።

በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን አይሆንም ዮሐንስ ይባል አለች። ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም አሏት። አባቱንም ጠቅሰው ማን ሊባል ትወዳለህ አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ይባል ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ።

ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንዲገድሉትም ጭፍሮችን ላከ ጭፍሮችም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ከእርሱ ፈለጉት አባቱም አንሥቶ በትከሻዎቹ ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ ከእርሱ ጋራ እንዲሔዱና ሕፃኑን ከዚያ እንዲወስዱት ወታደሮችን ለመናቸው።

ከዚህም በኋላ ሕፃኑን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረውና ከዚህ ራሳችሁ ተቀብላችሁ ውሰዱት አላቸው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው። ጭፍሮችም ባላገኙት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ።

የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እነሆ ብሎ ኢሳይያስ የተናገረለት ይህ ነው። ሚልክያስም ስለሱ እንዲህ አለ። በፊትህ ጐዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልእክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ።

ራሱ መድኃኒታችንም ስለርሱ ሲናገር ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም ብሏል። ይህ የእግዚአብሔርን ልጅ በአጠመቀውና የማትዳሠሥ ራሱን በዳሠሠው ጊዜ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና።

ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ። እኛም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ፡፡

#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#ምላስ

“የማይቆጣጠሯትን ምላስ ያህል መጥፎ ጾር የለም፤ እርሷ የፈተናዎች ሁሉ እናት ናት፡፡”

#አባ_አጋቶን

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#ብርሃናተ_ዓለም_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ!!!!

ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በጐልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሣ ማሥገር ጀመረ፡፡ ለደቀመዛሙርትነት ሲመረጥ እድሜው 55 ዓመት ሲሆን ወደጌታችን ያመጣውም ወንድሙ እንድርያስ ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲጠራ መተዳደሪያው የነበረውን መረቡን ታንኳውን እንዲህም አባቱን ትቶ ጌታውን የተከተለ ሐዋርያ ነው፡፡ በቂሳርያ ከተማ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ በጠየቀ ጊዜ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ ለአይሁድ ሊቃውንት የተሰወረ ምሥጢረ ተዋሕዶ ገልጦ በመመስከሩ ጌታችን አንተ ጴጥሮስ ነህ ብሎታል ይህን በጽርዕ ቋንቋ "ዐለት" ማለት ነው በአረማይክ ደግሞ ኬፋ ይባላል፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን ይወድ ነበር፡፡ ፍቅሩ ግን ቅንዓት የተቀላቀለ በመሆኑ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ የሞቱን ነገር ቀድሞ ሲነግራቸው አይሁንብህ በማለት ተከራክሯል፡፡ ማቴ 16፥23 በኋላም ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም ብሎ በራሱ ቅንዓት ተማምኖ ተናግሮ ነበር፡፡ ጌታችን ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው እንኳን ከአንተ ጋር መሞት እንኳ የሚያስፈልገኝ ቢሆን ከቶ አልክድህም በማለት የተናገረ ሐዋርያ ነው፡፡ ማቴዎስ 26፥34 ነገር ግን 3 ጊዜ ጌታችንን አላውቀውም ብሎ ካደ፤ ዶሮ በጮኸና አምላኩን መበደሉን እንዳወቀ ከግቢው ወጥቶ አለቀሰ ንስሐ ገባ፡፡

ጴጥሮስ በዕድሜው ታላቅነት በሐዋርያት ዘንድ እንደ አባት ይታይ ስለነበር ጌታ በተለየው ጊዘ? ሐዋርያቱን ሊመግብ ወደሚያውቀው ሙያ ዓሣ ወደማስገሩ ተሠማራ ጌታም አስቀድሞ የመረጠው እርሱ ነውና ቢከዳው እንኳን በንስሐ በመመለሱ ንስሐውን መቀበሉን ዛሬም እንደሚወደው ይገልጽለƒም ዘንድ በጥብርያዶስ ባሕር ተገለጠለት፡፡ ሦስት ጊዜ ክዶት ነበርና ቀኖና ሰጠው፡፡ አሁን ቅዱስ ጴጥሮስ በራስ መተማመኑ እንዳላዋጣው አውቆ ትወደኛለህ ተብሎ ሲጠየቅ አንተ ታውቃለህ ነበረ መልሱ የራሱ እውቀት የት እንዳደረሰው ያውቃልና ጌታችንም ኀዳጌ በቀል /በቀልን የሚተው/ ነውና ዛሬም እንደሚወደው በንሰሐ ተመልሷልና ዛሬም ለእርሱ የሰጠውን ክብር እንደማያጐልበት ሲነግረው ግልገሎቼን አሠማራ ጠቦቶቼን ጠብቅ በጐቼን አሠማራ በማለት አደራውን አስረከበው፡፡ ዮሐንስ 21፥15-17

