Forwarded from ታታ አፍሮ -Tata Afro
#ETHIOPIA ሚያዝያ 7/2009 ዓ.ም
ኢትዮጵያ የተሰኘው የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ነጠላ ዜማ በህጋዊ የዩትዩብ ቻናሉ ከተለቀቀ ዛሬ ስድስተኛ አመቱን ደፈነ። ይኼ ሙዚቃ ሚያዝያ 7/2009 ዓ.ም ምሽት ላይ ነበር የተለቀቀው። በተለቀቀ በሰዓታት ውስጥ ግን ድፍን አዲስ አበባ ውስጥ ሙዚቃው በመዳረሱ ከተማይቱ አዲስ ዘመንን የምታከብር ያህል በየ ስፍራው እንደ ባህላዊ ዘፈን ይኼ ሙዚቃ በስፋት ሲደመጥ አነጋ።
በዕለቱ በመዲናይቱ የተለያዩ ስፍራዎች እየተዘዋወርኩ ለሊቱን ሙሉ ስሜቱን ለማጣጣም የሞከርኩ ሲሆን በየ ቦታው የሚታየው የህዝቡ ስሜት እጅግ ልዩ ነበር።
ይህ ኢትዮጵያ የተሰኘ ተወዳጅ ሙዚቃ ከተለቀቀ በስድስት አመታት ውስጥ ይሄንን መረጃ እስከ-ለጠፍንበት ሰዓት ድረስ በዩትዩብ ብቻ ሀያ አራት ሚልየን ዘጠኝ መቶ አርባ ሶስት ሺ አንድ መቶ አድማጮችን አግኝቷል። ይኼ ደግሞ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ያለ ተንቀሳቃሽ ምስል እጀባ ብዙ ተመልካቾችን ያገኘ የመጀመሪያው ነጠላ ዜማ ነው። በተጨማሪም ባለፉት አመታቶች ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ የሙዚቃ ሰንጠረዦች ላይ ክብረ-ወሰኖችን የሰበረ የዓለማችን ተወዳጅ ሙዚቃ ለመሆን በቅቷል።
ይኽ ሙዚቃ በወቅቱ በፈጠረው ትልቅ የሚዲያ ንቅናቄ የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ከወትሮው በተለየ መልኩ ለቴዲ አፍሮ ትልቅ ትኩረት እንዲሰጡት ያስቻለ ከመሆኑም በላይ ዛሬም ድረስ BBC, CNN, Al Jazeera, CGTN Africa, BBC Africa, የቻይናው CC TV እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃኖች ቴዲ አፍሮ በአፍሪካ እና በዓለም ላይ በሚገኙ አድናቂዎቹ ባለው ሰፊ ተቀባይነት ምክኒያት ስለሱ መዘገብ አትራፊ መሆኑን ተረድተው ስለሱ አዳዲስ መረጃዎችን መዘገብ ቀጥለዋል።
✍ @TataAfro_official (ነፃ ብዕር)

የቴዲ አፍሮ ሽማግሌ
ሚያዝያ 10/1965 ዓ.ም (የዛሬ 50 አመት) ሺ አለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ የተወለደባት ዕለት ነች። ሀይሌ ገብረሥላሴ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በዓለም ላይ ከፍ አድርጎ ያውለበለበ ታላቅ አትሌት ነው። ሩጫን ከጀመረባት ዘመን እስከ አሁኗ ቅጽበት ድረስ ኃይሌ ገብረሥላሴ በዓለም ላይ ያለው ክብር ወደር የማይገኝለት ሲሆን ኢትዮጵያን በዘመኑ በትልቅ ክብር ለዓለም ህዝብ አስተዋውቋል።
