Amleset Muchie
1.17K subscribers
410 photos
11 videos
79 links
She is the winner of titles Miss University 2004, Miss World Ethiopia 2006, she is an actress, a model, film director and writer. she Studied film making at New York Film Academy and Journalisme at uuc.
Download Telegram
አርማሽ

አርማሽ የተሰኘው የአንጋፉውና የተወዳጁ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ሙዚቃ በአርቲስቱ ህጋዊ የዩትዩብ ቻናል ከተለቀቀ ዛሬ ህዳር 23 ቀን /2014 ዓ.ም አንድ ወር ሞላው። ይኽ ሙዚቃ ከተለቀቀበት ቅጽበት ጀምሮ በህዝብ ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትን ማግኘት የቻለ በመሆኑ በአርቲስቱ በኩል ሊኖር የሚችል ማንኛውም አይነት ግምት ግቡን የመታ እንደሆነ አልጠራጠርም።

አገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ በፍጥነት ትላቀቅ ዘንድ ብሎም ህዝባችን ከገባበት አሰልቺና አዝጋሚ ከሆነ የህይወት ግብ ግብ በድል አድራጊነት ይላቀቅ ዘንድ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በዚህ መልኩ የተቀነቀኑ ሙዚቃዎችን ማበርከታቸው እጅጉን መልካም ተግባር ነው። እንዲህ ያሉ ስራዎች የማህበረሰባችንን፣ በአመራር ደረጃ የተቀመጡ የህዝብ አገልጋዮችን፣ በጦር ግንባር ለኢትዮጵያ ክብር የሚዋደቁ ነፍጥ አንጋቢዎችንና በመላው ዓለም የሚገኙ የታላቂቷ ኢትዮጵያ ወዳጆችን ስሜት የሚያነቃና የመፍትሄ አቅጣጫ የሚጠቁም ብቻ ሳይሆን፥ ህዝብ በአንድ ልብ በአንድነት ፀንቶ ከቆመ፤ ሁሉም በተሰማራበት ሙያ ጊዜው የሚፈልገውን ተግባር በኃላፊነት ስሜት ከፈጸመ እንደ ህዝብም እንደ ሀገርም አሸናፊዎች እንደምንሆን አበክሮ የሚመሰክርና የሚያሳስብ ጭምር ነው።

የተለያዩ የአገራችን አርቲስቶች በወቅታዊው የአገራችን ጉዳይ ላይ ብዙ ስራዎችን በመስራት ወደ ህዝብ እያደረሱ የሚገኙ ሲሆን ሌሎችም በተመሳሳይ መልኩ ስራዎቻቸውን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ። የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ከምንም ጊዜው በላይ በዚህ ወቅት ህዝባቸውን የማነቃቃትና በግንባር የሚገኘውን የኢትዮጵያን ሰራዊት በቻሉት መልኩ እየደገፉ በመገኘታቸው ምስጋናዬን ላቀርብላቸው እወዳለሁ። ሁሉም በሙያው ይኼንን ተግባር እንዲፈጽምና የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ በታላቅ አክብሮት ለማሳሰብ እወዳለሁ።

እንደ አገር የተጫነብንን የሴራ ክምር ንደን ዳግም በአባቶቻችን መንፈስ ተሞልተን በአሸናፊነት ስሜት ቀና ብለን ልንቆም ግድ ይለናል። በአባቶቻችን ዘመን ያልተፈጸመ ሽንፈት በኛ ዘመን እንዲፈጸም አንፈቅድም። ምክኒያቱም እኛ የጀግኖቹ ልጆች ነን። እኛ የአሸናፊዎቹ ልጆች ነን። በአንድ ልብ ለማሸነፍ ጥንት አባቶቻችን ያቆዩትን ባንዲራ ከፍ አድርገን ይዘን የቆምን የዚህ ዘመን ሰው ነን።

ለማሸነፍ ተፈጥረናልና እናሸንፋለን። ከአሸናፊዎች ወገን በአሸናፊዎች ምድር ተገኝተናልና እናሸንፋለን!
ዳግም ቀና እንላለን!

#ቀናበል

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
ከባራክ ኦባማ ምርጥ ሙዚቃዎች ውስጥ አንዱ የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ ነው።

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ባራክ ኦባማ ዛሬ ታህሳስ 7/2014 ዓ.ም ከምሽቱ አንድ ሰዓት ገደማ፥ በህጋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ የተለያዩ ሙዚቃዎችን የማዳመጥ ልማድ እንዳላቸው ጠቅሰው በዚህ አመት /በ2021/ ዓለማችን ላይ ከተለቀቁ ሙዚቃዎች መኃል አዳምጠው ከወደዷቸው የሙዚቃ ዝርዝሮች ውስጥ "አርማሽ" የተሰኘው የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ አንዱ እንደሆነ በህጋዊ የፌስቡክ እና የኢንስታግራም ገጻቸው ላይ አጋርተዋል።

በህጋዊ የፌስቡክ እና የኢንስታግራም ገጻቸው የኔ ምርጥ ሙዚቃ ብለው 27 ሙዚቃዎችን ያጋሩ ሲሆን ከነዚህ መኃል በ45 ቀናቶች ውስጥ ብቻ ስድስት ሚሊየን አድማጮችን ያገኘው የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ሙዚቃ በመካተቱ ለኢትዮጵያ የሙዚቃ አፍቃሪያን እና ለመላው የቴዲ አፍሮ አድናቂዎች እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እንወዳለን።

የአገራችን የሙዚቃ ስልት ከዚህም በላይ ልቆ እንዲደመጥ ምኞታችን ነው።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

#አርማሽ
https://youtu.be/PkOstq4GuLk

የሚከተለው ጽሁፍ የ Barack Obama ነው...

I've always enjoyed listening to a wide variety of music, so it’s no surprise that I listened to a little bit of everything this year. I hope you find a new artist or song to add to your own playlist.
https://vm.tiktok.com/ZM8wRUGfp

#ጥቁር_ሰው

ለአገር ክብር ለተዋደቁ የዘመናችን ጀግኖች ምስጋና ይሆን ዘንድና በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖቻችን የገንዘብ ድጋፍና የተለያዩ ቁሶችን ማሰባሰቢያ እንዲሆን ያለመ እንደዚህ አይነት ግዙፍ ኮንሰርት በኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች እንዲዘጋጅ እመኛለሁ! እንደሚደረግም ባለሙሉ ተስፋ ነኝ። ምክኒያቱም እንዲህ አይነት ዝግጅት ሲያዘጋጅ ለክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የመጀመሪያው አይደለም! ይልቁንም የኖረበት ነው።