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ዘመን ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ስለነበረ በአይሁድ ሸንጐ አባልነት ለ2 ዓመታት በሠራበት ወቅት እምነቱ ቀናተኛ ፈሪሳዊ በመኾኑ ክርስቲያኖችን በማናቸውም አጋጣማ> ይቃወም ነበር፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ ተወግሮ በሰማዕትነት ሲያርፍም የወጋሪዎችን ልብe ይጠብቅ የነበረው እርሱ ነው፡፡

በ32 ዓመት ዕድሜው ከኢየሩሳሌም 223 ኪ.ሜ ርቀት በስተሰሜን በኩል በምትገኘው የደማስቆ ከተማ ብዙ ክርስቲያኖች መኖራቸውን ሲሰማ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቀርቦ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የሚያስችKውን የፈቃድ ደብዳቤ ጠይቆ ካገኘ በኋላ ጭፍሮችን አስከትሎ ወደ ደማስቆ አመራ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ከተማዋ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረው ነበር ከሰማይ የወረደው ብርሃን አካባቢውን ያለበሰውና ሳዖል፥ ሳዖል ስለምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ የሰማው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስም ጌታ ሆይ ማን ነህ? ብሎ ጠየቀ የምታሳድደኝ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል ሲል መድኀኒታችን ተናገረው፡፡ ያንን በወደቀበት ሆኖ እየተንቀጠቀጠ ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ ሲል ጠየቀው ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ወደ ደማስቆ እንዲገባ ተነገረው፡፡ ሐዋርያት 9፥1

የሐዋርያው ዓይኖች ለማየት አልቻሉም፡፡ እየተመራ ወደ ደማስቆ ገባ ለ3 ቀናት ያህልም እህል ሳይቀምስ ቆየ በዚያች ዕለት እግዚአብሔር አምላክ በደማስቆ ለሚገኘው እና ሐናንያ ለተባለው አባት በራዕይ ተገለጠለት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ያለበትን አድራሻ ነገረውና እንዲያጠምቀው አዘዘው፡፡ ሐናንያ አስቀድሞ የቅዱስ ጳውሎስን ማንነት ያውቃል፡፡ አብዛኞቹ በደማስቆ የሚገኙት ክርስቲያኖች ከኢየሩሳሌም በስደት ጊዜ የመጡ ናቸው፡፡ ያን ስደት ያስነሳው ደግሞ በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ የደረሰው መከራ ነው፡፡ በዚህ በቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማዕትነት ደግሞ ዋናው ተዋናይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ነበርና ነው፡፡

ሐናንያ ቅዱስ ጳውሎስን ካጠመቀውና ካስተማረውም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ዓረብ ሐገር መሄዱን :: ለሦስት ዓመታት በዓረቢያ በረሃ ከቆየ በኋላ ወደ ደማስቆ ከተማ ተመለሰ፡፡ በዚያም በነበሩ አይሁድ መካከል በፊት ያሳድደው የነበረውን ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ጀመረ፡፡ ከዚያ በፊት በፈሪሳዊነቱና ለአይሁድ ሕግ በነበረው ቅንዓት የሚታወቀው ጳውሎስ ዛሬ ወንጌል ሲሰብክ በማየታቸው አይሁድ ተነሡበት፡፡ በዚያም የተነሣ የደማስቆ ክርስቲያኖች በቅርጫት አውርደው ወደ ኢየሩሳሌም ላኩት፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ አይሁድ ጳውሎስን እንደሚያውቁት እና እንደለመዱት ሆኖ ስላላገኙት ሊገድሉት ተነሱ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ክርስቲያኖች የቅዱስ ጳውሎስን መመለስ ሊያምኑ አልቻሉም፡፡ በመጨረሻ ግን በርናባስ ወደ ሐዋርያት ዘንድ ወስዶ የጳውሎስን መመለስ በመተረክ እንዲያምኑት አደረጋቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም በድፍረት በማስተማሩ አይሁድ ስለተቃወሙት ከተማዋን ትቶ በቂሳርያ በኩል ወደ ትውልድ ሐገሩ ጠርሴስ ተመለሰ፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በጠርሴስ ከተማ ለ9 ዓመታት ቆይቷል፡፡ ከኢየሩሳሌም ውጭ የአሕዛብ ከተማ በነበረችው በአንጾኪያ የክርስትና ሃይማኖት ተስፋፋ፡፡ ከዚህም በኋላ ሐዋርያው ሦስት ታላላቅ ሐዋርያዊ ጉዞዎችን አድርጓል፡፡ በመጀመሪያው ጉዞው ወደ 2,ዐዐዐ ኪ.ሜ የሚደርስ መንገድ በእግር ተጉዟል፤ ይህም የተከናወነው በ46 ዓ.ም. ነው፡፡ በሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ከ18 በላይ ከተሞችን ሸፍኗል፤ ጉዞውም በ5ዐ ዓ.ም. የተደረገ ነው፡፡ በሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ከ2ዐ በላይ ከተሞችን ሸፍኗል፤ ጉዞውም በ54 ዓ.ም. የተደረገ ነው፡፡ ብዙም ጊዜ በቁም እሥር በብዙም መከራ ሥቃይ እንግልት ያሳለፈ ታላቅ ሐዋርያ ነው፡፡