የዓለማችን ትልቁ የመገናኛ ብዙሃን ጣቢያ /DSTV/ ስለ ሺ አለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ጀብድ በተደጋጋሚ ይዘግባል። ትልልቅ የዓለም መጽሔቶችም ኃይሌን አወድሰውታል። በተጨማሪም ኃይሌ ገብረሥላሴ ሽማግሌ ሆኖ ከዳራቸው ጥንዶች ውስጥ ቴዲ አፍሮ እና አምለሰት ሙጬ ተጠቃሽ ናቸው።
ሺ አለቃ አትሌት ኃይለ ገብረሥላሴ (የሀገር ሽማግሌ) አገርህን ያስከበርክ ሰንደቋንም ከፍ አድርገኽ ያውለበለብክ ታላቅ ሰው ነህና እንወድሃለን። በታላቅ ክብርም እናከብርሃለን።
ጥቁሩ የዓለማችን አንበሳ ሆይ እንኳን በምትወዳት ሀገርህ ላይ ተወለድክልን። መልካም ልደት።
"እዩት ንጉሡ ግርማ ሞገሱ
ዘውዱን ሸለመው ሰጠው ለአዲሱ"
✍@tataafro_official (ነፃ ብዕር)

የተደራጀ ውሸት።
የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እዮሪካ የተሰኘ አልበም ሊለቅ ነው የሚል የሀሰት ዜና Ethio Telecom ከ1.2 ሚሊየን በላይ ተከታይ ባለው በህጋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ከለቀቀ በኋላ የተለያዩ ግለሰቦች ሀሳቡን እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ እየተቀባበሉት ይገኛሉ። እርግጥ ነው ቴዲ አፍሮ እጅግ የሚደንቁ ዘፈኖች የተከማቹበት ክር እያዘጋጀ መሆኑን አውቃለሁ። ከሰማኋቸው ዘፈኖች ውስጥ አብዛኛዎቹ አሁንም ድረስ በልቤ ውስጥ የሚሯሯጡትን ዜማዎቹን በማስብ ጊዜ፥ ልክ በረሃ ላይ ደክሜ እንደ ነብዩ ዮናስ ጥላ አግኝቼ ያረፍኩ ያህል ደስ እሰኛለሁ። ከዜማዎቹ ትዝታ ስላቀቅ ደግሞ ዳግም እንደ ጥላዋ መጠውለግ ስሜቴን ሁሉ ብል ይወረዋል።

ቀኑ ደርሶ በሀገር አንጻራዊ ሰላም ነግሶ ይኼንን የሙዚቃ ክር ከክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እስክንታደል ድረስ የኔም ጉጉት ትልቅ ነው። ቴዲ አፍሮም መቼ እንደሚለቅ በጠየኩት ጊዜ የሀገራችን ሁኔታ ጥሩ በሆነ ጊዜ ነበር ያለኝ። ቴዲ አፍሮን በተመለከተ ለሌላው ጊዜ እንዲህ ያሉ መረጃዎች ከየትም በኩል ብትሰሙ ታማኝ ምንጮችን እንድትፈትሹ፥ በተለይም የቴዲ አፍሮን ህጋዊ የፌስቡክ ገጽ እና Teddy Afro Net የተሰኘውን ገጾች እንድትከታተሉ በትህትና ለመጠቆም እወዳለሁ።
ወደ ኢትዮ ቴሌኮም እንመለስ። ስለ ቴዲ አፍሮ አልበም የጠቀሰውን ዜና ከሰዓታት በኋላ ከገጹ ላይ ያስወገደ ቢሆንም ከድርጅቱ እንዲህ ያሉ የሀሰት ዜናዎች በሀገር ደረጃ ሲያሰራጩ ይኽ የመጀመሪያው ባይሆንም ህዝብ በሚያከብረው እና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባለው አርቲስት ስም አንደ የሀገር በቀል ድርጅት የሀሰት ዜናውን ሀላፊነት በጎደለው መልኩ ማሰራጨቱ ትልቅ ነውር መሆኑን ለድርጅቱ የበላይ አመራሮች እና ለሚመለከተው አካል ስጠቁም ተግባራቸው እንደየ ሁልጊዜ ህዝብን ያላከበረ በመሆኑ በድርጅቱ ዳግም የሆነ ትልቅ ሀፍረት እንደተሰማኝ በመጠቆም ጭምር ነው። ሌላ አማራጭ ቢኖረንና ከዚህ ተቋም ጋ ለዘለዓለም ደንበኝነታችንን ብናቋርጥም በተለየ መልኩ ትልቅ ደስታ እንደሚሰማኝ በዚሁ ለመጠቆም እወዳለሁ።