በኮንሰርቱ ላይ የሶስቱ ነገስታት ስም ይጠራል። /የዳግማዊ አጤ ቴዎድሮስ፣ የዳግማዊ አጤ ምኒልክ እና የቀዳማዊ አጤ ኃይለ ሥላሴ/ እነዚህ ነገስታቶች የኢትዮጵያ ታላቅነት ምንጭ ናቸውና ዳግም በዘመናችን ይታወሳሉ። ይሄ መሆኑ ደግሞ ዛሬም ድረስ የአባቶቻችን ስም ለወገኖቻችን የድጋፍና የጥንካሬ ብሎም የጀግንነት፣ የአንድነትና የአሸናፊነትን መንፈስ በፅኑ የሚያጎናጽፈን መሆኑን ለዓለም የምንመሰክርበት አጋጣሚ ሆኖ ያልፋል። የተጠቀሱት ታላላቅ መንፈሶች በኢትዮጵያ ታላቅነት ለሚኮሩ የድል ዜና ሲሆን ይህችን አገር ለሚጠሏት ደግሞ መራር መርዶ ይሆንባቸዋል።

ኢትዮጵያ የአባቶቻችን አገር ነች እኛም የአባቶችን ልጆች ነንና ተደጋግፈን ማለፍ ያለብንን ሁሉ እናልፋለን። የኛ ኢትዮጵያ ሁሉን አሸንፋ ዳግም በኩራት ትቆማለች።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

https://vm.tiktok.com/ZM8wRUGfp
የእውነት ቃል!

ዐይንህን ለማየት፥ ደምጽህን ለመስማት የሚጓጉ ዕልፍ ወዳጆች ያሉህ አንተ ትከሻዬ ላይ እጅህ አረፈ። ዕልፍ አዕላፍ አገር ወዳድና እውነተኛ የሙዚቃ አፍቃሪያን፦ ያዜምከውን የጥበብ ዜማ ብቻ ሳይሆን የተነፈስካትን አንዳች ቃል ለማዳመጥ የሚመኙልህ አንተን፤ ፊት ለፊትህ ቆሜ ሞገስ ያለውን ድምጽህን ሰማሁ። የምስጋና እና የአክብሮት ቃሎችህን አደመጥኩ። ሩቅ የሚመስል የልጅነት ምኞቴ በተደጋጋሚ ተሳክቷል። ሳታውቀኝ ወድጄህ ስሜን እንድትጠራ መልኬን እንድትለይ ያስቻለኸ ከልቤ ውስጥ ያለው እውነተኛ ፍቅር በመሆኑ እደሰታለሁ። ይኼንንም ሳስብ "መውደድ እንዴት ያለ መታደል ነው?" እላለሁ በልቤ።

ብዙዎች ባንተ ሊያከብሩኝና ሊቀርቡኝ ችለዋል። የኪነጥበብ ባለሙያዎች ሳይቀሩ ላንተ ባለኝ ፍቅር ለኔ ዋጋ መስጠት ችለዋል። አሁን ላለሁበት የህይወት ደረጃና ላለኝ ስብዕና አንተን መከተሌ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። ብዙ ቁምነገረኛ ሰዎችን ባንተ ማትረፍ ችያለሁ። ሰው መውደድ ዋጋ ሊያስከፍል ባይገባም እኔ ግን ብዙ አይቻለሁ። ተሰድቤ፣ ተተችቼ፣ ተገላምጬ እንዲሁም ሊፈጸሙልኝ የሚገባቸው ብዙ ጉዳዮችን እስከማጣት ደርሻለሁ። በስልክ እየደወሉና በውስጥ መስመር ባገኙት አጋጣሚ የዛቻ መልዕክቶችን የሚያደርሱኝ ጥቂቶች አይደሉም። የእነዚህ ነገሮች መደጋገም ግን ላንተ ያለኝን ፍቅር እንድተው አልያም እንድቀንስ ጉልበት አላገኙም። እኔም ብሆን በገጠሙኝ ነገሮች የምቆጭና የምጨነቅ ሳልሆን ይልቁንም ፍቅሬን እየጨመርኩ ባንተ ላይ ያለኝን አቋም እያጠበኩኝ መቀጠል ችያለሁ።

"አይሰለችህም? አይደክምህም? ያንተስ በዛ..." ወዘተ ተብዬ አውቃለሁ። ሰዎች ግን ምን ያህል ሞኞች ናቸው? እንዴት መውደድ ይሰለቻል? እንዴት ፍቅር ያደክማል? እግዚአብሔር የማያልቅ፣ የማይደበዝዝ አድርጎ ካጸናቸው መንፈሶች ዋነኛው ፍቅር መሆኑን እንዴት ልብ ማለት አቃታቸው? ዳሩ ሰው ለመውደድ ካልኩኝ ደከመኝ ያኔ ገና ውስጤን /ነፍሴን/ አመመኝ ነው ቁም ነገሩ። የሰውን ልጅ ለመፍጠር ካሳበበት ጊዜ አንስቶ ሰውን በጽኑ መውደድ ሲወድ የኖረ ቅዱስ እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው። አምላካችን የመዋደድ መንፈስን በልባችን ያሳደረ፣ የፍቅርንም ዋጋ በመስቀል ላይ ከፍ አድርጎ የሰቀለ ነውና ክብሩ አይጉደልበት። የከበረ ምስጋና ዘውትር ይድረሰው።

ለዘመናት በገጠሙህ መልካምም ሆነ ፈታኝ ነገሮች ላይ ያንተን ያህል ተደስቼም አዝኜም አውቃለሁ። የኔና ያንተ ነገር አፍንጫ ሲነካ ዐይን እንደሚያለቅስ አይነት ነው። ጤንነትህ ያሳስበኛል። ያሰብከው እንዲሳካ የዘራኸው እንዲያፈራ ካንተ እኩል እመኛለሁ። እንደ አንድ የኪነጥበብ ሰው ብቻ ሳይሆን ከቤተሰቦቼ አንዱ የሆንክ ያህል ነፍሴ አጥብቃ ትወድሃለች። ለአጤ ቴዎድሮስ ገብርዬ በጽናት እንደቆመለት ሁሉ እኔም ላንተ እጸናለሁ። ለአገር የከፈልከው በዋጋ የማይተመነው መስዋዕትነትህ ነው ይኼንን ፍቅር በልቤ ውስጥ የፈጠረው። በብዙ የቃላት ክምር ስላንተ የሚሰማኝን /የውስጤን/ የመግለጽ ጥበቡ ቢኖረኝ ያንን እወነት እየከተብኩ ለዘመናት በተቀመጥኩበት እቆይ ነበር። ግን የማይገለጹ ብዙ ነገሮች አሉ። ልቤ ውስጥ ካሉት ያነሱ ቢሆኑም የጻፍኳቸው ሁሉ የልቤ ውስጥ የእውነት ቃላቶች ናቸው። ብቻ ግን በእውነተኛ መውደድ ሁሌም እ...ወ...ድ...ኃ...ለ...ው...!