...#ረፍታቸው

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጴጥሮስ ከእዚያም እግዚአብሔር በሞቱ እንደሚያከብረው ነግሮት ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም አደባባይ በጨካኙ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት ቁልቁል (እንደ አምላኬ አልሰቀልም ብሎ) በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም. በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡

#ሐዋርያው_ቅዱስ ጳውሎስ ለ 2 ዓመት ከ6 ወር በጨለማ ቤት ታሥሮ ከቆየ በኋላ በ74 ዓመት ዕድሜው በሮም ከተማ በኦስትያ መንገድ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት አንገቱን በሠይፍ ተሠይፎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም. በሰማዕትነት አረፈ፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ ረድኤት በረከታቸው ይክፈለን፤ አሜን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#ነሐሴ_6

ነሐሴ ስድስት በዚህች ቀን ጌታችን ሰባት አጋንንትን ከእርሷ ያወጣላት የከበረች
#ቅድስት_መግደላዊት ማርያም አረፈች!

#ቅድስት_መግደላዊት_ማርያም

ነሐሴ ስድስት በዚህች ቀን ጌታችን ሰባት አጋንንትን ከእርሷ ያወጣላት የከበረች መግደላዊት ማርያም አረፈች። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስን ተከትላ ያገለገለችው በመከራውም ጊዜ ከባልንጀሮቿ ጋራ የነበረች እስከ ቀበሩትም ድረስ ያልተለየች እናት ነች።

በእሑድ ሰንበትም ገና ጨለማ ሳለ በማለዳ ማርያም ወደ መቃብር ገሥግሣ ሔደች ደንጊያውንም ከመቃብሩ አፍ ተገለባብጦ መልአክም በላዩ ተቀምጦ አየችው ከእርሷም ጋራ ጓደኛዋ ማርያም አለች። መልአኩም እናንተስ አትፍሩ ጌታ ኢየሱስን እንድትሹት አውቃለሁና ግን ከዚህ የለም እነሣለሁ እንዳለ ተነሥቷል አላቸው ።

ለእርሷም ዳግመኛ ተገልጾላት ሒደሽ ለወንድሞቼ እኔ ወደ አባቴ ወደ አባቴታችሁ ወደ አምላኬ ወደ አምላካችሁ እንደማርግ ንገሪያቸው አላት። ወደ ሐዋርያትም መጥታ የመድኃኒታችንን መነሣቱን እንዳየችውና ንገሪ እንዳላትም አበሠረቻቸው።

ከዕርገቱም በኋላ ሐዋርያትን እያገለገለቻቸው ኖረች። በኃምሳኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ በወንዶችና በሴቶች አገልጋዮቼ ላይ ቅዱስ መንፈሴን አሳድራለሁ አለ ብሎ ኢዩኤል ትንቢት እንደ ተናገረ ያንን አጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ከሐዋርያት ጋር ተቀብላለች።

ከዚህም በኋላ ከሐዋርያት ጋራ ወንጌልን ሰበከች ብዙዎች ሴቶችንም የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት መልሳ አስገባቻቸው። ሴቶችን ስለ ማስተማርም ሐዋርያት ዲያቆናዊት አድርገው ሾሟት ከአይሁድም በመገረፍ በመጐሳቈል ብዙ መከራ ደረሰባት። ተጋድሎዋንም ፈጽማ በሰላም በፍቅር አረፈች።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ እና #ከገድላት_አንደበት)

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721
#ሐምሌ_19

ሐምሌ ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሕፃኑ
#ቅዱስ_ቂርቆስ እና #እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ ተቀበሉ!!