በስተ-መጨረሻም በሰዋሰው መልቲሚዲያ ሙዚቃዎቻቸውን ለለቀቁ የሀገራችን ዘፋኞች በጠቅላላ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ። ከዚሁ ጋ በማያያዝ ቴዲ አፍሮ እገሌ ላይ አልበም ደረበ (ሊደርብ ነው) የሚል ስጋት ያደረባችሁ ግለሰቦችም ሆናችሁ ሌሎች አካሎች ይኼንን የሀሰት መረጃ በማመናችሁ ብቻ ይሄ ስጋት ሊሰማችሁ እንደቻለ በመረዳት ያሞኛችሁን ድርጅት ወቅሳችሁ የሀገሬ ክር እስኪለቀቅ በእጃቹ የደረሱትን ዘፈኖች አድምጡ ስል እመክራለሁ።
✍#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)

የዘለዓለም ሰንደቅ 💚💛❤️
ከ126 ሚሊየን በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ ሰንደቅ አላማ ስር በዓለም አደባባይ ታፍሮና ተከብሮ ይኖራል።
ይህችን ባንዲራ ዓለም ያከበራቸው ታላላቅ ኢትዮጵያውያኖች በየመድረኩ ከፍ አድርገው በመያዝ በኩራት ቆመዋል። ሀገር ጠሎች የእህቸን አርማ እንዳያዋርዷት ታላላቆች አክብረዋታል። የዛሬ ውሪዎች እንዳያሳንሷት የጥንት ኃያላኖች አንጸዋታል።
አፍሪካ ሲባል ጥንተ ሉአላዊት ኢትዮጵያ ነች ገዝፋ የምትታየው። ኢትዮጵያ ሲባል የነ አጤ ቴዎድሮስ ብርታት የሆነች ከዘመነ ኖኽ ጀምሮ በሰማይ የተሳለች የሀገሬ ሰንደቅ ነች በሁሉ ልቦና ቦግ ብላ የምታበራው።
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር።
🔥💚💛❤️🔥
“አርማሽ ከፍ ሲል ሰማይ ላይ ወጥቶ
እኛ ልጆችሽ ልናይ ቆመናል
አንድ ቀን መጥቶ አንድ ያደርገናል”

ናዕት ሙዚቃ ብቻ ሳይሆን የጭቁን ህዝብ ጥበባዊ ድምጽ ነው!
ለዛ አዋርድ ከሐምሌ 1/2013 - ሰኔ 30/2015 ዓ.ም የወጡ ነጠላ ዘፈኖችን በእጩነት ለውድድር ያቀረበ ሲሆን ከነዚህም መሃል የቴዲ አፍሮ ሁለት ስራዎች የአመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ በሚል ዘርፍ እጩ ሆነዋል። ስለሆነም መላው የቴዲ አፍሮ አድናቂዎች "ናዕት" የተሰኘውን ታሪካዊ ነጠላ ዜማ እንድትመርጡ እንጠቁማለን። ስለ አመራረጥ ሂደቱ አጠር ያለ ቪዲዮ ከሰአታት በኋላ በTata Afro የፌስቡክ ገጽ ላይ የምንለቅ ይሆናል።
ማሳሰቢያ፦ በአንድ ዘርፍ ከአንድ ስራ (አርቲስት) በላይ በአንድ ስልክ መምረጥ አይቻልም።
https://vote.leza.show/

ናዕት (ዳግማዊ ጃ ያስተሰርያል)