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
የመልካም ልደት መግለጫ!

ውዷ አምለሰት ሙጬ እንኳን ተወለድሽ! እንኳንም በሰላምና በጤና ለዚህች ዕለት አደረሰሽ! ኤሚዬ ብሩ እና መልካም ልደት ይሁንልሽ። ቀሪው ዘመንሽ በደስታና በብዙ በረከቶች የተሞላ ይሁን። የልጆችሽን ወግ ማዕረግ የባለቤትሽንም የስኬት ጥግ በዘመንሽ እንዲያሳይሽና የልብሽም መሻቶች በዘመንሽ የተፈጸሙ እንዲሆኑልሽ እመኛለሁ።

ከአክባሪ ወንድምሽ ✎#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
በቅድሚያ ጀግናው ልጃችን ቴዲ አፍሮ፦ እንኳን ለኢትዮጵያ ልጇ፥ ለልጆቿም ወንድሞቿ ሆነህ ተወለድክልን። ብዙዎች በዚህ ዓለም ላይ "ከከባድ ነገሮች ውስጥ አንዱ ከባድ ነገር የሚወዱትን ሰው በሚመጥኑ ቃላቶች ለመግለጽ መሞከር ነው" ሲሉ አውቃለሁ። በዚህ ጉዳይ በተወሰነ መልኩ ብስማማም ልቤ ግን አንደበት ከሚገልጸው በላይ ተግባር የሚገልጸው ፍቅር ይልቃል ብሎ ስለሚያምን ይኼን ሰው ለመግለጽ ቸገረኝ ብሎ ከማውራቱ ይልቅ እሱን በእውነተኛ የመውደድ ስሜት መውደዴ ብቻ በቂ ሆኖ ይሰማኛል። እንደ ቴዲ አፍሮ በጀግንነት እና በእርሱ ጽናት ልክ ባይሆንም ጥቂት ነገሮቹን በመውረስ ለአንዲትም ሰከንድ ቢሆን ሀሳቡን ሳልቋወም ከ20 አመታቶች በላይ ከርሱ ጋ ተጉዣለሁ። ይኼ እና ያልገለጽኳቸው እውነታዎች በተግባር የተገለጸውን ፍቅሬን በመጠኑም ቢሆን ይልጻሉ ብዬ አምናለሁ።

ሰውን ለመውደድ ሰው ከመሆን የላቀ ምክኒያት ባያስፈልግም የሰዎች አፍ ግን ስለምን ወደድከው ሲል ዕልፍ ጊዜ ጠይቆኛል። በመጀመሪያ ሰው በመሆኑ እንደ ሁሉ ሰው እንደወደድኩህ በኩራት ተናገርኩ። በመቀጠልም የእርሱን ስብዕናዎች እንዲ እያልኩ መጥቀስ ጀመርኩ። ቴዲ አፍሮን በጣም የወደድኩት ከሌሎቹ በተለየ መልኩ በሙዚቃዎቹ ስለ ፍቅር በጽኑ መንፈስ ስለሚያቀነቅን ነው። እኔ ደግሞ የፍቅርን ኃያልነት የማምን ሰው ነኝ። ፍቅር በእግዚአብሔር ከመወደድ እና እግዚአብሔርን ከመውደድ ይጀምራል። እግዚአብሔርን የሚወድ ሁሉ ሌሎችን ይወዳል። ይኼ የፍቅር ሉዓላዊ /ነጻ/ ህግ ነው።

ታዲያ ስለፍቅር ሌልች አላዜሙም እንዴ ብሉኝ ነጥቤ እሱ አይደለምና ሃሳቤን እንዲህ ስል እቀጥላሉ። ፍቅር ማለት መውደድ ብቻ አይደለም። መፍራት እና ማክበርም ጭምር ነው። በመፍራት የሆነ ማክበር እና አምልኮ ለእግዚአብሔር፥ በማክበር የሆነ መፍራት ደግሞ ለሰው ልጆች እና ለፍጥረት ሁሉ ይገባል። ይኼን መንፈስ የተጎናጸፈ ሰው ደግሞ ታላቁንም ታናሹንም ያከብራል፣ ይወዳል ይፈራልም። መፍራት በሃይለ ቃል ላላመናገር ነው። መፍራት ከላይም ከታችም በማሃከልም ለቆመው ለመታዘዝ መፍቀድን እንደ ሆነ ልብ ይሏል። ከዚህ አንጻር በኪነጥበቡ ዘርፍ እንዲህ ሆኖ ያገኘሁት ይኼንን ሰው ነው። ይኼንን ሰው መውደድ፣ ማክበር፣ መታዘዝ እንዲሁም እንደ ታላቅ ወንድም ማየት ፍጹም ጤናማ ከሆነ ልብ እና አዕምሮ የሚመነጭ ነው። በእግዚአብሔርም ዘንድ መውደድ ለሰው ልጆች ሁሉ የቀረበ የክርስቶስ አዋጅ ነውና ይኼን ሰው በመውደዴ ደስተኛ ነኝ እላለሁ በኩራት።

በመጨረሻም ለኢትዮጵያ አገራችን እና ለወገኖቻችን ላበረከተው አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ። የኪነጥበብ ሙያው እንዲከበርና እንዲታፈር ጭምር የእርሱ በዚህ ደረጃ መግዘፍ ዋናውን ሚና ተጫውቷል ለዚህም ትልቅ ክብርን እሰጠዋለሁ። ቴዲ አፍሮ በሚወዱት፣ በሚጠሉት፣ በሚተቹት /በሚቀኑበት/ ባለሙያዎች ልብ ውስጥ ሳይቀር ትልቅነቱ ሊገዝፍ የቻለው እግዚአብሔርን ይዞ በመቆሙ ስለሆነ እግዚአብሔር እስከ ፍጻሜው ድረስ አብሮት ይሆን ዘንድ መልካም ምኞቴ ነው።

ትንሽ ልከትብ ፈልጌ ብዕሬን አነሳሁት ግን ትልቅ ሰው ሆነብኝ እና በትንሽ አንቀጽ ልቋጨው ተሳነኝ። አሁንም ብዙ ጠልቄ መውጫው እንዳይጠፋኝ የልቤን ሀሳብ ገትቼ ምኞቴን ገልጬ ልተው። በእውነተኛ መውደድ የምወድህ የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ መልካም ልደት ይሁንልህ። የሚወድህ ልቤ የጸነሰውን ሀሳብ በሚያከብርህ ብዕሬ እንዲህ ከተብኩት።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
በአትሌቲክሱ ዘርፍ በአገሬ አሜሪካ ኦሪገን ግዛት ላይ ተካሂዶ በነበረው በ18ተኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አራት /4/ ወርቅ፣ አራት /4/ ብር እና ሁለት /2/ ናህስ በጥቅሉ አስር /10/ ሜዳሊያዎችን በማንሳት አገራችን ኢትዮጵያ በዓለም የሁለተኛ ደረጃነትን እንድትይዝ እና ለዚህ አንጸባራቂ ድል እንድትበቃ ያስቻላችሁ መላው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አባላት በሙሉ ከልብ ልናመሰግናችሁ እንወዳለን።