#ቅዱስ_ቂርቆስና_እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ

ሐምሌ ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ ተቀበሉ። ይህም ሕፃን ዕድሜው ሦስት ዓመት ሲሆነው ከሮሜ አገር ወደሌላ ሀገር እናቱ ይዛው ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኰንን አገኘችው።

ሰዎችም ነገር ሠሩባት ወደርሱ አስቀረባትና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኰንን ሆይ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው።

ሕፃኑም ወደአለበት ጭፍራውን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው። ሕፃኑም መልሶ አዎ ለእኔ ደስታ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ኀዘንና ልቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው መጽሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና አለው እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስከ አስደነገጣቸው ድረስ ንጉሡን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሣ አደነቁ።

መኰንኑም በአፈረ ጊዜ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ሥቃይን አሠቃየው እናቱንም ከርሱ ጋር እንደ እርሱ አሠቃያት እግዚአብሔርም ያለምንም ጉዳት ያነሣቸው ነበር። ብዙዎች አሕዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማዕትነት ሞቱ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ።

በሕፃኑ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት። ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው።

ከዚህም በኋላ መኰንኑ በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውኃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ሆነ ያን ጊዜም ፍርሀትና የሃይማኖት ጉድለት በእናቱ ላይ ደረሰባት ሕፃኑም ስለ እናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።

ያን ጊዜ ጌታችን ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አየች ከዚህም በኋላ ጸናች እግዚአብሔርንም አመሰገነችው ልጅዋንም ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አንተ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ አለችው።

ያቺ ከኔ የተወለድክባትም ቀን የተባረከች ናት አለች ወደዚያ ወደ ጋኑ ውስጥ በገቡ ጊዜም የውኃው ፍልሐት እንደ ንጋት ጊዜ ውርጭ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና።

ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው እንዲጐትቷቸው አዘዘ ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ አዳናቸው መኰንኑም በታላቅ ሥቃይ ያሠቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው።

ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕፃኑ ቂርቆስ ወርዶ አጽናናው አረጋጋውም። ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#እኔ_ግን_ኢትዮጵያዊ_ነኝ!!!!

ሐምሌ 22

አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ፡፡ መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት። ቀጥለውም በያዙት መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ፡፡ የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ከተቱት፡፡ ወዲያው ወታደሮቸ በሩምታ ተኩሰው ገደሏቸው፡፡ ይህ እንደሆነ አስገዳዩ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ። ማታ ከአስገዳዩ ኮሎኔል ጋር ተገናኝተን ስንጫወት በዚህ ቄስ መገደል እኮ ሕዝቡ ተደስቷል አለኝ፡፡ እንዴት?ብለው አላየህም ሲያጨበጭብ? አለኝ፡፡ ባታውቀው ነው እንጂ የሕዝቡ ባሕል ሲናደድም ያጨበጭባል አልኩት፡፡ እንዴት? ቢለኝ እጄን አጨብጭቤ አሳየሁት፡፡"

አቡነ ጴጥሮስ ሲገደሉ በቦታው ሆነው የተከታተሉት
#ሙሴ_ፓይላክን የተባሉ ግለሰብ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ለጳውሎስ ኞኞ ከነገሩት የተወሰደ፡፡

ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም መንፈስ ቅዱስ የቀረባቸው የኢትዮጵያ የኃይማኖት አባት እና የነፃነት አርበኛው ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ በፋሺስት ኢጣሊያ ወታደሮች በጥይት ተደብድበው የተገደሉበት ሰማዕትነትንም የተቀበሉበት ድንቅ እና እጅጉን የከበረች ዕለት ናት።

እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ። ኃላፊነትም ያለብኝ የቤተ ክርስቲያን አባት ነኝ። ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ። ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም። ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ። እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ አውቃለሁ። ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ። ግን ተከታዮቼን አትንኩ።

#ቅዱስ_ሰማዕት_አቡነ_ጴጥሮስ

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721
#የአንድ_ሰው_ውሎና_አመሻሽ!