ናዕት የተሰኘው የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ የክብር ዶክትሬት ከተበረከተለት በኋላ ለአድማጭ ያበቃው ሁለተኛ ነጠላ ዜማው ነው። መቼም እኔ ደፋር ስለሆንኩና ሙያዬ ስለሚጫነኝ ይኼንን ሙዚቃ ነጠላ ዜማ ነው ብዬ ልጥራው እንጂ ነገርየውማ የ6 ደቂቃ ሙሉ አልበም ቢባል ከግነት አይቆጠርም። እንደው የሚከተለውን ሀሳቤን ሳሰፍር ስለምትወደው ነው ሳትሉኝ ስለእውነትነቱ ብቻ እያሰባችሁ ታነቡ ዘንድ አደራ እላለሁ።
በእኔ እምነት "ናዕት" ዳግማዊ ጃ ያስተሰርያል ነው። ምክኒያቱም የህዝብን የታፈነ ስሜት እንጂ የአንዲን የኪነጥበብ ስጋዊ ወመንፈሳዊ ፍላጎት አይደለም የሚያወሳው። "ናዕት" የእናቶቻችንን ጩኸት ነው የጮኸው። በናዕት በከንቱ ስለፈሰሰ የንጹሃን ደም ነው ሙግት የቀረበ። ናዕት አንባገነናዊ ስርአትን በይፋ ያወገዘ ለሰው ልጆች ነጻነት የተደረሰ ዜማ ነው። "ናዕት" አምባገነኖችን ያበሳጨ የሉአላዊ ህዝብ ድምጽ ነው። ካለፉት 18 አመታት ወዲህ በዚህ ደረጃ የህዝብን ሰቆቃ ይዞ የወጣ ዘፈንም ጥበብም ኪነትም አልነበረም።
"ናዕት" ዳንኪራ የሚረግጡበት አሼሼ ገዳሜ የሚሉበት ዘፈን አይደለም። "ናዕት" በህይወትና በሞት መኃል እየታገለ ላለ ንጹህ ህዝብ ዘብ የቆመ ዜማ ነው። "ናዕት" በከንቱ በየሜዳው ስለፈሰሰ የወገን ደም የቃተት ድምጽ ነው። "ናዕት" የእምቢኝ ባይ ነፍስ መብትን የደገፈ የአርበኞች ምልክት ነው። "ናዕት" የነፃነት ታጋዮችን ሀሳብ ይዞ ብቅ ያለ የጥበብ ድምጽ ነው። "ናዕት" ከእግዚአብሔር የተሰጠችንን ተፈጥሯዊ የመኖር መብት የጠየቀ የጠቢብ ሰው ታላቅ ጩኸት ነው። "ናዕት" በንጹሃን ወገኖቿ የጅምላ ጭፍጨፋ የታመመች ነፍስ ጩኸት ነው።
ይኽ ስራ በ13ኛው ዙር የለዛ አዋርድ ላይ ባለፉት ሁለት አመታቶች ለህዝብ ከደረሱ ስራዎች ጋ የአመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ በሚል ዘርፍ በአድማጭ ድምጽ መሰረት ሊሸለም ለወድድር ቀርቧል። ይኼ ሙዚቃ ለኛ ሙዚቃ ብቻ ሳይሆን የነጻነታችንም ዜማ ነውና ለዚህ ሙዚቃ ድምጽ በመስጠት የዜማችንን ኃያልነት ለሁሉም እናረጋግጥ ስል እጠቁማለሁ!

መረጃ‼️
ሰኔ 23 /June 30/ ዱባይ Coca Cola Arena ላይ የሚካሄደው የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት 11 ቀናቶች ብቻ የቀሩት ሲሆን የመደበኛ ትኬት ሽያጭ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል። ስለሆነም ከዚህ በኋላ በኛ በኩል ወደ ዱባይ ተጉዛቹ መታደም የምትፈልጉ በሙሉ 70,000 Birr የነበረው የሙሉ ፓኬጅ ዋጋ የመደበኛ ትኬት በመጠናቁ ከዚህ በኋላ ለምትመጡ በSilver ደረጃ ትኬት ስለሆነ የምናስተናግዳችሁ ዋጋው 85,000 ሆኗል።
የቀረው ቦታ ጥቂት ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ!!!
ፓኬጆች!