ኢትዮጵያ ስሟ በዓለም ከፍ ይል ዘንድ ብሎም ኢትዮጵያውያን ወደ ብሄራዊ ስሜታቸው ይመለሱ ዘንድ እንዲህ ያሉ አነቃቂ እና አርኪ ተግባሮች በሁሉም ዘርፎች ይደገሙ ዘንድ መልካም መሆኑን ለማስታወስ እወዳለሁ። ሁሉም ኢትዮጵያ ሲል ማየት ደስ ይላል።

4 🥇 4 🥈 2 🥉

#WorldAthleticsChamps

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
ለውዴ ውዱ ነሽ

በጎደለ ሞልተሽ፤ በጠፋው ተክተሽ፣
ሲዝል አበርትተሽ፤ ግራውን ደግፈሽ፣
የብቸኝነት ጉዞውን፤ በጥንድ ቀይረሽ፣
ባብሮነትሽ አጅበሽ፤
ሙሉ አደረግሽው፤ መልኩን አሳቅፈሽ
እራሱን ደግመሽ፣ እራስሽን ደግመሽ።

መኑ ከመ ሄዋን፤ እንደ ሚካኤል እናት፣
መኑ ከመ ሄዋን፤ እንደ ብሩክቲ እናት?
ሁሌም አብራው ያለች፤ እየሆነች ብርታት፣
ለብላቴናው ክብሩ፤ ለልቡም ዘውድ ናት።

እንደ ግጥሜ ርዕስ፤ እንደ ስንኝ ቋጠሮ፣
እንደ ጠቢብ ቅኔ፤ እንደ ፀሐይ ኑሮ፣
ልብሽ ብሩህ ነው፤ ዘውትር የሚፈካ፣
መልክሽ በለስ ነው፤ ውዴ ባንቺ 'ረካ።

የሰጠሽው ፀጋ፤ የሰማይ ላይ መና፣
እንደ ምድር ሃመልማል፤ የፈካ ነውና፣
ልቡን ፍቅር ሞላው፤ ደስታውም አበበ፣
ለውዴ ውዱ ነሽ፤ በመልክሽ ተዋበ!

እንደ ከዋክብ ብዙ፤ እንደ ጀምበር ውብ፣
አንድ ሰው እልፍ ነው፤ ከተቸረው ልብ!!
አንድ ሳለሽ ብዝተሽ፤ ሁሉን የሆንሽለት፣
ጤና ይስጥሽ አምላክ፤ ዘላለም ኑሪለት!

እንደ ምድር አሸዋ፤ እንደ አባይ ጅረት፣
አንድ ሰው ብዙ ነው፤ ፍቅር ከሞላበት!
በዝተሽ አበዛሽው፤ በርተሽ አፈካሽው፣
ከፊትም ከኋላም፤ በሁሉም ከበሽው።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
ለውዴ ውዱ ነሽ

በጎደለ ሞልተሽ በጠፋው ተክተሽ
ሲዝል አበርትተሽ ግራውን ደግፈሽ
የብቸኝነት ጉዞውን በጥንድ ቀይረሽ
ባብሮነትሽ አጅበሽ፤
ሙሉ አደረግሽው መልኩን አሳቅፈሽ
እራሱን ደግመሽ፣
እራስሽን ደግመሽ።

መኑ ከመ ሄዋን እንደ ሚካኤል እናት፣
መኑ ከመ ሄዋን እንደ የማርያም እናት፣
መኑ ከመ ሄዋን እንደ የማሁስ እናት፣
መኑ ከመ ሄዋን እንደ ዘዳዊት እናት?
ሁሌም አብራው ያለች እየሆነችው ብርታት
ለብላቴናው ክብሩ ለልቡም ዘውድ ናት።

እንደ ግጥሜ ርዕስ እንደ ስንኝ ቋጠሮ
እንደ ጠቢብ ቅኔ እንደ ፀሐይ ኑሮ፤
ልብሽ ብሩህ ነው ዘውትር የሚፈካ
መልክሽ በለስ ነው ውዴ ባንቺ 'ረካ።

የሰጠሽው ፀጋ እንደ ሰማይ መና፤
እንደ ምድር ሃመልማል የፈካ ነውና
ልቡን ፍቅር ሞላው ደስታውም አበበ
ለውዴ ውዱ ነሽ በመልክሽ ተዋበ!

እንደ ከዋክብ ብዙ እንደ ጀምበር ውብ
አንድ ሰው እልፍ ነው ከተቸረው ልብ!!
አንድ ሳለሽ ብዝተሽ ሁሉን የሆንሽለት፤
ጤና ይስጥሽ አምላክ ዘለዓለም ኑሪለት!

እንደ ምድር አሸዋ እንደ አባይ ጅረት
አንድ ሰው ብዙ ነው ፍቅር ከሞላበት
በዝተሽ አበዛሽው በርተሽ አፈካሽው
ከፊትም ከኋላም በሁሉም ከበሽው።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

የክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና የአርቲስት አምለሰት ሙጬ የአብራክ ክፋይ የሆኑት ልጆች 4 ሲሆኑ ሁለት ወንድ እንዲሁም ሁለት ሴቶች ናቸው። ስማቸውም እንደየ የውልደት ቅደም ተከተላቸው፦ ሚካኤል ቴዎድሮስ፣ የማርያም ቴዎድሮስ፣ የማሁስ ቴዎድሮስ እና ዘዳዊት ቴዎድሮስ ይባላሉ።
የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ቦረና ላይ በድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችን ለመደገፍ "127ኛውን የአድዋ የድል በዓልን ለቦረና" በሚል መርህ እየተደረገ ባለው የእርዳታ ማሰባሰቢያ በኩል ለቦረና ወገኖቻችን ይውል ዘንድ የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ በማድረግ ግንባር ቀደም ሆኗል። ይኼ ተግባር ለድርጅቶችና ለሌሎች አካላቶች ትልቅ የቤት ስራ ጥሎ የሚያልፍ ከመሆኑም በላይ የተጠቀሱትንም ያልተጠቀሱትንም አካሎች የሚያነቃቃ ትልቅ ተግባር መሆኑ ግልጽ ነው።