ይህ እስካሁን ምንጩን ያላገኘሁት አንድ ወንድሜ የላከልኝ በፈረንጅ አፍ የተጻፈ የቆየ የአንድ ሰው ገጠመኝ ነው፦

አንድ ወንድም ስልኩን ድምፅ አልባ ማድረግ ረስቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ስብከት ይማራል:: በዚህ መካከል ስልኩ ይጮኃል::

ሰባኪው ስብከቱን አቁሞ በዓይኖቹ ተቆጣው:: ከስብከቱ በኋላ ምእመናን ስብከቱን በመረበሹ ወቀሱት:: አንዳንዶቹም እያዩት ራሳቸውን በትዝብት ነቀነቁ:: ከሚስቱ ጋር ወደ ቤታቸው ሲሔዱም ሚስቱ ስለ ቸልተኝነቱ ምክር መሥጠትዋን ቀጠለች:: እፍረት መሸማቀቅና ውርደት ዘልቆ እንደተሰማው በፊቱ ላይ ይታይ ነበር:: ከዚያች ሰንበት በኋላ እግሩን ወደ ቤተ ክርስቲያን አንሥቶ አያውቅም::

ውስጡ የተረበሸው ይህ ሰው ያንኑ ምሽት ወደ መጠጥ ቤት አመራ:: አእምሮው እንደታወከ ነበር::

ቁጭ ባለበት ድንገት የሚጠጣበት ጠርሙስ ወድቆ ተሰበረና መጠጡም በዙሪያ ተረጨ:: ፍንጣሪው የነካቸው ሰዎች ወደ እሱ መጠጋት ጀመሩ:: ሊጮኹበትና በጥፊ ሊሉት እንደሆነ ታውቆት ቀድሞ ዓይኖቹን ጨፈነ::

ሰዎቹ ግን በተሰበረው ጠርሙስ ስብርባሪ ተጎድቶ እንደሆነ ተጨንቀው ጠየቁት::

አስተናጋጁ መጥቶ የፈሰሰበትን እንዲያደርቅ ማበሻ ሰጠው:: የጽዳት ሠራተኛዋ መሬቱን ወለወለች::

የቤቱ ባለቤት "አይዞህ ያጋጥማል? ዕቃ የማይሰብር ማን አለና?" አለችውና ሌላ መጠጥ አስመጣችለት:: ከዚያች ቀን ጀምሮ ከዚያ መጠጥ ቤት ቀርቶ አያውቅም::

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስልክን ክፍት ማድረግና ሥርዓተ አምልኮ መረበሽ መቅደስ ውስጥ ጫማ አድርጎ የመግባት ያህል ስኅተት ነው:: እንኩዋን ቤተ ክርስቲያን ኤምባሲ እንኩዋን ስልክህን ውጪ አስቀምጠህ ትገባለህ:: ሰውዬው ላጠፋው ጥፋት ግን በፍቅር የሚያናግረው ሰው በማጣቱ ከነ ስልኩ ሊጠፋ ወሰነ::

ቤተ ክርስቲያን የድኅነት ሥፍራ ናት:: መጠጥ ቤት ደግሞ የጥፋት ጎዳና ነው:: በዚህ ሰው ታሪክ ውስጥ ግን በድኅነት ሥፍራ ካሉ ሰዎች ይልቅ በጥፋት ሥፍራ ያሉ ሰዎች ለሰውዬው ስኅተት የተሻለ ፍቅር አሳዩ:: አንዳንዴ የአንዳንድ ምእመናን ጠባይ ነፍሳትን ወደ ሲኦል ይሰድዳል::

አንዳችን የአንዳችን ጠባቂ መሆን እንችላለን ዓለምን ለመፈወስ የሚቻለንን እናድርግ:: ነፍሳትን ከማዳን ነፍሳትን ማጥፋት በጣም ቀላል ነው::

መድኃኔዓለም ክርስቶስ የኃጢአተኞች ወዳጅ ነበረ:: እሱ የማንንም ቅስም በክፉ ቃል አልሰበረም:: እኛ ግን ሰው ላይ ስንጨክን መጠን የለንም:: በዚህ ምክንያት እንደ ኒቼ ያሉ ሰዎች "ብቸኛው ክርስቲያን መስቀል ላይ የሞተው ነው" ብለው እስኪዘብቱብን ደርሰዋል::

መጽሐፍ ግን ሰው ሲሳሳት ስናይ ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲህ ሲል ይናገራል፦

"ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት" ገላትያ 6፥1

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሐምሌ 26 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

@Amon0721
@Amon0721
@Amon0721

#ለተጨማሪhttps://t.me/Amon_0721