ሶስት ቀን በዱባይ ቆይታ፣ የመኝታ፣ የቁርስ፣ የአየር ትኬት ደርሶ መልስና የአራት ቀን ቪዛ ብሎም የኮንሰርት መግቢያ ትኬቶችን ያካትታል።
የVIP እና የVVIP ፓኬጆችም አሉን።
ለበለጠ መረጃ
ኢትዮ- +251911072957 ታታ አፍሮ
ዱባይ- +971503365603 ተስፉ Dubai ብለው ይደውሉ

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
This is Coca-Cola Arena
ይህ Coca Cola arena ነው። በዚህ መድረክ የዓለማችን እውቅና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ብቻ ናቸው መቆም የሚችሉት። ከምስራቅ አፍሪካ ግን እስካሁን ማንም በዚህ መድረክ ቆሞ ስራውን ማቅረብ አልቻለም። የምስራቅ አፍሪካ ሰዎችም ለዚህ እድል ቀድመው አልበቁም።
ኢትዮጵያውያን ግን እነሆ በአንድ ልንሰበሰብበት ነው።
ዓለም የተስማማባቸው እውቅ ሰዎች አስደንጋጭ ዝግጅቶችን ባቀረቡበት በዚህ መድረክ ላይ ለአፍሪካውያን ወጣቶች ተምሳሌት የሆነው፡ በማንኛውም መድረክ ላይ ብቻውን በመቆም እልፍ አድናቂዎችን መሰብሰብ የተቻለው፡ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንጉስ የሆነው፡ የክብር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ በዚህ በግዙፍ አዳራሽ ስራውን ያቀርባል። ከምስራቅ አፍሪካም ቀዳሚ በመሆን በዓለም የኪነጥበብ ታሪክ ሲዘከር ይኖራል።
በዚህ ታሪካዊ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ለመታደም ከዓለም ጫፍ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እየተጠራሩ ይገኛሉ። በዕለቱ ዓለም እየሰማ ኢትዮጵያ በታላቅ የብሔራዊ ስሜት ትጠራለች ባንዲራዋም በባዕድ ምድር ከፍ ብሎ ይውለበለባል። ምን ይሄ ብቻ…! የኢትዮጵያ ነገሥታቶች ስማቸው በታላቅ ኩራትና በጀግንነት ስሜት ይወሳል። ምክኒያቱም ያለንን ማንነት የሰጡን እነርሱ ናቸውና።

ጥበብ እንጂ…
የነፍስህን ቃል እንጂ የመንጋዎችን ጩኸት አትሰማም። የፈጣሪህን ቁጣ እንጂ የሹሞችን ዛቻ አትሰጋም። የፊት መንገድህን በማለም ትራመዳለህ እንጂ የኋላህን በመቁጠር አትዘገይም። የወደድኩህ የኔን አይነት ባህሪ፣ ያንተን አይነት ስብዕና ስላለኝ ነው። “መፍራት ለፈሪዎች ስጋትም ለሰነፎች ናት” ብለኽ ስለምታስብ ለጀብደኞች እንኳን መራር የሆነችን እውነት በጥበባዊ ልሳን ገልጠሃታል። መኖር በሀገር፣ ለሀገር ሲሆን ሞት አያስፈራም። ብለኸ የነፍሴን ጽኑ እውነት በሊቅ ዜማ አንቆርቁረሃል።
ወንድ ልጅ ለሆዱም ለኪሱም ሳይረታ ሲቀር ወኔ አዘል ሽለላ አለው! እርሱም “አንገት ከሚሰበር ባይበላስ ቢቀር” ነው። ያንገት መሰበር መቀንጠስ ለሚመስላቸው መቀንጠስ አይደለም። በሐፍረት ዝቅ ማለት እንጂ! ሆድ ክፉ ነው ሲሉ እንደምስቀው ትስቃለህ ብዬ የማምነው ሆድ ሳይሆን ክፉ ሆዱን የወደደው ሰነፉ ሰው ነው ክፉ። ምክኒያቱም ሆድ እንዳረጉት ነው። ለሰው ልጅ ከሆድ የቀረበ፣ ከሆድም የቀደመ ተወዳጅ ተግባሩ ሰው መሆን ነው። ይሄን ደግሞ አንተ ጋ አይተናል!!!