ሁሌም ለመስጠት የሚጣደፍ እጅ ከአመታቶች በፊት ካቴና ገብቶበት ነበር። ሁሌም ለወገኔ የሚለው ይኽ ሰው ከአመታቶች በፊት ኦሮሞ ጠል ተብሎ ነበር። ዛሬ ግን እሱ ከሁሉ ቀድሞ ለገሰ። ሁሌም ካልሰጠሁ የሚለው ይህ ሰው በሰሜን በደቡብ በምስራቅ በምዕራብ ሰው ተራበ ቢሉት ከኔ ወገን አይደለም ብሎ ዘግይቶ አያውቅም። ስስ ልቡ ለሁሉ እኩል ያዝናል! ለጋስ እጁ ለሁሉ ይዘረጋል።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
የቴዲ አፍሮ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ቁርኝት ክፍል (፩)

በኢትዮጵያ እንደ ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ለወገኖቹ የወገነ ፖለቲከኛም ሆነ የኪነጥበብ ሰው የለም። በተለያዩ ወቅቶች ለህዝባቸው ድጋፍ ለመሆን እና በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሱ ያሉ መድሎዎችን ለመቋወም የተነሱ ግለሰቦች እና ተቋሞች በሚደርስባቸው ጫና አልያም በጥቅም የጀመሩትን ሳይጨርሱ የውሃ ሽታ ሆነው ቀርተዋል። ከሀገር ውጪ ይኖሩ የነበሩ የሰብዓዊ መብት ተሟጓቾችም ሆኑ ጭቁኑን አገዛዝ በመሳሪያም በዲፕሎማሲም እንገረስሳለን ያሉ የግንቦት ሰባት ዋና አመራሮች ሳይቀሩ ትግሉ ተጠናቋል ብለው የገዢው ፓርቲ አገልጋይ ሆነው ህዝባቸውን የራስህ ጉዳይ ካሉት አመታቶች ተቆጠሩ። ቴዲ አፍሮ ግን ያለፉትን 20 አመታቶች ያለማንገራገር ከምስኪን ወገኖቹ ጋ ጸንቶ በመቆሙ ብዙ ከባድ የሆኑ መስዋዕትነቶችን ለብቻው ተጋፍጧል።

ቴዲ አፍሮ በልዩ ሁኔታ በግል ህይወቱ ላይ አልያም በስራዎቹ ዙሪያ የሚፈጠሩ አልመግባባቶችን ተጎድቶም ቢሆን በጊዜ የመቋጨት ልማድ ያለው ብልህ ሰው ነው። በወገኖቹ ላይ የሚደርሱ በመንግስታዊ እና በሌሎች በተደራጁ ቡድኖች የሚደርሱ መድሎዎችን፣ ዘር ተኮር ማፈናቀሎችን፣ ማንነት ላይ ያተኮሩ ጭፍጨፋዎችን፣ ኢሰብአዊ ድርጊቶችን፣ ህገመንግስታዊ ስህተቶችን ብሎም የመብት ጥሰቶችን በግልጽ እና በቀዳሚነት በመቋወሙ ለአመታቶች ብቻውን ሲጨቆንና ኢፍትሃዊ የሆኑ ድርጊቶች በገዢው ቡድን ሲፈጸሙበት ቆይቷል። ከነዚህም ውስጥ በሀሰት ክስ ለ18 ወራቶች በእስር መቆየት፣ በሀገር ውስጥ የሚደረጉ የኮንሰርት ስራዎቹን ያለበቂ ምክኒያት መከልከል፣ በሚዲያዎች ላይ የኪነጥበብ ስራዎቹ እንዳይተላለፉ ማገድ፣ ከሀገር ለስራ የመውጣት መብቱን በመንፈግ በተደጋጋሚ ከኤርፖርት መመለስ እንዲሁም የአልበም የምረቃ ስነስርዓቱን እንዳይፈጽም ፍቃድ የለህም በሚል አግባባዊ ባልሆነ አካሄድ በዕለቱ (በምረቃው ዕለት) ቦታው ላይ በመገኘት በሀይል መሰረዝና በየመንገዱ እየተከታተሉ ድንገተኛ ፍተሻ ማድረግ ብሎም የስነልቦና ጉዳት ለማድረስ እና ውስጡን ሞቾት እንዲነሳው በማሰብ በሚንቀሳቀስባቸው ስፍራዎች ሁሉ የተለያዩ መከናዎችን በመመደብ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች እንዲከታተሉት ማድረግ እና የመሰሉ መንግስታዊ ውንብድናዎች ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው።

እንደ ሚታወቀው በቴዲ አፍሮ ልክ ግዙፍ ኮንሰርቶችን በኢትዮጵያ ያዘጋጀ አርቲስትም ሆነ መንግስታዊ ተቋም አልያም ሌሎች በዘርፉ የተሰማሩ ፕሮሞተሮች የሉም። የቴዲ አፍሮ ኮንሰርቶች በአገር ቤት በሚዘጋጁበት ወቅት በተለያዩ ዓለማት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኮንሰርቱን ለመታደም በማሰብ ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛሉ። እንዲሁም ከክፍለ ሀገርም ኮንሰርቱ ወደተዘጋጀበት ከተማ ይጓዛሉ። ይሄ ደግሞ የከተማውን ገበያ የሚያነቃቃ ትልቅ አጋጣሚ ነው። ለምሳሌ ባህርዳር ላይ ተዘጋጅቶ በነበረው ኮንሰርት ላይ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ከመጡ ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ ከአዲስ አበባ፣ ከጎንደር፣ ከኦሮሚያ ክልል እንዲሁም ከተለያዩ አከባቢዎች ወደ ከተማዋ በመግባታቸው በከተማዋ የሚገኙ ሆቴሎች በሙሉ አልጋቸው ለተከታታይ ሶስት ቀናት ተይዞ ቆይቷል። የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችም በልዩ ሁኔታ ሲንቀሳቀሱ ነበር። የምግብ ሰጪ ድርጅቶችም ከወትሮው በተለየ መልኩ በሰዎች ተሞልተው ነበር። ይኼንን በወቅቱ ቦታው ላይ ተገኝቼ አስተውያለሁ። እንዲሁም አዲስ አበባ ላይ ባዘጋጃቸው መድረኮችም ተመሳሳይ ነገሮች ተፈጥረዋል። ልጁ ለአንድ አዳጊ ሀገር ትልቅ ሀብት ነው። ሆኖም ግን ይኼንን ውድ ሀብት ጨቋኞች አምርረው ተጣሉት። ከነርሱ የሚፈልገው አንዳች ቢኖር ድሃ ወገኖቹን ሠላም ሰጥተው፣ መብታቸውን አክብረው ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲያኖሩለት ብቻ ነው።