የክብር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (Teddy Afro) መልካም ልደት ይሁንልህ አንበሳዬ!!!

Forwarded from Right Way Tour & Travel ✈️
የመልካም ምኞት መግለጫ!!!
ከ Right Way Tour and Travel የተላለፈ
ለክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና ለአድናቂዎቹ ብሎም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ።
ጉዳዩ፦ ከላይ በመግቢያው ለመግለጽ እንደተሞከረው መልካም ምኞትን መግለጽ (ማብሰር ነው።)
የክብር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ላይ ላለፉት 24 ተከታታይ አመታቶች አቻ ሳይገኝለት፥ የሀገራችንን ሙዚቃ በዓለም ደረጃ ያስተዋወቀ አንጋፋ የጥበብ ሰው ነው። ይህ ታላቅ የኪነጥበብ ሰው ሐምሌ 7/1968 ዓ.ም ነበር የተወለደው።
ድርጅታችን Right Way Tour and Travel ለዚህ ታላቅ ጥበበኛ የመልካም ልደት ምኞቱን እየገለጸ የድርጅቱ የስራ ባልደረቦችና የድርጅቱ ዋና አመራር የአርቲስቱን ልደት ምክኒያት በማድረግ እና ለአርቲስቱ ያለንን ታላቅ አክብሮት ለመግለጽ ለአንድ ወር የሚቆይ የ25% ቅናሽ ከታች በተዘረዘሩት ሀገራቶች ላይ ለማድረግ በስብሰባችን ወስነናል። ስለሆነም ወደ ተለያዪ የዓለማችን ሀገራት (ወደ ኢሮፕ፣ ካናዳ፣ ቻይና፣ ቱርክ፣ ህንድ፣ ዱባይና የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት) ለትምህርት፣ ለንግድ፣ ለጉብኝት ወዘተ መሄድ ለምትፈልጉ በሙሉ የዚህ እድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ እያልን ድርጅታችን የፍላጎትዎን ለመፈጸም ዝግጁ መሆኑን ስንገልጽልዎ በታላቅ ደስታ ነው።
ለበለጠ መረጃ ከታች በተጠቀሱት ስልኮች ይደውሉ አልያም ወደ ቢሯችን ጎራ ይበሉ።
አድራሻ መገናኛ ስለሺ ህንጻ
ስልክ
+251 9 11 07 29 57 / +251 9 70 00 04 70
Right Way Tour and Travel (Dream High ✈️)

የህዝብ ልጅ የሆነው የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ምክኒያት ህይወታቸውን ባጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ፣ ለደረሰው ድንገተኛ ጉዳት ድጋፍ ይሆን ዘንድ የአንድ ሚሊዮን ብር ቼክ ዛሬ 19/11/2016 ዓ.ም ፈርሟል።
ለህዝባችን መጽናናትን ህይወታቸውም ላለፈም ምህረትን ያድልልን!!!
✍#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
ለህዝባችን መጽናናትን ህይወታቸውም ላለፈም ምህረትን ያድልልን!!!
✍#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
Forwarded from ታታ አፍሮ -Tata Afro
የዛሬ 3 አመት ነበር ሐምሌ 22/213 ዓ.ም የጎንደር ዩኒቨርስቲ ለቴዲ አፍሮ የክቡር ዶክትሬት ማዕረግ ሊሰጠው የወሰነው። በእለቱ ሴኔቱ ባደረገው ስብሰባ ለአርቲስቱ የዶክትሬት ማዕረግ እንዲሰጠው አጽድቋል።
"ክብርህን ጠብቀህ ኢትዮጵያን ስላከበርክ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ይህን ክብር አበርክቶልሃል፡፡"
በዚህን ሰአት ጀምሮ ዓለም በሙሉ ስሙን እንዲህ እያለ ከነ ሙሉ ክብሩ መጥራት ጀመረ፦
የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
✍#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
"ክብርህን ጠብቀህ ኢትዮጵያን ስላከበርክ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ይህን ክብር አበርክቶልሃል፡፡"
በዚህን ሰአት ጀምሮ ዓለም በሙሉ ስሙን እንዲህ እያለ ከነ ሙሉ ክብሩ መጥራት ጀመረ፦
የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
✍#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
Forwarded from ታታ አፍሮ -Tata Afro
ሚሊዮን ፍቅር በአንድ ልብ። ♥️
ሀገሬን እወዳለሁ ካልክ በትንሽዬ ቀበሌ ውስጥ የሚኖሩ ምስኪን ወገኖችህን በእውነተኛ የመውደድ ስሜት መውደድ ይጠበቅብሃል። ምክኒያቱም ሀገር ያለነሱ ትንሽዬ ተሳትፎ ከወርቅነት ወደ መዳብነት ታንሳለች። (ሙሉ አይደለችም።) ወገኔን እወዳለሁ ስትል የፍቅርህ እውነትነት የሚጸናው በሙዚቃህ ዳንኪራ የሚረግጠውን (የሚዲያ ተደራሽነት አግኝቶ ማንነትህን የለየውን በመውደድ ብቻ ሳይሆን) ከተፈጠርክበት አፈር ተፈጥሮ ነገር ግን ማንነትህን ፈጽሞ የማያውቀውን ባላገር ጭምር ለመውደድ ብቁ ስትሆን ነው። (እንደ ቴዎድሮስ ካሳሁን።)
መቶ ሚሊዮን ህዝብ ምልክታችን ነህ ብሎ ከፊት ያሰለፈው የኔው ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጠጋ ብለ ‘ይሄ ድሃ ህዝብ ምንህ ነው?’ ብትለው “ወገኔ ለኔ ክብሬና ኩራቴ ነው ለዚህ ህዝብ ሁለት ነፍስ ቢኖረኝ ሁለቱንም ነፍሴን ለመስጠት አልሰስትም ይልሃል።”
ነፍስህ በጥበብ ስትመላ የድሃ ወገኖችህ እንባ አያስተኛህም። ሀዘናቸውም ሰላም ይነሳሃል። ምክኒያቱም ጥበብ ከግብዝነት መንፈስ የራቀች ነች። ቴዲ አፍሮ ደግሞ ለዚህ ህዝብ ዋጋ ከፍሏል። ታግሏል፣ ታስሯልም። ስለዚህ ሚሊዮኖች በአንድ ልብ ይወዱታል! እሱም ሚሊዮኖችን በአንድ ልብ ይወዳል። ♥️

ቢቂላ ሽልማት (Bikila Award 2024)
በሀገራችን እንቁ አትሌት የተሰየመው “ቢቂላ አዋርድ” ትልቅ ክብር ከሚሰጣቸው የሽልማት ተቋሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን እስካሁንም ለበርካታ የሀገር ባለውለታዎች እውቅናን በመስጠት ሲሸልም ቆይቷል። ቢቂላ ሽልማት (Bikila Award) ከሀይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊ እና ከምንም አይነት ትርፍ እራሱን ባገለለ መልኩ በካናዳ ከ50 አመታት በላይ በኖሩ ኢትዮጵያውያን ነው የተቋቋመው። ይህ ተቋም በትምህርታቸው፣ በንግዳቸው፣ በሙያቸው ብሎም በበጎ አድራጎት ስራ ተሰማርተው ልዩ ስኬት ያስመዘገቡ እና አርአያ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በየአመቱ በመሸለም እውቅናን የሚሰጥ ትልቅ ኢትዮጵያዊ መድረክ ነው።
በዚህ አመት አስረኛ (10) የምስረታ በአሉን የሚያከብረው የቢቂላ አዋርድ ተቋም፥ መስከረም 11 (21 September 2024) በሚያደርገው መርሃ ግብር ላይ በሙዚቃው ዘርፍ በዚህ አመት የሚሸልመው የግጥምና የዜማ ደራሲ ብሎም የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነውን የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁንን መሆኑን በህጋዊ ድህረገጾቹ በይፋ አሳውቋል።
አርቲስቱም በዕለቱ በዚህ ግዙፍ መርሃግብር ላይ በመገኘት ሽልማቱን እንደሚቀበል ተገልጿል።