ቴዲ አፍሮ ሀገር ውስጥ ሊያዘጋጃቸው አስቦ የተሰረዙበት ኮንሰርቶች በቅድሚያ አስፈላጊውን ነገር ሁሉ አሟልቶ ፍቃድ ተሰጥቶት ብዙ ሚሊዮኖችን ወጪ ካደረገባቸው በኋላ በድንገት ከሚመለከተው አካል የሚደረጉ የኮንሰርት ክልከላዎች ቴዲ አፍሮን ምን ያህል እንዳከሰሩት ላሰላ ሰው በግለሰብ ደረጃ ይሄንን ሁሉ ኪሳራ መቋቋም በጣም ከባድ እንደሆነ ይረዳል። ቴዲ አፍሮ ግን በዚህ ሲያማርርና ሲቆጣ ተስተውሎ አያውቅም። ተደጋጋሚ ኪሳራዎች ደርሰውበትም ለህዝቤ ስል ያጣሁን ገንዘብ በካሴት ሽያጭ አገኘዋለሁ ብሎ በማሰብ እንኳን ካሴቱ ላይ የሁለት ብር ጭማሪ አድርጎ አያውቅም። ይልቁንም አንድ ጀማሪ ሙዚቀኛ በሚያከፋፍልበት ዋጋ ነው ስራውን ገበያ ላይ የሚበትነው። እሱማ ቢቻለው ለሁሉ በነጻ ቢያደል ደስታው ነበር። ኮንሰርቶቹንም ስንመለከት ከሱ በታች ተከታይ ያላቸው የሀገራችን ሙዚቀኞች የመግቢያ ዋጋቸውን ለመደበኛ 600 ብር ለVIP ደግሞ እስከ 3000 ብር ድረስ ሲያስከፍሉ አስተውለናል። ቴዲ አፍሮ ግን መደበኛ የመግቢያ ዋጋ 300 ብር የVIP ደግሞ 500 ብር ነበር ትልቁ የትኬት መሸጫ ዋጋው። ይኼም በዛ ብሎ ከአዘጋጆች ጋ ሲከራከር ነበር። ምን ያህል ህዝቡን ቢረዳው እና ቢወደው ነው ኪሱ የሚገባው ብር ሳያጓጓው በጣም እርካሽ በሚባል ዋጋ ያንን የመሰለ የመድረክ ስራን የሚያቀርብልን ብዬ ሳስብ አንዴ ጅማ ለኮንሰርት ሄዶ የተናገራት አንዲት ቃል ትዝ አለችኝ። "በከፈላችሁት ልክ ሳይሆን በምወዳችሁ ልክ ነው የምዘፍንላችሁ" ሲል ሙዚቃውን ሊታደሙ ለመጡ አድናቂዎቹ ተናግሮ ነበር። እውነትም በሚወደን ልክ አዜመልን። በሚወደን ልክ በመከራችን ወቅት ለምን ብሎ ቆመልን። በያንዳዷ የችግራችን ወቅት ፊትአውራሪ ሆነልን። አንደበታችን ተይዞ አቅማችን ተዳክሞ ተስፋ በቆረጥን ጊዜ እሱ ጉልበት ሆነን። ቴዲ አፍሮ ሸክማችንን እንደ ግል ሸክሙ ቆጥሮ ጨቋኞችን ተጋፈጠ።

ክፍል ሁለት ነገ በተመሳሳይ ሰዓት ይለጠፋል

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
ቀኑ ደርሶ በሀገር አንጻራዊ ሰላም ነግሶ ይኼንን የሙዚቃ ክር ከክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እስክንታደል ድረስ የኔም ጉጉት ትልቅ ነው። ቴዲ አፍሮም መቼ እንደሚለቅ በጠየኩት ጊዜ የሀገራችን ሁኔታ ጥሩ በሆነ ጊዜ ነበር ያለኝ። ቴዲ አፍሮን በተመለከተ ለሌላው ጊዜ እንዲህ ያሉ መረጃዎች ከየትም በኩል ብትሰሙ ታማኝ ምንጮችን እንድትፈትሹ፥ በተለይም የቴዲ አፍሮን ህጋዊ የፌስቡክ ገጽ እና Teddy Afro Net የተሰኘውን ገጾች እንድትከታተሉ በትህትና ለመጠቆም እወዳለሁ።

ወደ ኢትዮ ቴሌኮም እንመለስ። ስለ ቴዲ አፍሮ አልበም የጠቀሰውን ዜና ከሰዓታት በኋላ ከገጹ ላይ ያስወገደ ቢሆንም ከድርጅቱ እንዲህ ያሉ የሀሰት ዜናዎች በሀገር ደረጃ ሲያሰራጩ ይኽ የመጀመሪያው ባይሆንም ህዝብ በሚያከብረው እና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባለው አርቲስት ስም አንደ የሀገር በቀል ድርጅት የሀሰት ዜናውን ሀላፊነት በጎደለው መልኩ ማሰራጨቱ ትልቅ ነውር መሆኑን ለድርጅቱ የበላይ አመራሮች እና ለሚመለከተው አካል ስጠቁም ተግባራቸው እንደየ ሁልጊዜ ህዝብን ያላከበረ በመሆኑ በድርጅቱ ዳግም የሆነ ትልቅ ሀፍረት እንደተሰማኝ በመጠቆም ጭምር ነው። ሌላ አማራጭ ቢኖረንና ከዚህ ተቋም ጋ ለዘለዓለም ደንበኝነታችንን ብናቋርጥም በተለየ መልኩ ትልቅ ደስታ እንደሚሰማኝ በዚሁ ለመጠቆም እወዳለሁ።

በስተ-መጨረሻም በሰዋሰው መልቲሚዲያ ሙዚቃዎቻቸውን ለለቀቁ የሀገራችን ዘፋኞች በጠቅላላ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ። ከዚሁ ጋ በማያያዝ ቴዲ አፍሮ እገሌ ላይ አልበም ደረበ (ሊደርብ ነው) የሚል ስጋት ያደረባችሁ ግለሰቦችም ሆናችሁ ሌሎች አካሎች ይኼንን የሀሰት መረጃ በማመናችሁ ብቻ ይሄ ስጋት ሊሰማችሁ እንደቻለ በመረዳት ያሞኛችሁን ድርጅት ወቅሳችሁ የሀገሬ ክር እስኪለቀቅ በእጃቹ የደረሱትን ዘፈኖች አድምጡ ስል እመክራለሁ።

#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
የዘለዓለም ሰንደቅ 💚💛❤️

ከ126 ሚሊየን በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ ሰንደቅ አላማ ስር በዓለም አደባባይ ታፍሮና ተከብሮ ይኖራል።

ይህችን ባንዲራ ዓለም ያከበራቸው ታላላቅ ኢትዮጵያውያኖች በየመድረኩ ከፍ አድርገው በመያዝ በኩራት ቆመዋል። ሀገር ጠሎች የ‍እህቸ‍ን አርማ እንዳያዋርዷት ታላላቆች አክብረዋታል። የዛሬ ውሪዎች እንዳያሳንሷት የጥንት ኃያላኖች አንጸዋታል።

አፍሪካ ሲባል ጥንተ ሉአላዊት ኢትዮጵያ ነች ገዝፋ የምትታየው። ኢትዮጵያ ሲባል የነ አጤ ቴዎድሮስ ብርታት የሆነች ከዘመነ ኖኽ ጀምሮ በሰማይ የተሳለች የሀገሬ ሰንደቅ ነች በሁሉ ልቦና ቦግ ብላ የምታበራው።

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር።

🔥💚💛❤️🔥

“አርማሽ ከፍ ሲል ሰማይ ላይ ወጥቶ
እኛ ልጆችሽ ልናይ ቆመናል
አንድ ቀን መጥቶ አንድ ያደርገናል”

#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
ናዕት (ዳግማዊ ጃ ያስተሰርያል)

ናዕት የተሰኘው የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ የክብር ዶክትሬት ከተበረከተለት በኋላ ለአድማጭ ያበቃው ሁለተኛ ነጠላ ዜማው ነው። መቼም እኔ ደፋር ስለሆንኩና ሙያዬ ስለሚጫነኝ ይኼንን ሙዚቃ ነጠላ ዜማ ነው ብዬ ልጥራው እንጂ ነገርየውማ የ6 ደቂቃ ሙሉ አልበም ቢባል ከግነት አይቆጠርም። እንደው የሚከተለውን ሀሳቤን ሳሰፍር ስለምትወደው ነው ሳትሉኝ ስለእውነትነቱ ብቻ እያሰባችሁ ታነቡ ዘንድ አደራ እላለሁ።

በእኔ እምነት "ናዕት" ዳግማዊ ጃ ያስተሰርያል ነው። ምክኒያቱም የህዝብን የታፈነ ስሜት እንጂ የአንዲን የኪነጥበብ ስጋዊ ወመንፈሳዊ ፍላጎት አይደለም የሚያወሳው። "ናዕት" የእናቶቻችንን ጩኸት ነው የጮኸው። በናዕት በከንቱ ስለፈሰሰ የንጹሃን ደም ነው ሙግት የቀረበ። ናዕት አንባገነናዊ ስርአትን በይፋ ያወገዘ ለሰው ልጆች ነጻነት የተደረሰ ዜማ ነው። "ናዕት" አምባገነኖችን ያበሳጨ የሉአላዊ ህዝብ ድምጽ ነው። ካለፉት 18 አመታት ወዲህ በዚህ ደረጃ የህዝብን ሰቆቃ ይዞ የወጣ ዘፈንም ጥበብም ኪነትም አልነበረም።

"ናዕት" ዳንኪራ የሚረግጡበት አሼሼ ገዳሜ የሚሉበት ዘፈን አይደለም። "ናዕት" በህይወትና በሞት መኃል እየታገለ ላለ ንጹህ ህዝብ ዘብ የቆመ ዜማ ነው። "ናዕት" በከንቱ በየሜዳው ስለፈሰሰ የወገን ደም የቃተት ድምጽ ነው። "ናዕት" የእምቢኝ ባይ ነፍስ መብትን የደገፈ የአርበኞች ምልክት ነው። "ናዕት" የነፃነት ታጋዮችን ሀሳብ ይዞ ብቅ ያለ የጥበብ ድምጽ ነው። "ናዕት" ከእግዚአብሔር የተሰጠችንን ተፈጥሯዊ የመኖር መብት የጠየቀ የጠቢብ ሰው ታላቅ ጩኸት ነው። "ናዕት" በንጹሃን ወገኖቿ የጅምላ ጭፍጨፋ የታመመች ነፍስ ጩኸት ነው።

ይኽ ስራ በ13ኛው ዙር የለዛ አዋርድ ላይ ባለፉት ሁለት አመታቶች ለህዝብ ከደረሱ ስራዎች ጋ የአመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ በሚል ዘርፍ በአድማጭ ድምጽ መሰረት ሊሸለም ለወድድር ቀርቧል። ይኼ ሙዚቃ ለኛ ሙዚቃ ብቻ ሳይሆን የነጻነታችንም ዜማ ነውና ለዚህ ሙዚቃ ድምጽ በመስጠት የዜማችንን ኃያልነት ለሁሉም እናረጋግጥ ስል እጠቁማለሁ!

https://vote.leza.show/

#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
This is Coca-Cola Arena

ይህ Coca Cola arena ነው። በዚህ መድረክ የዓለማችን እውቅና ተጽ
ኖ ፈጣሪዎች ብቻ ናቸው መቆም የሚችሉት። ከምስራቅ አፍሪካ ግን እስካሁን ማንም በዚህ መድረክ ቆሞ ስራውን ማቅረብ አልቻለም። የምስራቅ አፍሪካ ሰዎችም ለዚህ እድል ቀድመው አልበቁም።
ኢትዮጵያውያን ግን እነሆ በአንድ ልንሰበሰብበት ነው።

ዓለም የተስማማባቸው እውቅ ሰዎች አስደንጋጭ ዝግጅቶችን ባቀረቡበት በዚህ መድረክ ላይ ለአፍሪካውያን ወጣቶች ተምሳሌት የሆነው፡ በማንኛውም መድረክ ላይ ብቻውን በመቆም እልፍ አድናቂዎችን መሰብሰብ የተቻለው፡ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንጉስ የሆነው፡ የ
ክብር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ በዚህ በግዙፍ አዳራሽ ስራውን ያቀርባል። ከምስራቅ አፍሪካም ቀዳሚ በመሆን በዓለም የኪነጥበብ ታሪክ ሲዘከር ይኖራል።

በዚህ ታሪካዊ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ለመታደም ከዓለም ጫፍ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እየተጠራሩ ይገኛሉ። በዕለቱ ዓለም እየሰማ ኢትዮጵያ በታላቅ የብሔራዊ ስሜት ትጠራለች ባንዲራዋም በባዕድ ምድር ከፍ ብሎ ይውለበለባል። ምን ይሄ ብቻ
…! የኢትዮጵያ ነገሥታቶች ስማቸው በታላቅ ኩራትና በጀግንነት ስሜት ይወሳል። ምክኒያቱም ያለንን ማንነት የሰጡን እነርሱ ናቸውና።

#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
ጥበብ እንጂ…

የነፍስህን ቃል እንጂ የመንጋዎችን ጩኸት አትሰማም። የፈጣሪህን ቁጣ እንጂ የሹሞችን ዛቻ አትሰጋም። የፊት መንገድህን በማለም ትራመዳለህ እንጂ የኋላህን በመቁጠር አትዘገይም። የወደድኩህ የኔን አይነት ባህሪ፣ ያንተን አይነት ስብዕና ስላለኝ ነው። “መፍራት ለፈሪዎች ስጋትም ለሰነፎች ናት” ብለኽ ስለምታስብ ለጀብደኞች እንኳን መራር የሆነችን እውነት በጥበባዊ ልሳን ገልጠሃታል። መኖር በሀገር፣ ለሀገር ሲሆን ሞት አያስፈራም። ብለኸ የነፍሴን ጽኑ እውነት በሊቅ ዜማ አንቆርቁረሃል።

ወንድ ልጅ ለሆዱም ለኪሱም ሳይረታ ሲቀር ወኔ አዘል ሽለላ አለው! እርሱም “አንገት ከሚሰበር ባይበላስ ቢቀር” ነው። ያንገት መሰበር መቀንጠስ ለሚመስላቸው መቀንጠስ አይደለም። በሐፍረት ዝቅ ማለት እንጂ! ሆድ ክፉ ነው ሲሉ እንደምስቀው ትስቃለህ ብዬ የማምነው ሆድ ሳይሆን ክፉ ሆዱን የወደደው ሰነፉ ሰው ነው ክፉ። ምክኒያቱም ሆድ እንዳረጉት ነው። ለሰው ልጅ ከሆድ የቀረበ፣ ከሆድም የቀደመ ተወዳጅ ተግባሩ ሰው መሆን ነው። ይሄን ደግሞ አንተ ጋ አይተናል!!!

የክብር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (Teddy Afro) መልካም ልደት ይሁንልህ አንበሳዬ!!!

#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
የህዝብ ልጅ የሆነው የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ምክኒያት ህይወታቸውን ባጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ፣ ለደረሰው ድንገተኛ ጉዳት ድጋፍ ይሆን ዘንድ የአንድ ሚሊዮን ብር ቼክ ዛሬ 19/11/2016 ዓ.ም ፈርሟል።

ለህዝባችን መጽናናትን ህይወታቸውም ላለፈም ምህረትን ያድልልን!!!

#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
የዛሬ 3 አመት ነበር ሐምሌ 22/213 ዓ.ም የጎንደር ዩኒቨርስቲ ለቴዲ አፍሮ የክቡር ዶክትሬት ማዕረግ ሊሰጠው የወሰነው። በእለቱ ሴኔቱ ባደረገው ስብሰባ ለአርቲስቱ የዶክትሬት ማዕረግ እንዲሰጠው አጽድቋል።

"ክብርህን ጠብቀህ ኢትዮጵያን ስላከበርክ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ይህን ክብር አበርክቶልሃል፡፡"

በዚህን ሰአት ጀምሮ ዓለም በሙሉ ስሙን እንዲህ እያለ ከነ ሙሉ ክብሩ መጥራት ጀመረ፦

የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
ሚሊዮን ፍቅር በአንድ ልብ። ♥️

ሀገሬን እወዳለሁ ካልክ በትንሽዬ ቀበሌ ውስጥ የሚኖሩ ምስኪን ወገኖችህን በእውነተኛ የመውደድ ስሜት መውደድ ይጠበቅብሃል። ምክኒያቱም ሀገር ያለነሱ ትንሽዬ ተሳትፎ ከወርቅነት ወደ መዳብነት ታንሳለች። (ሙሉ አይደለችም።) ወገኔን እወዳለሁ ስትል የፍቅርህ እውነትነት የሚጸናው በሙዚቃህ ዳንኪራ የሚረግጠውን (የሚዲያ ተደራሽነት አግኝቶ ማንነትህን የለየውን በመውደድ ብቻ ሳይሆን) ከተፈጠርክበት አፈር ተፈጥሮ ነገር ግን ማንነትህን ፈጽሞ የማያውቀውን ባላገር ጭምር ለመውደድ ብቁ ስትሆን ነው። (እንደ ቴዎድሮስ ካሳሁን።)

መቶ ሚሊዮን ህዝብ ምልክታችን ነህ ብሎ ከፊት ያሰለፈው የኔው ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጠጋ ብለ ‘ይሄ ድሃ ህዝብ ምንህ ነው?’ ብትለው “ወገኔ ለኔ ክብሬና ኩራቴ ነው ለዚህ ህዝብ ሁለት ነፍስ ቢኖረኝ ሁለቱንም ነፍሴን ለመስጠት አልሰስትም ይልሃል።”

ነፍስህ በጥበብ ስትመላ የድሃ ወገኖችህ እንባ አያስተኛህም። ሀዘናቸውም ሰላም ይነሳሃል። ምክኒያቱም ጥበብ ከግብዝነት መንፈስ የራቀች ነች። ቴዲ አፍሮ ደግሞ ለዚህ ህዝብ ዋጋ ከፍሏል። ታግሏል፣ ታስሯልም። ስለዚህ ሚሊዮኖች በአንድ ልብ ይወዱታል! እሱም ሚሊዮኖችን በአንድ ልብ ይወዳል። ♥️

#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
ቢቂላ ሽልማት (Bikila Award 2024)

በሀገራችን እንቁ አትሌት የተሰየመው “ቢቂላ አዋርድ” ትልቅ ክብር ከሚሰጣቸው የሽልማት ተቋሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን እስካሁንም ለበርካታ የሀገር ባለውለታዎች እውቅናን በመስጠት ሲሸልም ቆይቷል። ቢቂላ ሽልማት (Bikila Award) ከሀይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊ እና ከምንም አይነት ትርፍ እራሱን ባገለለ መልኩ በካናዳ ከ50 አመታት በላይ በኖሩ ኢትዮጵያውያን ነው የተቋቋመው። ይህ ተቋም በትምህርታቸው፣ በንግዳቸው፣ በሙያቸው ብሎም በበጎ አድራጎት ስራ ተሰማርተው ልዩ ስኬት ያስመዘገቡ እና አርአያ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በየአመቱ በመሸለም እውቅናን የሚሰጥ ትልቅ ኢትዮጵያዊ መድረክ ነው።

በዚህ አመት አስረኛ (10) የምስረታ በአሉን የሚያከብረው የቢቂላ አዋርድ ተቋም፥ መስከረም 11 (21 September 2024) በሚያደርገው መርሃ ግብር ላይ በሙዚቃው ዘርፍ በዚህ አመት የሚሸልመው የግጥምና የዜማ ደራሲ ብሎም የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነውን የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁንን መሆኑን በህጋዊ ድህረገጾቹ በይፋ አሳውቋል።

አርቲስቱም በዕለቱ በዚህ ግዙፍ መርሃግብር ላይ በመገኘት ሽልማቱን እንደሚቀበል ተገልጿል።

#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)